cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጤናማ ህይወት በእግዚአብሔር ቃል

እንግድህ፡... አንተ፥በክርስቶስ ፥ኢየሱስ፥ባለው ፥ፀጋ፥ በርታ። ብዙ ሰዎች፥ የመሰከሩለትን፤ ከእኔም ደግሞ፥የሰመሀውን፤ሌሎቹን፥ሊያስተምሩ፥ለሚችሉ፥ለታመኑ፥ሰዎች፥አደራ፥ስጥ። 2ጢሞቴዎስ 2፥1-2

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
202Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጤንነት በመንፈሳዊ እይታ በሚል ርዕስ በቅርቡ ይጠብቁን
Show all...
Show all...
የኧገንዳና ታርቤ ቃ/ሕ/ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች ሕብረት

የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን። ነህ 2:20

የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን። ነህ 2:20 https://t.me/agendatarbeyouths
Show all...
የኧገንዳና ታርቤ ቃ/ሕ/ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች ሕብረት

የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን። ነህ 2:20

የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ 🔸ክፍል-11 ተጨማሪ ጉድጓዶች በቀጣዩ ጉድጓድ የነበረውም አጥንት እንደ ሌሎቹ ይመስል ነበር። ወደ ጉድጓዱ ስንቀርብ የበለጠ የሞት ሽታ ይሸተኝ ነበር። እዚህ ለምን እንደመጣ ነፍሱ ጥያቄ ሆነብኝ። ከፍሙ መሀል ያለው ነፍስ ወደ ጌታ መናገር ሲጀምር ሴት መሆኗን አወቅኩ ከመፅሐፍ-ቅዱስ የተለያዩ ጥቅሶችን ትናገር ነበር። " ምን እያደረገች ነው?" ብዬ ጌታን ጠየኩት። ጌታም "ስሚ።" አለኝ። "...ኢየሱስ እውነት ነው። መንገድ ነው ህይወት ነው ካለሱ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አይቻልም። ኢየሱስ የአለም ብርሀን ነው። ወደ ኢየሱስ ኑ እርሱ ህይወት ይሰጣችዃል ትድናላችሁ።.." ይህንን ስትናገር በአካባቢው ያሉ ነፍሶች ይሰሟት ነበር። አንዳንዶቹ በቁጣ እየሰደቧትና እየረገሟት እንድታቆም ይነግሯታል። አንዳንዶቹ ነፍሶች ደግሞ ' ተስፋ አለን በእውነት?.." ብለው በተስፋ መቁረጥ ይጠይቋታል። ታላቅ ለቅሶ እና ምሬት በአካባቢው ይሰማል። ሴቲቷ ምን እያደረገች እንደሆነ አልገባኝም ነበር። " ለምን ይቺ ሴት ወንጌልን በሲዖል ትሰብካለች ስል አሰብኩ።ጌታም ሀሳቤን አውቆ እንዲህ አለኝ። " ልጄ ይህች ሴት በ30አመቷ ነበር የወንጌል ምስክር እንድትሆን እና የቃሌ አገልጋይ እንድትሆን የጠራዃት። የተለያዩ ሰዎችን ለተለያየ አገልግሎት እጠራለሁ ግን ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት መንፈሴን ካልፈለጉት ከነርሱ አወጣለሁ። አዎ። ጥሪዬን ለአመታት መልሳ ነበር። በኔም እውቀት አድጋ ነበር።ድምፄንም መስማትን ተለማምዳ ነበር።ብዙ መልካም ነገሮችንም አድርጋ ነበር። ቃሌን ዘወትር ታጠና ያለማቋረጥም ትፀልይ ነበር። ብዙ ፀሎቶቿ ተመልሰውላትም ነበር። ብዙ ሰዎችን የቅድስና መንገድን አስተማረች።በቤቷም ታማኝ ነበረች። አመታት አልፈው አንድ ቀን ባለቤቷ ከሌላ ሴት ጋር እንደማገጠ አወቀች።ባለቤቷ ወደርሷ መጥቶ ይቅርታ እንድታደርግለት ጠየቃት እርሷ ግን አልፈቀደችም። መራር ሴት ሆነች ትዳሯን ከመፍረስ ማዳን አልቻለችም ነበር። በእርግጥ ባሏ ትልቅ ሀጥያት ሰርቷል። ተሳስቷል። ግን ሴቲቱ ቃሌን ታውቅ ነበር። ይቅር ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለች። ይቅርታ ባለቤቷ ደጋግሞ ቢጠይቃትም ልታደርግለት አልቻለችም።