cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Dossery 👉@[email protected]👈

ኢንሻ አሏህ በዚህ ቻናል የሚቀርቡ ነገሮች👇👇 ➽ ኢስላማዊ ታሪኮች እና ቂሷዎች ➽ኢስላማዊ ግጥሞች በድምፅ እና በፅሁፍ ➽ሀላል የሆኑ ቀልዶች ➽ አጫጭር የቁርአን ቃሪኦች በተለይ የYassir AlDossery እና የተለያዩ አለም አቀፍ ቃሪኦች ➽ እና አስተማሪ ሙሀደራዎች እና የመሳሰሉትን በዚህበDossery 👉@[email protected]👈 Channel ያገኛሉ። ሀሳብ እና አስተያየት 👉@AlDossery

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
154
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዚያም የፊት እግሩን……እየቆራረጠ ሳይሞት አሰቃይቶ ገደለው። የጠላት ወሬ እውነት መስሎት የልብ ወዳጆቹን ለጠላት አሳልፎ የሰጠው ጥቁሩ በሬ መጨረሻው ከጓደኞቹ የከፋ ሆነ። =___=____==______=_____=== ከዚህ ምን እንማራለን? ①ኛ:አንድነት ሃይል መሆኑን!!አራቱ በሬዎች ወደ አራት አቅጣጫ ዙረው በመጠበቃቸው አንድም ጠላት ሊደፍራቸው አልቻለም ነበር። ②ኛ:የመጀመሪያው የጠላት እስትራቴጂ መነጣጠል እና አንድነትን ማፍረስ እንደሆነ!! ③ኛ:ራስ ወዳድ እና ቃሉን የሚያጥፍ ጓደኛ አስቀያሚነት!! ④ኛ:የመጥፎ ሰው መጨረሻው እጅግ አስከፊ መሆኑን!! እና ሌሎችም!! ♨በመሆኑም ዛሬ የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሞችን ለማጥቃት ሲፈልጉ በፊርቃ ወይንም በግለሰብ ደረጃ እየነጣጠሉ ነውና ወገንህ ሲነካ አንተ ዝም ብለህ ዳር ቆመህ የምትመለከት ከሆነ በእርግጠኝነት ጥቁሩ በሬ ማለት አንተ ነህ!! ለግዜው ብትቆይም መጨረሻ ላይ ግን አንተንም ይበሉሃል!!ያውም የከፋ አበላልን!! ስለዚህ ልብ ግዛ!!!
Show all...
#አንተየተበላኸውኮ_ነጩንበሬ_አሳልፈህየሰጠኸኝእለት_ነው" #የአራቱበሬዎች_እና_የአያጅቦ_ታሪክ!! ____________________ ድሮ የፕራይመሪ ተማሪ በነበርኩበት ግዜ በአማርኛ ወይንም በስነዜጋ መማሪያ መፅሀፍ ላይ አንድ ትልቅ ቁምነገር ያላት ትንሽየ ተረት ነገር አስታውሳለሁ!ተረቱን እንደወረደ ባላስታውሰውም ከመልእክቱ ጋር በማይጋጭ መልኩ በራሴ አገላለፅ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ። "በድሮ ግዜ"ብሎ ይጀምራል ተረቱ!ያው የተረት ሙቀድማው ይሄ አይደል? በድሮ ግዜ ነጭ፣ጥቁር፣ዳለቻ እና ቀይ በሬዎች ካለምንም ጠባቂ በህብረት ይኖሩ ነበር። በሚኖሩበት አካባቢ ደግሞ ጅብ እና ሌሎች አውሬዎችም የሚኖሩበት ጫካ ስለነበር፣ራሳቸውን ከዚህ ጅብ ለመከላከል በማሰብ አራቱም ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ፊታቸውን በማዞር በአራቱም አቅጣጫዎች ሲጠብቁ ነበር የሚያድሩት አሉ። ሆኖም ከእለታት በአንዱ ቀን አያጅቦ ወደበሮቹ ሰፈር ይሄድና መግቢያ ሲያጣ ግዜ አንድ መላ ይዘይዳል!ይሄውም ቃስ ብሎ ጥቁሩ በሬ ፊቱን በዞረበት(በሚጠብቅበት አቅጣጫ)ይሄድና"አንዴ ስማኝማ"ይለዋል። "አንዴ ስማኝማ!እኔ ከእናንተ ጋር በሰላም መኖር ነው የምፈልገው።እናንተን የማጥቃትም ሆነ የመተናኮል ምንም አላማ የለኝም።እንዳውም ሌሎች አውሬዎች በእናንተ ላይ ሲያሴሩ እና እናንተን ለመብላት ሲያቅዱ እኔ በቅርበት ስለምሰማ መጥቼ መረጃ እነግራችሗለሁ።ነገር ግን ይሄ ነጩ በሬ በሩቁ እያንፀባረቀኝ በጣም አስቸገረኝ።እርሱ ከእናንተ ጋር እስካለ ድረስ ከእኔ ጋር በሰላም ለመኖር ያስቸግራልና እናንተ በሰላም ለመኖር ከፈለጋችሁ እርሱን ከቡድናችሁ ማውጣት ነው።ለማንኛውም እርሱ(ነጩ በሬ)ሳይሰማ ሶስታችሁ ጉዳዩን ተወያዩበትና ውሳኔያችሁን ታሳውቀኛለህ።ከአራታችሁ ውስጥ አንድ በሬ ቢኖር ባይኖር ብዙም የሚጠቅማችሁና የሚጎዳችሁ አይደለም።እንዳውም እንዳልኩህ እርሱን እንድበላው የምትፈቅዱልኝ ከሆነ ከእኔ ጋር በሰላም ከመኖርም አልፋችሁ እኔ ከእርሱ የበለጥ ልጠቅማችሁ እችላለሁ።