ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons
Open in Telegram
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ስለታሪካቸው፣ ሃይማኖታዊ ትርጉማቸው፣ አሣሣል መረጃ የሚያገኙበት ቦታ፡፡ A channel that discusses about icons of ethiopian orthodox tewahido church. Contact for questions @shihaile or ethioicons@gmail.com or www.ethioicons.wordpress.com
Show more4 968
Subscribers
-224 hours
+97 days
+4230 days
Posts Archive
የመጀመሪያው ሥዕል (የቀሲስ አማረ ክብረት ሥዕል)
የሥዕሉ አቀማመጥ ክፍፍል
ባለታሪኮች (ዋነኛው ምስል)፦ በግምት ከጠቅላላው ሥዕል ከ55% እስከ 60% የሚሆነውን ቦታ ይይዛሉ። ማዕከላዊ የሆኑት ምስሎች (ቅድስት ሐና፣ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅዱስ ኢያቄም) በትልቅ መጠን ተስለው በሥዕሉ የታችኛው ሁለት-ሦስተኛ ክፍል ላይ በጉልህ ይታያሉ።
ከላይ በግራ በኩል ያለው መልአክ ደግሞ ቀሪውን የላይኛው ቦታ በመያዝ፣ ተመልካቹ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን በባለታሪኮቹ ላይ እንዲያደርግ ያደርገዋል።
የጀርባ ገጽታ እና ክፍት ቦታ፦ በግምት ከሥዕሉ ከ40% እስከ 45% የሚሆነውን ቦታ ይይዛሉ። ምንም እንኳን የጀርባው መልክዓ ምድር (ተራራው፣ ዛፎቹ እና ወንዙ) በዝርዝር ቢሳሉም፣ ዋና ተግባራቸው ግን ለቅዱሳኑ ምስል እንደ "ክፈፍ" ወይም ማጀቢያ ሆኖ ማገልገል ነው። በሥዕሉ ላይ ምንም ዓይነት ባዶ ወይም ግልጽ ቦታ የለም፤ እያንዳንዱ ክፍል በለመለመ አረንጓዴ ተክሎች ወይም በሰማይ ተሞልቷል።
ክብደት (Visual Weight)፦ በባለታሪኮቹ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት ደማቅ ቀለሞች እና ትላልቅ አውድማዎች (Halos) ለሥዕሉ ከፍተኛ የክብደት ስሜት ይሰጡታል። ይህም ባለታሪኮቹ ከጀርባ ካለው ደብዛዛ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ተፈጥሮአዊ ቀለም ወጥተው በጉልህ እንዲታዩ ያደርጋቸዋል።
ውህደት፦ የጀርባው ገጽታ ዝም ብሎ መጋረጃ ሳይሆን ሰዎቹ ያሉበት አካባቢ ነው። ባለታሪኮቹ በተፈጥሮው ውስጥ (በአለት/በግንድ ላይ ተቀምጠው እና በዛፎች ተከበው) መሳላቸው በሰዎቹ እና በጀርባው ገጽታ መካከል ያለውን ክፍተት ያጠባል።
ጥልቀት (Perspective)፦ የጀርባው ገጽታ የሩቅ ተራራዎችን በማሳየት የጥልቀት ስሜት ይፈጥራል፤ ይህም በትልቅ መጠን የተሳሉት ባለታሪኮች ከሥዕሉ ወለል ጋር ተጣብቀው እንዳይታዩ (Flat እንዳይሆኑ) ይረዳል።
ሁለተኛው ሥዕል (የዲማ ጊዮርጊስ የሚገኝ) ከመጀመሪያው በከፍተኛ ሁኔታ የተለየ ሲሆን፣ ይህም የጥንቱን እና ትውፊታዊውን የኢትዮጵያ አሳሳል ስልት (አይኮኖግራፊ) የሚያንጸባርቅ ነው።
የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነቶች
ጥልቀት እና ቅርጽ፦ የመጀመሪያው ምስል እንደ ጥላ እና ብርሃን (shading) ያሉ ዘመናዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የምስሉን እውነታ ለመግለጽ ሲሞክር፣ ሁለተኛው ምስል ግን ጠፍጣፋ እና ምሳሌያዊ ነው። በሁለተኛው ምስል ላይ ያሉት ሰዎች አሳሳል እውነታን ከመከተል ይልቅ፣ ለባህላዊ ሃይማኖታዊ ስነ-ጥበብ የሚሰጠውን ትርጉም (በተለይም ትላልቅ እና የአልሞንድ ቅርጽ ያላቸው አይኖች) ይከተላል።
