en
Feedback
Great ideas

Great ideas

Open in Telegram

ይህ great ideas (የምረጥ ሀሳቦች )መፍለቂያ ቤት ነው ። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው። ሀሳብ እና አስተያየት ካለወት #great_ideas ላይ ያስቀምጡልን #great_ideas #great_ideas #great_ideas great_ideasኢትዮጵያ

Show more
198
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
📱 ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን ነገሮች🚫 : ✅ በዝናብ ሰዓት #Networking የሆኑ ነገሮችን ማጥፋት (Airplane Mode ላይ ማድረግ) Off Wifi | Bluetooth & Main Network : ✅ FM (ኤፍ.ኤም) በEarphone አለማዳመጥ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች #FM_Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደ አንቴና ነው የሚጠቀሙት ስለዚህ በኢርፎን ስናዳማጥ Electromagnetic ራዲየሽኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል! : ✅ ስልክን #Charge እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይም  አለመደዋወል #Wifi አለመጠቀም Game አለመጫወት : ✅ በEarphone ሙዚቃ ስናዳምጥ #Equalizer በመጠቀም ድምፁን #Bass ላይ ማድረግ (ምክንያቱም በNormal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል - የHz አለመጣጣም! : ✅ ትልልቅ Magnet (Magnetic field) ያላቸው ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁን አታስቀምጡ : ✅ የስልክ ስክሪን #Blue_Light የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን #Brightness መቀነስ Blue Light Filter App መጠቀም! : ✅ የባትሪ ቻርጅ በጣም #Low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል! : ✅ ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ ቢያንስ ከ5 Centimetre በላይ ራቅ ማድረግ #Electromagnetic_Radiation ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቃሉ! : ✅ የሞባይል ስልኮን ታቅፈው አይተኙ በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 Metre በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው #Electromagnetic ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ! : ✅ ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ የጽንሱ ሕዋሳት ለElectromagnetic radiation እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለበዎት : ✅ ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል አይጠቀሙ ብረት የElecroMagnetic ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል ስለዚህ መኪና ውስጥ፣አውሮፕላን ውስጥ፣ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታ ብረት ወርክ ሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ.. አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን! : 📵በተለይ! በተለይ!📵 ✍ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል! : ✅ በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል! : ✅ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ልሾ ቅል በጣም ሾሾ ነው ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ! : ✅ ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ሾለ ሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት! ✅ Smartphone አብዝተን ስንጠቀም የሚመጣው በሽታ:-     -> Premature Death     -> Diabetes     -> Heart disease     -> የተለያዩ የCancer በሽታዎች     -> Discomfort     -> Musculoskeletal Symptoms ⚛ ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የራሱም የሆነ ከፍተኛ ጉዳት አለው ስለዚህ በተቻለን መጠን የSmartphone አጠቃቀማችንን እንቀንስ!!! https://t.me/great_ideas5

በህይወት ስትኖር ማወቅ ያሉብህ 3 ነገሮች 1⃣ የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው ስለዚህ በሙሉ አቅም መጣር አለብህ 2⃣ ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ ላንተም የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ 3⃣ ስትፈልገዉ ያጣከውን ነገር ትንሽ ከታገስክ በተራው ሲፈልግህ ታገኘዋለህ ውብ ምሽት ተመኘሁላችሁ !!! https://t.me/great_ideas5

✳የሚገርመው በዚህች ምድር ላይ ለራሱ ብሎ የሚኖር አንድም ነገር የለም፤ ‼ወንዝ የራሱን ዉሃ አይጠጣም፣ ‼ ባህር የራሱን ዓሳ አይበላም፣ ‼ አትክልት የራሱን ፍሬ አይመገብም፣ ‼ ፀሐይ የራሷን ሙቀት አትሞቅም፣ ‼ ጨረቃ ለራሷ ብላ አትደምቅም፣ ‼አበባ ለራሱ ሲል አትፈካም፣ ‼ ፍየል በግቷ የያዘችዉን ወተት አትጠጣም፣ - ነገሮች አንዱ ለሌላኛው እገዛ ነው የተፈጠሩት፣ - አንዱ ሌላው የጎደለዉን ለመሙላት ነው የተገኙት፣ - እኛም አንዳችን ለሌላኛችን እንኑር፣ - አንበላላ፣ አንጠፋፋ፣ እንተጋገዝ፣ * ሀሳብ የገባዉን - አዳምጠው፣ * ያማከረህን - መላ ስጠው፣ * ይቅርታ የጠየቀህን - እለፈው፣ * ቸገረኝ ያለህን - እርዳው፣ በዙርያችን ያለ ነገሮች ሁሉ ይጠፉና በመጨረሻም የሚቀረው የሠራነው መልካም ሥራ ብቻ ነው፡፡ * መልካምነት ዕድሜው ረጅም ነው፣ * መልካምነትም መልሶ ይከፍላል፣ ሰዉን በመጥቀም ይበልጥ የምንጠቀመው የምናድገውም እኛ መሆናችንን እንወቅ፣ https://t.me/great_ideas5

ውሎህን አስተካክል!! አሁን ያለህበትን ቦታ የማትፈልገው ከሆነ እና የተሻለ ነገር እንደሚገባህ ካመንክ ከአሁን ጀምረህ የምትውልበትን ቦታ ቀይር የምትሰማውን የምታየውን እያንዳንዱን ነገር አስተካክል ! ከማይጠቅሙህ ነገሮች ረስህን አውጣ ነፃ ሆነህ ለማሰብ ሞክር ይሉኝታን ቀንስ ነገ ላይ ተነስተህ ራስህን ከምትወቅስ ዛሬ ላይ የሚገባህን ነገር ማድረግ ተለማመድ ! https://t.me/great_ideas5

"People who distance themselves from mixing with others will not achimemoryccess. Mixing activates and generates memory. https://t.me/great_ideas5

