cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Lucy Schools Sha grade12

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
842
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እግዚአብሔር ይስጥልኝ !!! አብዝቶም ይባርክልኝ !!! በሉሲ ት/ቤት ላይ ሰኔ 23/2012 አደጋ እንደደረሰ የተቋማችን ሠራተኞች በሦስት ወገን ተከፈሉ ። 1ኛ . ግማሽ (50%)የሆኑቱ እጅግ አዝነው በተሰበረ ልብ በፅናት ከድርጅቱ ጎን ቆሙ ። 2ኛ . 30% የሆኑቱ በጥቂት ተንኮለኞች ተታለው ወደ ክስ ቢሄዱም ወዲያው እውነታውን በመረዳት አብረውን ቆሙ ። 3ኛ . 20% የሆኑቱ ( 64 ሰዎች ) የቃጠሎው አመድ ሳይነሳ የግቢዎቹ አጥር እንደተበታተነ እያዩ የሰኔን ወር ደመወዝ ተቀብለው ወዲያው ሊከሱን ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ ። መልሰን እንዳንቋቋም የፈለጉ ይመስል በየሚዲያው እና በየአደባባዩ አሠጡን ። ወደ ሥራ እንዲመለሱ ቢጠሩም እምቢ ብለው በተለያዩ ት/ቤቶች በመቀጠር የግል ገቢያቸውን እያጧጧፉ ክሳቸውን ቀጠሉ ። አሁን ድረስ በ 5 ሚሊዮን ብር የካሳ ጥያቄ ክስ በየፍርድ ቤቱ እያመላለሱን ይገኛሉ ። "" በዘመናችን ተወዳዳሪ የሌለው ግፍ "" ....ለታሪክ ይቀመጥ ... እንግዲህ አሁን ላይ እጅግ አድርጌ የማመሰግናቸው 80% የሚሆኑቱ ያን ሁሉ ጫና ተቋቁመው ከእኛ ጋር ከመዝለቃቸውም በላይ ከሚከፈላቸው መጠነኛ ደመወዝ ላይ ቀንሰው ለድርጅታችን መልሶ መቋቋም የ 45,000 ብር ድጋፍ ያደረጉልንን ነው ። ከታች በደብዳቤያቸው ያሳወቁኝን ነው ። እናንተም ሁላችሁ አመስግኑልኝ ። እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው !!! አሜን !!!
Show all...
የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከጥር 27 እሰከ 30 ድረስ በOnline እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ። ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል። ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል። 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል። በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ። @FDRE_MOE @FDRE_MOE
Show all...
ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚውሉ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጿል።ሚኒስቴሩ ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ እንደሆኑ ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ 450 ሺህ ታብሌቶች ደግሞ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል። @FDRE_MOE @FDRE_MOE
Show all...
በጣም አስቸኳይ በመሆኑ ከላይ የተለጠፈውን ማስታወቂያ ተመልቱት ። ፎርም ላልሞሉት አሳውቋቸው ።
Show all...