cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Deleted channel

WeCare is Ethiopia’s digital healthcare platform where treatment seekers can discover practitioners to directly book appointments for online consultation or in clinic visits. [email protected] https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

Show more
Advertising posts
5 069Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
Repost from N/a
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በዛሬው ዕለት ሕዳር 27/2015 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ንፁሀን ዜጎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ስታዲየም በሚገኘው ዋና ጽ/ቤቱ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። የመገናኛ ብዙኃን በቦታው በመገኘት ሽፋን እንድትሰጡ እንጠይቃለን። ከመገናኛ ብዙኃን ተወክላችሁ የምትመጡ ጋዜጠኞች የድርጅቱን መታወቂያ እንድትይዙ እንገልፃለን። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
በቋንቋ እና በዘር ማንነት ላይ የተደራጀ የክልል መዋቅር የዜጎችን ደኅንነት ሊያስጠብቅ እንደማይችል ማሳያው ወለጋ ውስጥ ሰርክ የምንሰማው የወገኖቻችን ሰቆቃ ነው። የዜጎችን ሞት እና መፈናቀል ለማስቆም ጊዜያዊ መፍትሔው ዜጎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ሲሆን ዘላቂ መፍትሔው ግን ፖለቲካችንን ኋላቀር ከሆነው ከቋንቋ እና ከዘር ማንነት ማላቀቅ ብቻ ነው።
Show all...
የኢዜማ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ከውሰር ኢድሪስ የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በስኬት እያከናወኑ ነው። ከውሰር ኢድሪስ የሚመሩት የጉለሌ ክፍለከተማ ባህል እና ኪነጥበብ ጽሕፈት ቤት፤ በዓመታዊ የኪነጥበብ ውድድር በ17 ዘርፎች 1ኛ በመውጣት ከአሥራ አንዱ ክፍለከተሞች የአሸናፊዎች አሸናፊ ሆኗል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክፍለከተሞች ቆጥሮ በሰጠው ስኮር ካርድ በተደረገ ዓመታዊ ምዘና 1ኛ በመውጣት የዕውቀትና ሽልማት ተበርክቶለታል። ይህም ካውሰር ኢድሪስ የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በውጤታማነት እየተወጡ መሆኑን ያመለክታል። ከውሰር ኢድሪስ የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በስኬት፣ በሕግ አግባብ እና ከሌብነት በፀዳ መልኩ እየተወጡ በመሆኑ ኢዜማ ያለውን አድናቆት እየገለፀ፤ በቀጣይ ጊዜያትም የህዝብ እና የሀገርን ጥቅም ባስከበረ መልኩ በተለመደው ትጋትዎ እንዲያገለግሉ መልዕክቱን ከአደራ ጋር ያስተላልፋል። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
"ላለፉት 30 ዓመታት የተከተልነው ብሔርን መሠረት ያደረገው የፌደራል ሥርዓታችን ሕዝቦች እንዲቀራረቡ አድርጓል። ... [የብሔር ፌደራሊዝሙ] የኢትዮጵያን አንድነት ይበልጥ ለማጥበቅ ጠቅሞናል" (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር - ዛሬ በetv) ኢትዮጵያን ገፍቶ ገደል አፋፍ ያቆማት፣ ሕዝቧን ጦር አማዝዞ የሚያምሳት ቋንቋ እና ማንነት ላይ የተንጠለጠለው መርዘኛ የፌደራል ሥርዓት መሆኑን ከምክር መማር ቢያቅተን ከመከራ መማር እንዴት ያቅተናል ?
Show all...
የዜጎችን ደኅንነት ማስከበር ያልተቻለው ሽብርተኞችን የሚያቅፍ እና የሚደግፍ መዋቅር መንግስት ውስጥ በመኖሩ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከአባላቱ እና ከተለያዩ  ምንጮች ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ በኦነግ-ሸኔ የሽብር ቡድን የደፈጣ ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል፤ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፤ ታግተዋል፤ በሀገር ሀብት ላይም ውድመት እና ዝርፊያ ተፈጽሟል፡፡ ለአብነት ያህልም፦ - ጥቅምት 19/2015 የምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የሆኑ 11 ካህናት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን፤ ከታገቱት አገልጋዮች መካከል ሦስቱ ጥቅምት 23/2015 በተደረገ ድርድር ገንዘብ ከፍለው ሲለቀቁ የተቀሩት የደረሱበት አይታወቅም፤ - ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ አካባቢ የሽብር ቡድኑ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ከፍቶ የዳቦስ ወንዝ ድልድይን በመጣስ ወደ ወረዳው ለመግባት ከፍተኛ ሽብር ፈጥሯል፡፡ በዚህም በባምባሲ ወረዳ የሰዓት እላፊ እዲጣልና ዜጎች መደበኛ ኑሯቸው እንዲረበሽ አድጓል፤ - ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የሽብር ቡድኑ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ 4 ሰዎችን አግተው ከወሰዷቸው በኋላ እያንዳንዳቸው ሦስት መቶ ሺህ ብር (300,000) ካመጡ ከእገታው እንደሚለቀቁ ተገልጾላቸው የታጋቾች ቤተሰቦችም ገንዘቡን አሰባስበው ሲሄዱ የታገቱት ሰዎች በኦነግ-ሸኔ ታጣቂ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽነዋል፤ - ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት ላይ በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ‹‹አፍሪካ ጁስ ቲቢላ አክስዮን ኩባንያ›› የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት፣  ዘጠኝ ሰዎች መግደላቸውን የኩባንያው ሠራተኞችና አመራሮች ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል፤ - ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሐሩታ ዶሬ ቀበሌ  በሽብር ቡድኑ በተከፈተ ጥቃት 4 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ፤ - ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ዞን  የሽብር ቡድኑ ነቀምቴ ከተማ በመግባት ንጹሃን ሰዎች ላይ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዝርፊያ ከማድረሱም በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ ዜጎችን አግተው በመውሰድ አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል፤ - ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ በሚወስደው የፍጥነት መንገድ ላይ መቂ ከተማ አካባቢ የሽብር ቡድኑ በመንገዱ ሲጓዙ በነበሩ መኪናዎች ላይ ተኩስ ከፍቷ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በተወሱኑት ላይ አካል ጉዳት ደርሶ መኪናዎቹ ተቃጥለዋል፤ - ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞንና በቤንሻንጉል ክልል ከማሺ ዞን የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ለማድረስ የተላኩ ተሽከርካሪዎች ለሦስት ወራት አግቶ፣ የተወሰኑትን አቃጥሏል፤ ይህንን ሁሉ ሽብር፤ ግድያ፣ የጅምላ ፍጅት እና ዝርፊያ እየፈጸመ ሰላማዊ ዜጎችን ሲያሰቃይ በመንግሥት በኩል የተወሰደው የመፍትሔ እርምጃ ግን የችግሩን ጥልቀት እና ውስብስብነት ከግምት ያስገባ መሆን አልቻለም፡፡ ኢዜማ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጸው በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን የዜጎች ሰላምና ደኅንነት የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ኦነግ-ሸኔ በጫካ ውስጥ ያለ ሽፍታ ብቻ ሳይሆን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ባሉ ግለሰቦችም ጭምር እንደሚደገፍ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ሳይቀሩ በአደባባይ እየገለጹ ባሉበት በዚህ ወቅት፤ መንግሥት ለጉዳዩ ተመጣጣኝ ትኩረት ባለመስጠቱ እና ጠንካራ እርምጃ ባለመወሰዱ የሽብር ቡድኑ የሰላማዊ ዜጎችን የእለት ከእለት ኑሮ እያመሰቃቀለ ይገኛል፡፡ የሸኔ የሽብር ቡድን ከጥቂት ዓመታት በፊት በተወሰኑ ዞኖች ብቻ ይንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በብዙ ቦታዎች ጥቃት የሚደርስበት ደረጃ ላይ መድረስ ቡድኑ የሽብር ተግባሩን ማስፋፋቱን ያመለክታል፤ ሰለሆነም መንግሥት በመጀመሪያ በጉያው የተሰገሰጉትን የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎችን በማጽዳት ቁርጠኛ እርምጃ ሲወስድ ማየት እንፈልጋለን፤ የደኅንነት መዋቅሮችም አፋጣኝ እና ጠንካራ እርምጃዎችን ሊወስዱ እንደሚገባ ኢዜማ በጥብቅ ያሳስባል። መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ሽብርተኞች በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ዓላማው ማኅበራዊ መናጋት እንዲፈጠር በማድረግ አጠቃላይ ሀገራዊ ቀውስ መፍጠር መሆኑን በመገንዘብ የተለመደ አንድነቱን በማጥበቅ ሀገር አፍራሽ ቡድኖችን እንዲታገል እንጠይቃለን። ኢዜማ ከዚህ ቀደም ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ የሀገርን እና የህዝብን ህልውና የሚንዱ የዜጎችን ሰላምና ደኀንነት የሚያውኩ ቡድኖችን ለመታገል አሁንም ግንባር ቀደም ተሰላፊ እና ተሳታፊ ለመሆን ያለውን ቁርጠኝነት በይፋ ይገልፃል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሕዳር 19/2015 ዓ.ም
Show all...
