cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Muhammed Computer Technology (MCT)

#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው! በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ አስተያየት ካላችሁ @ma1000me ልታገኙኝ ትችላላችሁ በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!

Show more
Advertising posts
38 612
Subscribers
-1724 hours
-327 days
-8930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከዚህ በታች ያለው የቴሌግራም ቻናል ስለኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጥያቄ አጥቸ ሰዎች የሚፈተኑበት ቻናል ነው። እስከዛሬ ድረስ 50 ጥያቄዎች ያሉ ሲሆኑ በመግባት እራሳችሁን ፈትኑ እወቁ! መልሱን ወዲያውኑ ታውቃላችሁ! ወደፊት ጥሩ ጥያቄወችን እያዘጋጀሁ እለቅላችኋለሁ 👇👇ይግቡ ሊንኩ ከታች ያለውን ይጫኑ👇👇👇 https://t.me/mame_tech_QA
Show all...
MCT Questions and Answer

በዚህ ቻናል ጥያቄዎችን ፓስት አደርጋለሁ እናንተ ደግሞ ትመልሳላችሁ

👍 1
✅ የጥናትና ምርምር ቅደም ተከተላዊ ይዘቶች/ደረጃዎች/ ✅ በሁሉም የጥናትናምርምር ዓይነቶች ተቀራራቢ ይዘት /ደረጃዎች/ የሚኖራቸውቢሆንም የተወሰኑ ልዩነቶች ይኖራሉ፡፡ ✅ ነገርግን በተለይ በተግብራዊ ጥናትና ምርምር ውስጥ 🔴 1ኛው ክፍል መግቢያ /Introduction/ ሲሆን በዚህ ውስጥ የጥናቱን ርዕስከ መምረጥ ጀምሮ የጥናቱን አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጽ ፅንሠ ሀሣባዊና ታሪካዊ ዳራ፣ የጥናቱ ዓላማ፣ አስፈላጊነት፣ የጥናቱ ችግር ምንነትና የጥናቱ ወሰን ወዘተ ይገለጽበታል፡፡ 🔴 2ኛው ክፍል የተዛማጅ ጽሑፍ ክለሣ ሲሆን በዚህም ከጥናቱ ጋር ተዛማጅ የሆኑጽሑፎች የሚገመገሙበት፣ የሚነፃፀሩበትና ልምድ የሚወስዱበት ክፍል ይሆናል፡፡ 🔴 3ኛው ክፍል የጥናቱንዘዴ ( Methodology) የሚገለጽበትነው፡፡ 🔴 4ኛው ደግሞ የተሰበሰበው መረጃ የሚተነተንበትና የሚተረጐምበት ሲሆን 🔴 5ኛው ማጠቃለያ እና የውሣኔ አስተያየት የሚሠጥበት ክፍል ነው፡፡ ✅ ከነባራዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መረዳት እንደተቻለው ብዙሰዎች በትምህርት ነክ ችግሮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ✅ በምን መልክ የምርምር ሥራ መሥራትም እንዳለባቸው ይወስናሉ፡፡ ዋነኛው ችግርግን ምርምር የሚያደርጉበትን ርዕስ ማወቅና መወሰኑ ላይ ነው፡፡ ✅ አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ችግር ምንጭ ነው ተብሎ የሚገመተው ሰዎች መሥራት የሚፈልጉት ጥናት አዲስ፣ ልዩ የሆነ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ምርምር እንዲሆን ስለሚፈልጉ ነው፡፡ ✅ ፍላጐቱና ሃሣቡ ጥሩ ሆኖ ሳለየዚህ ዓይነት ሃሣብ ተመራማሪውን በጣም ከባድና መረጃ አልባ ወደ ሆነ መስክ ይመራውና ችግር ላይ ይጥለዋል፡፡ ✅ እዚህ ላይ እንድን ረዳው የሚያስፈልገን ዋነኛ ነጥብ ማንኛቸውም የምርምር ፕሮጀክቶች ከማንም አያንሱም፡፡ ✅ የሌሎች የምርምር ውጤቶችን ማንበብና ማጤን አዲስ አሠራርን እንድንፈጥር ወይም ለሌሎች አዳዲስ ግኝቶች እንድንጓጓ ወይም ግኝቶችን በተለየና አዲስ በሆነ መልክ ለመጠቀም ምርምር እንድናደርግ ይገፋፋናል፡፡ ✅ በአጠቃላይ የምርምርን ርዕስ ለመወሰን በመስኩ ጠለቅያለ እውቀት እንዲኖር መጣርን ይጠይቃል፡፡ አንድን ጥናት ወይም ምርምር ለማድረግ ከሚገፋፉ ምክንያቶች ውስጥ ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ ✅ 1.በአንድ በተወሰነ የጥናት መስክ የታወቀው ነገር ውሱን ሆኖ ሲገኝና ሰፋ ያለ እውቀትና ግኝት እንዲኖር ሲያስፈልግ፣ ✅ 2. በጥልቀት ያልተጠና ዕውቀት በመኖሩ ጅምር አስተሳሰብን ፍፃሜ ለማድረስና የተሟላ እውቀት ማግኘት አስፈላጊ ሲሆን፣ ✅ 3.የዕውቀት መረጃዎች ያሉና የታወቁ መስለው ነገር ግን ያልተረጋገጡ ሆነው ይህን መሥራት የግድ ሆኖ ሲገኝ፡፡ ✅ 4.እየሠራነው ላለው ተግባር ለውጥ/ውጤት ስለመምጣቱ ለማረጋገ ጥስንፈልግ ወይም ለውጥ አለማምጣታችንን ስናረጋጥ ምክንያቱን ለማወቅ ስንፈልግ፣ ✅ ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው የምርምር ዋና ዋናዎቹ ቅደም ተከተላዊ ደረጃዎች ምንድን ናቸው የሚለውን ነጥብ ስናነሣ የሚከተሉትን ደረጃዎች ማንሣት ይቻላል፡፡ ✅. የምርምርን ርዕሰ ጉዳይን በሚገባ መግለጽ/ Statement of the problem/ ✅ ከላይ እንደተገፀው ማንም ሰው የምርምር ርዕስ ነው በሚል አስተሳሰብ አንድን ርዕስ እንደ መሰለው ማስቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን በትክክልና በጥልቀት አውጥተው አውርደው በአእምሮ ውስጥ ጉልህ የሆነ ግንዛቤ/ምስል እንዲፈጥር ማድረግ ካልተቻለ ማንኛው ምርዕ ስለምርምር ብቁ ርዕስ ላይሆንልንይችላል፡፡ ስለዚህ ምርምር የሚደረግበት ርዕስ ጉልህና አሻሚ ትርጉም የሌለበት ሆኖ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ✅ ማንኛውም ተማራማሪ የምርምሩን ርዕስ በትክክል ለመግለጽ በሚፈልግበት ጊዜበ አጽህኖት ሊያስታውሳቸው የሚገባ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦች አሉ፡፡ እነዚህም፡- ✅ ✅መላምት /Hypotheses of the study/ ✅ መላምት/ Hypotheses/ ተመራማሪው ምርምሩን ለመተግባር ሲነሳ በመጀመሪያ አንዳንድ ጥርጣሬያዊ ጥያቄዎችና መልሶች ወይም መፍትሔዎች ይሆናሉ ብሎ የሚያስባቸው ናቸው፡፡ከዚህ ቀደም ባቀረብነው ምሳሌ የተማሪውን የሥነምግባር ጉድለት መንስኤዎች ብናስታውስ፡- የቤተሰብ አያያዝ ✅ በትምህርት ዝቅተኛ ውጤት ማምጣትና ተስፋመቁረጥ ወዘተ…. የሚሉት ለተማሪው የጠባይ መበላሸት ምከንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው በመላምት መልክ የቀረቡ ሃሳቦች ናቸው፡፡ እነዚህም በጥናቱ ውስጥ ሊረጋገጡ ወይም ሊሻሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ መላምት በጥያቄ ወይም በዓረፍተነገር መልከ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ✅ ለምሣሌ፡መላምት 1፡ተማሪውን በጥባጭ ያደረገው የቤተሰብ አያያዝና አስተዳደር መበላሸትነው፡፡ /ዓረፍተነገር/ መላምት 2፡በተማሪው ጠባይ ላይ ተጽእኖ ያደረገው የጓደኞቹ ግፊት ይሆን? /በጥያቄመልክ/ 🔴 መሠረታዊ ጥያቄዎች /Basic Research Questions/ ✅ እነዚህ በጥናቱ ውስጥ በተለያዩ ዘዴዎች መረጃዎችን በማሰባሰብ መመለስ ያለባቸው ጥያቄዌች ናቸው፡፡ የእነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የመላምቶችን እውነተኛነት ወይም ሃሰተኛነት ግልጽ ያደርጋል፡፡ ✅ ለምሳሌ ከላይ የተቀጠሰውን ተማሪ ሁኔታ ብናይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ✅ የትምህርት ውጤቱ ምን ይመስላል የቤተሰቡ አያያዝና አስተዳደር ምን ይመስላል ወዘተ እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ተመራማሪው መመለስ ከቻለ ለልጁ ጠባይ መበላሸት መንስኤ የሆነውን ነገር ማግኘት ይችላል፡፡ ስለዚህ በምርምር አለም ተመራማሪው በጥናቱ ሂደት ውስጥ አጥጋቢ ምላሽ ሊያገኝላቸው የሚገባው አብይ ነጥቦችና ጥያቄዎች እንዳሉ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ✅ ከላይ የተገለፁት ሁለት ጉዳዮች ተመሣሣይ አገልግሎት ያላቸው በመሆኑ አጥኝዎች ከሁለቱ አንዱን ብቻ በመውሰድ ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ሰለዚህ እኛም በጥናታችን የሚመቸውን አቀራረብ በምረጥ አንድም በመላምት ወይም በመሠረታዊ ጥያቄዎች ላይመሠረት አድርገን መነሣት እንችላለን፡፡ ✅.የጥናቱ አስፈላጊነት /Significance or Justification of the study/ ✅ አንድ ጥናታዊ ምርምር ሲደረግ/በተለይም በተግባር ተኮር ጥናትና ምርምር / በማንኛውም መልኩ ቢሆን የጥናቱ ዋነኛ ዓላማና ግብ የችግሮችን መፍትሔ ለማግኘት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁም መሠረት እንደ ችግሮቹ አንገብጋቢነት ደረጃ በወቅቱ መፍትሔ ቢሰጣቸው ምን ያህል ጠቃሚ እንደሚሆን መገለጽ ይኖርበታል፡፡ ገለፃው ከግል፣ከቡድን፣ ከብሔራዊና ከዓለም አቀፋዊ አኳያ ሊታይ ይችላል፡፡ ከማንኛወም አንፃር ቢሆን ጥናቱና ምርምሩ በውጤቱ ማኀበራዊ ጠቀሜታ እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡ ✅ ስለዚህ አንድ ተመራማሪ በአንድ ጉዳይ ላይ የሚያደርገው ምርምር በዘፈቀደለሱ እንደ ተሰማው ሳይሆን የችግሩን አንገብጋቢነት ከማኀበራዊ ጠቀሜታ አኳያ በመገምገምና ስለጥናቱም ያለውን ምክንያት በግልጽ በስቀመጥ መሆን ይኖርበታል፡፡ ✅.የጥናትና ምርምር ክልልን መወሰን ( Delimitation) ከብዙ ጥናታዊ ምርምር ግምገማ መረዳት እንደተቻለው የብዙ ጀማሪ ተመራማሪዎች ችግር የጥናትን ክልል መወሰን አለመቻል ነው፡፡ አንድ ተመራማሪ የምርምር ርዕሱን በሚገባ ከገለፀ በርዕሱ ስለተገለፀው ጉዳይ ከተለያዩ ገጽታዎች አንፃር በአንድ ወቅት በጥልቅማየት /ማጥናት/ ይቸግረውይሆናል፡፡ ወይም የአንድን ጉዳይ ሁለንተናዊ ገጽታ ላጥና ብሎ ቢነሳ ምምርምሩ ከጥልቀት ይልቅ ስፋት ብቻ ይኖረውና እያንዳንዱ ነጥብ በተሟላና በጥልቀት ሳይዳሰ ስሊታለፈይ ችላል፡፡
Show all...
