Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
@telemetr_io_bot
Telegram analytics bot

The bot can:

  • analyze channel audience
  • channels intersections
Category
Channel location and language
STUDENTS NEWS CHANNEL በሁሉም የሀገራችን አካባቢ እና በሁሉም የክፍል ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች ታማኝ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለማድረስ በበጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ መምህራን የተከፈተ የተማሪዎች ድምጽ በመሆን የሚያገለግል ቻናል ነው። አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መረጃዎችም ይቀርቡበታል Addis Ababa,Ethiopia 
Show more
40 873-25
~5 947
~4
14.54%
Telegram general rating
Globally
42 127place
of 3 824 617
61place
of 899
In category
291place
of 2 499

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ እና አክሱም ዩኒቨርስቲ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ህዳር 30 እና ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን በዩኒቨርስቲው የተመደቡት የፕሮግራም ዝርዝሮችና የመመዝገቢያ ቦታ እንደሚከተለው መሆኑን እናሳስባለን። ሀ. የምዝገባ ቦታ፡- ዋናው ግቢ 1. English (BED) 2. Anthropology 3. Journalism ለ. የምዝገባ ቦታ፡- ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ግቢ 1. Civil Enginnering 2. Electrical and Computer Enginnering 3. Mechanical and Industrial Enginnering 4. Manufacturing Enginnering 5. Information Technology (BED) ሐ. የምዝገባ ቦታ፡- ግብርና ኮሌጅ ግቢ 1. Food Science and Post-Harvest Technology መ. የምዝገባ ቦታ፡- ወንዶገነት ደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ግቢ 1. Soil Resource and Watershed Management 2. Natural Resource Economics and Policy ሠ. የምዝገባ ቦታ፡- አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክ ኮሌጅ ግቢ 1. Economics 2. Logistics and Supply Chain Management 3. Cooperatives ማሳሰቢያ፤ ተማሪዎች ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ 1ኛ. የመስናዶ ፈተና ያለፋችሁበት ሰርተፍኬት 2ኛ. የ10ኛ ክፍል ያለፋችሁበት ሰርተፍኬት 3ኛ. የዩኒቨርስቲ መታወቂያ 4ኛ. በእጃቸው ላይ የሚገኝ “Grade Report” እና “Registration Slip” 4ኛ. የሌሊት አልባሳት 5ኛ. 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ መምጣት የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እያሳሰብን፤ የመግቢያ ጊዜ በተጠቀሰው ቀን ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ እና ከተጠቀሱት ፕሮግራሞች ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
4 755
18
በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ትምርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ እና ወደ ኦደቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 23 እና ህዳር 24/2014 መሆኑ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ዩንቨርሲቲው በምትሄዱበት ወቅት ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች አሟልታቹህ እንድትገኙ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል። ፨የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰርተፍኬት ፨ከመጣችሁበት ዩንቨርሲቲ የምዝገባ ስሊፕ እና የግሬድ ሪፖርት ፨ከመጣችሁበት ዩንቨርሲቲ የተማሪነት መታወቂያ ካርድ ፨አራት ጉርድ ፎቶ ግራፍ @NATIONALEXAMSRESULT
4 328
3
የሰሜኑ ጦርነት በትምህርት ላይ ያደረሰው ጉዳት፦ • በአማራ ክልል 1 ሺህ 660 ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። • 277 ትምህርት ቤቶች እና ሁለት የመምህራን ኮሌጆች ሙሉ በሙሉ ውድመት ደርሶባቸዋል። • 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ሆነዋል። 47 ሺህ መምህራን ደግሞ ከሥራ ተፈናቅለዋል፡፡ • በአፋር ክልል እስከ አሁን 455 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውመዋል፡፡ • መንግስት የጉዳት መጠኑንና በቀጣይ ለሚሠራው ሥራ ጥናት እያደረገ ይገኛል፡፡ ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት @NATIONALEXAMSRESULT
4 207
1
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የተቋሙ የአካዳሚ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፕ/ር መንግስቱ ኡርጌ ገልጸዋል። ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች በቅድመ ምረቃ የትምህርት መስክ ከመጀመሪያ ዓመት ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ከአንደኛ ዓመት በላይ የሆኑት ተማሪዎች በነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበረው የትምህርት አይነት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ መሆኑና አለመሆኑን የመለየት ሥራ እየተሠራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እስከሚያደርግ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ም/ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
5 143
6
ከመቀሌ, ከአክሱምና ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በጋዜያዊነት ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚፈፀመዉ በመጪዉ ህዳር 27 እና 28/2014ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል። © JUSU @NATIONALEXAMSRESULT
5 035
7
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “የሀገርን ውለታ ክደዋል”ያላቸውን የቀድሞ ተመራቂዎቹን ዲግሪ ሊነጥቅ እንደሚችል አስጠነቀቀ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞም ይሁን የአሁን ምሁራን “የጀመሩትን ሀገርን የማዳን ትግል” እንደሚደግፍ አውቀው “እስከመጨረሻው እንዲፋለሙ”ም ጥሪ አቅርቧል፡፡ Al ain @NATIONALEXAMSRESULT
5 539
4
"በአገራችን አሁን ላለው ችግር መነሻው የትምህርት ሥርዓቱ ደካማ በመሆኑ ነው" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በአገራችን አሁን ያለው ችግር መነሻ የትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያለው ክፍተት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ ውይይቱም የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ወደ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንዲያድግ በመንግስት መወሰኑን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲን መልሶ በጠንካራ መሰረት ላይ ማደራጀት በሚቻልበትና እና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማድርግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ በውይይቱም አሁን በአገሪቱ በተለያየ መንገድ የሚስተዋሉ ችግሮች ዋና መነሻው የትምህርት ሥርዓቱ መውደቅ መሆኑን ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡ በትምህርት ሥርዓቱ ያለውን የትምህርት ጥራት መሰረታዊ ችግሮችን ከፖለቲካ አስተሳሰብ በማላቀቅና በጥልቀት በመረዳት ለመፍትሔው ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበትም ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነ መስቀል ጠና (ዶ/ር) ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከጅምሩ ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት ድረስ የነበሩ ስኬቶችና ከአደረጃጀት አንፃር የነበሩ ከፍተኛ ተግዳሮቶችን ለሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በመምህራን ሙያ ልማት ቀዳሚ ዩኒቨርሲቲ እንደነበርም ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በአዲስ መልክ የተቋቋመው በትምህርት ሥርዓቱ ያሉ መሰረታዊ ችግሮችና ውድቀቶች ከሥር መስረቱ በማጥናት ለመፍታት እንዲያስችል ነው ብለዋል፡፡ አሁን እንደ አገር በትምህርት ሥርዓቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሥርዓተ ትምህርቱን ማስተካከል፣ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በየትምህርት ተቋማቱ ሟሟላትና በየደረጃው ያሉ መምህራንን አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ ዩኒቨርሲቲው አሁን የተሰጠውን ተልዕኮ ሊመጥን የሚችል ራዕይና አደረጃጀት ቀርፆ ወደ ተግባር መግባት እንዳለበትም አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ _______________ @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
5 967
0
ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አሕመድ በጦር ግንባር ሆነው መልዕክት አስተላልፈዋል። © OBN/FBC 18.2 MB @NATIONALEXAMSRESULT

file

6 090
50