መንግሥት የጸረ ሙስና ትግሉን የሚመራና ሙሰኞችን ለሕግ የሚያቀርብ የጸረ ሙስና ብሄራዊ ኮሚቴ ከባለሥልጣናቱ መካከል መልምሎ መሰየሙን አስታውቋል። መንግሥት ሌብነትን "እጠየፈዋለሁ" ማለቱን እንደ በጎ እርምጃ መውሰድ ይችላል። ነገር ግን ከዚህ በፊት "ሙስናን እንዋጋለን" እያልን በሄድንበት የፌዝ መንገድ ተጉዘን የተለየ ውጤት መጠበቅ አንድም የዋህነት፤ አንድም ቁርጠኛ አለመሆን ነው። እንደ ሀገር የህልውና አደጋ የደቀነብንን በዋንኛነት በፖለቲካው ሹመኞች የሚዘወረውን ሥር የሰደደ ሌብነት ለመጋፈጥ ቁርጠኝነቱ ካለን ኮሚሽኑ መቋቋም ያለበት በባለሥልጣናት ኮሚቴ ሳይሆን እንደ ምርጫ ቦርድ እና ሰብአዊ መብት ኮሚሽኖች ሁሉ ከፖለቲካ ነጻ በሆኑ ገለልተኛ አካላት ሊሆን ይገባል።
Show all...
"ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የሕዝብም የመንግሥትም አይደለም። የደላሎች እና የሌቦች ሹመኞች ነው። ይህን ችግር ለመፍታት ሥር ነቀል ለውጥ ይፈልጋል። ቢያንስ ቢያንስ በከተሞች መሬት የግለሰቦች መሆን አለበት..." (ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት) በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ለዘመናት ሲቀርቡ ከነበሩት በርካታ የፍትህ እና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች አንደኛው የሚመለስበት ፍንጭ የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ መልስ ሊያገኝ ይመስላል። ቀጣዩ ጥያቄ በቋንቋ እና በማንነት ላይ በመመሥረቱ የግጭት እና የመለያየት ምክንያት የሆነውን የብሔር ፖለቲካ በኢትዮጵያዊ የዜግነት አስተሳሰብ መተካት ይሆናል። የተቀረው ችግር እዳው ገብስ ነው። በሂደት አንዱ ችግር ችግር ሌላኛን እየፈታ ይሄዳል።
Show all...
ነፍስህ በሰላም ትረፍ። አፈሩ ይቅለልህ! Lubbun kee nagayaan haa boqattu! Biyyon sitti haa salphatu.
Show all...
አሁን ጊዜው የፉከራ እና የቀረርቶ አይደለም። የወደመችው ሀገራችን፤ የተጎዳውም ሕዝባችን ነው። የሀገር እና የወገን ጉዳት ከዚህ በላይ እንዳይቀጥል የሰላም መንገድን ለመረጡት ኃይሎች የወንድ በር በመስጠት ማጀገን ያስፈልጋል። ወደፊት እንይ!
Show all...
ጦርነት ቆሞ የሠላም ስምምነት ላይ መደረሱ ትልቅ እርምጃ ነው። ከጦርነት የሚያተርፍ፣ ከሠላም የሚከስር የለምና የድርድሩ ሂደት እና ውጤት ላይ ከመበሻሸቅ መውጣት ተገቢ ነው። ቀጣዩ ሀገራዊ የቤትሥራችን በጦርነቱ ጦስ ለመከራ የተዳረገውን ሕዝባችንን ቁስል ማከምና ከብሔር ፖለቲካ መውጣትን ጨምሮ የግጭት ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች በሰከነ ሀገራዊ ውይይት አንድ በአንድ ነቅሎ መጣል ይሆናል።
Show all...
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሓት መካካል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ የሰላም ስምምነቱ መርህ በተከተለ መልኩ ለመፈራረም መብቃቱ ይበል የሚያሰኝ መልካም ጅማሮ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ ለተግባራዊነቱም ባለድርሻ አካላት ሁሉ ፍጹም ታማኝ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መስረከም 03/2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው ‹‹ እንደ ኢዜማ እምነት ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንዲቻል የክህደት በሮች ሁሉ መዘጋታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ከዚህም አንዱና ዋነኛው የሀገርን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስከበር ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስን ኃይል የማዘዝ ሥልጣን ሊኖረው የሚገባው የፌደራል መንግሥት ብቻ ስለመሆኑ ሀገራዊም ሆነ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን አስረግጦ በማስገንዘብ ህወሓት ትጥቁን እንዲፈታ ሊደረግ ይገባል፡፡ እኛ ሰላምን የምንናፍቀው ለአጭር ግዜ መፍትሔነት ሳይሆን በዘላቂነት ነው፤ ዘላቂ ሰላም ደግሞ መረጋገጥ የሚችለው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ፍፁም ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ መሆን አለበት። ስለሆነም በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚገኙ የፌደራል ተቋማትንም ሆኑ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የመጠበቅና የአየር ክልሉን ሙሉ ለሙሉ  የመቆጣጠር ሥልጣን በብቸኝነት የፌደራል መንግሥቱ መሆኑን ህወሓትም ሊገነዘበው፤ መንግሥትም ሊዘነጋው አይገባም፡፡›› በመሆኑም ይህን መርህ በተከተለ መልኩ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ይበል የሚያሰኝ ሲሆን መንግስት የተደረገው ስምምነት እንዳይጨናገፍ እና ተመልሰን የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳንገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ለተግባራዊነቱም ሁሉም አካል በትጋት መስራት የሚጠበቅበት ሲሆን በሌሎች የሀገሪቷ ክፍሎች ያሉ የታጠቁ ሀይሎችም ጋር በሰላማዊ ንግግር መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ ላይ በአፅንኦት መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል መርህ የአፍሪካ ህብረት ይህ የሰላም ስምምነት እንዲፈርም ያሳየውን ጥረት እያደነቅን ተግባራዊነቱንም ለማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ተስፋ እንደርጋለን፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም. #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
የኢዜማ ጋሞና አካባቢው ማስተባበሪያ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን አደረገ። ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም ዞን ማስተባበሪያ ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የአርባ ምንጭ፣ የብርብር ልዩ፣ የካምባ፣ የቦንኬ-ገረሴ፣ የጨንቻ፣ የዳራማሎ፣ የኧሌ የዲራሼ ልዩ፣ የጊዶሌ መደበኛ እና ቁጫ ምርጫ ክልሎች በተወካዮቻቸው አማካይነት ተሳትፈዋል። በውይይቱ ላይ በቀጣይ የኢዜማ የሥራ ተልዕኮዎች ላይ ዝርዝር መረጃ በማቅረብ ጥልቅ ውይይት አድርጓል። የዞኑ ማስተባበሪያ ምክር ቤት በቀጣይ ጠንካራ አደረጃጀት የሚፈጠርበትን መንገድ በመዘርዘር አዲስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጦ አስፀድቋል። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በተጠራው 77ኛው የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ለቀረበብን የሀሰት ውንጀላ በተፈቀደላቸው 2 ደቂቃ የሰጡት አስደናቂ መልስ -------------- " እየሰማን ያለነው የሰላም መልእክት አይደለም። ተከታታይ ማስጠንቀቂያዎችን ነው። ነገር ግን በርካታ የፖለቲካ ምስቅልቅሎችን ማለፍ እንደቻለች ኩሩ አፍሪካዊት ሀገር [የተባበሩት መንግሥታት] አባል ሀገራትን አንድ ነገር ማስታወስ እፈልጋለሁ። በርካታ ችግሮቻችንን ተጋፍጠን እንዳለፍናቸው ዛሬም የገጠሙንን ችግሮች በእርግጠኝነት እንሻገራቸዋለን። በአንዳንድ ኃያላን ሀገሮች ዐይን ፊት ልክ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እንደሆነው  [ኢትዮጵያውያን] ዐቅመቢስ መስለን እንታይ ይሆናል። ክቡር ሊቀመንበር አንድ ነገር ላረጋግጥልዎት እፈልጋለሁ። የውስጣችን መንፈስ ጽኑእ ነው። የውስጣዊ መንፈሳችን ጥንካሬ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመቆም ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ ለመሆን እና ተግዳሮቶቻችንን ለመፍታት ጭምር ነው። የ120 ሚሊዮን ሕዝባችንን ዕድል ለ200 ኤክስፐርቶች ልንተወው አንችልም። ይህንን ብዬ፤ ሁልጊዜም ቢሆን በጎ ሀሳብ ያላቸውን ተሳታፊዎች በደስታ የምንቀበል ሲሆን ሊያወግዙን እና ለሞት አሳልፈው ሊሰጡን ቀድመው የወሰኑትን ግን "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር ይበላቸው" እላለሁ። ስለዚህ እንደ [ኢትዮጽያ] መንግሥት ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ የተሳተፉትን ተጠያቂ እናደርጋቸዋለን። ይህንንም የምናደርገው የተወሰኑ ድርጅቶችን ወይንም ኤክስፐርቶችን ለማስደሰት ሳይሆን ለራሳችን መርኅ ስንል ነው። ዘላቂ ሰላም መስፈን የሚችለው በሁሉም አካባቢዎች ለተሠሩ ወንጀሎች ተጠያቂነት እና ፍትህ ሲሰፍን ብቻ መሆኑን እንረዳለን። ነገር ግን ይህ በሀገሪቱ ባለቤትነት መመራት አለበት። አመሠግናለሁ ክቡር ሊቀመንበር " ---------------- እንደ መውጪያ! እንደሁልጊዜውም ለአምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያለኝን ጥልቅ አክብሮት እየገለጽኩ በዲፕሎማሲው መስክ ብቁ እና ንቁ አምባሳደሮችን አሰልጥኖ ማሠማራት ለሚኖረውን ሀገራዊ ጠቀሜታ አምባሳደር ታዬ ማሳያ ተደርገው እንደ አብነት ሲጠቀሱ የሚኖሩ ይመስለኛል።
Show all...
ሀቅ! ህወሓት የሚዋጋው፤ ከሆነለት ወደ ቀደመ አምባገነን ሥልጣኑ ለመመለስ ካልሆነለትም ኢትዮጵያን ለመበተን ነው። ኢትዮጵያ የምትዋጋው ግን የህወሓትን ቅዠት በመቅበር ሉዓላዊ ህልውናዋን ለማስከበር ነው! #DisarmTPLF #EthiopiaPrevails
Show all...
USA was given the chance to observe the negotiations but not to command. The fact that they started meddling and issuing orders before the talk have even begun is perplexing. Going from being an observer to a commander is similar to what they did on GERD is not acceptable! #NO_MORE https://www.state.gov/on-the-start-of-northern-ethiopia-peace-talks/
Show all...
#ጥቅምት_15 #የሀገር_መከላከያ_ቀን! ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለሕዝብ ደኅንነት ስትሉ በደም እና በአጥንታችሁ ዋጋ የምትከፍሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ከመቀመጫችን ተነስተን፣ ባርኔጣችንን አንስተን በክብር እጅ እንነሳለን !!!
Show all...
2) ዕውቀት እና ሀብት ያላቸው የሀገሪቱ ዜጎች በመላዋ ሀገሪቱ ያለሰቀቀን ተንቀሳቅሰው ሥራ እንዳይፈጥሩ እና በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይሰፍን አድርጓል፡፡ 3) በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት እንደታዘብነው የክልል ከተሞች ጎብኚዎች እና ሥራ ፈጣሪ ባለሀብቶች በማጣታቸው በከፍተኛ ፍጥነት እየተዳከሙ እና እየተፋዘዙ እንዲመጡ አድርጓቸዋል፡፡ 4) በክልል ከተሞች ሀብት በመፍጠር እና ቀጣሪ በመሆን የሚታወቁ የሀገሪቱ ዜጎች ከክልሎቹ ባለሥልጣናት ትብብር እና ድጋፍ በማጣት አልፎ አልፎ በሚነሱ ብሔርን መሠረት ባደረጉ ግጭቶችም ሰለባ በመሆናቸው ሥራቸውን እየተዉ ወደ ማዕከል (አዲስ አበባ) ስለሚሰበሰቡ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመላ ሀገሪቱ እየተዳከሙ ሄደዋል፡፡ 5) ከግብር ከፋይ ዜጎች የተሰበሰቡ፣ በብድር እና በልመና የተገኙ የሀገሪቱ ውሱን ሀብቶች የፈሰሰባቸው የፌደራል ተቋማት በየውቅቱ የሚገነፍሉ ብሔር ተኮር ግጭቶች የጥቃት ዒላማ ስለሚሆኑ ለትውልድ የሚተርፍ ጥሪት ሳይሆን እዳ እና ኪሳራ ምክንያት ሆኗል፡፡ የመፍትሔ ሀሳች! መፍትሔው የዝግጅት ሂደቱን በማጠናቀቅ ወደ ትግበራ በመሻገር ላይ ባለው ሀገራዊ ምክክር ሁሉንም ባለድርሻዎች ያሳተፈ የሰከነ እና እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ሲሆን ምክክሩ የሚከተሉትን ውጤት ያስገኛል ብዬ ተሥፋ አደርጋለሁ፦ 1) የችግሮቻን ምንጭ የሆነውን የዘውግ (የብሔር) ፌደራሊዝም በዴሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም መተካት፤ 2) የሀገር ባለቤትነትን ሁላችንንም እኩል በሚያደርገን እና በሚያመሳስለን የጋራ እሴት በኢትዮጵያዊ ዜግነት ላይ ማቆም፤ 3) የሀገሪቱን የመንግሥት አወቃቀር የብሔሮችን ባህል፣ ቋንቋ እና ሌሎች የቡድን መብቶችን በሚያከብር ነገር ግን መሠረቱን ዜግነት ባደረገ ፍልስፍና መተካት ! 4) የኢኮኖሚ መዋቅራችንን በሂደት ማኅበራዊ ፍትህ በሚያሰፍን (ለሁሉም ዜጎች እኩል እድል በሚሰጥ እና የተለየ ድጋፍ የሚያሻቸውን በማገዝ) ሥርዓት መተካት ! ሠላም !
Show all...
ተፈትኖ በወደቀ የዘውግ ፌደራሊዝም የኢትዮጵያ አትፈወስም! --------------------- ይህንን ጽሑፍ እንዳጋራ ያነሳሳኝ ሰሞንን የብልጽግና ሹማምንት በበደል ትርክት ተጠንስሶ ዘውጌ ማንነት ላይ የተንጠለጠለውን "የፌደራል ሥርዓት" ከችግራችን መውጪያ "መድኃኒት" አድርገው ሲሰብኩ በማየቴ ነው። ፌደራሊዝም የሚለው ቃል ሥረወ ቃሉ የላቲኑ ፌደስ (Feodus) ሲሆን ትጓሜውም ‹‹ቃል ኪዳን›› ማለት ነው፡፡ (እንደ አላዛር እና ኦስተሮም ጥናት) የፌደራል ሥርዓት በዓለማችን ከተዋወቀ 230 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን በአሜሪካ በ1789፣ በስዊዘርላንድ በ1848፣ በካናዳ 1867፣ አውስትራሊያ ከ1901 ጀምሮ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ካናዳዊው የፌደራሊዝም ተመራማሪ ዋትስ “Federalism, Federal Political Systems, and Federations” በሚል ርእስ ባቀረቡት ጥናት ‹‹በምሥራቅ የአውሮፓ ሀገሮች እና በሦስተኛው ዓለም ሀገሮች ፌደራሊዝም እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ወድቋል›› ብለዋል (Watts1998)፡፡ ሽናይደር የተባሉ ሌላ አጥኚ በበኩላቸው የዩጎዝላቪያን እና የታላቋ ሶቪየት ኅብረት መፈረካካስ ምንጩ የተከተሉት የፌደራል ሥርዓት መሆኑን በጥናታቸው ሞግተዋል (Snyder 1999)፡፡ ሶቭየት ኅብረትና ዩጎዝላቪያ ውስጥ የነበረው ፌዴራሊዝም ከላይ ወደታች የተጫነ እንጂ የህዝቦች ቃልኪዳን ውጤት አልነበረም። ለዚህ ነው ሁለቱም ፈራርሰዉ ለብዙ ጥቃቅን ሉዓላዊ መንግሥታት መፈጠር ምክንያት የሆኑት። በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ፌደራሊዝም ሥርዓት በሁለት መንገዶች ሊዋቀር ይችላል፡፡ (ጋሽ ኤፍሬም ማዴቦ ‹‹አብረን እንኑር›› እና ‹‹ሀገር እናድን›› ሲል ይፈታቸዋል) (Stephan 2001) የመጀመሪያው አማራጭ ሉዓላዊ የሆኑ ሀገሮች በደኅንነት ወይንም በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ወደ አንድ ስብስብ ለመምጣት (Coming Together) ሲወስኑ የሚፈጠር ሲሆን ሁለተኛው በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች መካከል የብሔር ወይንም የቡድኖች ፍላጎቶችን ለማቻቻል ሲባል የሚፈጠር ነው፡፡ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አሠፋ ፍሰሐ “Federalism and the Accommodation of Diversity in Ethiopia: A Comparative Study’’ በሚል ርእስ ባሳተሙት ጥናት እንደሚጠቁሙት የአፍሪካ ፌደራሊዝም ቅኝ ግዛትን ተከትሎ አፍሪካውያንን ከፋፍሎ ለመግዛት የመጣ ሥርዓት ነው፡፡ ጋናዊው ክዋሜ ንኩሩማን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮች ፌደራል ሥርዓትን አምርረው የተቃወሙት በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡ በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ የመረጡት የአስተዳደር ዘይቤ በቅኝ ገዢዎች የተጫነባቸውን በዘውግ ማንነት (በብሔር) ላይ የተዋቀረ ፌደራሊዝም አሽቀንጥው በመጣል አንድነታቸውን ለማጠንከር አሀዳዊ ሥርዓት ማስፈንን መርጠዋል፡፡ ዛሬም