cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🔶Alhamdulillah🔶 Islamic advice

🍃﷽🌙 Any promotion doesn't express us!! If you wanna a good time, go to the first message and read posts 😎 In box me @Yutinnn @Lamborghini438

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
487
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
እስልምና ያልደረሰበት መንደር መኖሩን ሰምቷል። በዚህም በእጅጉ ተክዞ ያሰላስል ይዟል። ባልደረቦቹ በአዞዎች የተከበበ ወንዝ መሐል ላይ አለ ሲሉ አስጠንቅቀውታል። ስለራሱ ሲያወጋን እንዲህ ይለናል፡- "በጀልባ ላይ ተፈናጠን ጉዟችንን እስልምና ወዳልደረሰባት መንደር ማድረግ ጀምረናል። አዞዎች ጉዟችንን ሊያሰናክሉ ዙርያችንን ከበው ከዚህም ከዚያም ይራወጣሉ። ከእልህ አስጨራሽ ጉዞ በኋላ ያለአንዳች እንከን መንገዳችንን አጠናቀን ወደ ከተማዋ ዘለቅን። "እንዴት በሰላም ደረሳችሁ" ሲሉ የመንደሯ ነዋሪዎች ጠየቁን። "አላህ ጠብቆ እዚህ አደረሰን አልናቸውና ስለ እስልምና ገለጽንላቸው ስለ ዲኑም አስተማርናቸው" መሪያቸው እንዲህ አለ፡- "ቅድመ ሁኔታችንን ከፈፀምክልን ወደ እስልምና እንገባለን" አሉኝ "ምንድን ነው" አልኩት "ዝናብን ለዓመታት አይተን አናውቅምና ጌታህን ለምንልን" አሉኝ። "የመንደሩን ሰዎች ሰብስቡልኝ አልኳቸው። ተነሥቼ ውዱእ አደረኩና መስገድ ጀመርኩ። በጣም አልቅሼ አላህን ለመንኩት ሱጁድ ላይ አላህን ተማፀንኩት "ጌታዬ ሆይ! የአብዱረህማንን ዲን በአብዱረህማን ወንጀል ከመርዳት አትቆጠብ" እያልኩ አለቀስኩ። ቀና ስል ደመናን ከሰማይ ላይ ተመለከትኩ። ዝናቡ መንጠባጠብ ጀመረ። ህዝቦቹም እስልምናን ተቀበሉ። አዎ... በአፍሪካ አህጉር እስልምናን ለማስፋፋት ከ29 አመታት በላይ የለፋ ብዙ ሚሊዮኖችን በእጁ ያሰለመ ድንቅ ሰው ነው። ወደ 5,700 የሚጠጉ መስጂዶችና የውሀ ጉርጓዶችን ገንብቷል። 15,000 ወላጅ አልባ ህፃናትን ተንከባክቦ ያሳድጋል ያስተምራል። 124 ሆስፒታሎችንና ክሊኒኮችን፣ 840 ትምህርት ቤቶችን ገንብቷል። እርሱ በሀገረ ኩዌት የተወለደው አብዱረህማን አል ሱመይጢ ይሰኛል። አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው። Mahi Mahisho @strong_iman
Show all...
🚫:::::::::::ድንግል/ቢክራ አላገኘዉባትም:::::::🚫 ልጅ አገረድ አገባ ግን (ቢክራ) ድንግል አላገኘባትም ?? ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ :- ➪ ጥያቄ:- ሰውየው ልጅ አገረድ አግብቶ ድንግል ሁና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት ? ➪ መልስ:- ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል : ድንግሏ ምናልባት ያለ ዝሙት ሊፈርስ ይችላል። የልጂቱ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው። በዚያ ላይ ጥሩ ጥርጣሬን ማሳደር ግድ ይላል። - ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችሁ መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል። ከዚያም ወደ ጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች (ቢክራ) ድንግል አለመኖሯ እሱን አይጐዳውም። - ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምከንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል። ጠንካራ (ሃይድ) የወር አበባ (ቢክራን)ድንግልን ያፈርሳል። ይሄህ ኡለሞች አውስተውታል። - ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ከሆነ ቦታ ወደሆነ ቦታ ስትዘል። ወይንም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድ ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ➪ ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም። በጭራሽ። ከዝሙት ውጭ በሆነ ክስተት ነው ድንግል የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም። - ወይንም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሃይምነቷ ጊዜ እንደሆነም እናም አሁን ከዚያ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም። - ይሄን የሷን ሚስጥር ሊበትንባት እና ሊያሰራጭባት አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል። በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም መስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያስቀራታል። ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር በጭራሽ ሚስጥሯን ባደባባይ መግለፅ አይገባውም። ምንጭ፡- መጅሙዕ አል-ፈታዋ (287/286-30) ✍ (ሁሴን አህመድ)✍✍
Show all...
