403
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
😁#ባል ፦ ሹፌሬን ላባርረው ነው..ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ አጋጭቶኝ ገድሎኝ ነበር
#ሚስት ፦ አንድ የመጨረሻ ዕድል ብትሰጠው ምናለበት 🙄....
መስታወት፡- አትጨነቅ፣ በአለባበስህ አልስቅም..
😁ትራስ: አትጨነቅ፣ እንባህን እይዛለሁ..
ሙዚቃ፡- አትጨነቅ፣ ስሜትህን እይዘዋለሁ..
አልጋ፡- አትጨነቅ፣ ሲደክምህ እዚህ ነኝ..
ህልም: አትጨነቅ፣ከእውነታው እጠብቅሃለሁ..
ዝናብ፡- አትጨነቅ ከአንተ ጋር ለማልቀስ እዚህ ነኝ..
🌑የሌሊት ሀሳቦች🌑:- ምሽቱ እንዴት ይዟቾኃል....
@eiduka🦋
😄😄😄 አንዳንድ ወንዶች እና ሴቶች የመለያያያ ሠበባቸው
1,😂 አስራ ስድስት ሚስኮል በማረግ ባትሪዬን ገደልሽው ይሄንን እኔን ለመግደል ከመሞከር ለይቼ አላየውም የፍቅር ጊዚያችን እዚጋ ያበቃል!!
2, 😂አንቺ ለኔ ምንም ክብር የለሽም እኔ አወራለው አንቺ ትተነፍሻለሽ የኔና ያንቺ ጉዳይ እዚጋ ያበቃል!!!
3 , 😂ስደውልልሽ ገና ሳይጠራ ታነሽዋለሽ ይሄ ትዕግስት የለሽነት ያሳያል ከዚ በኋላ አልፈልግሽም!!!
4 , 😂የሞቀ ምግብ እንደምውድ እያወክሽ አይስክሬሙን አላሞቅልህም ብለሻል የኔና
ያንቺ ጉዳይ እዚጋ ያበቃል!!!
5 , 😂ሁለት እንቁላል ሰጥቼሽ አንዱን ጥበሽልኝ፣ አንዱን ቀቀይልኝ ስልሽ ጥበሽልኝ ያልኩሽን ቀቀልሸው፣ ቀቀይልኝ ያልኩሽን ጠበሽው አንቺ የኔን ትዕዛዝ ስለማታከብሪ ከዚ በኋላ ላይሽ አልፈልግም!!!
6 , 😂11:59 ሜሴጅ ልኬልሽ 12:00 ነው የመለሽልኝ ይሄ አንድ ቀን መሉ ቆይተሽ መመለስሽ ለኔ ያለሽን ንቀት ያሳያል ስለዚህ አልፈልግሽም!!!
7 . 😂እኔ የኔ ውድ ብዬ ጠራሁሽ፣ አንቺ ደሞ የኔ ማር ብለሽ መለሽልኝ ይሄ ማለት በሌላ
መንገድ እናትህ ንብ ናት እያልሽ ነው አንቺ ለአማቾችሽ ክብር ስለሌለሽ ሻንጣሽን ይዘሽ ከቤቴ ውጭልኝ!!!
@eiduka 🦋
የትኛው ንግግር ልብ ይሰብራል? 💔💔
1, ሁለተኛ አጠገቤ ድርሽ እንዳትል
2, ከአንተ የተሻለ ሌላ ወድጃለሁ
3, አንተ ለኔ አትመጥንም
4, ላይህ አልፈልግም አስጠልተኸኛል
Comment.....