ለማንኛውም ጉዳዩን ምከሩበት"ይልና አያጅቦ ወደ መኖሪያው ይመለሳል። ጥቁሩ በሬም ጉዳዩን ካመነበት በሗላ ነጩ በሬ ሳይሰማ ቀዩን እና ዳለቻውን በሬ በሚስጥር ይጠራና ድምፁን ዝቅ አድርጎ"እኔ አሁን የጠራሗችሁ በጣም አሳሳቢ ለሆነ ጉዳይ ነው።ጉዳዩ የህልውና ጉዳይ ነው።ጉዳዩ የእኛ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው።በአንድ ጓደኛችን ምክናየት ለብዙ ግዜያቶች ተከባብረን ከኖርን የዱር ወዳጆቻችን ጋር ወደመጣላት እየሄድን ነው።ይሄው አያጅቦ በአካል በቁምነገር መጥቶ የነገረኝ ይሄኑ ነው።እኔ ከእናንተ ጋር ምንም ፀብ የለኝም!ነገር ግን ይሄ ነጭ በሬ በሩቁ እያንፀባረቀ ሰላም ስለነሳኝ፣በእርሱ ምክናየት ሁላችሁም ከምትረበሹ እርሱን አሳልፋችሁ ብትሰጡኝ ከእኔ ጋር በሰላም ከመኖርም አልፋችሁ እኔ ከእርሱ የበለጥ እጠቅማችሗለሁ' ብሎ ነግሮኛል።እርግጥም ወዳጃችን አያጅቦ እንዳለው ነጩ በሬ በሩቁ ስለሚታይ አያጅቦን ከመረበሽም አልፎ ሌሎች ከባባድ አውሬዎችንም ያመጣብናል።ስለዚህ ያለን አማራጭ አንድና አንድ ነው!ነጩን በሬ ለአያጅቦ አሳልፈን ሰጥተን እኛ ካለስጋት የሰላም ኑሮ መኖር!!እስከ መቼ በስጋት እንኖራለን?እስኪ እናንተ ምን ትላላችሁ?"ይላቸዋል።እነርሱም ትንሽ እንደማሰብ ካደረጉ በሗላ በጥቁሩ በሬ ሀሳብ ተስማሙ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ነጩ በሬ እንድጠብቅ በተመደበበት አቅጣጫ እራሱንም ጓደኞቹንም በንቃት በመጠበቅ ላይ ነበር።ይሄን ሁሉ ሴራ አያውቅም። በማግስቱ ጨለምለም ሲል አያጅቦ በቀጠሮው መሰረት ጨለማን ተገን አድርጎ በጥቁሩ በሬ አቅጣጫ መጣ።እንዴደረሰም ጥቁሩ በሬ አያጅቦ ባነሳው ሀሳብ ላይ ሶስታቸውንም እንዳሳመናቸው እና ለዚህም የተለዬ ውለታ እንድደረግለት አያጅቦን ጠየቀ።አያጅቦም ከፍተኛ ምስጋና ካቀረበ በሗላ ጥቁሩ በሬ ላደረገለት ቀናነት ከሌሎቹ በሬዎች ረዘም ያለ እድሜ እንደሚኖረው አረጋገጠለት። ከዚያም አያጅቦ ዘና ብሎ ሶስቱንም በሬዎች ካለፈ በሗላ ሌሎች ጓደኞቹም እንዴ እርሱው በታማኝነት እየጠበቁ እንደሆነ በማሰብ እርሱ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ተመደበበት አቅጣጫ አድርጎ በመጠበቅ ላይ ወዳለው ነጩ በሬ በመሄድ ከሗላው ሞነተፈው።ነጩ በሬ ቢጮህም ሌሎቹ በሬዎች ባላየ ባልሰማ ዝም ጭጭ አሉ።አያጅቦም ነጩን በሬ ደጋግሞ በመሞንቸፍ ካለስጋት ዘና ብሎ በላውና ሶስታቸውንም አመስግኖ ወደጫካው ሄደ። ይህ ከሆነ ከወራት በሗላ አያጅቦ በድጋሜ ይመጣና አሁንም ለጥቁሩ በሬ በዝግታ ሰላምታ ያቀርብለታል።ጥቁሩ በሬም ሰላምታውን ከመለሰ በሗላ አሁን ደግሞ ምን ረብሾት እንደመጣ በአግራሞት ይጠይቀዋል።አያጅቦም ድምፁን ዝግ አድርጎ በሚስጥር"እንዳልኩህ ባለፈው ነጩን በሬ አሳልፋችሁ ሰጥታችሁኝ ከእናንተ ከተለዬ በሗላ እኔም እናንተም በሰላም እንኖራለን የሚል ትልቅ ተስፋ ነበረኝ።እኔ ከነጩ በሬ ውጭ ሌሎቻችሁ በሩቁ የምታንፀባርቁ አልመሰለኝም ነበር።ለካስ ከነጩ በሬ ጋር ሲነፃፀር ነው እንጅ ቀዩ በሬም ሲያንፀባርቅ ቀላል አይደለም!እንዳውም እርሱ ሳይብስ አይቀርም!!ስለዚህ ሁለታችሁ በሰላም ለመኖር ከፈለጋችሁ ያላችሁ ብቸኛ አማራጭ ልክ በነጩ በሬ እንዳደረጋችሁት ቁርጠኝነት እና ለሰላም መስዋእትነት ሁሉ አሁንም በቀዩ ጓደኛችሁ ላይ መድገም ነው።በእርግጥ ሰላም ከዚህም የበለጥ መስዋእትነትን ይጠይቃል…"ብሎ ይነግረዋል።ጥቁሩ እና ዳለቻው በሬም በአያጅቦ ሀሳብ ተስማሙና ቀዩን በሬ አሳልፈው ሰጡት።አያጅቦም እፊታቸው እንክት አድርጎ በልቶ አመሰግኖ እየሳቀ ወደ መኖሪያው አዘገመ። አሁንም ከወራት በሗላ አያጅቦ ጨለማን ተገን አድርጎ በደንበኛው በጥቁሩ በሬ አጠገብ ቀስ ብሎ መጣና ዳለቻው በሬ ሳይሰማው የተለመደውን ስብከት ቀጠለ። "እኔ ነጩ በሬ እና ቀዩ በሬ ብቻ ይመስሉኝ ነበር ከሩቅ የሚታዩት። ለካስ በሩቅ የማትታየው አንተ ብቻ ነህ!ይሄ ዳለቻ ጓደኛህም ትኩር ብለው ካስተዋሉት ከሩቅ ይታያል።ስለዚህ አውሬዎችን ከሩቅ እየተጣራ ከሚያስበላህ ቶሎ አትገላገልም?