ቁጣ በርሷ ስረሰ ሰደደ አብዝቶም አደገ። ጉዳይዋን ወደኔም ይዛ አልመጣችም ነበር። በየቀኑ በመራርነቷ እና በቁጣዋ ቀጠለችበት። እርሷም አለች "..እኔ እግዚአብሔርን ለማገልገል በዚህ እሯሯጣለሁ በዚ ደግሞ ባለቤቴ በኔ ለመወስለት ይሯሯጣል።እና አንተ ይሄ ልክ ነው ትላለህ?..."አለችኝ። እኔም "ልክ አይደለም። ግን ወደ አንቺ መጥቶ ይቅርታን ጠየቀሽ። እንደማይደግመውም ቃል ገባልሽ።ልጄ በራስሽ ላይ እያመጣሽ ያለውን ተመልከቺ።" አልኳት።እርሷም መልሳ " እኔ አይደለሁም እኔ ንፁህ ነኝ። እሱ ነው በሀጥያት የተሞላው" አለችኝ።ልትሰማኝ አልቻለችም። ጊዜ የበለጠ ሲሄድ መፀለይና መፅሐፍቅዱስን ማጥናቷን ተወች። በባሏ ብቻ ሳይሆን በአጠገቧ ባሉት ሰዎች ሁሉ ቁጡ ሆነችባቸው። ጥቅሶችን ትጠቅሳለች ግን ይቅር ማለት አልቻለችም። በጭራሽ አትሰማኝም ልቧም የበለጠ እየከፋ ሄደና ታላቅ ሀጥያት ወደርሷ ገባ።ፍቅር ተሞልቶ የነበረው ልቧ በጭካኔ ተሞላ። አንድ ቀንም ከቁጣዋ የተነሳ ባለቤቷን እና ውሸማውን ገደለቻቸው። ሰይጣን መላ ማንነቷን ተቆጣጥሮትም ራሷንም አጠፋች። በሲዖል ለዘልአለም የተተወችውን ነፍስ ከፍሙ መሀል ከስቃይዋ ጋር አየኋት።ለጌታ በአሳዛኝ ድምፅ ስትለምን ሰማኋት። "...አሁን ይቅር እለዋለሁ...አሁን እተወዋለሁ ጌታ እታዘዝሀለሁ ብቻ ከዚህ ቦታ ልውጣ .....አየኸኝ ጌታ ወንጌል እዚህ ስሰብክ አየኸኝ...ከአንድ ሰአት በዃላ ክፉ መናፍስት ወደዚህ ይመጣሉ። ስላንተ እዚ በማውራቴ ወደ ሌላ ክፍል ወስደው ለሰአታት ያሰቃዩኛል....እባክህ ጌታ ሆይ ልውጣ እባክህ...." ጉድጓዱ ውስጥ ካለችው ሴት ጋር አብሬ አለቀስኩ። ጌታ ልቤን የናንተንም ከመራርነት ይጠብቀው።" ጌታ ሆይ ጥላቻ በልቤ እንዳይገባ ጠብቀኝ.." አልኩት። እርሱም "..እንሂድ " ብሎኝ አልፈን ሄድን። ይቀጥላል በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ከሲዖል ማምለጫ ብቻ ሳይሆን ለዘልአለም በእግዚአብሔር ፍቅር መኖሪያ ብቸኛ መንገድ ነው።
Show all...
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ 🔸ክፍል-10 የሲዖል የቀኝ እግር ወደ ቤት ስመለስ ስራዬ ማልቀስ ብቻ ሆነ። በቀኑ ሰአት ደግሞ ያየሁትን የሲዖልን ሰቆቃ ማስታወስ ብቻ። በየዕለቶቼ የማገኛቸውን ሰዎች ለሁሉም ስለ ሲዖል እውነት መሆን እና ሲዖል ከሚያስቡት በላይ መሆኑን እነግራቸው ነበር። የሲዖል ስቃይ ከሚያስቡት በላይ እንደሆነም ጭምር.....ይሄንን እያነበባችሁ ያላችሁ እባካችሁ እለምናችኋለሁ ለሀጥያታችሁ በፈሰሰው በኢየሱስ ደም አምናችሁ ንስሀ ግቡ። ብቻውን የሚያድናችሁን ጌታ ጥሩት....እባካችሁ ልባችሁ እያወቀ ነገን አትጠብቁ ነገ ላይመጣ ይችላልና። ጊዜ ከምታስቡት በላይ ስለሚፈጥን ቶሎ ተንበርከኩና ንስሀ ግቡ....እርስበርስ መልካም ተደራረጉ። እባካችሁ ለጌታ ስትሉ ይቅር ተባባሉ። የተቀየማችሁት ሰው ካለ ይቅር በሉት...የቱም ቂም ሲዖል እንድትገቡ ሊያደርጋችሁ አይገባም።ጌታ ይቅር እንዳለን ይቅር በሉ። ጌታ ምንም ያህል አስቸጋሪ ልብ ቢኖረንም በደሙ አንፅቶ ይጠብቀናል። ወላጆች ልጆቻችሁን ልጆችም ቤተሰባችሁን ውደዱ...የቤተክርስቲያን ጌታ " በኔ በማመን ንስሀ ግቡና ዳኑ " ይላል። ምዕራፍ-4 | ተጨማሪ ጉድጓዶች በቀጣዩም ምሽት ጌታና እኔ ወደ ሲዖል የቀኝ እግር ተመልሰን ሄድን። ባለፈውም እንዳስተዋልኩት ዛሬም ጌታ በሲዖል ያሉትን ነፍሶች እስከ ዘልአለም እንደሚወድ ተረዳሁ። ለኔም ጥልቅ ፍቅሩ ተሰማኝ ጌታ አሁን በአለም ያላችሁ ሁላችሁንም ሰዎች ይወዳል። እንዲህ አለኝ "ልጄ ማንም እንዲጠፋ የኔም የአባቴም ፈቃድ አይደለም።