@eiduka 🦋
ስወድሽ ውደጂኝ😍
ውዴ.....❤️
እኔ አንቺን መውደዴ
መጥፎ እድል አይደለም ችግር የሚያመጣ😊
ወንጀልም አይደለም በህግ የሚያስቀጣ😇
ሀጢያትም አይደለም አንገት የሚያስደፋ
ሰማይ ቤት አትቆምም ነብሴ ተጠይቃ-ትዕዛዝ ተላልፋ
ታድያ አንቺን መውደዴ ምን ላይ ነው ጥፋቱ?😒
ወደድኩሽ ማለቴስ ምንድነዉ ክፋቱ?☹️
ጠልተሺኝ እንዳይሆን ቁርጡን እንዳላውቀው
እንደምትወጂኝ ነው ውስጥሽ 'ሚያሳብቀው።🤷♂
ታድያ እየተዋደድን አንድ ሆኖ ውስጣችን
ለምን እንራራቅ እንሁን ለብቻችን😐
ስለዚህ ውድዬ.......🥰
ባንቺ ጨርቅ ሳልጥል ወይ ሳታሳብጂኝ🤕
በፍፁም ተማምነን ሳልከዳሽ ሳትከጂኝ
-- ሳልጎዳሽ ሳትጎጂኝ♥️
መራራቁን ትተሽ ስወድሽ ውደጂኝ🤗
✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑
@eiduka🦋
የኔ ያልኩትን ሰው በፍቅር ያየሽው
እንደምን ብለሽ ሞትን ተመኘሽው
ማርያምን ብያለው ደግሜ አልምልም
እሱንማ ደፍረው ካዩብኝ አልምርም
✨@eiduka
፡ ከዛም ባሻገር ህይወት አለ…🖤
በድቅድቅ ጨለማ በዝናብ በታጀበ ምሽት ማሀል ብቻችንን ሆነን እየተጓዘን ነው…የደበራትም ትመስላለች…የህይወት መንገድ ያደከማት…ሁሉም ነገር ያስጠላት…የመኖር ትርጉምም የጠፋት…ጐኔም ቁጭ ብላ በግራ እጇ በያዘቺው እንጨት መሬቱን እየጫረች የልቧን ሀሳብ ታወራኛለች…
" ትዝ ይልህ ከሆነ…የሆነን ቀን ሁላችንም እምንኖረው የተፃፈልንን ነው ብለህኝ ነበር…ታዲያ ፈጣሪ ግን ምን አድርጌው ነው ይህን ለእኔ የፃፈልኝ…እያማረርኩ ደሞ እንዳይመስልህ…ለበጐም ነው ብለህም እንዳሸነግለኝ…አሁን ላይ የምሬን ነው እምልህ የእውነት ነው የደከመኝ!…ማረፍም እፈልጋለው(ማረፍ ሁለት ነው ትርጉሙ)…እረጅም እረፍት…እፎይም ማለት ናፍቆኛል…ባይገርምህ ግን ፊላ እንደ አንተ ብሆን እላለው…ሁሉም ነገር ለበጐ ነው ብዬ ባስብ እና ነገን ብናፍቅ……"
እኔ ግን እንደምታስበኝ ነኝ እንዴ?…ነገንስ እናፍቃለው? …ሁሉም ነገርስ ለበጐ ነው ብዬ ነው እማስበው?…ብቻ የልቧን መሻት ፈጣሪ ይሙላላት…የኔ ታራ የቃላት ድርደራም ከገባችበት ድባቴ እንደማያወጣት አውቃለው…ብቻ የድንግል ማርያም ልጅ እሱ ያሳርፋት…
#eidu
@eiduka
ከፍቅር በላይ❤🔥💔❤🩹
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወራሽው ወሬ፣
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ፣
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል፣
ያልሽውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል፣
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን፣
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን፣
ሁሉን ሰምቻለሁ ማን ምንስ እንዳለኝ፣
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ፣
ምንም ይሁን ምን፣
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም፣
እውነቱ ግን ይሄ ነው እኔ አላፈቅርሽም፣
እኔስ አልወድሽም፣
እርግጥ ነው አልክድም.....
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለሁ፣
እድል ያለቀናኝ ለት ያላየሁሽ እንደሁ ጭንቄን አምጣለሁ፣
ያየውሽም ከሆነ እንደረጋ ወተት በደስታ እናጣለሁ፣
እርግጥ ነው አልክድም....
ያ የሰፈራቹ ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሃል ሲሰድብሽ ስሰማ፣
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው እሮጫለሁ ጠብቄ ጭለማ፣
ደሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛዬ የለከፈሽ ለታ፣
ደም ፍላቴ መጥቶ አዝንቤበታለሁ የቡጢ ጋጋታ፣
እርግጥ ነው አልክድም....
ሳገኝሽም ስየ ሳጣሽም ከፍቶኛል፣
አንቺን ብቻ እያየሁ በመንገድ ሳቀና ስልክ እንጨት ገጭቶኛል፣
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል፣
እርግጥ ነው አልክድም.....
