cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:- https://www.youtube.com Email:- [email protected]

Show more
Advertising posts
222
Subscribers
No data24 hours
-27 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በሮሜ 1:16 ላይ "መዳን" ወይም "ደኅንነት" የሚለው ቃል፣ ከሲዖል ተርፎ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ብቻ አይደለም። "ደኅንነት" የሚለው ቃል የግሪኩን "ሶተሪያ" የሚለውን ቃል የሚያመለክት ሲሆን፣ ትርጉሙም:- ✔️መዳን፣ ✔️መጠበቅ፣ ✔️ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆን፣... ማለት ነው። ይህም እኛ በምሉዕነቱ መደሰት እንድንችልና በሥጋ፣ በነፍስ እና በመንፈስ ደኅንነታችን የተጠበቀ እንዲሆን መዳን በሚያስፈልገው የትኛውንም የሕይወታችንን ክፍል የሚሸፍን ነው። https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

ጌታ ኢየሱስ፣ በቅዱሱ እግዚአብሔርና በኃጢአተኛው መካከል ያለውን #ማናቸውንም_ርቀትና_ክፍተት በመሥዋዕቱ ቤዛነት ሞልቶታል። ➜በክርስቶስ ሥራ፣ እግዚአብሔር #በፍጹም_ጸጋው ወደ ኃጢአተኛው ዘንድ መጣ። ➜በክርስቶስ ሥራ፣ ኃጢአተኛው #በፍጹም_ጽድቅ ወደ እግዚአብሔር ቀረበ። https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

►የሰው በደል ምንም ያህል ቢጠቁርም፣ #የኢየሱስ ክርስቶስ #ደም አጥቦ ያስወግደዋል። ►እግዚአብሔርንና ሰውን የሚለየው ገደል በጣም ቢሰፋም፣ #የመስቀሉ_ሥራ ድልድይ ሆኖ ያገናኘዋል! ►የበደል ብዛት፣ ያንን በደል የሚያስወግደውን #የደሙን_ብቃት ይናገራል። ►እጅግ የከፋ ኃጢአተኛ ነኝ የሚል በደለኛ ሰው ቢኖር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ በማመኑ ብቻ፣ ሁለንተናው ንጹሕ ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚታይ አውቆ ደስ ሊሰኝ ይገባዋል !!! https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

"እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? #በላይ_የሚኖር፤ በሰማይና #በምድር የተዋረዱትን #የሚያይ፤" (መዝ 113:5-6) ➡እርሱ ሰማየ ሰማያትን ያስተዳድራል፤ ነገር ግን ስለ አንድ ትንሽ ፍጡር #መግቦት ግድ ሲለውና ሲተጋ ይታያል። ➡እርሱ የሰማያውያን መላእክትን የበረራ ሥምሪት ይመራል፤ ነገር ግን በምድር ላይ በልቧ የምትሳብንም #አንድ_ትል ልብ ብሎ ይመለከታል። ➡እርሱ ዳርቻ በሌለው ጠፈር ውስጥ ያሉ ግዙፍ ፍጥረታትን ዑደታቸውን፣ ምኅዋራቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ያስተዳድራል፤ ነገር ግን #የአንዲት_ድንቢጥ ውድቀትንም ያስተውላል። https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

ዓለቱ እና ውኃው ! ዓለቱ ተመትቷል፣ ውኃውም ፈልቋል፣ ሕዝቡም ጠጥቶታል። #ክፍል_4 “ዓለቱን በምድረ በዳ ሰነጠቀ፤ ከጥልቅ እንደሚገኝ ያህል በብዙ አጠጣቸው።” (መዝ 78፥15) ~ #መናው የክርስቶስ ምሳሌ እንደሆነ ሁሉ፣ ከተመታው ዓለት #የፈሰሰው_ውኃ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው። ጌታም ለሳምራዊቷ ሴት:- “... #የእግዚአብሔርን_ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ #የሕይወትም_ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።” (ዮሐ 4፥10) ~በዚህ ክፍል፣ "የእግዚአብሔር ስጦታ" የተባለው ክርስቶስ ሲሆን "የሕይወት ውኃ" የተባለው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን እናስተውላለን። ~ከተመታው ዓለት ለመንፈሳዊው አእምሮ ሊተላለፍ የተፈለገው ትምህርት ይህ ነው። ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን !!! ተ ፈ ጸ መ !!! https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

Show all...
እንኳን እኔ አንተም Hanna Belachew Amharic Gospel Song

እንኳን እኔ አንተን አንተም እኔን ወደሀል/2* ከነሐጥያቴ ከነእድፌ ከነድካሜ ወደኸኛል እንኳን እኔ አንተን አንተም እኔን ወደሀል ራስህን ስለሀጥያቴ ስትሰዋልኝ ርቄ የነበርኩትን አንተው ስታስጠጋኝ ሸክሜን አራግፈህ ሰው ስታደርገኝ እድፌን አጥበህ ጽድቄ ስትሆነኝ ከእቅፍህ አልወጣም አልኩኝ ከቤትህ አልወጣም አልኩኝ ምህረት ያልተገባኝ ሆኜ ሳለሁ ከፍጥረቴ የቁጣ ልጅ ምህረት የተገባት ብለህ ካልከኝ ከወደድከኝ ከመረጥከኝ ይኸው ምስጋናዬ ይኸው ዝማሬዬ ይኸው መስዋዕቴ ይኸው ደግሞ ክብሬ ይገባህ የለም ወይ

