en
Feedback
እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

Open in Telegram

@Eiduka ቻናል ገራሚ #ፎቶዎች 📂 #የፍቅር_መልክቶች📜 #ቪዲዮ 📀 #ደብዳቤዎች📝 #የልብን_የሚናገሩ_ሙዚቃዎች 🎶🎶 #ሌሎችንም.......... Administrators & create 👇👇👇👇 👇👇👇 @MarH_23 @eiduka23 Join&share Be happy Be smile

Show more
403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ስብዕና ፍቅር ከሌለ ይታመማል። ስብዕና ፍቅር ከሌለ ይሞታል። ፍቅር ሌሎችን መርዳት ሌሎችንም መረዳት ነው። ሁሉም ሰው እውነተኛ አፍቃሪ ይፈልጋል፤ ነገር ግን በእውነት ማፍቀር ይፈራል። ሁሉም ሰው ትክክለኛውን ሰው ይፈልጋል፤ ራሱ ግን ምንም ትክክለኛ የመሆን ሙከራ አያረግም። አንተ መፈቀርና መደነቅ እንደምትፈልግ ሁሉ ሌላውም መደነቅና መፈቅር ይፈልጋል። ማፍቀር እና ማድነቅ ሳትችል መፈቀርና መደነቅ የምትሻ ክሆነ እራስ ወዳድና አላዋቂ ሰው ትሆናለህ። ፍቅርን እንስበክ፤ ፍቅር ይለምልም፤ ፍቅር ይፋፋ፤ ፍቅር ይፍካ፤ ፍቅር ይግዛን፤ ከፍቅር ውጪ አንድ እርምጃ አናንሳ፤ በፍቅር ስም እንኑር። ✍️Edel🙏 @eiduka @eiduka23

#አናግሩልኝ ሀገር ምድሩ ፡ፌሽታ ገጥሟል ፡ባለዉ ነገር ፣ እኔ ሞኟ፡ መሃል ቆሜ፡ መደናገር ። ፍቅሩን ይዞ ሲረዳዳ፡ ሲጠቃቀም፡ ሲለጋገስ ፣ እኔ በእርሱ፡ መላ እንዳጣ፡ ስቅለሰለስ ፣ ያ አይናዉጣ ፡
#አናግሩልኝ ሀገር ምድሩ ፡ፌሽታ ገጥሟል ፡ባለዉ ነገር ፣ እኔ ሞኟ፡ መሃል ቆሜ፡ መደናገር ። ፍቅሩን ይዞ ሲረዳዳ፡ ሲጠቃቀም፡ ሲለጋገስ ፣ እኔ በእርሱ፡ መላ እንዳጣ፡ ስቅለሰለስ ፣ ያ አይናዉጣ ፡ የሰላሜ እዉን ቀሚ፡ ልዩ አማላይ ፣ ምን ነክቶት ነዉ ፡ ረግጦኝ የሚያልፍ፡ በላዬ ላይ ። ~እባካችሁ ወዳጆቼ~💔 ልቤን በልቶ፡ በዝምታ ፡ በሀሳቤ ላይ ለነገሰዉ ፣ ሁሉም ቀርቶ፡ አናግሩልኝ፡ ያን ክፉ ሰዉ ። ✍edel @eiduka23🥀 @eiduka🦋

#አልፎ_አልፎ_መሞት #ኤልያስ_ሽታኹን ሰው አንድም - በእግዜር፡ አንድም - በመውዜር፡ እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡ ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል። ሰው ቢያጣ መንገድ ሰው ቢያጣ ምርጫ፡ ተከፋፍለው ተስፋ
#አልፎ_አልፎ_መሞት #ኤልያስ_ሽታኹን ሰው አንድም - በእግዜር፡ አንድም - በመውዜር፡ እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡ ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል። ሰው ቢያጣ መንገድ ሰው ቢያጣ ምርጫ፡ ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ። ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡ አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ። እኔ ግን፡ ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡ ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን። ሰው ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡ ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት። @eiduka 🦋🦋

