cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋህዶ_ሃይማኖቴ 🌷✞🌷✞

#ተዋህዶ_ሃይማኖቴ #የጥንት_ነሽ_የናትና_ኣባቴ #ማዕተቤን_አልበጥስም #ትኖሪያለሽ_ለዘላለም።። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ⏩ለማንኛውም ሀሣብ,አስተያየት ጥያቄ ካለዎት በዚ @Avela_ye_Maryam_lj_21የሚል ሊንክ በመንካት ሃሳብዎን ያድርሱን

Show more
Ethiopia10 048The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
316
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ጥቅምት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ††† +" ቅዱስ አብላርዮስ ገዳማዊ "+ ††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን:: +ታላቁ ቅዱስ አብላርዮስ ደግሞ ካለ ማመን ወደ ማመን: ከማመን ወደ መመንኮስ: ከመመንኮስ ወደ መጋደል: ከመጋደል ወደ ትሕርምት: ከዚያም ወደ ፍጹምነት የደረሰ: በምድረ ሶርያም ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ አባት ነው:: +ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው:: +ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል:: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት:: +ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል:: +ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ 'የባሕታውያን አባት' ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ:: +ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ:: +እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል:: ከእነዚህም አንዱና ዋነኛው ዛሬ የምናከብረው ታላቁ ጻድቅ አባ አብላርዮስ ነው:: +ቅዱስ አብላርዮስ ሶርያዊ ሲሆን የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ነው:: በቀደመ ሕይወቱ ክርስትናን ፈጽሞ የማያውቅ ሰው ነበር:: ለዚህ ምክንያቱ የወላጆቹ ኢ-አማንያን መሆን ነው:: +ገና በልጅነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልስፍና: የዮናናውያንን ጥበብ ተምሮ ፈላስፋ ሁኗል:: በ16 ዓመቱም በምድረ ሶርያ አሉ ከሚባሉ የጥበብ ሰዎች አንዱ ሆነ:: ቅዱሱ ማንበብና መጠየቅን አብዝቶ ይወድ ነበር:: +የሚያነበው ነገር በሶርያ ቢያጣ በ17 ዓመቱ ተጨማሪ ጥበብን (እውቀትን) ፍለጋ ወደ ግብጽ (እስክንድርያ) ወረደ:: በዚያ ግን ከሰማቸው ትምሕርቶች አንዱ ልቡን ገዛው:: በወቅቱ በግብጽ ላይ ፓትርያርክ የነበረው ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ስለ ምድራዊው ያይደለ ስለ ሰማያዊው ጥበብ ሲያስተምር ሰምቶ ተገረመ:: +ቅዱስ አብላርዮስ በዚህ ሰዓት የሰበሰባቸውን የፍልስፍና መጻሕፍት ጥሎ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያነብ ጀመረ:: ቅዱስ እለ እስክንድሮስም የሚከብድበትን እያፍታታ ተረጐመለት:: በአጭር ጊዜም ክርስቲያን ሆኖ ተጠመቀ:: +በዚያው ዓመትም ከከተማ ወጥቶ ወደ በርሃ ገባ:: ከአባ እንጦንስ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርት አንዱ ሆኖ መነኮሰ:: በዚያም በጾምና በጸሎት: በመታዘዝና በትሕትና ለዓመታት ኖረ:: ቀጥሎም ወሬ ነጋሪ መጥቶ ወላጆቹ ማረፋቸውን ነገረው:: +በዚህ ጊዜ ቅዱስ አብላርዮስ ከአባ እንጦንስ ዘንድ ተባርኮ: ማኅበሩንም ተሰናብቶ ሶርያ ገባ:: የወላጆቹን ሃብትና ንብረት በሙሉ መጽውቶ ወደ ሶርያ በርሃ ወጣ:: በወቅቱ በአካባቢው ምንኩስና እየተነቃቃ ነበርና የቅዱሱ መምጣት ይበልጥ አጠናከረው:: +ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ኤዺፋንዮስን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፈራ:: በአካባቢውም ታላቅ መካሪ: ናዛዥ: አጽናኝ: መሪ ሆነ:: ከብዙ ተአምራቱ ባለፈ ሃብተ ትንቢት የተሰጠው አባት ነውና እጅግ ክቡር ነበር:: *የገድሉን ነገርማ ማን ተናግሮ ይፈጽመዋል! +እርሱ ከዕለተ ሰንበት በቀር እህልን አይቀምስም:: ለዚያውም እሑድ በነግህ (ጧት) ትንሽ ሳር ነጭቶ ከመብላት በቀር ሌላ የሚበላው አልነበረውም:: እንዲህ ባለ የበርሃ ሕይወት ለ63 ዓመታት ኖረ:: በዓለም የኖረበትን 17 ዓመት ብንደምረው 80 ይሆናል:: ቅዱሱ በተወለደ በ80 ዓመቱ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን ዐርፏል:: +አምላከ ቅዱስ አብላርዮስ ጥበቡን: ፈሊጡን: ሕይወቱን ይግለጽልን:: ከበረከቱም አይለየን:: +ጥቅምት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አብላርዮስ ገዳማዊ 2.ቅድስት ጸበለ ማርያም 3.ቅድስት አውስያ 4.አባ ዻውሎስ ሊቀ ዻዻሳት ++"+ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁን ተመልከቱ:: እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች: ኃይለኞች የሆኑ ብዙዎች: ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም:: ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝነት መረጠ . . . ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ:: ነገር ግን:- የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ:: +"+ (1ቆሮ. 1:26) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Show all...
