en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 559 subscribers, ranking 8 384 in the Technologies & Applications category and 2 165 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 559 subscribers.

According to the latest data from 23 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 0 over the last 30 days and by -2 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.89%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 15.48% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 026 views. Within the first day, a publication typically gains 2 408 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 24 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 559
Subscribers
-224 hours
-37 days
No data30 days
Posts Archive
በጣቢያው ሲከናወን የቆየዉ የመቆጣጠሪያዎች ቅየራ ተጠናቀቀ …….///………. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 2 ሪጂን ሥር በሚገኘው የሠመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሲከናወን የቆየው የመቆጣጠሪያ ወይም ስዊችጊር ቅየራ መጠናቀቁን የመምሪያው ዳይሬክተር አስታውቁ፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ሐሰን ሙሓመድ እንደገለፁት በተቋሙ በራስ አቅም የማከፋፈያ ጣቢያውን የመቆጣጠሪያ ክፍል የማሻሻልና የማዘመን ሥራዎች በመስራት የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝነት ለመጨመር ተችሏል፡፡ በማከፋፈያ ጣቢያው ለረጅም ጊዜ ያገለገለውን በአየር የሚሰራ መቆጣጠሪያ በጋዝ ወደሚሰራ መቆጣጠሪያ መቀየር መቻሉ የጣቢያውን የኦፕሬሽን አቅም በማሳደግ አስተማማኝ እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል። የተቀየሩት መቆጣጠሪያዎች ቀደም ሲል የሚያጋጥመውን የኃይል መቆራረጥን ለማስወገድ እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማዘመን እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡ በ2003 ዓ.ም ተገንብቶ ለአፋር ክልል በዋነኝነት ኃይል እያቀረበ የሚገኘው የሰመራ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ከኮምቦልቻ በ230 ኪሎ ቮልት የተቀበለውን ኃይል ወደ አፍዴራና ዲቾቶ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በማስተላለፍ ከ80 በመቶ በላይ የሆነውን የአፋር ክልል ተደራሽ ያደርጋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ኑሀ/ሞመ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

የማከፋፈያ ጣቢያውን መቆጣጣሪያዎች የማዘመን ሥራ እየተከናወነ ነው …….///…….. በሁርሶ ባለ 230/33/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፊያ ጣቢያ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ መቆጣጠሪያዎችን በዘመናዊ መቆጣጠሪያዎች በመቀየር ጣቢያውን የማዘመን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ  ተወካይ ገለፁ። ተወካዩ  አቶ  ናትናኤል ምንተስኖት እንደገለጹት ማከፋፈያ ጣቢያው ላይ የነበሩ መቆጣጠሪያዎች ለብዙ ዓመት ያገለገሉ ከመሆናቸው ባሻገር ዘመኑን የዋጁ አልነበሩም። ይህም የማስተላለፊያ መስመሮቹ ከጣቢያው እየራቁ ሲሄዱ እና በመስመሮቹ ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ በቀላሉ ቮልቴጅ እንዲዋዥቅ በማድረግ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ያስከትሉ እንደነበር ተወካዩ ገልጸዋል። አሁን የተቀየሩት በጋዝ የሚሰሩት የጂ አይ ኤስ መቆጣጠሪያዎች በጣቢያው እና በመስመሮቹ ላይ ችግሮች ሲከሰቱ ቀድመው በማሳወቅ መቆጣጠሪያው በራሱ ችግሩን እንዲለይና እርምጃ እንዲወስድ በማድረግ በጣቢያው እና በመሳሪያዎቹ ላይ ችግር እንዳይከሰት እንደሚያደርጉ አስረድተዋል። በጣቢያው የሚከናወነው የመቆጣጠሪያ መሳሪዎች ቅየራ ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የኮሙዩኒኬሽን እና ሌሎች መሳሪያዎችን በመግጠም ከስካዳ ስርዓቱ ጋር