cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Missionary University

+251960840001 Online Learning www.missionaryuniversity.org Website www.missionaryuniversity.com Chat @musupport Register https://bit.ly/3y46rtB Address፦ Lafto, Gebre Buildg 4th Floor, Addis Abeba

Show more
Advertising posts
11 872
Subscribers
+924 hours
+1517 days
+65030 days
Posts Archive
በቀጣይ ሽልማት የሚያስገኝ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄ ስላዘጋጀን ውደእሱ እናልፋለን ዝግጁ ✊
Show all...
ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ እና Free card gift ስላለ ከ online እንዳትወጡ😳
Show all...
. "አንተ ባለአደራ" 🎵🎶 BY ህያብ ✨HAPPY EASTER✨ ✨መልካም ፋሲካ✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
. አምናለሁኝ ውዴ ◉-====◊====-◉ ከዚያ ቅጣት መንደር በደል በበዛበት ሀጢያቱ በርክቶ ሞት በሚሰመኝበት የበደል ግፍ ናዳ መሸከም አቅቶኝ የጠላት ክስ በዝቶ ተስፋ አስቆርጦኝ ተስፋ ከእኔ ሲርቅ ሞቴን ስጠባበቅ መጣህ ውዴ ለእኔ እጅግ አሳስቦህ መባዘን መድከሜ ውዴ የኔ አዳኝ ስትመጣ ልትረዳኝ ምን ያልሆንከው አለ ምንስ ያልከፈልከው? ዘርዝሬ (2x) ከቶውን አልጨርሰው አውይ ውዴ ለኔ እምባህን አፍሰህ ደስታን ሸለምከኝ ግርፋቴን ወስደህ ሰላምን ሰጠኸኝ የእሾህ አክሊል ደፍተህ ክብር አጎናፀፍከኝ በመስቀል ተሰቅለህ ሞቴን ደግሞ ሞተህ ህይወትን አለበስከኝ ውዴ እስቲ ምን አለ ለኔ ያልሆንክልኝ? ምንም ሳትበድል የተንገላታከው በስቃይ በደዌ እስከ ሞት የሄድከው አምንሀለሁኝ ውዴ ሌላ ምንም የለህ ተገርፈህ ተወግተህ የደም ላብ ማላበህ ትልቅ ሚስጥሩ አንደ ና አንድ ነው ይሄን ሁሉ ናዳ ችለህ የደከምኸው አምናለሁኝ ውዴ እኔን ለማዳን ነው አምንሀለው አምንሀለው የውዴ መስቀል መሞት ለኔ ነው ታዲያ እኔም አምኜ ከብር ወርቅ እንቁ ጋር ማላወዳድረው በምንም በማንም ልቀይር ማልችለው የህይወቴ ቤዛ ውዴ ክርስቶስ ነው ◉=====◊=====◉ ✍ተፃፈ በተስፋቃል ክበበው
Show all...
. "ስቀሉት" 🗣ገጣሚ ማቴዎስ ለትንሳኤ የተገጠመ በጣም ገራሚ ግጥም ነው ስሙት ❤️ ✨HAPPY EASTER✨ ✨መልካም ፋሲካ✨ ✨ @christ_progeny_tube ✨ ✨ @christ_progeny_tube ✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
. "ቤዛዬ" 🎵🎶 ዘማሪት ውዴ ከበደ ✨HAPPY EASTER✨ ✨መልካም ፋሲካ✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
ፕሮግራማችንን በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ መንፈስ ቅዱስ አንደ አምላክ ስም እንጀምራለን ። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ
Show all...
እስከዛው ድረስ ግጥም ፣ ዝማሬ ፣ መነባነብ ያላችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን 👉 @NoneoneT
Show all...
ዛሬ ምሽት 2:30 ላይ በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የፋሲካ ዝግጅት ማለትም ግጥም ፣ መነባነብ፣ ዝማሬ እንዲሁም ነፃ የሞባይል ካርድ ስጦታ ስለሚኖሩን ማታ online እንዳትቀሩ ስንል በጌታ ፍቅር እናሳስባቹሀለን ። ❤️ CHRIST FAMILY TUBE
Show all...