ሀገር አፍራሹን የህወሓት ቡድንን የሚደግፉ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ምሁራን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳሰበ ******************* ሀገር አፍራሽ የሆነውን የህወሓት ቡድንን የሚደግፉ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ምሁራን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ካልሆነ ግን ዲግሪያቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል። ዩኒቨርሲቲው አሸባሪው ህወሓት በንፁሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ እና ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገውን ሴራ አውግዟል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች አሸባሪውን ህወሓት እና ደጋፊዎቹን በማውገዝ ከኢትዮጵያ ጎን መቆማቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በተቃራኒው ግን ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለሀገር የዋለውን ውለታ በመካድ ከሀገር አፍራሽ ሽብርተኞች ጋር የተባበሩ ጥቂት ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቅሷል። እነዚህ ከሃዲዎች ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ዲግሪያቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝቧል። EBC @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
6 224
7
#WolaytaSodoUniversity ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ህዳር 27 እና 28 /2014 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ዛሬ አሳውቋል። በተጨማሪ ፦ ከመቐለ፣ ከአክሱም እና ከወልዲያ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በጊዜያዊነት ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች መግቢያ ህዳር 27 እና 28 /2014 ዓ/ም መሆኑ ተገልጿል። @NATIONALEXAMSRESULT
5 909
12
አሜሪካ በኢትዮጲያ የምታደርገውን ጣልቃገብነት ተቃውሞ ሰልፍ በአሜሪካ ኤምባሲ በር ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል። @NATIONALEXAMSRESULT
6 693
4
የፈተና ስርቆት ለትምህርት ጥራት እንቅፋት ከሆኑት ምክያቶች አንዱ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጠቀሱ። በኢትዮጵያ ሦስተኛ ክፍል ከደረሱ አምስት ተማሪዎች ውስጥ ማንበብ የሚችሉት ሁለቱ ብቻ መሆናቸውንና እንዲሁም ካሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 89 በመቶዎቹ ከደረጃ በታች እንደሆኑ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሐብት ልማት፣ የሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ከትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባካሄዱት የትውውቅ መድረክ ላይ ነው። ሰብሳቢው የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራም ለጥራት የነበረው ትኩረት አነስተኛ ስለነበር በቀጣይ የትምህርት ጥራትንና ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ማፍራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመድረኩ የትምህርት አስተዳደርና የመምህራን የብቃት ችግር፣ የፈተና ስርቆት፣ የምመህራንና የተማሪዎች ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና አካባቢያዊ ችግሮች ለትምህርት ጥራት መሠረታዊ እንቅፋቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። (HOPR) @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
7 148
5
ሳይንስን ለመማር እና ለማስተማር የሚጠቅሙ 5 የነፃ ድህረገፆች 1👉Scitable ዝንባሌዎ ስለ ጅኔቲክስ እና ስለሮቦት ሳይንስ ማወቅ ከሆነ እንግዲያውስ ሳይቴብል ለርሶ የተከፈተ ድህረገፅ ነው፡፡ ይህ ድህረገፅ በማበብ ብቻ በግልዎ መማር የሚችሉበት ሲሆን ልክ እንደ ት/ቤት በጋራም ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በኦንላይን ክፍል ውስጥ መማር ይችላሉ፡፡ ፡ 2👉 iTunes U ይህ ድህረገፅ ከ 600 በላይ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች የሚደገፍ ሲሆን ዓለም ላይ አሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎችን ማለትም የስታንፎርድ፣ የያሌ እና የኤም አይቲን ዩኒቨርሲቲዎችን የማስተማሪያ መፅኃፎችና ሌክቸር ኖቶች ሰብስቦ ይዟል፡፡ ይህ ድህረገፅ በተለይ ለመምህራን ትልቅ እፎይታን ያመጠጣ ሲሆን የማስተማሪያ መፅሀፎች፣ ቪዲዮዎችን እና ፈተናዎችን አካቶ ይዟል፡፡ 3👉Space.com ዝንባሌዎ በምድር ወጣ ስላሉ ጉዳዮች ከሆነ እንግዲያውስ ይህ ድህረገፅ የእርስዎ ነው፡፡ በዚህ ድህረገፅ ውስጥ ስለ ሌሎች ዓለማት ስለፕላኔቶች እና ከነርሱ ስለተያያዙ ሌሎች ነገሮች በሰፊው ይተነተናል፡፡ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን፣ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን "This Week in Space"(ሳምንቱ በስፔስ ውስጥ) በሚለው ፕሮግራማቸው ውስጥ ያስቃኛሉ፡፡ 4👉Scientific American ስለጤና፣ ስለዝግመተለውጥ፣ እና ስለ ተለያዩ የሳይንስ ክፍሎች በሰፊው የሚተነተንበት እና ይበልጡን ለመማር ማስተማር ሂደት እንዲመች ተደርጎ የተሰራው ይህ ድህረገፅ በአሜሪካን ውስጥ በሳይንስ ምንጭነቱ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆነው ከአሜሪካን ሜጋዚን ጋር በጥምረት የሚሰራ ሲሆን ወቅታዊ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩም ያቀርባል፡፡ 5👉PhysicsCentral የፊዚክስ አምሮትዎን የሚቆርጥና በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ፈጣን አዕምሮ ባለቤቶች የሚመች ድህረገፅ ነው ፡፡ በ American Physical Society ተዘጋጅቶ የሚቀርበው ይህ ድህረገፅ ተመራማሪዎችን እና ተማሪዎችን የሚያገናኝ መድረክ ነው፡፡ Source- Muhammed Computer Technology @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
6 830
79
የመዲናዋ ትምህርት ቤቶች በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ። የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በከተማ መስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ያሰባሰበውን 100 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቁሳቁስ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አስረክቧል። በድጋፉ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስና የመማሪያ ቁሳቁስ የተካተቱ ሲሆን በአፋር እና በደብረብርሃን ለሚገኙ በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ይውላል ተብሏል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
5 841
1
ሀዋሳ፣ መቱ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች የኮቪድ-19 ክትባትን ለተማሪዎቻቸው፣ ለመምህራን እና ሰራተኞቻቸው መስጠት ጀምረዋል። የኮቪድ-19 ክትባት ከኅዳር 13 እስከ 22/2014 ዓ.ም በዘመቻ መልክ በመላ ሀገሪቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል። @NATIONALEXAMSRESULT
6 146
6
አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2013 ዓ.ም የገቡ የሁሉም ዲግሪ ተማሪዎች የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ ኅዳር 29 እና 30/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። ዘግይተው ለሚመጡ ተማሪዎች ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል ተብሏል። ታህሳስ 04/2014 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ያለው ኮሌጁ፤ ከተገለጹት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ገልጿል። @NATIONALEXAMSRESULT
5 798
1
#DillaUniversity በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ኅዳር 20 እና 21/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዲላ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። ተመዝጋቢ ተማሪዎች የ10 እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት እንዲሁም ትራንስክሪፕት ኦሪጅናልና ኮፒውን ሊይዙ እንደሚገባ ተገልጿል። ተማሪዎች በኦዳያ ግቢ እና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል። ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። @NATIONALEXAMSRESULT
5 442
1
በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲከተቡ የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ --------------------------------- የትምህርት ሚኒስቴር ከ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ_19 ክትባት በትምህርት ቤቶች ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል። የጤና ሚኒስቴር በትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ ለሆኑ ህፃናት የኮቪድ-19 ክትባትን እየሰጠ ነው ። ነገር ግን በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ በሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት የቤተሰቦች ፍቃደኝነት አናሳ መሆኑ ተስተውሏል። ይህንን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ በትምህርት ቤቶች የሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት በተፈለገው ደረጃ እንዲደርስ የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል። ስለዚህም ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሰጠውን ክትባት እንዲወስዱ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል። በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት በትምህርት ዘርፉ ላይ ሊከሰት የሚችለውን የኮቪድ-19 ስርጭት እንደሚቀንሰውም ተናግረዋል። የኮቪድ 19 ክትባት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘመቻ መልክ እየተሰጠ ይገኛል። MoE @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
