cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

E4J ስነ ፅሑፍ

በተሰጠን ፀጋ እግዚአብሔርን እናገልግል የተለያዩ መንፈሳዊ የስነ ፅሑፍ ስራዎችን የሚያገኙበት Channel @e4jgxm ❤️መንፈሳዊ መፅሐፍት ❤️ግጥሞች ❤️ወግ እና ❤️ሌሎች መንፈሳዊ ፅሑፎች ይገኙበታል ዋናውን ግሩፕ ለማግኘት 👇👇👇👇 ❤️ @e4jesus❤️

Show more
Advertising posts
539
Subscribers
No data24 hours
+27 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ይሰበር ብልቃጤ እሩቅ በተባለች ቢታንያ መንደር፤ ኢየሱስ ሲገባ በትንሿ መንደር፤ ከፈሪሳዊው ቤት ግብዣ ለመታደም የድግሱ ተስካር፤ ምርጫውም አልነበር፤ ጣፋጭ ህይወት ሊቸር፤ የእርሱማ ቁም ነገር፤ ጎራ ሲል ወደቤት፤ ወደ ታደመበት፤ አስተናጋጅ ጠፍቶ ሀጥዕ በሞላበት ድንገት ከተፍ አለ ወደ ታደመበት፤ ድግሱን ታዳሚ ይመስላል ሲቀመጥ፤ ዙሪያውን ቢያማትር ወደ ግራና ቀኝ እራሱን እሚጋልጥ አጣ እኔነኝ ባይ አንዲት ሴት ተነሳች ጌታ ማረኝ ብላ የያዘችው ብልቃጥ በሽቶው የሞላ በፊቱ ሰበረች፤ እግሩንም በጸጉሯ እየደባበሰች፤ የእንባዋን መንታ ከአኖቿ እየቀዳች፤ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፤ እኔን ማረኝ አለች፤ ዝግት ባለ ልሳን ስቅ ስቅ እያለች የድንጋይ ውርምታ የሰዎች ጫጫታ ዙሪያዋን ቢከባት ነፃነቷ እንጂ እሚሰጣት ህይወት ፃድቅ ፊት ልትቀርብ፤ ምንም እንኳ ባይኖር፤ ልቧንም ሰብራለች ውድ ስጦታዋን የስምዖን ደስታ፤ አይጠቅመው ለጌታ፤ ለጊዜው ነው እንጂ አያልፍም ከማታ፤ ብልቃጡ ይሰበር ይታይ የእኛ ደስታ፤
Show all...
👍 5
#አይቆጨኝም መንገድእናእውነት ህይወትንማወቄ፤ መከተል ብጀምር የመዳኔን ፅድቄ፤ ሀጥዕ ሥሬን ሳይሰድ ጉልበቴ ሳይላላ፤ አይቆጨኝም እኔ፤ በወላፈን እሳት በእቶን ብበላ፤ መንገዱ እኔነኝ ልጄ ካለኝማ፤ ተዉኝልከተለው ምንም ሳላቅማማ፤ የህይወት ሚዛኔ የኔነቴ ካስማ፤ ሽቶዬ ቢያርሰው፤ የእግሮቹንም ወዝ ፀጉሬ ቢያብሰው፤ በቃ አይቆጨኝም ግራ መጋባቱ፤ መስማማትን መረጥኩ ልቤን ካሸፈተው ከዚህ ክንደብርቱ፤ እራሴን ብሰጠው አትርፌ ከእሳቱ፤ ከሲዖል ይሻላልሰማይን መምረጡ፤ የምድር ደስታ ፌሽታ ባይገባኝም እዛ፤ ፍፁም አይቆጨኝም ብመስል ፈዛዛ
Show all...
#እኔነኝ በጊቷ ሁሉ ከሞላበት ከአባቴ ቤት ርቄ፤ በድፍርሱ ውሀ ላልጠራ ጠልቄ፤ ውስጠቴ ቆሽሾ ተጨመላልቄ፤ በሀጢአት አሻራ ወድቄ ዘፍቄ፤ መልኬን ሲያበላሸው የራሴ እኔነት የእኔ ያልኩት ጉልበት፤ አውቃለሁ ባይነት፤ የእኔ ጠባብነት፤ ግድፈቴ ላይጠራ፤ ጉድለቴ ላይሞላ፤ ያተረፍኩ ሲመስለኝ ጥብቀቴ ሲላ
Show all...
