403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
😘አለሜ ነሽ😘
🔥ክፍል 11
✍ እድል
.
.
.
የፈጣሪ ያለ ኮሊደሩን ያናጋው ኮቴ ቀረበ አዳም የእዚህን የኮቴ
ወይም ዱካ ባለቤት አየው የጠርጠርው ነው ያ እርኩስ እና
ለሰው የሚራራ ልብ የሌለው ጊዲዮን ነው
አዳም ጌዲዮንን ሲያየው ፍርሀቱ እና ድንጋጤው ጨመረ ደፍርት
እና ወኔው የለም አዳም በተቆጣ እና በገነፈለ ስሜት ጊዲዮንን ተጠጋው ተጠጋው
ተጠጋው በጣምም ተጠጋው ተጠፋጠጡ ጊዲዮን ያ ስድ ሳቁን
ለቀቀው አዳም አሁን ይበልጥ ተበሳጨ ሊመታው ፈለገ ግን ደሞ
ይህንን ቆሻሻ ሰው ለመምታት መንካት ይጠበቅበታል መንካት
ደሞ አልፈለገም ጊዲዮን እእእእእ አ መቼስ እንዲህ
የምትፈታተነኝ በጣም ናፍቄክ ነው ከቅጣቶቼ የምትማር
አይመስለኝም ኧረ እንዳውም ሱስ ሳይዝክ አይቀርም አለና
በድጋሜ መብርቅ የሚያስደነግጠውን ሳቁን ለቀቀው ጠላቱ
የጊዲዮን ሳቅ ጩከት ከ ሚያፍቅራት እና እንደ ነፍሱ ሳይሆን
ከነብሱ በላይ ከሚወዳት ሄዋን ጋር ያመሳስለዋል በእርግጥ ሄዋን
ስትስቅ የአለምን ድምፅ ወክላ የምትስቅ ነው የሚመስለው
ከጊዲዮን እጥፍ ነው ሳቋ እና ለአዳም ከሁለቱ ጩከት የሄዋን
ቢበልጥም የሄዋንን ሳቅና ንንግር እንደ ዘፈን የጊዲዮንን ደሞ እንደ
ቆርቆሮ የሚንፈቀፈቅ ድምፅ ነው ጆሮ የሚስማው
አዳም በንዴት ግን በተርጋጋ ድምፅ ምን ፈለክ አለው ጊዲዮን
አሁንም ሳቀና ምን ፈለክ አትበለኝ የፈለኩትን ብነግርክ
ትስጠኛለክ? እ መለስልኛ አስጠኝም ግን ደሞ ብስጠኝም
ባስጠኝም ከፈልኩኝ እወስድብካለው አንተ ማለት ለእኔ የሆነ
ነገር ፈልጎ በእጁ እቃ ይዞ እንዳይወስድበት የሚታገል ህፃን
ስትሆን እኔ ደሞ ላንተ ወደድክም ጠላክም እቃውን የምወስድብክ
አዋቂ ነኝ አንተ ፍላጎት እንጂ ጉልበት የለክም እኔ ግን ፍላጓት
እንዳለኝ አቅም ስላለኝ ሁሉ ነገርን እወስደዋለው እና አንተም
እቃው እንደተቀማ ህፃን ታለቅሳለክ አልቃሻ ሀሀሀሀሀ አልቅሻ
ነክካ ምንም አታመጣማ እህ እህ እህ አህ እያልክ ሀሀሀሀሀሀሀ
የማያቆርጥ ሳቅ ሳቀበት አዳምም አብሮት ሳቀ ጊዲዮን ግራ
ገባው ደንግጦ ሳቁን አስቆርጦ ምን ያስቅካል አለው አፍክን
በከፈትክ ቁጥር ባዶነትክ ይበልጥ ጎልቶ ስለታየኝ ልበልክ ወይስ
ሳቅክ አስቆኝ ነው ልበልክ ሲለው ጊዲዮን በጣምም ተበሳጨ
አዳምን በጥፊ ሊመታው ፍለገ ግን አልቻለም
ዲና ካቀረቀረችበት ከነቃች ቆየች ጊዲዮንን ስታየው አዳም
የነገራትን የጊዲዮንን አቋም ስታይ እና የተፃፈውን ጊዲዮን የላከለትን ፁሁፍ ስታስታውስ ደርቃ ቀርች
ዲና 100% ያ ሰው ጊዲዮን ነው አለች አዎ እሱ ነው አዎ ያ
አረመኔ ነው የፈጣሪ ያለ ምን አባቱ ይመስላል ወይ አያምር ወይ
አያፍር አለች በጥላቻ እና በአስቀያሚ አንዲሁም በዘግናኝ
አስተያያየት እያየችው ነው ጊዲዮን ዲናን አያት እና አሁንም ያ
መብርቅ አስናቂውን ድምፅ ለቀቀው ያቺ ሴት ምንድነው በፍቅር
አይን የምታየኝ በእርግጠኝነት ስለ ጥሩነቴ ነግረካት ነው አይደል
አለው አዳምም የፊዘት ሳቁን እየሳቀ አዎ ልክ ነክ ስላንተ ጥሩነት ያልተወራ ስለማን ይወራል አሁን ትሄዳለክ ወይስ ብሎ ሳይጨርስ ጊዲዮን ወደፊት እየቀረበ ወይስ
ምን እእ አለው ያ ስው ፊት የማይቀርበውን ፉንጋ ፊቱን ወደ