6 559
4
ውድ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የህዳር ወር የአምቡላንስ ተረኛ ከላይ ባለው መሰረት እንድትጠቀሙ እናሳስባለን። ===== Dabaree Ambulaansii kan ji'a Sadaasaa sagantaa bahee kanaan akka fayyadamtan isin yaadachiifna. © metu university students union @NATIONALEXAMSRESULT
7 523
8
#ሰበርዜና #BREAKINGNEWS ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ከነገ ጀምሮ ወደግንባር ሊዘቱ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነገ ጀምሮ ወደ ጦርነቱ አውደ ግንባር ሄደው ሊዘምቱ ሲሆን የአመራር ቦታዎችን ከግንባር የቀሩ ሃላፊዎች እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ከላይ ተያይዟል። @NATIONALEXAMSRESULT
8 867
53
7
0
#ሰበርዜና #BREAKINGNEWS ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ከነገ ጀምሮ ወደግንባር ሊዘቱ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነገ ጀምሮ ወደ ጦርነቱ አውደ ግንባር ሄደው ሊዘምቱ ሲሆን የአመራር ቦታዎችን ከግንባር የቀሩ ሃላፊዎች እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ከስር ተያይዟል። @NATIONALEXAMSRESULT
189
3
ሰበር ዜና… #BreakingNews
7 784
2
ዋዜማ ራዲዮ- በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን በተባረሩት የሱዳን ሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ የተጣለው የቤት ውስጥ ቁም እስር ዛሬ ከቀትር በኋላ እንደተነሳላቸው የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርኻን እና ሐምዶክ ትናንት በደረሱበት ስምምነት መሠረት ሐምዶክ ወደ ጠቅላይ ሚንስትርነታቸው ተመልሰው የሽግግር ሂደቱን እንዲመሩ እና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተሰምታል። ጀኔራል ቡርሃን፣ ሐምዶክ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ታጣቂ ቡድኖች ከመጋረጃ ጀርባ የደረሱበት አዲሱ የሽግግር ስምምነት ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ከደቂቃዎች በፊት ሐምዶክ በፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት ተገኝተው የጠቅላይ ሚንስትርነት ሥልጣናቸውን እንደገና በይፋ ተረክበዋል። [Wazema] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
9 002
7
ቢሮው በወቅታዊ ጉዳዩች ላይ ከመምህራን ጋር ውይይት እያደረገ ነው ************** የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ጉዳዩች ዙሪያ ከመምህራን ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡ በመድረኩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ2200 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ መምህራን ተሳታፊ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ እና የክፍለ ከተሞች ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡ በመድረኩ መምህራን ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። በመድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በአቶ ዘላለም ሙላቱ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
8 622
6
#WerabeUniversity ከመቐለ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ኅዳር 20 እና 21/2014 ዓ.ም መሆኑን ወራቤ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች ኅዳር 22/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በማይሰጥ የትምህርት መስክ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ለትምህርት ሚኒስቴር በማመልከት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ማድረግ እንዳለባቸው ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። @NATIONALEXAMSRESULT
6 991
5
#MaddaWalabuUniversity መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በጤና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 229 ተማሪዎች አስመርቋል። ተመራቂዎቹ በሚድዋይፈሪ፣ ነርሲንግ፣ ፐብሊክ ሄልዝ እና ሜዲካል ላቦራቶሪ ትምህርታቸውን በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ተከታትለዋል። በዩኒቨርሲቲው ጎባ ካምፓስ የተመረቁት ተማሪዎቹ ከ4 እስከ 7 ዓመታት ስልጠናቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል። ከዛሬ ተመራቂዎች 86ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው። @NATIONALEXAMSRESULT
7 515
2
መንግስት ያለበቂ ምክንያት የመማር ማስተማር ስራቸውን ላቆሙ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ! የኢፌዴሪ መንግስት ያለበቂ ምክንያት የመማር ማስተማር ስራቸውን ላቆሙ ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ የሚገኙ የማሕበረሰብ እና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች በሀሰተኛ መረጃዎች ጫና እንዲያድርባቸው እና የመማር ማስተማር ስራቸውን እንዲያቆሙ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያስታወሱት ሚኒስትር ድኤታዋ ይህም ጥረት አንዳንዶቹ ስራቸውን እንዲያቆሙ እንዳደረገ ገልፀዋል። የትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ምልከታ እና ከአንዳንድ ወላጆችም በቀረበ ቅሬታ መሰረትም 7 የማሕበረሰብ እና 19 ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች መማር ማስተማር ማቆማቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር ለ3 ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ይፋዊ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መፃፉንም ነው የገለፁት።ደብዳቤው የደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ሳንፎርድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት፣ ቤንግ ሀም ትምህርት ቤት እና አይሲኤስ መሆናቸውን ሚንስትር ዴኤታዋ አስታውቀዋል። Via Ebc @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
7 296
4
የምትማሩት ፊልድ ከሌለ ለትምህርት ሚኒስቴር አመልክቱ! ከመቐለ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ኅዳር 20 እና 21/2014 ዓ.ም መሆኑን ወራቤ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች ኅዳር 22/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በማይሰጥ የትምህርት መስክ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ለትምህርት ሚኒስቴር በማመልከት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ማድረግ እንዳለባቸው ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። @NATIONALEXAMSRESULT
7 962
7
"የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወደ ታህሳስ ወር ተራዝሟል።" የጤና ሚኒስቴር በኅዳር 2014 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ የነበረው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወደ ታህሳስ ወር መራዘሙን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የፈተናው ምዝገባ ለሁለት ጊዜ በመራዘሙ ምክንያት ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ወደ ታህሳስ መሸጋሸጉን በሚኒስቴሩ የብቃት ምዘና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አበባው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። የምዘና ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከጥቅምት 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። የግል አመልካቾች የትምህርት ማስረጃ ሕጋዊነትና ትክክለኛነት ማረጋገጫ እንዲያገኙ ለማስቻል ምዝገባው ሁለት ግዜ መራዘሙን አስታውሰዋል። ተማሪዎች ለሙያ ብቃት ምዘና ፈተናው ዝግጅት ተጨማሪ ጊዜ መጠየቃቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በመሆኑም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተናው በታህሳስ ወር እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።            @nationalexamsresult
Show more ...