በዚያ ላይ እስከ መቸ በሚስጥር እናወራለን?በነፃነት ዘና ብለህ ለመኖር እርሱን አሳልፈው ልትሰጠኝ ይገባል።እርሱን ከሰጠኸኝ በሗላ ምንም ነገር እንደማልጠይቅህ ቃል እገባልሀለሁ"ይለዋል። ጥቁሩ በሬም በእርግጥም እርሱ በጨለማ እንደማይታይ እርግጠኛ ስለሆነ ብቻውን በነፃነት ለመኖር እና ለአያጅቦም እጅግ ትልቅ ውለታ በመዋል ወዳጅነቱን ለማጠናከር በማሰብ የመጨረሻ ጓደኛውን አሳልፎ ሰጠው። አያጅቦም ዳለቻውን በሬ በልቶ ጥቁሩን በሬ ስሞ ወደ ጫካው አመራ። ከዚያም አንድ ቀን እንኳን ሳይቆይ እና እንደስከዛሬው ጨለምለም ሳይል አያጅቦ እየሳቀ ዘና ብሎ ወደ ጥቁሩ በሬ መጣ።ጥቁሩ በሬም ሁኔታው ስላላማረው ቶሎ ብሎ ሰላምታ ቢያቀርብለትም አያጅቦ ጆሮም ሳይሰጠው ቀረበውና አንዴ ሞነቸፈው። ጥቁሩ በሬም እንዴ ማሳዘን እየሞከረ"አሁን ደግሞ እኔን ልትበላኝ ነው?እኔኮ ከሩቅ አልታይም…!ደግሞስ ከጓደኞቸ ረዘም ያለ ግዜ እንደምቆይ ቃል ገብተህልኝ አልነበር!?"እያለ ማለቃቀስ ጀመረ። አያጅቦም ቆጣ ብሎ"እባክህ ለወሬ ግዜ የለኝም ርቦኛል! ቃል በገባሁት መሰረት ከሌሎቹ ጓደኞችህ ረዘም ያለ ግዜ ቆይተሀል! ነገር ግን አንተ የተበላኸውኮ አሁን አይደለም!"ሲለው ጥቁሩ በሬ ቀበል ብሎ"እና መቸ ነው የተበላሁት?"ሲለው፣ "አንተ የተበላኸውማ ነጩን በሬ አሳልፈህ የሰጠኸኝ እለት ነው!እርሱን እንድበላው ባትፈቅዱልኝ ኖሮ ሁላችሁም መኖር ትችሉ ነበር!ለማንኛውም አንተ የመጨረሻ ስለሆንክ እንዳታልቅብኝ ቀስ እያልኩኝ እና እየቆጠብኩኝ ነው የምበላህ"ካለው በሗላ አንድ ቀን ቀኝ ታፋውን፣በሌላ ቀን ግራ ታፋውን፣ከ
Show all...
ይወት ቀረ።" ይሄ ግጥም ራሄል ተስፋዋ ሙጥጥ ሲልናራሷን ልታጠፋ በወሰነችበት ቅፅበት የፃፈችዉ እንደሆነ ገመትኩ። "ምን ያህል እንደምወድሽ ብታዉቂ!" አልኩ በልቤ! ግን ህይወት የእዉነታ እንጂ የስሌት ጉዳይ አይደለችምና እዉነቱን ማስተናገዱ ይሻላል። ስለዚህ ነገር አልተነገረኝም ነበር። የሪቾን ግጥሞች በዚህ መልኩ ሳያቸዉ እንድደመም አስባ ይሆናል ሀዩ ያልነገረችኝ። የራሄል ቤተሰቦች ባዩት ነገር በጣም ተደምመዋል። ምን እነሱ ብቻ እኔ ራሱ የሌለ ተደንቄያለሁ። ሌላዉ በጣም የሚገርመዉ ራሄል ለእኔ የፃፈችዉ የስንብት ደብዳቤ በትልቁ ግድግዳዉ ላይ የተፃፈበት ልዩ የመመገቢያ ክፍል መኖሩ ነዉ። ስገምት ሴቶች ባላቸዉን ለመጋበዝ የሚመርጡት ሁነኛ ቦታ የሚሆን ይመስለኛል። ስታጣኝ እዉነቱን ትጋፈጣለህ አይነት ማስፈራሪያ ሲፈልጉ ማለት ነዉ። በሀዩ የአመራር ብቃት ተደመምኩ። በቀጣይ ደግሞ ሆቴሉ የአስጎብኚ ቡድን እንዲኖረዉ ለማድረግ አቅደዋል። ሀዩ ታቅዳለች እኔ እየሳቅኩ እፈርማለሁ። . ጉብኝቱን ጨርሰን ምግብ ልንበላ የምግብ አዳራሹ ዉስጥ ስንገባ ሰዒዶናኢማን ይዘዉኝ ያደረግከዉ ንግግር የፖለቲከኛ ይመስላል ብለዉ ፎገሩኝ። ሰኢዶናኢማን አንድ ወንድ ልጅ ወልደዋል። ሙሀባ ብለዉታል። የራሄል አባት በተሰራዉ ስራ የተሰማቸዉን ደስታ ገለፁልኝ። ወዲያዉ አንድ የራሄል ቤተሰብ የሆነ ልጅ መጥቶ አድናቆቱን ከገለፀልኝና በዚህ እድሜዬ እንደዚህ ለስኬት መብቃቴ እንደገረመዉ ነግሮኝ ጥያቄ አዘነበብኝ። እሱ ሀብቴ ብዙዉን የዉርስ መሆኑን አያዉቅም። ሲቀጥል ሆቴሉን በዚህ መልኩ የማስተዳድረዉ እኔ መስየዋለሁ። ሀዩ እንደሆነች አያዉቅም። "አንድ ቆንጆ ምክር እስኪ ምከረኝ!" አለኝ ከኔናከሀዩ ጋር እየተቀመጠ "በወንድናበሴት መካከል ተፈጥሯዊ መፈላለግ አለ። ስለዚህ ሴት ልጅ ሚስትህ እንጂ የልብ ጓደኛህ አትሁን!" አልኩት። ሀያት ሳቋን ለቀቀችዉ። እኔ ጓደኞቼ ሴቶች በመሆናቸዉ የገባሁበትን ጭንቅ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። ራሄል ጓደኝነት በቀደደዉ መንገድ ፍቅር ላይ ወድቃ ነዉ እስከሞት የደረሰችዉ። "አንተ ጓደኛህን አይደል እንዴ ያገባኸዉ?" አለኝ ወደ ሀያት እየጠቆመ "አዎ ግን የሞተችዉም ጓደኛዬ ናት።" አልኩትና ወደ ሀዩ እየጠቆምኩ "እሷም ብትሆን ደስታዬ የሆነችዉ ከተጋባን በኋላ ነዉ።" አልኩት። ልጁ ፈገግ ብሎ ልጃችንን እና ከኛ ቀጥሎ ያለዉ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡትን ቤተሰቦቻችንን እያየ ሳቀና "የናንተ ቤተሰብ በጣም ያስቀናል!" ብሎን እየሳቀ ከመቀመጫዉ ተነስቶ ወደ ቤተሰቦቻችን ጠረጴዛ ሄደ። የልጁ ድፍረት ገረመኝ። ራሄል በወንዱ ነገር ነዉ። ከእናቴ ጋር ማዉራት ጀመረ። ስቀን ዞር አልን። . ከሁለት ቀን በኋላ እኔ መኝታ ክፍል ዉስጥ ጋደም ብያለሁ። ሀዩ ራህማን ስታጫዉት ይሰማኛል። የምትለዉን ራህማ እንድትደግመዉ እያደረገች ትስቃለች። "ረበና" አለች ሀዩ "አፐና" ትላለች ራህማ! ሀዩ በሳቅ ፍርስ ትላለች "ማ ኸለቅተ ሀዛ" "ማተዛ" ትላለች ራህማ! አሁን እኔም በጣም መሳቅ ጀምሬያለሁ። ሀዩ በጣም እያዝናናት ነዉ መሰለኝ ቀጠለች። "ባጢለን ሱብሀነክ!" "ባክነን" አለች ራህሚ! በሷ ቤት ሀዩ ያለችዉን መድገሟ ነዉ። አንደበቷ ይጣፍጣል። ከምር ግን እንደ ልጅ ምንም የሚያስደስት ነገር የለም። ሀያት ራህማን ስታስብላት የነበረዉ የቁርዓን አንቀፅ ነዉ። "ረበና ማ ኸለቅተ ሀዛ ባጢለን ሱብሀነክ!" ነበር ያለችዉ። ትርጉሙ "ጌታችን ሆይ ይህን (ድንቅ አለም) እንዲሁ (ያለ ዓላማ) አልፈጠርከዉም ..." ማለት ነዉ። ፈጣሪ ምድርና ሰማይን እንዲህ ያስዋበዉ የስዕል ጥበቡን ለማሳየት አይሆንም። ስለዚህ በከንቱ ያልተፈጠረ ምድር ላይ ከንቱ መሆን አይገባም። ምድር በከንቱ አልተፈጠረችም። እኛም ለጨዋታ አልተፈጠርንም። ህይወታችን ቁምነገር ሊሆን ይገባል!! "የራሄል አምላክ እዉነት ተናገረ!" አልኩ አልጋዉ ላይ እንደተዘረርኩ። አልረሳት ነገር ከልቤ ታትማ ፤ የኔ አትሆን ነገር ከመቃብር ከትማ! ጌታዬን ራህማን እና ሀያትን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። የተከለከልናቸዉ ከሚመስሉን ነገሮች ይልቅ የተሰጡን ዋጋ አላቸዉ። . ተፈፀመ!! ️join join join 👇👇👇👇👇👇👇 https://telegram.me/Dsseryy https://telegram.me/Dsseryy https://telegram.me/Dsseryy Föŕ åñŷ Ĉömment 👇👇👇👇 @AlDossery
Show all...

መንታ መንገድ ክፍል አስራአምስት (ፉአድ ሙና) . . ሀዩዬ እንደሷ ቆንጆ ልጅ ወልዳልኝ ሆስፒታል ከተኛች በኋላ በሀኪሞቹ ፈቃድ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ወሰድናት። እናቷ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተዉ ጨርሰዉ ነበር። ገንፎ ለሀዩ ይሰራል መግፊ በሷ እያሳበበች ትበላለች። የኔናየመግፊ የሰሞኑ ትርርባችን በገንፎዉ ጉዳይ ላይ ነዉ። ፓምፐርስ ምናምን ከመግፊ ጋር ሆነን ገዝተናል። መግፊ ሆነ ብላ ሴሪፋም አስገዝታ መሳቂያ አደረገችኝ። ለካ እስከ ስድስት ወር ከጡት ሌላ ምንም አይነት ምግብ ለህፃናት አይሰጥም። ሀዩዬን ልጃችንን ስታጠባ አየኋት ፤ የሆነ ልብ የሚይዝ ነገር አለዉ። ልጇን ስትንከባከብ በጣም ደስ ትላለች። . በሰባተኛዉ ቀን ሁለት በግ አርደን ሰደቃ አወጣን። ሰደቃ ማለት ምፅዋት ማለት ነዉ። በሀይማኖታችን መሰረት ልጅ በተወለደ በሰባተኛዉ ቀን የሚደረገዉ ይህ የምፅዋት ዝግጅት አቂቃ ይባላል። በነገራችን ላይ ለልጃችን ስም ለማዉጣት በጣም ብዙ ክርክር ነበር የተፈጠረዉ። መጀመሪያ ራሄል እንድትባል ፈልጌ ነበር። ግን የሀዩም የኔም ቤተሰቦች በራስ ላይ ሀዘንን ማባባስ አያስፈልግም ብለዉ ተቆጡኝና ተዉኩት። እንደዉም የሀዩ እናት "ለሀያትም ስሜት አስብ እንጂ! ማትፈልጋት እንዳይመስላት!" ነበር ያሉኝ። ሀዩ ብዙ ነገር ስላደረገችልኝ ስሜቷን መጠበቅ ይኖርብኛል። ራሄልን ለመዘከር ሆቴሉ ይበቃል። ብዙ የስም ምርጫዎች ከቀረቡ በኋላ መጨረሻ ላይ "ራህማ" የሚለዉ የኔ ምርጫ ተቀባይነት አገኘ። እኔ ራህማ እንድትባል የፈለግኩት ከራሄል ሞት በኋላ የነበርኩበትን መጥፎ ሁኔታ ፣ አልጋ ላይ የነበረብኝን ያለመረጋጋት ችግር እና ጥፊዬን ችላ ለኖረችዉ ዉዷ ሚስቴ ሀያት ስጦታ እንዲሆን በማሰብ ነዉ። ነብዩ አዩብ(እዮብ) በሽታ ሲፈራረቅበት ፣ ሀብቱ ሁሉ ሲወድም እና ሌሎች ሚስቶቹ ትተዉት ሲሄዱ በፅናት ከጎኑ የቆየችዉ አንዷ ሚስቱ ራህማ ብቻ ነበረች። እናም የኔ ልጅ ከብዙ ችግር በኋላ የተገኘች ናትና የሚስቴን ትዕግስት ለመዘከር ራህማ አልኳት። ራህማ ማለት እዝነት ማለት ነዉ። . ሀጅራ ፣ እስክንድር እና የሪቾ ቤተሰቦች ፤ ቤት መጥተዉ ሀዩን አራስ ጠይቀዋታል። በነገራችን ላይ ሀጅራ ታጭታለች። በቅርቡ ማግባቷ አይቀርም። የአክስቴ ልጅ እና የዉዱ ጓደኛዬ ሰዒድ ሚስት ኢማን ሰሞኑን ከነሀያት ቤተሰቦች ቤት ጠፍታ አታዉቅም። ኢስራዕ እና መርየም ቤታቸዉ አድርገዉታል። ከመግፊራ ጋር ሆነዉ ሀዩን ያዳብሯታል። እናቴም ከአባቴ ሞት በኋላ ትንሽ ስርዓት ይዛለች። ከአክስቶቼም ጋር ታርቀዋል። ምግብ እየሰራች ለሀዩ ይዛላት ትመጣለች። ከምር ልጅ ግን የደስታ ምንጭ ነዉ። ስራ ዉዬ ማታ አይኗን እስከማይ እንዴት እንደምጓጓ! በርግጥ ለሀዩዬ ያለኝም ፍቅር በጣም ጨምሯል። . ጊዜዉ በሀዩ ፍቅርና በራህማ ጨዋታ ታጅቦ ነጎደ። ራህማዬ ሁለት አመት ሞላት። የራሄል ሆቴል ግንባታም ተጠናቀቀ። አጠቃላይ እቃዎቹን ሳይጨምር ለግንባታ ብቻ አስር ሚሊየን ብር አዉጥተናል። በርግጥ ቢዝነሱ አስተማማኝ ስለሆነ በአመት ዉስጥ ይመልሰዋል። በዛ ላይ ሀዩን የመሰለች የምርጥ ጭንቅላት ባለቤት ናት የምታስተዳድረዉ። የዉስጥ እቃዎቹን ከዉጭ ካስመጣንናእነሀያት ሰራተኞችን ከቀጠሩ በኋላ የሚመረቅበት ቀን ደረሰ። ሆቴሉ በአክሲዮን የተከፈተ ነዉ። የእኔ ቤተሰብ ፣ የሀያት ቤተሰብ ፣ የራሄል ቤተሰቦች ፣ እስክንድር ፣ ሰዒድ እና ሀጅራ ነን ባለድርሻዎቹ። ትልቁ ድርሻ ግን የኔ እና የሀዩ ቤተሰቦች ነዉ። የሆቴሉ የቦርድ ሰብሳቢ እኔ እንድሆን ተወስኗል። ሆቴሉን በስራ አስኪያጅነት ደግሞ ሀያት ትመራዋለች። ምክትል ስራ አስኪያጁ ልምድ ያለዉ ሰዉ ነዉ። ሀጅራ እና እስክንድርም ዉስጥ ላይ የሀላፊነት ቦታዎችን ይዘዉ ይመራሉ። ከምርቃቱ በፊት የማስታወቂያ ክፍላችን ሆቴላችን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እንዲተዋወቅ አደረገ። እነሀያት በስራዉ በጣም ተወጥረዋል። እኔ እንኳ የራሴን ስራ ስለምሰራ በሳምንት አንዴ ነዉ ሪፖርታቸዉን ለማዳመጥ የምሄደዉ። . ጠዋት ቢሮ ስገባ ፀሀፊዬ ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ ስላሉ እቃዎች ካወራችኝ በኋላ አንድ ደብዳቤ ሰጥታኝ ወጣች። ከራሄል ሆቴል ይላል። እነሀያት እንደላኩት ገመትኩ። ከፍቼ አነበብኩት። "የራሄል ሆቴል የምርቃት ስነ ስርዓት በቀጣዩ ሳምንት እንደሚደረግ ይታወቃል። በመሆኑም ሆቴሉ የራሄል መታሰቢያ እንደመሆኑ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ስለ ራሄል የሚዳስስ አጭር ፅሁፍ መቅረብ ይኖርበታል። ስለሆነም እንደ ሆቴሉ የቦርድ ሰብሳቢነትዎ በእለቱ ይህን ሀሳብ ባካተተ መልኩ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን። ከሰላምታ ጋር!" ይላል። ከስሩ የሀያት ፊርማ አለዉ። ረዥም ሰዓት ብቻዬን ሳቅኩ። ለምን ሳቅኩ? ሀዩ ለኔ ደብዳቤ መፃፏ ገርሞኝ! እሷ ስራ ላይ ቀልድ አታዉቅም። . የሆቴሉ ምርቃት ሲጠጋ ሀያት ስራ ስለበዛባት አንዳንዴ አስፈቅዳኝ እዛዉ ታድራለች። ራህማን ሁሌም ስራ ስትሄድ ይዛት ነዉ የምትሄደዉ። "አንተ እኔን እንጂ እሷን ማቀፍ አትችልበትም!" ትላለች ሀዩ። ለነገሩ ራህማ መራመድ እና ትንሽ ትንሽ መናገር ጀምራለች። ከብዙ ዉጥረት በኋላ የራሄል ሆቴል ምርቃት ደረሰ። የዛን ቀን ሀዩ ሆቴል ስለነበር ያደረችዉ ከኢስራዕናማማ ጋር ሄድኩ። መርየም ከባሏ ጋር ሄዳለች። የሆቴላችን በር ላይ ስደርስ ድባቡ ለየት ያለ ነዉ። መኪናዬን የሆቴሉ ፓርኪንግ ጋር አቁመን ወደ ዉስጥ ገባን። ሱፍ የለበሱ ወጣቶች ወዲያዉ እየተቀላጠፉ ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ይዘዉን ሄዱ። ብዙ ሰዉ አለ። አዳራሹ ጋር ስንደርስ ሀዩ በሩ ጋር ቆማ እንግዳ እየተቀበለች አገኘኋት። ሰላም ካለችን በኋላ ኮሌታዬን