ድረስ በርካታ አፍሪካውያን "ፌደራሊዝም ጠባብ ብሔርተኝነትን ያስፋፋል" በማለት አምርረው ይቃወሙታል። (Kimenyi 1998) ቅኝ ገዢዎች ለአፍሪካ ምንም ጥሩ ነገር ይዘው አልመጡም፡፡ ጥሩ ነገር ካመጡም ለነሱ በጣም ጠቅሟቸዋል ማለት ነው፡፡ ፌዴራሊዝምን የአፍሪካን ሕዝብ ከፋፍለው ለመግዛት ተጠቅመውበታል፡፡ በናይጄሪያ የፌደራል ሥርዓት ላይ ጥናት በማቅረብ የሚታወቁት J.Isawa Elaigwu “ፌደራሊዝም በአፍሪካ ግጭት ማርገቢያ ሳይሆን የግጭት መንስኤ ነው” ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች በሕገመንግሥቶቻቸው የፖለቲካ ፓርቲን በብሔር ማደራጀትን ክልከላ እስከመጣል መድረሳቸው ነው፡፡ ይህም ሆኖ ሀገራችንን ኢትዮጵያ ጨምሮ 10 ያህል የአፍሪካ ሀገሮች የፌደራል ሥርዓትን ተከታይ ሲሆኑ የተቀሩት ከ40 በላይ ሀገራት አሀዳዊ ሥርዓት ተከታዮች ናቸው፡፡ የደርግ ሥርዓትን በማስወገድ መንበረ ሥልጣኑን የወረሰው ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ የተከተለው ዘውግን (ብሔርን) መሠረት ያደረገው የፌደራል ሥርዓት አወቃቀር ምንም እንኳን "ለህዝቦች ሰላም እና አንድነት ያመጣል" ቢባልም በተግባር እንደታየው ባለፉት ሠላሳ ዓመታት የግጭት እና የቀውስ ምንጭ ሆኗል። አሁን በሥራ ላይ ያለው የፌዴራል ሥርዓት አንደኛ በህሕዝብ መልካም ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በጉልበትና በኃይል የተጫነ ፌዴራሊዝም ነው፡፡ ሁለተኛ መሠረቱ በየትም ያልታየ ብሔር እና ቋንቋ ብቻ ነው፣ ሦስተኛ የፌዴራል ክልሎቹ ሉዓላዊነት የተረጋገጠ አይደለም፡፡ አራተኛ- ከዲሞክራሲ ጋር የማይተዋወቅ ፌዴራሊዝም ነው። በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ይተተበተበውን የዘውግ ፌዴራል ሥርዓት ነው እንግዲህ ሰሞኑን "ኢትዮጵያን ከግጭት የሚያወጣት ክትባት ነው" እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት። ይህንን የፌደራል ሥርዓት ታቅፈን የግጭት እና የድህነት ምንጭ መሆኑ ሊገርመን አይገባም፡፡ Monahan እና Biyant የተባሉ አጥኚዎች በጥናታቸው እንደሚገልጡት በዓለማችን ከሚገኙ ከ89 ሕገ መንግሥታት መገንጠልን የሚፈቅዱት ሰባቱ (ኦስትሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፣ ሲንጋፖር፣ ቅዱስ ክርሰቶፈርና ኔቪስ፣ የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት እና ቸኮዝሎቫኪያ) ብቻ ሲሆኑ ከሰባቱ ሁለቱ ሀገሮች (ሶቪየት እና ቸኮዝሎቫኪያ) ብትንትናቸው ወጥቷል። ከላይ የጠቀስኩት የተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አሠፋ ፍሰሐ ጥናት ማጠቃለያ እደሚመሰክረው ኢትዮጵያ ውስጥ የተተከለው የጎሳ (የብሔር) ፌደራሊዝም በተግባር ተፈትኖ ወድቋል፡፡ (Asefa 2007) በህወሓት የተዘጋጀልን እና በሥራ ላይ ያለው የሀገራችን ሕገ መንግሥት ሀገሪቱን የዜጎች ሳትሆን የዘውጌዎች (የብሔሮች) አክስዮን አድርጎ ቀርጿታል። በዚህ ስሌትም የሀገሪቱን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የደኅንነት ተቋማትን በጎሳ ለተደራጁ #አንደኛ_ደረጃ_ዜጎች በማስረከቡ በብሔር ከረጢት የማይመደቡ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር እና #ሁለተኛ_ዜጋ አድርጓቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ፌዴራሊዝም ያስፈልጋል ተብሎ የሚታመነው ብዝኀነትን ያቀፈ ሀገራዊ አንድነት እንዲፈጠር፣ ለዘመናት የተጠየቀውን ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ስለሚመልስ ኅዳጣንን (አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን) እንዳይበድል ነው። የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም መሠረቱን ያደረገው የልዩነት ምልክት በሆነው በብሔር ላይ በመሆኑ ያስወግዳል የተባለውን ዋናውን የሀገሪቱን ችግር አባባሰው እንጂ አልፈታውም፣ ሁሉንም ነገር ከብሔር ጋር አያያዞ ሀገራዊ አንድነትን አዳከመው እንጂ ጠንካራ አንድነት አላመጣም፣ ብዙኅኑ አናሳውን እንዲረግጥ መንገድ ከፈተ እንጂ ዲሞክራሲን አላመጣም፡፡ አሁን ባለው ሕገመንግሥት ማህቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያን ችግሮች መፍታት በፍጹም አይቻልም፡፡ ይህንን የሀገርን ሉዓላዊነት ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝቦች ለሚባሉ ልዩነታቸውና አንድነታቸው በውል ለማይታወቅ ስብስቦች የሰጠውንና በተለይ ለብሔሮች ገደብ የለሽ መብት እንጂ መብታቸውን ከምንም ዓይነት ግዴታ ጋር የማይያያዘውን ሕገመንግሥት ይዘን እስካሁንም እንደ ሀገር መዝለቃችንም በራሱ አስገራሚ ነው። ከላይ ከጠቃቀስኳቸው እና ሌሎች ጥናቶች በመነሳት ሀገራችን ኢትዮጵያ የተከተለችው ዘውግን (ብሔርን) መሠረቱ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት አደረጃት ተፈትኖ የወደቀ እና በተጨባጭ የሚከተሉት ሀገራዊ ቀውሶች አስከትሏል እላለሁ፡፡ 1) ዜጎች ከክልል ወደ ክልል በነጻነት እና በሰላም ተንቀሳቅሰው እንዲሠሩ ስለማያበረታታ ሀብት ፈጣሪዎችን በማብዛት ኢኮኖሚያችንን ለማሳደግ የምናደርገው ሀገራዊ ጥረት ከንቱ ልፋት አድርጎታል፡፡
Show all...
ወዳጄ ሆይ ዛሬ በእርሳስ የሚሠራን የወረቀት ፈተናን ብትሸሸው ነገ በእንባ የምትጽፈው የሕይወት ፈተና ከቋጥኝ ከብዶ ይጠብቅሃል።
Show all...