ወጣት ሆይ... Part 2 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ቢስሚላሂ ወጣት ሆይ በክፍል 1 ባጭሩም ቢሆን የጊዜን መብረር አይተናል። አሁን ላይ ሁነህ ስታስበው ታምንበታለህ። የጊዜን ፍጥነት መቼ ነግቶ መቼ መሸ የሚባልበት ዘመን መሆኑንም ጭምር ግን ለምን ይህን እሳቦህን እራስህ ላይ ለመስራት አትጠቀምበትም ማለትም:- 1 የሆነ ቀን ላይ ሲከፋህ ብቸኝነት ሲሰማህ ሂወት አንተ ላይ ብቻ የተደራረበች ሲመስልህ ለምን ለዚህ ለሚሮጥ ጊዜ 1 ቀን ያመት ያህል አዝናለሁ ነገ ለሚያልፍ ቀን አትልም? 2 ወጣትነት ስሜት አጉል ደስታና ጊዜ አዊ ስሜት ስይዝህ ለየትኛው እድሜ ለየትኛው ቀን ለየትኛው ጊዜዬ ነው ጌታዬን የማስቀይመው? ይህኮ ደስታ አጉል ድበር ማለፍ ሳላቀው ያልፋል ግን ነገ ሂሳቤ ይወራረዳል፡ ነገ ይች ስራዬ ትጽፋ ትሰጠኛለች ነገ ይች ስራዬ ብዙ የኸይር በሮችን ትዘጋብኛለች። ለመሆነ የቱን ያህል ልደሰት? አመት ወር በሆነበት ጊዜ? ለምን አትልም? 3 አንድ በድሜ ሸምገል ያሉ ሰው ዘንድ አንድ ወጣት ተቀምጦ እያወጉ ሳለ ወጣቱ ከፊት ለፊቱ ያሉትን አዛውንቶች ተመልክቶ እዲህ አለ:- ' አባባ እኒህ አዛውንቶች በዚህ እድሜቸው ሰው ያማለሁ አጂብ ነው የሸይጣን ስራ! ' ሽማግሌውም ' አይ ልጄ ይሄ የሸይጣን ስራ ነውን?' ወጣቱ ' አባባ ታዲያ ይሄ የማን ስራ ሊሆን ይችላል? እኒህ ሰወች በዚህ እድሜያቸው ማሃርታን መጠየቅ ምን ያማረ ስራ ነበር። ግን ሸያጣን እነሱን በማሳሳት ተጠምዷል!!' ሽማግሌውም:- ' ልጄ እኔ ከሂወት የተማርኩትን ስማኝ ሸይጧን የ አደም ልጆች ላይ ስራውን የሚሰራው በወጣትነት እድሜ ላይ ነው ያኔ አቅሙም ጉልበቱም እዳለህ ከዛማ አካልህ ያንን ትለምድና ስታረጅ ያለ ሰይጣን ውስወሳ ያኔ የምታደርገውን ታደርጋለች።' ወጣቱም ' አባባ ቲኒሽ ጨምሩልኝ?' ሽማግሌውም:- 'ለይል የመቆም አቅም ያለህ ጊዜ መተኛትን ይመክርሃል ያኔ እሺ ካልከው ጉልበትህ ሲዝልና አቅምህ ሲደክም ይተውሃል ያኔ አስለምዶሃልና! ልጄ ጠንካራ ቆዳ እያለህ ውዱን ይቀዘቅዘኛል ብለህ ከተውከው ስታረጅ ያቃጥለኛል ብለህ ትፈራለህ። ልጄ ደአዋ በሚያደርግ አንደበትህ ሰው መዝለፍ ላይ ከተጠመደ ስታረጅ ምላስህ በራሷ ማማትን ልክ እንደ ሱስ ታዝሃለች። ልጄ ወጣትነት የልምምድና እራስን ማሰልጠኛ ጊዜ ነው። እርጅና ግን ያኔ የተለማመድከውንና የሰለጠንከውን መተግበሪያ መሙያ ነው። ለዛ ነው ዛሬ እነሱን የምታያቸው በዚህ ሃል ላይ። አሁን ከነሱ ሸይጧን ሃጃ የለውም ያኔ ጨርሷል።' አሉም ይባላል። እናም ወጣት ሆይ ዛሬ ልምምድ ነው የሆነ ቀን እራስህን አርጅተህና አቅምህ ተዳክሞ ታገኘዋለህ። ያኔ ግን ዛሬ እራስህን ባትተማርከው ላይ ነህ።
Show all...