#7ቱ_የሀብት_መንገዶች #1_ሹፌሩ_አንተ_ነህ በፍጥነት ሀብታም መሆን ከፈለግክ ሹፌር መሆን አለብህ። አንተ ተቆጣጠር:: 👉ገንዘብህን 👉አስተሳሰብህን 👉የወደፊት ገንዘባዊ እጣ ፈንታህን ሌሎች ሰዎች ሕይወትህን እንዲነዱ አትፍቀድ- አንተ ስኬትህን ትወስናለህ- አልያም ውድቀትህን። #2_ፈጣኑ_መሾመር ሚሊየነር መሆን ሁልጊዜ አዝጋሚ ሂደት መሆን የለበትም። የሚከተሉትን ካደረግክ ሀብታም ልትሆን ትችላለህ- 👉 ፍጠር 👉እሴት አምጣ 👉መልሶችን አቅርብ ለሌላ ሰው ችግር መፍትሄ ሁን። ያኔ ገንዘብ ታገኛለህ። #3_ለማሸነፍ_ፍጥነት_ያስፈልግሃል በፍጥነት ሚሊየነር መሆን  - በብዙ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ ነው። 👉የግል ጥረት 👉አስተሳሰብህ 👉ወጥነት 👉ቁርጠኝነት በመጨረሻው ውጤት ላይ አታተኩር፤ ወደ ውጤቱ የሚያመጣህ መንገድ ላይ አተኩር። #4_ገንዘብ_ቅዠት_ነው። ገንዘብ እውነተኛ ሀብት አይደለም። እውነተኛ ሀብት፡- 👉ጤና 👉ነፃነት 👉ደስታ 👉ከሰዎች ጋር ያለህ መልካም ግንኙነት… ናቸው ገንዘብ ደስታን አይገዛም፤ ገንዘብ ጊዜ ይገዛልሃል፤ ይህም ነፃነት ይሰጥሃል። #5_የሀብት_ቀመር ደመወዝ በፍጥነት ሀብትን አይገነባም። ሀብት = የተጣራ ገቢ + የንብረት ዋጋ የሚከተሉት ከፍተኛ የተጣራ ገቢን ይገነባሉ:- 👉ምርቶችን መሸጥ 👉ቢዝነስ መገንባት 👉የምርት ዋጋን ከፍ ማድረግ የፈጣን መሾመር ትኬትህ ለደንበኛህ ችግሩን መፍታት ነው። #6_የሀብት_ህግ ሚሊዮኖችን (በሀብት) መገንባት ማለት ሚሊዮኖችን (ሰዎችን) ማገልገል አለብህ ማለት ነው። ገቢን ለማሻሻል 2 መለኪያዎች አሉ፡- 1. ስፋት (ምን ያህል ይሸጣል) 2. መጠኑ (የሚሸጠው ዋጋ) ለደንበኞችህ እሴት ስትጨምር ገንዘብ ታገኛለህ። #7_ልማዶችህ_ድሃ_ያደርጉሃል ልማዶችህ ድሃ የመሆንህ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ባህሪ ወደ ድህነት ይመራል፡- 👉ለመማር ፈቃደኛ አለመሆን 👉ሰዎችን ለመማረክ መሞከር 👉ከገቢ በላይ ማጥፋት በሚሊየነር ፈጣን መሾመር ላይ መዝለል ከፈለግክ መጀመሪያ ጠንካራ እቅድ ያስፈልግሀል። https://t.me/great_ideas5

ውሎህን አስተካክል!! አሁን ያለህበትን ቦታ የማትፈልገው ከሆነ እና የተሻለ ነገር እንደሚገባህ ካመንክ ከአሁን ጀምረህ የምትውልበትን ቦታ ቀይር የምትሰማውን የምታየውን እያንዳንዱን ነገር አስተካክል ! ከማይጠቅሙህ ነገሮች ረስህን አውጣ ነፃ ሆነህ ለማሰብ ሞክር ይሉኝታን ቀንስ ነገ ላይ ተነስተህ ራስህን ከምትወቅስ ዛሬ ላይ የሚገባህን ነገር ማድረግ ተለማመድ !ውሎህን አስተካክል!! አሁን ያለህበትን ቦታ የማትፈልገው ከሆነ እና የተሻለ ነገር እንደሚገባህ ካመንክ ከአሁን ጀምረህ የምትውልበትን ቦታ ቀይር የምትሰማውን የምታየውን እያንዳንዱን ነገር አስተካክል ! ከማይጠቅሙህ ነገሮች ረስህን አውጣ ነፃ ሆነህ ለማሰብ ሞክር ይሉኝታን ቀንስ ነገ ላይ ተነስተህ ራስህን ከምትወቅስ ዛሬ ላይ የሚገባህን ነገር ማድረግ ተለማመድ ! https://t.me/great_ideas5

#ህይወት_ፈተና_ነው በጣም ከምወዳቸው ጥቅሶች አንዱ “ህይወት ፈተና ነው። ፈተና ባይሆን ኖሮማ በእያንዳንዱ ሁኔታ የት መሄድ፤ ምን ማድረግ እንዳለብን ይነገረን ነበር።” ይላል። ይህን ወርቃማ ጥቅስ ባሰብኩ ቁጥር በህይወት ውስጥ ሁሉን ማካበድ እንደሌለብኝ ይሰማኛል። ህይወትንና በውስጧ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን እንደፈተና ማየት ስትጀምር የሚያጋጥሙህን ችግሮች ለማደግ እንደሚረዱ እድሎች መመልከት ትጀምራለህ። ተከታታይ ችግሮች፣ ተደራራቢ ሀላፊነቶችና  የማይታለፉ የሚመስሉ ጉዳዩች ጭምር ከነገሮቹ በላይ እንድትሆን ለመፈተን የሚቀርቡ እድሎች ይሆናሉ። ነገር ግን በተቃራኒው የሚያጋጥሙህን ጉዳዮች ሁሉ እንደ የሞት ሽረት ትግል የምትመለከታቸው ከሆነ ህይወት ኮሮኮንች መንገድ ይሆንብሀል። “ደስተኛ የምሆነው ሁሉም ነገሮች የተስተካከሉ ሲሆኑ ብቻ ነው!” ብለህ ትደመድማለህ። የሚያሳዝነው ሁሉም ነገሮች የተስተካከሉ የሚሆኑት ከስንት አንዴ ነው። ነገሮች አስቸጋሪ ሲሆኑ ለሙከራ ያክል ይህን መንገድ ሞክረው። ምናልባት የሚያስቸግር ወንድም ወይም የሚያስጨንቅ አለቃ ይኖርሀል። ለሙከራ ያክል የሚያጋጥምህን ሁኔታ “ችግር” ከማለት “ፈተና” ብለህ ጥራው። በሁኔታው ከመናደድ ከሁኔታው መማር የምትችለውን ነገር ፈልግ። “ይህ ነገር በህይወቴ ለምን ተከሰተ?” እንዴት በተለየ መንገድ ልመለከተው እችላለሁ? የሆነ አይነት ፈተና ይሆን?” ብለህ ራስህን ጠይቅ። ይህንን ስትራቴጂ ከሞከርክ ለነገሮች የሚኖርህ ምላሽ ሲለወጥ አይተህ መገረምህ አይቀርም። "ጊዜ ያጥረኛል" በሚል ሀሳብ እቸገር ነበር። ሁሉንም ነገሮች ለማከናወን እሯሯጣለሁ። የፕሮግራሜ መጣበብ፣ መስሪያ ቤቴን፣ ቤተሰቤን በአጠቃላይ ጊዜዬን እየተሻሙ የመሰሉኝን ነገሮች ሁሉ እወቅሳለሁ። ከዛ ድንገት ብልጭ አለልኝ። ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልገው አንዳንዱን ነገር በደንብ መስራት ሳይሆን የሚችሉትን ያክል ሰርቶ የቀረውን “ስራው ያውጣው!” ብሎ መተው መቻል ነው። በሌላ አነጋገር ችግሮችን እንደፈተና ማየት ስጀምር በፊት በጣም ያሳስቡኝ የነበሩትን ችግሮች በቀላሉ መወጣት ችያለሁ። ይሁን እንጂ አሁንም አልፎ አልፎ ጊዜ እያጠረኝ እንደምቸገር ግን አልክድም። ቀላሉን ነገር አታካብድ !https://t.me/great_ideas5 ከወደዱት_ለወዳጅ_ዘመድዎ #share Join&share 👉 https://t.me/great_ideas5