ሰይጣን ብዙዎችን እያታለለ የራሱ ያደርጋል። ግን እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው። የፍቅር አምላክ ነው። በዚህ በሲዖል ያሉት ነፍሶች ሁሉ ወደርሱ መጥተው ንስሀ ቢገቡ ኖሮ ይቅር ይባሉ ነበር።..." ጌታ ይሄንን ሲናገር ፊቱ ላይ ሀዘን አይ ነበር። ስንሄድ ብዙ ጉድጓዶች ነበሩ ከሁሉም እጆቻቸውን እየዘረጉ ጌታን ይጣራሉ... በዚያ ያለው ሀዘን ፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ እና እሳቱ ሲሰማቸው እያዘንኩ አይ ነበር። ሀዘናቸውን ሳይ የማልቋቋመው ሰቀቀን ፈጠረብኝ...." ምናለ ሰምተው እዚህ ባልመጡ ኖሮ" ስል አሰብኩኝ። በሲዖል ያሉ ነፍሶች ሁሉም ስሜቶች እንዳሏቸውና በፊት የተነገራቸውን ነገር በሙሉ እንደሚያስታውሱ ተረዳሁ። ከዚህ ለመውጣት ለዘልአለም ባይቻልም ጌታን ሲያዩ ግን ተስፋ እያደረጉ ምህረትን ይለምኑ ነበር። ጥቂት ተጉዘን ከአንድ ጉድጓድ አጠገብ ቆምን። ይሄኛውም እንደበፊቶቹ ያለ ነበር። በውስጡ ዃላ ላይ ሴት መሆኗን ያወቅኳት ነፍስ ነበረች። ጌታ ከፍሙ እንዲያወጣት ለመነችው። ሴቲቷን በፍቅር አይኖች እያያት እንዲህ አላት። " በምድር ሳለሽ ወደኔ እንድትመጪ ስለምንሽ ነበር።ልብሽን በኔ እንድትቀይሪ ለመንኩሽ ግን አልሰማሽም። ብዙ ጊዜ ወደ አንቺ መጣሁ ጎበኘሁሽ ፍቅሬን ነገርኩሽ ወደኔ በመንፈሴ ሳብኩሽ..."እሺ ጌታ ሆይ" አልሽ። "በከንፈርሽ እሺ እከተልሀለሁ.... እወድሀለሁ"አልሽ ግን የልብሽ እውነት እርሱ አልነበረም። ልብሽ የት እንደነበር አውቃለሁ። መልዕክተኞቼን ወደ አንቺ ልኬ ንስሀ እንድትገቢና እንድትመለሺ ስነግርሽ ነበር።....ግን አትሰሚም ነበር። ሌሎችን እንድታገለግይ ላደርግ ነበር ለሌሎች እኔን እንዲያውቁ እንድትናገሪ ነበር ያሰብኩሽ።...አንቺ ግን ከኔ በላይ የአለምን ፈለግሽ። ስጠራሽ አትሰሚም ንስሀ ሳትገቢም በጣም ብዙ ቆየሽ።ሴትየዋም እንዲህ አለች። "ታሰሰታውሳለህ ጌታ ሆይ ሁሌ ቸርች እሄድ ነበር....ጥሩ ሰው ነበርኩ። የአንተው ቤተክርስቲያን አባል ነበርኩ። በህይወቴ ጥሪህ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍለኝም አውቅ ነበር። ዋጋም ከፍያለሁ...." አለች። "..አሁንም በውሸት እና በሀጥያት እንደተሞላሽ ነው። ጠራሁሽ ግን አትሰሚኝም ነበር። እውነት ነው የቤተክርስቲያን አባል ነበርሽ ግን ቤተክርስቲያን መሄድሽ ብቻ መንግስተ-ሰማያት እንድትገቢ አያደርግሽም። ሌሎች በቃሌ ላይ እንዲያምፁ አደረግሽ።....የጎዱሽንም ይቅር ማለት ፈፅሞ አትፈልጊም ነበር። ከክርስቲያኖች ጋር ስትሆኚ የምትወጂኝ እና የምታገለግይኝ ታስመስይ ነበር። ከነርሱ ስትለዪ ግን ትዋሺ፣ ትሰርቂና፣ታጭበረብሪ ነበር።ለክፉ መናፍስት እድልን ሰጠሽ እነርሱም መንታ ህይወትሽ ተመቻቸው አብረውሽም መኖር ጀመሩ።ነገር ግን ብቸኛው ጠባቡና ትክክለኛው መንገድ የቱ እንደነበር ታውቂ ነበር። አንቺ ግን ሁለት ምላስ ነበረሽ የኔ በሆኑ ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶችሽ ላይ በሀሜት ታወሪ ነበር። ደግሞም ራስሽን ከነርሱ በላይ ቅዱስ እንደሆንሽ እያሰብሽ ሰዎችን ከላይ ብቻ እያየሽ አማኝ መሆናቸውን ዘንግተሽ ፈረድሽባቸው። በአፍሽ እወድሃለሁ ብትይም ልብሽ ከኔ ሩቅ ነበር። የኔን መንገድ እያወቅሽ ልትቀልጂ ሞከርሽ ሁሉንም ግን እኔ አውቃለሁ። መንፈሴ የሚልሽን መስማት አልቻልሽም ነበር። ንስሀ ገብተሽ በትህትና አገልግለሺኝ ቢሆን እዚህም ባልመጣሽ ነበር።እኔንና ሰይጣንን እኩል ማገልገል አይቻልም....."አላት።ጌታ ወደኔ ዞሮ በመጨረሻው ዘመን ብዙዎች ከእምነት ፈቀቅ ይላሉ። በዚህም ለክፉ መናፍስት እየተጋለጡ ሀጥያትን ማገልገል ይጀምራሉ።ከነርሱ ተለዩና ውጡ መንገዳቸውንም አትከተሉ አብራችኋቸውም አትሂዱ። የለያችሁ ሁኑ። ከሴትየዋ ርቀን ስንሄድ መሳደብ ጀመረች በታላቅ ድምፅም እየጮኸች መራገም ጀመረች።....ከሷ ራቅን ሰውነቴን በጣም ሲደክመኝ ይታወቀኛል። ክፍል ፦11 ይቀጥላል ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!!!