ከመውደቁ አወዳደቁ! -------------------------- የአዋሳ ዩኒቨርስቲ ሁለቱን ግቢ እንዲያገናኝ ታስቦ የተገነባው የብረት ድልድይ በዛሬው እለት በመውደቁ የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን እና በሌሎች ተማሪዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ልብን በሚሰብር ኀዘን ውስጥ ሆነን ሰምተናል። የሞተውን ነፍሱ በሰላም እንድታርፍ፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ እመኛለሁ። ይህ ያልተጠበቀ ክስተት ተማሪዎች መረበሻቸው ወላጆች መጨነቃቸው የሚጠበቅ ቢሆንም ያለፈውን መመለስ ስለማንችል ሁሉም ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲፈተኑ ማረጋጋት ይጠበቅብናል። ከዚህ በተረፈ ግን አደጋውን መሸፋፈኑን ወይንም ማጋነኑን ትተን በጥንቃቄ በመመርመር እንደ ሀገር ይህን የመሰለ ጉዳት ደግሞ እንዳያገኘን ሙያዊ መድኃኒት እንድናገኝ ሙያዊ ምርመራ ማድረግ ይገባል እላለሁ። በጥቅሉ አንድ ግንባታ በንድፍ ችግር (Design Failure), በግንባታ ቁሳቁስ ጥራት ማነስ (Material Failure), በግንባታ ጥራት ችግር (Construction Failure) ወይንም ከአጠቃቀም ችግር (Misuse) ሊከሰት ይችላል። ከዚህ የተነሳ ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነቱን የሚወስደው ነዳፊው (Designer), ሥራ ተቋራጩ (Contractor), አማካሪው (Consultant) ወይንም አስተዳዳሪው (Administrator) ሊሆኑ ይችላሉ። ይህንን ማረጋገጥ ያለበት ገለልተኛ የባለሙያዎች ሳይንሳዊ ምርመራ ብቻ ነው። በሌሎች ሀገሮች ይህንን የመሰለ አደጋ ሲከሰት በፍጥነት የባለሙያዎች ፓናል በመመሥረት በዝርዝር የሚጠና ሲሆን ለጉዳቱ ኃላፊነት የሚወስደውን አካል ከመለየት ባሻገር "እንደ ሀገር ምን ተማርንበት?" ብለው በመጠየቅ አዳዲስ ንድፈ ሐሳቦችን፣ ኀልዮቶችን እና ቀመሮችን ያስተዋውቁበታል። የተወሰኑ ተመሳሳይ አብነቶችን ከዓለም ዙሪያ በአጭር በአጭሩ እንመልከት። ------------------------- 1) ፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ድልድይ (ሚያሚ - አሜሪካ) ኮሌጁን ከተማሪዎች መኖሪያ እንዲያገናኝ ታስቦ "accelerated bridge construction" በሚባል የግንባታ ዘዴ የተገነባው የእግረኛ መተላለፊያ ድልድይ ለመገጣጠም ስድስት ሰአታት ብቻ ነበር የፈጀው። የድልድዩ ንድፍ ደረጃ አምስት አውሎ ንፋስን እንዲቋቋም እና ለ100 ዓመታት እንዲያገለግል ታስቦ ቢዘጋጅም እድሜው ግን አንድ ሳምንት ሳይደፍን በ6ኛው ቀን በመውደቁ 6 ሰዎችን ገድሎ፣ ዘጠኝ ሰዎችን አቁስሎ፣ ስምንት መኪናዎችን ደፍጥጧል። በኋላ በጥናት እንደተረጋገጠው ችግሩ የንድፍ ጉድለት ጋር የተያያዘ ነበር። 2) ኒለም ሸለቆ - ድልድይ ካሽሚር - ፓኪስታን በፓኪስታኗ ካሽሚር ግዛት በካሽሚር ወንዝ ላይ ከእጨት የተገነባ ድልድይ በአንድ ጊዜ ከአራት ሰው በላይ መሸከም እንደማይችል ማስጠንቀቂያ ተለጥፎበት ነበር። በፈረንጆቹ 2018 ፋይሲላባድ እና ላሆሬ ከተባሉ የግል ኮሌጆች ለልምድ ልውውጥ የተሰባሰቡ የሕክምና ተማሪዎች በድልድዩ ላይ የተለጠፈውን ማስጠንቀቂያ ችላ ብለው 20 በመሆን በቡድን ፎቶ ሲነሱ ድልድዩ በመውደቁ አምስት ተማሪዎች ወዲያው ሲሞቱ ሃያ ተማሪዎች በወንዙ ተወስደው ጉዳት ደርሶባቸዋል። በኋላ በጥናት እንደተረጋገጠው ችግሩ ከአጠቃቀም ጉድለት ጋር የተያያዘ ነበር። 3) ባውቺ ድልድይ ባውቺ - ናይጄሪያ በናይጄሪያ ATBU ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያን ከመማሪያ ክፍሎች (Lecture Halls) እንዲያገናኝ ታስቦ ከብረት የተሠራው ዩኒቨርሲቲው ድልድይ በፈረንጆቹ August 2019 በአካባቢው የጣለውን ዝናብ ተከትሎ በመውደቁ ስምንት ተማሪዎች ሲሞቱ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም። 4) ታኮማ - ድልድይ (ዋሽንግተን - አሜሪካ) በአሜሪካ ዋሽንግተን ከተማ በፈረንጆቹ 1940 ዓ.ም ተገንብቶ ለትራፊክ ክፍት ተደረገ። በዓይነቱ (በተገመደ ብረት የተወጠረ) በዓለማችን የመጀመሪያው የሆነው ይህ ድልድይ አገልግሎት መስጠት የቻለው ለአራት ወራት ብቻ ነበር። በወቅቱ በሰአት 70 ማይል በሚከንፍ ነፋስ በመመታቱ ድልድዩ ወድቋል። በርካታ የፊዚክስ፣ የሒሳብ እና የምሕንድስና ሊቃውንት በአወዳደቁ ላይ ጥናት እና ምርምር አድርገውበታል። ለምሳሌ በምሕንድስናው ስለ mechanical resonance አዲስ ኀልዮት እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል። ማጠቃለያ -------------- በተለያዩ ጊዜያት፣ በልዩልዩ ሀገሮች፣ በተለያዩ ንድፎች (Design)፣ በተለያዩ የግንባታ ቁሳቁሶች (Materials) እና የግንባታ ጥበብ (Method) በተለይ ለተማሪዎች አገልግሎት የተገነቡ ድልድዮች በተለያዩ ምክንያቶች ወድቀው ጉዳት አድርሰዋል። ጋዜጠኞች ስለመውደቁ አጋንነው ወይንም ሸፋፍነው ዜና መሥራታቸው የተለመደ ነው። ቢያንስ የዘርፉ ምሑራን ግን ስለመውደቁ ሳይሆን ስለ አወዳደቁ እንዲያጠኑ እና ከስህተታችን የምንማርበትን መድኃኒት እንዲያገኙልን እንጠብቃለን።
Show all...
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች ከመስከረም 1- መስከረም 30 ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ። የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ይደረጋል በተባለው የህወሓት እና መንግስት ድርድር ዙሪያ ከሸገር FM 102.1 ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ https://t.me/ShegerFMRadio102_1/12185 የኢዜማ ትግራይ ክልል አስተባባሪ አንጋው ሲሳይ ይደረጋል በተባለው የህወሓት እና መንግስት ድርድር ዙሪያ ከፋና ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://www.facebook.com/139294240239063/posts/1283347465833729/?app=fbl የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አንድነት ሽፈራው በ 2014 የነበረው የፖለቲካ ምህዳር እና በ 2015 ሊሻሻሉ ስለሚገባቸው ሁነቶች ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://youtu.be/mC9whHLRtyA ከ 9፡50 ጀምሮ የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የአካል ጉዳተኞች መምሪያ ሐላፊ ማዕረጉ ግርማ ይደረጋል በተባለው የሕወሓት እና መንግስት ድርድር ዙርያ ከየኛ ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://youtu.be/NX5Exyby_IE የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አብርሃም በርታ (ዶ/ር) በሉዓላዊነት ዙርያ ከአሃዱ ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ https://drive.google.com/file/d/1BOkshBz-X3Nl_DukRvIhf5WyrTIQ-o0I/view?usp=drivesdk የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሣፍንት ተመድ በኢትዮጵያ ላይ ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ሪፖርት አስመልክቶ ከፋና ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ https://www.fanabc.com/%E1%8B%9C%E1%8A%93-%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88%9D%E1%8C%A1/ ከ 26:30-32:00 ያለውን ዘገባ ያድምጡ የኢዜማ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ለኮሬ ሕዝብ ተደጋጋሚ ግድያ መንስኤው ምንድነው? በሚል ዙርያ ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ https://youtu.be/BKn9-JPuZgU የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሣፍንት ዓለም አቀፍ ተቋማቶች በኢትዮጵያ ላይ በሚያንጸባርቁት አቋም ዙርያ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ https://drive.google.com/file/d/1Bn98njomh6SRY2zqBPXBKlz23Ee0JaGF/view?usp=drivesdk እና https://drive.google.com/file/d/1Bqcf0tqHBODLzRmQ4ut7et-eQ-NqBd1Q/view?usp=drivesdk የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሃገራዊ ጉዳይ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ https://www.ethiopianreporter.com/111076/ የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ግርማ ሰይፉ በሙስና እና ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ https://www.ethiopianreporter.com/111500/
Show all...