ልጁና አያትየው እየተጫወቱ ሳለ አያትየው :- "ልጄ ሆይ! #ጀነት የሚገባው በነፃ ሲሆን #ጀሀነም ግን በገንዘብ ነው የሚገባው" ልጅየው :- "ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል አያቴ?" አያትየው :- "ቁማር የሚጫወት ሰው ገንዘብ ይከፍላል፣መጠጥ የሚጠጣ ሰው ገንዘብ ይከፍላል፣ለፋሂሻ (ሃራም ተግባር) ለመፈፀም ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ የሚጓጓዘው ሰው ገንዘብ ይከፍላል፣ሙዚቃ ለማዳመጥ የሚፈልግ ሰው ገንዘብ ያወጣል፣ነገር ግን ከዚህ በተገላቢጦሽ #ጀነት አንዲትም ወጪ አታስወጣም፡ ምክንያቱም ሰጋጁ ሲሰግድ ገንዘብ አይከፍልም፣ጿሚውም ሲፆም ወጪ አያወጣም፣እስቲግፋር የሚያደርገውም በኢስቲግፋሩ ወቅት ወጪ አያወጣም፣ዓይኑን ከአላስፈላጊ ዕይታ ላይ የሚቅብ ገንዘብ አይከፍልበትም ፣…" "ስለሆነም ልጄ #ጀሀነም ለመግባት ወጪ ማውጣት ነው የሚሻልህ ወይስ ወደ #ጀነት በነፃ ነው መጓዝ የሚያዋጣህ ! ? " የዕድሜ ባለፀጋዎች ምክራቸውና ማስተንተናቸው ምን ያህል ያማረ ነው? ••••••••••••••••••••••°••••••••••••••••• #ወንድሜ_ሆይ ይህች መልዕክት ስትደርስህ በነፃ ነው የደረሰችህ አይደል? ስለሆነም ላልደረሳቸው ወንድሞችህ ላለምንም ወጪ ሳትዳረግ መልዕክቷን አስተላልፍላቸው። Copy
Show all...
ተመኘሁ....🤲🤲 " ልቤ የሚጠቅመኝ ላይ ብቻ እንዲጠለጠል የማይጠቅመኝ እንዲያስጠላኝ ከዛሬው ይልቅ ለነገው አብዝቼ መስራትኝ ከስሜት ሃቅን ከጊዜአዊ ስሜት ሶብርን ጃሂል ሲናገረኝ ፈገግ ብሎ ማለፍና ያኔ እደነበሩት ጀግና ለኢልም ሲል እግሬ የዛለ ስሜ በሰማይ የገነነ ጀግና ተራራ የማይበግረው ቆራጥ አላህንጂ ማንንም የማይፈራ ደንዳና ልብ ያላት ቤቴ በድቅድቅ ጨለማ ለሰማይ የሚያበራ እዲሆን ተመኘሁ።"
Show all...