8 508
14
#ArbamichUniversity በ2014 የትምህርት ዘመን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ #አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት የሚደረግበት ቀን #ኅዳር 12/2014 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባ የሚካሄድበት ቀን #ኅዳር_13 እና 14/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል። ፨መደበኛ ትምህርት የሚጀመረው ኅዳር 15/2014 ዓ.ም በመሆኑ፡- •አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ •አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና የስፖርት ትጥቅ •ስምንት 3 x 4 የሆነ ጉርድ ፎቶ እና •ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀናት ውጭ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እንገልጻለን፡፡ ©የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
10 139
20
#ማስጠንቀቂያ‼️ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀንአ ያደታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። መመሪያው ሰላማዊ እና ፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመለየት፣ የሐሰት መታወቂያ የሚሰጡ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለመለየት እንዲሁም የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ሆነው ያለ አግባብ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚሰጡትን ለመቆጣጠር ያግዛል ብለዋል። ዶ/ር ቀነዓ ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት ያስቀጣል ያሉ ሱሆን ከህዳር 6 /2014 እስከ ህዳር 15/2014 በሚቆየው የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ሂደት ማህበረሰቡ መታወቂያ ማውጣት እንዳለበት ተናግረዋል። የሎጂስቲክ እና የሰው ኃይል ቅድመ ዝግጅት ተካሂዶ አርብ ህዳር 10/2014 በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ መታወቂያ ለማህበረሰቡ ለመስጠት ዝግጅት መጀመሩም ተገልጿል። @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
9 477
23
ከትግራይ ክልልና ወልድያ ዪኒቨርሲቲዎች ወደ ዋቸሞ ዪኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ኀዳር 22 እና 23 2014 ዓ.ም መሆኑን ዪኒቨርሲቲው አሳውቋል። @NATIONALEXAMSRESULT
8 473
8
#JimmaUniversity ተራዝሞ የነበረው የ2014 የትምህርት ዘመን ምዝገባቸው በመጪው ህዳር 20 እና 21/14 የሚካሄድ ስለሆነ ትምህርታችሁን በምትከታተሉባቸው የኮሌጅ ወይም የኢኒስቲትዩት ሬጂስትራር ጽህፈት ቤቶች በግንባር በመቅረብ ምዝገባችሁን እንድትፈፅሙ ተብላቹሃል። #ጅማ_ዩኒቨርሲቲ @nationalexamsresult
9 309
17
#JigJigaUniversity የጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ነባር የሶስተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ከህዳር 15 እስከ ህዳር 17/2014 ድረስ ሲሆን የአንደኛ ዓመት የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከህዳር 23 እስከ ህዳር 25/2014 ድረስ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አስታውቋል። በተጨማሪም በጊዜያዊነት በትምህርት ሚኒስቴር ከመቀሌ ፣ከአክሱም እና ከወልድያ ዩንቨርሲቲዎች ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹህ ተማሪዎች ከህዳር 23 እስከ ህዳር 25/2014 ድረስ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል። @nationalexamsresult
8 614
12
Jimma University ማስተካከያ ተደርጓል የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ግቢ መመለሻ ቀን ህዳር_ 20 እና ህዳር 21/2014 እንደሆነ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የግቢውን ሪጂስትራር ዋቢ በማድረግ አሳውቋል። @nationalexamsresult
9 560
53
የሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ት/ ቤት ከሳምንት በኋላ በተማሪ ወላጆችና በኢትዮጵያውያን አስተማሪዎቹ ጥረት ዛሬ ተከፍቷል። የተፈጠረው ነገር ይሄ ነበር ; አሜሪካዊቷ የትምህርት ቤቱ ሀላፊ" ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነገር ተረጋግተን /ትምህርት ማስተማር አንችልም ።ሳምንትን ዘግተን እንየው ።በኦንላየን ልጆቹን እናስተምር" በማለቷ ት/ ቤቱ ባለፈው ሳምንት የተዘጋ ሲሆን የወጭ ዜጋ ያላቸው አብዛኞቹ አስተማሪዎችም ከሀገር ወጥተዋል። በዚህ የተበሳጩት ወላጆችና ኢትዮጰያዊ የት/ ቤቱ አስተማሪዎች " ይሄ ሀገርን ማሸብር ነው ።ት/ት ለማቆም የሚያበቃ ነገር የለም በማለት ለት/ ቤቱም ለት/ት ሚኒስቴርም ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሳምንት የተዘጋው ት/ቤት ዛሬ ተከፍቷል ። ከ400 በላይ የት/ቤቱ ተማሪዎች ውስጥ ከግማሹ በላይ ዛሬ መምጣቱን ፊደል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል። @nationalexamsresult
Show more ...
8 667
5
እድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያን በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና አሰታወቀ። ከዛሬ ሰኞ ህዳር 6 እስከ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያ በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንደሚችሉ የቢሮ ሃላፊው ዶክተር ዮሃነስ ጫላ አስታውቋል። ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት በትላልቅ የገበያ ቦታዎች ፣ ሞሎች ፣ በባንኮች ፤ በትራንሰፖርት መናህሪያዎች ፤ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች የተመረጡ ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ እስከአሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት የተሰጠ ሲሆን ለ10 ቀናት በሚካሄደው የክትበት ዘመቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የክትባት ቡድኖች መደራጀታቸውን ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ገልጸዋል፡፡ የኮቪድ- 19 ክትባት በመከተብዎ • በበሽታው የመያዝ እድሎን ይቀንሳሉ • ቤተሰቦን እና የሚወዳቸውን ሰዎች ለበሽታ የማጋለጥ እድሎን ይቀንሳሉ • የበሽታውን ስርጭት መግታት ፣አዳዲስ እና አደገኛ የኮቪድ 19 ዝርያዎች እንዳይፈጠሩ ደርጋሉ ፡፡ Via AAPS @nationalexamsresult
Show more ...
8 938
6
የዮኒቨርስቲዎች ድረገፅ ❓ ስለ ኢትዮጵያ ዮኒቨርስቲዎች ምን ማወቅ ይፈልጋሉ ❓ ስለሚሰጡት ፊልድ ስለ ግቢው ዕይታ በፎቶ ስለሚጠሩበት ቀን እና ሌሎችም መረጃዎች በዮኒቨርስቲያችሁ ዌብሳይቶች ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ ። ከዚ በታች የ45ቱም ዮኒቨርስቲዎች ድህረገፁ ይገኛል ፤ በማስፈንጠሪያው የምትፈልጉትን መረጃ ማግኘት ትችላችሁ ። Acronym and Website ፦ 1.AASTU http://www.aastu.edu.et/ 2. ASTU http://www.astu.edu.et/ 3.Addis Ababa University (AAU) http://www.aau.edu.et/ 4. Adigrat University (AGU ) http://www.adu.edu.et/ 5. Ambo University (AU) http://www.ambou.academia.edu/ 6. Arba Minch University (AMU ) http://www.amu.edu.et/ 7.Arsi University ( ARU ) https://www.arsiun.edu.et/ 8 ASOSSA UNIVERSITY(ASU) http://www.asu.edu.et/ 9.Axum University (AXU) http://www.aku.edu.et/ 10 Bahir Dar University ( BDU) http://www.bdu.edu.et/ 11. BONGA UNIVERSITY (BU) http://www.bongau.edu.et/ 12 BULE HORRA UNIVERSITY (BHU) http://www.bhu.edu.et/ 13 DEBARK UNIVERSITY (DKU) http://www.dku.edu.et 14 Debrebirhan University (DBU- http://www.dbu.edu.et/ 15 Debremarkos University (DMU) http://www.dmu.edu.et/ 16 DEBRETABOR UNIVERSITY (DBTU) http://www.dtu.edu.et/ 17 DEMBI DOLO UNIVERSITY (DeDU) http://www.dedu.edu.et 18 Dilla University( DU) http://www.du.edu.et/ 19 Dire Dawa University ( DDU ) http://www.ddu.edu.et/ 20 Gambella University (GMU) http://www.gmu.edu.et 21 Gondar University( GU) http://www.uog.edu.et/en/ 22 Haramaya University (HRU) http://www.haramaya.edu.et/ 23 Hawassa University (HWU) http://www.hu.edu.et/hu/ 24 INJIBARA UNIVERSITY( IU) http://www.inu.edu.et/ 25 Jigjiga University (JGU https://www.jju.edu.et/) 26 Jimma University (JU) https://www.ju.edu.et/ 27 JINKA UNIVERSITY (JNU) http://www.jnu.et/ 28 Kebri Dehar University (KDU) http://www.kdu.edu.et/ 29 Kotebe Metropolitan University ( KMU) http://www.kmu.edu.et/ 30 Meda Welabu University (MWU) http://www.mwu.edu.et/ 31 Mekelle University( MU) http://www.mu.edu.et/ 32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY ( MAU )http://www.mau.education/ 33 METU UNIVERSITY (MEU) http://www.meu.edu.et/ 34 Mizan-Tepi University (MTU) http://www.mtu.edu.et/ 35 Oda Bultum (OBU) http://www.odabultum.edu.et 36 RAYA UNIVERSITY( RU) http://www.rayu.org/ 37 Selale University (SLU) http://www.seu.edu.et 38 Semera University( SU) https://www.su.edu.et/ 39 WACHAMO UNIVERSITY (WCU) http://www.wachemouniversity.academia.edu/ 40 Welketie UNIVERSITY (WKU) http://www.wku.edu.et 41 WERABE UNIVERSITY ( WRU) http://www.edu.et/ 42 Wolayita Sodo University (WSU) http://www.wsu.edu.et 43 Woldiya University (WDU) http://www.fh2web.academia.edun 44 Wollega University( WU ) www.wollegauniversity.edu.et 45 Wollo University (WOU) http://www.wollo.academia.edu @nationalexamsresult
Show more ...
