cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ya hala❤️❤️❤️

በዚህ ቻነል ጠቃሚ የሆኑ (አስፈላጊ)የሆኑ ትምህርት ነው የምንሰጠው

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
322
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:33
Video unavailableShow in Telegram
11.06 MB
አይ አሏህዬ [ ደንበር አልባው እዝነት ] ……… በሰይድና ሙሳ ዐ.ሰ ዘመን አንዲት ሴት ትመጣና ለ ሙሳ ዐ.ሰ እንዲህ ትላቸዋለች፦ "አላህ ሳሊህ የሆነ ቀልቤን ሚያስደስት ልጅ እንዲሰጠኝ ዱዓ አድርጉልኝ" እሳቸውም ጥያቄዋን ተቀብለው ባለችው መሰረት ሳሊህ ልጅ እንዲሰጣት ዱዓ አደረጉላት። አላህም እንዲ ሲል መለሰላቸው፦ "መሀን ብዬ ፅፊያታለሁ" እሳቸውም ለሴትየዋ ምላሹን ነገሯት... እሺ ብላ ሄደች። ዳግም ከአንድ አመት በኋላ ተመልሳ መጣችና "አላህ ሳሊህ የሆነ ቀልቤን ሚያስደስት ልጅ እንዲሰጠኝ ዱዓ አድርጉልኝ" አለቻቸው። እሳቸውም ለሁለተኛ ግዜ ጌታቸውን ለመኑላት። አላህም ምላሹ እንደመጀመሪያው ነበር፦ "መሀን ብዬ ፅፊያታለሁ" አላቸው። እሳቸውም አላህ መሀን እድርጎ እንደፃፈላት ነገሯት። ከአመት በኋላ ይህች ሴት ህፃን ልጅ ተሸክማ ሙሳ ተመለከቷትና... "የማን ልጅ ነው?" አሏት። "የኔ ልጅ ነው" አለቻቸው። ያው እንደምታውቁት ሙሳ ከሊሙሏህ በሚል ቅፅል ስማቸው ይታወቃሉ አላህን ቀጥታ ያናግሩት ስለነበር.. እናም የዚች ሴት ልጅ መውለድ ይገርማቸውና "እንዴት መሀን ብለህ ፅፈሀት ልጅ ልትወልድ ቻለች?" ብለው አላህን ሲጠይቁት አላህም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ ላንተ "መሀን ናት" ብዬ በመለስኩልህ ቁጥር እሷም፦ {አንተ ደሞ አዛኝ ነህ} ትለኝ ነበር። እንዲህ ስትለኝ እዝነቴ ውሳኔዬን አሸነፈው እና ልጅ ረዘቅኳት" በማለት አዛኙ ጌታ አል–ራሕማን ምላሽ ይሰጣል። የ አሏህ ራህመት ስፋቱ ከወሰን ያለፈ ነውና! ላ ተቅነጡ ሚን ረህመቲሏህ ኸሚስ ሙባረክ ሶለዋት እናብዛ ቢያንስ 10 ሶለዋት እናውርድ :: T.me/halute77
Show all...
ya hala❤️❤️❤️

በዚህ ቻነል ጠቃሚ የሆኑ (አስፈላጊ)የሆኑ ትምህርት ነው የምንሰጠው

01:39
Video unavailableShow in Telegram
Show all...
6.28 MB
ረሱል (ﷺ) ምርጡ ሞዴል! ከአል‐አስወድ ቢን የዚድ رحمه ﷲ እንዲህ ይላል፦ ﴿ما كانَ النبيُّ ﷺ يَصْنَعُ في بَيْتِهِ؟ قالَتْ: كانَ يَكونُ في مِهْنَةِ أهْلِهِ. فَإِذا حَضَرَتِ الصَّلاةُ خَرَجَ إلى الصَّلاةِ.﴾ “አዒሻን ነቢዩ (ﷺ) ቤት ሲሆኑ ምን ይሰራሉ? ብዬ ጠየኳት። እንዲህ አለችኝ፦ በቤት ውስጥ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውን በስራ ያግዛሉ። የሰላት ወቅት በሚደርስ ሰዓት ለሰላት ይወጣሉ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5363 T.me/halute77
Show all...
Islamic channel