❤ ፍቅርና ጊዜ ❤ ሁሉም አይነት ስሜቶች የሚኖሩበት አንድ ደሴት ነበር፡፡ የደስታ ስሜት፣የመከፋት ስሜት፣ እውቀት እና ሌሎቹ ስሜቶች ፍቅርን ጨምሮ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ደሴቱ ሊሰምጥ እንደሆነና ሁላቸውም ስሜቶች ሊያመልጡ የሚችሉበትን ጀልባ መስራት እንዲችሉ አዋጅ ተነገረ፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን ሲሰሩ ፍቅር ግን ደሴቱ እስኪ ሰምጥ ድረስ ጀልባ አልሰራም ነበርና ከሊሎቹ ስሜቶች እገዛ ለመጠየቅ ወሰነ፡፡ ሀብታምነት የሚባለው ስሜት በፍቅር በኩል ሲያልፍ “ሀብታም ሆይ ከአንተ ጋ ይዘኸኝ ልትሻገር ትችላለህ?” አለው ፍቅር፡ “አይሆንም፡፡ አልችልም በጀልባየ ውስጥ በርካታ ወርቅና መዳብ የያዝኩ በመሆኑ ለአንተ የሚሆን ቦታ የለኝም” ሲል ጥሎት ሄደ፡፡ ፍቅር አቶ ስግብግብን ሲያልፍ ተመለከተውና እንዲረዳው ጠየቀው፡፡ “አልችልም አቶ ፍቅር ጀልባየን ታበላሽብኛለህ አይሆንም ብሎ” ትቶት ሄደ፡፡ አቶ መከፋትን በቅርብ አገኘውና አሁንም ፍቅር አብሮ እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡ “ኦው! ፍቅር አዝናለሁ እኔ ብቻየን ነው መሆን የምፈልገው፡፡” ብሎ አሰናበተው፡፡ ደስታም ፍቅርን አልፎት እየሄደ በጣም በፈንጠዝያ ደስታ ላይ ስለነበር ፍቅር ሲጠራውም መስማት አልቻለም፡፡ ባጋጣሚ “ፍቅር ና እኔ እወስድሃለሁ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲዞር የተባረከ አዛወንት ነበር፡፡ “ጊዜው ነው” ወዳጀ ፍቅር ሲል እውቀት የተባለው ስሜት መለሰ፡፡ “ጊዜ ማለት!?” ፍቅር በመደነቅ ጠየቀው “ነገር ግን ለምን ጊዜው ሊረዳኝ ቻለ?” እውቀት ፈገግ እያለ ምክንያቱም “የፍቅርን ዋጋ መረዳት የሚችለው ጊዜ ነው፡፡” ሲል መልስ ሰጠው፡፡ ✍Edel_ @eiduka23 @eiduka🦋 መልካም ሰንበት ይሁንላቹ 🙌🙌

መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ 😘😘😘
መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ 😘😘😘

ሰዉስ አይደለህም በሰማሁኝ ቁጥር የዝናቡን ኮቴ በደስታ ይሞላል የደረቀው ፊቴ ያለ ይመስለኛል መንፈስህ ከፊቴ የማታውን ተወው ጭራሽ ጨልላለሁ ሲያሻኝ እስቃለው ሲያሻኝ አለቅሳለው ከትራሴ ጋራ ሳልሳ ደንሳለው ከጎኔ አንተ እንዳለህ በሀሳቤ ስላለው መልሼ አለቅሳለው እነፋረቃለው በዝናቡ ኮቴ የምታሳስቀኝ የማታ የማታ የምታጃጅለኝ ቁጭባልኩኝ ቁጥር ትውስ የምትለኝ ሰውስ አይደለህም ሰው ነኝ አትበለኝ ✍️Edel🥀 @eiduka🦋

"የት ነበርሽ " 🤔 የት ነበርሽ ....??? ስትርቢኝ ስጠሚኝ እንደውሀ እንደ'ህል ልቤ ሲንከራተት ሲናፍቅ ያን ያህል የትዝታሽ ለበቅ ሌተቀን ሲገርፈኝ እንቅልፍ እየነሳ ሀሳብ ሲያንሳፍፈኝ የት ነበ
"የት ነበርሽ " 🤔 የት ነበርሽ ....??? ስትርቢኝ ስጠሚኝ እንደውሀ እንደ'ህል ልቤ ሲንከራተት ሲናፍቅ ያን ያህል የትዝታሽ ለበቅ ሌተቀን ሲገርፈኝ እንቅልፍ እየነሳ ሀሳብ ሲያንሳፍፈኝ የት ነበርሽ .....??? ጥርስ ተናክሼ ብሶት ጋር ትንቅንቅ ቀን የይምሰል ስስቅ ሌት በእንባ ስቅስቅ እያልኩ ብቻዬን ዕልፍ ቀን ስገፋ የት ነበርሽ ያኔ ድምፅሽ ለምን ጠፋ ? ትታህ ይሆን ሲሉኝ አተወኝም እያልኩ ከድታህ ነው ከሚሉኝ ጠብ እየተጋበዝኩ ወዲህ በሌላ ጎን ለኔው በመወገን አትመጣም ቀርታለች አታልማት በቃ እስከመች ተኝተህ ይበቃሃል ንቃ እያሉ ሊመክሩኝ ወሬ ሲጀምሩ አፌ ተሽቀዳድሞ ሌላ ሳይጨምሩ ስላንቺ ሊያስረዳ ቃል እየመረጠ እንደማትቀሪ ምሎ እያስረገጠ አታውቋትም እሷን አትጨክንም በኔ ትመጣልኛለች ናፍቆ አይቀርም አይኔ እያለ በኩራት ከራሱ አንቺን አምኖ ተስፋ ሲጥልብሽ ምኞቱን ወጥኖ የት ነበርሽ ???.... #አንዳንድ_አርፍዶ_መምጣቶች_ከመቅረት_እኩል_ናቸው 😞 #ሼር ✍ @eiduka23 @eiduka