Home Page - Addis Ababa Science and Technology University
10 794
233
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 302 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው። ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። ከዛሬዎቹ ተመራቂዎች 237ቱ የጤና ሳይንስ መደበኛ መርሃ ግብር ተማሪዎች ናቸው። @NATIONALEXAMSRESULT
9 379
7
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰኞ ተፈትና ማክሰኞ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለችው ተፈታኝ ፈተናዋን ሙሉ በሙሉ ተፈትና አጠናቃለች በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጀመረችበት በሁለተኛው ቀን አንድ ሴት ተፈታኝ ወንድ ልጅ በሠላም ከመገለገሏም በላይ ፈተናዋን ሙሉ በሙሉ ተፈትና አጠናቃለች፡፡ በሁለት ፈተና ጣቢዎች ወንድ 627 ሴት 429 ሲሆን በድምር ከ1 ሺህ 50 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል:: ከእነዚህ ተፈታኝ ሴት ተማሪዎች መካከል ወ/ሮ ትዕግስት ጎኣ አንዷ ስትሆን ማክሰኞ ጠዋት ወደ ፈተና አደራሽ ከመግባቷ በፊት 1 ሰዓት ልዩነት በቦዲቲ ከተማ ጤና ጣቢያ ውስጥ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች:: ወ/ሮ ትዕግስት ክስተቱን ተቋቁማ ፈተና ሙሉ በሙሉ የተፈተነች ስትሆን የልጇን ስም ከሁኔታው ጋር በተመሳሰለ ሁኔታ ለመሰየም ማሰቧንም ገልጻለች:: የክስተቱ ግጥምጥሞሽ አስገራሚ ቢሆንም ከዓላማዬ ሊያስቀረኝ አይችልም በማለት ተናግራ ፈተናዬን ተረጋግቼ እንድፈተን ከፈታኞችና ከሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ከጤና ባለሙያዎች ስለተደረገልኝ እንክብካቤ አመሰግናለው ብላለች:: በአሁኑ ሰዓት ወላዷና ልጇ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ:: @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
9 163
13
ለህወሓት ቡድን መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ ስድስት ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ❗️ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ከሰሜን ወሎ አካባቢ የመጡ ተማሪዎችን ለአንድ አመት ለማስተማር ቃል በተገባው መሰረት 10 ሺ ተማሪዎች ወደ ከተማው መግባታቸው ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ለሽብርተኛው የህወሓት ቡድን መረጃ ሲያቀብሉ የተገኙ ስድስት ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልፆል፡፡ የተያዙት ተማሪዎች ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ ፣ከሞጣ፣ከፍናን ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሲሆኑ  በሂሳብ ደብተራቸው ገንዘብ ተቀምጦላቸው የሚንቀሳቀሱ እንደሆኑን እና  ከተያዙት ውስጥ አንዱ ተማሪ ተቆጣጠሪ ሆኖ የተሰጣቸውን ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን የፖሊስ መረጃ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ምንዋጋው አንዷለም በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት አራቱ ተማሪዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ ሲያዙ ሁለቱ ደግሞ በሌላ ወረዳ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ብስራት ሬድዮ @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
7 774
3
#Ethiopia ባለፉት ቀናት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት #ቴሌግራም እና #ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ትላንት ፈተናው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል። በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው። @NATIONALEXAMSRESULT
7 583
6
የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል። በመጀምሪያ ዙር ፈተና 565ሺ 255 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 96 ከመቶ ነው። የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተናግረዋል። በ2ሺ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው በዚህ ፈተና፣ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617ሺ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565ሺ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ዘርፉ ሰራተኞችና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል። "በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ፈተናዎች ተሰርቀው ወጥተዋል የሚባለው ጉዳይ እውነት ነወይ" ተበለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ምርምርራዎችና ትንተናዎች ተደርገው አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ምንም የሚያስጋ ነገር የለም ብለዋል። በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሏል።
Show more ...
6 997
5
ለ12 ዓመታት አንገታቸውን ደፍተው ፡ ብዙ ነገር እያማራቸው ነገር ግን ዓላማቸውን ይዘው እዚህ የደረሱ ተማሪዎች ልፋት በደቂቃ ውስጥ ባዶ ሲሆን እና ዓላማ በሌላቸው ከንቱዎች ፈተና እንደ ወፍጮ ቤት ቆሎ እየተዘገነ ሲሰረቅ እና ሲሰራጭ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንዳልተፈጠረ ሲክድ እና ደረቅ መከራከሪያ ሲያቀርብ የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ትውልድ መግደል ይብቃ❗️ @NATIONALEXAMSRESULT
7 152
17
በደቡብ ክልል አራት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው በመገኘታቸው ፈተናቸው ተሰርዟል። በደቡብ ክልል 90 ሺህ 33 ተማሪዎች በ516 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ገልጸዋል። 2 ሺህ 373 መምህራን እና 595 ሱፐርቫይዘሮች ፈተናውን እየተቆጣጠሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል። ብሔራዊ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ ለመግባት መሞከር እና የማርፈድ ችግሮች መታየታቸውን ጠቁመዋል። በክልሉ አራት ተፈታኞች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው በመገኘታቸው ፈተናቸው የተሰረዘ ሲሆን በሕግም ተጠያቂ እንደሚሆኑ ኃላፊው አረጋግጠዋል። [ኢፕድ] @NATIONALEXAMSRESULT
7 617
10
8፤ በኢትዮጵያ ከትናንት ጀምሮ የተቋረጡት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዛሬም አገልግሎት መስጠት እንዳልጀመሩ ታውቋል። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል መባሉን ተከትሎ የተቋረጡት፣ ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ኢንስታግራም እና በተወሰነ ደረጃ የዋትስአፕ እና ቴሌግራም ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ናቸው። ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ መቋረጣቸውን ያሳወቀው የሀገራት ኢንተርኔት ፍሰት የሚከታተለው ኔትብሎክስ የተሰኘው ድርጅት ነበር [Wazema] @NATIONALEXAMSRESULT
6 654
11
ከ2 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎች በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ፈተናን እየወሰዱ ነው። ብሔራዊ ፈተናው በአራት የፈተና ጣቢያዎች ያለምንም ጸጥታ ችግር እየተሰጠ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ሀለኔ ሀሰን ገልጸዋል። ፈተናው ያለምንም ጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። [DDMMA] @NATIONALEXAMSRESULT
6 355
0
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር በኋላ ይሰጣል። በአማራ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያልወሰዱ ከ36 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከአንድ ወር በኋላ ለፈተና ይቀመጣሉ። በክልሉ በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ትናንት በተጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አልተቀመጡም። "የተማሪዎቹን የስነ ልቦና ዝግጅት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሌላ ፈተና ከአንድ ወር በኋላ እንደሚሰጥ" የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳውቋል። ተማሪዎቹ ከመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ጋር የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚደረግላቸው የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ተናግረዋል። ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ዋግምራ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ሰሜን ጎንደር (ጠለምት እና አዳርቃይ) እንዲሁም ሰሜን ሸዋ (አጣዬ፣ ግሸርአባሌ፣ ኤፍረታና ግድም፣ አንጾኪያ) በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያ ዙር ፈተናው የማይሰጥባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ናቸው። [ሸገር ኤፍኤም] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
5 704
6