✞አዳምን ለማዳን✞ አዳምን ለማዳን ሰው የሆነ ወዶ ስደትን ጀመረ በፍቅር ተዋርዶ ሰአሊ ለነ ማርያም ብርድ በጸናበት በክረምት ወራት ልጅሽን ታቅፈሽ ተነሳሽ ስደት ሰአሊ ለነ ማርያም የሄሮድስ ጭፍሮች ከሐገር ሲያሳድዱሽ ልጅሽን ታቅፈሽ እንባሽን አፈሰስሽ ሰአሊ ለነ ማርያም ለምኝልን ማርያም ከአንድዬ ከልጅሽ ከመድኃኔዓለም አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ለእግዚአብሔር ፍጹም ሰሎሜና ዮሴፍን ዘመድ አግኝተሽ ልጅሽን ታቅፈሽ ስደትን ጀመርሽ ሰአሊ ለነ ማርያም ፍጡራን በሙሉ ከቤታቸው ሆነው አንቺ መሰደድሽ ኧረ ለምንድን ነው ሰአሊ ለነ ማርያም ከረሃብ ጋር ጸሐይ አንዴት አረገሽ ሀዘንሽን ልካፈል ስለሆንኩ ልጅሽ ሰአሊ ለነ ማርያም አንድ ፍሬ ሕጻን ትንሽ ብላቴና እንዴት አቋረጥሽው በረሃውን ሲና ሰአሊ ለነ ማርያም አዝ= = = = = ምን አለች ኮቲባ ያልታደለች ፍጡር ጌታዋን ታቅፈሽ ስትዞሪ መንደር ሰአሊ ለነ ማርያም አንቺን የመሰለች አንዲህ መቸገሩ ብሆትኚ ነው ክፉ ያዞረሽ ባገሩ ሰአሊ ለነ ማርያም ብላ ተናገረች ምስጢሩ ሳይገባት ውሃን ለመዘከር ልቧ ጨክኖባት ሰአሊ ለነ ማርያም ክፉም አልመለስሽ እንባሽን አፈሰስሽ ለውሻ እራርተሽ ውሃን የተዘከርሽ ሰአሊ ለነ ማርያም አዝ= = = = = ድንገት ወንበዴዎች ደርሰው ሲይዙሽ ከሰሎሜ ወስደሽ ልጅሽን ታቀፍሽ ሰአሊ ለነ ማርያም የሌሊት ቁርና የቀን ሀሩርን የተቀበልኩብህ ላላድን ነውን ሰአሊ ለነ ማርያም እያልሽ አለቀስሽ ምርር ብለሽ ፊቱ ላይ ወረደ የሐዘን እንባሽ ሰአሊ ለነ ማርያም ልጄን ሲገድሉብኝ ከማይ በህይወቴ እኔን ያስቀድመኝ ይቅረብልኝ ሞቴ ሰአሊ ለነ ማርያም አዝ= = = = = ያበሰረኝ መልአክ ትወልጂያለሽ ያለኝ ዛሬ በስደቴ ይምጣና ያጽናናኝ ሰአሊ ለነ ማርያም ብለሽ ማልቀስሽን ባስታወስኩኝ ጊዜ ልቤ ይቃጠላል በሀዘን በትካዜ ሰአሊ ለነ ማርያም ከዘመድ መለየት ከሀገር መውጣት እንዴት ያሳዝናል የድንግል ስደት ሰአሊ ለነ ማርያም አዝ= = = = = እንባሽ የወረደው አንደ ሐምሌ ደመና ሐዘንሽ ልዩ ነው የእስራኤል መና ሰአሊ ለነ ማርያም ጥቂት እፎይ ያልሽው ያኔ በስደትሽ ኢትዮጵያ ስትደርሺ ነበር የተጽናናሽ ሰአሊ ለነ ማርያም እንግዲህ አሳስቢ ድንግል ስደትሽን የደረሰብሽን እረሃብ ጥምሽን ሰአሊ ለነ ማርያም ስደትሽን ላስብ ስደተኛ ነኝ የሰማዩ ቤቴ የሚናፍቀኝ ሰአሊ ለነ ማርያም አዝ= = = = = ነይ ነይ ነይ በረድኤት በአማላጅነትሽ ይሰጠን ምህረት ሰአሊ ለነ ማርያም ነይ በእናትነትሽ አመሌን ቻይው ትህትና እንደሆን ከተፈጥሮሽ ነው ሰአሊ ለነ ማርያም መዝሙር ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ
Show all...
❤2,አብ መዓሙቕ ልበይ❤ ✞ አብ ዓሙቕ ልበይ ፍቕርኺ ይንገሰለይ ✞ ብህድአት ምርሕኒ ናብ ናይ ሰላም ወደበይ ✞ ድኹም ግዲ ኾይነ እነኹ ጠሊቐ ✞ ኣሳግርኒ እባ ከይተርፍ ወዲቐ ✞ ኣቲ ኮ ትማል ካብ ሓመድ ክፍጠር ✞ ብምስሊ አምላኸይ አብ ገነት ክኸብር ✞ ብገዛእ ምርጫይ ብላሽ ምስተረፍኩ ✞ ተስፋይ ዝነበርኪ ትዕድልተይ ብኹሉ ✞ ሎሚ ውን ድንግለይ ከይከብድ ፃር ልበይ ✞ ንዒ ደኣ ንዒ ከራግፍ ሸኸመይ ✞ እመብርሃን ለምንለይ ንዓይ ✞ ትሕዞይ ነፂፉ ከይ ጉልበብ ሕፍረተይ ✞ ባዶ ገንኢ ሒዘ ቤተይ ከይጠመየ ✞ ከም ኣብ ቃና ገሊላ ዝተረኸብኪ ኣብ ቤተይ ✞ ናተይ እውን ድንግለይ ክፋት እዩ ልዳተይ ✞ ንዒ ምስ ወድኺ ንዒ ማርያመየ ✞ ውሽጠይ ክረግኣለይ ክባረኽ ቤተየ ✞ አደ ጎይታይ ክባረኽ ቤተየ ✞ ሕስብ ከብሎ ይገርመኒ ምሒር ✞ ሕልፊ አለዎ ናትኪስ ድንቂ እዩ መስተንክር ✞ ነብሳት ዘጥፍአ ዶ ምሕረት ምተውሃበ ✞ ኣይ ሳላ ስምኪ እንድዩ ገነት ዝረኸበ ✞ ካብ ውሒዝ ፍቕርኺ ክተካፍልኒ ✞ ይልምን አለኹ ዋሕስ ክትኮንኒ ✞ ፅዬንየ ፀግዒ ክትኮንኒ ✞ ጃጅየ ከይተርፍ እኖ ትኾንኒ ✞ ከማኺ ዝበለስ አነ መን ኣሎኒ ✞ ካባኺ ሓሊፈ ስ የብለይን ዝኸዶ ✞ ማርያመይ ሓደራ ንገርለይ እንዶ ✞ ክቐንዓኒ መታን ኩሉ ዝኸድኩዎ ✞ ንፋቑር ወድኺ ብፅሓያ በልዮ ✞ ማርያመየ ርድኣያ በልዮ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ✞✞✞✞❤❤❤✞✞✞✞ ✞✞✞✞❤❤❤✞✞✞✞ Abel Gebreyowhans✅: Abel Gebreyowhans✅: ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን¡¡ ውድ የዚህ ቻነላችን ወንድሞች እህቶች የቻነላችን ሊንክ copy በማረግ ለ 10 ሰዎች እድትልኩ በ እመቤታችን ስም እማፀናለን። ⏩በዚ ቻነላችን ላይ የተለያዩ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ መዝሙሮች በበገና የታጀበ ÷ጥያቄና መልስ ከነ ሽልማቱ እና ትምህርቶች በ እግዚአብሄር አጋዥነት እንለቃለን። ⏩ላልደረሳቸው ውንድሞችና እህቶች ከታች ያለውን #ሊንኩን ወይም #open_chanel የሚል በመንካት የቻነላችን ቤተሰብ ይሁኑ። https://t.me/joinchat/AAAAAFMpwmfqZHU2jOD_ug
Show all...
ተዋህዶ_ሃይማኖቴ 🌷✞🌷✞

#ተዋህዶ_ሃይማኖቴ #የጥንት_ነሽ_የናትና_ኣባቴ #ማዕተቤን_አልበጥስም #ትኖሪያለሽ_ለዘላለም።። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ⏩ለማንኛውም ሀሣብ,አስተያየት ጥያቄ ካለዎት በዚ @Avela_ye_Maryam_lj_21የሚል ሊንክ በመንካት ሃሳብዎን ያድርሱን

