cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የብዕር ቃል ✋(በሱራፈል ደጀኔ)

ከእኔ ለእናንተ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
262
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

t.me/erkanewnetsurafi አዲሷን ቤቴን ተቀላቀሉልኝ🙏
Show all...
እርቃን እውነት

ያለፈው ትውልድ አካል እና እውነትን ፍለጋ የምንከራተት እኔ ነኝ። ሱራፌል ደጀኔ

እኛ በምንድነው የታነፅነው?! (ሱራፌል ደጀኔ-እንደፃፈው) ?ብረት ጠንካራ ነው።ላላወቀበት ደግሞ ዝገታም ሲዝግ ራሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ማበላሸት የሚቻለው። ልብስ አጥበህ የዛገ ብረት ላይ አስጣው እንደዝገቱ አይነት ስሜት ልብስህ ላይ ያጋባብህና ወይ እንድትጥለው አሊያም እየቀፈፈህም ቢሆን እንድትለብሰው ያስገድድሃል። ማንነትህ የታነፀበት ነገር ጥንካሬ የሚመጣውን ሁሉ ያሳምርልሃል ማለት አይደለም ልልህ ነው።ሁሉም ተገለባባጭ ነው። ብረትም ዛጊ ፣ትልቁ ሰማይ ምድር እንኳን ቢሆኑ ጠፊ ናቸው።ያኔ አንተም ነህ ተከትለሃቸው የምትጠፋው። ታዲያ ኖሪ ማንነትህን ነው የምልህ። አሊያማ ነፍሴ ዘላለማዊ ነች።የምኖረው ለዛኛው ትልቀቴ እኔጂ ለምዳሪዊው አይደለም ትለኛለሃ።ነገሩ የምድሩንም በማይናወጥ ቃል ካላነፅከው ሰማያዊውስ መች ተገኝቶ።(በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ) ገነባሁት የምትለው ማንነት ላይ ጥርጣሬ እና አለማወቅህን የሚያስታውስ ነገር አክልበት።በገነት በለስ እፅ ለምን የኖረ መሰለህ?አዳም ከሱ በላይ የሚያዘውም እንዳለ ጭምር እንዲረዳ ነው።ምን ትዝ ብሎኝ እንዳነሳሁብህ ልንገርህ! ብዙ አጋፋሪ ያላቸው አዋቂዎቻችን የአዳምን እድል ቢሰጡ አምላክ ነኝ ከማለት ወደኋላ አይሉም።ለራሳቸው አንዳች ጥርጣሬ እና ከነሱ የተሻለ ነገር ያለው የሌለ ስለሚመስላቸው ሌሎችን ለመስማትም እድል አይሰጡም።እነሱው ተሳድበው፤ እነሱው መርቀው ፤አሸብሽበው ዘፍነው ፤ለግሰው አስገድለውም ፤የሰማዩን ደጅ ቀድሞ እንደሚከፍቱ ነው የሚያውቁት።እግዜሩ ግን ለምን ለእነሱ በለስ እፅ አላዘጋጀላቸውም? እንጃ! እንዲህ ነን እኛነታችን የታነፀበት ነገር በውል ሳናውቀው ሰማይ እና ምድር ያለ መገናኘት በተዓምሩ እንደቆሙት አይነት ባህሪ የተለበጠብን ይመስለናል። ቀን ሸሽቶ ግን እውነትን ሲያረዱን የረጋገጥናቸው እውነቶች ሁሉ ዳግም እየረገጡን የማይታረሙ የሚመስሉ ኩነኔዎች መከማቸታቸው ሲታወሰን ለራሳችን ሌላ ጥያቄ እንጭራለን? እኔ ግን በምንድነው የታነፅኩት?ብረት እንኳን ቢሆን ዛጊ አይደለምን?!ታዲያ ያ ሁሉ ትምክህቴ ከየት መጣ?ዛሬስ ምን አኮስምኖት ፍርክስክሱ ወጣብኝ?የማያልቅ ዝቅታችን ይታየናል። የማያልቅ ከፍታን በሌሎች ውስጥ እናስተውላለን። እኛስ ግን ከምንድነው የታነፀው? እንጃ! (ጅጅጋ ኢትዮጵያ)
Show all...