በዚህ ቻነል ጠቃሚ የሆኑ (አስፈላጊ)የሆኑ ትምህርት ነው የምንሰጠው

01:31
Video unavailableShow in Telegram
1.53 MB
💫💫 ለ አሽረል አዋኺር መረሳት የሌለባቸው 3 ነገሮች 💞💞 -ለመስራት ቀላል -ቦታ የማይመርጡ -ጊዜ የማይወስዱ -ትልቅ አጅር የሚያስገኙ 💞💞 💌በየቀኑ ከኢሻዕ ቡሃላ ቢያንስ 1ብር ሰደቃ ላገኘነው ድሀ መስጠት 💮1ዱ ለሊት ለይለቱል ቀድር ላይ ስለምንሰጥ 84 ዓመት ሙሉ ሰደቃ የሰጠን ያህል ይፃፍልናል 💌ሁለት ረከዐ በየለሊቱ መስገድ 💮ለይለቱል ቀድር ላይ 84 ዓመት ሙሉ ለይል እንደቆምን ይፃፍልናል 💌ሱረቱል ኢኽሏስ 3 ጊዜ መቅራት 💮ሱረቱል ኢኽላስ 3 ጊዜ የቀራ ሰው ቁርአን ሙሉ እንደቀራ ይቆጠራል፡ ለይለቱል ቀድር ላይ ስንቀራ 84 ዓመት ቁርዓን እንዳከተምን ይፃፍልናል 💥ሱብሀነላህ!! ይሄን ቪዲዮ ቢያንስ ለ30 በመላክ ተጠቃሚ አንዲሆኑ አድርጉ Share T.me/halute77
Show all...
Islamic channel

በዚህ ቻነል ጠቃሚ የሆኑ (አስፈላጊ)የሆኑ ትምህርት ነው የምንሰጠው

ዱዓ የሚያደርግ አካል ማሟላት ያለበት እና መከልከል ያለበት ነገራቶች አሉ ‼️ አንድ አማኝ በዱዓ ጊዜ ማሟላት ያለበት ነገር 1⚡️ኢኽላስ ለአላህ ጥርት ያደረገ ሆኖ ዱዓ ሊያደርግ 2 ⚡️ከአላህ ጋር እውነተኛ መሆን 3⚡️ለአላህ እና ለመልዕክተኛው ትዕዛዝ እጅ መስጠት እና በእነሱም ማመን በአላህ ላይ መልካም ግምት እና ጥርጣሬ ሊኖረው ዱዓዬን ይቀበለኛል ብሎ ሊያስብ 4⚡️ በቁርዓን እና ሀዲስ በተረጋገጡ ዱዓዎች አላህን መለመን 5⚡️በዱዓ ወቅት እጅን ከፍ ማድረግ 6⚡️አላህን በማሞገስ እና በነብያችን ላይ ሰለዋት በማድረግ ዱዓን መጀመር 7⚡️በጭንቅ ጊዜ አላህ እንዲደርስልን በምቾት ጊዜ ዱዓን ማብዛት 8⚡️ አላህን አብዝተው ከሚያወሱ ከሚዘክሩ መሆን 9⚡️ከግዴታ በኋላ ሱና በሆኑ ነገራቶች ወደ አላህ መቃረብ 10 ⚡️አላህን በመልከ መልካም ስሞቹ እና በታላላቅ ባህሪዎቹ መለመን T.me/halute77
Show all...
Islamic channel

በዚህ ቻነል ጠቃሚ የሆኑ (አስፈላጊ)የሆኑ ትምህርት ነው የምንሰጠው

በረመዷን መዘንጋት የሌለባቸው ወሣኝ ነገሮች ፡ - # ሰሑር ፡ ሰሑር ማለት ከንጋት በፊት የሚበላ ፆም መያዣ ነው፡፡ ሱሑርን መመገቡም ሆነ ወደ ንጋት ማዘግየቱ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ነቢያችን  ‘ ሱሑርን ተመገቡ በሱሑር ዉስጥ በረካ አለና’ ብለዋል ።   # ለማፍጠር መቻኮል - አላህ ሱ.ወ. ያገራልንን ነገሮች ስንጠቀምበት ይወዳል፡፡ ፀሀይ መጥለቋ እንደተረጋገጠ ወዲያውኑ ማፍጠር ተወዳጅ ድርጊት ነው፡፡ ‘ፍጡርን እስካፈጠኑ ድረስ ሰዎች ላይ መልካም ነገር ላይ ናቸው፡፡’ ብለዋል ረሱላችን ሰ.ዐ.ወ.። # ተመራጩ ማፍጠሪያ - በትኩስ /እሸት/ ተምር ማፍጠር፤  ካልተገኘ በደረቅ ተምር፤ ካልተገኘም በዉሃ ካልሆነም በተገኘው ነገር ማፍጠር ሱና ነው ። # ዱዓእ - የረመዷን ዉስጥ ዱዓእ የሚፈለግ ነው፡፡ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ. ‘ አላህ የሦስት ሰዎችን ዱዓዕ ምላሽ ላይነፍግ ሐቅ ነው በማለት፡ - ፆመኛ እስኪያፈጥር፣ ተበዳይ ድልን እስኪያገኝ ፣ መንገደኛ ወደ ሀገሩ እስኪመለስ ” ብለዋል ።   # ሲዋክ -   በዉዱእ ጊዜ፣ ለሰላት ሲቆሙ፣ ቁርኣን ለመቅራት ሲዘጋጁ፣ ከእንቅልፍ ሲነሱ .. ሲዋክ መጠቀም በእጅጉ ተፈላጊ ነው፡፡ ሲዋክ ለመልካም የአፍ ጠረን ሲዋክ ጉልህ አስተዋፅኦ አለውና፡፡ ከሀሉም በላይ ደግሞ ተወዳጅ ነቢያዊ ፈለግ ነው።  ‘በህዝቦቼ ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ዉዱእ ላይ በሲዋክ ባዘዝኳቸው ነበር ።’ ብለዋልም፡፡ # ምጽዋትና ሌሎች ሰናይ ተግባራት  - ‘በላጩ ምጽዋት የረመዷን ዉስጥ ምጽዋት ነው፡፡’ ብለዋል ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ.፡፡ ነቢዩ በልግስናቸው የሚታወቁ ሲሆን በረመዷን ዉስጥ ደግሞ የበለጠ ለጋስ ይሆናሉ፡፡ # ከአስፀያፊ ንግሮችና ቃላት መራቅ   - ‘ አንዳችሁ የፆም ቀናችሁ ሲሆን መጥፎ ንግግርን አይናገር፣ አይጩህ፣ የሆነ ሰው የሰደበው አሊያም የተጣላው እንደሆን ፆመኛ ነኝ ይበል’ ብለዋል ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ.፡፡ # ተራዊሕ -  ረመዷን ለአላህ ቂያም /በሰላት መቆምን ማብዛት/ የሚበረታታበት ወር ነው፡፡ ለተራዊሕ መስጊድ የመጣም ኢማሙ እስከሚጨርስ አብሮት ቢቆም የተሻለ ነው። # ኢዕቲካፍ -    በተለይም በመጨረሻዎቹ አሥር የረመዷን ቀናትመስጂድ ዉስጥ መቆየትን (ኢዕቲካፍ) ነይቶ መስጅድ መግባት ተወዳጅ የአምልኮ ተግባር ነው፡፡ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ. የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥር ቀናት  በዒባዳ ይበረቱ፣ ቤተሰቦቻቸዉን ያነቁ፣ ለሊቱንም በዒባዳ ያሣልፉ ነበር።  ❁👀 → በረመዷን መዘንጋት የሌለባቸው ወሣኝ ነጥቦች T.me/halute77
Show all...
Islamic channel

በዚህ ቻነል ጠቃሚ የሆኑ (አስፈላጊ)የሆኑ ትምህርት ነው የምንሰጠው

❓❓ሶላት ከሰገዱ ቡኋላ መስገጃዎ ላይ መቆየት ምን ያህል አጅር እንደሚያስገኝ ያውቃሉ? ✿┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿ 👉👉 የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ከእናንተ መካከል አንዳቹ ሶላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለ እና ውዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዱለታል። "አላህ ሆይ! ወንጀሉን ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት።" ይላሉ።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል) 👉 ኢብኑ በጣል(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እጅግ ብዙ ወንጀል ያለበት ያለ ብዙ ልፋት ወንጀሉን አላህ እንዲያራግፍለት የሚፈልግ ሰው ካለ፦ መላኢካዎች እርሱ ላይ የሚያደርጉት ዱዓ እና ኢስቲግፋር ይበዛለት ዘንድ ሶላት ከሰገደ ቡኋላ መስገጃው ላይ በመፅናት እድሉን ይጠቀሙ። T.me/halute77
Show all...
Show all...
4_5922482326037597447.mp42.73 MB