403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
አንዷ ላጤነት ስልችት ብሏት የሰፈሯን ወጠምሻ ጉልበተኛ ልጅ አግብታ ቤተሰቦቿ የጥሪው ካርድ ላይ የፃፉት ጥቅስ...
የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን🤣🤣
የህይወትህ መጥፎ ጊዜ
ጥሩ ነገሩ ምን እንደሆነ ታውቃለ፤የሰዎችን ትክክለኛ ማንነት ታውቅበታለህ።
እና ልክ እንደእኔ ታዝበህ ዝም ትላቸዋለህ,
@eiduka
ብዙ ጊዜ ከምንወዳቸው ሰዎች የተሰጡን ትንንሽ ነገሮች ከነበሩን ውድ ነገሮች በላይ ዋጋ ያላቸው ይሆናሉ።
ምክንያቱም እኛ ዋጋ የምንሰጠው ለስጦታዎቹ ሳይሆን ለስጦታዎቹ ባለቤቶች ስለሆነ ነው!!!!
በዋጋ ሲተመን ትንሽ ዋጋ ያለው ስጦታ
በዋጋ የማይተመን ስሜትን ያንፀባርቃል!!!
-@eiduka
🥀🥀🥀
አንዲት ውብ ፅጌሬዳ ከግንዷ ተለይታ ከወደቀች በኃላ ስታብብ ሳይሆን ስትደርቅ ነው ምናያት 😔 አበቃ ! ሚስተካከል ትላንት ወይም አሁን ወይም ነገ የላትም. . አለቀ!
እራሴን ኮረኮምኩት ቀጣይ ያንቺ ተራ ቢሆንስ ? ፣ ነገ ወይም በኃላ እረ አሁንስ ምን እደሚፈጠር ታውቂያለሽ ?? የራሴ ጥያቄ ለራሴው አስተጋባ . . 🙄 ምን ትፈልጊያለሽ ? ባትኖሪና ድጋሚ እድትኖሪ እድል ቢሰጥሽ ምትቀጥይው ድርጊት እየሰራሽ ነው 😳😔
አሁን ነፍሴ ዝም
እያለች ስመጣ ተሰማኝ
ምን ላይ ናቹ ?
ቀጥሎ የእኛ አይደለም 🤷♀. . . በዚች ህይወት ምንም እርግጠኛ ነገር የለም!
👉even 1ሰዓት ላይ እየተነፈስክ
1:30 ትንፋሽክ ልትቆም ትችላለክ ህይወት ይሄን ያህል ናት🤷♀
#edu
@eiduka🦋
🦋@eiduka23
@eiduka🦋
አራዳው የጻፈው የስራ ማመልከቻ ደብዳቤ ነው።
ዲር ማናጀር አማን ነው? ክብሩ ይስፋ፣ አንተ አትከፋ፣ ምቀኛሽ አንገቱን ይድፋ፣ ድርጅትሽ ይስፋ፤ እኛ ምችት ብሎናል ይኸው አራት አመት ወጥረን ቸክለን ካምፓስን ቻው ብለን ቀሚሶችን ገላልበን ጋውን ለብሰን ፋሚሊን ሀፒ አስነክሰን ጀል ጀል እያልን ሰፈር ገብተን አቦ ሚስማር እየቃምን ቦዛ እየቀመቀምን ዱቅ ካልን አመት ሊያልፈን ነው።
ጀለሴ እሙች ..... ኧረ ምን በወጣሽ እኔ ልሙት የሰፈር ሼቦች የሌለ መሬ ብለዋል በቃ ሲሄዱ እርግማን (እዛው ባህር ዳር ሰምጠህ በቀረህ) ሲመለሱ ስድብ (እዚህ ዲንጋይ ላይ ለመቀመጥ ነው አራት አመት የተወዘወዝከው።) ኧረ ታክቶናል። እና የኔ ማኛ እእ... በቃ አለ አይደል ማዘርም ደንፉ እየጫረች ስለሆነ እእእ ቺኳም ስለጫነች ምናምን ሳቢ ግድ ይላልና ያው በፈጋውባት ፊልድ የድርጅቱ ባሉካ አንቺ ስለሆንሽ የሆነች ቦታ ሰካ ብታደረርጊኝ ያው ደስ ይለኛል።
@eiduka
SHARE👉@eiduka
በህይወት ስትኖር ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች
1. የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው።
2. ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ።
3. ስትፈልገዉ ያጣከውን ሲፈልግህ ታገኘዋለህ ።
እኔ ከእኔ 👀
🙎♀edelህልምሽ ምንድንነው?