🫧ስለ 5ጂ ሰምተው ተደንቀው ይሆናል፤ የ6ጂ መንገድ መጀመሩን ቢያውቁስ? 🧵የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል መሐንዲሶች እስከ 100 ጊጋኸርዝ ባለው የራዲዮን ፍሪኩዌንሲ መስራት የምትችል ገመድ አልባ ትራንሲቨር ሰርተዋል፡፡ 🧵ይህም በአሁኑ ሰዓት በግንባታ ላይ ካለው የአምስተኛው ትውልድ ገመድ አልባ ግንኙነት (#5ጂ) መስራት ከሚችለው አራት እጥፍ የላቀ ነው፡፡ 🧵በፈጣሪዎቿ “#end-to-end transmitter-receiver” የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች ባለ 4.4 ካሬ ሚ.ሜ ቺፕ ለተላበሰችው የተለየ የዲጂታል-አናሎግ አወቃቀር ምስጋና ይግባውና ዲጂታል ሲግናሎችን ፈጣንና ኃይል ቆጣቢ በሆነ መልኩ ማንቀሳቀስ ትችላለች፡፡ 🧵በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፓያም ሄይዳሪ አዲሱ ፈጠራቸው የሚያቀርበው የፍጥነት እና ዳታ መጠን ከአዳዳሶቹ የገመድ አልባ ግንኙነት ደረጃዎች እንኳን ሲነፃፀር በሁለት #orders of magnitude የላቀ መሆኑን በመጥቀስ መሳሪያውን 5ጂን የተሸገረ ብለውታል፡፡ 🧵ይህ እውነት አለው፡፡ #5ጂ መስራት የሚችለው ከ28 እስከ 38 ጊጋ ኸርዝ ባለው ገደብ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ መልኩ #6ጂ ከ100 ጊጋ ኸርዝ በላይ እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡ 🧵ይህች አነስተኛ ቺፕ ዳታን በከፍተኛ ፍጥነት ማዘዋወር መቻሏ የነገሮች ከበይነ-መረብ ጋራ ያላቸው ትስስር (#Internet Of Things) እየላቀ በመጣበት በዚህ ወቅት እጅጉን አስፈላጊ ያደርጋታል፡፡ 🧵ከዚህም ባሻገር መረጃን በማዘዋወር ረገድ ያላት ፍጥነት ከገመድ ጋር ተወዳዳሪ ስለሆነ እንደ ዳታ ሴንተር ባሉ ስፍራዎች ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የገመድ ዝርጋታ እና እርሱን ተከትሎት የሚመጣውን ከፍተኛ ወጪንም እንደምትቀንስ ይጠበቃል፡፡                                                                                         https://t.me/great_ideas5

🧵የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካል መሐንዲሶች እስከ 100 ጊጋኸርዝ ባለው የራዲዮን ፍሪኩዌንሲ መስራት የምትችል ገመድ አልባ ትራንሲቨር ሰርተዋል፡፡ 🧵ይህም በአሁኑ ሰዓት በግንባታ ላይ ካለው የአምስተኛው ትውልድ ገመድ አልባ ግንኙነት (#5ጂ) መስራት ከሚችለው አራት እጥፍ የላቀ ነው፡፡ 🧵በፈጣሪዎቿ “#end-to-end transmitter-receiver” የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች ባለ 4.4 ካሬ ሚ.ሜ ቺፕ ለተላበሰችው የተለየ የዲጂታል-አናሎግ አወቃቀር ምስጋና ይግባውና ዲጂታል ሲግናሎችን ፈጣንና ኃይል ቆጣቢ በሆነ መልኩ ማንቀሳቀስ ትችላለች፡፡ 🧵በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፓያም ሄይዳሪ አዲሱ ፈጠራቸው የሚያቀርበው የፍጥነት እና ዳታ መጠን ከአዳዳሶቹ የገመድ አልባ ግንኙነት ደረጃዎች እንኳን ሲነፃፀር በሁለት #orders of magnitude የላቀ መሆኑን በመጥቀስ መሳሪያውን 5ጂን የተሸገረ ብለውታል፡፡ 🧵ይህ እውነት አለው፡፡ #5ጂ መስራት የሚችለው ከ28 እስከ 38 ጊጋ ኸርዝ ባለው ገደብ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ መልኩ #6ጂ ከ100 ጊጋ ኸርዝ በላይ እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡ 🧵ይህች አነስተኛ ቺፕ ዳታን በከፍተኛ ፍጥነት ማዘዋወር መቻሏ የነገሮች ከበይነ-መረብ ጋራ ያላቸው ትስስር (#Internet Of Things) እየላቀ በመጣበት በዚህ ወቅት እጅጉን አስፈላጊ ያደርጋታል፡፡ 🧵ከዚህም ባሻገር መረጃን በማዘዋወር ረገድ ያላት ፍጥነት ከገመድ ጋር ተወዳዳሪ ስለሆነ እንደ ዳታ ሴንተር ባሉ ስፍራዎች ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የገመድ ዝርጋታ እና እርሱን ተከትሎት የሚመጣውን ከፍተኛ ወጪንም እንደምትቀንስ ይጠበቃል፡፡ https://t.me/great_ideas5