አዳም እያስጠጋ አዳምም ድፍርት እና ወኔ በሞላው አነጋገር
ደርቱን ገልበጥ ነፋ አገጩን ቀና አይኑን ፍጥጥ አርጎ በተራው ወደ ጊዲዮን ፊት
ተጠጋና ትሄዳለክ ወይስ እስከ ቡችሎችክ ቱሪናፋ ወሬክን ታወራለክ አለው ጊዲዮን
ንድድድ አለ በእዚህ አይነት ንቀት እና ድፍርት ቀና ብሎ አይቶት
አያውቅም ። ከጊዲዮን ከኋላው የቆሙ ሁለት ወንዶች የጊዲዮን
እና የአዳምን ንትርክ ይሰማሉ ጊዲዮን ከተለያዩ የወለዳቸው እሱን
መሳይ አንድ አይነት እና አንድ ናቸው የቆሙት ልጆች የጊዲዮን
ልጅ እንደሆኑ መልካቸው ያሳብቃል ለእዛም ነው ያልገደላቸው
እራሱን ስለሚመስሉ ።
ጊዲዮን አዳምን በበሸቀ ስሜት እያየው አሁን ሲኦልን ላሳይክ ነው
የመጣውት ድምፅ አልባ መሳሪያውን ይዞ በል አሳልፍኝ እስቲ ያቺ እንደ
ነብስክ የምታያትን ሴትን ልጠይቃት ብሎ ገፍትሮት ሄዋን
ወዳለችበት ክፍል መራመድ ጀመረ ድንገት 3 የነርስ ልብስ
የለበሱ ሴቶች ጊዲዮንን እና ሁለት ከጀርባው የነበሩትን ልጆቹን
እጃቸው ላይ በያዙት ትንሽዬ መሳሪያ ስውነታቸው ላይ በማብራት
ስውነታቸው እንዲልፈሰፍስ አደረጓቸው በፍጥነት ጊዲዮን እና
ልጆቹ እንደ ቀወሰ ሰው እየተርገፈገፉ እሮጠው ከ አይኑ ተስውሩ
አዳም ምን እንደተፈጠረ ግራ ገብቶት ቆመ ከነርሶች ውስጥ
አንደኛዋ አዳም እግር ስር የተጣጠፈ ወርቀት ጥላለት ሄደች
ጊዲዮን ወርቀቱን ዘርጋው አንተ ብቻ የወዳጄን ነገር አደራ እኔ
በዙሪያክ ካሉ ሰዎች ሁሉ እጠብቅሀለው ይላል አዳም ያ ባለ ላዳ
እንዲህ እንዳርገለት እርግጠኛ ሆነ ዲና የሚሆነውን ሁሉ እያየች
ነበር በጣም ተደምማ አፏን ከፍታ ቀርች እንዲህ ያለ ነገር
በፊልም ካልሆነ በቀር አይታ አታቅም አዳም ወደ ዲና አመራ ዲና
ምን እየተፈጠርረ ነበር ቆይ አለች ተይው ባክሽ ቱሪናፍውን
ሲለቀው ነው እንጂ ምንም አያመጣም አላት ዲና በአዳም ልበ
ሙሉነት ተገርማ ቆይ አንዴት ነው አንዲህ ዘና ያልከው አለችው
አዳምም ምን እንዳያረግ ነው የፈራሽው አቃለው አውሬ ነው ግን
እኔን እንዲህ በቀላሉ አይጎዳኝም ምክንያቱም ሊያሳብደኝ
ስለሚፈልግ እኔም በፍፁም አልረታለትም አለ በእሱ መርጋጋት
ውስጥ ዲና ይበልጥ ተርጋጋች እስቲ ሄዋኔን ልያት ብሎ ወደ
ሄዋን ክፍል አመራ ሄዋን ለጥ ብላለች ትንሽ አይቷት ወደ ዲና
ተመለሰ ዲና አሁንም በብስጭት እና ድንዛዜ አልወጣችም
ብትርጋጋም አልተርጋጋችም አዳም ኧር ነቃ በይ ምንም አይፈጠርም
አላት ዲና እሺ ግን መጨርሻ ላይ የመጡት ሴቶች ማን ልኳቸው
ነው አለችው ከዛ በእጁ የያዘዉን ወርቀት ሰጣትና አነበበችው ቀና
ብላ ማነው አለች ይመስለኛል ያ የነገርኩሽ ባለ ላዳ ነው አላት
ዲና ዛሬ ያየችው እና የስማችው ህልም መሰላት አዳም በቃ
ተርጋጊ አሁን ዘና እንድትይ ስለ ሄዋን ልንገርሽ አላት ዲና እሺ
ንገርኝ እንደውም ባለፍው ከብዙ ወንዶች ጋር አይተካት እሷም
ሁሉንም ስማቸው ከዛ ከአንተ እሷን መከተል ፈልገክ እንደነበር
ነግርከኝ ነው ያቋርጥከው አለችው አዳም ዋውውው በጣም
ጓበዝ አዳማጭ ነሽ ከዛ እማ ተከተለሸኳት እና የሆነ ሰአት ከ
አይኔ ጠፋች ዲና ተገርማ ማለት የት ሄደች እኔ እንጃ ወደየት
ከቅፅፈት እንደተሰወረች ለኔም ግራ ገብቶኝ ነበር በአይን ፈልጌ
ሳጣት እየተናደድኩ መንገድ ላይ ብና ለመጠጣት ቁጭ አልኩ