🚨የፋሲካ መልዕክቴ 🔥🔥 ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ 🚨#ፋሲካን እንዲህ አክብሩት🙏 🚨ዛሬ #ዶሮ የበላችሁም #ያልበላችሁም ይሄ ይመለከታችኋል‼️ 🚨አገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ 🚨ፌስቡክ ፔጄ👇 https://www.facebook.com/ashenafi.mulugeta.146 በ youtube ቤተሰብ በመሆን አዳዲስ ትምህርቶችን በየእለቱ ያግኙ 👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ Holy Tube Ethiopia ........................………………………… #ራስዎን_በቤት_ይገንቡ ............▪️•°○.......................... ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ 👇👇👇በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot @christ_progeny_tube @christ_progeny_tube
Show all...
Repost from Bible Quote 📢
ኢየሱስ ሊሰቀል ሲል በስራቸው ያልተባበረዉ ሰው ስሙ ማን ነው? " እነሆም፥ በጎና ጻድቅ ሰው የሸንጎ አማካሪም የሆነ --------የሚባል ሰው ነበረ፤ ይህም በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር"Anonymous voting
  • ዘካርያስ
  • ጺላጦስ
  • አናንያ
  • ዮሴፍ
0 votes
🔔ተለቀቀ🔔✝✝ እንኳን ለብርሃነ #ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ✝✝ #በአይነቱ #ልዩ ጊዜ🤣🤣 Watch "🛑"ኧረ ፈረስን..🤣🤣" ልዩ የኢንተርቪው ጊዜ ከአገልጋይ መልካሙ ሙልጌታ ጋር.." on YouTube https://youtu.be/g9OtP2FuZs0
Show all...
"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።" - ኢሳይያስ 53፥5 ፍሲካን ስናስብ በቸርነቱ ያደረገልንን ፈዉስ ልናስብ ግድ ነው በአንድ የአዳም ሀጥያት ምከንያት ወደሰው ልጆች ሁሉ የሀጥያት በሽታ ገባ ከዚህ የተነሳ ሁሉም ሰው ታማሚ ሆነ የሄ ታማሚ የሆነ ሰው በሰራው መተላለፍ መቁሰል ሲገባው በበደላችን ምክንያት መድቀቅ እና ቁጣ ሲገባን ምንም በደል የሌልው መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰለሰው ልጆች መተላለፍ ሲል ቁሰለ፤ ደቀቀ፤ የእኛን ቁጣ ተሸክሞ ከሀጥያት በሽታ በመስቀሉ ስራና በትንሳኤው ሀይሎ ፈወሰ የማይገባንን እኛን ፈወሰን አሜን ብዙ ክብር ለሱ ይሁን። ስለዚ ፋሲካን ስናከብር የተደረገልንን ቸርነት በማሰብ ይሁን መልካም ፋሲካ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
✝ ክርስቶስ ተንስኣ እሙታን፣ ሞተ ወኬዶ ለሞት፣ ለእለ ዉስተ መቃብር፣ ወሃበ ህይወተ፣ ዘለዓለም ዕረፍት። ✝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል፤ ሞቶ ሞትን ሽሮታል፤ በመቃብር ለነበርን ህይወትን ደግሞም ዘለአለማዊ ዕረፍትን አግኝተናል። ✝ Christ is Risen from the Dead, by death hath he trampled down death and those in the graves hath he bestowed. 🎆🎆🎆 እንኳን አደረሳችሁ! 🎆🎆🎆 💝💝💝💝 @thewordofGod92 👆👆Join👆👆👆
Show all...
https://youtu.be/UCZPnXKZYBk ተወዳጅ የስቅለት መዝሙር ይገርማል ፍቅርህ |ዘማሪ ምህረት ኢተፋ YouTube ገብታችሁ ማየት ላልቻላችሁ ከLyricsu👇👇
Show all...
04:47
Video unavailableShow in Telegram
የስቅለት መዝሙር Lyrics ከBe Informed First |YouTube channel |telegram |Facebook | ይገርማል ፍቅርህ | ዘማሪ ምህረት ኢተፋ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Jesuschristinheaven
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለprofile ምሆኑ መንፋሳዊ ጥቅሶችን ለማግኘት ይፋልጋሉ? አሁኑኑ ከታች ያለውን ሊንክ በመጨን ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇😒😒😒👇
Show all...