👍 7🔥 1
ስለዚህ አንድ ተመራማሪ እላይ የተጠቀሰው ችግር እንዳይከሰት ገና ከመነሻው ጥናቱ የሚወስደውን ጊዜ፣ የገንዘብ አቅምና የሚያስፈልጉትን ሌሎች መሣሪያዎች ማግኘት የሚቻልበትን ዘዴ ማወቅና የመረጃዎችን አሰባሰብ ስልት በመቀየስ የጥናቱን ክልል መወሰን አለበት፡፡ ✅ አንድ ምሳሌ ወስደን ለማየት እንሞክር፡፡ ✅ የምርምር ርዕስ የ “HIV መስፋፋትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ያጋጠሙ ችግሮች” ይህ ርዕስ በጣም ሰፊ በመሆኑ ሰፊ ጊዜና ብዙ ገንዘብ ከመጠየቁም በላይ መመለስ የሚፈለገው ጥያቄ በግልጽ ስላልተጠቆመ ለምርምር አመች አይደለም፡፡ ግን ጥሩ መነሻ ነው፡፡ በቦታ፣ በጊዜና በሁኔታ ሊከለልና ሊጠብ ይችላል፡፡ የሚከተሉትን ርዕሶች እንመልከት፡፡ 🔴 ሀ/ በአዲስአበባየHIV መስፋፋትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ያጋጠሙ ችግሮች /በቦታሲከለል/፣ 🔴 ለ/ በአዲስየአበባየHIV መስፋፋትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ከ199ዐዓ.ም ወዲህ ያጋጠሙችግሮች /በጊዜ ሲከለል/፣ 🔴 ሐ/ በአዲስአበባ የHIV መስፋፋትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ከ199ዐዓ.ም ወዲህ ያጋጠሙ የማቴሪያል ችግሮች/ በሁኔታ ሲከለል/ በዚህ ሁኔታ ማንኛውንም ሰፊ ጊዜ ብዙ ገንዘብና ማቴሪያል የሚጠይቅ ርዕስ ጥናትና ምርምሩን ለሚያካሂደው ግለሰብ ከጊዜ ከገንዘብና ማቴሪያል አቅም ጋር እንዳስማማ አድርጐ ማጥበብ ይቻላል፡፡
Show all...
👍 14 3
ዲጅታላይዜሽን ተግበራ በአብክመ ስራና ስልጠና በቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሬጅስትራር ሲስተም (Students Information Management System SIMS) ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገባ ማድረግ ችለናል። አንጋፋው ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኮሌጁ ዲኖች፣ የዲፓርትመንት ሀላፊዎች፣ መምህራኖች፣ የሬጅስትራር ሀላፊ፣ የሬጅስትራር ባለሙያዎች፣ ለፋይናንስ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ ሀላፊ፣ ለተማሪዎች ስልጠና በመስጠት የኮሌጁን ነባር ተማሪዎችና አዲስ ተማሪዎችን መረጃ እንዲገባ በማድረግ አሰራር ከማንዋል ወደ ዲጂታላይዝ አሰራ በመቀየር ሲስተሙን ኦንላይን ማድረግ ችለናል። ለዚህም ስልጠናና ተግበራ መሳካት የኮሌጁ ዲን አቶ አስጨነቅ ካሳ፣ ም/ዲን ዶ/ዋል ፍሬው፣ የኮሌጁ የሬጅስትራር ሲስተም አድሚኒስትሬተር መ/ር ታየ፣ የICT ዲፓርትመንት ሀላፊ አቶ በላይ ጸጋ እንዲሁም የኮሌጁ የማኔጅመንት አባላትን ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ለዚህም ተግባርም የምስክር ወረቀት አበርክተውልኛል አመሰግናለሁ። በነበረኝ ቆይታ የስልጠናውን በከፊል ፖስት አድርጌላችኋለሁ። ለበለጠ መረጃ 0929273364 መደወል ይቻላል።
Show all...