ለማገናኘት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ጣቢያው 125 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያላቸው ሁለት ትራንስፎርመሮች እና 50 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያለው አንድ ትራንስፎርመር ያለው ሲሆን እስከ 180 ሜጋ ዋት ኃይል የመጫን አቅም አለው። እንደ ተወካዩ ገለጻ ማከፋፈያ ጣቢያው ከቆቃ እና ከአይሻ ሁለት በ230 ኪሎ ቮልት ጥምር መስመር ኃይል ተቀብሎ  ለድሬዳዋ ፣  ሀረር፣  ጅግጅጋ ለአዲጋላ እና ጅቡቲ በአጠቃላይ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል ዋንኛ የኃይል ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

በጣቢያው የሚከናወነው የትራንስፎርመር ቅየራ የኃይል አቅርቦቱን ያሳድጋል ………///……… በወልቂጤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እየተከናወነ የሚገኘው የትራንስፎርመር ቅየራ ሥራ የኤሌክትሪክ አቅርቦቱን እንደሚያሳድገው የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ አቶ ሙጀረብ የኑስ እንደገለፁት 63 እና 7 ነጥብ 3 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸው ሁለት ትራንስፎርመሮች ተጓጉዘው ትናንት ማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ደርሰዋል፡፡ ትራንስፎርመሮቹ የቴክኒክ ችግር የገጠመውን ባለ 40 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለውን ትራንስፎርመር በመተካት በፍጥነት ኤሌክትሪክ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ዝግጁ እየተደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ የትራንስፎርመሩ ኃይል የመሸከም አቅም ከ40 ወደ 70 ነጥብ 3 ሜጋ ቮልት አምፒር ከፍ ማለቱ ከጣቢያው ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ለማቅረብ እንደሚረዳ የገለፁት አቶ ሙጀረብ ይህም አካባቢዎቹ ለኢንቨስመንት ተመራጭ እንዲሆኑ ድርሻው የጎላ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡ በማከፋፈያ ጣቢያው ትራንስፎርመሮቹን ለማስቀመጥ የሚያስችሉ የመሰረት ግንባታ፣ ከትራንስፎርመሮቹ ጋር የሚገናኙ ሽቦዎች ዝርጋታ፣ የብሬከር እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች መጠናቀቃቸውንም ነው የገለፁት፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የትራንስፎርመር ቅየራ ሥራውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኝ እየተሰራ ነው፡፡ ማከፋፈያ ጣቢያው ከግልገል ጊቤ 1 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በባለ 230 ኪሎ ቮልት ኃይል ተቀብሎ ለሰበታ፣ ለሆሳዕናና ለወሊሶ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ለጉራጌ ዞንና አካባቢው ማህበረሰብ ኃይል ያቀርባል። ከዚህ በተጨማሪም ጣቢያው ለሊፍ የተፈጥሮ ውሃና ለዘቢደር ቢራ ፋብሪካዎች  እንዲሁም ለወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

ኃይል ሳይቋረጥ የኮንዳክተር ቅየራ ሥራ እየተከናወነ ነው …..….//…….. በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ጉዳት የደረሰበትን የለገጣፎ- ኮምቦልቻ- አላማጣ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ሁለተኛ ሰርኪዩት መስመር ኃይል ሳይቋረጥ በአዲስ ኮንዳክተር የመቀየር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የራስ ኃይል መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የለገጣፎ- ኮምቦልቻ- አላማጣ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ሁለተኛ ሰርኪዩት ሆት ላይን የኮንዳክተር ዝርጋታ ፕሮጀክት የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ነጋ እንዳስታወቁት ኮንዳክተሩን የመቀየር ሥራው ከ86 ነጥብ 8 በመቶ በላይ ተከናውኗል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው ከ2013 ዓ.