#EthiopiaCheck Update በኢትዮጵያ የፌስቡክ፣ ፌስቡክ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል! በኢትዮጵያ የፌስቡክ እና ፌስቡክ ሚሴንጀር እንዲሁም ቴሌግራምና ዋትስአፕ የተወሰኑ አገልግሎቶች መቋረጣቸውን ተመልክተናል። ኔትብሎክስ የተሰኝዉ አለም አቀፉ የኢንተርኔት ክትትል ተቋምም ይህን በመረጃ አስደግፎ አውጥቷል። አገልግሎቶቹ ዛሬ ከሰአት ጀምሮ እንደተቋረጡም ተቋሙ በድረ-ገጹ አስነብቧል። የአገልግሎቶቹ መቋረጥ ምክንያትም “የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተሰርቆ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቋል” የሚሉ መረጃዎች መዘዋወር ከጀመሩ በኋላ እንደሆነም ተገልጿል። ይሁንና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰአት በሰጡት መግለጫ የፈተናው ሂደት በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸው "ምንም ዓይነት ፈተና፣ በማንም፣ በምንም፣ በየትም ቦታ አልተሰረቀም" ብለዋል። ነገር ግን ፈተናውን ፎቶ በማንሳት የመኮረጅ ሙከራ ያደረጉ አራት ተማሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ከኢመደኤ እና ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካም። አሁንም ሙከራ እያረግን ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ስናገኝ ይዘን እንቀርባለን። [Ethiopia Check] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
589
1
'' ፈተናውም በማንም፤ በምንም፤ በየትም አልተሰረቀም '' - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትሩ ር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ መሰጠት የተጀመረው የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ቲክቫህ መግለጫውን ተከታትሏል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ በመግለጫቸው ከሞላ ጎደል ፈተናው በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸዋል። ''ፈተናውም በማንም በምንም በየትም አልተሰረቀም'' ሲሉ ገልጸዋል። በዛሬው ዕለት 2 ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል 2 ተማሪዎች በደቡብ ክልል በስልካቸው ፎቶ አንስተው ''ኤሌክትሮኒክ ኩረጃ'' ሊፈጽሙ ሲሉ መያዛቸውን ጠቅሰዋል። ተማሪዎቹ ፈተና ክፍል ከገቡ በኋላ ፈተናውን በፎቶ አንስተው ሲላላኩ መያዛቸው ነው የተጠቀሰው። ይህም ተማሪዎች ለፈተና ከገቡ በኋላ የተለቀቀ በመሆኑ ፈተናው ተሰርቋል ሊባል አይችልም ተብሏል። ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ከፌደራል ጀምሮ እስከታች ባሉ የኮማንድ ፖስቱ አባላት ያደረጉት አስተዋጽኦ የተሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ትብብሩ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተማሪዎች የሞባይል፣ የስማርት ሰዓትም ሆነ ሌሎች ዲጂታል ኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት እንደማይፈቀድ አጽንኦት ተሰጥቶ ተገልጿል። [tikvah ethiopia] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
885
0
#WollegaUniversity ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በሴሚስተር ዕረፍት ላይ የሚገኙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አሳውቋል። የቀጣይ ሴሚስተር ምዘገባ የሚከናወንበት ጊዜን በማስታወቂያ እንደሚያሳውቅም ገልጿል። @NATIONALEXAMSRESULT
848
2
በሀረሪ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው ጥቅምት 29/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው እለት ፈተናው መሰጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ሙክታር ሳሊህ ፈተናው እንዳይስተጓጎል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡ ከፈተና ኩረጃ ጋር ተያይዞም ከሥነምግባርና ፀረሙስና ጋር በመቀናጀት ግንዛቤን የማስፋት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡ በመሆኑም የፀጥታ ኃይሉ፣ ወላጅና አጠቃላይ ማህበረሰቡ የፈተና አሰጣጡ በሰላም እንዲጠናቀቅና ስኬታማ እንዲሆን የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በክልሉ በሁለት ጣቢያዎች በሚሰጠው ፈተናም 1 ሺሕ 267 ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
697
0
"በሶማሌ ክልል ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን እየወሰዱ ነው።" የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሶማሌ ክልል መሰጠት ጀምሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር የ12ኛ ክፍል ፈተናን በጅግጅጋ አስጀምረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው ፈተናው እየተሰጠ ያለበትን አግባብ ተመልክተዋል። በክልሉ 20 ሺህ 211 ተማሪዎች በ128 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዱላሂ አብዲ አደን ገልጸዋል። SMMA @NATIONALEXAMSRESULT
681
0
ትናንት ሴት ልጅ የተገላገለችው ተማሪ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየወሰደች ነው ጥቅምት 29/2014 (ዋልታ) ትናንት ሴት ልጅ የተገላገለችው የሸዋሮቢት አጠቃላይ 2ኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳራ ሽመልስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየወሰደች ነው። በአማራ ክልል ሸዋሮቢት ከተማ የሸዋሮቢት አጠቃላይ 2ኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ሲሆን በትምህርት ቤቱ 775 መደበኛና 11 የግል ተፈታኞች ብሄራዊ ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ። ከትምህርት ቤቱ ተፈታኞች መካከል በትናንትናው ዕለት ሴት ልጅ የተገላገለችው ተማሪ ሳራ ሽመልስ ትገኛለች። ተማሪ ሳራ በጥሩ ጤንነት ላይ ሆና በዛሬው እለት ፈተናውን እየወሰደች እንደሆነ መግለጿን ኢዜአ ዘግቧል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎችም ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል። @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
665
0
"የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 91.5 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን እየወሰዱ ነው።" የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስጣጥን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ተመልክተዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ሀገር አቀፍ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ 91 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል። ፈተናው በመጀመሪያ ዙር በሚሰጥባቸው ሁሉም አካባቢዎች በሰላም እየተሰጠ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በከተማዋ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በ64 ጣቢያዎች እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እስከ ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ይቆያል። #ትምህርትሚኒስቴር የፈተናውን መጀመር ተከትሎ የቴሌግራም አገልግሎት በመደበኛ የስልክ ዳታ እየሠራ እንደማይገኝ ለማወቅ ችለናል። ከ36 ሺህ በላይ ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተናውን በሁለተኛ ዙር እንደሚወስዱ መገለጹ ይታወሳል። @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
869
0
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እክል መሰጠት ተጀምሯል። የ2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 62 የፈተና ጣቢያዎች ለ36 ሺህ 401 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል፡፡ በጠዋቱ የመፈተኛ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የእንግሊዝኛ ፈተና መሰጠት የጀመረ ሲሆን፤ ተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላቸው እንዲሁም ፈተናውን በፍፁም መረጋጋት እና ሥነ- ምግባር በተሞላበት መልኩ እንዲፈተኑ መልካም ምኞቱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስተላልፏል። በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተናው በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር ለመስጠት እቅድ የተያዘ ሲሆን፤ በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር እንደማይቀመጡ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ማስታወቁ ይታወሳል [Adiss maleda] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
896
0
ከንቲባዋና ሚነስትሩ የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጣጥን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ተመለከቱ ------------------------------------------- የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ( ፕሮፌሰር) እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ በሚገኙ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥን ተመልክተዋል። በጉብኝቱም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የፈተና አሰጣጥ ሂደት ምን እንደሚመስል ምልከታ ተካሂዷል። የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዛሬውን ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ 91.5% የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል። ፈተናውም በሁሉም አካባቢ በሰላም እየተሰጠ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ አዲስ አበባ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በ64 ጣቢያዎች እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው በሁሉም ቦታ አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረትም ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እና ከንቲባዋ ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ እንዲወስዱ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ተማሪዎችን አበረታተዋል። የ 2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም አካባቢዎች እየተሰጠ ይገኛል። ፈተናው እስከ ህዳር 02/2014 እንደሚቆይ ይታወቃል። [MoE] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
