Peka - ፔካ
Open in Telegram
The Great source of Knowledge. ፔካ ብሩህ የሆነ ነጭ ዕንቁ ነው። እውቀትም ብርሃን ነው። You Tube => ? Channel 2 => t.me/Peka369 Owner - @Lumos1
Show more2 958
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-2930 days
Posts Archive
2 958
📌 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
👉 በዓለ ጥምቀትን በፍጹም ትህትናና ጸሎት የተቸገሩትን፣ የተፈናቀሉትን የተራቡትን፣ የተጠሙትን፣ የታረዙትን በመከራና በችግር ውስጥ ያሉትን እንዲሁም ጽኑ ምጥ ውስጥ የምትገኘውን ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ሌሎችንም ሀገራት እያሰብን እናክብረው!
'ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት'
@EthiopeTowoderos

📌 እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
👉 ሥሉስ ቅዱስ ሁላችንንም በምሕረት ዓይን ይመልከተን፤ የንስሃ ልብ፣ ሰሚ ጆሮ፣ አስተዋይ ልቡና፣ የተግባር ኃይል ይስጠን ሀገራችንን ስለአያቶቻችን ስለቃለኪዳኗ ብሎ ይጠብቅልን።....
👉 እኛም እንደ መላእክት
" አሐዱ አብ ቅዱስ
አሐዱ ወልድ ቅዱስ
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" እንላለን።
👉 #ሥሉስ ቅዱስ ይባርኩን።
ጥር 7 2014 ዓ.ም
@EthiopeTowoderos
2 958
🗓 ጥር 3 1997 ዓ.ም
🔰እግዚአብሔር ይመስገን ጥር 03/05/1997 ዓ.ም በአምሓራ ክፍለ ሃገር : በደቡብ ጎንደር ዞን : የዛኔ ወደ 220,000 ሰዎች በነበሯት እብናት ወረዳ ከእናትና ከአባቴ ተወለድሁ። አሁን ግን የምኖረው ባሕር ዳር ነው።
📜 እነሆ እስከ አሁን በምድር ላይ 17 ዓመታትን ኖርኩ።
በአንድነቱ መንታዌነት በሦስትነቱ ርባዔነት የሌለበት ልዑል አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ክብር ይግባውና እንደርሱ ፈቃድ በእድሜ ላይ እድሜን፣ በጸጋ ላይ ጸጋን ከጨመረልኝ በዚሁ ቻናል ወደፊትም በYoutube ቻናሌ ቀረጻ ስጀምር በጣም ድንቅ ጥልቅ ረቂቅ የሆኑ የትም ያልተነገሩና ያልተሰሙ እውቀቶችን እንደማጋራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
📌 እኔን ኃጥኡን ልጅሽን ከክፉ ሥራና ከክፋት መናፍሥት ሁሉ በግልጽና በኅቡዕ የምትጠብቂኝ ባአታ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ምስጋናዬ ይድረስሽ።
📌 ከልጅነቴ ጀምሮ በድንቅ ክንፎችህ የምትከልለኝ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ምስጋናዬ ይድርሰህ።
📌 ለዛሬ ሁላችሁም የቻናሌ ቤተሰቦች በውስጥ መስመር በኩል እየገባችሁ እንኳን ተወለድክ : ቀሪ ዘመንህን የንስሓ ዘመን ያድርግልህ በማለት መልካም ምኞታችሁን እንድታደርሱኝ ስል በአክብሮት ጋብዣችኋለሁ ፤ ቀድማችሁ አስታውሳችሁ መልካም ምኞታችሁን ያደረሳችሁኝንም በጣም ላመሰግን እወዳለሁ።
በዛሬው እለትም አንድ ውለታ እንድትውልሉኝ እፈልጋለሁ ፤ ለ1 ቅጽበት ብቻ በጸሎታችሁ እሰቡኝ🙏 እናንተንም ቸሩ እግዚአብሔር ያስብልኝ።
📌 ኢትዮጵያችን እንኳንም ተወለድኩልሽ!