ትችትን እንዴት መቋቋም ይቻላል? ===================== በስራችን ላይ አሉታዊ ነገር ተነግሮን ይቅርና ፌስቡክ ላይ ፖስት ያደርግነው ሁለት ላይክ ብቻ ሲያገኝ ጥሩ ስሜት አይስማንም፡፡በስራችንም ሆነ በግል ህይወታችን ስኬታማ ለመሆን ትችትን መቋቋም ብሎም መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ትችት ምንድነው? --------------------- ትችት ሰዎች ለሆነ ድርጊት ወይም ሁኔታ የሚሰጡት አስተያየት ሲሆን ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል ፡፡ ትችት ሁሉም ቦታ አለ፡፡ በስራቦታ፤በጓደኛ፤በቤተሰብ፤በፍቅረኛ፤ሊሆን ይችላል፡፡ሰዎች በተለያየ ምክንያት ትችት ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡ቤተሠብ ጓደኛ በቀና አስተሳሰብ የተሠማቸውን ለመግለፅ ወይም እንድንሻሻል በማሠብ አለቆች ሠራተኞች የበለጠ እንደሰሩ ለማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡በተቃራኒው ደግሞ በቅናት ፤በጥላቻ ስህተት ፈላጊ በመሆንና የተሻሉ እንዲሆኑ ለማሣየት ሊሆን ይችላል፡፡ ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች ሰዎች ለራሣቸው የሚሰጡትን ግምት በመቀነስ የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ፡፡ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች መብሰልስል፤ጭንቀት፤ድብርት “ለምን እንደዚህ ተባልኩ?” እያሉ እንቅልፍ ማጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ትችትን በመፍራት አቅም እያላቸው መስራት የሚያቆሙም አይጠፉም፡፡ትችት የማይቀር ነገር በመሆኑ ብዙ መጨነቅ አይገባንም፡፡የሚሰነዘሩብንን ትችቶች ለማቋቋም የሚረዱ የተወሰኑ ነጥቦች፤ ማዳመጥ ------------ ለትችት ምላሽ ከመስጠታችን በፊት ጠቃሚ ነው አይደለም የሚለውን መለየት አለብን፡፡ ጓደኛችን አብረን ከተዝናናን በኃላ ‘’ገንዘብ ታባክናህ’’ ቢለን ሊሠማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ያመለከተው ነገር ራሣችንን እንድንለውጥ የሚያግዘን ይሆናል፡፡ምላሽ ለመስጠት ከመፍጠናችን በፊት ማዳመጥና ምን ለማለት እንደሆነ መረዳት ጥሩ ነው፡፡ በተረጋጋ ሁኔታ መመለሾ ----------------------------- የተሰጠን ትችት ጠቃሚ ከሆነ በአክብሮት አመስግነን መቀበል፤አሉታዊ ከሆነም በአክብሮት ምላሽ መስጠት (አሉታዊ ሲሆን ቀላል ላይሆን ይችላል)፡፡ በግል አለመውሰድ ------------------------ ሰዎች የሚሰጡት ትችት ስለኛ ከሚናገረው ይበልጥ ስለእነሱ እንደሚናገር ማወቅ አለብን፡፡በተጨማሪም አንድ ድርጊት ላይ ያለን ድክመት ስለማንነታችን እንደማይናር ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሂሣብ ላይ ቀሽም ከሆንን የሚያሳየው ሂሳብ ላይ ቀሽም እንደሆንን እንጂ እኛ ቀሺም እንደሆንን አይደለም፡፡ አንዳንዴ ትችት ደካማ ጎን ላይ በማተኮር ራሣችንን እንድንጠራጠርና ያሉንን ብዙ ብቃቶች እንድንዘነጋ ያረገናል፡፡ ስለዚህ ትችትን በግል አለመውሰድ ለራሣችን ያለን ግምት እንዳይቀነስ ይረዳናል፡፡ ጠንክሮ መቀጠል --------------------- ጠቃሚ ትችትን ተቀብሎ መቀጠል ራሣችንን እንድናሻሽል ይረዳል፡፡አሉታዊ ትችት የአንድ ሰው አመለካከት ብቻ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡መድረስ ያሰብንበትን አላማ ላይ እንዳንደርስ አሉታዊ ትችቶች እንዲገድቡን መፍቀድ የለብንም ፡፡ትልልቅ ፈጠራ የሰሩ ሰዎች መጀመሪያ ሀሣባቸውን ሲናገሩ “ዋው የሚገርም ትልቅ ሀሣብ ነው” አልተባሉም፡፡ በተቃራኒው “ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡” እና “አትጃጃል ጊዜህን አታጥፋ፡፡” ነው የተባሉት፡፡    ለማጠቃለል ሼክስፒር እንዳለው የመስታወት ያህል ጥራት የበረዶ ያህል ንጣት ቢኖረንም ሰዎች ከሚስነዝሩብን ትችት አናመልጥም፡፡የሚያደርሰውን ተፅእኖ መቋቋም እንዲሁም ራሣችንን ለማሻሻል መጠቀም ግን ይቻላል፡፡ https://t.me/great_ideas5

R E M E D A N ለእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ 🍁 እንኳን ለ ታላቁ የ ረመዳን ፆም አደረሳችሁ።🌿 https://t.me/great_ideas5

ደፋር ሰው !   'ደፋር ሰው ማለት ፍርሀት የማይሰማው አይደለም ግን ከፍርሀቱ ጋር ፊት ለፊት የሚፋለም ነው' ይለናል ኔልሰን ማንዴላ። ይሄን የምናነብ ሁላችንም ፍርሀታችንን ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን ምክንያቱም ፍርሀታችንን የምናስተናግድበት መንገድ የህይወት መዳረሻችንን በሁለት መንገድ ይወስነዋል።  * አዲስና አስገራሚ የህይወት አጋጣሚዎችን እናጣጥማለን * ምንም ሳንሞክር እንደፈራን እናልፋለን https://t.me/great_ideas5

#ውሎህን_ፈትሽ   አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት " ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል። የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል:: አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት ☞ "ውሎሽ የት ነው?" ☞እንግዲህ እዚህ ጋር ቆም እንበል፣ ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ መቼም ማንም በጤፍ ማሳ ላይ ስንዴን አይጠበቅም። ስለዚህ ምንጊዜም:-ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ምክንያቱም :-ሀሳባችን ስራችንን ስራችን ውጤታችንን ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና!    ከወደዱት_ለወዳጅ_ዘመድዎ #share https://t.me/great_ideas5 Join&share 👉 https://t.me/great_ideas5

