cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

GRACE FAMILY

CHRISTIAN EVANGELICAL MOVEMENT #YOUTH_4_CHRIST በዚህ ቻናል #Christian_radio_program #sermons #praise_hour To any comment @its_written

Show more
Advertising posts
366
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከሀጥያተኞች ዋና በምሆን በኔ ላይ ምህረቱ በዝቶ በዝቶ በእኔ ሊያሳይ! ባለማመን ባደረኩት፤ ባለማወቅ ያሳደድኩት ያሳይ ዘንድ ትዕግስቱን፤ አበዛልኝ ምህረቱን! በደማስቆ ላይ ተንበርክኬ፤ በፍቅሩ ተማርኬ እንዳላሳደድኩ ተከተልኩት፤ ከአዕላፋት መረጥኩት ከማህፀን የለየኝ የርሱ እንድሆን የጠራኝ ልጁን በእኔ እንዲገልፀው መማከሬ አይደል ከሰው ሀጥያተኞችን ሊያድን መጣ ከሲዖል ሊያወጣ ከቁጣ ፍርድ ሊያወጣ ከእነርሱም መሀል ዋና የሆንኩ ይኸው ዳግም ተወለድኩ በኢየሱስም አመንኩ ለአዋጅ ቃል ተናጋሪ፤ የምስራቹን መስካሪ ምርኮኛ ነኝ የይቅርታው፤ ኑ ስሙልኝ ስለውለታው ያሳደደውን ማን ይምራል ማን ጠላቱን ይወዳል? ማን እስከሞት ያፈቅራል? የማልጠቅመውን ምርጥ ዕቃ አለኝ፤ ሰይፌን ከእጄ አስጥሎ ምህረቱን አስታቀፈኝ ሾመኝ ሾመኝ ታማኝ አርጎ ቆጥሮኝ ሾመኝ ሾመኝ ኢየሱስ ወደደኝ
Show all...
ኑዛዜ ፩፫ ወደአድራሻህ ላለመቅረብ ሰበብ የሚያበዛ ሰው መች እግሩን ይጠብቃል? እዚም እዛም የረገጠ እግር በንስሀ እንባ ሳይኘፃ እየተንፏቀቀ እፊትህ ሲያደርሰኝ ከሰነፍ መስዋዕት ውጪ ምን ላቀርብልህ እችላለሁ? እውነታውን ስናዘዝ በነዚያ ወቅቶች የቀረብኩህ ራሱ ልሰማህ ሳይሆን የማያባራውን ብሶቴን ሰምተህ መፍትሄ እንድትሰጠኝ ነው፡፡ ራሴን ከእኔው ክፋት ፤ አረማመዴን ከወደቀችው አለም ፈተና ሳልጠብቅ.. ቅዱሳን መላዕክት ፊታቸውን ሳይሸፍኑ የማይቀርቡትን ሀልዎት በስልቹ ሽምደዳ ፀሎት ዘው ብዬ መግባቴን ስንቴ ከፅድቅ ቆጥሬው ይሆን? ቃልህ እንደሚል የስንፍናን መስዋዕት አቅራቢ በፊትህ ክፉን እንደሚሰራ አያውቅምና ተላላ ነው፡፡ የራሱን ትከሻ እየመታ በደሉን እያበረታታ መኖሩን ማን ደፍሮ ይነግረዋል (ከቃልህ ውጪ..) ይልቅ ስንፍናዬን ሰይፍ በሆነው ቃልህ ገስፅልኝና አንተን ለመስማት ልቅረብህ! አንተ እኮ የህይወት ቃል አለህ! ከሰማሁህም በኀላ ምላሽ ስሰጥ ስሜታዊነት በችኮላ ያንደረደረው ድንፋታዬ አሸማቆኛል! መልካምነትህን ስሰማ እኔም ልመስልህ ወድጄ ስንቱን ሸጋ ነገር አደርጋለሁ ለማለት ልቤ እንደሚቸኩል ታውቃለህ.. አንደበቴም ያልተብላላን ምኞት ሲተፋ አይሰክንም ለመደመጥ ይፈጥናል እንጂ፡፡ ድፍረቱን ከየት አመጣሁት ቆይ? አንተ በሰማይ ምትኖር አምላክ እኔ ደግሞ በምድር ያለው ፍጡር ነኝ.. ምናልባት "ሩቅ" ስለሆንኩ ቃልአባይነቴ consequence የለውም ብዬ ይሆናል.. ተላላነቴን ይቅር በል፡፡ ለሰው እንኳን ቃል ገብቶ መካድ ያስጠይቅ የለ? አንተ ደግሞ በሰማይ ነህ..