Show all...
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ 🔸ክፍል-7 የሲዖል የቀኝ እግር ጌታ ይህን ካለኝ በኋላ ሀዘን ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር። በድጋሚ እንዲህ አለኝ። በሚመጡት ቀናት የበለጠ ሲዖልን ሳሳይሽ ያልኩሽን ነገር አስታውሺ በሰማይም በምድርም ሀይል የኔ ነው። ብቻሽን የተውኩሽ የሚመስልሽ ሰአቶች ይመጣሉ ግን አልተውሽም። በሲዖል ያሉ ነፍሶችን ስንጎበኝ የሚያዩንም የማያዩንም ጊዜ ይኖራል።የትም ብንሄድ ግን እኔን ለመከተል አትፍሪ።" አለኝ። አብረን መሄዳችንን ቀጠልን ለቀናት በውስጤ የሰቀቀን እንባዬን ማቆም አልቻልኩም በማየው ነገር ነፍሴ በጣም አዝና ነበር። ወደ ሲዖል የቀኝ እግር ክፍል ደረስን። ከፊታችን የተቃጠለና የደረቀ የመሰለ መንገድ ተዘርግቷል። በአካባቢው ካለው ቆሻሻ አየር በተጨማሪ የሚበሰብስ ስጋ ሽታ ይበልጥ ገኖ ነበር። አንዳንዴ ሽታውን መቆጣጠር ሲያቅተኝ ውስጤን ሲያቅለሸልሸኝ እና ሲያመኝ ይታወቀኛል። በዚህ ስፍራ ከሩቅ ከሚታዩት ፍም የተሞሉ ጉድጓዶች በቀር ብርሀን አልነበረም። ከጌታ የሚመነጨው ብርሀን አካባቢውን ማየት እንድችል አድርጎኛል። ከላያችን መናፍስት አየር ላይ እንደቆሙ ቀና ስል አየሁ። በተለያየ መጠንና ቅርፅ ነበሩ። ከመካከላቸው ተለቅ የሚለው ለሌሎቹ ትዕዛዝን ሲሰጣቸው ተመለከትኩና ምን እንደሚል ለመስማት ከጌታ ጋር ቆምኩ። ጌታም "..በዚህ ስፍራ ከምናያቸው ከነዚህ መናፍስት በተጨማሪ የማይታዩን እንደ የበሽታ መንፈስ የመሳሰሉም አሉ።.." አለኝ። "ሂዱ!" ብሎ ትልቁ መንፈስ ለሌሎቹ ተናገራቸው። "...ሂዱ! መጥፎ የተባሉትን ሁሉ በምድር ስሩ ቤተሰቦችን እየከፋፈላችሁ በትኗቸው! ደካማ ክርስቲያኖችን የበለጠ አታሏቸው! በቻላችሁት ሁሉ የምታገኙትን በሙሉ ወደ ተሳሳተው መንገድ ምሩ! ስትመለሱ ሽልማታችሁን ታገኛላችሁ! ግን አስታውሱ ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልባቸው አዳኝ አድርገው የተቀበሉ ሰዎችን ተጠንቀቋቸው በውስጣቸው እናንተን ማስወጣት የሚችል ሀይል አላቸው።..ሂዱ! ከእናንተ በፊት የሄዱም አሉ ሌሎችም እናንተን ይከተሏችኋል። እኛ የጨለማው ንጉስ የአየር ላይ አለቃ አገልጋዮች ነን! ..." መናፍስቱ ከሲዖል በፍጥነት እየበረሩ ሲወጡ የሲዖል የቀኝ እግር በር በፍጥነት ተከፍቶአሳልፎአቸው በፍጥነት ተመልሶ ተዘጋ። የተቀሩት መናፍስት እኔና ጌታ በመጣንበት ዋሻ የሚመስል መንገድ ወጥተው ሄዱ። እነዚህ ያየኋቸው መናፍስት ምን ይመስሉ እንደነበር ለመግለፅ ልሞክር...ትዕዛዝ ሲሰጣቸው የነበረው ትልቅና ሙሉ እድገቱን የጨረሰ ድብ ይመስል ነበር። ጭንቅላቱ የለሊት ወፍ ይመስላል። አይኖቹ በጣም ተራርቀው በጭንቅላቱ ላይ ይታያሉ። ሙሉ ፊቱን ከሸፈነው ፀጉር መሀል አራት ረዘም ያሉ የላይና የታች ጥርሶች ወጥተው ነበር። የሰውነቱ ቀለም ሙሉ ለሙሉ ቡናማ ነበር። ሁለተኛው መንፈስ አካሉ የጦጣ አይነት ቅርፅ ነበረው።