የካሳ ተራቤ ልጅ (ሱራፌል ደጀኔ -እንደፃፈው) ካልሲ በርካሽ በአስር ብር ብቻ ቲሸርት፣ሹራብ በርካሽ በርካሽ እያለ ይለፍፋል።ሰልባጅ (ልባሽ) ይበዛዋል። ድሮ እኔን ጨምሮ ሰልባጅ ከምለብስ ስናፍጭ በአፍንጫዬ ይውጣ ባይ ነበርኩ። አሁን ሳይ የባለስልጣናቱ ግፊያ ይበልጣል። እነሱ ደሞዝ ላይ ሙስና ጨምረው ያልተሳካላቸውን ልብስ እኔ ከፑቲክ ለመግዛት የምጣጣረው ሳስበው አሳቀኝ። ሞኝ ነበርኩ ለካ! ልኬን የማላውቅ ፤ከአቅሜ በላይ እንቡር እንቡር የምል። ወይኔ ለካ ቆሜ ነው የማስበው ልግዛ? አልግዛ? ግፊያው ራሱ ግዛው ግዛው ያሰኛል። በርሬ ካልገባሁበት አልኩ። ከፊት ያሉትን ሁሉ ሳንገዳግዳቸው ይታወቀኛል። ያን ለየት ያለ ጠረን ያለውን ልብስ አንዴ ሹራቡን አንዴ ሱሪውን ብድግ ቁጭ እያደረኩ ነው። ''ሁልሽም የተሰጠሽን ብዪ ማርን ማር ያደገው ምላስሽ ነው እኔ ቀምሼው ሁሉም ማር ነው'' ይላል ከበስተጀርባ አሁንም መረጣዬ ላይ ነኝ። እቡዱ ቀጠለ ''ከንቲባችን መሃላችሁ ለሰልባጅ እየተጋፋ ስለሆነ አትገረሙ እናንተም የራሳችሁ ከንቲባ ናችሁና ሰውነትን በስልጣን በቦታ አትሸምኑ ሁላችንም አፈር ናችሁና።"ሁሉንም ከንቲባውን ይፈለግ ይመስል አካባቢውን መቃኘት ጀመረ ሰውየው እንደቀጠለ ነው። ገብያው ደርቷል ልብስ ከምግብ በልጦ ሳይበላ የሚሽቀረቀረው በዝቷል።''ሁላችሁም እለተኞች ናችሁ ሆዳሞች ፣ሴሰኞች ፣ሙሰኞች እርባና ቢሶች ናችሁ እድሜያችሁ ከእባብ ገላ የተሰራ ነው የሚመስላችሁ የምትሞቱ አይመስላችሁም።" ይሄ ምን ይላል? ድምፄን ጮክ አድርጌ ነበር መሰለኝ ቀድሞ ገበያውን የተወው ከእርሱ ፊቱን ወደኔ መለሰ።አፈርኩኝ ለካ እኔ የካሳ ተራቤ ልጅ ሰልባጅ ተራ ነኝ። አሁን ሞት ባይሳሳ ምን አለበት እዚሁ ቢደፋኝ።ጭራሽ ሰውዬው ወደኔ መጣ ''ምን አልል?እባክህ?ሁሉም አብዶ እኔን እብድ ይላሉ ያበዳችሁትስ እናንተ ጓተራችሁን አራቁታችሁ ለልብስ የምትሻኮቱት፤ ለቁርጥራጭ ልብስ ለዛውም እናንተ ከገለጣችሁት ገላ የኔ ችግር የገለጠው ገላ አይሻልም? ከንቲባው ስላችሁ ፈልጋችሁ አጣችሁት አይደል እኔ እኮ ነኝ ከንቲባው የእብድ አለቃ ሰልባጅ ተራ እጋፋለሁ። ምን ታመጡ? ሺህ ምንተሺ ነው ሚከፈለኝ።ምን ታመጡ?" እፍረቴን የገፈፈልኝ መሰለኝ ግን ለምንድነው ሰልባጅ ተራ ነኝ ብዬ የተሰማኝ? ከንቲባችንስ አለ አይደል? ወይኔ ይሄንን እብድ አመንኩት! ሰው አሁንም ፊቱን አዞረ!ይሄም ያው ነው መጠቋቆሙን ያዙት።" እመነኝ "እያለ ቀጠለ "ተከተል ህይወትም መንገድም እኔ በምሄደው ጋር ነው ያለፋት እመነኝ።" ጮክ ብዬ ይሄ ደሞ ከሰሙት ክርስቶስ ነኝ ይላል። ብዬ ሰውን እየተጋፈሁ ወጣሁ ፊቴን ወደ ቤተ በሚወስደው መንገድ ሳዞር በስሜ ይጠራኝ ጀመረ "እንዳሻው ካሳ ተራቤ "... @surataaa
Show all...