አስተካክላልኝ ወደ ተዘጋጀልን መቀመጫ ወሰደችን። እንግዳዉ ሁሉ ቦታ ቦታ ከያዘ በኋላ መድረክ መሪዉ ወደ መድረክ ወጥቶ የእለቱን ዝግጅቶች አስተዋወቀ። ከዚያም ሀያትን ወደ መድረክ ጠርቶ እኔን ንግግር እንዳደርግ እንድትጋብዘኝ አደረገ። እንግዲህ የቦርድ ሰብሳቢዉ በስራአስኪያጇ መጋበዙ ነዉ። ሀዩ ስታወራ አንቱ እያለችኝ ነበር። እኔ ሳቄን ለመቆጣጠር እየታገልኩ ነዉ። . መድረኩ ላይ ወጥቼ ንግግሬን ጀመርኩ። ሁሉም አፉን ከፍቶ ያዳምጣል። "ዛሬ በዋናነት በስራ አስፈፃሚዎቻችን ብርታት ሆቴላችንን ለመመረቅ በቅተናል። ግን መረሳት የሌለበት፤ ሆቴሉ ትናንት አብራን በአንድ ጎዳና ላይ ስትጓዝ የነበረችናብዙ ህልም የነበራት ጓደኛችን መታሰቢያ መሆኑ ነዉ። የራሄል ዉበት በሆቴላችን አይነግቡነት ይገለፃል። የሰላ ብዕሯን የማስታወቂያ ቡድናችን ተቋማችንን ያስተዋዉቅበታል። ለሰዉ የነበራትን ፍቅር ሰራተኞቻችን እርስ በእርስ ይዋደዱበታል። እሷን መልሰን ማግኘት ባንችልም ሆቴሉን ትልቅ ደረጃ በማድረስ ከፍ አድርገን እንዘክራታለን። ራሄል ሆቴል በይፋ ተከፍቷል!!" አልኩና ከመድረኩ ወረድኩ። ታዳሚዉ ያጨበጭባል። . የመንግስት ባለስልጣናት ዲስኩራቸዉን ካሰሙ በኋላ ታዳሚዉ ሆቴሉን እንዲጎበኘዉ ተደረገ። በየኮሪደሩ ላይ የራሄል ፎቶ በሚያምር ፍሬም ተሰቅሏል። አንድ ጥግ ላይ ደግሞ የራሄል የተመረጡ ግጥሞች በልዩ ዲዛይን ተሰርተዉ ግድግዳዉ ላይ ተሰቅለዋል። አይኔ አንዱ ግጥም ላይ አረፈ። መንታ መንገድ ይላል አርዕስቱ "መንታ መንገድ ፊት ቆሞ ፈራጁ፣ ምረጥ ተባለ ከመንገዶቹ፣ ግራዉን መንገድ እየወደደዉ ለሀይማኖት ሲል ቀኙን መረጠዉ። ቀኝ በጎ ነዉ ሲባል የሰማ፣ ነገዉን ብሎ ግራዉን ያማ፣ ሚስኪን አፍቃሪ ፍቅሩን ተቀማ። ግራዉ ፈራጁን ማግኘት ቢነፈግ፣ ፈገግታ ሰጡት ለቅሶ ሚሸሽግ። ሳቀ ሳቀና አንብቶ አንብቶ፣ ፈራጅን ሲያልም ዉሎ አምሽቶ፣ ተስፋ ሲቆርጥ ፣ ፈርሶ አደረ፣ ከተጠራበት ፣ ከህ
Show all...
የመጨረሻው ክፍል ይለቀቅAnonymous voting
  • 👍
  • 👎
0 votes
ቻናናሉ ተመቻሁAnonymous voting
  • 👎👍
  • ከከ
0 votes
Choose a bot from the list below:
Show all...
መንታ መንገድ ክፍል አስራአራት (ፉአድ ሙና) . . ራሴን ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ አላዉቅም ነበር። አይኔን ስገልጥ ነጭ አምፖል ሰማያዊ ኮርኒስ ላይ ይታየኛል። ወዲያዉ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ ሰዒድ እና ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉዬ እየተመለከቱኝ ነበር። ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉ ወዲያዉ ጌታዬን እንዳመሰግን አዘዘኝ። አመሰገንኩ። ወዲያዉ ወደ ጆሮዬ ተጠግቶ ለስግደት ጥሪ የሚደረገዉን አዛን እያደረገ የማጅራቴን ደምስሮች በጣቱ ነካካቸዉ። "ሴቶች በጣም ይወዱህ ነበር?" አለኝ ኡስታዙ ሰዒድ አጠገብ እየተቀመጠ "እንደዛ ነገር" አልኩት። "ያይኔአበባ የምትባል ሴት ታዉቃለህ?" አለኝ አይን አይኔን እያየ። "አዎ ዩኒቨርሲቲ ስማር የምጠቀምበት ምግብ ቤት አስተናጋጅ ናት።" አልኩት። ሰዒድ በግርምት አንገቱን ነቀነቀ። ኡስታዙ "እዛ ቤት በጣም ጣፍጦህ የበላህበት ቀን ትዝ ይልሀል?" አለኝ። እንደድንገት አንድ ቀን የበዓል ስጦታ ብላ ያይኔአበባ የሰጠችኝ ምግብ ትዝ አለኝ። እንደዉም ብቻዬን ዶርም ነበር የበላሁት። ኡስታዙ ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠይቆኝ ከመለስኩለት በኋላ ድግምቱ የተሰራብኝ በያይኔአበባ እንደሆነ ነገረኝ። ያይኔአበባ ወዳኝ እንደነበር ግን ልትፎካከራቸዉ በማትችላቸዉ ቆንጆ ሴቶች ተከብቤ የነበረ በመሆኑ ድግምት እንዳሰራችብኝ ራሴን በሳትኩበት ሰዓት ዉስጤ የነበረዉ ጋኔን መናገሩን አረዱኝ። ኡስታዙ አሁን በፈጣሪ ፈቃድ ድግምቱ መክሸፉንና ዉስጤ የነበረዉ መጥፎ ስሜትም እንደሚወገድ አበሰረኝ። በሀይማኖቴ መጠንከር እንደሚኖርብኝ መክሮ ከግብረስጋ ግንኙነት በፊት ላደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን መከረኝ። . በተፈጠረዉ ነገር እኔም ሰዒድም ተገርመናል። መኪና ዉስጥ እንደገባን ሰዒድ "በል እስኪ ዛሬ ሂድና ሞክራት እና ጉዱን እንየዉ!" አለኝ እየሳቀ። እዉነት ለመናገር በጣም ቅልል ብሎኛል። . ማታ ቤት ስገባ ሀዩ አኩርፋ መጅሊሱ ላይ ተቀምጣለች። ደሞ ምን ተፈጠረ? "ሀዩዬ ምን ተፈጠረ?" አልኳት ከጎኗ እየተንበረከክኩ። "አክረሜ ልዉለድልህ ፍቀድልኝ!" አለች እያለቀሰች። የአልጋ ላይ ፀባዬ እስኪስተካከል ላለመዉለድ ወስኜ መድሀኒት እንድትወስድ አዝዣት ነበር። አይ ሀዩ! ከነዚህ የአልጋ ላይ ፀባዬ ምንም ሳትጠላኝ ልትወልድልኝ መጓጓቷ የፈጣሪ ስጦታ እንደሆነች እንዳስብ አደረገኝ። ፈገግ አልኩና "አላህ ካለ ነገ ጠዋት መልሴን እነግርሻለሁ!" አልኳት ዛሬ ማታ ሊፈጠር የሚችለዉን ሰላማዊ ለሊት ተስፋ እያደረግኩኝ። . ማታዉን ኡስታዙ በነገረኝ መልኩ ግንኙነት ከመፈፀማችን በፊት ሰግጄ ፀሎት አደረስኩ። ከዛም የሀዩ ጭንቅላት ላይ መዳፌን አስቀምጬ ጌታዬን ለመንኩ። ዉስጤ በእርጋታ ተሞልቷል። ሀዩን ሳምኳት ፣ እጄ ጥፊ እንዳይቀድመዉ ፈርቼያለሁ። እየተሳሳምን በስሜት ጠፋን። እጆቼ ሰዉነቷ ላይ ተንሸራሸሩ። ልክ እንደሰዉ ተገናኘኋት። ሀዩ ፊቷ በእርካታ ተሞልቶ እየሳቀች "ጌታዬ እንደማያሳፍረኝ አዉቅ ነበር።" አለችኝ። የረዥም ጊዜ ፀሎቷ ይሄ ነበር መሰለኝ። ሁለታችንም መድገም ፈለግን! ሀይል አሰባስበን ደገምነዉ። እርካታ ጣራ ነካ! ማመን ከበደኝ። የምድርን ጣፋጩን ነገር በእርጋታ ማጣጣም ቻልኩኝ። ሀዩ እቅፌ ዉስጥ ቀለጠች። ፍልቅልቅ እያለች "አፈቅርሀለሁ።" አለችኝ። ጌታዬን አመስግኜ ሀዩን እቅፍ አድርጌ ተኛሁ። . በነጋታዉ ጠዋት ሀዩ ከእንቅልፍ እንደተነሳን የወሰደችዉ የመጀመሪያዉ እርምጃ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን መጣል ነበር። አሁን ልጅ ያስፈልገናል። ጠዋቱን ሰዒዶ ደወለና "እ ጄኪጃን አደብ ገዝተህ አደርክ ወይስ?" አለኝ። "ኧረ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ጥፍጥናን አጣጣምኩት። አሁን ከልቤ እንድትቀምሰዉ ተመኝቼልሀለሁ።" አልኩት። ተገናኝተን ስለጋብቻዉ ለማዉራት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋዉ። ሀዩን በሙሉ አይኔ ለማየት ደፈርኩ። ግንኙነት የፈፀምን ለሊት ያዉ ስለምመታት ጠዋቱን ቀና ብዬ ላያት በጣም ነበር የምሸማቀቀዉ። ጠዋት ቁርስ እኔ ካልሰራሁ ብላትም ከለከለችኝ። ሁኔታዬ ሁሉ እያሳቃት ነዉ። ወንድነቴ ልኩን መያዙ ከሀዩ ጋር የተሻለ ቅርርብ እንዲኖረኝ አደረገኝ። . ጠዋቱን ሀዩን ወደ ቢሮዋ አድርሼያት እኔ ወደ ስራ ሄድኩ። የራሄል ሆቴልን ጉዳይ በተመለከተ በዋናነት እየመራችዉ ያለችዉ ሀዩ ናት። አሁን ግንባታዉ ተጀምሯል። ሀጅራም አዲስአበባ ሆና ስራዉ እንዲቀላጠፍ ለማድረግ እየጣሩ ነዉ። እስክንድር አዲስ ፍቅረኛ ይዟል። እስክንድርን ካየሁ ሁሌም ራሄል ትዝ ትለኛለች። አሁን እንኳ ሀዘኔ በጣም ደብዝዟል። ግን በጣም የገረመኝ የተሰራብኝ ድግምት ከዝሙት እኔን ለመታደግ ምክንያት መሆኑ ነዉ። ከራሄል ጋር ያደርን ለሊት ስሜቴ ሲግል በጥፊ መታኋት እና አልጋ ላይ ተዘረረች። እዛዉ እንዳለች ልገናኛት ወደ አልጋዉ ስሄድ እንደዉም አብሬያት መተኛት ያልፈለግኩ መስሏት ተፈናጥራ ተነሳች። ለመጥፎ የተደረገብኝ ለጥሩ ጠቀመኝ። ምንም የስድስት ወሩ የስቃይ ጊዜ ባይረሳም ማለት ነዉ። ለሀዩ ትዕግስት ግን ምድር ላይ የሚመጥነዉ ሽልማት አላገኘሁም። . ጊዜዉ ሄዶ የሰዒዶ እና የኢማን ኒካህ ደረሰ። ደስ በሚል ስነ ስርዓት የኒካህ ስነ ስርአቱ ተደረገና ከሁለት ቀን በኋላ ሰርጉ ተደገሰ። ሚዜ ነበርኩኝ። በጣም ደስ የሚል ነበር። የሰርጉ ቀን ማታዉን ሆቴል እንዳደረስናቸዉ ፈገግ ብዬ "በል ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም!" አልኩት። ሰዒዴ ንግግሬን ጠምዝዞ "ኧረ እኛ ተዋጊ አንፈልግም!" አለኝ እየሳቀ። በጥፊ የሚማታ አንፈልግም ማለቱ እንደሆነ እኔናእሱ ተግባብተናል። . ጊዜዉ ሄዶ የሀዩ ሆድም ገፋ! እየደከማት ስትቸገር የሷን ስራ ከነሀጅራ ጋር እየተደጋገፍን ለመሸፈን ሞክረን እሷ ቤት እንድታርፍ አደረግን። ሀዩዬ ስታረግዝ አንዳንድ የፀባይ መቀያየሮች ቢስተዋሉባትም እንደምንም ታግሼ ተንከባከብኳት። አንዳንዴ ለአይኗ ሁሉ አስጠላታለሁ። አንዳንዴ ድብርት በጣም ይጫጫናታል። የእርግዝናዉ ፀባይ እንደሆነ ስለገባኝ ምንም ሳልበሳጭ የምትፈልገዉን ሁሉ ለማቅረብ ሞከርኩ። . ሀዩ ዘጠነኛ ወሯን ከያዘች በኋላ ብዙም ከሀዩ ቤተሰቦች ቤት አልጠፋም ነበር። ቢሮ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን አስተካክዬ ወደሀዩ ወላጆች ቤት እመለሳለሁ። ከሀዩ ጋር ግንኙነት መፈፀም ካቆምን ሁለት ወር ሆነን። የእዉነት አግኝቶ ማጣት ከባድ ነዉ። ወንድነቴ ሀዩን አምጣ ብሎ ሊገለኝ ምንም አልቀረዉም። ገና ወልዳ ደሞ የወሊድ ደም እስከሚቆም ግንኙነት እንደማንፈፅም ሳስበዉ ሰቀጠጠኝ። የሀዩ ገላ ናፍቆኛል። የሀዩ ፅንስ በጣም ስለገፋ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ሄዳ እናቷ በጣም እየተንከባከቧት ነዉ። ጁምዓ(አርብ) ጠዋት ላይ መግፊራ ደወለችልኝ። "እሺ እጩ አክስት!" አልኩ ስልኩን አንስቼ "እጩ አባት! ሚስትዎ እያማጠች ነዉ። ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እየሄድን ስለሆነ ቢመጡ!" አለችኝ። መግፊ ቀልዷናምሯ አይለይም። "መግፊ እስኪ ወላሂ በይ!" አልኳት። ወዲያዉ ስልኩን ወደ ሀዩ አስጠግታ ስታምጥ አሰማችኝ። መኪና እንደዚህ በፍጥነት መንዳት እችል ነበር እንዴ? በሀያ ደቂቃ ዉስጥ ሆስፒታል ደረስኩ። መግፊራ ጋር ደዉዬ ወጥታ ይዛኝ ገባች። ሀዩ የማዋለጃ ክፍል ዉስጥ ናት። መግባት እንደማልችል ተነግሮኝ በር ላይ ከነመግፊር ጋር ተቀመጥኩ። ደስ የሚለዉ አዋላጆቹ ሴቶች ናቸዉ። ወንድ የሚስትህን ብልት እየነካካ ሲያዋልዳት በጣም ይቀፋል። በተቻለዉ መጠን ሴቶች ስራዉን በፍጥነት ሊቆጣጠሩት ይገባል። የሀዩ የስቃይ ድምፅ አልፎአልፎ ይሰማኛል። ሀዩ ስትሰቃይ እኔን አመመኝ። ለሰዒዶ መንገድ ላይ እያለሁ ደዉዬ ነግሬዉ ስለነበር ደርሶ ከኛ ጋር ተቀምጧል። የሀዩ እያንዳንዷ ጩኸት በጣም አ
Show all...
መመኝ። ከአይኔ እንባ ፈሰሰ። "ኧረ በፀጋ አይለቀስም! አላህን ፍራ!" አሉኝ የሀዩ እናት። ሰዒዶ ከክፍሉ ራቅ ብሎ ወዳለ መቀመጫ ወሰደኝ። ሰዒድ እያየኝ ይስቃል። "ልጅም አባትም አልቅሳችሁ እንዴት ይሆናል!" አለኝ እየሳቀ! ንግግሩ እያሳቀኝ "እሱን ኢማን ስትወልድልህ ትቀምሰዋለህ!" አልኩት። ወዲያዉ የማዋለጃዉ ክፍል በር ሲከፈት አየን። ከተቀመጥንበት ተነሳን። ከክፍሉ አንድ ዉሀ ሰማያዊ የህክምና ልብስ የለበሰች ሴት ወጥታ እነመግፊራን ማናገር ጀመረች። ወደ ክፍሉ በፍጥነት እየተራመድን ተጠጋን። የህፃን ልጅ ለቅሶ ይሰማል። የነመግፊራ ፊት ላይ ደስታ ይነበባል። ወዲያዉ መሬት ላይ በግንባሬ ተደፍቼ ጌታዬን አመሰገንኩ። እነመግፊን ተከትዬ ወደ ማዋለጃ ክፍሉ ገባሁ። ሀዩዬ ፊቷ በላብ ተጠምቆ ተጋድማለች። ስታየኝ ፈገግ አለች። ተንደርድሬ ሄጄ አልጋዉ አጠገብ ተንበርክኬ እጇን ያዝኩት። ጠጋ ብዬ ግንባሯን ሳምኳት። "ደሞ አሁን ቆንጆ የሴት ስም እንፈልግ!" አለች መግፊራ! ልጄ ሴት ነበረች። ደስ አለኝ። ደስታዬ ወደር የለዉም። በጣም ደስስስስ አለኝ። "ያንተንም ጉድ እናየዋለን ሰዒዶ!" አለች ሀዩ ወደ ሰዒድ እያየች። "እስኪ አላህ ያድርሰን!" አለ እየተሽኮረመመ። ወዲያዉ ሀኪሞቹ ግርግሩን እንድንቀንስ እና እንድንወጣ አዘዙን። እናቷ ብቻ ቀሩ። እኔና መግፊራ ለጊዜዉ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመግዛት ሄድን። . ይቀጥላል... adoseryy
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.