እጆቹ ረጃጅም ሆነው እንደበፊቱ መንፈስ ሰውነቱ በፀጉር የተሸፈነ ነበር። ፊቱ አነስ ያለ ሆኖ አጭር አፍንጫ የሚመስል ነገር ከመሀሉ ይታያል። በየትኛውም የጭንቅላቱ ቦታ አይኖች ማየት አልቻልኩም ነበር። ሌላኛው ተለቅ ያለ ጭንቅላት ከትልቅ ጆሮዎች ጋር ነበሩት። የሰውነቱ ቀለም ይሄም ቡናማ ሲሆን መጠኑ ተለቅ ያለ ፈረስ ያክላል። እነዚህን መናፍስት ስመለከት ከእይታዬም ከእነርሱ ከሚመጣው አስቀያሚ ሽታም ውስጤ ታሞ ነበር.....በኋላ ጌታ ነግሮኝ እንደተረዳሁት እነዚህን ጨምሮ ሌሎች በየስፍራው ያየኋቸው መናፍስትን ሲያዙ የነበሩት ትልልቆቹ መንፈሶች ትፅዛዛቸውን የሚቀበሉት በቀጥታ ከሰይጣን ነበር። ጌታን እየተከተልኩ ጉዞአችንን ቀጠልን። እየሄድን እያለ ሌሎች መናፍስት ሳያዩን በአጠገባችን አልፈው ወደ አንድ ጉድጓድ ሄዱ....እኔና ጌታም አንድ ፍም የያዘ ከሌላ ጉድጎድ ጋር ስንደርስ ቆምን። የቆምንበት አጠገብ ያለው ጉድጓድ ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ አጥንት ያለው ሰው ከፍሙ መሀል ነበረ። ወንጌል ለመመስከር ሲሞክር ይሰማኛል። በመገረም ወደ ጌታ በጥያቄ ተመለከትኩ። ጌታም ሁሌ ሀሳቤን ቀድሞ ያውቅ ስለነበር እንዲህ አለኝ። " በምድር ይኖር ሳለ ወንጌልን ይሰብክ የነበረና በአንድ ወቅት እውነትን ይናገር የነበረ ሰው ነው።" አለኝ። ታድያ ይሄ ሰው ሲዖል ምን ይሰራል ስል አሰብኩ።... ክፍል ፦8 ይጥላል ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Show all...
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ 🔸ክፍል-9 የሲዖል የቀኝ እግር ወደ ሌሎች ጉድጓዶች ስንሄድ በምናልፍበት መንገድ ሁሉ ያሉ ነፍሶች እጆቻቸውን እየዘረጉ ወደ ጌታ በልመና ምህረትን ይጠይቁ ነበር። የሁሉም እጆች አጥንት ብቻ ሆነው በእሳቱ ከመቃጠል የተነሳ ጠቁረዋል። ስጋ ፣ደምና አካል የሚባል የላቸውም። በአለም የምትኖሩ ሆይ እባካችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ አምናችሁ ንስሀ ካልገባችሁ ወደዚህ ስፍራ መምጣታችሁ አይቀርም። ከመርፈዱ በፊት ወስኑ።ወደ ቀጣዩ ጉድጓድ ስንሄድ አካሌም መንፈሴም ተሰብሮ መራመድ እንኳን አቅቶኝ ነበር። ያለማቋረጥ የምሰማው ለቅሶ ውስጤን በሰቀቀን ሞላው። በዚህ በደረስንበት ጉድጓድ ውስጥ ያለችው ነፍስ ከፍሙ መሀል ተቀምጣ ትታያለች። መላ አካሏ በበሰበሰ ስጋና በትሎች ተሞልቷል። እሳቱ እየተፍለቀለቀ ሰውነቷን ያቃጥላል። ወደ ጌታ አጥንት ብቻ የሆነው እጆቿን ዘረጋችና "...ጌታ ሆይ እባክህ አሁን ከዚህ ልዉጣ...አሁን ልቤን ለአንተ እሰጥሀለሁ ...ስለ ምህረትህ ምስክር እሆናለሁ ለሌሎች እናገራለሁ.....እባክህ ልውጣ አለች። ጌታም " ቃሌ እውነት ነው። ቃሌም ደግሞ የሚለው ሁሉም ሀጥያተኛ በኔ አመነው ንስሀ ካልገቡ እዚህ ስፍራ ከመምጣት ማምለጥ አይችሉም። የፈሰሰው ደሜ ለሀጥያት ሁሉ ምህረትን ያስገኛል። እኔም ወደኔ የሚመጡትን ይቅር ለማለት ታማኝ ነኝ። ወደኔ የመጡትን ከራሴ አለያቸውም።" ወደ ሴትየዋ ዘወር ብሎ " ወደኔ ተመልሰሽና ንስሀ ገብተሽ ቢሆን ኖሮ ይቅር እልሽ ነበር።" ሴትየዋም ጌታን " ጌታ ሆይ ከዚህ የምወጣበት ምንም አይነት መንገድ የለም?.." አለችው። " ለአንቺ ንስሀ እንድትገቢ ብዙ እድሎች ተሰጥተውሽ ነበር ግን ልብሽን አደነደንሽ። ቃሌ የማይታዘዙት ከእሳት ባህር ድርሻ አላቸው እንደሚል ታውቂያለሽ።.."