03/05/2014 ዓ.ም
✍ ኃይለሚካኤል ደሣለኝ።
📥 Inbox 👉 @HailemichaelDesalegn
2 958
🗓 ጥር 3 1997 ዓ.ም
🔰እግዚአብሔር ይመስገን ጥር 03/05/1997 ዓ.ም በአምሓራ ክፍለ ሃገር : በደቡብ ጎንደር ዞን : የዛኔ ወደ 220,000 ሰዎች በነበሯት እብናት ወረዳ ከእናትና ከአባቴ ተወለድሁ። አሁን ግን የምኖረው ባሕር ዳር ነው።
📜 እነሆ እስከ አሁን በምድር ላይ 17 ዓመታትን ኖርኩ።
በአንድነት መንታዌነት በሦስትነቱ ርባዔነት የሌለበት ልዑል አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ክብር ይግባውና እንደርሱ ፈቃድ በእድሜ ላይ እድሜን፣ በጸጋ ላይ ጸጋን ከጨመረልኝ በዚሁ ቻናል ወደፊትም በYoutube ቻናሌ ቀረጻ ስጀምር በጣም ድንቅ ጥልቅ ረቂቅ የሆኑ የትም ያልተነገሩና ያልተሰሙ እውቀቶችን እንደማጋራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
📌 እኔን ኃጥኡን ልጅሽን ከክፉ ሥራና ከክፋት መናፍሥት ሁሉ በግልጽና በኅቡዕ የምትጠብቂኝ ባአታ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ምስጋናዬ ይድረስሽ።
📌 ከልጅነቴ ጀምሮ በድንቅ ክንፎችህ የምትከልለኝ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ምስጋናዬ ይድርሰህ።
📌 ለዛሬ ሁላችሁም የቻናሌ ቤተሰቦች በውስጥ መስመር በኩል እየገባችሁ እንኳን ተወለድክ : ቀሪ ዘመንህን የንስሓ ዘመን ያድርግልህ በማለት መልካም ምኞታችሁን እንድታደርሱኝ ስል በአክብሮት ጋብዣችኋለሁ ፤ ቀድማችሁ አስታውሳችሁ መልካም ምኞታችሁን ያደረሳችሁኝንም በጣም ላመሰግን እወዳለሁ።
በዛሬው እለትም አንድ ውለታ እንድትውልሉኝ እፈልጋለሁ ፤ ለ1 ቅጽበት ብቻ በጸሎታችሁ እሰቡኝ🙏 እናንተንም ቸሩ እግዚአብሔር ያስብልኝ።
📌 ኢትዮጵያችን እንኳንም ተወለድኩልሽ
📌 እመሰ ረሳእኩክሙ ሃገርየ ኢትዮጵያ ፡ ወማርያም ድንግል ወኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለትርስአኒ የማንየ ፤ ወይጥጋዕ ልሣንየ በጉርዔየ ለእመ ኢተዘከርኩክሙ !!!
✍ ኃይለሚካኤል ደሣለኝ
📥 Inbox 👉 @HailemichaelDesalegn
2 958
📌 ስለ ሰብአ ሰገል ታሪክ ማወቅ ከፈለጋችሁ ባለፈው ዓመት የጻፍኩትን ጽሑፍ ወይም አጭር ጥናቴን ከላይ ተጭናችሁ( https://t.me/EthiopeTowoderos/3688) ማንበብ ትችላላችሁ።
2 958
📌 ሊቃውንት በቅኔያቸው ከልደት ጋር የተያያዘ ምን አመስጥሮት አስቀምጠውልን ይሆን?
1. 👉 ሥላሴ:-
ለልደተ ክርስቶስ ወማርያም፣
ስብሐተ ናዝልፍ ይሜህረነ መምህር፣
ወይመርሐነ መራሒ መዝሙር።
ለአዳምሰ ዘተሠገወ እምድር፣
ዜናሁ ኀደግነ በኀጺር፣
ሶበሰ ይነውኅ አንቀጸ ነገር፣
በውስቴቱ እምተረክበ ነውር
👉 ትርጉም፦
ለክርስቶስና ለማርያም ልደት፣
ምስጋናን እናዘወትር ዘንድ፣ መምህር ያስተምረናል፣
መሪ መዝሙርም ይመራናል።
ከምድር ሰው የሆነ የአዳም ዜናን፣
ግን በአጭር ተውን፣
የነገር አንቀፅ ቢረዝም ግን፣
በውስጡ ነውር በተገኘ ነበር።
👉 ምስጢር:-