👉!!!! ጓደኛዬ ጋር ለቅሶ ለመድረስ ሄጄ ከሌሎች ባልንጀሮቻችን ጋር ተሰባስበን ካዝሚር ዛፍ ስር ተቀምጠን ነበር፡፡ ፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ የበሰለ ፍሬ እጄ ውስጥ ወደቀ፡፡ ስቀምሰው እጅግ ጣፋጭ ሆኖ አገኘሁት በኋላ እንጨት አምጡ ብዬ ፍሬውን ዳግም አርግፌ መብላት ስጀምር መረረኝ፡፡ ፡ እንዴት ነው እጄ ላይ የወደቀው ጣፋጭ ነበር ያራገፍኩት ግን መረረኝ ስል፤ ከጓደኞቼ መካከል አንዱ እንዲህ አለኝ "የመጀመሪያው በጊዜው ስለወደቀ ጣፈጠህ ሁለተኛውን ያለጊዜው ስላራገፍከው መረረህ" አለኝ፡፡ ተመልከቱ ፈጣሪ የሚጠቅመንን ነገር በጊዜ እጃችን ውስጥ ይጥለዋል፡፡ እኛ ግን በግድ ይሁን ብለን በምናስቸግረው ጊዜ ጣፋጭ ያልሆነ ፍሬ እጃችን ውስጥ ይቀራል፡፡ ስለዚህ የትዕግስት ተራራ ላይ ሆነን አምላካችንን እንጠብቀው፡፡ ልመናችንን በራሱ ጊዜ ይፈጽመው ዘንድ እድል እንስጠው፡፡ የእርሱ ከሆነ ጣፋጭ ነውና። መልካም ምሽት መልካም አዳር ደግሞ ብርድ ነው ደረብ ደረብ አርጉ Copy
Show all...
Repost from Ibnu Muhammedzeyn
➥ ከዙል ሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናቶች ያላቸው ትሩፋት ✔️ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ለአማኝ ባሮቹ መልካም ሾል ምንዳው የሚበዛባቸው የተለያዩ ጊዜያትን እና ወራቶችን አድርጓል። ከእነዚህ ወራቶችና ቀናቶች መካከል የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናቶች ናቸው። በእነዚህ ቀናቶች የሚሰራ መልካም ሾል ከሌሎቹ ቀናቶች ከሚሰሩ መልካም ስራዎች በእጥፍ ድርብ ይበልጣል ለዚህም መልእክተኛው (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ በሌሎች ቀናቶች ከሚሰሩ ስራዎች የበለጠ ተወዳጅ እንደሆነ እንድህ ሲሉ ተናግረዋል:- عَنْ Ř§Ř¨Ů’نِ عَبَّاسٍ ŘŒ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشْرِ " فَقَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ "  ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንድህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል:- «አላህ ዘንድ መልካም ሾል ተወዳጅ የሆነበት ከእነዚህ አስር ቀናቶች የበለጠ ማንም ቀን የለም። –ሶሐቦች አንተ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በአላህ መንገድ መታገል(ጅሃድ እንኳ) ቢሆን አሉ– ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይ ወሰለም) «በነፍሱም በገንዘቡም ጅሃድ ወጥቱ ከእርሱ በምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጅሃድ) እንኳ ቢሆን (በእነዚህ አስር ቀናቶች ከሚሰራ መልካም ሾል አይበልጥም) Âť አሉ [ ቡኻሪ (2/457) እና ሌሎችም ዘግበውታል] ✔️ በዚህ ሐዲሥ ግልፅ እንደተደረገው በሌሎች ቀናቶች ከሚሰራ መልካም ሾል በእነዚህ አስር ወናቶች የሚሰራ መልካም ሾል አላህ ዘንድ ተወዳጅ ነው። [ኢማሙ ዳርሚይ (1/358)] በዘገቡት ሌላም ሐዲሥ ላይ በእነዚህ አስርቀናቶች