ገና ሽለላዬን ስደነፋ የልቤን ቆራጥነት ፣ የውሳኔዬን intention፣ የችኮላዬን ምክኒያት እንዳትረዳ የፉከራዬ ድምፅ መች ይከልልሀል? ታውቀኝ የለ? እራሴን ከምረዳው በላይ የምታነበኝ በሰማይ ከፍ ብለህ አለህ፡፡ ስለዚህ ቃሌን ጥቂት አድርግልኝና ውርደቴን ማርልኝ፡፡ በምድር እንደሚኖር ሰው መማልን አስተምረኝ.. ህልምን የሚገልጠው ስራ ነው.. የኔ ስራ የሚያሳብቀው ደሞ ህልሜ ነው ብዬ የምፎክረው ቅዱስ ህይወት አይደለምና ብዙ ልፈፋዬ "የሞኝ ንግግር" ብቻ ሆኗል፡፡ ሁለት ነገር ልለምንህ.. የተሳልኩትን ስዕለት ለመፈፀም ስንፍና እንዳያዘገየኝ እርዳኝ.. የማልፈፅመውን ነገር አደርጋለሁ ብሎ ከመሳል ጠብቀኝ፡፡ በእርጥም አንተን ለመዋሸት ከመሞከር ቃል አለመግባት ብልህነት ነው፡፡ የልብን ስለምታይ አንደበት ልብ ያላመነበትንና እሰራለው ብሎ ያላቀደበትን ነገር በችኮላ እንዳይለፍፍ ልጓም አበጅለት፡፡ አንደበቴ ወደ ሀጥያት ለመራኝ እልፍ ጊዜያት ሁሉ የሚያኖረኝ ምህረትህ ይግነንልኝ ፤ ከቁጣህም አድነኝ፡፡ በእርግጥም ብዙ ህልምና ብዙ ቃል ከንቱ ነው! አቤቱ ሰው ብቻ መሆኔን ተረድቼ እንደአምላክነትህ አንተን መፍራት አስተምረኝ፡፡ ድኩም ምስኪን ነኝና ጆሮዬን አንተን ለመስማት የፈጠነ ፣ ምላሴን ስዕለት ለመሳል የዘገየ ፣ ቃሎቼንም ጥቂት አድርግልኝ፡፡ ከትህትናህና ፍቅርህ የተነሳ እንዳትቀልብኝ እግዚአብሄር በሰማይ፥ እኔ ደግሞ በምድር እንደሆንኩ ዘወትር እንዳልረሳ.. ወደ አንተ ስመጣም ደግሞ "ባልተጠበቀ እግር" እንዳይሆን ፈሪሀ እግዚአብሄርን አስተምረኝ፡፡ እንኳን አንተን ራሴንም መዋሸት አልቻልኩምና የምህረትህን ኪዳን ተደግፌ ድካሜን እናዘዛለው ፤ ሀጥያቴን ይቅር በለኝና ልረፍ፡፡
Show all...
ኑዛዜ አቤቱ ጌታዬ ሆይ በጣም ደከምኩኝ ከኅጢአት ጋር ግብግብ አዛለኝ እምነቴም ሲፈተን ተሰማኝ ውስጤ ሰላም በማጣቱ ተንኮታኩቻለው ድሮ የነበረኝ ግለት አሁን ላይ የት እንደገባ ግራ ገብቶኛል ዳዊት እንደፀለየው "የማዳንህን ደስታ መልስልኝ" ብዬ እኔም እቃትታለው ያኑን ግለት በራሴ ልመልሰው እንዲሁ እጣጣራለው ግን ጌታ ሆይ ፈፅሞ አልቻልኩም አው ጌታዬ ሆይ በራሴ እንደማልችል በደምብ ተረድቼአለው ደሞስ ክርስትናስ እኔ አልችልም ማለት አይደለምን? ምርኩዜ ሆይ ለመቆም ዝያለውና እባክህን በምህረትህ ድገፈኝ ወናነት ሲሰማኝ በሀልወትህ ሙላኝ ባዶነቴን ምትሞላልኝ ብቸኛ መድህኔ አንተ ነህና ዝም አትበለኝ ደሬ እንደዘመረው አክሊሌን በደምህ እንድሽሸገው እርዳኝ የቆሰለው ልቤን በቁስልህ አክምልኝ የተዋረደን ልብ ስጠኝ ጉልበቶቼን ከዙፋንህ ደጆች ጋር አጣብቅልኝ ሌላ ሌላ እንዳላይ ለአይኖቼ ልጓም አበጅላቸው ትምክህቴ ሆይ እመካብሀለው ፈፅሞ እንደማትጥለኝ አስረግጬ አውቃለው ግን ዝም ያልከኝ ሲመስለኝ ልቤ ይጨነቃልና በማስተዋል እንድመላለስ በእርጋታ መቀመጥ እንድችል አቤቱ ጌታዬ እርዳኝ
Show all...