የቀለም ምርጫ፦ በዚህ ምስል ላይ ያሉት ቀለሞች የመሬት ቀለሞችን (እንደ ቀይ አፈር፣ ቢጫ እና ጥቁር ሰማያዊ) የመሰሉ ናቸው። ይህም በጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከእጽዋት እና ከማዕድናት የሚዘጋጁ ቀለሞችን ያሳያል። የመጀመሪያው ምስል ግን በጣም ደማቅ እና ዘመናዊ ቀለሞችን ይጠቀማል።
ዝርዝር አሳሳል፦
ይህ ምስል በደማቅ ጥቁር መስመሮች የተከበበ ሲሆን፣ እንደ ልብሶቹ ላይ ያሉት ኮከቦች እና አበቦች ያሉ ተደጋጋሚ ዲዛይኖችን ይጠቀማል። የመጀመሪያው ምስል ግን ቅርጾችን ለመለየት ከመስመሮች ይልቅ ቀለሞችን የማዋሃድ ዘዴን ይጠቀማል።
ክፍት ቦታ እና የጀርባ ገጽታ ንጽጽር
በዚህ በሁለተኛው ምስል ላይ "ክፍት ቦታ" (Negative Space) የሚባል ነገር የለም ማለት ይቻላል።
ይህ ዘይቤ "ባዶ ቦታን የመጥላት" (horror vacui) የተባለውን ጥንታዊ የአሳሳል ፍልስፍና ይመሳሰላል።
ባለታሪኮች (Subject)፦ ከምስሉ ውስጥ ወደ 75% እስከ 80% የሚሆነውን ቦታ ይይዛሉ። ሰዎች እርስ በርስ ተቀራርበው እና ተደራርበው በመሳላቸው በሥዕሉ ላይ ምንም ክፍት ቦታ እንዳይኖር ተደርጓል።
ክፍት ቦታ እና የጀርባ ገጽታ፦ የሚቀረው ቦታ 20% እስከ 25% ብቻ ነው። ሰዎች በሌሉበት ቦታ እንኳን እንደ አምዶች፣ የጂኦሜትሪ ቅርጾች፣ ጽሑፎች እና የአበባ ዲዛይኖች ተሞልተውበታል።
የሁለቱ ንጽጽር፦
በመጀመሪያው ምስል ላይ የጀርባው ገጽታ (ተራራው እና ጫካው) እንደ መስኮት ሆኖ ያገለግላል፤ ይህም በሰዎቹ ዙሪያ ሰፊ አየር እንዲኖር ያደርጋል።
በዚህ በሁለተኛው ምስል ላይ ግን የጀርባው ገጽታ እንደ ምንጣፍ ወይም ጌጣጌጥ ነው። የጀርባው ገጽታ እና ሰዎቹ በአንድ ወጥ ጠፍጣፋ ቦታ ላይ ያሉ ይመስላሉ።<<ዕቅበተ እምነት በእንተ ቅዱሳት ሥዕላት>> ቨርቹዋል ሌክቸር (online iconography lecture series)
ቅጽ 1 ክፍል 2
ርእስ:- የቤተ ክርስቲያን ሠዓሊ ሕይወትና ፈተናዎች በዚህ ዘመን
ቀን፦ ሚያዚያ 18 2018
ሰዓት፦ 2:00- 3:30 ማታ
በኃይለ ማርያም ሽመልስ ( ሠዓሊ፣ በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ መጻሕፍት አዘጋጅ፣ አማካሪ፣ ጥናትና ሒስ አድራጊ )
ሊንክ:- የቤተ ክርስቲያን ሠዓሊ ሕይወትና ፈተናዎች በዚህ ዘመን
Google Meet joining info
Video call link: https://meet.google.com/dap-vmga-wrp
ይጠቀማል ብለው ካመኑና ከወደዱ ለሌሎች ማጋራት ይችላሉቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ ለጥያቄ፣ አስተያየት 📩 ሠዓሊ ኃይለማርያም ወይም ☎️ 0913052824 ላይ ያናግሩን። ++++++⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️+++++++++ ትውፊቱን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ። ቤተሰብ ለመሆን በፈለጉት መንገድ መቀላቀል ይችላሉ። 👇👇👇👇👇👇👇 YouTube website Telegram Facebook Instagram || Tiktok ++++++++⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️+++++
ከላይ በነበረው መጠየቂያ የሞሉ ወንድምና እህቶች
43% በመቶ እሑድ
35 % ደግሞ አርብ እና
28% ሐሙስን መርጠዋል።
በመሆኑም መርሐግብሩን የሞሉትን መሠረት በማድረግ እሑድ አንደኛውን እና አርብ ሁለተኛው መርሀግብር ለዚህ ወር ተመርጧል።
በቀጣይ እሑድ የመጀመሪያው መርሐግብር የሚኖር ሲሆን ከ15 ቀን በኋላ አርብ ሁለተኛው መርሀግብር ይከናወናል።
ሰዓቱ 2:00- 3:30 ይሆናል።
በሰዓት መገኘት ወሳኝ ሲሆን፤ አርፋጆችን አንታገስም።
የተለየ ነገር ቢያጋጥም እንኳን 15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ሰው አንቀበለም።
በተጨማሪም ከተቀመጠው የጊዜ መርሀግብርም ሰዓት አናሳልፍም።