ም በፊት ተጠናቆ ለፍተሻና ሙከራ ሥራ ዝግጁ እንደነበር ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ በወቅቱ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት መስመሩ መጎዳቱን ገልፀዋል፡፡ እንደ አቶ ዮሐንስ ገለፃ ፕሮጀክቱ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን መስመሮች በመለየትና በአዲስ ኮንዳክተር በመቀየር ለህብረተሰቡ ያልተቆራረጠ ኃይል ለማቅረብ እየሰራ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ ዮሐንስ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከለገጣፎ- ኮምቦልቻ 61 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ሁለተኛው ምዕራፍ ከኮምቦልቻ- አላማጣ 114 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ተናግረዋል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ የለገጣፎ- ኮምቦልቻ የኃይል ማሰተላለፊያ መስመር የኮንዳክተር ቅየራ ሥራ መጠናቀቁን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ ይህም ከመስመሩ ኃይል ለሚያገኙ አካባቢዎችና ለለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ አስተማማኝ እሌክትሪክ ለማቅረብ ማስቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሁለተኛው ምዕራፍ የኮምቦልቻ- አላማጣ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የኮንዳክተር ቅየራ ሥራ የአንደኛው ሰርኪዩት መስመር ኃይል ሳይቋረጥ እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው የገለፁት፡፡ ይህም በኮምቦልቻና አጎራባች ከተሞች በኤሌክትሪክ መቋረጥ ሳቢያ ሊፈጠር የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማስቀረት የጎላ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል፡፡ የመስመር ዝርጋታውን ኃይል ሳይቋረጥ ማከናወን መቻሉ ለተቋሙ ትልቅ እምርታ መሆኑን ያብራሩት አቶ ዮሐንስ ሥራው በተቋሙ የራስ ኃይል መምሪያ ሠራተኞች አቅም እንዲከናወን መወሰኑ የዕውቀትና ልምድ ሽግግር እንዲኖር በር የከፈተ መሆኑንም ነው የጠቆሙት፡፡ የለገጣፎ- ኮምቦልቻ- አላማጣ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ሁለተኛ ሰርኪዩት ሆት ላይን የኮንዳክተር ዝርጋታ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ ከ86 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተያዘ ሲሆን የፋይናንስ ወጪውም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸፈም ነው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

የኮንዳክተር ቅየራው 83 በመቶ ተጠናቋል .....///..... ከሁርሶ - ድሬዳዋ ቁጥር 3  ማከፋፈያ ጣቢያ የተዘረጋውን ባለ 132 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር የመቀየር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ማስተባበሪያ ቢሮ ቁጥር ሁለት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፀሐይነህ አበበ እንደገለጹት የኮንዳክተር ቅየራው  23 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እና በ84 የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ የሚከናወን ነው።  መስመሩ ከ28 ዓመት በላይ ያገለገለና የኮንዳክተሩ ዓይነትና መጠን አሁን ካሉት የኮንዳክተር ገመዶች ያነሰ በመሆኑ ለኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት እንደነበር ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል። የቅየራ ሥራው በዓይነትና በመጠን ከፍ ያለ አቅም ያለው እና የኃይል ጭነትን መሸከም የሚችል ኮንዳክተር በመተካት በአካባቢው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የኮንዳክተር ቅየራው ሲጠናቀቅ የኃይል መቆራረጥን ከማስቀረቱ በተጨማሪ በሌሎች መስመሮች ላይ እክል ቢያጋጥም በአካባቢው ኃይል እንዳይቋረጥ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ አስረድተዋል። አሁን ላይ ኮንዳክተሩን የመቀየር ሥራው በ70 ታወሮች ላይ የተከናወነ ሲሆን አጠቃላይ አፈጻጸሙም 83 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለጻ በቀሪ 14 ታወሮች ላይ የቅየራ ሥራውን  በአጭር ቀናት በማጠናቀቅ መስመሩን አገልግሎት ለማስጀመር በትጋት እየተሠራ ነው። ሥራው የሚከናወነው በራስ አቅም መሆኑ  የዕውቀት ሽግግር ከማድረጉ በተጨማሪ የፕሮጀክት አስተዳደር አፈጻጸምን በማሻሻል ሥራዎችን በተቀመጠላቸው ጊዜና ጥራት ለማከናወን ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ለወልቂጤ ማከፋፈያ ጣቢያ ተቀያሪ ትራንስፎርመር እየተጓጓዘ ነው ………///……… የቴክኒክ ችግር ለገጠመው የወልቂጤ ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ከአዲስ አበባ ተቀያሪ ትራንስፎርመር እየተጓጓዘ ነው። 