#ሰማራዊቷ ነኝ ውሀዬን ልቀዳ ገንቦዬን ሸክፌ፤ ማዶማዶ እያዩ ሲያማትሩ አይኖቼ ከጉድጓድ አጠገብ አንድ ሰው ተቀምጧል፤ ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ሔደዋል ገና ጎንበስ ብዬ፤ ውሀ ከመቅዳቴ፤ ከጥሙ እንዲረካ፤ ሲጠይቀኝ ለአፍታ፤ ቀድቼ ሰጠሁት የውሀ ጠብታ፤ ሰማራዊነቱ ግራ ቢያጋባኝም፤ ጥያቄ ጠየኩት፤ አንተማነህ አልኩት፤ ጥያቄ ተሞልቶ የእኔነት አንደበት፤ ደግሜ ጠየቅሁት አንተአይሁዳዊ፤ ከእኔ ሰማራዊት ምን ትፈልጋለህ፤ እንዴት ከመንደሬ ውሀ ትለምናለህ ብዬ ከማለቴ፤ እርሱም መለሰልኝ በጥያቄ ብዛት ውስጥሽን ስታኪ፤ ብዙ ከነበሩት በአንዱ ሳትረኪ፤ ግድ ነበር የኔ በበርሽ ማለፌ፤ ወደ ባዶነትሽ ወደ አንቺ መቅረቤ፤ ከጉድጓዱበታች ቢመስልሽም ቀልቤ፤ ይህ የእኔ አይደለም ሀሳቤ የልቤ፤ የአንቺ እርካታ እንጂ የኔ እርካታዬ
Show all...
#ሰማራዊቷ ነኝ ውሀዬን ልቀዳ ገንቦዬን ሸክፌ፤ ማዶማዶ እያዩ ሲያማትሩ አይኖቼ ከጉድጓድ አጠገብ አንድ ሰው ተቀምጧል፤ ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ሔደዋል ገና ጎንበስ ብዬ፤ ውሀ ከመቅዳቴ፤ ከጥሙ እንዲረካ፤ ሲጠይቀኝ ለአፍታ፤ ቀድቼ ሰጠሁት የውሀ ጠብታ፤ ሰማራዊነቱ ግራ ቢያጋባኝም፤ ጥያቄ ጠየኩት፤ አንተማነህ አልኩት፤ ጥያቄ ተሞልቶ የእኔነት አንደበት፤ ደግሜ ጠየቅሁት አንተአይሁዳዊ፤ ከእኔ ሰማራዊት ምን ትፈልጋለህ፤ እንዴት ከመንደሬ ውሀ ትለምናለህ ብዬ ከማለቴ፤ እርሱም መለሰልኝ በጥያቄ ብዛት ውስጥሽን ስታኪ፤ ብዙ ከነበሩት በአንዱ ሳትረኪ፤ ግድ ነበር የኔ በበርሽ ማለፌ፤ ወደ ባዶነትሽ ወደ አንቺ መቅረቤ፤ ከጉድጓዱበታች ቢመስልሽም ቀልቤ፤ ይህ የእኔ አይደለም ሀሳቤ የልቤ፤ የአንቺ እርካታ እንጂ የኔ እርካታዬ
Show all...
#ድርሻችን የቱ ነው? የአደባባይ ጩኸት ሆኖ ፀሎተችን፤ ቂምና አድመኝነት ተሞልቶ ልባችን፤ አመፅን በክፋት ወርሶትውልዳችን፤ እንዴት እንመለስ ታውሮ ልባችን፤ ሰማያዊው ቀረ የእኛ መክሊታችን፤ ሻማውም ቀለጠ ጠፋ ብርሀናችን፤ በማይመጥን ምኞት ስልጣናችንበዝቶ፤ በወኔያችን ላይ ደርበን ብትቶ፤ ውስጣዊው ፀጋችን፤ በሸረሪት ብልጠትድርንም አድርቶ፤ ሻገተ እንጀራችን እሚበላው ጠፍቶ፤ አንቅረን ጥለናል ከቤታችን ሸቶ፤ እንቅቡም አረጀተጠቃሚው ጠፍቶ፤ ለአምላክ ሳናስተውል፤ ትዕዛዙን ሳንፈፅም፤ ቃላችን ታጠፈ ኪዳናችን የለም፤ እንዴት እንፈወስ፤ ማንስ እኛን ያክም፤ ውስጣችን ባዶነው፤ መፍትሔ ያጣ ህመም፤ ወላፈኑ በዝቶ በእሳት ስንፋጅ፤ ምልጃና ፀሎቱ፤ ሲርቀን ከእኛውደጅ፤ ማን ደፍሮ ይመስክር፤ ማንስ ይበል አዋጅ፤ በአደባባይ ቀርቶ የእኛ ጩኸትማ፤ እንዴት አንድ እንሁን እንዴት እንስማማ፤ ወንጌሉን ጥለናል እግዜ/ን ሳንሰማ ይህ ጭካኔያችን አርጎናል ጨለማ፤
Show all...
በስምህ  ያሾፉት  የተዘባበቱት  ትመጣለህ ስንል መቼ ከወዴት ያሉት አይነን ሁሉ እያየህ ኢየሱስ ትመጣለህ ናፍቀናል የመለከቱ ድምፅ ሲነፋ ልንሰማ ናፍቀናል ለማየት አዲሲቱን ምድር አዲሱን ከተማ ናፍቀናል ልዑል ሆይ  ፊትህ ከማይደክሙት ከማያርፉት ጋራ ቅዱስ ቅዱስ ማለት ናፍቀናል ልዑል ሆይ ተስፋችንን ማየት ከረፍታችን ደርሰን ከአንተ ጋር መሰንበት ናፍቀናል ጌታ ሆይ ልንሆን ባለህበት
Show all...
