403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
🌺 ቅምጥሏ 💋
ቅምጥል አፍቅሬ ፣
ለሷ ተቸግሬ
ኩሽና እንዳትገባ ፣ ካልጋ እንዳትነሳ
ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ፣ ሳስብላት ለሷ
የእንጀራ ጠርዝ ጣቷን ፣ እንዳይቆርጣት ብዬ
አጉራሽም ቀጠርኩኝ ፣ አሳቢ መስዬ
ቅምጥሏን ፍቅሬን ፣ ድንገት ቢያስነጥሳት
ይማርሽ የምትል ፣ ሞግዚት ቀጠርኩላት
የሞልቃቃ ነገር ፣ መጨረሻው አያምር
ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ፣ ውስጤን ስላየችው
ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ፣ ብላኝ አረፈችው።
😂😂😂
ፈገግ በሉበት 😀😀😀😀
@eiduka
።።።።።።አጠይቁኝ ይቅር💔።።።።።።
ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር
ሁሉን ብነግራችሁ ላይገባችሁ ነገር😕
እንዴት አትበሉ ለማወቅ ጓጉታችሁ
ነገሩን ብታውቁ ምንም ላይጠቅማችሁ
አጠይቁኝ እኔን ትላንትስ ብላችሁ
ታሪኬን የዃሊት እያስታወሳችሁ😡
የት ነበርሽ አትበሉ አታብዙ ጥያቄ
የትስ እንደነበርኩ እኔ የት አውቄ
ምላሼን በመሻት ጥያቄ አታብዙ
ዃላ ብነግራችሁ ብዙ ነው መዘዙ
አታድሙት ቁስሌን በሾክ ወጋግታችሁ
የማያባራ ደም ጉድ እንዳይሰራችሁ😔
ዝምታዬ ጎልቶ ስሜት ካልሰጣችሁ🙍♂
አላደክምም ራሴን አንዱም ላይገባችሁ🤦♀
ስለዚህ እባካችሁ።።።።።።።
አጠይቁኝ ይቅር የለኝም መልሳችሁ።🤷♂🤷♀
🦋🥀🦋
@eiduka23
Join share
@eiduka
🍂🍂🍂
በአንድ የአበባ ማምረቻ ውስጥ የምትሰራ ሰላምተኛ ሴት ነበረች። በገባች በወጣች ቁጥር ሃላፊውንም ጥበቃውን ሳትመርጥ ሰላም ትላለች። አንድ ቀን ውስጥ እየሰራች ትልቅ የአበባ ፍሪጅ ስታጸዳ በሩ እላይዋ ላይ ይዘጋል። የስራ ሰዓት መውጫ ደርሶ ሁሉም ወደ ቤቱ ሄደ። ማንም የሚደርስላት አልነበረምና በቅዝቃዜው እየደከመች መጣች። ድንገት ያለወትሮ አንድ ጥበቃ ውስጥ ከፍቶ ገብቶ የፍሪጁን በር ሲከፍተው ውስጥ ያገኛትና አውጥቶ ወደ ህክምና ወስዶ አተረፋት። ደህና ስትሆን እንዴት ባልተለመደ ሁኔታ ከስራ ሰዓት ውጭ ውስጥ ገብቶ ፍሪጅ እንደከፈተ ስትጠይቀው፣ ስትገባ ስትወጣ ሁሌም ሰላም የምትለን ሴት ዛሬ የት ጠፋች? ደህና እደሩ ሳትለን ሄዳ አታውቅም ትለን ዛሬ ምን ሆና ነው? ብዬ ልፈልግሽ ወጣሁ አላት። የመልካምነት ትንሽ የለውም። ሰውን በመልካም ፊት መቀበል ምን ያህል ውለታ እንደሆነ ሰው የራበው ሰው ያውቀዋል። "በጎ ነገር ግንባርን ከመፍታት ይጀምራል።" መልካምነት ውስብስብ አይደለም። ቅንነት ቀላል ስራ ነው።
🦋🥀🦋
@eiduka
https://t.me/eiduka
የህልሜ ንጉስ ❤️
አንተ የህልሜ ንጉስ የተስፋዬ ስሬት
ሁሌም የማስብክ የፍቅሬ ተምሳሌት 🥰
ፍቅርን ያወኩብክ እውነተኛን ስሜት
አላርፍ አለ ልቤ አንተ የሌለህበት😔
አንተን ሳላይ ውዬ ትንፋሽ ከሚያጥረኝ
ሳላገኝክ ውዬ እኔን #ከሚጨንቀኝ
በናፍቆት ሰክሬ እኔን ከሚያመኝ
ናልኝና ፍቅሬ አንተው መላ ስጠኝ😊💓
መናገር #ቢያቅተኝ ላንተ ያለኝን ስሜት💘
#መተንፈስ ቢያቅተኝ ላንት ያለኝን እውነት
ውስጤ ያለው #ፍርሀት ሁሌም ቢያሸንፈኝ😧
#መናገሬ አይቀርም አንድ ቀን ጠብቀኝ❤️🔥
🦋🥀🦋
@eiduka23
@eiduka
💔ይናፍቅሽ ይሆናል💔
....የሚወድሽን ሰው አትራቂ፣ ስላንቺ የሚያስብን ሰው እና በንጹህ ልቡ የወደደሽን ሰው አትግፊ፤ ምክንያቱም አንድ ቀን ሰው ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብሽ ያ ሰው ይናፍቅሽ ይሆናል!💔
መልካም ምሽት 🙏
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━
@eiduka 🦋🥀🦋
🌹 "አንቺ እና አበባ" 🌹
እንኳን እሺ ብለሽ
ፍቅሬን ተቀብለሽ
.