Mechem ❤️❤️❤️ 💔💔💔💔💔💔💔💔 @eiduka23

Guadegnaye😘😘 Mrtye zefen @eiduka 🦋

......... አለኮ 🤔 ውስጣችሁ ላይ የሆነ አንዳች ውጋት አለ አይደል ? የሆነ አንዳች ምቾት የሚነሳ የሚቆረቁር ብሶት ላያችሁ ላይ ጭናችዃል አይደል ? የኔ የምትሉትና የሚረዳችሁ ሰው ብታገኙ ል
......... አለኮ 🤔 ውስጣችሁ ላይ የሆነ አንዳች ውጋት አለ አይደል ? የሆነ አንዳች ምቾት የሚነሳ የሚቆረቁር ብሶት ላያችሁ ላይ ጭናችዃል አይደል ? የኔ የምትሉትና የሚረዳችሁ ሰው ብታገኙ ልታወሩት የምትፈልጉት የሆነ ህመም አላችሁ አይደል ? የህመሙ ስሜት እንደናንተ የሚሰማው ስሩ ሽጉጥ አድርጎ አይዞህ (አይዞሽ) ብሎ የሚያባብላችሁ የራስ ሰው ቢኖራችሁ የምታለቅሱት የሆነ የሂዎት ቁስልና የመኖር እንቅፋት አላችሁ አይደል ?? 🤔 @eiduka 🦋

✨🌕✨ አንቺ ውብ ጨረቃ ሰምተሽኝ እንድሆን ብቻዬን ሳወራ ለሰው አትንገሪ ሚስጥሬን አደራ ወስጤ ሰውን ፈራ መስሎኝ ከዳተኛ😔 እባክሽ ጨረቃ አድርጊኝ ጓደኛ🌚 :¨· .·¨ : `· . . @eiduka23

🙍‍♀👸ስለ ሴት ልጅ ከጠየቁህ እንዲህ በላቸ፦ እሷ ነብስ እንጂ አካል አይደለችም። አዛኝ እንጂ ደካማ አይደለችም። እውቀት እንጂ ፅልመት አይደለችም። ብርሃን እንጂ ጨለማ አይደለችም። ጥሩ እንጂ ሞኝ አይደለችም። አምላክ ከአዳም አጥንት የሰራት የሁሉም አዳም አደራ ናት በላቸው። እናትየ😍❤️❤️❤️❤️🥰

አትምጪ 🤔🤔🤔 ደጄ የረገጥሽዉ ነሀሴ መባቻ በእንጭጭ በቆሎ ተከፋቹ መምቻ ...... ነሀሴን የት ነበርሽ ማረፊያሽ አብቅቶ ወደኔ የመራሽ ናፍቆት አመካኝቶ .......... ሰኔን ከየት አደርሽ መስከረም ሲጠባ ጸሀይ ሲወጣልኝ ጥቅምቱ ሳይገባ ....... ምነዉ ጥርን ጠበቅሽ ዘገሊላ ልቀር የክቴን ለብሼ ሎሚ ላዉረዉር ..... ምነዉ በ የካቲት በፍቅር ወራት ልታሰናክይኝ ልቤን ልትደልያት ..... ምነዉ በ ሁዳዴ ካላጣሽዉ ቀናት አለምን አጋርተሽ ነፍሴን ልታረክሻት ....... ምነዉ ቀን አትመርጪ ደስተኛ ሁን ብለሽ ደስታዬን ልትነጥቂ ማልደሽ የምትመጪ ........ አራቱን ወራት ግን የችግሬ ጊዜ በሸነና ስትይ ሳለሁ በትካዜ ....... ስሜ እንኮን ጠፍቶብሽ ብጣሻሙ ያልሽኝ ወዳጅ ቢጠይቅሽ ....... አራቱ ወራትስ በምን ልትክሽኝ ፍቅርሽ አልቆብኛል ዳግም አታርክሽኝ ............ አትምጪ ........... የተጻፈ በ ፊፊ ቅኔ ራስ ግጥም ❤️❤️❤️❤️ @eiduka 🦋 @eiduka 🦋🦋