ክረምቱ መጥቶ ወደ ሰማይ ሽቅብ አንጋጥቼ ስመለከት የጠቆረው ዳመና ልቤን ያስታውሰኛል ጭጋጉንም ሳይ ኅጢአት ያጠለሸው ልቤ ፊቴ ላይ ድቅን ይላል ከዛ ደግሞ እርጥበቱ ሞልቶ የዝናብ ነጠብጣቦች ሲወርዱ በንስሀ ልብ ያፈሰስኳቸውው እንባዎቼ ትዝ ይሉኛል ለጥቆም ዝናቡ ሲያበቃ የጠቆረው ዳመና ቀለል ብሎ ሳየው ከንስሀ በኃላ የሚሰማኝን እረፍት ያስታውሰኛል ከሰዓታት በኋላ ግን መልሶ ሰማዩም ይጠቁራል የእኔ ልብም እንዲሁ። በዚህ የማያልቅ ዑደት ውስጥ ኅጢአቴ ደጋግሞ በብርድ አንዘፈዘፈኝ ግን የሚያሞቀኝ አንድ ፅኑ ተስፋ አለኝ በዚህ ውጥንቅጥቅ ውስጥ እንኳን አቅንቶ የሚያቆመኝ። "እሄዳለው ወደዛች ሀገር ወደ በጉ ከተማ" የሚል ፅኑ ተስፋ ብርድም ሙቀትም ወደ ሌለበት ክርስቶስ ብቻ ወደሚያበራበት ሀገር በእሱ ወደሚደምቀበት ደመና እና ጭጋግ ክረምት እና በጋ ቀን እና ማታ ፍፁም ወደ ሌለበት ወደ በጉ ከተማ ልሄድ እጅግ ናፍቄአለው በቃ የኅጢአት ደመና ልቤ ላይ አይደምንም እንዴት ደስ ይላል! Macarthur አንዴ እንዲህ ብሎ ነበር "መንግስተ ሰማይን ሳስብ የሚያጓጓኝ በወርቅ የተለበጡት በእንቁ የተዋቡት መንገዶች ሳይሆኑ የኅጢአት አለመኖር ነው" የእኔም ጉጉት ይሄ ነው ኢየሱስ ቶሎ ና
Show all...
ጌታ ለአገልግሎት ሲጠራኝ ጭንቅ የሆነብኝ ምንም አልነበረም የእናቴ ነገር እንጂ። በጣም ነበር የሷ ጉዳይ የከበደኝ... በመጨረሻም እንዲህ አልኩት "ታስታውሳለህ ያኔ መስቀል ላይ ሳለህ የእናትህ ጉዳይ ግድ ብሎህ ለዮሐንስ አደራ ስትሰጠው? አሁን አንተ መስቀል ላይ አይደለህም። እኔ ለማገልገል እወጣለሁ። እባክህ የእናቴን ነገር አደራ።" ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን (paraphrased)
Show all...
Imagine how its gonna be so beautiful ቸርቾቻችን ውስጥ ስብሀት ለአምላክ ብንዘምር ኖሮ?
Show all...