#የሃሞተኞቹ_ቁስል (ሱራፌል ደጀኔ - እንደፃፈው) የህይወትን ትርጉም መረቅ የሚጠጡት በመረቅ አንጀታቸው ሃሞት የሚጠጡት በሃሞታም አንጀታቸው ይረዱታል።መረቀኞች የሃሞተኞችን አንጀት ይበልጥ ማምረርን ያውቁበታል ሃሞተኞች ደግሞ እናንተ ምን አለባችሁ አልታረዛችሁ አልተቀጣችሁ እያሉ ያዜማሉ። ታዲያ ዜማው ድምፅ መፈተኛ አይደለም ከምሬት የመነጨ እንጂ። እንዲህ ነው ነገሩ ህዝቡ ትንታኔ ጠግቧል አነሰም በዛም ስለፍቅር ለማወቅ ጦርነትን አይቷል ስለ እውነት ለመረዳት ከሃዲዎችን ሰምቷል ስለ ሞት ለመረዳት የአለመኖርን ኑሮ ዛሬ ያየውን ነገ በማጣት ተረድቷል። ምን ጎደለው ታዲያ?ውርግጥና ተጫጫነውሳ?ቅዠቱን ከህልሙ መለየት ተሳነው?!ተራሮች እየተፈለፈሉ ኪን በሚሆኑበት ዘመን ደልዳላው መንገድ አሸዋ ለበሰ ብሎ መቦረቅ?! ቆይ ግን እኔ የምለው መንገዱ ነው መንገድ ጠራጊው ነው የጠፋብን? ቆይ እንደውም የልጅ ስም ነው የአባት ስም መጀመሪያ መጠራት ያለበት?! እሱጋ መስሎኝ የተሳሳትነው ያስጀመሩን መንገድ ትተን የጀመርነው መንገድ ''የአባቶቼን እርስ አለቅም '' የሚል አምልኮተ ህግ እኮ ሳያፈርሰው አይቀርም።ታዲያ የአባቶቻቸውን አቋቋም ያላወቁ ልጆች ስማቸው ከስሙ የቀደመባቸው ልጆች እንዴት ብለው ነው ከራሳቸው በላይ ሊያከብሩት የሚነሱት? ለሙት ከደግደነቱ ህፀፁን ከኗሪ ከንፉግነቱ ደግነቱን እያወጣን እንዴት ነው ለይምሰል እየተቀባባን እስከ መቃብር የምንወርደው?!ከዛ በኋላ እኮ ህፀፁን ብናወጣ ባናወጣ መንገዱ የእኛ አይደለም አንድም የእግዜሩ አንድም የነዲዱ ነው። ወደዛው ወደ ሃሞተኞቹና እና ወደ መረቀኞችህ ተመለስ እስኪ! ልክ እንደዛ ኗሪ እያለባበሱ ሟችን ደግመው የሚቀብሩ እንከፎች መረቀኞቹ መስለውኝ።ለእለት ጥጋባቸው ሲሉ ደሃ ትከሻ ላይ በፈረስ ጉልበታቸው ካልወጣን የሚሉት የራሳቸውን ምኞት በአፈ ቀላጤ መቀነት ቋጦረው ከፍታን ሊወጡ ሲሹ እንደ ማየት ሃሞተኞችን የሚያቆስል ምን ነገር ሊገኝ? ምንም! ብቻ ተው የሃሞተኞቹ ቁስል አይመርቅዝ የፈረጠ እለት መፈናጠሩ አይቀርም እና ለእናንተም የማይድን ህመም ከመሆኑ በፊት ህመማቸውን ከመረቁ ጋር ጣል እያደረጋችሁ ቅመሱላቸው ህሮብ አርቡን ሁዳዴ ፍስለታውንም ቢሆን አብራችሁ ሃሞታቸውን ተጎንጩላቸው አንድም ከስጋ እንጥልጥል ሌላም ከነፍስ እውረት ትድናላችሁና። 9/6/2012 ዓ.ም
Show all...