🖼መንፋሳዊ ጥቅሶችን🖼
🖼profile picture 🖼
🖼wallpaper pictures 🖼
🖼all join🖼
. "የህማም ፍሬ" ክፍል አራት °°°°°°°°°°° 🗣ተራኪ ሜርሲ ለትንሳኤ የተተረከች ወግ ናት ስሟት ✨HAPPY EASTER✨ ✨መልካም ፋሲካ✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
. ተነስቷል አውታሩ ከበደ ✨EASTER SONG✨ 🕐-6:47Min-||-💾-4.7MB ▷THE GOSPEL IS CHRIST◁ Share 📲 Share 📲 Share ▷ @Zema_Sink ◁ ▷ @zema_Sink ◁ △Join US △
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
HAPPY EASTER ✝✝✝✝ 💝💝💝💝 👉 @thewordofGod92 👈 Share💕
Show all...
. ተፈፀመ ቤተልሔም ተዘራ ✨EASTER SONG✨ 🕐-4:59Min-||-💾-4.8MB ▷THE GOSPEL IS CHRIST◁ Share 📲 Share 📲 Share ▷ @Zema_Sink ◁ ▷ @zema_Sink ◁ △Join US △
Show all...
#የዋዜማ መልዕክት በህይወቴ በጣም ከምገረምበት ነገር አንዱ በአል ሲመጣ በአል ነው ብለን ያመንበትን ምክንያት ከማሰብ ይልቅ ስለምንበላው ፣ ስለምንጠጣው ፣ ስለ ልብሳችን መጨነቃችን ነው ። 👉 አዲስ አመት መጣ አዲስ ልብስ ልግዛ ፣ 👉 ገና ነውና ስጦታ ካልተሰጠኝ ፣ 👉ፋሲካ ነው ዛሬ በጉን ዶሮውን ልግዛ ሆኖል የኛ ህይወት መብላቱ መጠጣቱ ክፋት ሆኖ ሳይሆን ከርሱ በላይ እግዚአብሔርን እንድናስበው ስለምፈልግ ነው እንደሚታወቀው ነገ ፋሲካ ነው ዛሬ ዋዜማው ላይ ቆመናል ብዙዎቻችንን ያስጨነቀን ነገር ግን የሽንኩርት ፣ የዘይት ፣ የዶሮ መወደድ ነው እስቲ ስንቶቻችን ነን ከበአሉ ሽር ጉድ ውጪ በፅሞና ስለተደረገልን ስለተከፈለልን ዋጋ የምናስበው ? 📌 ከምንበላው በግ በላይ የናዝሬቱ ኢየሱስ ለኛ እንደ በግ ታርዶልናል እሱ ነው ሊያሳስበን የሚገባው !!! 📌የተከፈለልኝ ዋጋ ዋጋቢስ አድርጌዋለሁ ወይስ ገብቶኛል ብሎመፈተሹ ተገቢ ነው ።በአል ወር ሲቀረው ጀምረን በወጪ ከምንጨናነቀው በላይ ስለነፍሳችን ፣ ስለመዳናችን እንጨነቅ ። 🌹እንደ ፅጌረዳ ፈክተን ተሽሞንሙነን እየበላን እየጠጣን ብቻ ከምናሳልፈው ይልቅ ምንም ሳይኖረን የተደረገልንን እያሰብን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርገን ብናሳልፈው እሱ ለእግዚአብሔር ታላቅ ዋጋ አለው ። ይህን ስል መብላቱ መጠጣቱ አያስፈልግም ማለቴ ሳይሆን በምቾታችን ተታለን ቅድሚያ መሰጠት ያለበትን ነገር እየረሳነው ይመስለኛል ። ከጎረቤት አላንስም ፣ ያስለመድኩት አይቀርም እያልን አጉል መጨናነቅ ውስጥ ከመግባት ባለን ተደስተን ከቻልን አካፍለን እግዚአብሔር እያመሠገንን ባዕሉን ማሳለፍ ነው ። ቅድሚያ ትኩረታችን #ኢየሱስ ላይ ይሁን ሌላው ትርፍ ነው ። በሰበብ ባስባቡ አመት ባል በመጣ ቁጥር ልዝናና ፣ ልጨፍር ፣ ልብላ ከማለት ይልቅ ልክ እንደ ወርቃማ እድል ቆጥረነው የምንችል ቤተክርስቲያን ያልቻልን ቤታችን ወይም ባለንበት ቦታ እግዚአብሔርን ፣ የተደረገልንን ነገር እያሰብን እናክብረው ማሰብ ብቻ ሳይሆን በቀረም ዘመናችን የመስቀሉን ስራ እያሰብን በዋጋ ተገዝተናልና ስለዛ እንኑር ። 🙏🙏 መልካም የፋሲካ በአል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ተመኘሁ 😊 ✍በያኔት ማስረሻ #share @yanet_literatures
Show all...
Don't post admin ‼️
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለprofile ምሆኑ መንፋሳዊ ጥቅሶችን ለማግኘት ይፋልጋሉ? አሁኑኑ ከታች ያለውን ሊንክ በመጨን ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇😒😒😒👇
Show all...
🖼መንፋሳዊ ጥቅሶችን🖼
🖼profile picture 🖼
🖼wallpaper pictures 🖼
🖼all join🖼
🔔ተለቀቀ🔔✝ እንኳን ለብርሃነ #ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ እነሆ የበአል ፕሮግራማችን አንድ ብሎ ከዛሬ ጀምሯል ✝✝👇 https://youtu.be/KmINoKxyBC4 https://youtu.be/KmINoKxyBC4
Show all...
ቅዳሜን አዘልለኝ " ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር፥ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ። የማርቆስ ወንጌል 14 : 52 በደጉ ዘመን ከብቤህ ነበር አንዳች አልጎደለኝ፤ ከእጅህ እበላለው አልተራብኩም፣ በእጅህ እፈወሳለው አልታመምኩም፣ በእጅህ እደገፋለው አልወደቅሁም፣ አይኔ እልፈዘዘም መልክህን እያየሁ እደሰታለው፣ ጆሮዎቼ አልተራቡም ህይወት ባለው ቃልህ እረክተዋል፣ ፀጉሬን ስታሻሸኝ እናትና አባቴን ረስቼ ጉያህ ውስጥ እገባለው፣ እግሮቼን ስታጥበኝ እየኮረኮርክ ስታስቀኝ ፍቅርህን ስታሳያኝ ልቤን በደስታ ታዘልልብኝ ነበር፣ ቃልህን ስሰማ ስታቆላምጠኝ ነፍሴ ውስጤ ትፈስብኝ ነበር ። አይ ቅዳሜ ......ነበር አስባለችኝ። የደስታ ቀን እንጂ የክፉ ቀን ወዳጅ አልሆንኩም። ሁሉን ትተህ ተከተለኝ ስትለኝ ሁሉን ትቼ ተከተልኩ። ዛሬ ቃልኪዳኔን አፍርሼ ሁሉን ትቼ እርቃኔን ሸሸውህ። መጠጊያዬ ብዬ ሳመሰግንህ ኖሬ ዛሬ ግን መጠለያ ዋርካዬ ፈረሰብኝ ብዬ ሌላ መጠለያ ፍለጋ ያገለደምኩትን ነጠላዬን ጥዬ ጠፋው። የኔ መውደድ እዚህ ድረስ ነው። ዛሬም እኮ ቅዳሜ ላይ ነኝ! ተከተሉኝ እንዴ ብዬ ስርቻ ስር ተወትፌ እያጮለኩ ነው። ላንተ ጀርባ ሰጥቼ አለምን ለማሳደድ ዛሬም ሩጫዬን አልገታሁም። ትቼው የመጣሁትን የአለምን ግሳንግስ ዛሬ እያግበሰበስኩ ነው። ካንተ እንደተለየሁ ተራቆትኩ የሰው ማሟሻ አዳም አንተን እንደተለየ መራቆቱን አወቀ እርቃኑን ሊሸፍን ቅጠል ቢሰፋም አልታደገውም። ነፋስ ይገልብበታል። እኔም ካንተ ተለይቼ እርቃኔን ነኝ በዝና አልሸፈን፣ በስልጣን አልከልለው፣ በሀብት አልጋርደው ሁሉም ይገጣል። ገበናዬን ሸፋኝ አንተ ብቻ ነህ። ጌታዬ ሆይ አትዘንብኝ! አስተካክለኝ! ተንሸራታች ነኝ፣ አፅናኝ ወላዋይ ነኝ፣ ልቤን ደግፈኝ ወደሞቀበት ነኝ፣ ፅኑ ፍቅር የለኝም በፍቅርህ ያዘኝ፣ እንደገና ስራኝ የምፈርስ ነኝ፣ ክህደቴን ክጄ ፀንቼ ልመንህ፣ ፍርሀቴን ክጄ አለቴን ልያዝህ እባክህን ቅዳሜን አሻግረህ እሁድን አሳየኝ። ከሞትህ አልፌ ትንሳኤህን ልየው። ✍አዶኒ ✨ @christ_progeny_tube ✨ ✨ @christ_progeny_tube ✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
Cross until tomorrow ‼️ Don't post admin
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለprofile ምሆኑ መንፋሳዊ ጥቅሶችን ለማግኘት ይፋልጋሉ? አሁኑኑ ከታች ያለውን ሊንክ በመጨን ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇😒😒😒👇
Show all...
