en
Feedback
Ethio Menzuma

Ethio Menzuma

Open in Telegram

Welcome to Ethio Menzuma! We preserve the traditional spiritual music and prayers of Ethiopia. Join us to experience the beauty and power of this spiritual music. Stay connected for daily updates, unique content, and a chance to celebrate and honor our cu

Show more
9 103
Subscribers
No data24 hours
-307 days
-18030 days
Posts Archive
photo content

photo content

እንኳን ለ1446 ኛው አመተ ሒጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። EID MUBAREK 🐏

እንኩዋን አዳርሳችሁ

ከኡዱሂያ ጋር የተያያዙ ወሳኝ ትምህርቶች (ክፍል ሁለት ) ======== 💠 ጥያቄ አራት ኡዱህያ የሚደረጉት እንስሳት ምን አይነት ናቸው? የኡዱህያ አይነት ከቁም ከብቶች መካከል   ግመል፣በሬ፣በግ እና ፍየል ሲሆኑ  ከእነርሱ ውጪ ሌላው ኡዱህያ አይደረግም። በብቸኝነት ለሚያርድ ሰው  በላጩ ግመል፣  ከዚያ  በሬ ከዚያም በግና ፍየል ናቸው ፤ ግመል ለሰባት እንዲሁም በሬ ለሰባት ይቻላል ። 💠 ጥያቄ አምስት የኡድህያው(የሚታረደው ከብት) መስፈርት ከኡዱህያ መስፈርቶች መካከል የሚታረደው እንስሳ  በሸሪዓ የተቀመጠውን  እድሜ መድረሱ አንዱ  ነው ግመል ከሆነ ሙሉ አምስት ዓመት መሙላት ፤ በሬና ፍየል ከሆኑ   ሙሉ ሁለት አመት መሙላት፤ በግ ከሆነ አንድ አመት መሙላት ወይም ከአመት በፊትም ቢሆን ጥርሱን መጣል ነው። ቡሽርል ከሪም  ገፀ 698 ውስጥ እንዲህ ይላል ፦ "በግ አመት መሙላት ወይም ጥርሱን መጣል አለበት ከአመት በፊት ቢሆንም በአጠቃላይ እንደ ዘካ ነው።" 💠 ጥያቄ 6 ኡዱህያ መቼ ነው የሚታረደው ? የኡዱህያ ሸርጥ ፀሐይ ከወጣች በኃላ ቀለል ባለ ሁኔታ ሁለት ረከዓ ከነ ኹጥባው የሚሰገድበት ጊዜ ካለፈ በኃላ ልትታረድ ነው ። በላጩ ግን ፀሐይ የዘንግ ያክል ከፍ እስክትል እርዱን ማዘግየት ነው። በአያመ ተሽሪቅ በቀንም ይሁን በለሊት ማረድ ይበቃል ነገር ግን ያለ ምክንያት በለሊት ማረድ ይጠላል ። 💠 ጥያቄ ሰባት አንድ ግመል ለሰባት ሰው ይበቃልን ? አንድ ግመል በጋራ ለሰባት ኡዱህያ ቢያደርጉት ይበቃል ሁሉም ለኡዱህያ እንዲሆን ቢስማሙም ወይም ከፊሉ ለኡዱህያ ከፊሉ ለአቂቃ ከፊሉ ለስጦታ ከፊሉ ለስጋም ቢፈልገው ይበቃል።

ቁርአን 💠💠 ✍አሽዐሪዮች ዘንድ ቁርአን የሚለው ቃል ለሁለት ትርጓሜዎች ይውላል ፦ 1) ከመኽሉቃት አንደበት ለሚወጣው ቃላዊ ንግግር እንዲሁም በማተሚያ ቤቶች ለሚታተመው ሙስሀፍ 2) አሏህ ዘንድ ላለው ዘልአለማዊ ንግግር 🛑 አሽዐሪዮች ከነዚህ የቁርአን ትርጓሜዎች መካከል የትኛውን ቀዲም ( ዘልአለማዊ ) እንደሚሉ የትኛውን ደግሞ ፍጡር ነው እንደሚሉ ራሳችሁን ጠይቁ ፤ ቁርአን ፍጡር እንደሆነ የሚገልፁ የቁርአን አንቀፆች ለየትኛው ትርጓሜ እንደሚውሉ መፅሀፍትን አገላብጡ https://t.me/sufiyahlesuna

ከኡዱሂያ ጋር የተያያዙ ወሳኝ ትምህርቶች (ክፍል አንድ ) ========= ጥያቄ ቁጥር አንድ ኡዱህያ ምንድ ነው? ኡዱሁያ ማለት በኢደል አድሀና በአያም አትተሽሪቅ ቀናት  ወደ አላህ ለመቃረብ የሚታረዱ ከብቶች ስም ነው። ጥያቄ ሁለት ኡዱህያ የተደነገገ ለመሆኑ ማስረጃው ምንድነው? ኡዱህያ የተደነገገ ለመሆኑ ማስረጃው "ለጌታህም ስገድ፣  እረድም " የሚለው የአላህ ቃል ነው። በእርግጥ ከነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም  ንግግር ፣ ተግባርና  አፅድቆትም የተረጋገጠ ነው። ከዚህም ውስጥ ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ፡ " የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቀንዳማ የሆኑ ሁለት በጎችን ኡድህያ አደረጉ " የሚለው ሀዲስ አንዱ ነው ። ጥያቄ 3 ኡዱህያ ፍርዱ ምንድ ነው ?  ግዴታ የሚሆነውስ መች ነው ?? የኡዱህያ ፍርድ :- በነፍስ ወከፍ (ሁሉም በየግሉ)የተወደደ ተግባር ነው። ቤተሰብ ከሆኑ አንዳኛቸው ማረዱ  የተወደደ ተግባር ነው ኡድህያ ግዴታ የሚሆነው በስለት ብቻ ነው ፣ ሁለት አይነት የስለት አይነቶች አሉ ፦ 1:-እውነተኛ ስለት :- የሚባለው ሲሆን (ይህችን በግ ለአላህ ማረድ በኔ ላይ ይሁንብኝ ማለትን የመሰለ)ነው። 2:-ፍርዳዊ ስለት:- የሚባለው ሲሆን ይህች  በግ ለኔ ኡዱህያ አድርጌያታለሁ ማለት የመሰለ ነው ። https://t.me/sufiyahlesuna

⬇️ Downloaded in @AllSavesBot

HAMZA FAJII NEW MENZUMA COMING SOON FUHAD MOHAMMED OFFICIAL YOUTUBE ላይ ይጠብቁን #share

Share በ ማድረግ ይታባባሩን ዉድ የ ኢትዮ መንዙማ ቻናል ተከታታይ

በ ቅርብ ይጠብቁ

إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ
إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ إِنَّا لِلَّٰهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