1 101
0
"የ12ኛ ክፍል ፈተና ተስርቋል…" እና መሰል የተለመዱ የፈጠራ ማዘናጊያ ወሬዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቃችሁ ፈተናችሁን በተረጋጋ መንፈስ እንድትቀጥሉ መልዕክታችን ነው። @NATIONALEXAMSRESULT
1 632
0
🌼 ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለምትወስዱ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ መልካም ፈተና መልካም እድል 🌼 Team: @NATIONALEXAMSRESULT
7 176
10
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከነገ ጥቅምት 29/2014 ዓ.ም እስከ ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ ሀገሪቱ ይሰጣል። በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያ ዙር ፈተናው #የማይሰጥባቸው የአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሚከተሉት ናቸው፦ • ሰሜን ወሎ፣ • ደቡብ ወሎ፣ • ዋግምራ፣ • ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን፣ • ሰሜን ጎንደር (ጠለምት እና አዳርቃይ)፣ • ሰሜን ሸዋ (አጣዬ፣ ግሸርአባሌ፣ ኤፍረታና ግድም፣ አንጾኪያ) በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር አይቀመጡም። @NATIONALEXAMSRESULT
4 442
3
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ግምጃ ቤቱ የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል። ሀረር ከተማ የሚገኘው ግምጃ ቤቱ፤ በቆርቆሮና ችፑድ የተሰራ ሲሆን ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ አልጋዎች፣ ትራሶች እና ችፑድ የሚከማችበት መሆኑ ተገልጿል። ግምጃ ቤቱ ትላንት ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም ምሽት 5፡00 ሰዓት መነሻው ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። እሳቱን ለማጥፋት የኮሌጁ ማህበረሰብና የሀረሪ ክልል የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ጥረት አድርገዋል። በማከቻው ውስጥ የነበሩ ያገለገሉ ንብረቶች የተቃጠሉ ሲሆን በሰው ላይ ያደረሰው ምንም ጉዳት አለመኖሩን የኮሌጁ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ያደሴ ተናግረዋል። #ሐረማያዩኒቨርሲቲ @NATIONALEXAMSRESULT
5 051
8
ሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 846 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡ ኮሌጁ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ከማፍራት አንፃር እያከናወነ ባለው ተግባር የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል፡፡ እንደ ሀገር ያጋጠመንን የህልውና አደጋ በማያዳግም ሁኔታ መቀልበስ የሁሉም ዜጋ ርብርብ ወሳኝ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል፡፡ ተመራቂዎችም ከሀገር መከላከያ ፣ የፌደራልና የክልሎች የጸጥታ ኃይል አባላት ጎን በመሰለፍ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ በበኩላቸው÷ ተመራቂዎች የቀሰሙትን እውቀት ተግባር ላይ በማዋል በተለይም የማህበረሰቡን የጤና ችግር እንዲቀርፉ ጥሪ አቅርበዋል። በእለቱ የጤና ሳይንስ ኮሌጁ በ9 የዲግሪ እና በ8 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 846 ተማሪዎችን የሥመረቀ ሲሆን÷ ከተመራቂዎቹ መካከልም 49 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን ከሃረር ጤና ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከልም 82 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል የተሰጡ ናቸው ተብሏል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
5 094
4
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29/-ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል። ይሄን አስመልክቶ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው የተጠቀሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ - 617,991 ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበሩ የተፈታኞች ቁጥር በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል። (የ2012 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ቁጥር 321,000 ነበር) - ይህንን ዝግጅት ለማስተባበር በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት ፈተናውን ወደ መፈተኛ ጣቢያ የማድረሱ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ለዚህም የየብስና የአየር ትራንስፖርት ግልጋሎት ላይ እንደዋለ ተጠቅሷል። - ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች የዘንድሮው የሚለየው በዙር የሚሰጥ በመሆኑ ነው ተብሏል። በዚህም የጸጥታ ችግር ካለባቸው አከባቢዎች ውጪ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር ውስጥ ይሰጣል ተብሏል። - በአማራ ክልል በፌደራል በተወሰነ ውሳኔ መሰረት በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ በኦሮሞ ብሔረሰብ በዋግኽምራ ዞኖች እንዲሁም ሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ጠለምት ወረዳዎች ሰሜን ሸዋ ዞን ደግሞ ኤፍራታና ግድም፣ አንጾኪያ ጋምዛ ና ግሼ ራበን ወረዳዎች በሁለተኛው ዙር ተካተዋል። - በአጠቃላይ በአማራ ክልል 36,340 ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም ተብሏል። - በሌሎችም ክልሎች ያለው የጸጥታ ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት በጣም ጠባብ በሆነ ሁኔታ ወደ ሁለተኛ ዙር ሊጠቃለሉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። - በአጠቃላይ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች ከ94% - 92% ያህሉ በፈተና ወንበራቸው ላይ ይቀመጣሉ ተብሏል። [tikvah eth magazine] @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...

record.ogg

5 252
11
4 009
0
#Update ዛሬ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከጥቅምት 29 እስከ ኀዳር 02/2014 ዓ.ም የሚሰጠውን የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ • 617, 991 ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። ይህም ከባለፈው ዓመት የተፈታኞች ቁጥር በእጥፍ ይበልጣል። • የፈተናውን ዝግጅት ለማስተባበር በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት ፈተናውን ወደ መፈተኛ ጣቢያ የማድረሱ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ለዚህም የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት ግልጋሎት ላይ ውሏል። • ፈተናው በመጀመሪያ ዙር የጸጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ይሰጣል ተብሏል። • በአማራ ክልል በፌደራል በተወሰነ ውሳኔ መሰረት በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ በኦሮሞ ብሔረሰብ በዋግኽምራ ዞኖች፤ በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ጠለምት ወረዳዎች፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም፣ አንጾኪያ ጋምዛ እና ግሼ ራበን ወረዳዎች በሁለተኛው ዙር ተካተዋል። • በአጠቃላይ በአማራ ክልል 36, 340 ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም ተብሏል። • በሌሎች ክልሎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ሁለተኛ ዙር ሊጠቃለሉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። • ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች ከ92 እስከ 94 በመቶ ያህሉ በፈተና ወንበራቸው ላይ ይቀመጣሉ ተብሏል። @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
4 132
3
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺሕ 559 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው ጥቅምት 27/2014 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺሕ 500 በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺሕ 6 ተማሪዎች ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል። ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቃቸው በመደበኛና ተከታታይ መርኃግብር ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች መሆናቸውም ተመላክቷል። Via walta @NATIONALEXAMSRESULT
4 031
2
አዲስ ነገር ከቴሌ ለእናንተው 👌 ያለዎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው😒 ስልክ መደወልዎ ደግሞ ግድ ነው ነገሮች አሁን ቀለዋል ፤ በቀጥታ ጥሪውን ያድረጉ የደወሉላቸዉ ደንበኛም የቢፕ ኮል መልዕክት ይደርሳቸዋል። @NATIONALEXAMSRESULT
4 114
5
ተማሪዎች ሊከተቡ ነው ትምህርት ሚኒስቴር ከጤና ሚንስቴር ጋር በመተባበር ለትምህርት ማኅበረሰቡ የጸረ-ኮቪድ ክትባት በዘመቻ ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ ለኮቪድ ወረርሽኝ ተጋላጭ ከሆኑ ዘርፎች መካከል የትምህርት ተቋማት ይገኙበታል ያለው ቢሮው የዘመቻው ዓላማ ይህንን ስጋት መቀነስ ነው ተብሏል፡፡ ዘመቻው የጤና ሚኒስቴር የጸጥታ ችግር ለሌለባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ሊያዳርስ ያቀደው 12 ሚልዮን በላይ ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት አካል ነው መባሉን ሰምተናል፡፡ የክትባት ዘመቻው የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን፣ የከፍተኛ ትምህርት መምህራን እና ተማሪዎችን እንዲሁም የትምህርት ማኅበረሰቦችን እንደሚያዳርስ ተነግሮለታል፡፡ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር የቻይና መንግሥት ለ150 ሺህ መምህራን የሚሆን የኮቪድ 19 ክትባት ለኢትዮጵያ መንግሥት በድጋፍ መልክ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡ በልገሳው 50ሺህ የሚጠጉ መምህራን ክትባቱን መውሰዳቸው ተዘግቧል፡፡ MoE @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