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1497ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ! #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
በዓለም የመምህራን ቀን መምህራኖቻችንን ብናመስግንስ? -------------------- እኔ በተማርኩበት የምእራብ ሸዋ፣ ቱሉቦሎ ከተማ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስታፍ ቢሮ መምህራኖቼ ልከውኝ በገባሁ ቁጥር ከግድግዳው ላይ ተሰቅሎ ያነበብኩት ጥቅስ እስከዛሬም አይረሳኝም፡፡ ጽሑፉ እንዲህ ይላል፦ ‹‹እኔ የማደንቀው ጨረቃ ላይ የወጡትን ሳይሆን ጨረቃ ላይ መውጣት እንደሚቻል ያስተማሯቸውን ነው›› በተለይ ሙያውን ወደው እና ፈቅደው ለተሠማሩበት ኢትዮጵያውያን መምህራን ትውልዱን በዕውቀት እና በሞራል ለማነጽ ያላቸውን የማይተካ ሚና መዘንጋት አይቻልም። በግል ሕይወቴ በጎ ተጽእኖ ያሳረፉብኝን መምህራኖቼን ዛሬም ድረስ በክብር አስታውሳቸዋለሁ። ከትምህርቱ ባሻገር እንደ ታላቅ ወንድም ቤታቸው ድረስ እየጠሩ ይመክሩን እንደነበር ትዝ ይለኛል። ዛሬ የዓለም የመምህራን ቀን ታስቦ የሚውልበት ቀን እንደመሆኑ መምህራኖቼን በአደባባይ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። - የኋላሸት ገ/ማርያም (የሒሳብ መምህሬ) - ያሳቡ ብርቅነህ (የጂኦግራፊ መምህሬ) - ሶሎሞን ማሞ (የፊዚክስ መምህሬ) - ሻይቦ መሐመድ (የታሪክ መምህሬ - በፍቃዱ ረፌራ (የባዮሎጂ መምህሬ) - አንዱዓለም በፍቃዱ (የእንግሊዝኛ መምህሬ) የእናንተ ተማሪ ስለነበርኩ እድለኛ ነኝ። ሁሌም ውለታችሁን በክብር አስታውሳለሁ። አመሠግናለሁ !!!
Show all...
"...ምንም የፖለቲካ ልዩነቶች እንኳን ቢኖሩ ትምህርትን የዛ መጠቀሚያ አናድርገው። ትምህርትን ከዛ ውስጥ እናውጣው። ትምህርት ስለልጆቻችን ነው። " ___ ይህንን መልእክት የማጋራው የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሥራ ባልደረባ ስለሆንኩ አይደለም። መምህር በመሆኔ እና ስለመጪው የሀገሬ ትውልድ ስለሚገደኝ ነው። እናንተም አንብባችሁት ለሌሎች እንድታጋሩት አስታውሳችኋለሁ! ___ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ከቤተሰባቸው ርቀው ነው ፈተናውን የሚወስዱት በዚህ ወቅት ስልክን ጨምሮ ምንም አይነት የመገናኛ ቁሳቁስ ይዘው መሄድ አይችሉም ፤ ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት ባለመቻላቸው የሚፈጠር #የስነልቦና_ጫና ይኖር ይሆን ? ይሄ እንዴት ይታያል ? የወላጆች ኃላፊነትስ ምንድነው ? " .... ሆን ብለው ችግሮችን ለመፍጠር ካሰቡ ብዙ ምክንያቶችን ማድረግ ይቻላል ግን አሁን እነዚህ ልጆች ማትሪክ ሲያልፉ ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሊኖሩ ነው አይደለም እንዴ ለረጅም ጊዜ ፤ ለአራት ቀን ለአምስት ቀን ሲሆን እንደውም በዛ እድሜ ላይ ያሉ ልጆች ደስ እያላቸው የሚሄዱ ነው የሚመስለኝ። ይሄ አድቬንቸርም ነው ከቤት ወጥተው ፣ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ይፈተናሉ ይሄ አዲስ ነገር ነው። በዚህ አመት ለሚያደርጉት ይሄ ነገር የተጀመረው የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች ስለሚሆኑ ለልጆቻቸውም የሚነግሩት ነገር ይዘው ነው የሚሆነው፤ ታሪካዊም ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይሄ የተደረገው፤ በእኛ ጊዜ ነው ይሄ የሆነው፣ ይሄ ነገር ምን አለው የሚለውን ያያሉ። በእኛ በኩል ዋና ኃላፊነታችን ሰላማቸው እንዲጠበቅ ማድረግ፣ በምግብ ችግር እንዳይኖርባቸው ማድረግ፣ ህክምና ማዘጋጀት በየዩኒቨርሲቲዎቹ ይሄንን እያዘጋጀን ነው። ሰላም መግባታቸውን፣ ችግር በሚኖር ጊዜ ለማሳወቅ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች አሉ አብረው የሚመጡ ወደ ግቢ አይገቡም፤ ግን ችግር በሚኖር ጊዜ ከእነሱ ጋር ግንኙነት እየተደረገ ለቤተሰቦቻቸው መንገር የሚቻልበትን መንገድ አስቀምጠናል። ሁሉን ነገር ለማየት ሞክረናል። ይሄ ነገር አዲስ ስለሆነ ቀላል የሎጅስቲክስ ስራ አይደለም። አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ሰው አንቀሳቅሶ ይሄን ማድረግ በተወሰነ ደረጃ እንደ ሀገርም ያውም ጦርነት እየተዋጋን ባለንበት ሁኔታ መንግሥት ይሄን ማድረግ መቻሉ በእውነት የሚገርም ነው። እኛ ውስጥ ስላለንበትም እያየን ስለሆነ ነው ይሄን የምናገረው። ቀላል የሎጅስቲክስ ሥራ አይደለም። እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነው የሚሳተፍበት። ወደ 8 ሺ የፌዴራል ፖሊስ ይሳተፍበታል፣ 30 እስከ 40 ሺህ ፈታኞች ከየዩኒቨርሲቲው ወጥተው ይሳተፋሉ፣ ብዙ ምግብ አብሳዮች ይሳተፋሉ። በአጠቃላይ ትልቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ነው። እንደ ሀገርም ችሎታችንን አቅማችንን፣ በተወሰነ ደረጃ እየተጠናከረ ትላልቅ ነገሮችን ለመስራት ያለን ብቃት እየጨመረ የሚሄድበት ነው፤ ስለዚህ ደስ የሚልም ነገር አለው። ለቤተሰቦች የምንለው በተቻለን መጠን የልጆቻችሁን ኃላፊነት ወስደን ነው ይሄን ነገር የምንሰራው። እንደ ልጆቻችን ልንጠብቅ፣ እንደ ልጆቻችን እንዳይራቡ እንዳይጠሙ ልናደርግ፤ ምንም አይነት የደህንነት አደጋ ውስጥ እንዳይገቡ ተጠንቅቀን ነው ይሄንን ነገር የምናደርገው። ይህ ማለት ግን ምንም ነገር አይፈጠርም ማለት አይደለም። መቶ በመቶ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም። ማንኛውም ተማሪ ወደዚህም ቦታ ባይመጣ ቤቱም ሆኖ ሊታመም ይችላል ግን በእኛ በኩል ከህክምና ጋር በተያያዘ የጤና ባለሞያዎችን በየቦታዎቹ ላይ አስቀምጠናል፤ ችግር በሚኖር ጊዜ ልጆቹ ህክምና እንዲያገኙ። ቁርሳ፣ ምሳ እንዲሁም እራታቸውን እንመግባቸዋለን፤ ምግብ እንኳን ስናዘጋጅ የሃይማኖት፤ የባህል ነገሮችም እንዳይመጡ እሱን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረግን ነው። ወላጆች ያምኑናል ብለን ተስፋ እንደርጋለን። ...