cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮ - News

ጥያቄ ወይም አስተያየት ካሎት @Alllllllllllllllllllbot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
1 321Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሳውዲ አረቢያ ገባ‼️ በሚንስትሩ የሚመራው የልዑካን ቡድን በሳዑዲ አረቢያ ቆይታው በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች እና በዜጎች አያያዝ እንዲሁም በእስር ቤት ያሉ ዜጎችን በተመለከተ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል:: በኢትዮጰያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታዎችም ገለጻ ይደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ በሪያድ ከኢትዮጰያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: https://t.me/Etv_zena_ETH
Show all...
በወልድያ በወራሪው ሃይል በቡድን አስገድዶ መድፈርና ጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱ ተገለፀ‼️ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ወልዲያ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት እጅግ አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱን ነዋሪዎች ለኢዜአ ገልፀዋል። የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች በከተማዋ ሴቶችን አስገድደው በመድፈር ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ በመጨፍጨፍና ንብረት በማውደም ግፍ መፈጸማቸውንም ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት፡፡ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወልዲያን ጨምሮ የሰሜን ወሎ ዞንን ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪው ህወሃት ወረራ ነጻ ማውጣቱ ይታወቃል። አሸባሪ ቡድኑ ወደ ከተማዋ ከገባበት እለት ጀምሮ የሰቆቃ ጊዜ እንዳሳለፉ የገለፁት የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች "በርካታ ወጣቶችን በአደባባይ በግፍ ገድለዋል፤ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፤የግለሰቦችን ቤት በየቀኑ እየፈተሹ ሃብት ንብረት ዘርፈዋል" ብለዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ ለዓዕምሮ የሚከብድ ወንጀል ፈጽሟል ያሉት ነዋሪዎቹ በከተማዋ በርካታ ወጣቶች በአደባባይ በግፍ መገደላቸውንም ገልጸዋል። ኢትዮ - News ጥያቄ ወይም አስተያየት ካሎት @Alllllllllllllllllllbot https://t.me/Etv_zena_ETH
Show all...
ኢትዮ - News

ጥያቄ ወይም አስተያየት ካሎት @Alllllllllllllllllllbot

🛑 የቴዲ አፍሮ 'አርማሽ' የተሰኘ ሙዚቃው ኦባማ በአመቱ ከወደዷለው ምርጥ ስራዎች ውስጥ ነው ሲሉ ጠቅሰውታል‼️ ↘️ ባራክ ኦባማ የ2021 ምርጥ ዘፈን በማለት በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ዘርዝረዋል። ባራክ ኦባማ አመታዊ ምርጥ ሙዚቃ ምርጫቸውን ቀደም ባሉ አመታትም ያደርጉት የነበረ ተግባር ነው። በሳቸው ምርጥ ውስጥ የሚካተቱ ዘፈኖች እጅግ የበዛ ተመልካች ገቢ ሲጎርፍላቸው እንደነበር ይታወሳል። ↘️ የቢልቦርድ ድረገፅ ዘገባ በ2019 የኦባማ ምርጥ ውስጥ የተካተቱ ሙዚቃዎች ያገኙት ጭማሪ ማሳያ የሚሆን ነው።ባራክ በወቅቱ የዘረዘሯቸው 44 ስራዎች ከሳምንት ወደ ሳምንት የተመልካችና ገቢ መጠናቸው በሺዎች እጥፍ ነው ያደገው። https://t.me/Etv_zena_ETH
Show all...
ወልዲያ ነፃ ወጣች‼️ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት የወልዲያ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ። ወልዲያ ፣ ቆቦ፣ ሳንቃ፣ ሲሪንቃ፣ ጎብዬና ሀራ ከተሞችን ሙሉ ለሙሉ ከወራሪው የሽብር ቡድን ነጻ ወጥተዋል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ከተማዋን ተቆጣጥሯል። @Etv_zena_ETH
Show all...
Hi
Show all...
ምክር ቤቱ ዛሬ ልዩ ስብሰባውን ያካሄዳል‼️ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ዛሬ ከጧቱ 3:30 ጀምሮ ያካሄዳል። ም/ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ኘሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያደምጣል። በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል። በመጨረሻም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ በማጽደቅ የእለቱን ልዩ ስብሰባ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። Etvnews
Show all...
#SNNPRS : የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ። የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ይፋ አድርጓል። በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በክልሉ ሁሉም የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቅቂያ ፈተና በ16 ዞኖችና በ7 ልዩ ወረዳዎች ተሰጥቷል ። ለፈተናው ከተመዘገቡት 237,116 ተማሪዎች 234,790 ፈተናውን ወስደዋል፡፡ በዚህም የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ፦ - ለወንዶች 42 ፣ - ለሴቶች 41 - ለአይነ ስውራንና መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ደግሞ 40 ሆኖ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት ተወስኗል። ለዚህ ውሳኔ እንደ መነሻ በ2012 ዓ/ም ኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ባሳደረው ጫና በወቅቱ 7ኛ ክፍል የነበሩ ተማሪዎች 2ኛ ሴሜስተር ሳይማሩ ወደ 8ኛ ክፍል መዛወራቸውንና በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንደሆነም ተመላክቷል። ምንጭ ፡ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ https://t.me/Etv_zena_ETH
Show all...
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በፈረቃ ሲሰጥ የቆየው ትምህርት በ2014 የትምህርት ዘመን ወደ መደበኛው እንደሚመለስ አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለ "አዲስ ማለዳ ጋዜጣ" ነው። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲረዳ በማሰብ በ2013 የትምህርት ዘመን ትምህርት በፈረቃ ሲሰጥ ነበር። በተጨማሪ ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረው የቀናት ቁጥር በሳምንት ወደ 3 ቀን ተቀንሶ ተማሪዎች በቀናት ፈረቃ ተምረው አሳልፈዋል። ከሚቀጥለው ትምህርት ዘመን (2014 ዓ.ም) ጀምሮ የትምህርት ስርዓቱ ከዚህ ቀደም ወደ ነበረበት ማለትም ከሰኞ - አርብ የትምህርት ጊዜውን ለመመለስ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። Credit - Addis Maleda Newspaper https://t.me/Etv_zena_ETH
Show all...
#ጥንቃቄ ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ያጋጠመውን ከባድ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ ክፍት ለማድረግ ርብርቡ እየተደረገ ነው። በዛሬው ዕለት ይህን መስመሩን ለመክፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከኢትዮጵየ መንገዶች ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያሳያል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስቸኳይ ጥገናው ተጠናቆ መንገዱ ክፍት መሆኑን የሚያሳውቅ ይሆናል። በመሆኑም አሽከርካሪዎች እና የመንገዱ ተጠቃሚዎች ይህን የባለስልጣን መስሪያቤቱን መረጃ ሳታረጋግጡ እንቅስቃሴ እንዳታደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ከቀናት በፊት በስፍራው የሚንሸራተት ጠመዝማዛና ናዳ በሚበዛበት በዚሁ ስፍራ ከወትሮ የተለየ ግዙፍ ናዳ መከሰቱ የሚታወስ ነው። ይህን ተከትሎ ኢመባ ችግሩን ለመፍታት በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል፣ በርካታ ማሽነሪና የሰው ሀይል በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ በማሰማራት በተደረገው ጥረት መንገዱን የዘጋውን ቋጥኘ ድንጋይ በደማሚት እና በማሽነሪዎች በመታገዝ አብዛኛው የመንገዱን ክፍል ነጻ ለማድረግ ተችሏል። ቀሪ ስራዎችን አጠናቆ መስመሩን ክፍት ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል ኢመባ። https://t.me/Etv_zena_ETH
Show all...