በሰዓታችን እንጀምራለን በሰዓታችን እንጨርሳለን።
በዚህ ወር የሚገኘውን የሰው ብዛት ዓይተን በቀጣይ ወር በአንዱ (ከእሑድ ወይ ከአርብ) እንቀጥላለን።
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 0913052824 ላይ ማነጋገር ይችላሉ።
መርሐግብር ይዘት
5 ደቂቃ መግቢያ ጸሎት
40 ደቂቃ ገለጻ (presentation)
40 ደቂቃ ጥያቄና መልስ ውይይት (reflection,and discussion)
5 ደቂቃ መዝጊያ ጸሎት
ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች
ባለፉት የጾም ወራት ለራሴ አረፍት በማሰብ ከአገልግሎት ርቄ ነበር። በዚህ በበዓለ ሐምሳ የተመለስኩኝ ሲሆን በቀጣይ የሚኖሩን አቅም እንደ ፈቀደ
1. በየ 15 ቀኑ በኦንላይን ቨርቹዋል ሌክቸር (online iconography lecture series) የሚኖር ይሆናል
ቀኑ በዚህ የወሰንኩት ርእሰ ጉዳዮችን ለመወያየትና ለመማር ብሎም ያገኘነውን መረጃ ለማሰላሰል ጊዜ ስለሚሰጥ ነው።
በዚህ በበዓለ ሐምሳም በተከታታይ ከሚቀርቡ ይዘቶች መካከል
ሀ. የሠዓሊው ሕይወትና ፈተናዎች በዚህ ዘመን (መጽሐፍ ቅዱስና የአበው አስተምህሮን መሠረት በማድረግ)
ለ. ሠዓሊው ስለሚጠቀምባቸው ቀለማት ታሪክ፣ ባሕርያት፣ ትርጉሞች
በዚህ ዘመን ስለሚታዩ ዐበይት መልካም እና ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች
ሐ. ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል
2. በተወሰኑ ዕለታት ደግሞ የተመረጡ ቅዱሳን ሥዕላቸውን ከአጫጭር መግለጫዎች
(ጥንታዊ ይሁኑ በዚህ ዘመን የተሣሉ) በጽሑፍ የሚቀርብ ይሆናል።
ይጠቀማል ብለው ካመኑና ከወደዱ ለሌሎች ማጋራት ይችላሉቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ ለጥያቄ፣ አስተያየት ወይም ለማሳል 📩 ሠዓሊ ኃይለማርያም ወይም ☎️ 0913052824 ላይ ያናግሩን። ++++++⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️++++++++++ ትውፊቱን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ። ቤተሰብ ለመሆን በፈለጉት መንገድ መቀላቀል ይችላሉ። 👇👇👇👇👇👇👇 YouTube || website || Telegram|| Facebook || Instagram || Tiktok ++++++++⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️+++++
+4
ሐሙስ ፡-አዳም ሐሙስ
እንኳን ለአባታችን አዳምና
ለእናታችን ሔዋን መታሰቢያ ዕለተ ሐሙስ አደረሳችሁ።
አዳም በበደለ ጊዜ በደሉን አምኖ ንስሓ ገባ፤ ተጸጸተ፤ እግዚአብሔርን መበደሉንና ትእዛዙን መጣሱን አምኖ ለብዙ ዓመት ሲያለቅስ ኖረ፤ ጠላትም አስጨንቆ ገዛው፤ የዕዳ ደብዳቤ አጽፎ ‹አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ፣ ሔዋን ዓመቷ ለዲያቢሎስ› የሚል የዕዳ ደብዳቤ አጻፋቸው፤ አዳምም ስለበዱሉ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ጌታችንም የአዳምን መጸጸትና መመለስ ተቀብሎለት አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ገባለት፤ ይህም ዕለት በዚህ ቀን ይታሰባል፤ አዳም ሐሙስ መባሉ ለዚህ ነው፡፡
ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌግራም ቻናል
ሥዕል፦
1 ደብረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙና
2 በሠዓሊ ኃይለማርያም ሽመልስ የተሣለ
ዜና_ዕረፍት