የሆነ እጅ አይኔን ጨፍነው ይህ እጅ የሄዋን ነው እጆቿን
ዳሰስኳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ እጇን ነካውት ከዛ እኔ ማን ነኝg
አለችኝ ዲና የአግራሞት ሳቋን ስቃ ሆሆ እብድ ናት አለች
አዳምም ፈገግ ብሎ ከዛ ስሟን ስለማላቀው ዝም አልኩኝ እሷም
እጇን ከአይኔ ላይ ለቃ የእኔ ቆንጆ ምነው ደነገጥክ
እእእ ብላ ከጀርባዬ እንዳለች አቀፈችኝ ከዛ አብርን ብና ጠጣን
እሷን ሳገኛት የምስጣት ሁለተኛ ግጥም ግጥሜን በኪሴ ሁሌም
ይዤው እዞር ስለነበር አውጥቼ ሰጠዋት ምንድነው አለችኝ
የሰጠዋትን ወረቀት እያየች ግጥም አልኳት ለኔ ነው አለችኝ ላንቺ👇👇
🎖🎖መሳሳም ሲተረጎም🎖🎖
🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖🎖
1.ከንፈር ላይ መሳም...."አፈቅርሻለው
2.ጉንጭ ላይ መሳም ....ጉዋደኛ መሆን እፈልጋለው"
3.አንገት ላይ መሳም....."እፈልግሻለው"
4.እጅ ላይ መሳም....."እወድሻለው"
5.ጆሮ ላይ መሳም....."እየተጫወትኩ ነው"
6.አይን ውስጥ መሳም....."ሳሚኝ"
7.ከፀጉር ጋር መጫወት....."ያላንቺ መኖር አልችልም"
8.ወገብ አቅፎ መያዝ....."በጣም ስለምወድሽ አልተውሽም"
9.ከእነዚህ ውጭ መሳም......በስሜት እንነዳ እንደማለት ነው ይቀላቀሉን
Join & share
👇👇👇
@Hayitiye
@Hayitiye
እሱ 👨💼 ☆ የኔ ፍቅር 🥺
እሷ 👩💼 ☆ ወዬ 😍
እሱ 👨💼 ☆ አፈቅርሻለሁ ❤️
እሷ 👩💼 ☆ እኔም አፈቅርሀለሁ 🥰
እሱ 👨💼 ☆ ምንም ነገር እንደማትዋሺኝ ቃል ግቢልኝ 🥺
እሷ 👩💼 ☆ ቃል እገባልሀለሁ 🙏
እሱ 👨💼 ☆ ዳዊት ማነው? 🙄
እሷ 👩💼 ☆ ራሔል ማናት? 🤔
እሱ 👨💼 ☆ አፈቅርሻለሁ የኔ ውድ 🤗
እሷ 👩💼 ☆ እኔም አፈቅርሀለሁ 😂
••●◉Join us share◉●
@Hayitiye 🦋🦋
@Hayitiye 🦋🦋
"ምን አይነት ገልቱ ወንድ ነው አንቺን የሚጎዳው!?" እያልክ እያባበልክ ጠጋ ብለክ ከእሱ በላይ አንኮታኩተህ የምትሄድ ወንድ ሆይ ውሎህ እንዴት እያለፈ ነው?😐
@Hayitiye ¿¿¿
እስማኤል ከነ ቤተስቦቹ ስላደርሰበት አሰቃቂ ነገር ነገራት ዲና
አልቻለችም በዚን ያህል ጭካኔ የሰው ልጅ ይደርሳል ማለት
ከበዳት ይህንን አውሬ ለማጥፍት በሚያርገው ነገር
እንደምታግዘው ቃል ገባችለት።
አዳም ተገረመ አንድም በራሱ ሁለት ደሞ በእሷ በራሱ
የተገረመው እንዴት ባጭር ጊዜ ለማቀው ሰው እንዲ ግልፅ
ሆንኩኝ ብሎ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ ዲና እሱን ለመርዳት
በገባችው ቃል ነበር ።
እንዲህ እያወሩ ኮቴ ሰሙ የሚያነክሱ እግሮች እና አንድ ምርኩዝ
ይሰማዋል የድምፁን ቦታ መገመት አልቻለም ። አዳም ደነገጠ
የፈጣሪ ያለህ እንደባለፈው በህልሜ በሆነ ብሎ ተመኘ የሌሊቱ
ቀጠሮ ደርሷል እንዴ?ዲና ተደፍታ በጭንቀት ስለነበረች ኮቴውን
አላስተዋለችም የአዳም ልብ ጭንቀት ወረረው አዳም ግን አሁንም
ደፋር ነው ውስጥ ላላችው አለሙ ለሆነችው ሄዋን እና ለዲና
በሱ ምክንያት አንድ ነገር እንዳይሆኑበት ይጨነቃል ኮቴው አሁን
እየተቃርበ ነው አዳም ደርቆ ቀረ......
ይቀጥላል....
@Hayitiye 🦋
😘አለሜ ነሽ😘
🔥ክፍል 10
✍ እድል
.
.
.