❤2,አብ መዓሙቕ ልበይ❤ ✞ አብ ዓሙቕ ልበይ ፍቕርኺ ይንገሰለይ ✞ ብህድአት ምርሕኒ ናብ ናይ ሰላም ወደበይ ✞ ድኹም ግዲ ኾይነ እነኹ ጠሊቐ ✞ ኣሳግርኒ እባ ከይተርፍ ወዲቐ ✞ ኣቲ ኮ ትማል ካብ ሓመድ ክፍጠር ✞ ብምስሊ አምላኸይ አብ ገነት ክኸብር ✞ ብገዛእ ምርጫይ ብላሽ ምስተረፍኩ ✞ ተስፋይ ዝነበርኪ ትዕድልተይ ብኹሉ ✞ ሎሚ ውን ድንግለይ ከይከብድ ፃር ልበይ ✞ ንዒ ደኣ ንዒ ከራግፍ ሸኸመይ ✞ እመብርሃን ለምንለይ ንዓይ ✞ ትሕዞይ ነፂፉ ከይ ጉልበብ ሕፍረተይ ✞ ባዶ ገንኢ ሒዘ ቤተይ ከይጠመየ ✞ ከም ኣብ ቃና ገሊላ ዝተረኸብኪ ኣብ ቤተይ ✞ ናተይ እውን ድንግለይ ክፋት እዩ ልዳተይ ✞ ንዒ ምስ ወድኺ ንዒ ማርያመየ ✞ ውሽጠይ ክረግኣለይ ክባረኽ ቤተየ ✞ አደ ጎይታይ ክባረኽ ቤተየ ✞ ሕስብ ከብሎ ይገርመኒ ምሒር ✞ ሕልፊ አለዎ ናትኪስ ድንቂ እዩ መስተንክር ✞ ነብሳት ዘጥፍአ ዶ ምሕረት ምተውሃበ ✞ ኣይ ሳላ ስምኪ እንድዩ ገነት ዝረኸበ ✞ ካብ ውሒዝ ፍቕርኺ ክተካፍልኒ ✞ ይልምን አለኹ ዋሕስ ክትኮንኒ ✞ ፅዬንየ ፀግዒ ክትኮንኒ ✞ ጃጅየ ከይተርፍ እኖ ትኾንኒ ✞ ከማኺ ዝበለስ አነ መን ኣሎኒ ✞ ካባኺ ሓሊፈ ስ የብለይን ዝኸዶ ✞ ማርያመይ ሓደራ ንገርለይ እንዶ ✞ ክቐንዓኒ መታን ኩሉ ዝኸድኩዎ ✞ ንፋቑር ወድኺ ብፅሓያ በልዮ ✞ ማርያመየ ርድኣያ በልዮ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ✞✞✞✞❤❤❤✞✞✞ ✞✞✞✞❤❤❤✞✞✞ https://t.me/joinchat/AAAAAFMpwmfqZHU2jOD_ugh
Show all...
➖➖➖➖➖➖➖━⊱✿⊰━➖➖➖➖➖➖➖ 🌹 #ግራት_ልብኻ_ኣጽርዮ፡ 🌹 ➖➖➖➖➖➖➖━⊱✿⊰━➖➖➖➖➖➖➖ ✍ጀሚርካዮ ዘለኻ ህይወት ልክዕ ናይ ሓረስታይ ህይወት እዩ። እቲ ግራት፣ ማይ፣ ዘርኢ፣ ሙቐት ጸሓይ፣ ኲሉዚ ዉህብቶ ኣምላኽ እዩ፣ እቲ ዕዮ ግና ናይቲ ሓረስታይ።📖 ✍ሓረስታይ ጽቡቕ እቶት ንክረኽብ፣ ኣበርቲዑ ክጽዕር ኣለዎ። ንግሆን ምሸትን ክዓዪ ይግባእ፣ ክኹስኩሶ፣ ክጽህዮን፣ ካብ ባልዕ ክከላኸሎን ካብ ኣዕዋፍ ክሕልዎን ይግባእ። ኲሉ ግዜ ተጊሁ ክሰርሕ ይግባእ፣ ብዘይ ዕረፍቲን፣ ብዘይ ምስልካይን ክሕልዎ ዉን ኣለዎ። ዋላ ነዚ ኲሉ ጻዕሪታት ምስ ገበረ፣ ናይዚ ሕርሻ እቶት ኣብ ሓደ ዓቢ ሓይሊ ይምርኮስ፣ ኣብ እግዚአብሔር።📖 ✍ክንሕልዎን ክንከናኸኖን ተዋሂብና ዘሎ ዕዮ፣ ግራት ልብና እዩ፣ እቶቱ ኸኣ ዘለዓለማዊ ህይወት ኢዩ። ምክንያቱ ብግዜን ቦታን ዘይዉሰን፣ ብግዳማዊ ኩነታት ዘይጽሎ፣ ኣማናዊ ሓርነት ዘለዎ፣ ገደብ ኮይኑ ዝዓግቶ ዘይብሉ፣ ፍቕሪ፡ ምሕረትን፡ ብርሃንን ዝመልኦ ህይወት ስለዝዀነ። ብመንፈስ ዝንበር፣ መንፈሳዊ ኩነታት ዘለዎ፣ መንፈሳዊ ህይወት እዩ። ኣብዚ ምድሪ ይጅምር፣ መወዳእታ ዉን ይበሉን፤ ማንም ምድራዊ ሓይሊ ዘየናዉጾ ሕይወት እዩ፤ እዚ ህይወት እዚ ካብ ልቢ ይጅምር።