"መርሳት እና ማስታወስ" . . . 'ጠቅላይ ሚኒስትሩ' ሲባል ምን ትዝ ይለናል? ንግግራቸው? ፈገግታቸው? አመራራቸው? ሰላምታቸው? ወይስ ምናቸው? የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዳ ሞዲ ትዝ አይሏችሁም መቼስ። አትሌት ኃይሌ ገ/ ስላሴ ሲባልስ ምን ትዝ ይለናል ሩጫው? ዝናው? ሃብቱ? ሆቴሉ? ሜዳሊያው? ሳቁ? ንግግሩ? ወይስ "ዌል እንግዲህ?" ሁ ? እንዲህ የሚባል ኢትዮጵያዊ አትሌት አላወቅም የሚለኝ ይኖራል ? ስለ ሁለቱም የምናወቀው የተወሰነ ነገር በመኖሩ ... ፈጥኖ ወደ ጭንቅላታችን የሚመጣ ማንነት አላቸው በትክክል ይግለፃቸውም አይግለፃቸውም። እግዚአብሔር ሲባል ምን ትዝ ይለናል? ሰማይ? ምድር? ጨረቃ? ፀሐይ? ሰው?ቤተክርስቲያን ? በምኑ ይሆን የምናስታውሰው? የሆነ ጊዜ እንዲህ አለ ... "ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ ስለዚህ … ረሱኝ" እነዛ ረሺዎች " እግዚአብሔር" ሲባሉ ምን? ማን? የቱ? ብለው ሌላ ከስሙ ሌላ ማስታወሻ ምልክትን ይሻሉ ፡፡ ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ "ቆንጆ ጌጧን ሙሽራ ልብሷን (ቬሎዋን አለ አንዱ ሰባኪ በደንብ ሲያስረዳ) ትረሳለች? ህዝቤ ግን ለማይቆጠሩ ወራት ረሳኝ"አለ የጥር ማለቂያ ላይ ስለ ቬሎ ብናወራ ሩቅ አይሆንብንም ቬሎ ምንድነው ? ማነው ያመጣው ? ሴት ሙሽራ ሁሉ ቬሎ ትልበስ ያለው ማነው? ለመቆም አይመች ለመቀመጥ ... ለመነካት ተፈርተሽ ለመታቀፍ እርቀሽ ... ብቻ መቼም ይምጣ ሙሽራን ያለ ቬሎ ማሰብ ይከብዳል ወይም ሌላ የሙሽራ ልብስ እነዚህም "እግዚአብሔር" ሲባሉ "ማን ነበር?" ብለው ይጠይቃሉ "ያ እንኳ ከግብፅ ያወጣን አምላክ" ሲባሉም የሚያስታውሱት አይመስለኝም "ጥ ጥ ይቅርታ አላስታወስነውም" ይላሉ "መናን ያበላን" እ እ የሆድ ጉዳይ ላይ በጥቂቱ ሊያስታውሱት ይሞክራሉ መልሰው ይረሱታል፡፡ እርሱ ግን ስለ እነርሱ ሲጠየቅ "ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ይላል ደግሞም "ሴት ከማህፀኗ የወጣውን ትረሳለች እስከማታስታውሰውስ ትጨክናለች አዎ ትረሳ ይና እኔ ግ አልረሳሽም በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ" ነው መልሱ ። የጉዳዩ እጅግ አስገራሚነት እዚህ ላይ ነው ይህ ትንሹ ሰው በዚህች ሚጢጢ ጭንቅላቱ ያቅሙን ያህል ጉዳይ አጭቆ ለማስታወስ እየጣረ ... ፎርሙላ እየሸመደደ ፤ የታክሲ መልስ እየተቀበለ፤ ቁርስ ምሳ እራቱን ሳይረሳ ፤ ከረቫት ማሰሩን ሳይረሳ ፤ ኩል መቀባቷን ሳትረሳ … እግዚአብሄርን ያህል ታላቅ እና ትልቅ አምላክ ሲረሳ፡፡ እሱኮ... ዩኒቨርስን ለአፍታ ሳይዛባ እየተቆጣጠረ ፤ የምድርን እና የሰማይን ፍጥረታት ስርአት አስይዞ እያስወጣ እያስገባ ፤ ለፀሀይ ቀንን ፤ ለጨረቃ ከዋክብት ለሊትን መድቦ ፤ ምድርን መስርቶ ፤ መስፈሪያዋን ወስኖ ፤ ለባህር ማእበል ገደብን አበጅቶ ፤ ዝናብን እያዘነበ ከዋክብተትን እያሰረ ሲፈታ … ምኑ ቅጡ! በዚህ ሁሉ ስራ በዚህ ሁሉ ፋታ ማጣት ትንሹን ሰው ማሰቡ አለመርሳቱ፤ "ረሳኋችሁ" ቢል እኮ በቂ ምክንያት አለው፡፡ "ለፈረስ ጉልበቱን ስሰጥ ፤ አንገቱን ጋማ ሳለብስ" ሊል ይችላል "የሚያግዘኝ እንደሁ የለ ፅንስን በማህፀን ስገጣጥም" ረሳኋችኁ ቢል ያሳምናል፡፡ "እናንተ ደግሞ እነማን ናችሁ? መቼም በምድር ላይ ስንት እና ስንት ቢልዮን ህዝብ የሚጠጋ ህዝብ ነው የሚርመሰመሰው" ቢል