አንኳንስ አጠገቤ ከጉያዬ ተኝተሽ
እንኳንስ አካሌ ደረቴ ላይ አርፈሽ
ፍቅርሽ ይርበኛል ከኔ ርቀሽ ሄደሽ
.
.
በአይኖችሽ ውበት
ሺ ገለሽ ሺ ማርከሽ
በተክለ ቁመናሽ
አፍዘሽ አደንዝዘሽ
.
.
የአንደበትሽ ለዛ የድምፅሽ ስርቅርቅ
የከንፈሮችሽ ውበት የጥርስሽ ፍልቅልቅ
.
.
የሀገራችን ወንዞች ቢወርዱ ቢወርዱ
እንዳንቺ ፀጉሮች
በንፋስ ታግዘው ንፋስ አያበርዱ
.
የአለማችን ሀይቆች መሬትን ቢያርሱ
ከፀጉሮችሽ ጫፍ አንዱንም አይደርሱ
.
.
ደሞ ፊትሽን ምን ይሆን ያበራው?
ፀሀይ እና ጨረቃ እንዳይጣሉ ፈራሁ
እነሱ ሚወጡ ሁሌ በፈረቃ
ለራሴ ባዘንኩኝ በፍቅር
በዉበት ሁሌ የምንቃቃ
.
.
የአበባ ጥቅሞች ሁለቱ ቢገቡኝ
አንደኛው ወደድኩት አንደኛው ፈራሁኝ
.
.
ልብሽ ቢፈልገኝ እሺታሽ ራቀብኝ
ኮኮብ ከጨረቃ ብታይም አርቅቀሽ
እንድላይ እንድንሆን ብትወስኝ ዘግይተሽ
.
.
አታኩርፊ ውዴ ምንም አልከፋኝም
ከእላዬ ተኝተሽ ጠረንሽ ቢርቀኝም
.
.
ከአበቦች መሀል ብትሆኝብኝ ልዩ
ከቶ እንዳታለቅሺ ቢሉም ተለያዩ
.
.
.ከአበባ ጥቅሞች እንደኛው ነው ልዩ
ለካ ከላይ ይነጠፋል ህይወት
በቃኝ ብለው በሞት ለተለዩ!!😥
🦋🥀🦋
@eiduka
@eiduka
ናፍቀሽኛል ሆዴ😞
መንገድሽ መንገዴ
ሆኖ የዘለቀው
ፍቅርሽ ስለገዛኝ
ባሪያሽ ስለሆንኩ ነው
ሆዴ ናፍቀሽኛል
ምፈልገው ቢሟላ
የጠየኩትንም ባገኝ
አልጠግብም እኔ
አይንሽ ነው የራበኝ
ፍቅር ናፍቀሽኛል
ሆዴ ናፍቀሽኛል
አንቺን ለማግኘት
ልቤ አጥብቆ ይመኛል
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ Share ❤️❤️❤️
@eiduka
(አሳዛኝ ታሪክ)
አንዲት ሴት ለፍቅረኛዋ ያለእሷ አንድ ቀን እንዲኖር challenge ትጠይቀዋለች፣ ምንም ሳያወሩ ሳይገናኙ ቀኑን ካሳለፈ ለዘላለም እንደምታፈቅረው ትነግረዋለች እሱም ይስማማል።
በቀጣዩ ቀን ፍቅረኛዋ ቀኑን ሙሉ መልእክት ሳይልክ ሳይደውል ዋለ ግን ያላወቀው ነገር ቢኖር ፍቅረኛው በካንሰር በሽታ ምክንያት ለመሞት 24 ሰአታት ብቻ ነበር የቀራት
በቀጣዩ ቀን ልጁ ወደፍቅረኛው ቤት ሄደ
"አደረኩት የኔ ፍቅር🥰" አለ ግን ከመቀፅበት ከአይኖቹ የእንባ ዘለላዎች ወረዱ ምክንያቱም ፍቅረኛው በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነበረች😔 ለመጨረሻ ጊዜ የፃፈችለት ደብዳቤ ይህ ነበር....." አደረከው ፍቅሬ በል አሁን ሁልቀን አድርገው እሺ እወድሀለው"❤️
@eiduka
@eiduka