Repost from @Seleslamenwk
ሊጠቅማችሁ ስለሚችል አንብቡት 👇 ጌታን በትጋት የሚያገለግሉ ስወች ምክርና ምክርነት መስማት በጣም እወዳለሁ ምክኒያትም ያለፉበትን ስለሚያስተምሩ ይጠቅማልና ። በቅርቡ ወደ ጌታ የሔዱት #ወንጌላዊ #ገብሩ እንዲህ ብለው መከሩን 1/ ለታመሙ ስወች ሁሉ ጸልይ እግዚአብሔር ይፈውሳል ያልተፈወስውን ስው ስታይ እኔ እምነት የሌኝ ሆኖ ስውየው እምነት የለው ሆኖ አትበል እግዚአብሔር የሚፈውስውን ይፈውሳል ያልተፈወሱትን ለምን እንዳልፈወስ እግዚአብሔር ያውቃል 2/ ወንጌል ለመመስከር ስትወጡ 2 ሁኑ አንዱ ይመስክር አንዱ በልቡ ይፀልይ 3/ እየስራችሁ ማንንም ሳትንቁ በስራችሁ ጌታን አሳዩ ለሚስሩት ስወች መስክሩ ከሁሉ በላይ በህይወታችሁ ጌታን ይይዩት ታማኞች ሁኑ ። 4/ ለመመስከር ስትወጡ ስወች ጋር አትከራከሩ መስክራችሁ እለፉ እናተ መስክራችሁለታል ደንዳና ልቡን አነቃንቃችሁለታልና ሌላ ስው ደግሞ ሲመስክርለት ያምናል ። 6/ ስወችን እንደ ሁኔታቸው ቅርቡ ከምስጊኑም ጋር እንደ ስውየው ሁኔታ ቅርቡት 7/ የምትፈልጉትን ጌታን በትጋት ጠይቁት 8/ ለዲያቢኖስ ምንም ክፍተት አትስጡት 9/ አገልጋዮች ከሌሎች አገልጋዮች ተማሩ ከመፅሃፍ ቅዱስ ውጭ የሚጠቅማችሁን መፅሃፍ በብዛት አንብቡ 10/ የምታገለግሉትን ህዝብ ምንም ባይረዳችሁም ውደዱት 11/ ከሁሉ በላይ ትሁትና የፍቅር ስወች ሁኑ በዚህ ህይወት ነው ጌታ የሚስራው 12/ ስራ ቦታችሁን እና ስራችሁን ለወንጌል አድርጉት ታማኞች ሁኑ ፣ እየስራችሁ ድሆችን እርዱ 13/ ለምታገለግሉት አገልግሎት የሚረዳችሁን ጸጋ ለምኑ 14/ ምንም ስወቹን ባታውቁም ባትግባቡም ለቅሶ ቤት ሒዱ ህዝቡን በእግዚአብሔር ቃል አፅናኑ እግዚአብሔር በዛ ይስራል 15/ ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሁሌ ጸልዩ የጸጋ ስጦታ አጠቃቀሞችን በደንብ ተማሩ 16/ ስነፎች አትሁኑ ትጋት ይኑራችሁ 17/ የማካፈል ህይወት ይኑራችሁ 18/ እግዚአብሔር ሲናገር ጫፍ ይዛችሁ አትሩጡ እግዚአብሔር ተናግሮ መጨረሻ ላይ ምን አለ ? ንስሃ ግቡ አለ ? እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ አለ ? እፈውሳለሁ አለ ? ተዘጋጅ ልወስድህ ነው አለ ? የመጨረሻዋን ቃሉን በደንብ ስሙ ስምታችሁ ታዘዙ 19/ ከበሽታ እግዚአብሔር ፈውሳችኋል ይተባላችሁ ስወች ህመሙ አለባችሁ ያላችሁ ሃኪም ነውና ሔዳችሁ አርጋግጣችሁ ነው መዲሃኒት መጣልና ምስክርነት መስጠት ያለባችሁ ። 20/ ስውን በፍፁም በፍፁም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ 21/ በአስተምሮ የሳቱትን ወገኖች ምከሩ አስተምሩ እንጂ ስውየውን በፍፁም አትሳደቡ አትናቁትም
Show all...
1)
Show all...
ህይወት ለየቅል። ድርሻ ተቀብሎ ከአባቱ ጉያ፤ የጠፋው ልጅ ሔደ፤ ተሰነባበተ ያው በራሱ ፈቃድ፤ አንዳች ሳያቅማማ፤ አንድ ሀሳብ ሳይኖረው፤ በሁለቱ እይታ ልቡ የታተመው፤ የእግዜሩ ቢሰወር፤ ታድያ ምን ዋጋ አለው?፤ ፈቃዱ ይበልጣል፤ ይሁን እርሱ ያለው፤ ይሔ ካልሆነማ ህይወት፤ ለየቅል ነው።
Show all...