ዲና ምን እንደምትል ጠፋባት ተርበተበተች ከዛ ዲና ልክ ብርድ
እንደመታው እየተርገፍገፍች እእእ እኔ ያንቺ እኔ ማለት ያንቺ እኔ
ያንቺ እህት ነኝ ሄዋን በጩከት ደምፅ የምርሽን ነው አለቻት
ዲናም እህ አዎ አለቻት ዲና የሄዋንን ድምፅ ጩከት ስሰማ
ድምፆን ሳይታወቃት ጮክ አድርጋ ነበር ለካ አዳም ግቢ እያለን
ድምፇ የግቢውን ተማሪ በሙሉ ይወክላል ያለው እውነቱን ነው
አለች። ሄዋን ግን አልሰማቻትም ምክንያቱም የእሷን ድምፅ
ግማሽ እንኳን የዲና ድምፅ አይሰማም ከሄዋን ጋር ለማውራት
ደሞ የግድ እንደሷ ማንቧረቅ ይጠበቅባታል ወይም ለሌላ ሰው
ደንበኛ ደምፅ ኖርማል የሆነ ለሄዋን ደሞ የሹክሹክታ ድምፅ
የሆነውን ድምፅ ማውጣት ይጠበቅባታል የድምጿ ጩከት ሀሳብ
ውስጥ ያለ እና እንቅልፍ ውስጥ ያለን ያነቃል ያውም
አስበርግጎ ቢባል ማካበድ አይሆንም አይ ሄዋንንንንን ሄዋን ቲንሽ
ዝም አለች ዲናም የምትለው ጠፍቶባት ዝም ብላለች ያስ አሁን
የወጣው ማነው አለች ሄዋን ዲና ይህን መመለስ ከበዳት አዳምን
ለእሷ የሁለታችን ጓደኛ ነው ብላ ማብራራቱ አስጨነቃት ልክ
የምጥ ያክል ጓደኛችን ነው ብላ መናገሩ ከበዳት በጣምምምም
ከበዳት ዲና ለሄዋን አዳም ማለት የሁለታችን ብላ ልክ ባትሪው
እንዳለቀ ስልክ ጥርቅም አለች ሄዋን ከ አፏ የሚወጣውን ቃል
በጉጉት ትጠብቅ ጀመር ሄዋን እ ንገሪኛ ዲና ጨነቃት
ኡፍፍፍፍፍፍ አለችና አዳም ይባላል እሱ ማለት የሁለታችን ብላ
ሳትጨርስ እንባ ቀደማት ሄዋን ግራ ገባት ግን ምኗ እንደሆነ
ማወቅ ፍልጋለች አሁን እንደውም ይበልጥ ጓጓች ዲና ግን ላብ
በላብ ሆነች እሱ ሄዋንን ግለፃት ሲባል መግለፅ አቅቶት እኔ
እንዴት ቀለል አድርጌ ጓደኛችን ነው ልበላት አለች በውስጧ። በቃ
ልንገራት ያው ውሽት ነው ብላ እራሷን አደፍፈራ ለመገላገል
በሚመስል መልኩ የሁለታችን ጓደኛ ነው የትምህርት ቤት እና
ሶስታችን አንድ ላይ ነው የምንኖርው ሶስታችንም የሆነ ድርጅት
ውስጥ ነው ያደግነው እና 18 አመት ሲሞላን ወጣን እና አዳም
ከእኛ በ2አመት ቀድሞ ወጣ ስንወጣ እሱ ቤት ገባን አለች ዲና
ፍጥነት በተሞላበት አነጋገር ።
ልክ ይህን መልክት አድርስሽ ይህቺ ምራቅ ሳትደርቅ ነይ
እንደተባለች ወይም ወተት ጥዳ እንደመጣች አውርታ ከጨርስች
በኋላ ውይይይ ኡፏፏፏፏ ብላ አይኗን
ወደጣሪያው ተወርውራ የተናነቃትን እንባዋን ልትገታ ብትታገልም
አለሆነላትም ልክ እንደ ዝናብ ያረዘው አይኗ ተዘረገፈ።
ሄዋን በአትኩሮት እና ግራ በተጋባ ስሜት ታያት ጀመር ዲና
በፍጥነት እንደ ንፋስ በንፋስ ፍጥነት ክፍሉን ጥላ ወጣች።
ከወጣች በኋላ ዲና ስቅስቅ ብላ አለቀስች እያለቀስች እንዳለ
አዳም መጣ የሆነ ወርቀት በእጁ ይዞል ወርቀቱን የያዘበትን እጁን
ያለ ሟቋረጥ ይወዘውዘዋል ዲና ከተቀመጠችበት ወንበር
አቀርቅራ ስለተቀመጠች አዳም የዲናን ፊት አላየውም ዲናም ቀና
ስላላለች የአዳምን የተርበተበተ እጅ እና በጣም ቁጡ የሆነ ፊቱን
አላየችውም ዲና ቀና አለች አዳም አቀርቅሮ ቆሟል አሁን ፊቱን
አየችው አዳምን በእዚህ ፊት አታቀውም ደነገጠች በጣም እጅግ
በጣም እሱን መጠጋት እና ምን እንደሆነ ለመጠየቅ ፈራች አሁን
የአዳም ፊት ከእዚህ በፊት እንደምታውቀው በፍቅር የተጓዳ ፊት
ሳይሆን በጣም የተቆጣ ልክ እንደ ተናዳጅ አንበሳ ልክ እንደ
ተናዳፊ ንብ ልክ እንደ አራስ ነበር እንደ እሳት እሳት ለብሶ እሳት
ጎርሶ ነበረ ሀሳብ ውስጥ ነው ተመስጦ ውስጥ በጣም መመስጥ