#ቢሆንም_ባይሆንም_ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም። እናንተ እንዴት አይነት ሰው ናችሁ ቢሏችሁ መቼም ራሳችሁን እንደ አንዱ ፃድቅ ማሰባችሁ የማይቀር ነው።በፃድቅ ሰው ማዕድ ብትገኙ ተርፎት እንዴት እርሱ እንደሚበላ ሳይሆን እናንተን እንዴት ማጥገብ እንዳለበት ነው የሚያሰላስለው። እኛስ በሉኛ እናንተማ እንዴት ለራሳችሁ አስተርፋችሁ እንደምትሰጡ ነው ቀድማችሁ የምታስቡት ለፍቅሩም፣ለጦርነቱም እንደዛው ከአንዱ ጓደኛችሁ ጀርባ ተከልላችሁ የራሳችሁን ህይወት ስለማትረፍ እንጂ የራሳችሁን ሰጥታችሁ ጓደኛችሁን ስለማይኖር አታልሙም።እኔ ግን እላለሁ ሳታማኻኝ ብላ አይሰራም ማመኻኘትማ አለብህ የፃድቁን መሶብ ብትችሉ ፀልያችሁ ሙላለትን እወቁበት ያኔ ያለ ሰቀቀን ከመሰቡ እየመረጣችሁ እንድትበሉ ይሁን እንጂ የሌለውን ጨርሳችሁ አትጨርሱበት። ወይንም የሞሰባችሁን እንደ እናንተ ሳይሆን እንደ ፃድቁ ሰው ያለስስት ስጡ። ፎቶ-በእኔ 2/5/2012 ዓ.ም Surafel Dejene
Show all...
#ሀበሻ_ዛሬም_ምስጢሩ_መፅሐፍ_ውስጥ_ተቀብሯል።(እንደማታነቡት እያወኩም እፅፋለሁ)🙏 ምን ታስባለህ? #ልበ ደንዳና ሁን ኩሩዎች የለበሱትን ካባ ለመጎናፀፍ በሰበረህ ሁሉ አትሰበር በበተነህ ሁሉ አትበተን። አለሜ ደካሞችም በላቸው ጠንካሮች ሁሌ ማንም የሚወደው ልፍስፍሱን ሳይሆን የጠነከረውን ነው። ለዚህ ደሞ ልበ ደንዳና መሆን አለብህ በተራ ነገር የማይሸበር ኣንበሳ። በሰማው ሁሉ ድምፅ የማይበረግግ ሰው ሁን። ስትደነድም ቢሆን ከሰውነት ተራ አትውረድ ሲያሳዝን እዘን ግን ሀዘኑ ለታዘነለት የሚጠቅመው ስለሌለ የሚጠቅመውን ጥንካሬ ለመስጠት ሞክር። ይሄ ልበ-ደንዳና ነው አረመኔ ነው ይሉሃል።ግን ህይወት ውጣም ውረድም ደጋግማ ቀምራ የምታስተምርህ ሁሉም ጠንካራውን እንደሚፈልግ እና መውደቅ መነሳት ውስጥ የሚያበረታ ጉልህ ደንዳናነት እንደሚያስፈልግህ ነው። #ጠንክር_ደንድን_ሰውነትህንም_አትርሳ። ሱራፌል ደጀኔ የገና እለት
Show all...