🖼መንፋሳዊ ጥቅሶችን🖼
🖼profile picture 🖼
🖼wallpaper pictures 🖼
🖼all join🖼
በሜርሲ እና ብዕሯ ተዘጋጅቶ በ CHRIST FAMILY TUBE የሚቀርብ . #ካልተፈቱ_እስራቶች ክፍል 6 (ሜርሲ✍) . . ሶስቱም ማቆያ ውስጥ ከገቡ ቀናት ተቆጠሩ...ሳምንታት አለፉ..ሰላም የምትረጋጋው እርሷ የምትፈልገውን ትምህርት እየተማረች እንደሆነ ስታስበው ነው...ጓደኞችዋ ብዙ ርቀት እንደተጓዙ ማሰብ አትፈልግም።ሮዳስን ለመለወጥ ብዙ መሄድ እንዳለባቸው አምነዋል...ለዛም ስትል ኤደን በተደጋጋሚ ታገኛት እና ከእርሷ ጋር ታሳልፍ ነበረ።ዮዲት ሌሎችን መኖሯን አላቆመችም ነበር..የሌሎችን እንባ ታነባለች...ሳቃቸውን ትስቃለች...ህመማቸው ህመሟ ነው።....እርሷ ግን አልነበረችም። "ሶስቱንም የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ለእራሳቸው የሰጡት ዋጋ ተመሳሳይ መሆኑ ነው...ሶስቱም ያሉበትንም ሆነ ማንነታቸውን ሊቀበሉ ፍቃደኛ አይደሉም።" ብላ ደምድማለች ኤደን። * * * * * ቁርሳቸውን እየተመገቡ እያለ ፀሎት ልንገረው ልተወው በሚል ውዝግብ ውስጥ ሆና አባቷን ትመለከተዋለች።ሊያጎርሳት ቀና ሲል ነበር አስተውሎ ያያት የጠቀለለውን እያጎረሳት "ችግር አለ የኔ ልጅ?" ያጎረሳትን በውሃ ካወራረደች በኋላ ጥቂት አሰብ አደረገችና አማኑኤል ሆስፒታል ላይ ታደርጋቸው ስለ ነበረው ክንውኖች አጫወተችው።ከጨረሰች በኋላ ባለማመና ቀና ብሎ እያያት ዝም አለ። "አባዬ...አንተ እንደማትፈቅድልኝ ስላወቅኩ ነው ቅድሚያ አማኑኤል የሄድኩት።" "እንደማትፈቅድልኝ?" "አዎን...ያኔ ማዕከሉ ከተመረቀ በኋላ እንኳ እዛ እንድሄድ ፍቃድህ አልነበረም።አንተ ብቻ ሃላፊነቱን ልትወጣው ትወዳለህ...ሃኪም ሁኚ ስትለኝ እንኳ ከልብህ አይደለም። እግዚአብሔር ደግሞ ይሄን ሸክም ውስጤ ሲያስቀምጥ ማንም ጣልቃ ገብቶ እንዲያስቆመኝ አልፈቀድኩም....ያንንም አደረግኩት....በሳምንት ቆይታዬ ብዙ ነገሮችን ለማየት ቻልኩ።"በሁለቱ መሃከል ዝምታ ሰፈነ።ምን እንደደበቃት ባታውቀውም ብቻውን የተሸከመው ሚስጥር እንዳለ ግን ተረድታዋለች።ስልኳ ሲጠራ ቀና ብላ አነሳችው "ሄለው...ደህና ነኝ ዶክተር እንዴት ነህ...እሺ..እሺ እመጣለሁ" ስልኳን በመዝጋት የበላችበትን ሰሃን ይዛ ተነሳች "ፀሎት" ዞራ አየችው "ስለነገርሽኝ ነገር ደስ ብሎኛል..ቢቻልሽ ደግሞ እኛ ጋር ብትመጪ እና ስራሽን ብትሰሪ ደስ ይለኛል።" ባለማመን እንባ ባቀረሩ ዓይኖችዋ ተመለከተችው "አመሰግናለሁ አባዬ::" * * * * ዶክተር ኤሊያስ እና ኤደን ሶስቱንም እያፈራረቁ ያያሉ።ሮዳስ እየሰረቀች ሁለቱንም ታያለች...ሰላም ደግሞ ቀና ብላ ሳታያቸው ከመፅሃፍ ጋር ታወራለች...ዮዲት ግን ሁለቱንም እያየች ፈገግ ትላለች። ዶክተር ለመናገር ጎሮሮውን ሲጠራርግ ዮዲት ቀደመችው "ማይ ስሪ ሲስተር ላይ እንዳሉት መሆን እንችላለን እኮ" "በሚገባ...አንቺ ቀደምሽን እንጂ እኛም እህትማማች እንደምትሆኑ ልንነግራችሁ ነበር የጠራናችሁ" አለች ኤደን ፈገግ አለች ሮዳስ ቀና ብላ በቁጣ ተመለከተቻቸው። "እኔ እህት አልፈልግም።" "እኔም እንደዛው"አለች ሰላም ቀበል አድርጋ ከመፅሃፉ ቀና ብላ። በዚህ መሃል ፀሎት ከነጊታሯ በሩን አንኳክታ ብቅ አለች።ሮዳስ ጊታሩን ስታይ ውስጧ ላይ የማታውቀው ስሙት ተሰማት "ይቅርታ እረበሽኳችሁ መሰለኝ።"ልትወጣ ስትል "ቆይ" የሚል ድምፅ ከበስተኋላዋ ሰማችና ዞር አለች ዮዲት ወደ እርሷ እየመጣች ነበር። .............. ይቀጥላል............ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦ ⇨ @christ_progeny_tube@christ_progeny_tube@christ_progeny_tube ─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