የሚሰራ መልካም ሾል በሌሎች ቀናቶች ከሚሰራ መልካም ሾል ምንዳው(አጅሩ) እንደሚበልጥ ተላልፏል። ✔️እነዚህ አስርቀናቶች በጣም ከባድ ለመሆናቸው ዑለሞች ዘንድ ከዙልሒጃ የመጀመሪያ አስር ቀን እና ከረመዳን የመጨረሻ አስር ቀን ማን ይበልጣል በማለት ጠንከር ያለ ኺላፍ አላቸው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ(ረሒመሁሏህ) እሄን ሁለት ኺላፍ እንድህ በማለት አሰማምተዋል የዙልሒጃ የመጀመሪያ አስር ቀን ከረመዳን የመጨረሻ አስር ቀን ይበልጣል የረመዳን የመጨረሻ አስር ለይሎች ከዙልሒጃ የመጀመሪያ አስር ለይሎች ይበልጣሉ። ✔️ ስለዚህ በቅድሚያ አላህ በሰላም ካደረሰን እንድህ የመልካም ሾል ምንዳ የሚበዛበትና መልካም ሾል ከሌሎቹ ቀናቶች በተለዬ አላህ ዘንድ የሚወደድበት ጊዜዎች ላይ ስላደረሰን አላህን ልናመሰግን በውስጣችን በጣም ትልቅ ኒዕማ እንዳገኝን ልናውቅ ይገባል። በእነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ሁሉም መልካም ሾል ይወደዳል ስለዚህ ከእነዚህ መልካም ስራዎች የተገራልንን በመስራት የብዙ አጅር ባለቤት ለመሆን እንጣር ከእነዚህ መልካም ስራዎች መካከል ➼ ነፍል (ትርፍ ግዴታ ያልሆኑ) ዒባዳዎችን ማብዛት ለምሳሌ ሱና ሶላቶችን መስገድ፣ሶደቃ መሶደቅ ➼ ዚክር ማብዛት: አልሐምዱሊላ ተክቢር(አሏሁ አክበር) ተሕሊል (ላኢላሀ ኢለላህ) ተስቢሕ (ሱብሓነላህ) እና ቁርኣን መቅራትን ማብዛትና ዱዓእ ማብዛት ➼ ፆም የዙል ሒጃን ወርቃማ ቀናቶች ሁሉንም ወይንም ብዙውን በመፆም የብቻው መረጃ ባይመጣም ፆም ከመልካም ስራዎች ጭምር ስለሆነ መፆምን ያነሳሱ ዑለሞች ስላሉ ብንፁም ጥሩ ነው ➼ እንድሁም አቅሙ የሚፈቅድ ሰው ኡዱሕያን ማረድን መዘናጋት የለበትም ➼ ለወላጅ መልካም መዋል፣ዝምድና መቀጠል የተቸገሩን መርዳት ➼ እንድሁም ተውበትና በቁርጠኝነት ወደአላህ መመለሾ ✔️ በነዚህ የተከበሩ ቀናቶች ወንጀልን መራቅ አለብን ኢብኑ ረጀብ እንድህ ይላሉ:- «ወንጀልን ተጠንቀቁ እርሷ በሚታዘንባቸው አጋጣሜዎች መሀርታን ትከለክላለች» «ወንጀል(አላህን ማመፅ ከአላህ እዝነት) የመራቅ እና የመባረር ሰበብ ስለሆነች ተጠንቀቁ» [ለጧኢፉል መዓሪፍ (254)] 👉 እነዚህን አስር ቀናቶች እንድንጠቀምባቸው ከሚያነሳሱን ነገራቶች መካከል:- ➼ ይህ በእኛ ላይ የተዋለለን የአላህ ትልቅ ኒዕማ እንደሆነ ማወቅ እዚህ ትልቅ ኒዕማ ላይ ጤና እና እድሜ ሰጥቶን በሰላም ከደረስን ይህን ኒዕማ ሳናባክን ሌሎችን በሞት ወይ በበሽታ እንዳለፋቸው እኛንም የሚያልፍብን ቀን ሳይመጣ የተሰጠን እድል ሳያልፍ በአግባቡ መጠቀም እንዳለብን ቆራጥ ውሳኔ መወሰን ኢብኑ ረጀብ እንድህ ይላሉ «ዘንጌዎች ባጠፉት ጥፋት ከመለደማቸው (የሞት) ጊዜ ሳይወርድብን እነዚህን ቀናቶች በመጠቀም እንቻኮል» [ለጣኢፍ (255)] ➼ በእነዚህ ቀን ከማንም ሰው በበለጠ ወደአላህ ለመቃረብ መወሰን እና ቆርጦ መነሳት ➼ ጊዜን በማይጠቅም ነገር ሳያባክኑ በዒባዳ ለማሳለፍ ከወድሁ እራስን ማዘጋጀት አላህ ጘፍላችንን አስወገዶልን ከወንጀል ጠብቁን እርሱ የሚወደውን ሾል በመስራት የምናሳልፈው ያድርገን ✍ወንድማችሁ/ ኢብኑ ሙሐመድዘይን [ዙልቂዕዳህ 29/1443ሂ] ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• t.me/IbnuMuhammedzeyn t.me/IbnuMuhammedzeyn
Show all...
Ibnu Muhammedzeyn

ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ አቅም በፈቀደ መልኩ ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት፦ ① ከቁርኣን፣ ② ከሐዲሥ √ በሰለፎች አረዳድ እንድሁም ③ ከቀደምት እና በዘመኑ ካሉ የሱናህ ዑለሞች ይቀርብበታል።

ጠቅለል ያሉ መልክቶች!!!! አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ. 1 ኢልም ስትማር አደብንም የምትማርበት ሰው ጋር ተማር ስታየው የምታከብረው ከዛዛታና ከክርክር የራቀ ሰው ጋር ሁን። አሊም ነን የሚሉ ብዙ ናቸው አተ ግን አዋቂነቱን በተግባር የምታይበት ሰው ጋር ቅራ። 2 አንዳዴ ሰወችም መልካም አስበህ ቀርበሃቸው ክፉ ይሆኑባሃል። ኢልምን ስትጠይቃቸው ጃሂል የሆንክ ይመስላቸዋል። በነሱ ስራ አትከፋ ምክንያቱም ሰው የሚሰጠው ካለው ነውና። 3 አንዳንድ ሰወች ድገት ይመጡና ከየትም የሰሙትን ሃሜት ተመርኩዘው ልዘልፉህን ሊያንቋሽሹህ ይፈልጋሉ ያም አላስ ብሎ እዲህ ነህ እዲህ ነህ እያቱ አተን ለመግለጽ ይፈልጋሉ። ለነሱ ላስረዳ ብለህ ጊዜ አታባክን ምክንያቱም የመጡት ሊነግሩሕጂ ሊሰሙህ አይደለም። ያኔ ስላተ ብዙ ሲያወሩ " እሺ " በላቸው ቀን ያስረዳቸው ዘንድ። 4 በሰው ሃሳብ አትመራ ማንም ላይ አትገደፍ ከመደገፍ በኩል አላህ ይበቃሃል። ለማን ብለህ ነው ጥገኛ የምትሆነው በቃ ላተ አተ በቂ ነህ ዱኒያ ላይ የመጣከው ከራስ ጋር ነው ስትሄድ እደዛው ስለዚህ መደገፍ ያለብህ ላመጣህና ለምትሄድበት ነው። 4 ክብርህ ከማያውቁ ሰወች ጋር አትዋል። ዝቅ ብለህ ከነሱ ጋር እኩል እድትሆን ይፈልጋሉ በልባቸው እያወቁህ በምላሳቸው ያጎድፉሃል። ይችን በተለይ ተማሪወች ትኩት አርጉባት። 5 እህቴ ጅልባብ ለብሰሽ ወንድ አላወራም እያሽ ህግ በሌለበት እስልምናዬን ብለሽ። አተም ሱሪ አሳጥረህ ሴት አላይም ብለህ አገት ደፍተህ እየኈድክ ለፈተና ልታጋጥጥ ነው። መኮረጅ ሃራም ነው እያልኩ አይደለም እሱን ለ አሊሞች እንተወውና ግን ከ ልቅና ጋር የሚኈድ አይደለም። ሙስሊም ጥብቅ ነው ከማንም አትከጅል በቃ አንብብ ስራ ከዛ ተወኩል ይኑርህ እስኪ አስበው ሙስሊም የክፍሉ 75% ሁኖ 1-3 ካፉር ሲወጣ ልታጨበጭብ ነው። ብቻ ግን " ሃራም ነው ሃላል ነው አንልም ግን ከ ልቅና ጋር አይሄድም" የ አለምን ግማሽ ሲያስተዳድሩ ያልከበዳቸው ኡማ ልጆች ዛሬማ ከ ካፊር በታች አንሆንም በል። እኔ እያለሁ መድረኩን ካፊር አይቆጣጠረውም በል። ከተሳሳትኩ በደስታ እቀበላለሁ ጠቁሙኝ። 📝ju
Show all...
sticker.webp0.60 KB
sticker.webp0.27 KB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.