👍 15 4
VLC ቪዲዮ ማጫወቻ አቋራጭ ቁልፎች (Shortcuts) ዛሬ ከበርካታ ሚዲያ ማጫዎቻዎች መካከል በአቀራረቡ ተወዳጅነትን ያተረፈዉን   ቪ ኤል ሲን(VLC) እንዴት አቋራጭ ቁልፎችን በመጠቀም በቀላሉ መገልገል እንደምንችል እናያለን፡፡ 1.  Play/pause   Space bar የተሰኘዉን ቁልፍ በመጠቀም የምናየዉን ቪዲዮ ማቆም ና እንደገና ማጫዎት እንችላለን፡፡ 2.  Mute audio   የምናየዉን ቪዲዮ ደምፅ ሚዉት(ለማጥፋት) ‘M’ን በመጫን ማጥፋት ና ደግመን ተጭነን ማብራት እንችላለን፡፡ 3.  Full screen   ‘F’ን በመጠቀም በኮምፒዉተራችን ስክሪን ሙሉ ማየት ና ደግመን በመጫን ወደ ነበረበት መመለስ እንችላለን፡፡ 4.  Change audio track   አንዳንድ ቪዲዮዎች ከአንድ በላይ የድምፅ (audio track) አማራጭ ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ‘B’ን በመጠቀም መቀያየር እንችላለን፡፡ 5.  Volume control   ድምፅ ለመጨመር Ctrl + arrow up   ድምፅ ለመቀነስ Ctrl + arrow down 6.  Video play speed   የምናየዉን ቪዲዮ ፍጥነት ለመቆጣጠር የሚከተሉትን ቁልፎች መጠቀም እንችላለን፡፡ •  + ለመጨመር •  - ለመቀነስ 7.  Seeking   ቪዲዮዉን ለማሳለፍ 3 አይነት መንገዶችን መጠቀም እንችላለን፡፡ I.  አጭር ወደ ፊት  shift+right arrow (3 sec II.  አጭር ወደ ኋላ shift +left arrow III.  መካከለኛ ወደ ፊት alt +right arrow (10 sec IV.  መካከለኛ ወደ ኋላ alt + left arrow V.  ረጅም ወደ ፊት ctrl + right arrow (1 min VI.  ረጅም ወደ ኋላ ctrl + left arrow 8.  Remaining time   Full screen አርገን ቪዲዮ የምናይ ከሆነ ምን ያክል ሰዓት እንደቀረን አያሳየንም ስለዚህ ‘T’ን በመንካት ማየት እንችላለን ፡፡ 9.  Subtitles   የምናየዉ ቪዲዮ subtitle ካለዉ  ነገር ግን ፅሁፉ የሚረብሸን ከሆነ ‘V’ን ነክተን ማጥፋት እንዲሁም  እንደገና ማምጣት እንችላለን፡፡ 10.  Record video   እያየን ያለዉን ቪዲዮ ሪከርድ ማድረግ ብንፈልግ Shift + Rን በመጠቀም መቅዳት እንችላለን፡፡ ይህም cut አርገን ቪዲዮ ለመስራት ያስችለናል፡፡ 11.  Quit   ጨርሰንም ሆነ አቋርጠን ቪዲዮዉን ለመዝጋት ከፈለግን ctrl + Q በመጫን መዉጣት እንችላለን፡፡
Show all...
👍 39 3👏 1
VLC ቪዲዮ ማጫወቻ አቋራጭ ቁልፎች (Shortcuts) ዛሬ ከበርካታ ሚዲያ ማጫዎቻዎች መካከል በአቀራረቡ ተወዳጅነትን ያተረፈዉን   ቪ ኤል ሲን(VLC) እንዴት አቋራጭ ቁልፎችን በመጠቀም በቀላሉ መገልገል እንደምንችል እናያለን፡፡ 1.  Play/pause   Space bar የተሰኘዉን ቁልፍ በመጠቀም የምናየዉን ቪዲዮ ማቆም ና እንደገና ማጫዎት እንችላለን፡፡ 2.  Mute audio   የምናየዉን ቪዲዮ ደምፅ ሚዉት(ለማጥፋት) ‘M’ን በመጫን ማጥፋት ና ደግመን ተጭነን ማብራት እንችላለን፡፡ 3.  Full screen   ‘F’ን በመጠቀም በኮምፒዉተራችን ስክሪን ሙሉ ማየት ና ደግመን በመጫን ወደ ነበረበት መመለስ እንችላለን፡፡ 4.  Change audio track   አንዳንድ ቪዲዮዎች ከአንድ በላይ የድምፅ (audio track) አማራጭ ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ‘B’ን በመጠቀም መቀያየር እንችላለን፡፡ 5.  Volume control   ድምፅ ለመጨመር Ctrl + arrow up   ድምፅ ለመቀነስ Ctrl + arrow down 6.  Video play speed   የምናየዉን ቪዲዮ ፍጥነት ለመቆጣጠር የሚከተሉትን ቁልፎች መጠቀም እንችላለን፡፡ •  + ለመጨመር •  - ለመቀነስ 7.  Seeking   ቪዲዮዉን ለማሳለፍ 3 አይነት መንገዶችን መጠቀም እንችላለን፡፡ I.  አጭር ወደ ፊት  shift+right arrow (3 sec II.  አጭር ወደ ኋላ shift +left arrow III.  መካከለኛ ወደ ፊት alt +right arrow (10 sec IV.  