ወላጆች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ልጆቻቸው ወደ ፈተና በሚሄዱበት ጊዜ ትብብር ማድረግ፤ ፈተናውን ለመፈተን በሚሄዱበት ጊዜ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ ከቤት ነው ይሄ ነገር የሚጀምረው ምክንያቱም የ12 ዓመት ጥረት አፈር ነው የሚገባው አንድ የተከለከለ ነገር ይዘው ቢገቡ፤ ስለዚህ እኛ እንደውም ፍተሻው ፖሊስ ጋር መጥቶ ከመድረሱ በፊት ቤት ወላጆች ናቸው አይተው መላክ ያለባቸው። ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጧቸው የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ይኖራሉ ለምሳሌ፦ እንደ ደረቅ ምግብ ድንገት ለሊት ሲያጠኑ ቢያስፈልጋቸው ቆሎም ይሁን ሌላ የሚሰጧቸው ነገር ካለ፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ እነዚህን እንደሚያዚዟቸው ሁሉ የዛን ያህል የተከለከሉ ነገሮችን እንዳይዙ መቆጣጠር አለባቸው፤ ይህንንም ያደርጋሉ ብለን እናምናለን። ከዛ ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚጮኸውን አለመስማት ነው። ምክንያቱም ዋነኛው ሥራቸው በእንዲህ ዓይነት ነገር ማኅበረሰብን ማሸበር እንደ ችሎታ እና እንደእውቀት የወሰዱ ጤነኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ወላጆች የልጆቻችሁን ጉዳይ በሚመለከት በቀንጥታ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር፤ የምንነግራችሁ ቁጥሮች አሉ፣ የምንልካቸው የአካባቢው ትምህርት ተወካዮች አሉ። በዛ በኩል መገናኘት ያስፈልጋል። አንድ ነገር ቢፈጠር በእርግጠኝነት የምንነግራችሁ፤ ከእኛ ውሸት አትጠብቁ። የሆነውን ነገር ይሄ ነው የሆነው ብለን እንነግራችኃለን። ምንም የምንደብቅበት ምክንያት የለም። ይሄ የፖለቲካ ሥራ አይደለም ፤ ይሄ የትምህርት ሥራ ነው። የትምህርት ሥራ ደግሞ ሁላችንንም የሚያገናኝ እና የሚያጣብቅ ሥራ ነው። ወላጅን ከአስተማሪዎች፣ አስተማሪዎችን ከአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱና ከትምህርት አስተዳዳሪዎች ጋር የሚያይዘው ውስጣችን ለልጆቻችን ጤንነት፤ ለልጆቻችን የእውቀት ጥማት እና ሕይወትን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት ከማገዝ በላይ ምንም ሌላ ነገር የለም። ከዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ጥቅም ሆነ ትርፍ የለም። ይሄን ማወቁ ምንም የፖለቲካ ልዩነቶች እንኳን ቢኖሩ ትምህርትን የዛ መጠቀሚያ አናድርገው። ትምህርትን ከዛ ውስጥ እናውጣው። ትምህርት ስለልጆቻችን ነው። ___ የኢዜማ መሪ እና የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለዘንድሮው የማትሪክ ፈተና ሥርዓት ከሰጡት ማብራሪያ!
Show all...
የዜጎችን የደህንነት ስጋት አለብን የሚለው ጥያቄ ከሁሉም ጉዳይ ቀድሞ አትኩሮት ሊሰጠው ይገባል! በኦሮሚያ ክልል በወለጋ አምስቱም ዞኖች፣ መተሃራ እና ሌሎች አከባቢዎች ውስጥ ያሉ ዜጎች የደኅንነት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ እየተገለጸም ቢሆን አሁንም የማያባሩ ግድያዎች እና መፈናቀሎች መቀጠላቸው እጅግ አሳሳቢም አስጨናቂም ነው፡፡ በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ ያለው አሸባሪ ቡድን ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ የንጹሐንን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ መንግስት የኀዘን መግለጫ ጋጋታ ማውጣቱ ትርጉም አልባ ተግባር ነው፡፡ ዛሬም በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ በተለያየ መንገድ ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛል፡፡ ኢዜማ መጋቢት 24/2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ "የፌደራል መንግስት በኃይል እጥረት ምክንያት ማስፈር በማይችልባቸው ቦታዎች ላይ ማኅበረሰቡ እራሱን መከላከል የሚያስችለው አደረጃጀት እና ትጥቅ እንዲኖረው እንዲያደርግ እንጠይቃለን" በማለት ያቀረብነው ምክረሀሳብ ሰሚ አላገኘም፡፡ አሁንም የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ቁርጠኛ ሥራ መሥራት የክልሉ አስተዳደር ብሎም የፌደራል መንግሥት ተቀዳሚ ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ የሚገባውን አትኩሮት እንዲሰጠው በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በንጹሐን ዜጎች ጭፍጨፋ የሚሠራ የፖለቲካ ትርፍም ሆነ የፕሮፓጋንዳ ሥራን ፓርቲያችን ኢዜማ አምርሮ የሚኮንነውና የሚፀየፈው ተግባር ነው። የትኛውም የፖለቲካ ኃይል ከመሰል የሽብር ተግባር እንዲታቀብ እና በዜጎች ደኅንነት የፖለቲካ ቁማር ከመጫወት እንዲታቀቡ እናሳስባለን። የትኛውንም ዓይነት የፖለቲካ ጥያቄ ያነገበ ኃይል ችግሮችን በመነጋጋር ለመፍታት መሥራትን ቢያስብ የሚረፍድ ጊዜ አይኖርም ብለን እናምናለን፡፡ ከዚህ ውጪ ንጹሐንን በመጨፍጨፍ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ሊኖር አይችልም። ይህን ነውረኛ ተግባር በማስታከክ የተለየ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ለሚሽቀዳደሙ ኃይሎችም የማኅበረሰቡን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው ለዜጎች ሰላም እና ደኅንነት በጋራ በመቆም እንጂ ጣት በመጠቋቆም፣ የጠላትና የወዳጅ ትርክትና በጥላቻ የተመረዘን የብሔር ፖለቲካ ማራገብ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምም ሆነ በአካባቢው በመከራ እየተለበለበ ላለው ህዝባችን ጠብ የሚል መፍትሄ ማምጣት አለመቻሉን ነው፡፡ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
Show all...
"በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ ያለው አሸባሪ ቡድን ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ የንጹሐንን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ መንግሥት የኀዘን መግለጫ ጋጋታ ማውጣቱ ትርጉም አልባ ተግባር ነው"
Show all...