ለበርካታ ዓመታት ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ቅዱሱን ሕያው ወንጌል በታማኝነትና በትጋት ያለዕረፍት ያገለገሉት መምህር_ዘለዓለም_ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከድካመ ሥጋ ዐረፉ።
ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ ገብርከ ወልደ_ሰማዕት
ሀገረ ሕይወት መንግስተ ሰማያት ያውርስልን፤ በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን፤
ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service
ትላንት በነበረን መርሐግብር ላይ በኦንላይን ሲከታተሉ የነበሩ ወንድምና እህቶች የድምጽ አለመደመጥና የኔትወርክ መቆራረጥ አጋጥሞ ነበር።
በመሆኑም ይህንን ለመቅረፍና በአካል ሊገኙ ወደው በተለያየ ምክንያት ያልተገኙ ወንድሞች በጉባኤው ላይ የቀረበው መነሻ የምክረ ሀሳብ ጽሑፍ በድጋሚ በኦንላይን እንዲቀርብ ጠይቀዋል።
ስለዚህ ነገ የካቲት 24 2018 ከምሽቱ 1:30 እስከ 3:00 ገለጻና ውይይት ይኖረናል።
በኦንላይን ለተመዘገባችሁም በአካል መገኘት ላልቻላችሁና ላመለጣችሁ መርሐግብሩ በድጋሚ ተዘጋጅቷል።
በኢትዮጵያ ማታ 1:30 – 3:00
Google Meet joining info
Video call link: https://meet.google.com/pvs-kuaf-gtx
ሰላም
የቤተ ክርስቲያን ሠዓሊያን ኅብረት ጉባኤ
ጉባኤውን በኦንላይን ለመከታተል
Sunday, March 1 · 2: 30 – 5: 00 pm
Google Meet joining info
Video call link: https://meet.google.com/vow-vvxi-anr
ማስታወቂያ
ለኦርቶዶክሳዊያን ሠዓሊያን፣ ቀራጺያን፣ አርክቴክቶች፣ ግራፊክስ ዲዛይነሮች
በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተና እና ችግር ላይ ናት። ይህንንም ፈተና በዘላቂነት ለመቅረፍና ጥበቧን ለቀጣይ ተውልድ ለማስተላለፍ ኅበረት አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው።
ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሠዓሊያን ኅብረት ለመመስረት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
ውድ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የሆናችሁ የጥበብ ሰዎች በዚህ
ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ በቅዱስ ሉቃስና በቅዱስ መብዓጽዮን ስም ጥሪ እናቀርባለን።
ቦታ፥ ገርጂ ማርያም የሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ቀን፥ የካቲት 22፣ 2018 ዓ.ም. (እሑድ)
🕰 ከ 8:00 - 11:00 (ከሰዓት)
በእለቱ መሳተፍ የምትፈልጉ እስከ የካቲት 20 2018 ዓ.ም.
ከታች👇👇👇👇 ባሉው መመዝገብ ትችላላችሁ።
ፎርም
https://forms.gle/G7bFf5D4bj7m9RBa7
በዚህ ጽሑፍ ሳፍራ (እሥራልዩ) የሚባለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሱርያል ሥዕል አሣሣል በጥቂቱ እንዳስሳለን።
ሳፍራ “እሥራልዩ” ማለት “የእሥራኤል ረዳት” ማለት ሲሆን። የመላእክት መዓርግ ሲነገር ከቅዱስ ሚካኤል፡ ቅዱስ ገብርኤል፡ ቅዱስ ሩፋኤል በመቀጠል አራተኛ የሚመጣው ቅዱስ ሱርያል ነው።
ሙሉውን 👇👇👇 ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።
https://ethioicons.wordpress.com/2026/02/04/st-sureyal-angel-icon/
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሱርያል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።