መካከለኛ ወደ ኋላ alt + left arrow V.  ረጅም ወደ ፊት ctrl + right arrow (1 min VI.  ረጅም ወደ ኋላ ctrl + left arrow 8.  Remaining time   Full screen አርገን ቪዲዮ የምናይ ከሆነ ምን ያክል ሰዓት እንደቀረን አያሳየንም ስለዚህ ‘T’ን በመንካት ማየት እንችላለን ፡፡ 9.  Subtitles   የምናየዉ ቪዲዮ subtitle ካለዉ  ነገር ግን ፅሁፉ የሚረብሸን ከሆነ ‘V’ን ነክተን ማጥፋት እንዲሁም  እንደገና ማምጣት እንችላለን፡፡ 10.  Record video   እያየን ያለዉን ቪዲዮ ሪከርድ ማድረግ ብንፈልግ Shift + Rን በመጠቀም መቅዳት እንችላለን፡፡ ይህም cut አርገን ቪዲዮ ለመስራት ያስችለናል፡፡ 11.  Quit   ጨርሰንም ሆነ አቋርጠን ቪዲዮዉን ለመዝጋት ከፈለግን ctrl + Q በመጫን መዉጣት እንችላለን፡፡
Show all...
ማንኛውም የፋይል አይነት (doc, ppt, pdf, jpeg, jpg, GIF, mp3, mp4...) ወደ ፈለጋችሁት ሌላ የፋይል አይነት ለመቀየር የሚያግዟችሁ ዌብሳይቶች። ⚫ https://www.cleverpdf.com/https://pdf.io/https://tinywow.com/https://convertio.co/https://cloudconvert.com/https://www.i2pdf.com/https://www.ilovepdf.com/https://www.pdf2go.com/https://pdfcandy.com/https://onlineconvertfree.com/ ©big_habesha
Show all...
CleverPDF - 44 Free Online PDF Tools

CleverPDF offers dozens of high quality free online PDF tools, including PDF to Office, iWork and other format conversion, merge or split PDF, PDF security and more!

👍 42 10🌭 1
✳️ መልቲ ሜትር በመጠቀም እንዴት ስልክ ላይ የሚገኙ electronic ዲቫይሶችን መለካት ይቻላል❓ 🚩 Resistor - መልቲሜትሩን ኮንቲኒቲ ላይ ካደረግነዉ ቡሃላ ቀዪንና ነጩን ፕሮብ ሪዚስተሩ ላይ ማገናኘት       ➬ ድምፅ(beep sound) ካሰማ ይሰራል       ➬ ድምፅ ካላሰማ አይሰራም። 🚩 Capacitor - ከላይ እንዳደረግነዉ እናረግና       ➬ ድምፅ ካሰማ አይሰራም       ➬ ድምፅ ካላሰማ ይሰራል 🚩 Diode -       ➬ ድምፅ ካሰማ አይሰራም       ➬ ድምፅ ካላሰማ ይሰራል 🚩 LED - መልቲሜትራችንን buzzer mode ላይ ካደረግን ቡሃላ       ➬ ledዉ መብራት ከሰጠ ይሰራል       ➬ ካልበራ ደግሞ አይሰራም። 🚩 Ringer - መልቲሜትሩን buzzer mode ላይ ካደረግን ቡሃላ       ➬ መልቲሜትሩ (ከ 8-10) ካነበበ ይሰራል       ➬ መልቲሜትሩ (ከ4-5 ወይም ከ12-14)ካነበበ አይሰራም 🚩 Vibrator - ringer mode አድርገን (ከ8-16) ካነበበ ይሰራል። 🚩 Speaker(earpiece) - መልቲሜትሩን buzzer mode አድርገን       ➬ መልቲሜትሩ (ከ25-30) ካነበበ ይሰራል 🚩Microphone(mic) - መልቲሜትሩን buzzer mode አድርገን       ➬ መልቲሜትሩ (ከ600-1800) ካነበበ ይሰራል 🚩 Keypad -      መልቲሜትሩን ኮንቲኒቲ ላይ ካደረግነዉ ቡሃላ       ➬ ድምፅ(beep sound) ካሰማ ይሰራል       ➬ ድምፅ ካላሰማ አይሰራም። 🚩 Battery connector - መልቲሜትሩን 20V dc ላይ ካደረግን ቡሃላ የbattery connecteru +ve እና -ve ላይ እናደርግና       ➬ (ከ1.5-3.5V ) ካነበበ ይሰራል 🚩 battery - መልቲሜትሩን 20V dc ላይ ካደረግን ቡሃላ የባትሪዉ+ve እና -ve ላይ እናደርግና (3.7 በላይ) ካነበበ ይሰራል       ➬ ቻርጅ ለማድረግ 3.0,3.2 እና ከዛ በላይ መሆን አለበት። 🚩 On/off switch- መልቲሜትሩን 20V dc ላይ       ➬ ቡሃላ የswitchu +ve እና -ve ላይ እናደርግና (ከ2.5-3.7) ካነበበ ይሰራል
Show all...