ዓለቱ እና ውኃው ! ዓለቱ ተመትቷል፣ ውኃውም ፈልቋል፣ ሕዝቡም ጠጥቶታል። #ክፍል_3 “ዓለቱን በምድረ በዳ ሰነጠቀ፤ ከጥልቅ እንደሚገኝ ያህል በብዙ አጠጣቸው።” (መዝ 78፥15) ~ዓለቱ እስከተመታበት ጊዜ ድረስ፣ ውኃው ከውስጥ እንደታቆረ ነበር፤ ሰውም ምንም ማድረግ አይችልም። ►ከዚያ ታላቅና ጠንካራ ዓለት፣ ውኃን ማውጣት ለሰው እጅ እንዴት ይቻለዋል? ►የእግዚአብሔርን ፍቅር እንደ ጎርፍ የሚያፈሱ የምሕረት በሮችን ሊያስከፍት የሚችል የሰው ልጅ ጽድቅስ ከወዴት ይመጣል? ~ሰው በሥራው ወይም በንግግሩ ወይም በስሜቱ፣ መንፈስ ቅዱስ ወደእኛ የሚመጣበትን መንገድ ሊያመቻች አልቻለም። የሰው ልጅ ምንም ያድርግ ወይም ምንም ይሁን አንዳች ማድረግ አይችልም። ክርስቶስ ግን ይህንን አድርጓል። ➜ክርስቶስ ሥራውን በማከናወን ፈጽሞታል፣ ➜እውነተኛው ዓለት ተመትቷል፣ ➜የተጠሙ ነፍሳትም ይጠጡ ዘንድ ከእርሱ የሚያረካው ጅረት ፈሷል። ~ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ:- “እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ #የውኃ_ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።” (ዮሐ 4፥14) ~በሌላ ቦታ ደግሞ:- "ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ #የሕይወት_ውኃ_ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው #ስለ_መንፈስ_ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።" (ዮሐ 7:37-39) ይቀጥላል ... https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

➜ሕግ "የኃጢአት ኃይል" ከሆነ፣ ጸጋ ደግሞ ኃጢአትን ኃይል የሚያሳጣው መሆን አለበት። ➜ሕግ ኃጢአት በእኛ ላይ ኃይል እንዲያገኝ ካደረገ፣ ጸጋ ግን እኛን በኃጢአት ላይ ኃይል ሰጪ መሆን አለበት! https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

ዓለቱ እና ውኃው ! ዓለቱ ተመትቷል፣ ውኃውም ፈልቋል፣ ሕዝቡም ጠጥቶታል። #ክፍል_2 “ዓለቱን በምድረ በዳ ሰነጠቀ፤ ከጥልቅ እንደሚገኝ ያህል በብዙ አጠጣቸው።” (መዝ 78፥15) ~እስራኤል ዓለቱን በዓይናቸው አፍጥጠው እያዩት በውኃ ጥም ሊሞቱ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ዓለቱ #በእግዚአብሔር_በትር ከመመታቱ በፊት፣ #ጥምን_የሚመልስ ውኃ አይወጣውምና። ይህም ለእግዚአብሔር የምሕረት፣ የጸጋና የፍቅር መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ያሳያል። ➜በረከት ሁሉ ወደ ሰው ልጆች #የሚፈሰው፣ በእርሱ በኩል ነው። ➜የጸጋው ወንዝ እንዲፈስ የታቀደው፣ ከእግዚአብሔር በግ ነው። ➜ነገር ግን ጸጋው እንዲፈስ፣ በጉ መታረድ ነበረበት። ➜ከእነዚህ ነገሮች ሁሉም ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ የመስቀሉ ሥራ የተከናወነ እውነታ ሆኖ መገኘት ነበረበት። ➜ዘላለማዊ ፍቅሩን እንደጎርፍ የሚያፈሱ የምሕረት በሮች በሰፊው ተከፍተው፣ ወደ ጥፋት በመሄድ ላይ የነበሩት ኃጢአተኞች በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ተጋብዘው እስኪረኩ ድረስ አብዝተው በነፃ እንዲጠጡ ለማስቻል፣ አስቀድሞ የዘመናት ዓለት በያህዌህ እጅ የግድ መመታት ነበረበት። ~"የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ" (ሐዋ 2:38)፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የፈጸመው ሥራ #ያመጣው_ውጤት ነው። ክርስቶስ:- ✔️ጽድቅን በሙላት ፈጽሞ፣ ✔️ቅድስናን በተመለከተ ለሚነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቶ፣ ✔️ሕግን በማክበር አጠናቆ ፈጽሞ፣ ✔️በኃጢአት ላይ የሚመጣውን ኃያሉን የእግዚአብሔርን ቁጣ ተሸክሞ፣ ✔️የሞትን ኃይል ጉልበት አሳጥቶ፣ እና ✔️መቃብርን ድል ነስቶ በሰማያት በግርማው ቀኝ ሳይቀመጥ በፊት፣ "አብ የሰጠው የተስፋ ቃል (የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ)" (ሐዋ 1:4) ሊፈጸም አይችልም ነበር። ~እርሱ ይህንን ሁሉ አከናውኖ #ወደላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ፣ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል። ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፣ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው? ይህ የወረደው #ሁሉን_ይሞላ_ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው (ኤፌ 4:8)። ይቀጥላል ... https://t.me/kalewengel
Show all...
ቃለ ወንጌል መንፈሳዊ አገልግሎት

"...አፌ #ጽድቅህን ሁልጊዜም #ማዳንህን ይናገራል።” (መዝ 71፥15) ለበለጠ መረጃ:- 251913337934 ግርማ መንግስቱ You tube:-

https://www.youtube.com

Email:- [email protected]

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.