ኖላዊነ አምላክ ከሰው ልጅ ከድንግል፣ የእርሱ በሆነ ቃል፣ የአዳምን ጥንተ ሀጢያት፣ ለመሻር በእውነት ፣ የበረቱን ፅልመት በብርሃን ናደ፣ እራሱን በእሷ ውስጥ በምስጢር ወለደ። እሰይ ኖላዊነ፣ እሰይ መድኃኒነ። ሱራፌል ደጀኔ 24/04/2012 ዓ.ም (ኖላዊነ-የሚጠብቀን/ጠባቂያችን) #መልካም ገና @surataaa @surataaa
Show all...
**** አለማየሁ ገላጋይ ከ "ወሪሳ" መፀሀፍ የተወሰደ*** አንዳንድ ጠላቶቼ ሌባ ነው ይሉኛል። ከኋላዬ ምን እንደሚወራ አውቃለሁ። አሁን እኔ "አትስረቅ" የሚለውን ትዕዛዙን አጥቼው ነው የምሰርቀው? በፍጹም! የሰው ሃቅ ወደኔ አልፎብኝ አያውቅም። ለምን ብዬ? እርግጥ የወደቀ ካገኘሁ የማነው? አልል ይሆናል። ይሄ ግን ሌባ አያሰኘኝም። አንዳንድ ዝንጉዎች ልብሳቸውን ሽቦ ላይ አስጥተው ቤታቸው ይቀመጣሉ። ይሄኔ ልብሱን ከሽቦው ላይ አላነሳም። ይሄማ ሌብነት ነው። ጎትቼ እጥለዋለሁ። እና እግዚአብሔር ችግሬን አይቶ፣ ጸሎቴን ሰምቶ በቸርነት እጁን እንደዘረጋልኝ ቆጥሬ ከመሬት አነሳዋለሁ። 'የወደቀ አንሱ የሞተ ቅበሩ' አይደል እስተነተረቱስ? እና ሰው እንዴት የፈጣሪውን ትዕዛዝ ይጥሳል? ሰው መሆኑ እምኑ ላይ ነው?"🙃 ከስንታየሁ አዲሱ (ሳንታ) ገፅ የተወሰደ
Show all...
#ማረኝ ማ ረ ኝ ከእንቅፋት ማሳ ታጭዶ ጎተራ ላይሞላ ቃሌ ለአንተነትህ ሳልታመን በራሴ ህልም መሰለሌ ነው በደሌ አውቃለሁኝ ነው ቀትርህን ንቂያለሁኝ ደግሞም ከሀቅህ የጎደፍኩት ከምህላህ የቀጠፍኩት ፍሬ አልባ ምፅድቅና ገደብ የለሽ ስይጥይና የቀለብ ጎርፍ ወረዳዬ ላይበላ እየፆመ ላያደርስ እየዘራ፤ላያበቅል እያረመ ከንስሃው መስተማሩን ከአምላክ ቃል መፈጠሩን ቢዘነጋ ጊዜ ዘመመ ከአለት ቋጥኝ ተላተመ ያኔ ነው ከሀቅህ የጎደልኩት በሃጢአቴ ፍራቻ ከክህነት ቤትህ የራኩት ግን አላውቅም መራቄን እንድወደው ምን አዚም አገናኝቶኝ ከክታቤ እንዳዋለው ምን ሸር ተሸርቦ ቀኖናዬ እንደጎደፈ የት እንቅልፍ አዳፍቶኝ ህልም-እውኔ እንዳለፈ አላውቅም ሀቂቃዬ ምስክሬን እልሃለሁ ማ ረ ኝ ብቻ ዘላለሜ በአንተነትህ እሽራለሁ ፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤ እ ግ ዚ ኦ መ ሀ ረ ነ ክ ር ስ ቶ ስ እ ግ ዚ ኦ መ ሀ ረ ነ ክ ር ስ ቶ ስ እ ግ ዚ ኦ መ ሀ ረ ነ ክ ር ስ ቶ ስ .................................................... በ እ ን ተ ማ ር ያ ም መ ሀ ረ ነ ክ ር ስ ቶ ስ በ እ ን ተ ማ ር ያ ም መ ሀ ረ ነ ክ ር ስ ቶ ስ በ እ ን ተ ማ ር ያ ም መ ሀ ረ ነ ክ ር ስ ቶ ስ ፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤ ስማነ ስማነ ብዙ አትቁጠርብነ ሀጥኡ በህሊናው ሊሽረው በደሉን ከስሜት ተጣልቶ ቢግተው መራሩን መዋጥ ወቸ-ጉዱ አለመደም ሆዱ እናማ ማረኛ እኔን ዘይረኛ እንዳመኑህ ሁሉ ተወለደልኛ እንዳንካቸውም ተሰቀልልኛ እንደውም እንደውም የሆንከውን ሁሉ የረገጥክበትን ፤ትርታህን ሁሉ ነግረውኝ ካላወኩ ምኑን ባንተ አመንኩ?! እንደውም እንደውም ያልኩህ ምፅድቅና ያልኩህ ስይጥንና እንዲቀየርልኝ ፤ እንዲገፈፍልኝ ከእኔነቴ ሽረህ አንተነትን ቀባኝ ከትቢያነት ነስተህ ሳትሰስት ማረኝ! ሱራፌል ደጀኔ 27/03/2012 ወልድያ ዩኒቨርስቲ
Show all...
እማኮ የትብት ኪዳን የእምነት ውርሴ የአድባር መንበር የቃል ምሴ ካበቀለሽ አባ ገዳ ከጫኝ ዳሪሽ አባ ፈርዳ መሰጠትሽን ቀልመሺኝ ንፁህ ፍቅርን አቁርበሽኝ በእንትፍትፍሽ ፋፍቼ በአደይ መልክሽ ፈክቼ ልለቅም ብሄድ ከማሳው የሰቀቀን ቃርሚያውን ነፍስኝ በእልፍኜ ተገኝታ ታደገችን ከመቁነን ኖረችልኝ ነፍሷን ትታ ሜዳ ገደል ተንከራታ እማኮ የትብት ኪዳን የእምነት ውርሴ የአድባር መንበር የቃል ምሴ ከቸርነት የእምነት ጥግሽ ከአዳር እንቅልፍ እስትንፋስሽ ቢዳኘኝ ፤ቢቃኘኝ ጠረንሽ ላልዋሽ እውነት፤ ቃል ላልከዳ በማበይ ልክ ፤ ከከንጂ ጋር ላልከነዳ ስንቅ ሰንቄ ጦር ሰብቄ ከድብ ከድጥ ተደብቄ አሸታለሁ ጠረንሽን የነባቢት መቅለምሽን ምንም ሳልሆን የሚያባንን የቀን ቅኝት ቅዠትሽን እማኮ የእትብት ኪዳን የእምነት ውርሴ የአድባር መንበር የቃል ምሴ በጭነትሽ ተሰፍሬ ስንከላወስ በጀርባሽ ውል ፊትሽ ቀንሽ ፤አካል ክብርሽ ቢመስል ከል ውጊያ ቦታ ያደሰረች ብርቱ ፈረስ ሲዋጉ እያየች ከመለመን ወይ ከማልቀስ የፈረስ ግብር አይዘነጋም ለሞት ደግማ አትዋጋም። ሱራፌል ደጀኔ ወልድያ_ዩኒቨርስቲ 27/3/2012ዓ.ም @surataaa @surataaa
Show all...