አላት። ጌታ ፊቱን ወደኔ አዙሮ..." ይህች ሴት ከብዙ ወንዶች ጋር በሀጥያት የተሞላ ዝሙት ትፈፅም ነበር። ለብዙ ቤተሰብ መበታተንም ምክንያት ነበረች። ይሄን ሁሉ እያደረገች እሷን እወዳት ነበር የመዳን መንገዴን ላሳያት ወደሷ ሄድኩ። ከክፉ ስራዋ እንድትመለስና ንስሀ እንድትገባ ብዙ ሰራተኞቼን ወደሷ ላኩኝ። ግን ንስሀ አትገባም ነበር። በጣም ወጣት እያለች ወደሷ ሄድኩኝ አልሰማችኝም። ብዙ ስህተትንም ሰራች ቢሆንም ግን ወደኔ ተመልሳ ቢሆን ኖሮ ይቅር እላት ነበር። ግን ሰይጣን በውስጧ ገባ የበለጠ መራር ሆነች። ማንንም ይቅር ማለት አትፈልግም ነበር። ወደ ቤተክርስቲያን ወንዶችን ፍለጋ ትሄድ ነበር። የምታገኛቸውንም እያማለለች ትወስድ ነበር። ወደኔ ተመልሳ ቢሆን ኖሮ ግን ሙሉ ሀጥያቷን በደሜ አጥቤ አነፃት ነበር። በግማሽ ልቧ እኔን ማገልገል ትፈልግ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔርም ሰይጣንንም በአንድ ጊዜ ማገልገል አይቻልም። ሁሉም ሰው ማንን እንደሚያገለግል መምረጥ አለበት። "..ጌታ ሆይ እባክህ ጥንካሬን ስጠኝ የማየውን ነገር መቋቋም አልቻልኩም..."ብዬ አለቀስኩ። ጌታም " አይዞሽ ተረጋጊ" አለኝ። " እባክህ ጌታ ሆይ እርዳኝ...ሰይጣን አለም ሲዖል መኖሩን እንዲያውቅ አይፈልግም ...ጌታ ሆይ እንዲ ይሆናል ብዬ በህልሜም አስቤ አላውቅም ነበር... ውዴ ኢየሱስ መች ነው የሚያበቃው ሲዖል....." " ልጄ ሲዖል መች እንደሚያበቃ አባቴ ያውቃል። አይዞሽ ተረጋጊ። .." ሲለኝ ጥንካሬ ተሰማኝ። እኔና ጌታ ባለፍንባቸው ጉድጓዶች ሁሉ ያሉትን ነፍሶች ስቤ አውጥቼ ወደ ጌታ እግር ስር ባደርጋቸው ደስ ባለኝ ነበር።...በልቤም መቼም ልጆቼ ወደዚህ ስፍራ እንዲመጡ አልፈልግም ስል አሰብኩ። በመጨረሻም ጌታ "...ልጄ አሁን ወደ ቤትሽ እንመለሳለን ነገ ምሽት ተመልሰን ወደ ሲዖል እንመጣለን አለኝ።.... ይቀጥላል
Show all...
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ 🔸ክፍል-8 የሲዖል የቀኝ እግር የሰውየው ቁመት 6ጫማ ወይም 1ሜትር ከ80 የሚሆን ይመስላል። በፍሙ የተቃጠሉት አጥንቶቹ ግራጫ ቀለም ነበራቸው። የተወሰነ ልብስ መሳይ የተቀዳደደ ነገር ሰውነቱ ላይ አይቼ እንዴት በፍሙ እንዳልተቃጠለ አስቤ ገረመኝ። ከአጥንቶቹ ጥቂት ተቃጥለው የተንጠለጠሉ ስጋዎች ነበሩ በጭንቅላቱ ላይ እሳት ይታየኝ ነበር። ይሄንን እየተመለከትኩ ሳለ ከሰውየው ጠንካራና አስቀያሚ ሽታ ወደኔ መጣ....