📖 ✍ቅዱስ ይስሃቅ ሶርያዊ ከምዚ ይብል "ጸላኢኻ ከም ኣቀራርባኻ እዩ፣ ዝሕይለካ እሞ፣ ገዛእ ርእስኻ ቅጻዕ። ምስ ገዛእ ርእስኻ ተዓረቕ (ሰላም ግበር)፣ ሽዑ ሰማይን ምድሪን ምሳኻ ክዕረቕ እዩ። ናብ ዉሽጣዊ ህይወትካ (ልብኻ) እተው፣ ሽዑ ናብ ውሽጢ ሰማያዊ ድንዃን ዉን ክትኣቱ ኢኻ። ክልትኤን ሓደ እየን፣ ናብ ልብኻ ምእታዉ ማለት፣ ናብ ሰማያዊ ድንዃን ምእታዉ ማለት እዩ። 📖 ✍ናብታ ቀዳመይቲ ክትኣትዉ ከላኻ፣ ናብታ ዳሕረወይቲ ዉን ኣቲኻ ኣለኻ። ናብ መንግስቲ ኣምላኽ ዘብጽሕ መሳልል፣ ኣብ ዉሽጥኻዩ ዘሎ፣ ኣብ ነፍስኻ ብምስጢር ክትረኽቦ ኢኻ። ጾር ሓጢኣት ቀንጢጥካ ደርብዮ እሞ፣ ሽዑ ናብ ላዕሊ ናብ ሰማያት ዘብጽሓካ ህይወት ክትረኽብ ኢኻ።"📖 ✍ኣቦታትና ሰማያዊ ድንኳን ዝብልዋ፣ ንመንግስቲ ኣምላኽ እዩ፣ መንግስተ ሰማያት ዉን ካልእ ስማ። መንግስተ ሰማያት ማለት ብሓጺሩ ክርስቶስ እዩ። ብክርስቶስ ምንባር ማለት ዘለዓለማዊ ህይወት ምንባር እዩ።📖 #ሓሳብ_መውሃቢ @Merhawii_bot ╭══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╮ 👉 @tsyonawi21 👈 👉 @tsyonawi21 👈 👉 @tsyonawi21 👈 ╰══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╯ ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
Show all...
Frezer(ch): <<በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን።>> ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ <<ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።>>ማቴ 18÷20 ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ 👉ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እንኳን በሰላም መጣቹ። የድንግል ማርያም ልጆች በተከታታይ ያለማቋረጥ በዚህ ቻናል የተለያዩ ፕሮግራሞች የሚተላለፉ ሲሆን ከነሱ መካከል 👉 በየቀኑ መንፈሳዊ መልእክት 👉 በየቀኑ የዕለቱ ስንክሳር(የቅዱሳን ተጋድሎ ታሪክ) 👉 መዝሙር ከነግጥሙ 👉 ስነ-ጽሁፍ እና ትረካ 👉 ኣጫጭር መንፈሳዊ ትምህርቶች በኣጠቃላይ መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮች በዚህ ቻናል ይለቀቃል። እናም እኛም ተምረንበት ሌሎች ወንድሞቻችን እንዲማሩበት በተቻለን መጠን ሼር(Forward )እናርግ። 👉 እናም ሀሳብ ኣስተያየት ካላቹ 👉 @Frewhh 👈 በዚህ Link መስጠት ትችላላችሁ ለመቀላቀል (to Join Telegram Channel) <<ኑ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ>> ኢሳ 2÷5 👇👇👇👇👇👇👇 👉 @dnglanate21 👈 👉 @dnglanate21 👈 👉 @dnglanate21 👈 👆👆👆👆👆👆 https://t.me/joinchat/AAAAAEwulz31KCjega3Nxw
Show all...
