cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሶዶ ቡኢ ከፍተኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ስለ ትምህርትና ስለትምህርት ቤታችን ብቻ።

Show more
Advertising posts
290
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

☝️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! ======================== 👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው 👉ያይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ ------------------------------------------------ ☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ 👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። ለተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ!👏👏
Show all...
👉ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ 👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። 👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። 👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: 👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ 👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። 👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 👉በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። 👉ወቅቱ የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈተና ተመኘን👏👏👏👏
Show all...
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል። የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላት #ማረጋገጥ ችሏል። በዚህ መሰረት ፦ 1ኛ. በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት #በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ኘሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደትም እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስመቅጧል። 2ኛ. በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 /2015 እስከ ሐምሌ 13 /2015 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል። 3ኛ. የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል። በተጨማሪም እንደ አገር ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር ከ2016 ጀምሮ ለማስተካከል ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚሁ ማዕቀፍ አንዲያስተካክሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል። ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የተለያዩ #ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እየሰሙ አለመረጋጋት ውስጥ መግባታቸውን ሲገልፁልን ነበር ፤ በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር / የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሚሰጡት ትክክለኛ መረጃ #ብቻ እንድትከታተሉ ፤ በቀረው አጭር ጊዜም ዝግጅታችሁን ታጠናክሩ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
Show all...
በባእዳን ተዘውትረው የተገፉ ኢትዮጵያኛ ቃላት Airplane(አውሮፕላን)-------ጥየራ:የአየር ሰረገላ Budget(በጀት)--------ድልድል(የገንዝብ) Business(ቢዝነስ)-ተግባር:ስራ(የንግድ) Company(ካምፓኒ)(ኩባንያ)--የንግድ ማህበር Computer(ኮምፒዩተር )--መቀመሪያ Economics(ኢኮኖሚክስ)--ስነ ብዕል Economy(ኢኮኖሚ)---ምጣኔ ሀብት Geography(ጂኦግራፊ)--መልክዓ ምድር Industry(ኢንዱስትሪ)--ተግባረ ምርት Internet(ኢንተርኔት)---የኅዋ አውታር Investment(ኢንቨስትመንት)-ሙዓለ ንዋይ Policy(ፖሊሲ)------መመሪያ Tourism(ቱሪዝም)---ሥነ ሕዋጼ Transportation(ትራንስፖርቴሽን)----- ማጓጓዣ
Show all...
The biggest animal on the planet 🐋 Blue whale is the biggest animal on the planet, weighing up to 400,000 pounds (approximately 33 elephants) and reaching up to 98 feet in length.🤔 🐋 A Blue Whale Heart Weighs 600kg. A Human could crawl through their Arteries.🤔 🐋 As the largest animal on Earth, blue whales area bout the length of three school buses, their heart alone is the size of a small car and they weigh on average 200,000 to 300,000 pounds. Our telegram channel 👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/s112b
Show all...
ሶዶ ቡኢ ከፍተኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ስለ ትምህርትና ስለትምህርት ቤታችን ብቻ።

Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና ‼️ " የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል። ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡ ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! https://t.me/s112b
Show all...
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፦ - በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ባ1 ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ብሔራዊ ፈተና አላለፈም። - የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል ነው 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ የታወቀው። - ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል። - 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦ 👉 ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣ 👉 ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣ 👉 ባህርዳር ስቴም ት/ቤት  ፣ 👉 ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤ 👉 የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው። ምንጭ፦ WMCC ፎቶ፦ ትምህርት ሚኒስቴር ፈጣን መረጃዎች እንዲደርስዎ ሼር ያድርጉ
Show all...
የ12ኛ ክፍል ውጤት አሁን ተለቋል! ከእነዚህ አንዱን በመጠቀም ፤ ውጤታችሁን ማየት ትችላላቹ:- 1. eaes.edu.et 2. eaes.gov.et 3. eaes.et 4. result.neaea.gov.et 5. Telegram 👉 @EAESbot 6. SMS 8046 • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ መላክ ፈጣን መረጃዎች እንዲደርስዎ ሼር ያድርጉ
Show all...
28ሺ ተማሪዎች ብቻ‼️ የ2014 የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ከ980 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 28 ሺ ነው ። የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር፣ ዩኒቨርስቲዎች ካላቸው የመቀበል አቅም ጋር በፍፁም እንደማይጣጣም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 150 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
Show all...
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል። ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡- • በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም • በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል። ማሳሰቢያ፡- • ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል። • ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል። ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
Show all...
EAES 🇪🇹 Result bot

EAES: Educational Assessment and Examination Service Official Bot. Use this bot to check your Result.