የመዝሙር ዘማሪ መዝሙሩን እያቀነቀነ ተቀባዮቹን እንደሚመራቸው የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድና የቅድስት ማርያም መወለድ አስቀድሞ በምሳሌና በትንቢት ተነግሮ ስለተፈፀመ እንከን የሌለበት ሆነ። አንዳንድ አሳፋሪ ድርጊት ያለበትን ነገር አብራርቶ ከማቅረብ ይልቅ ሸፋፍኖ እንዲያልቅ ማድረግ በሽማግሌዎች ዘንድ የተለመደ ነው። የሰው ዘር ሁሉ አባት የሆነው አዳምም አትብላ የተባለውን በለስን በልቶ ያመጣው ፍዳ ለልጆቹ ተረፏቸው። ከዚህም የተነሳ የአባትነቱ ታሪክ የሚያስመሰግን አይደለም። በማለት ባለቅኔው አዳምና ሔዋን የበለስን ፍሬ በመብላታቸው ምክንያት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ተወስኗል የሚባለውን የሞት ፍርድ በቅኔያቸው ምስጢር ያስረዳል።
2. 👉 ሥላሴ፦
ታሰምዕ ለእዝነ ኵሉ፣
ፅንስት ዖፍ ድምፀ አእባን፣
እስከነ ሕማማ ትረስዕ እምከርሣ ጊዜ ወሊዶታ ዕጓለ፣
ከመትርከብ በሰሚዐ ዝንቱ ዕፍረት ወሣህለ።
ርግበ ነጋሢ ሰሎሞን ባሕቱ በዘተረኮቦታ ድንግለ፣
እምከርሣ ሕማም እስመ ሰሰለ፣
ጊዜ ወሊዶታ እምከርሥ ሕፃና ልዑለ፣
ለጾታሃ ኢያስምዐት ቃለ።
👉 ትርጉም፦
የፀነሰች ወፍ የድንጋዮች፤
ድምፅን ለሁሉ ጆሮ ታሰማለች፤
ከሆዷ ልጅን በመውለዷ ጊዜ ህመሟን እክስትረሳ ድረስ ይህን በመስማት እረፍትን፣ ይቅርታንና ሰላምን ታገኝ ዘንድ።
ነገር ግን የነጋሽ ሰሎሞን ርግብ ድንግልን ሆና በመገኘቷ ምጥ ከሆዷ ተወግዷልና፤
ከፍተኛ(የከበረ) ልጅዋን በመውለጃዋ ጊዜ፤
ለወገኖችዋ ቃልን አላሰማችም።
👉 ምስጢር፦
እንደ ግንደ ቆርቁር ያለች አንድ ወፍ አለች፤ ይህች ወፍ ፀንሳ በምትወልድበት ጊዜ የድንጋይ ድምፅ ስታሰማና ስትሰማ ህመሟ (ምጧ) ይቀልላታል ይባላል። ርግብ የተባለችው ቅድስት ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ልጇ ክርስቶስን ስትወልድ እንደሌሎቹ ወላድ ሴቶች ምጥ የሌለባትና የምጥ ቃልን ያልሰማች ተባት የሌላት ርግብ ሆነች።
👉 ታሪክ፦
አንዲት ዖፈ ያሬድ የምትባልና ሦስት አይነት ድምፅ የምታሰማ ወፍ አለች፤ በምጧ ጊዜ ኪል እንደምትባል ስስ ድንጋይ ያለ ድምፅን ለሌሎቹ ሁሉ ታሰማለች። በዚህ ጊዜ ምጧ ይቀልላትና በቶሎ ትወልዳለች። ሌሎቹንም በድምጿ ቶሎ ይወልዳሉ ይባላል።
👉 እንግዲህ ሊቃውንት በረቀቁ ቅኔያቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደትና ተያያዥ ታሪኮችን እንዲህ አራቅቀው አመስጥረውልናል። እኔም ይሄው ከዓለም ሁከትና ግርግር ርቃችሁ ተራቀቁበት ብዬ ጽፌ ለጠፍኩላችሁ።
✍ ኃይለሚካኤል ደሣለኝ።( @HailemichaelDesalegn )
🔰 ቻናል - @EthiopeTowoderos
2 958
🔆 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
👉 “ ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት ” እንዲሉ የእግዚአብሔር ወልድ ልደቱ ሁለቴ ነው። ማለትም ቅድመ ዓለም ዘእንበለእም(ያለ እናት) ከአብ፤ ድኅረ ዓለም ዘእንበለአብ(ያለ አባት) ከማርያም ተወልዷልና ነው።
👉 አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በገነት 7 ዓመት ከ3 ወር ከ17 ዕለት በንጽሕና ፍጹም እንደ ፀሐይ እያበሩ፣ እንደ መላእክት እየኖሩ ሳለ በአሣቹ መንፈስ ከሳቱና ድል ከሆኑ በኋላ ለክብርና ለሕይወት ብቻ ተፈጥረው የነበሩት ዓይኖቻቸው ተከፍተው ለክብርና ለውርደት፣ ለሕይወትና ለሞት ሆኑ።..... መዳኛቸውንም እግዚአብሔር ተናገረ።