እውነቱን ነው። ሰው ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሄር ግን አንድ ነው ፤ አልረሳንምና አላለም። እንደ ዳዊት እጠይቃለሁ "አቤቱ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው ትጎበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?" ለራሴም እጠይቃለሁ "ሰው ሆይ እግዚአብሔርን ትረሳ ዘንድ አንተ ማነህ?" ለአብረሃም እና ለዘሩ ለዘለአለም ምህረቱ ትዝ እያለው ቅዱሱን ኪዳን አሰበ። ቃሉን አሰበ። እውነቱን አሰበ፡፡ ካልካድን በስተቀር የእግዚአብሄርን አስታዋሽነት መፅሐፍ ቅዱስና ታሪክ ይነግሩናል፡፡ በአመፀኛ ትውልድ መካከል የተገኘው አንዱ ኖህ አምላኩን ሰምቶ በሰራው መርከብ ቤተሰቦቹን ካስመለጠ በኋላ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳንን ተቀበለ፡፡ ዳግመኛ በምድር ዘመን ሁሉ መዝራት እና ማጨድ ፤ ብርድና ሙቀት በጋ ክረምት፤ ቀን እና ለሊት እንዳያቋርጥ በልቡ ካሰበ በኋላ ለኖህ አለው፡፡ ቃል ኪዳኔን ከእናንት በኋላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋ አቆማለሁ አለ፡፡ አዎ አቁሟል፡፡ ዘርቶ የማያጭድ ገበሬ ማን አለ? ክረምትና በጋ ቀንና ለሊትስ መቼ ተቋርጠው ያውቃሉ? እርሱ እግዚአብሄር ቃሉን አይረሳምና። ከባርነት የወጡ እስራኤላውያን ... 'ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ' ማለቱን ዘንግተው ፤ የራሳቸውንም ቃል ረስተው ጥጃ ሊሰሩ ወርቆቻቸውን ከጆሯቸው ሲያወልቁ ግን ገና 40 ቀንና 40 ሌሊት ብቻ ነበር ያለፈው፡፡ "ህጉን እና ስርአቱን ባለመጠበቅ አምላክህ እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ" ቢባሉም አነርሱ ግነ ሊያስተውሱት ከቶ አልቻሉም። ከርሱ ይልቅ የግብፅ ዱባና ሽንኩርት ትዝ ይላቸውና ጣእሙም በአፋቸው መአዛው ባፍንጫቸው እየመጣ ምራቅ ያስውጣቸው ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ግን እነርሱን ከማጥፋ በፊት ለአባቶቻቸው የማለላውን ባሪያዎቹን አብርሃምንን እና ይስሃቅ ፣ እስራኤልን አስቦ ራራላቸው፡፡ ዳግመኛ ማደሪያውን በመካከላቸው አደረገ። ምክንያቱም ሳሩ ይደርቃል አበባውም ይግፋ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለአለም ፀንታ ትኖራለች፡፡ የ Solomon Abebe Gebremedhin "የዱባ ጥጋብ " መፅሐፍ ምርቃት ላይ የቀረበ ! ጽጌሬዳ ጎንፋ
Show all...
Show all...
'ክርስቲያን ነኝ ካሉ መኖር ነው' // ማዕረግ ታዬ // Meareg Taye - 2022

ማቴዎስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጣዕሙን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጪ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም። ¹⁴ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ ¹⁵ ሰዎችም መብራት አብርተው ከዕንቅብ ሥር አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ። ¹⁶ እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ። ዋና መዝሙር - አሸናፊ ጉልቲ!

Subscribe
Show all...