✞ የድንግል ማርያም ልጆች ❤ @🇩 🇳 🇬 🇱 🇦 🇳 🇦 🇹 🇪 21✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ኣስተምህሮ ስርዐት የጠበቁ መዝሙር፣ ስንክሳር፣ትምህርት ሌሎችም ለማግኘት <<ኑ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ>> ኢሳ 2÷5 👉 @Dnglanate21 👈ተቀላቀሉ። ለማነኛውም ሀሳብ አስተያየት @Dnglanate21CommentBot ይስጡን። " ጽዮንን ክበቡአት በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቍጠሩ" መዝ 48:12

††† እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ ††† ††† በእስክንድርያ (ግብጽ) ሊቀ ዽዽስናን ከተሾሙና በጐ ሥራን ከሠሩ አበው አንዱ አባ ዮሴፍ ነው:: እርሱ ለግብጽ 52ኛ ፓትርያርክ ነውና በ9ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ እንደ ነበር ይታመናል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በግብጽ የሚኖሩ የዘመኑ ክርስቲያን ባልና ሚስት ወደ ፈጣሪ ለምነው ልጅ ሲወልዱ 'ዮሴፍ' አሉት:: እጅግ ሃብታሞች ቢሆኑም እርሱ ገና ልጅ እያለ ሁለቱም ዐረፉ:: ሕጻኑ ዮሴፍም ዕጓለ ሙታን (ወላጅ አልባ) ሆነ:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተ አንድ ደግ ጐረቤቱ ግን ወደ ቤቱ ወሰደው:: እንደ ልጁ ተንከባክቦ: ክርስትናንም አስተምሮ አሳደገው:: እድሜው 20 ሲደርስም "የወላጆችህን ንብረት ንሳ" ብሎ አወረሰው:: ወጣቱ ዮሴፍ ግን "አኮኑ ዝንቱ ኩሉ ኃላፊ-ይህ ሁሉ ሃብት ጠፊ አይደለምን" ብሎ ናቀው:: ለነዳያንም በትኖት እያመሰገነ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገሰገሰ:: በዚያም የአሞክሮ ጊዜውን ፈጽሞ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበለ:: ለዓመታትም በዲቁና ገዳሙን እያገለገለ: እየተጋደለ ኖረ:: የአባ ዮሴፍን ደግነት የሰማው የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ማርቆስም ከገዳም አውጥቶ በመንበረ ዽዽስናው እንዲራዳውና ሕዝቡን እንዲያስተምርለት ወደ ከተማ አመጣው:: ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን አባ ዮሴፍ ወደ ፓትርያርኩ አባ ማርቆስ ቀርቦ "አባቴ! ወደ ገዳሜ አሰናብተኝ:: ለመነኮስ በከተማ መኖር ፍትሕ አይደለምና" ሲል ተማጸነው:: ፓትርያርኩም "እሺ" ብሎ ቅስናን ሹሞ አሰናበተው:: ወደ ገዳመ አስቄጥስ ከተመለሰ ጀምሮ አባ ዮሴፍ በዓት ለየ:: እስከ 59 ዓመቱም ድረስ በጾምና በጸሎት በበዓቱ ጸንቶ ኖረ:: በአጠቃላይ በገዳም የኖረባቸው ዓመታትም 39 ደረሱ:: በዚህ ጊዜ ግን የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ስምዖን (ከአባ ማርቆስ በኋላ 3 ፓትርያርኮች ዐርፈዋል) በማረፉ ግብጽ እረኛን ስትፈልግ ነበር:: 'ማንን እንሹም' እያሉ ሲጨነቁ አንድ ሰው ጉቦ ሰጥቶ ሊሾም መሆኑን አበው ሰሙ:: ይህ ሰው ደግሞ ጭራሹኑ ልጅ ያለው ነው:: አባቶች ተሯሩጠው ያ ጉቦኛ ባለ ሚስት እንዳይሾም አደረጉ:: ቀጥለው ማንን እንደ ሚሾሙ ሲጨነቁ የሁሉም ሕሊና ስለ አንድ ሰው (አባ ዮሴፍ) ያስብ ነበር:: ሁሉም ተሰብሳቢዎች ስለ ነገሩ ተጨዋውተው አባ ዮሴፍን ይሾሙ ዘንድ ቆረጡ:: ተሰብስበው በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ ተባባሉ:: "ወደ በዓቱ ስንደርስ ቤቱ ክፍት ከቆየን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ዝግ ከሆነ ግን ፈጣሪ አልፈቀደም ማለት ነው" ሲሉ ተስማሙ:: ምክንያቱም የአበው በዓት ቶሎ ቶሎ አይከፈትምና:: ነገሩ ጥበበ እግዚአብሔር ነበረበትና ልክ ሲደርሱ እንግዳ ሊሸኝ በዓቱን ከፍቶ አገኙት:: እንዳያመልጣቸው ተረባርበው ያዙት:: ግጥም አድርገው አሥረው "አክዮስ-ይደልዎ-ይገባዋል" እያሉ ሥርዓተ ሲመት አደረሱለት:: እርሱ (አባ ዮሴፍ) ግን "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ: አይገባኝም: ልቀቁኝ" እያለ ይጮህ ነበረ:: አበው ግን ሥርዓተ ሢመቱን ፈጽመው ወስደው በመንበረ ዽዽስና: በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ዙፋን ላይ አስቀመጡት:: በቁጥርም 52ኛ ሁኖ ተቆጠረ:: አምላክ ደጉን ሰው ጠቁሟቸዋልና ለቤተ ክርስቲያን ይተጋ ጀመር:: ሕዝቡን እያስተማረ: አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ: መጻሕፍትን እየተረጐመ: ተአምራትን እየሠራ: በመንኖ ጥሪት ለ19 ዓመታት አገልግሏል:: ወቅቱም ተንባላት (አማሌቃውያን) በምድረ ግብጽ የሰለጠኑበት ነበርና ብዙ ችግሮችን አሳልፏል:: የግብጹ ሱልጣንም ሊገድለው 2 ጊዜ ሞክሮ አልተሳካለትም:: 2 ጊዜም ለአባ ዮሴፍ የሰነዘረው ሰይፍ በመልአክ እየተመለሰ ተመልክቶ ትቶታል:: አባ ዮሴፍ በዘመኑ ተሰዶ የነበረውን የኢትዮዽያ ዻዻስ አባ ዮሐንስንም ከተሰደደበት ወደ ሃገራችን እንደ መለሰው በዜና ሕይወቱ ተጽፏል:: አባ ዮሴፍ እንዲህ ተመላልሶ በ78 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ††† ቸር አምላክ በጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ጸሎት ይማረን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: ††† ጥቅምት 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ዮሴፍ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት 2.ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ኢላርዮስ 4.ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት ††† "ኤዺስ ቆዾስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና:: የማይኮራ: የማይቆጣ: የማይሰክር: የማይጨቃጨቅ: ነውረኛ ረብ የማይወድ: ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ: በጐ የሆነውን ነገር የሚወድ: ጠንቃቃ: ጻድቅ: ቅዱስ: ራሱን የሚገዛ ይሁን::" ††† (ቲቶ. ፩፥፯) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Show all...
ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ እናቱ ነሽና ለአዶናይ በስላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ የባህርያችን መመክያ ነሽ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.