5 180
19
በመቐለ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን ጊዚያዊ ምደባ በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል። መምህራኑ የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የኦንላይን አድራሻ አማካኝነት ምዝገባቸውን ከጥቅምት 22 እስከ 24/2014 ዓ.ም አድርገዋል፡፡ መምህራኑን በጊዚያዊነት ለመመደብ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። የመምህራኑ ጊዚያዊ ምደባ በቀጣይ ሳምንት ይፋ ሊደረግ እንደሚችልም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በተገለጹት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። @NATIONALEXAMSRESULT
5 980
2
#MeddaWalabuUniversity የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት እና የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ፕሮግራም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የዩንቨርሲቲው ሬጂስትራር አልሙናይ ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ አሳውቋል። @NATIONALEXAMSRESULT
5 635
12
የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደም ለገሱ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ደማችን ለአርበኞቻችን፤ ህይወታችን ለሀገራችን” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሄደዋል፡፡ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የግሸ አባይ ግቢ ተማሪዎች ለሃገራችን ህልውና እና ለእያንዳንዳችን መኖር እየተዋደቁ ላሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚኒሻ እና የፋኖ አባላት ደም በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋፆ አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንደገለጹት ገንዘብ ከማዋጣትና ደም ከመለገስ ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያን ከገጠማት ችግር ለማውጣት ሁሉም ወጣት ወደ ጦር ግንባር በመዝመት አጥፊውን የህወሓት የሽብር ቡድን ለመደምሰስ መዋጋት አለበት ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ 414 ተማሪዎች ደም ለግሰዋል፡፡ Bahir Dar University, Bahir Dar-PR @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
5 122
4
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት 29 ስለሚጀምር ተማሪዎች እንዳይዘናጉ ተጠየቀ ጥቅምት 26/2014 ዋልታ) የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ኅዳር 2 እንደሚሰጥ አገር ዐቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ። ተፈታኝ ተማሪዎችም ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚሰጥ መሆኑን በማወቅ በተረጋጋ ሥነ ልቦና ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
6 163
17
" በአማራ ክልል 33 ሺህ ተማሪዎች የ12 ክፍል መልቀቂያ አይፈተኑም " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ከሚገኙ 357 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በ112ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው ይህ ያሳወቀው ለጀርመን ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው። በአማራ ክልል ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 164 ሺህ ተማሪዎች መካከል ጦርነቱ በፈጠረው ችግር ምክንያት 33 ሺህ ተማሪዎች መፈተን አይችሉም። የአማራ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ እንደተናገሩት ፦ • በሰሜን ወሎ 42፣ • በዋግኽምራ 16፣ • በደቡብ ወሎ 48 • በደሴ ከተማ አስተዳደር 3፣ • በሰሜን ጎንደር 3 ሁለተኛ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን አያስፈትኑም፡፡ በክልሉ ለፈተናው የሚቀመጡት 131 ሺህ 167 ተማሪዎች ብቻ ሲሆኑ 123 ሺህ 159 በመደበኛ፣ 8 ሺህ 8 ደግሞ የግል ተፈታኞች መሆናቸውን ቢሮው ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከፊታችን ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል፡፡ @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
6 855
18
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ ይሰጣል። ኤጀንሲው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ቅዳሜ ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም ጠዋት ይሰጣል። @NATIONALEXAMSRESULT
7 682
59
#JIMMAUNIVERSITY የጂማ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን #ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል። Waamichi yuunibarsiitii jimmaa yeroo hin murtoofneef dheeraffameera @NATIONALEXAMSRESULT
5 780
15
የዪኒቨርስቲ ምደባ ለመቐለ ፤ አክሱም ፤ አዲግራት ፤ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ ከላይ በተጠቀሱት ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በፀጥታ ምክንያት ትምህርታችሁን መቀጠል ያልቻላችሁ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በወሰነው መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊነት የተመደባችሁ ስለሆነ በተቀመጠዉ አድራሻ https://www.placement.ethernet.edu.et/ የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ጥሪ ሲያደርግላችሁ ብቻ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡ #ማሳሳቢያ 1. ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡ 2. ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻላችሁ ተማሪዎች ስማችሁን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላታገኙ ስለምትችሉ፣ በነበራችሁበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመዳባችሁ፣ የተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ፡፡ 3. ተመዝግባችሁ ሳትመደቡ የቀራችሁ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረባችሁ በመሆኑ ያልተመደባችሁ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላችሁ የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳዉቃለን፡፡ 4. ያልተመዘገባችሁ እና ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላችሁ ተማሪዎች በተቀመጠዉ የቴሌግራም ቦት አድራሻ(@moeplacementbot) አቤቱታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን አቤቱታዎችን በአካል የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ 5. በዩኒቨርስቲዎቻችሁ ተፈቅዶላችሁ እረፍት(Withdrawal) ላይ የነበራችሁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላችሁ ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቻዉን አቅርባችሁ የሚታይላቸዉ ይሆናል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
6 194
22
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጊዚያዊ ምደባ ይፋ ሆኗል። ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመከተል የዩኒቨርሲቲ መለያ ቁጥር እና ሙሉ ስም በማስገባት ጊዚያዊ ምደባቸውን መመልከት ይችላሉ፦ http://Placement.ethernet.edu.et @NATIONALEXAMSRESULT
5 565
13
በአማራ ክልል የግዕዝ ትምህርትን ለማስጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቀቀ። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የግዕዝ ትምህርትን በክልሉ ለማስጀመር የስርአተ ትምህርት ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቀይቷል፡፡ በዘርፉ ምሁራን የተዘጋጀው የስርአተ ትምህርት መጠናቀቁን ተከትሎ የመማሪያና ማስተማሪያ መፀሀፍት ዝግጅት ተደርጓል፡፡ የተዘጋጀው የመማሪያና ማስተማሪያ መፀሀፍት ወደ ሙከራ ከመግባቱ በፊት በዘርፉ ምሁራን ይሁንታ ያገኝ ዘንድ በባህርዳር ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ግዕዝ ከሚያስተምሩ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ እንዲሁም ታዋቂ የግዕዝ ምሁራን በተገኙበት ለመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍቱ ግብአት ያግዛሉ የተባሉ ሀሳቦች ለአዘጋጆቹ ተሰጥተዋል፡፡ የመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍት አዘጋጆችም የተሰጡ ሀሳቦች መፀሀፍቱን ይበልጥ የሚያለጽጉ በመሆናቸው በግብአትነት እንደሚጠቀሙባቸው ተናግረዋል፡፡ በ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ይጀመራል የተባለው የግዕዝ ትምህርት በተያዘው የትምህርት ዘመን በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡ Credit: አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ @NATIONALEXAMSRESULT
Show more ...
6 338
0
Last updated: 27.11.21
Privacy Policy