#ባንተ_ብቻ_አይደለም 🙏 "መኖር ድክም ብሎኛል ፣ ተስፍ ልቆርጥ ነው የምትሉ በሙሉ ኑና ይሄን ግጥሜን ልጋብዛችሁ" 👇 አንዳንዴ ስትኖር ..... እንዳሰብከው ሳይሆን ፣አንተ እንደጠበከው ፍፁም ተቃራኒ ፣ ሁኖ ነው ሚገኜው ጎንህ ላለው በርቶ ፣ አንተ ጋር ጨልሟል ሌተቀን እየጣርክ ፣ ትርፍህ ድካም ሁኗል ያቀድከው ያለምከው፣ አልሳካ ብሎህ መጣ ያልከው ቀርቶ፣ ደግ ያልከው ከፍቶብህ የኔ ያልከው ወዳጅ ፣ የሩቅ ሰው ሁኖብህ ውስጥህ ብቸኝነት ፣ ተሞልቶ ባዶነት ድንግርግር ብሎህ ፣ ትርጉሙ የሂዎት በቃ ሁሉም ነገር ፣ ስልችት ብሎሀል በዚህ የተነሳ ከተስፋ መቁረጥ ፣ ስር ካፍፉ ቁመሀል 🚶‍♂ , , ልብ በል ወዳጄ " መኖር ይቀጥላል" እስኪ ልጠይቅህ ....?🤔 የሂዎትን ጉዞ የመኖርን መንገድ ማን ቀጥብሎ ሄደ ማን ሳይወላገድ ? ማንስ ነው የኖረው ሁሌም እንደሳቀ ለአፋታም ሳይከፋው ሰርክ እንደቦረቀ ? ማንስ ይሆን ከቶ በእንባ ምንጭ ያራሰ ሀዘን ሳይዳስሰው ብሶት ሳይጎበኜው በ አልጋ ባልጋ ድሎት ዛሬን የደረሰ ? ማ•••••••••ን•••••••••ም 🤷‍♂ እየህ አይደል ጓዴ🤔 ይብዛም ይነስ እንጂ • • በመኖር እንቅፋት ሁሉም ተደናቅፏል? የግዜን አቀበት በማቃሰተ አልፏል ? የተፃፈለትን የእጣ_ፈንታ ድርሻ ? የማሩን የሬቱን የ'ሰው' ነት ቅምሻ ? መራራ ጣፋጩን ውጧል የድርሻውን እ ና ም ••••••• እ ል ሀ ለ ው አሁንህ ቢጨልም ባይሆን እንዳሰብከው አይዞህ ቀና በል 💪 ባንተ ብቻ አይደለም እስኪነጋ ድረስ በትእግስት አለፈው • • ቢለያይ ነው እንጂ ስፋቱ ጥበቱ ሽንቁር አልባ ኗሪ የለም በምድሪቱ ጨለማን ባናውቅ ኗሮኮ የብርሀንን ዋጋ ባልተገነዘብን ነበር ፣ ማጣትን ባናይ ኗሮም የማግኜት ትርጉም በቅጡ ባልገባን ነበር 🤷‍♂ የደግ ሰዎችን ግምት አንድታውቅ የሚያደርጉህም የክፉወች መኖር ነው 🤔 አየህ ሁሉም የሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው የሂዎት ገፆች ብዙና የተለያዩ ናቸው ሁሉም ገፆች መልካምና ጥሩ እንዲሆኑ ግን መጠበቅ የለብህም። የንጋቷን ፀሀይ ለመሞቅ የለሊቱን ፅልመት በትእግስት ማሳለፍ ግድ ነው ። #ልብ_በል ባንተ መቆም የሚቆም፣ ባንተ መኖር የሚኖር ቢያንስ አንድ ሰው አለ ስለዚህ የፈለገውን ያክል ነገሮች አሰልቺ ቢሆኑብህ እንኳ ተስፋ መቁረጥን የመጨረሻ ምርጫህ እንኳ አታድርገው 🙏ከፈጣሪህ አትራቅ ፣ ዛሬ ላይ ማድረግ ያለብህን ካንተ የሚጠበቀውን እያደረክ ነገን መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርግ ።ማን ያውቃል ባልጠበከውና ባላሰብከው መንገድ ሂዎት በራሷ የተቃናች ትሆን ይሆናል ምክንያቱም " እስካልሞትን ድረስ መኖር ይቀጥላል" #ሼር ✍ 👇 @eiduka 🦋