👍 41 7🥰 4👎 1👏 1
ተጠንቀቁ! ⚠️ ስለ ኦንላይን ቢዝነስ እና ፎሬክስ እየተማሩ መስራት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ እያሉ በማጭበርበር $100 USD Deposit ማድረግ እንዳለባችሁ ጥያቄ በማቅረብ ስልጠናውን በመውሰድ ገንዘብ በቀላሉ እንደምታገኙ በመንገርና በማሳመን $1000 በኢትዮጵያ ከ55,000 ብር በላይ ተበልተህ ስራህን ትጀማራለህ ማለት ነው። ⚠️ የተለያዩ የቴሌግራም VIP1..... የሚሉ ብዙ ግሩፖችን በመፍጠር ሰዎች ወደ ግሩፑ እንዲገቡ በማድረግ በForex ስም ብዙ ገንዘቦችን ወደ እራሱ አካውንት ብር እንዲያስገቡ እንዲያደርጉ አሳማኝ ቃላቶችን በመጻፍና በመናገር እያጭበረበረ ነው። ⚠️ ከታዋቂ ሰዎች ጋር የተነሳውን ፎቶ በማሳየት፣ የራሱ ፈጠራ ሳይሆን የሌላን ሰው የፈጠራ ሀሳብ ኮፒ በማድረግ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች የማጭበርበር ኢንተርቪው በማድረግ፣ የማሳመኛ ቃላቶችን በመደርደር፣ ውጭ ሀገር እወዳችኋለሁ በማለት በብዙ ሽህ ብሮችን በአካውንቱ እንድታስገቡ በማድረግ የመጭበርበር ስራውን እየቀጠለ ሲሆን ከዚህ በፊት ብዙ ኢትዮጵያዊያንን በብዙ ሚሊየን ብር አጭበርብሮ፣ ታይላንድ ሀገር በፖሊሶች ተይዞ ብዙ ጊዜ በመታሰር ወደ ሀገሩ የተመለሰና፣ አሁንም በማጭበርበር ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ብዙ ስዎችን እያስለቀሰ ነው። ⚠️ በዚህ የማጭበርበር ተግባሩ የማይተውና አጭበርብሮ የወሰደውን ገንዘብ የማይመልስ ከሆነ መረጃዎችንን አጠናከረን ይፈ የምናደርግ ይሆናል። ⚠️ ስለሆነም ውድ ኢትዮጵያዊያን አውስትራሊያና አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የአለማችን ክፍሎች ስራ አስቀጥራችኋለሁ። የቅጥር ፎርም ልኬላችኋለሁ ሞልታችሁ ላኩልኝ በፍጥነት የአየር ትኬት ትቆርጣላችሁ፣ እኔ ቆርጬ እልክላችኋለሁ፣ ነገር ግን ብር አስገቡ እያለ የሚያምታታውን ሰው አትመኑ። ተጠንቀቁ! በቀጣይ መረጃዎችን አጠናክረን የምንለቅቅ ይሆናል።
Show all...
👍 121 22👏 9👌 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.