👉 በሴት እንደሳትክ ከልጅ ልጅህ ከሴት ተወልጄ፣ ከዛፍ ግንድ እንደበላህ በዛፍ ግንድ ተሰቅየ( ዕፅ የሐዩ ዕፅ ይቀትል ማለትም እንጨት ያድናል እንጨት ይገድላል ሚባለው ለዚህም ነው)፣ አሣቹ መንፈስ ዲያብሎስ በትዕቢትና በሴረኝነት እንዳሳተህ አሳቹን መንፈስ በትህትናና በፍቅር ድል ነሥቼ፣ በአንተ ምክንያት በተረገመችው ምድር ነፍስህን ወደ ሲኦል አግብቼ፣ ሥጋህ ገነትን አያያትም እኔ እንደተነሳው በፍጻሜ ሥጋህንና ነፍስህን አዋህጄ የማይሞት የማይበሰብስ መንፈሳዊ ሥጋ ሆኖ ይነሳል።.... የሚለው ሕያው ቃል መሠረት የተጣለበት ዕለት ናት።
👉 ዛሬ የዓለም ፈጣሪ አዳምና ሔዋንን እንዲሁም ዘሮቹን ለማዳን በገባው ቃል መሠረት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅጸን ያለ መለወጥ አድሮ፣ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደበት ዕለት ነው ። በዚህች ዕለትም ለሰው ልጅ እውነተኛው ሰላም ስለተሰጠ መላእክት አመሰገኑ፤ የሰው መዳን ለእነርሱም ደስታቸው ነውና። የጥበብ ሰዎችም ከጥበብ ሀገራቸው ከምሥራቅ ተነስተው የሀገራቸውን ንጹሕ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤና ሌሎችንም መባቸውን ሰግደው አቀረቡ፤ ኑኀ(ሩቅ) ዘመን ከአያቶቻቸው ዘንድ ታዘዋልና የሄሮድስን ሽንገላ እንጂ የአያቶቻቸው ጠቢባኑን ትንቢት አላቃለሉም፤ እነርሱም ጠቢባን ነበሩና ነው።
👉 በዓል ሽሮ የከበረ፣ ጦም ገድፎ የወፈረ የለም እንዲሉ፤ ጾሙን በሰላም ያስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን። በዓሉንም የበረከት ያድርግልን!
📌 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
✍ ሊቃውንት በቅኔያቸው ከልደት ጋር የተያያዘ ምን አመስጥሮት አስቀምጠውልን ይሆን? የሚለውን በቀጣይ ጽሑፌ አሰፍራችኋለሁ።
✍ ተጻፈ በታዳጊ ኃይለሚካኤል ደሣለኝ።
ቻናል - @EthiopeTowoderos

📚 " መልክአ ሚካኤል ወገብርኤል ካልዕ ጸሎቱና ገቢሩ "
በጥያቄያችሁ መሠረት ከሥራይ መተት፣ ዛር፣ ዓይነጥላ፣ ቡዳ፣ ጥላወጊ... ከርኩሳን መናፍሥት የሚጠብቀው ' መልክአ ሚካኤል ወገብርኤል ካልዕ' የተባለው ጸሎት ከነሙሉ ገቢሩ በPDF አዘጋጅቼ ይሄው በወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት ቻናሌ ላይ ለቀቅኹት።
📌 በዚህ PDF ላይ ፦
ሙሉ ጸሎቱን፣ የጸሎቱን ጥቅም በአጭሩና ገቢሩን ታገኙታላችሁ፤ እንዲሁም ንባቡንና የጠለቀ ማብራሪያ የምትፈልጉ እዛው ፒዲኤፉ ላይ የምታገኙትን ሊንክ በመጫን ' ወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት' ከሚለው የYouTube ቻናሌ ላይ የለቀቅኹትን ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ።
👉🏾 አስተያየት ካላችሁ በውስጥ መስመር @HailemichaelDesalegn ላይ ታገኙኛላችሁ።
👉🏾 ቻናል- @EthiopeTowoderos
2 958
📌New Video:
Watch " [ሳታዩት እንዳታልፉ] ከርኩሳን መናፍስት የሚጠብቅ ጥንታዊ ጸሎት - ከሥራይ፣ መተትና ዛር ዓይነጥላ የሚጠብቅ ንባቡና ገቢሩ! Wedehuala Ancient Wisdoms " on YouTube
👇👇👇
https://youtu.be/3ZqHkzJscOo
2 958
🤔የባለ አደራ ዕዳ🤔
መሆን ቢያዳግትም - አሁን ባለንበት፣
ሰልጥኖ የላቀ፣
ጥበብን ቀማሪ - እንደ ጥንታዊያን፣
ዝናው የታወቀ፣