👉👩‍💻👨‍💻 በ20ዎቹ_እድሜ_ክልል • ጤናህን ጠብቅ-- በ20ዎቹ እድሜ ክልል ጤናህ የመጀመሪያዉና ወሳኙ ነገር መሆኑን ተረዳ። • የራስህን ልክ እወቅ--የራስህንም ሆነ የሰዎችን ልክ ማወቅ በጣም ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰዉ መናገር ካልፈለገ እንዲናር አታስገድደዉ...መሄድ ካልፈለገ 'ለምን አልሄድክም?' ብለህ አትነዛነዝ፡፡ • ሰዎች የምትፈልገዉንና ያልፈለከዉን ነገር ረግጠዉ ሊገቡ ሲሞክሩ አስቁማቸዉ፡፡ ማንም ይሁኑ ምን በራስህ ላይ እንዲረማመዱ አትፍቀድ። • ለራስህ እዉነተኛ ሁን፡፡ ሰዎችን ለማስደሰት ብለህ ተራራ አትዉጣ ድንጋይ አትቆፍር፡፡ ሰዎች በራሳቸዉ የማይረካ አይነት ባህሪ ሊያንፀባርቁ ስለሚችሉ ጊዜህን አታጥፋ። • እራስህን ቻል፡፡ የራስህን ችግር በራስህ ፍታ፣ ቤትህን አፅዳ፣ ወጪህን በራስህ ሸፍን ብቻህን የምትኖር ከሆነ ምግብ ስራ፡፡ ‘ሚስት ቢኖረኝ እኮ...’የሚለዉን የስንፍና ምልክት አትጠቀም፡፡ ስለሚስት ሳይሆን እራስህን እንዴት ማሻሻል እንዳለብህ ተረዳ። • ከሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብህ እወቅ፡፡ ሃሳብህን በተረጋጋና ስርአት ባለዉ መንገድ ተናገር፡ ሰዎች ሲያወሩም ማዳመጥን ተማር። • እድሎችን ተጠቀም--በ20ዎቹ ያልተጠቀምክበትን እድል መቼም ልትጠቀምበት አትችልምና ደፈር ብለህ ሃላፊነቶችን ዉሰድ። • መዉደድን ተማር--ፍቅር መስጠትንና መቀበልን ተማር፡፡ ይህ ልምድ ህይወት እንዳይሰለችህና ለሰዎች የማሰብ ባህሪን ታዳብርበታለህ። • የሰነፍ አንደኛ አትሁን--በምትሰራዉ ሾል ይብዛም ይነስም ያለህን አቅም አሟጠህ ተጠቀምና ፍሬ አፍራ፡፡ ለራስህ ህይወት ሃላፊነቱን የሚወስደዉ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ መንግስት፣ ሀገር ምናምን እያልክ ዉስጥህ የተቀጣጠለዉን ሃይል አታጥፋዉ፡፡ ዛሬን ተነስተህ ድከም...ነገ ታርፋለህ። • ገንዘብን እወቅ--ገንዘብን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብህ ከህይወትህ ልምድ፣ ካጋፈጡህ ችግሮች እንዲሁም ከተለያዩ መፃህፍቶች ተረዳ። • ተዝናና--ያለህን ጊዜ በሙሉ በስራና በትምህርት ብቻ ካዋልከዉ አንድ ቀን ምንም ደስ የምትሰኝበትን ትዉስታ ስላላሳለፍክ ይቆጭሃል፡፡ በመጠኑና በልኩ ተዝናና፣ አሪፍ ጊዜ ከቤተሰቦችህ፣ከጓደኞችህ ወዘተ ይኑርህ፡፡ ነገ ለልጆችህ እንዲህ ነበር ብለህ የምታወራዉን አሪፍ ትዝታ ቅረፅ።                                   ከወደዱት_ለወዳጅ_ዘመድዎ #share https://t.me/great_ideas5 Join&share 👉 https://t.me/great_ideas5

👉"በይነ መረብ(internet) ምንድን ነዉ?"                                                  🔘 በይነመረብ(internet) በአለም ዙሪያ ባሉ ኮምፒውተሮች እና መሳሪያዎች መካከል ግንኙነትን እና መረጃን መጋራት የሚያስችል አለምአቀፍ ትስስር ያለው የኮምፒውተር ኔትወርኮች ነው። 🔘 ደረጃውን የጠበቀ የኮሙዩኒኬሽን ፕሮቶኮሎችን በመጠቀም በአንድነት የተገናኙ ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች፣ ራውተሮች፣ ስዊች እና ሌሎች መሳሪያዎች መረጃን  ለመለዋወጥ ሰፊ መሠረተ ልማት ለመፍጠር የሚያስችል ሰፊ የኮምፒዩተር፣ ሰርቨር፣ ራውተር፣ ስዊች እና ሌሎች መሳሪያዎች ኔትወርክ ነው። 🔘 በይነመረብ ሰዎች መረጃን እንዲያገኙ እና እንዲለዋወጡ፣ በኢሜል፣ በመልዕክት እና በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች እርስ በርስ እንዲግባቡ፣ የመስመር ላይ ግብይቶችን እንዲያካሂዱ እና ከአውታረ መረቡ ጋር ግንኙነት የሚጠይቁ ሌሎች ተግባራትን እንዲያከናውኑ ያስችላቸዋል።                                         https://t.me/great_ideas5