ለመሆኑ ተስፋ አለሽ?🤔 አላማሽስ? አይ አይ የለሽም
🙍♀እንዴ አለኝ😔
🙎♀ቢኖርሽ ኖሮማ ጊዜሽን እንደዚ አታባክኝውም ነበር
ህይወትሽ ላይ አትቀልጂም ነበር🤨
🙆♀እሱማ አዎ🥺ለምን እንደምኖር ለማን ስል እንደምማር አላውቅም።🙉
እኔነቴን ከማይወክሉ ሰዎች መራቅ እፈልጋለሁ። ግን ምን ብዬ እንደምርቃቸው አላቅማ
መቼስ አልፈልጋችውም አልላቸው ነገር፤
ጨነቀኝ እኮ እኔ አላማ ካለው ሰው ጋር ነው ህብረት መፍጠር የምፈልገው ግን እምችለው አይደለማ።
🙅♀አይ አንቺ ካሰብሽበት የማይቻል ነገር የለም እሺ የኔ ቆንጆ😘
🙇♀እሱስ ልክ ነው ግን....☹️
🤦♀ግን የሚባል ነገር የለም በቃ አትፍሪ ፍርሃትሽን ተይው!😤
👱♀እህህ ማለት እንዴት ነው ተፈጥሮዬን የምቀይረው እንዴ ፍርሃትንማ መቀየር አልችልም😲 👩አይ አትሸወጂ ተፈጥሮሽ አይደለም ሆ ተፈጥሮ ቢሆንማ ኖሮ ልጅ እያለሽ ለምን አትፈሪም ነበረ።😑
👱♀እሱማ አዎ😔ግን ሁፍፍፍ በጣም ይከብዳል ያሰብኩት ቦታ መድረስ🗣
👩አይከብድም 😡
👱♀እኔንጃ ብዙ የሚያዘናጉኝ ነገሮች አሉ እነሱን መጋፈጥ አልችልም በቃ በቃ🙅♀
🙎♀አይበቃም በደንብ አስቢበት ቆንጂት😈
🤷♀እሺ በቃ አሁን ልተኛ👋
👱♀አረ ላሽ😳 ተይ ግን እድል አሁንም ልተኛ ትያለሽ አጥኚ እንጂ ቢያንስ ግጥሞችሽን አንብቢ ትምህርቱ ከሰለቸሽ🤗
👱♀ኡፍፍ🙄እኔ መተኛት ብቻ ነዋ የሚያስደስተኝ
🙎♀ላንቺማ ፀበል ያስፈልግሻል 😳አየሽ ለዚ ነው እኮ የማትለወጪው ትርፉ ድካም ብቻ።
🤦♀ካልተኛው እኮ ማሰብ የማልፈልገውን ነገር እንዳስብ እገደዳለሁ ምን ላርግ በእንቅልፍ ውስጥ ሰላም አለ እኮ ለዛ ነው።💔
🧏♀በቃ እሺ እንደፈለግሽ አንቺን ተከራክሮ ማሸነፍ ዘበት ነው።🏃♀
👆እራሴው ከራሴው ያወራውት፧ አንደኛዋ እኔነቴ🧐 ፧ከሌላኛዋ ጋር 😛
@eiduka23🤎
💖 @eiduka
@eiduka23💞
💓@eiduka
ዝለለው!!
ለሱ መገኘትህ
ግድ ለማይሰጠው
እሱን ሰው ዝለለው
አትለማመጠው
ባንተ ለጎደለ
ዙርና ተመለስ
በካፊያ ሽንገላ
"ሞላሁ" ላለ አትፍሰስ !!
@eiduka🦋
#ታዉቂያለሽ_ግን?❤️🔥
አንቺ ጋ ስገናኝ ቀኑ ያጥርብኛል
ደሞ ሥንለያይ ወዳዉ ይከፍኛል
የቀረሽ ቀን ደሞ ህመም ይሠማኛል
አይንሽን ካለየሁ እንደ እብድ ያረገኛል
ብቻ ምን ልበልሽ አለሠራ ብሎኛል
ሀሳቤ አንቺ ሆነሽ ማሠብ አቅቶኛል
አንቺን ያየሁቡት ቀኑን ባላዉቀዉም
አጋጣሚም ቢሆን ፈፅሞ አልጣለዉም
ይገባሽ ይሆናል አንድ ቀን አምናለሁ
ባንቺ ፍቅር ምክንያት እኔ እንደተጎዳሁ
💖💖💖💖💖💖
@eiduka🦋
።።።።።♥️ሳይበረታ ድረስ♥️።።።።።
አየኸው ዝናቡን አንተን ሲያስታውሰኝ
ካለፈው ትዝታህ ወስዶ ሲመልሰኝ
ተመለከትክልኝ የብርዱንስ ብርታት
አንተን እያስመኘ ሲናፍቅ ቀን ከሌት
አስተውለኸዋል የበረዶውን ዶፍ
ወደነዛ ቀናት የዃሊት ሲያከንፍ
አየህልኝ ውዴ ክረምቱ በረታ
ልቤም አንተን አለኝ ፍቅርህ ልቤን ረታ
ታድያልህ አለሜ............
ናፍቆትህ በርትቶ ካልጋ እንዳላድር
በትዝታህ ባህር ሰምጬብህ ሳልቀር
ዝናቡ ሳይጠና ብርዱም ሳይጠነክር
ሳይበረታ ድረስ ህመሜም እንዲሽር።
✍eidu
@eiduka🦋
እሱን ተይው ..... 🤦♂
ስትወጅው ካልወደደሽ
ስትቀርቢው ካልቀረበሽ
ስትጠጊው ካልተጠጋ
ስለፍቅር ካላወጋ
አይሆንሽም እሱን ተይው
አትድከሚ ላታገኚው
ማፍቀርሽን እያወቀ
በፍቅራችሁ ካልፀደቀ
በቃልሽ ላይ ካላመነ
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድሽ እየኮራ
የውሸት ፍቅር ከሚሰራ
ልብሽ ይቁረጥ እሱን ተይው
ላንች ላይሆን አትወትውችው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@eiduka🦋🦋
❣#ናፈከኝ💓
♥ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ
ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ❤🩹
ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ💕
💗የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው
ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው
በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት
ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት❤🔥
💗ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር💞
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር❣
ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ 💖ባስተውለው
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ❤
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ
አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ
የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ💞
ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ💖💔💞
@eiduka 🦋
@eiduka23🥀