በብራና መጽሐፍት - ትተውት ያለፉት፣
የታሪክ አሻራ፣
የተሻልን ልንሆን - መነሻ ሰጥተውን፣
ለትውልድ በአደራ፣
በጥልቀት ሳናውቀው - ሳንጠቀምበት፣
በእኛ ዘንድ ተንቆ፣
ጠብቆ እንደመያዝ - አሳልፈን ሰጥተን፣
በባእዳን ታውቆ፣
ታሪክን ለማጥፋት - ያለእረፍት ለሚጥር፣
ለተነሳ ታጥቆ፣
ቅርስን ለማቀበል - ይፈር ሕሊናችን፣
ይቅርብን!! ክብረቱ፣
ያለፈው ሳይበቃ - ሸር ተሰርቶብን፣
ሳይለቀን ቁጭቱ፣
ይብቃ! ሞኝነቱ - ባታለሉን ቁጥር፣
ዳግመኛ መሞቱ።
🔰የባለ አደራ ዕዳ የግጥም መድብል በልዑል ሰገድ ደረሰ ገጽ 47🔰
©#በወደ_ኋላ_የተዘጋጀ

🔔 Watch " [አትሳሳቱ!] እውነት ጤፍ ከዘንዶ ተገኝቷልን? የአባ ተስፋ ሥላሴ መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ጥናት Wede Huala Ancient Wisdoms " On YouTube
👇👇👇
https://youtu.be/aSLkytXQXao
2 958
🔔 Watch " [አትሳሳቱ!] እውነት ጤፍ ከዘንዶ ተገኝቷልን? የአባ ተስፋ ሥላሴ መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ጥናት @Wedehuala Ancient Wisdoms " On YouTube
👇👇👇
https://youtu.be/aSLkytXQXao
2 958
📚 የቢቢሲ(BBC) የጥያቄ ጥበቦችና የአባ ተስፋ ሥላሴ የምስጢር መልስ
👉🏾 Size - 22 MB
' ኹሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ ' እላለሁ መልካም ንባብ!
📎 በወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት የተለቀቀ
Join: @EthiopeTowoderos
2 958
🔔 የቴሌግራም ቻናል ያላችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
👉🏾 ትውልድን የሚያንጽና የሚያነቃ በጎ አላማ ያለው ቻናል አሎት?
ቻናልዎትን እኛጋ ያስመዝግቡና ያለምንም ክፍያ በነጻ በተለያዩ ቻናሎች ላይ የምናስተዋውቅልዎት ይሆናል።
👉🏾 የምዝገባውን ሂደት ጨምሮ ምዝገባውን ከሥር ባለው ቦት ገብተው መጠየቅና መረዳት እንዲሁም መመዝገብ ይችላሉ።
💬 ወደ ኋላ ፕሮሞሽን ላይ ቻናል ለማስመዝገብ 👇🏼👇🏼👇🏼
@WedehualaPromotion_Bot
@WedehualaPromotion_Bot
@WedehualaPromotion_Bot
ይሄን ይጫኑ።
2 958
⚠️ Read Carefully before you join Our Promotion
ይህ Wede huala Promotion / ወደ ኋላ ፕሮሞሽን ነው።
🔅 500 - 1K
🔆 1K - 5K
🔱 5K - 10K
🔊 የፕሮሞሽን/ ማስታወቂያ ፕሮግራም
👉🏾 ሰኞ
👉🏾 ረቡዕ
👉🏾 ዓርብ
👉🏾 እኁድ
⏰ የፕሮሞሽን ሰዓት ⏰
👉🏾 ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ
👉🏾 ጠዋቱ 1 ሰዓት ።
🔊 የፕሮሞሽናችን ደንቦች 📣
👉🏾 በፕሮሞሽን እለታት የማስታወቂያ ጽሑፎችን ከተለቀቁ በኋላ ማጥፋት አይፈቀድም፤ ሌላ ልጥፎችን ባትለቁም ይመረጣል።
👉🏾 በተጨማሪም እየደለታቹ የምታስቸግሩ አድሚኖች ካላችሁ ከ3 ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ቻናላችሁ ከፕሮሞሽን የሚባረር ይሆናል።
21/02/2014 ዓ.ም ተጀመረ!
💹 ፕሮሞሽን ለመመዝገብ፡ @WedehualaPromotion_Bot
✅ Our Channel : @WedehualaPromotion