Show all...
. "የህማም ፍሬ" ክፍል ሶስት °°°°°°°°°°° 🗣ተራኪ ሜርሲ ለትንሳኤ የተተረከች ወግ ናት ስሟት ✨HAPPY EASTER✨ ✨መልካም ፋሲካ✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” — ኢሳይያስ 53፥5 Graphics by @suraphl12 #መልካም_ፋስካ @mezmure_graphics
Show all...
Repost from Bible Quote 📢
መፅሐፈ ዘፍጥረት ስንት ምዕራፍ አለውAnonymous voting
  • 23
  • 50
  • 39
  • 40
0 votes
Photo unavailableShow in Telegram
🚨ሻሎም ውድ የአባቴ ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እንዲሁም የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ!!✝✝✝ ……………………………………………………… 🚨ጌታ ቢፈቅድ እሁድ(የትንሳኤ እለት) ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በ Facebook ላይቭ አገለግላለሁ!👇👇👇👇 https://www.facebook.com/ashenafi.mulugeta.146 🚨Melkamu Mulugeta🚨 ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ 🚨በእለቱ ልዩ የትምህርት ፣ የፀሎት እና የፀሎት ጊዜ ይኖረናል !!🔥🔥🔥🔥 🚨ስለሆነም ከላይ የሚገኘውን ሊንክ በመጫን ከወዲሁ አገልግሎቴን በፌስቡክ መከታተል ይችላሉ!! 🚨ኢየሱስ ተነስቷል! ሞት ድል ተነስቷል! ...........……….▪️•°○........….......... ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ 👇👇👇በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot 🚨 #ሼር Share Share #ሼር🚨 ቻናሉን ይቀላቀሉ ✨ @christ_progeny_tube✨ ✨ @christ_progeny_tube
Show all...
መፅሐፈ ዘፍጥረት ስንት ምዕራፍ አለውAnonymous voting
  • 23
  • 50
  • 39
  • 40
0 votes
Photo unavailableShow in Telegram
አንተ የሌለህበት ጥጋብ ደስታ ና ፍስሀ ተጠምቶ እንደ መቃጠል ነው በደረቅ በረሃ ልዩነቴ እኮ ነህ ጌታ አለመኞች ያጡህ የምታረካ የህይወት ዉሃ ነህ ለጠጡህ 💨Bible quote graphics💨 @biblequote123 @biblequote123 ✨join as✨
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
✝✝✝✝ ➿➿➿➿➿➿ (ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53) ---------- 1፤ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? 2፤ በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። 3፤ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። 4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። 5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ➿➿➿➿➿➿ 💝💝💝💝 👉 @thewordofGod92 👈 Share💕
Show all...