የሰው ልጅ ዕውቀት ብቻውን የትም አያደርሰውም፡፡ ዕውቀት በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን የተወሰነ ምክንያታዊ ሃሳብ ነው፡፡ ምናብ ግን ሰፊ ነው፡፡ ምናብ የመሬቱን ብቻ ሳይሆን የሰማዩን ሃሳብ በሃሳባችን የምንደርስበት የአእምሮ መነፅራችን ነው፡፡ ሰው ተኝቶ ብቻ ሳይሆን በእውኑም ሆኖ በምናቡ ብዙ ነገር ያስባል፡፡ ሰፊውን ዓለም ይቃኛል፡፡ ከየት ተነስቶ ወደየት እንደሚሄድ መድረሻውም ምን እንደሚመስል በአዕምሮው ያካልላል፡፡ ብዙ የሳይንስ ሰዎች ሳይንሳዊ ግኝታቸውን ዕውን ከማድረጋቸው በፊት ስለሚመረምሩት ጉዳይ ቀድመው በምናባቸው የአዕምሮ ንድፍ ያወጣሉ፤ በሃሳባቸው ይስላሉ፣ ቅርፅ ያወጣሉ፡፡ ዓለም እዚህ የስልጣኔ ርቅቀት ላይ የደረሰችው ምናባቸውን በተግባር በለወጡ ምናባዊ ሰዎች ነው፡፡ የማይታየውን የሚያዩ፣ የማይሰማውን የሚያዳምጡ፣ የማይታሰበውን የሚያስቡ ምናባዊ ሰዎች ናቸው፡፡ ብዙ ሰው ከሚያየው ርቀው ያልታየውን ለማየት የአዕምሯቸውን ቴሌስኮፕ የሚጠቀሙ ዓለምን በምናባቸው ለመረዳት የሚጥሩ አሳቢያን ናቸው፡፡ ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን፡- ‹‹ምናብ ከዕውቀት የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ ዕውቀት ውስን ነው፡፡ ምናብ ግን ዓለሙን ሁሉ ያካልላል (Imagination is more important than knowledge. Knowledge is limited. Imagination encircles the world)፡፡›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ አዎ ምናብ ሐገሩ ሰፊ ነው፡፡ ምናባዊ ሰው በኖረበት፣ ባደገበትና ሕብረተሰቡ በጋተው ሃሳብ ብቻ አይወሰንም፡፡ አልፎ ይሄዳል፡፡ የማይርስበት የዓለም ጥግ የለም፡፡ ምናብ የምታየውን ነገር ቅርፅ የምታሲዝበት፤ የምትሰማውን አዳምጠህ ትርጉሙን የምትፈታበት የረቀቀ ሃሳብ ነው፡፡ በሚታየው ውስጥ የማይታየውን ፍቺ መፈለግ ነው ምናባዊነት፡፡ ምናብ ያለው ሰው የሚታመነው ዓለሙ ባሰቀመጠለት ትርጉም ብቻ ሳይሆን በገዛ ሃሳቡ ከፍቺው በላይ ያለውን ሚስጥር በመፈለግ ነው እውነታውን የሚቀበለው፡፡ በሚሰማው ብቻ ጆሮውን አይዘጋም፤ ከሚሰማው በላይ ያለውን የተፈጥሮ ዝምታ እስከማዳመጥ ይደርሳል ምናባዊነት፡፡ የፀጥታውን ድምፅ መፈለግ ነው ምናባዊነት፡፡ ከሚታየው በላይ ማየት መቻል ነው የምናብ ሰው መሆን ማለት፡፡ አልፎ ማየት፣ ርቆ መስማት፤ አሻግሮ መመልከት፣ እንደነብይ ዘመናትን ቀድሞ መረዳት ነው ምናባዊነት፡፡ ምናባዊነት መሠረቱ ማሰብ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል እየተመራ ብዙ ሰው ያልደረሰበትን ይመረምራል፡፡ ምናብ ባይኖር ደራስያን አይኖሩም ነበር፡፡ የፊልም ሰዎች ያለምናብ የተለየ ትዕይንት አያሳዩንም፡፡ ምናብ የሌላቸው ደራሲዎች አዲስ ነገር አይፅፉም፡፡ ልብ ውልቅ ናቸው! የኖርንበትን እውነት ቀለም ቀብተው ከማቅረብ ውጪ የተለየ ያላየነውን አይተው ለማሳየት አይችሉም፡፡ ምናብ ባይኖር የሳይንስ ሰዎች ዓለምን እዚህ አያደርሷትም ነበር፡፡ ምናብ ባቡር ነው፤ ዓለምን በፍጥነት በመንታ የሃሳብ ድልድይ ይዞ የሚነጉድ፡፡ ይሆናል እና አይሆንምን በጀርባው አዝሎ ከድብቁ ዓለም ሚስጥሩን የሚተነትንና የሚመረምር ነው ምናብ ማለት፡፡ አንዳንድ ሰው ምናባዊ ነኝ ለማለት ከሰውነት ጎዳና ሲወጣ ይታያል፡፡ ምናባዊነት ራስን መዘንጋት አይደለም፡፡ ምናባዊነት በአዕምሮ መደንዘዝ፣ በሃሳብ መፍዘዝ አይደለም፡፡ ምናባዊነት በሱስ ጅረት መፍሰስ ሳይሆን በሃሳብ ባህር ውስጥ መቅዘፍ ነው፡፡ ምናባዊነት ራስን ይዞ ዓለምንም ማሳደግ ነው፡፡ ራስን ጥሎ አዲስ ነገር መፍጠር አይቻልም፡፡ አንዳንዶች ተፈላሰፍን ብለው ተልፈስፍሰው ይወድቃሉ፡፡ አዲስ ነገር አገኘን ብለው ራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ የፍልስፍና ሀሁ ራስን አውቆ ራስን መጠበቅ ነው፤ ሲከተልም ዓለሙን መረዳት፤ ሲሰልስም የማይታየውን ማየት፣ ሲቀጥልም የማይደረስበት ላይ መድረስም ጭምር ነው፡፡ የሰው አዕምሮ ማሰብ እስከሚችለው ድረስ እንዲያስብና አዲስ ነገር መፍጠር እንዲችል ተደርጎ ነበር የተፈጠረው፡፡ ግና ግን ማሰቢያውን የተጠቀመ ጥቂት ነው፡፡ ምናብ የሌለው ሰው ግን የሌሎች ጭንቅላት ባሪያ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ጭንቅላቱ ሰርቶ እንዳይበላ አዕምሮውን የበይ ተመልካች ያደርገዋል፡፡ ከሌሎች ኮርጆና ቀድቶ መኖርን አንጂ አስቦ አዲስ ነገር መፍጠርን አያስተምረውም፡፡  ጭንቅላትን አጎንባሽ ባሪያ ማድረግ ራስን ማዋረድ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለዓለም የሚያዋጠው የራሱ እሴት ከሌለው ከሞተው በምንም አይሻልም፡፡ በመኖርህ ለዓለም የምትጨምረው አዲስ ዕውቀት፣ ልዩ ሃሳብ ከሌለህ የመኖርህ ትርጉም ምንም ይሆናል፡፡ https://t.me/great_ideas5