እኔን የሚገርመኝ #ለሴቶች💁 ሲሆን ጠበሰችው #ለወንዶች💁‍♂ ሲሆን ለከፋት ቆይ ወንዶች ውሻ ናቸዉ እንዴ🤦‍♂🤷‍♂ #ይሔማ_Fair_አይደለም😳

❤️እወድሀለሁ❤️ ዘመኑ ቢራቀቅ እሳቱ ቢጨመር ፈታኞች ቢበዙም ቃልኪዳን ቢሰበር ትውልድ ቢዘምን ቢጨልምም ፍቅር ሁሉም ነገር ረክሶ ቢቀዬር ወደ አፈር ቆርቤያለው ባንተ በውስጥህ ልቀበር ❤️እወድሀለሁ❤️ @eiduka23🥀

ተግደርዳሪ.....😁 ሁለት ጎንደሬዎች በድካም የዛሉ ሲሄዱ አንግተው ሲጓዙ የዋሉ ማታ አመሻሹ ላይ ከአንዱ ሁቴል ገብተው ትንሽ እፎይ አሉ ከአልጋው ተዘርግተው ረሀቡ ሲጸና ቶሎ ተነሱና ቋጠሮውን ፈቱት ስንቃቸውን አዩት አልቋል ቁራሽ የለም ካንድኛው አገልግል ካንደኛው ተርፋለች ዝግን የምታክል ያችኑ ጎራርሰው ማደሩን ትተውት ሳህኑን አንቀውት ጀመሩና ትግል አንዱ ጉረሳት ሲል አንዱም ላጉርስህ ሲል ከትግሉ መካከል ሳህኑ ከእጃቸው አምልጦ ተደፋ ቁራሿም ከሰረች ትልቅ ጥፋት ጠፋ ከዛማ ረሀቡን ለመርሳት በተመሳጨ ጥርስ ትንሽ ተሳስቀው በአንዱ የሆድ ጩኸት አንዱ እንዳይስቅበት ተኙ ተራርቀው ታዲያማ በሌሊት መጣች ሙሽራዋ የጉድጓዷ ንግስት ደግስ ድግስ ሸቷት ደርሶ ኖሯል ለካ ልመናዋን ሰምቷት ወንድም አማቾቹ ከእጃቸው የጣሉት ለካስ ሲሳይ ኖሯል መሬት ውስጥ ላሉት እናት አይጥ ወጣች ጸሎቷ የሰመረላት ለሷና ለልጆቿ መና የወረደላት ልጆቿን ጠርታቸው እስኪጠግቡ ድረስ ጎርሳ አጉርሳቸው ለእራሷም በልታ አጠገበቻቸው የአይጦች ማህበር ሁሉም ተጎራርሰው በጥጋብ ሰከሩ እኒያ ጎንደሬዎች በመግደርደራቸው እየጾሙ አደሩ [Eidu] @eiduka23 @eiduka 🦋