ውስጥ የፈጣሪ ያለ አለች ዲና በደነገጠ እና ለዘዝ ባለ ድምፅ
አዳም ከገብቶ ከነጎደበት ሀሳብ ባነነ ዲና ሲያያት በጣም
ፈርታዋለች ደነገጠ አስደንገጣት ስትደነግጥ መልሶ ደነገጠ
አሁን በትንሹም ፈገግ ሲል ወደ ቅድሙ ፊቱ ተመለስ ዲና አሁን
ምን እንደሆነ ለመጠየቅ ድፍረቱን አገኘች አዳም ወደ ቀድሞ እና
ቅድም ፊቱ የተመለሰ መሰላት ዲና በድንጋጤ ውስጥ ሆና ምን
ተፈጥሮ ነው ቆይ አዳም ፊትክ እንዲ የሆነው አለችው አዳምም
ፊቱን እየነካካ ምን ሆንኩ አላት ዲናም ባክህ የሆነ ነገር ሆነካል
ስትለው ጠቅልሎ እና አስጨንቆ የያዘውን ወርቀት ሰጣት ወርቀቱ
ላይ ዛሬ ለሊት የምድርን ሲኦል አሳይካለው ሄዋንን እና ካጠገብክ
ያለችውን ሴት እስከማታ ጠብቅ ምን እንደማረጋቸው
አታመልጠኝም የምድርን ሲኣል አሳይካለው የሚል ነበር ዲና
ደነገጠች ተርበተበተች በተቆራርጠ እና ፍርሀት ባዘለ ስሜት
ውስጥ ሆና ቆይ ማነው የላከልክ አለችው ወርቀቱን ተቀብሏት
ከጀርባው የተፃፍውን ስም አሳያት ከ ጊ ይላል ዲና አለገባትም
ቆይ ጊ ምንድነው አለች ኩምሽሽ ብላ ጊ ማለት ጊዲዮን ነው
በጥብቅና ህይወቴ በጣም እየተፍታተኝ ያለ ሰው በጣም ክፉ እና
ጨካኝ አረመኔ ሰው ነው የብዙ ደሀዎች እና የፍትህ ፈላጊዎች
ነብስ መጥፍት ተጠያቂ ነው አለና ዝም አለ ዲና እና. ና..
አለቸው እየተርበተበተች እናማ እኔ የእሱን ጉድ ለማውጣት
ስጥር ነው ከእሱ ጋር ያስተዋወቀኝ አላት አዳም የጭንቀት ትንፋሽ
እያወጣ ዲና ማለት አለችው ግራ እየተጋባች አዳምም ማለትማ
በቃ ልክ እንደኔ አልበገር ያለ እስማኤል የተባለ ጠበቃ ነበር ጉዱን
እንዳያወጣበት በብዙ ሚሊዮን ብር ሊያስማማው ቢሞክርም
አይሆንም ብሎ ከነ ቤተሰቦቹ የተስዋው የሚገርምሽ ጠበቃ
እስማኤል የገንዘብ ስምምነቱን ሲያቀርብለት ደሀ ነበር ደሀ
የሆነበት ምክንያት ደሞ በተቻለው አቅም ያለውን ገንዘብ
ለተቸገሩት ስለሚስጥ ነው ዝርዝሩን ሌላ ቀን ነግርሻለው ግን
ጊዲዮን አቁም ብሎት አላቆመም ። ጠበቃው ከፃፋቸው
ከመንገደኛው ሎሌ ታሪክ ያቺ ህፃን ጠያቂ ልጅ እና ሳይታክታታት
መላሽ እናት ታሪኩን ለዲና ነገራት ስለ ልጇ ፍቅርን የተረዳችበትን
መንገድ ስለ ሎሌ እናትና ልጅ ገለፀላት ።
እናት እና ልጅ ከሎሌ ትንሽ እንደራቁ በጥቁር እና በጣም
በሚያምር መኪና ከሇላጨይከታተላቸው ነበር እናትና ልጅም
ማውራታቸውን ቀጥለዋል ልጂትም አንዴ እናቷን አንዴ መሬቱን
እያየች ትጓዛለች ነገር ግን ያ ከሇላ የሚከተላቸው መኪና ሚስኪን
እናት እና ልጅን ቀጠፋቸው አይኑ እያየ ገጫቸው ምግብ ያጠረው
እና በንፍስ የሚወድቅ የሚመስል ሰውነታቸው ተለያይቶ ሞቱ ።
ሎሌ ሲያጣራ ያቺ ሚስኪን እናት ጊዲዮን ካስወለዳቸው ሴቶች
መካከል ስትሆን ያቺም ቲንሽዬ ደሞ የጊዲዮን ልጅ ናት ። ጊዲዮን
ከእሱ ያረገዘውን ሁሉ ከወለዱ በኋላ ልጁ እሱን ካልመስለ
እንደሚገል ስለሰማች ድምፆን አጥፍታ ስው ቤት ልብስ በማጠብ
እና በመለመን ስትተዳደር የኖረችው ነገር ግን ያቺ እንቡጥ
የወለደቻት ልጅ የእሱ እንደሆነ ሲያውቅ በእዚህ መልኩ ገደላቸው
ሎሌ ጊዲዮንን ያወቀው ይህንን ጉዳይ ሲያጣራ ነበር የእናት እና
ልጅን ደም ለማስመለስ ይጥር ነበር ነገር ግን የጊዲዮን አሽከር
ጊዲዮን በሚያረገው ነገር ሁሉ ህሊናው ስለወቀስው እና
ስላልቻለ ለጠበቃ እስማኤል ጉዱን ነገርበት ጊዲዮንም የራሱን
አሽከር ለእስማኤል እንደነገረበት ሲያውቅ በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለው
ብሎ አዳም ነገራት ። ዲና በደነገጠ እና በተረበሸ መንፈስ ሆና
አዳምን እየሰማችው ነበር በተጨማሪም ጊዲዮን ጠበቃ👇👇
✍ፍቅር፦በብዙ ፈታናዎች ተፈትኖ ብዙ እንግልትና የስቃይ ሰቆቃ ተይቶው የሚደርስ የደስታ ጥግ ነው።
#ፍቅር የማያልቅ ሀብትና ደስታ ነው።ሀብት እንደው ልናገኝ አንችልም ብዙ ያልፋል ብዙ ጥራትንና ትግልን ብርታት ጥንካሬን ይጠይቃል፤ ፍቅርም ብዙ ፈታናዎች ይጠብቃሉ በእሳት ነበልባል በጭስ በውለፍን ተፈትኖ ነው፤የመሪውን ደስታና ሀሴትን መውለድ መፈራት የሚችለው።
#መጀመሪያ ፍቅርን ከራሳችሁ ተማሩ ቀጥሎም ከራሳችሁ የተማረችውን ለሌሎችም አስተምሩ ከዚያም የሚመጣውን ፈታናን ለመቀበል ራሳችሁን አዘጋጅ፤ምክነያቱም ብዙ የፍቅረኞች ስተት ስንመለከት በፍቅር በነበሩበት ጌዜ ምንም ማንም የሚለያቸው የሌላቸው ይመስላሉ ነገረ ግን አንድ ፈታና እፊታቸው ስቀርብ ወደውኑ ይጠላሉ ይለያያሉ፤ምክንያቱም ምንድነው ብባል ፍቅርን ከጊዜው የደስታ ስሜት ብቻ ጋር አያይዘው ስለሚመለከቱ ነው።
#ፍቅረኞሞች የሆነችው በመካከላቸው ብዙ ፈታነና እንግልት እፊት ለፈተችው ስለሚጠብቃቸው ከወድውኑ አስቀድማችሁ የፍቅርን ስንቃቸውን ትዕግስትን፣ይቅርታ ባይነትን፣ሪሬን ይዛቸው ሰንቃችሁ የህይወትን ጉዞ መጀመር አለባቸው ❤❤❤❤❤❤❤❤❤☝👉☝👆💛👯👭💖💖💖💖💖💖from love zone💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖❤💖👬💑👪👫👭👯❤💋💛👆☝👋👉👋@Hayitiye
ሳይህ የምፈራው ❤️
ልቤ ሚደነግጠው ❤️❤️
ቃላቶች የሚያጥሩኝ❤️❤️❤️
ሳይህ የምፈዘው ❤️❤️❤️❤️
ባይኔ ምፈልግህ ❤️❤️❤️❤️❤️
ሳይህ ፈገግ ምለው ❤️❤️❤️❤️
ሁሉም በምክንያት ነው❤️❤️❤️
ስለምወድህ ነው ❤️❤️
@Hayitiye 🦋🦋🦋
😘አለሜ ነሽ😘
🔥ክፍል 9
✍ እድል
.
.
.
መኪናው ሲገለበጥ ግማሾቻችን ደነዝዘን ግማሾቻችን ጮክን
ሌሎቻችን ደሞ ለማምለጥ በመስኮት ሞከርን ግን አልሆነም
መኪናው ተገልብጦ ሁላችንንም ጣር እና ስቃይ ላይ ሆንን በጣም
ተስቃየን አንዱ ጓደኛችን በትንሽ ማቃሰት በኋላ ህይወቱ አለፈ
ከዛም በተራ በተራ ቀስ በቀስ የጣር ድምፅ ጠፋ ካንደኛው
ጓደኛዬ በስተቀር። ከዛም ከብዙ ስቃይ በኋላ የነብስ አድን
ሰራተኞች መጥተው ወደ ጣሬዛ እያርጉ በመኪና ይዘውን ሄዱ
ኡፍፍፍፍፍፍ ስቃይ ውስጥ ሆኔ ከጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩትን
እያስብኩ አዘንኩኝ በጣም እወዳቸው ነበር ልክ እንደ ነብሴ ከ
ነብሴ እኩል ብወዳቸውም የራሴን ነብስ እንጂ የእነሱን ማትርፍ
አልቻልኩም ለነገሩ የኔንም ነብስ ፈጣሪ በጥበብ ነው ያተርፍው
የአንደኛው ጓደኛዬን ጭምር አጋጣሚ እኛ ሁለታችን ከ ጋቢናው እና
ከኋላኛው ወንበሮች መሀል ያለው ወንበር ላይ ነበር የተቀመጥነው
መሀለኛው ቦታ ብዙ አልተጎዳም አለ አዳም ባዘነ ድምፅ ዲና
እየሰማች ሳታስበው ማልቀስ ጀመርች አልቻለችም አዳምም
አብሯት አለቀሰ አዳም እንባውን ጠርጎ ወደ ወሬው ተመለስ
እምምም እና ከዛ እኔ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ብቻ የሆነ ጊዜ
ላይ ካለሁበት ድንዛዜ ስነቃ ሆስፒታል ነኝ ሳሚን አየውት ሳሚ
ማለት መዝናናት የሚባል ነበር በጭራሽ የማይወድ እና ከራሱ
ጋር ጊዜ የሚያሳልፍ ሰው ነው በእዛ ምክንያት እኛ ለመዝናናት
ስንሄድ እሱ አልመጣም ነበር የሚለን ሁሌም እንዲህ አይነት