የሰው ልጅ ዕውቀት ብቻውን የትም አያደርሰውም፡፡ ዕውቀት በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን የተወሰነ ምክንያታዊ ሃሳብ ነው፡፡ ምናብ ግን ሰፊ ነው፡፡ ምናብ የመሬቱን ብቻ ሳይሆን የሰማዩን ሃሳብ በሃሳባችን የምንደርስበት የአእምሮ መነፅራችን ነው፡፡ ሰው ተኝቶ ብቻ ሳይሆን በእውኑም ሆኖ በምናቡ ብዙ ነገር ያስባል፡፡ ሰፊውን ዓለም ይቃኛል፡፡ ከየት ተነስቶ ወደየት እንደሚሄድ መድረሻውም ምን እንደሚመስል በአዕምሮው ያካልላል፡፡ ብዙ የሳይንስ ሰዎች ሳይንሳዊ ግኝታቸውን ዕውን ከማድረጋቸው በፊት ስለሚመረምሩት ጉዳይ ቀድመው በምናባቸው የአዕምሮ ንድፍ ያወጣሉ፤ በሃሳባቸው ይስላሉ፣ ቅርፅ ያወጣሉ፡፡ ዓለም እዚህ የስልጣኔ ርቅቀት ላይ የደረሰችው ምናባቸውን በተግባር በለወጡ ምናባዊ ሰዎች ነው፡፡ የማይታየውን የሚያዩ፣ የማይሰማውን የሚያዳምጡ፣ የማይታሰበውን የሚያስቡ ምናባዊ ሰዎች ናቸው፡፡ ብዙ ሰው ከሚያየው ርቀው ያልታየውን ለማየት የአዕምሯቸውን ቴሌስኮፕ የሚጠቀሙ ዓለምን በምናባቸው ለመረዳት የሚጥሩ አሳቢያን ናቸው፡፡ ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን፡- ‹‹ምናብ ከዕውቀት የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ ዕውቀት ውስን ነው፡፡ ምናብ ግን ዓለሙን ሁሉ ያካልላል (Imagination is more important than knowledge. Knowledge is limited. Imagination encircles the world)፡፡›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ አዎ ምናብ ሐገሩ ሰፊ ነው፡፡ ምናባዊ ሰው በኖረበት፣ ባደገበትና ሕብረተሰቡ በጋተው ሃሳብ ብቻ አይወሰንም፡፡ አልፎ ይሄዳል፡፡ የማይርስበት የዓለም ጥግ የለም፡፡ ምናብ የምታየውን ነገር ቅርፅ የምታሲዝበት፤ የምትሰማውን አዳምጠህ ትርጉሙን የምትፈታበት የረቀቀ ሃሳብ ነው፡፡ በሚታየው ውስጥ የማይታየውን ፍቺ መፈለግ ነው ምናባዊነት፡፡ ምናብ ያለው ሰው የሚታመነው ዓለሙ ባሰቀመጠለት ትርጉም ብቻ ሳይሆን በገዛ ሃሳቡ ከፍቺው በላይ ያለውን ሚስጥር በመፈለግ ነው እውነታውን የሚቀበለው፡፡ በሚሰማው ብቻ ጆሮውን አይዘጋም፤ ከሚሰማው በላይ ያለውን የተፈጥሮ ዝምታ እስከማዳመጥ ይደርሳል ምናባዊነት፡፡ የፀጥታውን ድምፅ መፈለግ ነው ምናባዊነት፡፡ ከሚታየው በላይ ማየት መቻል ነው የምናብ ሰው መሆን ማለት፡፡ አልፎ ማየት፣ ርቆ መስማት፤ አሻግሮ መመልከት፣ እንደነብይ ዘመናትን ቀድሞ መረዳት ነው ምናባዊነት፡፡ ምናባዊነት መሠረቱ ማሰብ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል እየተመራ ብዙ ሰው ያልደረሰበትን ይመረምራል፡፡ ምናብ ባይኖር ደራስያን አይኖሩም ነበር፡፡ የፊልም ሰዎች ያለምናብ የተለየ ትዕይንት አያሳዩንም፡፡ ምናብ የሌላቸው ደራሲዎች አዲስ ነገር አይፅፉም፡፡ ልብ ውልቅ ናቸው! የኖርንበትን እውነት ቀለም ቀብተው ከማቅረብ ውጪ የተለየ ያላየነውን አይተው ለማሳየት አይችሉም፡፡ ምናብ ባይኖር የሳይንስ ሰዎች ዓለምን እዚህ አያደርሷትም ነበር፡፡ ምናብ ባቡር ነው፤ ዓለምን በፍጥነት በመንታ የሃሳብ ድልድይ ይዞ የሚነጉድ፡፡ ይሆናል እና አይሆንምን በጀርባው አዝሎ ከድብቁ ዓለም ሚስጥሩን የሚተነትንና የሚመረምር ነው ምናብ ማለት፡፡ አንዳንድ ሰው ምናባዊ ነኝ ለማለት ከሰውነት ጎዳና ሲወጣ ይታያል፡፡ ምናባዊነት ራስን መዘንጋት አይደለም፡፡ ምናባዊነት በአዕምሮ መደንዘዝ፣ በሃሳብ መፍዘዝ አይደለም፡፡ ምናባዊነት በሱስ ጅረት መፍሰስ ሳይሆን በሃሳብ ባህር ውስጥ መቅዘፍ ነው፡፡ ምናባዊነት ራስን ይዞ ዓለምንም ማሳደግ ነው፡፡ ራስን ጥሎ አዲስ ነገር መፍጠር አይቻልም፡፡ አንዳንዶች ተፈላሰፍን ብለው ተልፈስፍሰው ይወድቃሉ፡፡ አዲስ ነገር አገኘን ብለው ራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ የፍልስፍና ሀሁ ራስን አውቆ ራስን መጠበቅ ነው፤ ሲከተልም ዓለሙን መረዳት፤ ሲሰልስም የማይታየውን ማየት፣ ሲቀጥልም የማይደረስበት ላይ መድረስም ጭምር ነው፡፡ የሰው አዕምሮ ማሰብ እስከሚችለው ድረስ እንዲያስብና አዲስ ነገር መፍጠር እንዲችል ተደርጎ ነበር የተፈጠረው፡፡ ግና ግን ማሰቢያውን የተጠቀመ ጥቂት ነው፡፡ ምናብ የሌለው ሰው ግን የሌሎች ጭንቅላት ባሪያ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ጭንቅላቱ ሰርቶ እንዳይበላ አዕምሮውን የበይ ተመልካች ያደርገዋል፡፡ ከሌሎች ኮርጆና ቀድቶ መኖርን አንጂ አስቦ አዲስ ነገር መፍጠርን አያስተምረውም፡፡  ጭንቅላትን አጎንባሽ ባሪያ ማድረግ ራስን ማዋረድ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለዓለም የሚያዋጠው የራሱ እሴት ከሌለው ከሞተው በምንም አይሻልም፡፡ በመኖርህ ለዓለም የምትጨምረው አዲስ ዕውቀት፣ ልዩ ሃሳብ ከሌለህ የመኖርህ ትርጉም ምንም ይሆናል፡፡ https://t.me/great_ideas5