230/66/33/15 የሆነው ትራንስፎርመር ዛሬ ማምሻውን ደቡብ ምዕራበ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ደርሷል። በማከፋፈያ ጣቢያው ትራንስፎርመሩን ለማስቀመጥ የሚያስችል የመሰረት ግንባታ፣ ከትራንስፎርመሩ ጋር የሚገናኙ ሽቦዎች ዝርጋታ እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። ትራንስፎርመሩ ችግር የገጠመውን ባለ 230/66/15 በመተካት ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል በፍጥነት እንዲያገኙ  ያስችላል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስፎርመሩ ሲጓጓዝ መንገድ በማስከፈት ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉት የፌደራል ፖሊስ፣ የሸገር ከተማ ፖሊስ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምስጋናውን ያቀርባል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

በአፋር ክልል የወደቁት ሰባት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች የስርቆት ሙከራ ተደርጎባቸዋል ……..///……. በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ከተማ አቅራቢያ ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀን 8፡50 አካባቢ በከባድ ንፋስ የወደቁት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች የስርቆት ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ  2 ሪጅን አስታወቀ። በሪጅኑ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጎሳዬ ደምሴ እንዳስታወቁት ወደ ቦታው የተንቀሳቀሰው የጥገና ቡድን የወደቁት የብረት ምሰሶዎች የመፈታታት ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር በምልከታ አረጋግጠዋል። ምሰሶዎቹ በወደቁበት አካባቢ ብሎኖችን  ለመፍታት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ መፍቻዎች መገኘታቸውን ተናግረዋል። ከአዳማ 2 - አዋሽ ሰባት የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሚሸከሙት የብረት ምሰሶዎች የወደቁት ከባድ ንፋስ ቀላልቅሎ በጣለ ዝናብ ቢሆንም መነሻ ምክንያቱ ግን የስርቆት ሙከራ እንደነበር አቶ ጎሳዬ አስታውቀዋል። የጥገና ባለሙያዎች የወደቁትን የብረት ምሰሶዎች በመፈታታት መልሶ ለማቆም ሥራዎች መጀመራቸውንና በዚህ በየተነሳ የተቋረጠ ኃይል አለመኖሩን ገልፀዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ለሰባት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መውደቅ ምክንያት ሆኗል ……..///……. በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ከተማ አቅራቢያ ትናንት ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀን 8፡50 አካባቢ ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ  2 ሪጅን አስታወቀ። በሪጅኑ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጎሳዬ ደምሴ እንዳስታወቁት ንፋሱ ከአዳማ 2 - አዋሽ ሰባት የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሚሸከሙ ሰባት የብረት ምሰሶዎችን ጥሏል፡፡ አሁን ጉዳት በደረሰባቸው የብረት ምሰሶዎች አቅራቢያ ሁለት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በተፈጸመባቸው ስርቆት ከሳምንታት በፊት መውደቃቸውን አስታውሰዋል። እንደ ሥራ አስኪጁ ገለጻ አሁን ላይ የወደቁት ሰባት ምሰሶዎች ቀደም ሲል  የተሰረቁትን ሁለት ምሰሶዎች ጠግኖ መስመሩን ኃይል ለመስጠት እየተሰራ ባለበት ወቅት መሆኑ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል። የደረሰውን ችግር ስፋት ለመለየት እና የወደቁትን የብረት ምሰሶዎች ለመጠገን እንዲቻል የጥገና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ገልጸዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

