cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

በዚህ ቻናል ላይ ማንኛውንም ☦☦የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአትን የጠበቁ ✥ አስተምሮቶችን ✟ ❖ ስብከቶችን ✟ ❖ መዝሙሮችን ✟ ❖ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ያገኛሉ።☨☨ "መፅሐፍ ቅዱስን ወዳጅህ አድርገው አንተ የቃሉ ወዳጅ ስትሆን እግዚአብሔር ደግሞ የልቡ ወዳጅ ያደርግሀል።"      /አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ/

Show more
Advertising posts
1 011
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+5130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ሦስቱን  ደጅ  ያልከፈተ የአብን ልጅ ጠበቡን አደንቃለሁ !!! 👉 ያለመለወጥ በኅቱም ድንግልና በመወለዱ 👉 የመቃብሩን ደጅ ሳይከፍት ሳለ ተነስቶ በመውጣቱ ፣ 👉 የቤቱ ደጅ  ተዘግቶ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ተሰብስበው ወዳሉበት ገባ ሳይከፍት ወጣ ። ስለዚህ ሶስት ደጆች ልቤ አደነቀች ። #ስለሁለቱ ምክንያት አገኝሁ የመቃብሩን ደጅ የሚመሥለው ነገር አለ ። /ዮሐ ፳፥፲፱-፳፮ / #ብልጣሶር የተባለ ዳንኤልን በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ በጣሉት ግዜ ጉድጓዱን በታላቅ መዝጊያ ዘጉት ዳንኤልም በርኃብ እንደተጨነቀ ልዑል እግዚአብሔር ባየ ግዜ መላዕኩን ወደ ነብዩ እንባቆም ላከ ። (ዳን ፮፥፲፮ - ፲፯) በራሱ ተሸክሞ ዳንኤል ወደአለበት ጉድጓድ አገባው ። ዳንኤልና ዕንባቆም  እንጀራውንና ንፍሮውን በልተው እግዚአብሔርን አመሠገኑ ። ዕንባቆምም ደጁ ተዘግቶ ሳለ ወጣ ። #ስለቤቱም ደጅ የሚመሥል ነገር አለ በግብረ ሐዋርያት እንደተጻፈ የእግዚአብሔር መላዕክ ከሰማይ ወርዶ ጴጥሮስን ከእስር ቤት እዳስወጣው  ጴጥሮስንም ካወጣው ቡኋላ ደጁ ተቆልፎ ዘበኞቹ በሁሉ ወገን ይጠብቁ ነበሩ ። (ሐዋ ፲፪፥፮) #ስለዚህ ለሁለቱ ደጆች ለቅዱሳን የተደረገውን ምክንያት አገኘሁ ስለ ድንግልናሽ ደጅ እጠናለሁ  ግን ምክንያት አላገኝሁም ሴት በድንግልና ወለደች ሲሉ አልሰማሁም ። ከወለደችም ቡኃላ በድንግልና የኖረች አላየሁም !!! #ይህ ነገር ምን ይረቅ ምን ይደንቅ ድንግል ሆይ ለዚህ አንክሮ ይገባል !!!        (አርጋኖን ዘቀዳሚት ፫፥፯-፲፱) 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ ? ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና  ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር ። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት ። #እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር !!! 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ዳግም_ትንሳኤ ፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል ፡፡ " ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።" (የዮሐንስ ወንጌል 20:26) 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ቅዳሜ #ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #አርብ #ቅድስት_ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ሐሙስ #አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች ። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡ #ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው። #በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።" #የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን (Orthodox and Bible fb page) 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ረቡዕ #አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን ፡፡ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #ማክሰኞ #ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/ankets_adeheno
Show all...