በፍልስፍና ታሪክ #ከኢማኑኤል_ካንት በፊትና በካንት ዘመን  የነበሩ ሁለት የፍልስፍና ጎራዎች ከፍተኛ የሙሁራዊ ፍጭት ውስጥ የገበቡት ወቅት ነበር። አንደኛው ጎራ በዲካርቴስ፣ ሲፒኖዛና ሌቤንዝ ፊት አውራሪነት የሚመራው እና ትክክለኛ እውቀት ከሰው ልጅ ህሊና ውስጥ  ይመነጫል በሚል የሚከራከሩት በተለምዶ Rationalists ተብለው የሚጠሩት ናቸው፡፡ በሌላው ጎራ እውቀት የሚገኘው ከሰው ልጅ ህሊና ውስጥ ሳይሆን በልምድ የሚገኙ ዉጫዊ ተሞክሮዎችን በማሰባሰብ በሚፈጠረው ግንዛቤ እውቀት በማደራጀት ነው የሚሉት እንደ ሁም፣ ሎክ ባርክሌይን የመሳሰሉ  እንግሊዛውያን ፈላስፋዎች የሚገኙበት Empiricists ምድብ ነው፡፡ ካንት ታዲያ በፍልስፍናው የሁለቱን የሙህራን ፍጭት እልባት ለመስጠት የሚያስችል ሀሳብ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ካንት ሀይማኖት በተለይም ክርስትና ከሳይንሱ ጋር የሚዛመድብትን መንገድ ለማመላከት ጥረት አድርጓል፡፡ የካንት ፍልስፍና ትንታኔ መንገድ በመሰረታዊነት ምክንያታዊ አሳቦችን በጥልቀት በማጥናት የሰው ልጅ ግንዛቤ የሚዳበርብትን መንገድ በተለይም ደግሞ በልምድ ሊገኙ የማይችሉ የተፈጥሮ እውነታዎችን ምክንያታዊ ትንታኔ በመስጠት እውቀት የሚዳብርበትን መንግድ መጠቆም ነበር፡፡ 1. #ምጡቅ_አሳባዊነት (Transcendental idealism) ____ ምጡቅ አሳባዊነት (Transcendental idealism) ካንት ለፍልስፍናው የሰጠው የዶክትሪን ስያሜ ሲሆን የሰው ልጆች በልምድ የሚያገኟቸው እውቀቶች በትክክል ነገሩን (a thing itself) የሚያንጸባርቁ ሳይሆን በምስል ደረጃ ግንዛቤ መፍጠር የቻሉትን ብቻ ነው የሚል ነው፡፡ እንደ ካንተ ሀሳብ ከሆነ ጊዜና ቦታ (Time and space) በትክክል ያሉ ቁሶች ሳይሆኑ አእምሮ ነገሮችን ለመረዳት የሚጠቀምባቸው የግንዛቤ ዉጤቶች ናቸው፡፡ በካንት ሀሳብ መሰረት የአእምሮ ግንዛቤየሚፈጥረው እውቀት የነገሮችን ባህሪያትን የሚመስል የውክልና ምስል እንጂ ትክክለኛ የነገሩን (a thing itself) ትክክለኛ ባህሪያት የሚያመላክት አይደለም፡፡ በዚህ መሰረት ካንት የሰው ልጅ ስለማንኛውም ነገር የሚፈጥረውን  ግንዛቤ ... ሀ ) የነገሩን ባህሪ በራሱ ይዘት በማጥናት የፈጠር  ግንዛቤ ጥናታዊ ግንዛቤ (analytic Judgement)  እና ለ ) በነገሩ ባህሪያት ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን በመጨመር የሚገኝ ግንዛቤ ደግሞ ዉህድ ግንዛቤ (Synthetic Judgement) በሚል በሁለት ይከፍለዋል፡፡ ጥናታዊ ግንዛቤ (analytic Judgement) የሚባለው ነገርየው በራሱ የተዋሀደው መሰረታዊ ባህሪ ሲኖር ነው፡፡ ለምሳሌ "አበበ ረጅም ነው" የሚለው ጥናታዊ ግንዛቤ (analytic Judgement) ግንዛቤ ነው ምክንያቱም "ረጅም" የሚለው ባህሪ "ከአበበ" ጋር  የተጣበቀ ውስጣዊ ባህሪ በመሆኑ "ረጅም" የሚለውን ባህሪ መገንዘብ የሚቻለው የአበበን ቁመት በማየት ስለሚሆን ነው፡፡ በአንፃሩ የውህድ ግንዛቤ (Synthetic Judgement የሚፈጠረው በነገርየው ላይ ተጨማሪ ተቀፅላ ባህሪያትን በመጨመርና ከነገሩ ጋር በማዋሀድ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ "ቢጫ ሸሚዝ"  በሚለው አገላለፅ ውስጥ "ቢጫ" የሚለው ባህሪ ከነገሩ ጋር የውስጥ ዉህደት የለውም፡፡ በዚህ የተነሳ ከልምድ ተቀጥሎ የሚገባ ዉህድ ግንዛቤ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህ የግንዛቤ አይነት ባህሪው በነገሩ ውስጣዊ ይዘት ከሌለውና ተቀጥሎ የሚጨመር ባህሪ ከሆነ በዉህድ ግንዛቤ (Synthetic Judgment) ደረጃ ይወሰዳል፡፡ 2. #ክፍፍሎሽ_ግንዛቤ (Categories of thought) ___ ለካንት  የሰው ልጅ ግንዛቤ የተለያዩ የተቆራረጡና የተበጣጠሱ ልምዶችን አንድ ላይ በማቀናጀትና በመዋሀድ ወጥ ግንዛቤን በመፍጠር የሚገለፅ ነው፡፡ ሂደቱም የሰው ልጅ አእምሮ በስሜት ህዋሳቱ በኩል ከልምድ የሚያገኛቸውን መረጃዎች ከጊዜና ቦታ (Time and space) ጋር በማደራጀት የተደራጀ የግንዛቤ ክፍል ይፈጠራል፡፡ ለካንት ጊዜና ቦታ (Time and space)  ማለት የራሳቸው ባህሪያት ያላቸው እውነታዎች ሳይሆኑ አእምሮ ነገሮችን ለመገንዘብ የሚጠቀምባቸው የግንዛቤ መፍጠሪያ የአሳብ ምስሎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ አእምሮ የሆነ ጠረጴዛን  ለመረዳት በመጀመሪያ ጠረጴዛው የያዘውን ቦታ እና ከጠረጴዛው ውጪ ያለውን ባዶ ቦታ በማስላት በጊዜ ሂደት ውስጥ በማገናዘብ ስለጠረጴዛው መሰረታዊ ባህሪ ይረዳል፡፡ በዚህ መሰረት በልምድ የሚገኙ መረጃዎች ከጊዜና ቦታ (Time and space) አንፃር እየታዩ የተለያዩ ክፍልፋይ አሳቦች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ክፍፍልፋይ አሳቦች በአንድ ላይ ይዋሀዱና ወጥ የሆነ ግንዛቤን ይፈጥራሉ ማለት ነው፡፡ 3. #የሚታይ እና #የማይታዩ_እውነት ( Phenomenal and Noumenal reality) __ እንደ ካንት እምነት የሰው ልጅ አእምሮ የመረዳት አቅሙ የተገደበ ስለሆነ ለመረዳት የማይችላቸው እውነቶች አሉ፡፡ ይሔ ሀሳቡ ደግሞ ካንትን እውነትን የሚታይ እና የማይታይ እውነት ( Phenomenal and Noumenal በሚል በሁለት እንዲከፍል አደረገው፡፡ ካንት የሚታይ እውነት ( Phenomenal በሚል ያስቀመጠው የሰው ልጅ በልምድ የሚያገኛቸውን መረጃዎች ተጠቅሞ የሚፈጥራቸው ግንዛቤዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ እኔ ሾለ ጠረጴዛ የሚኖረኝ ግንዛቤ በዚህ ምድብ ሊመደብ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል የማይታይ እውነት ( Noumenal) የሚባለው እውነት ደግሞ ከአእምሮ ደካማ የመረዳት ችሎታ የተነሳ ከሰዉ ልጅ ግንዛቤ ዉጪ የሆነ እውነት ነው፡፡ ካንት እንደሚለው የሰው ልጅ አእምሮ በትክክል መረዳት ባለመቻሉ የተነሳ ከሰው ልጅ ግንዛቤ ዉጪ የሆኑ  የማይታዩ እውነታዎች ( Noumenal)  አሉ፤ እነዚህም የእግዚአብሔር መኖር፣ ከሞት በኋላ ያለ ህይወት እና ነፃነት፡፡ https://t.me/great_ideas5

ዲጂታል ማርኬቲንግ ዲጂታል ማርኬቲንግ ማለት ምርትና ብራንዶችን ከተጠቃሚዎች ጋር በኢንተርኔት እና መሰል የዲጂታል መግባቢያዎች የሚያስተዋውቅ አንዱ የማርኬቲንግ መንገድ ነው። ይሄም የኢሜል ፣ የ ማህበራዊ ሚዲያ ፣ እና ሌሎችንም የማስታወቂያ አይነቶች ያካትታል። በትምህርት ችሎታችሁን በማዳበር፣ ዲጂታል ማርኬቲንግን የትርፍ ጊዜ ስራ አልያም የሙሉ ሰዓት ስራ አድርጋችሁ ልትይዙት ትችላላችሁ! https://t.me/great_ideas5