የሥራ ክፍሎች ለሚያቀርቡት የሕግ ድጋፍና ምክር ጥያቄ ተገቢው ድጋፍ እየተሰጠ ነዉ ……..///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕግ አገልግሎት መምሪያ በሁሉም የሥራ ዘርፎች ሕግና መመሪያን መሠረት
የሥራ ክፍሎች ለሚያቀርቡት የሕግ ድጋፍና ምክር ጥያቄ ተገቢው ድጋፍ እየተሰጠ ነዉ ……..///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕግ አገልግሎት መምሪያ በሁሉም የሥራ ዘርፎች ሕግና መመሪያን መሠረት ያደረገ የአሠራር ሥርዓት ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኑን የመምሪያው ተወካይ ዳይሬክተር አስታወቁ። ዳይሬክተሯ ወይዘሮ መስከረም በቀለ እንደገለፁት የሥራ ክፍሎች ላቀረቡት 166 የሕግ ድጋፍና ምክር ጥያቄ ተገቢ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ መምሪያው የባለሙያዎችን አቅምን በማሳደግ የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ገጽታውን ለመገንባትና መልካም ስሙን ለማጎልበት እንደሚሰራ ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል፡፡ በተቋሙ ውስጥ ንቃተ ህግ እንዲያድግ በማድረግ የህግ ተገዢነትን ማሳደግ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑንም ወ/ሮ መስከረም ተናግረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

#examResult የፈተና ውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡
+2
#examResult የፈተና ውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ በመንገድ ትራንስፖርት በሚፈቅደው ህግ እና ደንብ መሰረት 74 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ ሲሆን ከተራ ቁጥር 1 እስከ 20 ስማችሁ የተገለጸው ተወዳዳሪዎች ግንቦት 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እና ከተራ ቁጥር 21 እስከ 40 ስማችሁ የተገለጸው ተወዳዳሪዎች ግንቦት 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የየኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የሠራተኞችን ጤናና የሥራ ላይ ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ……..///……… በአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ ላይ የሚሳተፉ ሠራተኞችን ጤናና የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ ተቋራጭ አስታወቀ፡፡ የተቋራጩ ሲመንስ ጋሜሳ ኩባንያ የአካባቢ፣ የሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት አማካሪ አቶ ቻላቸው ሽፈራው እንደተናገሩት በፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሠራተኞች የሥራ ደህንነታቸውና ጤንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከፕሮጀክቱ ባህርይና ከማሽነሪዎች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ሠራተኞች ለአደጋ ተጋላጭ እንደሚሆኑ በመገንዘብ የሥራ ስጋት ምርመራ መከናወኑንም አንስተዋል፡፡ በዚህም የጤናና የአደጋ ሥጋቶችን በመለየት አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል አሰራሮችን በመዘርጋት ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመዋል፡፡ ስለ አሰራር ሥርዓቱ፣ ስለ አደጋ አጋላጭ ሁኔታዎች እና አደጋን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ለሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሠጥ አማካሪው አስረድተዋል፡፡ እንደ ሥራው ባህሪ ለሠራተኞች የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እንደሚቀርቡና በአተገባበሩ ላይም ክትትል እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡ እንደ አቶ ቻላቸው ገለፃ በፕሮጀክቱ ላይ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ማዕከል ከማቋቋም ጀምሮ የጤናና ከፍተኛ አደጋዎች ሲከሰቱ ሠራተኛው የህክምና አገልግሎት የሚያገኝበት አሰራር ተዘርግቷል፡፡ ሠራተኛው የሥራ ላይ ደህንነት ህጎችን ባህል በማድረጉ እስከ አሁን ባለው የግንባታ ሂደት ከቀላል ጉዳቶች ውጭ ምንም አይነት የከፋ ጉዳትና ሞት ሳይከሰት ፕሮጀክቱ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡  💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4