ነገሮች ላይ አይሳተፍም ሳሚን ሳየው ፈገግ አልኩኝ እሱም ፈጠን
ብሎ እ አንዴት ነክ ብሎ ረጋ ባለ መልኩ ጠየቀኝ እኔም በፊቴ
ደህንነቴን ገለፅኩለት ነርስ ጠርቶ እስኪመጣ እርፍት እንዳደርግ
እና አንድ ጓደኛው ከሻይ ቤት ቡና ልታመጣ እንደሄደች እና
እንደምትመጣ ነገረኝ ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ እሺ አልኩት ከዛም ሄደ
እንደሄደ በእጇ 2 ሻይ ይዛ መጣች ሳያት በጣም ደነገጥኩኝ
በጣም ልቤ ሲመታ ክፍሉን ያናወጠው መሰለኝ የፈጣሪ ያለ
እንዴት መጣች ብዬ ገረረመኝ ሄዋን ነበርች ደስስስ አለኝ ስታየኝ
ሞቅ ደመቅ ባለ ደምፅ እንዴዴዴዴ አዲዬ ፍቅር ነቃክ ብላ ጭምቅ
አድርጋ አቅፋኝ ማውራት ጀመረች የድምጿ ጩሀት እና
የተጫነችኝ ቁስሌን መቆጣጠር እስኪሳነኝ አቅፍኝ ስማኝ አዲዬ
አስደነገጥከን እኮ የኔን ውድ እያለች ትጨምቀኝ ጀመር ቢያመኝም
ህመሜን ዋጥ አደርኩት ምክንያቱም ስታቅፍኝ ካመመኝ ይልቅ
ስላቀፈችኝ ብቻ ደስታዬ በጣምም ትልቅ ስለነበር ከዛም ሁለቱን
አይኔን ግንባሬን ሁለት ጉንጮቼን እና አገጬን አንገቴን ያለ ፋታ
እያፈራርቀች ሳመችኝ ደስታዬ ወደር አልነበርውም የቁስሌም
ህመም በጣም አየለብኝ እእእእ ይቅርታ ግን ቁስሌን ስላት ኣ
ይቅርታ በጣም ስለተደስትኩኝ አላስተዋልኩም የሆነ ነገር ልንገርክ
አለችኝ እሺ አልኳት በጉጉት አፍ አፍፏን ማየት ጀመርኩኝ ቀኝ እጄን
ብድግ አድርጋ ልቧ ላይ አደርገችው የልብ ምቷን እጆቼን
አስጠግታ አስዳሰሰችኝ ልብዋ በጣም ይመታል እጄ ከ አካሏ ጋር ሲነካካ ትንፍሽ አጠራት ዲና አስቆመችው እና እሺ እና አንተስ አለችው አዳምም ቀጠለ የኔን ነገርማ ተይው እንደ ውሀ ፈስሼ እንደሻማ ቀለጬ ምንም አላልኩም ከዛ እሷ
በድጋሚ አይኔን ትኩር ብላ አየችው አየዋት የሆነ ነገር በለኝ
እንጂ አለችኝ ምን ልበልሽ አልኳት በፍቅር አይን አያየዋት አዲዬ
አፍቅርካለው ካላንተ መኖር አልችልም እያልኩክ እኮ ነው አለች
እንባ እየተናነቃት እየተናነቃት መጣና ማልቀስ ጀመርች
በጣም ደነገጥኩ እና በድንጋጤ ብድግ ብዬ እንባዋን ጠርኩላት
አቀፍኳት ለምን ታለቅሻለሽ አልኳት እንባዋን በእጄ እያበስኩ በጣም ደስስስ
ብሎኝ አለችኝ እኔም በምኑ ስላት እንደማፍቅርክ ስነግርክ አይንክ ውስጥ አንደምታፈቅረኝ ስላየው አላስቻለኝም እውነተኛ ግን ያልጠበኩት መልስ ስለሆነ በድጋሚ ደነገጥኩኝ ምንም ቃል ካፌ ሊወጣልኝ አልቻለም በውጤ ግን ለካ
ፍቅር እንዲ ነው? አልኩኝ ከዛም ህመሜ ተነሳብኝ አአ አ አአ ስል
ድንግጥ ብላ ምነው ምን ሆንክ ስትለኝ አይ ምንም ትንሽ አመመኝ
አልኳት እሺ እርፍት አድርግ በላኝ አመቻችታኝ ተኛው ግን እንቅልፍ
አልወሰደኝም ከዛ ትንሽ ቆይቼ እእ ስል ከወንበሯ ብድግ ብላ
ምነው አለችኝ አፍቅርሻለው ያላንቺ መኖር አልችልም እንዳትተይኝ
ልልላት አሰብኩና ፈራው አይ ተይው ምንም አልኳት ልቤ ግን ያለ
ማቋርጥ ይመታል ደስስስ እያለኝ መጣ ከዛ ስናወራ ሰው የሰማን ይመስልሻለል አልኳት እኔጃ ግን ለምን ጠየከኝ ስትለኝ አይ ምን አልባት ስላት ፊቷን አኮሰታትራ እ
መልስልኛ ምን ልትለኝ ነው ሰው ከሰማስ ምን ይሁን እ ንገርኛ
አለች እየጮከች ድምጿ እንኳን ጮሃበት እንዲሁም በጣም ጮክ
ያለ ስለሆነ ሽምቅቅ ድንግጥ አልኩኝ ክትክት ብላ መሳቅ ጀመርች
ግራ ገብቶኝ አፍጥጬ ዝም ብዬ አያት ጀመር ሳቋን ገታ አድርጋ
አትደንግጥ የጮኩብክ ላስደነግጥክ ነው ደሞ ተሳክቶልኛል