ሰውየው በእጆቹ መፅሐፍ-ቅዱስ እንደያዘ ሰው አድርጎ ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተፃፉ የመፅሐፍ-ቅዱስ መፀሐፍቶችን ይናገራል። ከምዕራፍ ምዕራፍ ከመፅሐፍ መፅሐፍ እየቀያየረ ይሰብካል። እኔ የሚናገረው ጥሩ መስሎኝ ነበር። ጌታም እሱን " ሰላም... እረፍ " ሲለው ሰውየው በዚ ጊዜ ተረጋግቶ መጮኹን አቆመና በቀስታ ወደ ጌታ ተመለከተ። ድምፁን ቀስ አድርጎ በልመና "...ጌታ ሆይ አሁን ወጥቼ እውነትን ለሰዎች እናገራለሁ። አሁን ወጥቼ ስለዚህ ስፍራ ለሰዎች አወራለሁ።አውቃለሁ በምድር ሳለሁ ሲዖል መኖሩን አላምንም ነበር። አንተም ተመልሰህ ትመጣለህ ብዬም አስቤ አላውቅም.....ሰዎች ይሄን መስማት እንደማይፈልጉ ከተረዳሁ ጀምሮ ሰዎች እንዲቀበሉኝ ስል እውነትህ ላይ ውሸትን ቀላቀልኩ። ዘራቸውና ቀለማቸው ከኔ የሚለዩ ሰዎችን አልወድም ነበር። ብዙዎችም በኔ ምክንያት አንተን እንዲርቁህ አደረግኩ ስለ መንግስተ-ሰማይ እና ሲዖል የራሴን ህግ አወጣሁ....ብዙዎች በአንተ ላይ እንዲያምፁና ቅዱሱን ቃልህን አቃለው አንዲያዩት አደረግኩ....ከደሀው ገንዘቡን እያታለልኩ ወሰድኩ.... ጌታ ሆይ እባክህ አሁን ከዚህ ልውጣ! በትክክል ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደርጋለሁ።....ከቤተክርስቲያን ገንዘብ መውሰዴን አቆማለሁ።....,ንስሀ ገብቼ ሁሉም ከኔ በዘርም በቀለምም የሚለዩ ሰዎችን እወዳለሁ።...እባክህ ጌታ ሆይ።.." ጌታም እንዲህ አለው። "...አንተ ቅዱሱን ቃሌን አሳስተህና አበላሽተህ ስትናገር ብቻ አልነበረም የነበረው...እውነትን እንደምታውቅ ትዋሽ ነበር።..ግን ከእውነት ይልቅ የምድር ህይወት እርካታ በልጦብህ ነበር። ራሴ ጎብኝቼህ ወደ እውነቴ ልመልስህ ሞክሬ ነበር።ግን አልሰማኸኝም ነበር። በራስህ መንገድ ሄድክ ክፉውንም አለቃህ አድርገህ ሾምክ። እውነት የቱ እንደነበር ተረድተህ ግን ንስሀ ገብተህ ወደኔ አልተመለስክም ነበር። ሁሌ ከአንተው ጋር ነበርኩ። እየጠበቅኩህም ነበር። ንስሀ እንድትገባ ስለምንህ ነበር አንተ ግን አልገባህም ነበር....እናም አሁን ፍርድህ ተፈፅሟል." ሀዘን በጌታ ፊት ላይ አይ ነበር። ሰውየው ምድር ሳለ ጌታ ብሎት የነበረውን ቢሰማ እዚ ባልተገኘ ነበር። እባካችሁ ሰዎች ጌታ የሚላችሁን ስሙ።.....ጌታ መልሶ ለሰውየው መናገር ቀጠለ። "...እውነትን መናገር ነበረብህ እውነትን ብትናገር ኖሮ ብዙዎችን በእግዚአብሔር ቃል ወደ ቅድስና በመለስክ ነበር። ቃሌም የሚለው ሁሉም የማያምን በዲን እና በእሳት ከሚቃጠል ባህር የድርሻውን ያገኛል ነው። የመስቀሉን መንገድ ታውቅ ነበር።የቅድስናንም መንገድ ታውቅ ነበር። እውነት መናገር እንደነበረብህም እንደዛው ነገር ግን ሰይጣን ልብህን በውሸት ስለሞላው ወደ ሀጥያት ሄድክ። በትህትና ንስሀ መግባት ነበረብህ....ቃሌ እውነት ነው! ቃሌ በውስጡ ውሸት የለውም።....አሁን በጣም ረፍዶብሀል....በጣም ረፍዷል።." በዚህ ጊዜ ሰውየው እጆቹን አወናጭፎ ጌታን መራገም ጀመረ። በሰቀቀን ተሞልቼ ከጌታ ጋር ወደ ቀጣዩ ጉድጓድ ሄድን። ሰባኪው ከኋላ ተቆጥቶ ያለማቋረጥ ሲራገም ይሰማኛል። ይቀጥላል... ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Show all...
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ 🔹ክፍል-5 የሲዖል የግራ እግር መጀመርያ ያየኋት ትልቅ ሴት ከኋላ ታየችኝ አሁን ሳያት ያስተዋልኩት ግን አንድ እግር ብቻ እንዳላት ነበር። በአጥንቶቿ ቀዳዳዎች ይታዩኛል። "...ምንድነው ጌታ ሆይ ?" ብዬ ጠየቅኩ። ጌታም " በምድር ሳለች ካንሰር በሚባለው በሽታ በጣም ታማሚ ነበረች። ህይወቷን ለማዳን ቀዶ ጥገና ተደርጎላት ነበር። ከተደረገላት በኋላ ግን ለአመታት መራር ሴት ሆና አረጀች። ብዙ የኔ ሰዎች ሊፀልዩላት ይመጡ ነበር። ትፈወሻለሽ ሲሏት " እግዚአብሔር ራሱ ነው ይህንን ያደረገብኝ " ብላ ታባርራቸውና ወንጌሌንም ታጥላላ ነበር።ንስሀ አልገባችም ነበር። ቀድሞ ታውቀኝ ነበር ኋላ ላይ ግን ጠላችኝ። እግዚአብሔር አያስፈልገኝም ፈውሱንም አልፈልግም ትል ነበር። ስለምናት ጀርባዋን ሰጠችኝ። አልፈልግህም አለችኝ። መንፈሴ ወደኔ እንድትመጣ አጥብቆ ለመናት አትሰማም ነበር። ኋላ ሞተችና ወደዚህ ስፍራ መጣች። ሴትየዋን ጥቂት ስንጠጋት " ጌታሆይ አሁንስ ይቅር አትለኝም? በምድር ሳለሁ ንስሀ ባለመግባቴ እባክህ ጌታ ይቅርታ አድርግልኝ።" እያለች አለቀሰች። " ምናለ ድሮ ንስሀ ገብቼ ቢሆን ኖሮ። አሁንማ በጣም ረፈደብኝ። ግን ጌታዬ ከዚ አውጣኝ እባክህ ካወጣኸኝ አገለግልሀለሁ ጥሩ እሆናለሁ......የእስካሁኑ ስቃዬ አይበቃም ጌታ ሆይ እባክህ" ".....ወይኔ ለምን እስኪረፍድብኝ ድረስ ቆየሁኝ ለምን መንፈስህ እስኪተወኝ ከአንተ ራቅኩ....." ብላ አለቀሰች። ጌታም መለሰላት " በኔ አምነሽ ንስሀ ገብተሽ እንድታገለግይኝ በተደጋጋሚ ብዙ እድል ነበረሽ።...." በጌታ ፊት ሀዘን እየተነበበ ተመልሰን ከሷ ርቀን ሄድን።ፍርሀት ብቻ ነው የሚሰማኝ ለቅሶ፣ሰቆቃ፣እና ሞት በአካባቢው ሰፍኗል። ከጌታ ጋር መሄዴ ነው ጥንካሬ የሆነኝ እንጂ አልችለውም ነበር። ከሷ በጣም ርቀን እንኳ ለቅሶና ልመናዋ ይሰማ ነበር። እባካችሁ ማናችሁም አሁን በሀጥያት የምትኖሩ እስኪረፍድባችሁ አትጠብቁ እባካችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ገና ሳይርቃችሁ ወስኑ። በቀጣዩ ጉድጓድ የተንበረከከች ሴት ትታያለች ከፍሙ መሀል አንዳች ነገር የምትፈልግ ይመስል መሬቱን ትጭራለች። እንደቀደሟ ሴት አጥንቷ በቀዳዳዎች የተሞላ ነበር። የተቀደደና የተቃጠለ ቀሚስ መሳይ ነገር በሰውነቷ ይታያል።ጭንቅላቷ ላይ ፀጉር አልነበረም። አይኖቿና አፍንጫዋ በነበረበት ቦታ የማየው ባዶ ቀዳዳ ብቻ ነበር። የተንበረከከችባቸው ጉልበቶቿ ስር እሳት በጥቂቱ ይነዳል። በእጆቿ መሬቱን በጫረች ቁጥር ሰውነቷ ላይ ተቃጥለው የተንጠለጠሉት ስጋ መሳይ ነገሮች ይረግፋሉ። ድንገት ቀና ብላ ስታየን " ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ መውጣት እፈልጋለሁ ..." ብላ እየተንደረደረች ወደ ጉድጓዱ ጫፍ ለመውጣት ታገለች። ልትወጣ መስሎኝ ነበር ነገርግን ከፊት ለፊት አንድ ክንፎቹ የተዛነፉ አጋንንት ወደሷ እየተንደረደረ መጥቶ ገፈተራት። አጋንንቱ ቀለሙ ጥቁር ቡኒ ነበር። መላ ሰውነቱ በፀጉር ተሸፍኖ ነበር። አይኖቹ ከጭንቅላቱ ዳርና ዳር በጣም ተራርቀዋል። የሰውነቱ መጠን አንድ ትልቅ ድብ ይመስል ነበር። ሲገፈትራት የወደቀችውን ዘግናኝ አወዳደቅ እየተሳቀቅኩ ተመለከትኩ። አጠገቤ አድርጌያት አቅፌ ጌታ እንዲምራትና እንድትወጣ ተመኘሁ። ጌታ ሀሳቤን አውቆ እንዲህ አለኝ። " ልጄ አባቴ ተናግሮ ፍርዷ ተፈፅሟል። ገና ልጅ እያለች ጀምሮ ነበር ንስሀ ገብታ በኔ አምና እንድታገለግለኝ ስጠራት የነበረው። የ16አመት ልጅ እያለች ወደሷ ሰዎቼን ልኬ ' እወድሻለሁ ህይወትሽን ለኔ ስጭኝ። ተከተይኝ ለተለየ አላማ ጠርቼሻለው። አልኳት እርሷ የምትለኝ ግን "አንድ ቀን አገለግላለሁ ጌታ ሆይ። አሁን ጊዜ የለኝም። አሁን ጊዜዬ ለመዝናናትና ለጨዋታ ነው እንጂ ቤተክርስቲያንም አንተን ላገለግልህ ጊዜ የለኝም። ነገ አገለግልሀለሁ ነገ " አለችኝ። " የቀጠረችው ነገዋ ሳይመጣ ግን ረጅም ጊዜ አሳለፈች" ይቀጥላል ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Show all...