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለሁ፣
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለሁ፣
አዝነሽ ያየውሽ ቀንም ደም እምባ አልቅሻለሁ፣
ይህንም አልክድም፣
ምንም ቢሆንም፣
እኔ አንቺን አልወድም፣
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም፣
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም፣
ይህ ፍቅር አይደለም፣
ይህ መውደድ አይደለም ፣
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ፣
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ፣
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደይ፣
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በይ፣
ከመውደድ በላይ ነው የወደደኝ በይ፣
Join
🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢
ሼር 💚
@eiduka
@eiduka
እኔ ማነኝ ቆይ ፖሊስ ወይስ ዳኛ
በሰው ላይ ምፈርደው የእግዜሩ ጠበኛ😒
ኑሮን ለማሸነፍ ሲራወጡ ላይ ታች
እኔ የማነኝ ዝፍዝፍ እነሱን ተመልካች ።
enja😜
@eiduka
ስርዙ ደብዳቤዬ
በዳብዳቤዬ ላይ ፣ ልነግርሽ ያሰብኩት ፣
አስቤ የፃፍኩት ፣ ፅፌ የሰረዝኩት ፣
ሰርዤ የላኩት ።
ስርዝ ድልዝ ሆኖ ፣ አልነበብ ካለሽ ፣
ሳልሰርዘው በፊት ፣ ምን ይላል መሰለሽ ፣
መግቢያው መደምደሚያው ፣ ሀተታው በሞላ ፣
ሌላ አይናገርም ፣ አንቺን ከማፍቀሬ ከመናፈቅ ሌላ።
❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥❤️🔥
@eiduka
እብድ ቤቷን አቃጥላ አሁን በራልኝ አለች" አሉ
የሆነች እብድን አስቧት ከቤቷ ቁጭ ብላ ድንገት ጭልምልም ቢልባት ጨለማው ቢከብዳት እቤቷን አቃጠለችና እሷቱ ሲነድ አሁን በራ መብራት መጣ ብላ ስትፈነድቅ ያዩ አንድ አዛውን እብድ ቤቷን አቃጥላ አሁን በራልኝ አለች አሉ !!
፣
ለእብዷ ቤቷን ማቃጠሏ ለጨለማው መፍትሔ መስሏታል ግን ቤት አልባ አደረጋት ፡፡ አንዳንድ መፍትሔ የምንለው በራሱ የበለጠ ችግር ውስጥ የሚከተን ከህይወት ገፅ የሚፍቀን ይሆናል ፡፡
፣
ኢቺው ናት የኛ ኑሮ የጠበቅነው ሲቀር የሞከርነው ሳይሳካ መፍትሄ የሚመስለን ራስን ማጥፋት ነው ፡፡ ራስን ማጥፋት ብርሀን መስሎ ስለሚታየን ነው እድላችን የቋጠርነው ገመድ ውስጥ ያለ እየመሰለን አንገታችንን ለገመድ ልንሸልም ተዘጋጀ ፡፡ አንድ እውነት ልንገርህ የቆምክበት ቦታ ካልተመቸህ ተንቀሳቀስ አንተ ዛፍ አደለህም !!
፣
የሚያስብልኝ የለም ብለህ አትዘን አለም የውድድር መድረክ ናት ሁሉም ስለራሱ ነው የሚያስበው ስለዚህ እስኪያስቡልኝ ብለህ ራስህን አትጣል ላንተ ካንተ የተሻለ ሰው የለም ፡፡ አንተ ልዩ ነህ ያንን ሁሉ አሳልፈህ በዚህ አትሸነፍ ፡፡
፣
ዶፍ ዝናብ የወረደበት ለካፊያ አይደነግጥም ይባል የለ ስለዚህ ችግርህን አትሸነፍለት ፡፡ ሁሌም ይመሻል ይነጋል ሳይነጋ የቀረ ምሽት የለም ፡፡ በአዲስ ቀን ውስጥ አዲስ ሰው ሁን ፡፡ ሁሌም ወደፊት ብቻ ተራመድ አትሸነፍ ንቃ ተንቀሳቀስ ለረዥም ጊዜ አንድ ቦታ የተኛ ውሀ ይሸታል ፡፡
፣
ንቃ ወዳጄ ፀጉሬ አደገ ብለህ ጭንቅላትህን አትቁረጥ ችግር ደረሰብኝ ብለህ ራስህን አታጥፋ ህይወትን አጣጥማት አትሸነፍላት ህይወትን የታገለ ነው የሚጥላት !! ጠንካራ ሁን መከራህን ተሻገር ያኔ ሌሎችን ማሻገር ትችላለህ !!!
🦋🥀🦋@eiduka