አይደል አለችኝ እኔም ቁስሌን በማይጎዳ መልኩ ስቄ በጣም
ጓበዝ ነሽ አልኮት አይዞክ አትደንግጥብኝ የኔ ፍቅር ጓደኛክ ደሞ
ነገ ነው የሚመጣው ቅድም ቡናውን ይዤ ወደክፍል ስመጣ
አግኝቼው እንዳይመጣ እና እኔ ካንተ ጋር ብቻዬን መሆን
ስለምፈለግ እንዳይመጣ ነግሬዋለው ሀኪሞቹም ካላመመክ
አይመጡም ማለቴ ካልጠራናቸው ጠዋት ነው የሚመጡት
አለችኝና በል አሁን ተኛ ብላ አደላድላ በድጋሜ አስተኛችኝ
ግንባሬን ሳመችኝና ወንበሯ ላይ ልትቀመጥ ስትል እጇኝ ያዝ
አረኳትና አጠገቤ ሁኚ አልኳት ት አላርም ቅጠሪና ዶክተሮች
ሳይመጡ ትነሻለሽ አልኳት ፈገግ እያለች እሺ ብላኝ ለሊቱን ሙሉ
ተቃቅፍን ተኛን ከሚያፍቅሩት ከሚወዱት ጋር መሆን እንዴት ደስስስ
ይላል ። አላርሙ ጩኸ አልስማነውም ነበር ጠዋት ዶክተሩ
ሊያየኝ ከ ነርሷቹ ጋር ሲመጣ አየን ሁሉም በስሱ ፍገግ ብለው
ቁልቁል ሲያዩን ጀመር አይኔን ስገልጥ እና ሳያቸው ደነገጥኩኝ
ሄዋንም ተነሳች ግን እሷ ምንም አልመስላትም ደና አደራቹ ብላ
ዘብነን ብላ ጉንጮቼን ስማኝ እርቦኛል ቁርስ በልቼ እመጣለው
ውዴ ብላኝ ወጣች ብሎ አዳም ንግግሩን ገታ። ዲና አዳምን
ኮስተር ብላ እያየችው እንዴ ቀጥልልኛ አለችው ብዙ አስወራሽኝ
የቀር ረው ለነገ ይሁንልሽ ነገስ ማን አለው አላት እሺ አለችው ዛሬ
አላስጨነቀችውም ሄዋን ክፍል ተያይዘው ገቡ። ሄዋን ጣራ ላይ
አይኗን ልክ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ስው ተክለዋለች አተኩሮም
ሆነ ሳያተኩር ላያት አንድ በጣም ትንሽ ነገር ጠፍታት ወዴትም
እንዳትሄድ ጠብቂያት የተባለች ትመስላለች አዳም እና ዲናን
አላየቻቸውም በመጨርሻ ዲና እህም እህም ብላ ከተመስጦዋ
አነቃቻት ሄዋንም ሁለቱንም እያፈራርቀች አየቻቸው ከዛም አዳም
ላይ አይኖን ጥላ ቀርች አፈጠጠች አስተያየቷ የፍቅር ነው ልክ
ከአደጋው በፊት እንደምታየው አስተያየት አዳም እንባው በአይኖቹ
ሊወጡ ክፉኛ ታገሉት ታገሉት ከዛም አዳም ክፍሉን በፍጥነት ጥሎ ወጣ ሄዋንም በደከመ ድምፅ እናንተ ማናቹ አለቻቸው ዲና ምን እንደምትል ጠፍባት
ተርበተበተች ከዛ...
ይቀጥላል...
••●◉Join us share
@Hayitiye
ፍቅር👩❤️👨 በአጋጣሚ 🦋♥️
Hayitiye ቻናል ገራሚ
#ፎቶዎች 📂
#የፍቅር_መልክቶች📜
#ቪዲዮ 📀
#ደብዳቤዎች📝
#የልብን_የሚናገሩ_ሙዚቃዎች 🎶🎶
#ሌሎችንም..........
Administrators & create
👇👇👇👇 👇👇👇
@MarSilas_23 @Hayitiye
Join&share
Be happy
Be smile
https://t.me/hayitiye
#ግዛቸው_ተሾመ🔥🔥
#እንዴት_ሰራት 😊🔥🔊
ምን ይሆን ሚዛኑ የተፈጥሮ ልኳ እንደ ቀጥር ፀሀይ ያቃጥላል መልኳ ወርዳ ከላይ አየው ፀሀይ☀️😊
ቃሌን የምሰጥህ ለፌሽታህ ብቻ አልነበረም ህመምህን ልታመምልህ እንጂ……
ቃል የምገባልህ ሰፈገግታህ ብቻ አልነበረም እንባህን ላነባልህ እንጂ……
ግን አይገባህም ነበር💔
@Marsilas_23🥀
“እናቴ እወድሻለሁ፤ ፈጣሪ እድሜ ከኔ ቀንሶ ይስጥሽ” ሲል የነበረዉ ልጅ “እናቴ ትሙት የምሬን ነዉ በጣም ነዉ የምወድሽ” ብሎኝ ነበር ዛሬ ግን የለም🙆♀
#ብቻ_ነፍሰ_ገዳይ_በዝቷል_ለማለት_ነው
@Hayitiye 🦋🦋🦋🦋
ሁሌ ደስተኛ ነሽ ታድለሽ አለኝ
ፈገግ አልኩለትና😁
በውስጤ ወይ ታድለሽ
ውስጤን አንዴ ቢያይ
ይታዘበኝ እና አስመሳይ ሚለውን ማእረግ ይቸረኝ ነበር😁😆😅
አደል😇
@Marsilas_23 🥀