ኳስ እንጫወት የሚል ሀሳብ በላይ በሚባለዉ ጓደኛችን ተነሳ። ሁላችንም እሽ ብለን ኮስ ስንጫወት አመሸን ወደ ቤት ስገባ ከምሽቱ 1 ሰዐት አልፎ ነበር።እስካሁን የት አምሽተህ ነዉ ግባና ተንበርከክ እኔ ተነስ ሳልልህ መነሳት የለም ዉርድ ከራሴ የምትለዋን የእናቴን ቃል እየጠበኩ ወደ ቤት ስገባ ለምንድን ነዉ የምታመሸዉ ዛሬ በዐል ስለሆነ ነዉ የማልቀጣህ ታጠብና እራት ብላ አለችኝ እናቴ። በሆዴ የነገን እግዚአብሔር ያዉቅልኛል እያልኩ ተጣጠብኩና እራቴን በልቸ ተኛሁ ።አቤት የ እሁድ ቀን ፍጥነት ተሎ እኮ ነዉ የመሸዉ እያልኩ በቀጣይ የእንቁጣጣሽ በዐል ደርሶ የማገኘዉን የገንዘብ መጠን እና በገንዘቡ ምን ላደርግበት እንደምችል እያሰብኩ ቀኑ አልመሽ የሚለብኝን የእንቁጣጣሽ ዋዜማ ቀንን ወይም እኛ ኢትዮጲያንን ከሌሎች የአለም ሀገራት ልዩ የምታደርገንን የጷግሜ ወር የመጨረሻ ቀን የሚደርስበትን ዕለት እየናፈኩ ተኛሁ። የእንቁጣጣሽ ዕለት ከ 10 ብር በላይ እንደማገኝ ተስፋ አድርጋለዉ።ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ! @eiduka

​​​​​​​​​​​​ ​ 💞 ለፍቅሬ ስል 😢 ❐ የመጨረሻ ክፍል ❑​​​​ የመጨረሻው ነው 😔 ነገር ግን ህይወት ቀጥላለች🚶‍♀️ ..."መሄድሽ ካልቀረማ የግድ ሴክስ ታረግያለሽ ከኔ ጋር" አለ በተቆጣ ድምፁ ሰውየው <የማዳም ባል> እደፍርሻለው ብሎ ከተናገረባት ደቂቃ ጀምሮ ደንዝዤ ለደቂቃዎች ቆምኩ ከዛ ግን እራሴን እንደምንም ማደፋፈር አለብኝ ብዬ አሰብኩና ሰውየውን 'እስቲ ተጠጋኝና ሞክር ኢንተርኔት ላይ አሰራጭልሃለው' አልኩት ደስ የሚለው ይፈራል... እየዛተና ብቻውን እያጉረመረመ ወደ ሳሎን ተመለሰ እኔም ተኛው ...ተመስገን ነገ ለሊት ጉዞ ወደ አሜሪካ አደርጋለሁ ከዛ በፊት የነበረኝን ብር ለናቴ ዛሬ ላኩላትና በዛውም ደወልኩ እናቴ ከበቀደሙ ይልቅ ዛሬ ድምጿ ይሻላል ትንሽ እንደተሻላት ታስታውቃለች እናም ትንሽ ጭንቀቴ ቀለል አለልኝ ከዛም ለወንድሜ እናቴን እንዲጠብቃት በደምብ አደራ ሰጥቼውና አሜሪካ ልሄድ እንደሆነ ነግሬው ደስ ብሎት እሱንም ስልኩን ዘጋሁ... የፍቅር ነገር አልቆርጥልሽ ቢለኝም ባለፈው ማንነቴ ስለሚያፍርብኝ ደግሜ እንደማላገኘው ወስኛለው ግን በሀሳቤ ሁሉ ጣልቃ እየገባ ስለሱ ማሰቤንና ማፍቅሬን ማቆም ተስኖኛል ...በቃ ባላገኘውም ልጠላው ግን አቅም አጣሁ እሱም ስልኬን በከፈትኩ ቁጥር መልክት ሳይልክልኝ አይውልም ተፀፅቶ ይሆናል ብዬ ባላምንም ሲለምነኝ ግን ያሳዝነኛል... ዛሬ እሁድ ነው ልደቴም ነው አሜሪካ ከገባው ድፍን 2 ወር ሞላኝ አሁን ሁሉም ሰላም ነው ቤተሰቤንም በፈለኩ ሰአት አወራለው ፈጣሪ ከፈቀደ ደሞ እናቴን ደና ሆስፒታል አሳክማታለው ብያለው ...የፍቅርን ነገር ግን ውሳኔ ላይ መድረስ ስላልቻልኩ እንዲው እያፈቀርኩት እኖራለው!!! 💘💘💘 . . . ህይወት ግን ይቀጥላል....!! የመጨረሻ የኑኑሻ መልዕክት👉 ❝እናንተም ከእኔ ህይወት ብዙ እንደ ተማራቹ ተስፋ አደርጋለ።❞♥️♥️♥️ ----------------------------------------- ተ ፈ ፀ መ ----------------------------------------- 🙏ምስጋና 😍ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ! 📬በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት መስጠት ትችላላችሁ @eiduka @eiduka23