cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Our World

Show more
Ethiopia6 339Amharic6 107The category is not specified
Advertising posts
833Subscribers
No data24 hours
-67 days
-3830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በስዊዘርላንድ የ11 ዓመት እድሜ ያላቸው ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት እንዴት እንደሚጠቀሙ ስለማያውቁ ዳይፐር አድርገው ወደ ትምህርት ቤት እየመጡ መሆናቸው ተነገረ በስዊዘርላንድ ልጆች ትምህርት የሚጀምሩት በ4 ዓመታቸው ሲሆን ዳይፐር አድርገው ወደ ትምህርት ቤት መምጣታቸው የተለመደ ነገር ነው። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በአውሮጳ ሀገራት በርካታ መምህራን እየተጋፈጡ ያለው ችግር ይህ አይደለም።  ዕድሜያቸው 11 ዓመት የሆናቸው ተማሪዎች ሳይቀሩ ዳይፐር አድርገው ወደ ትምህርት ቤት እየመጡ መሆኑን አስተማሪዎች አስታውቀዋል። በስዊዘርላንድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተማሪዎቹን ማጽዳት እና ዳይፐር መቀየር ይጠበቅባቸዋል።መምህራን ባስተላለፉት መልዕክት ወላጆች  ከበጋ በዓል በኋላ ወደ ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን ሲልኩ ያለ ዳይፐር እንዲመጡ እና የልጆችን ዳይፐር የመቀየር ሃላፊነት መመህራን እንደሌለባቸው ገልፀዋል። በስዊዘርላንድ የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዳግማር ሮስለር እንደተናገሩት ወላጆች ለትምህርት የደረሱ ልጆቻቸው ዳይፐር እንዳይጠቀሙ  የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብለዋል። "የ11 አመት ልጆች ዳይፐር አድርገው ወደ ት/ቤት ሲመጡ ይህ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ብለዋል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጆች ዳይፐር በስፋት እየተጠቀሙ መሆኑን ተከትሎ የዳይፐር ማስታወቂያ እየጨመረ ሲሆን በስዊዘርላንድ ለ 11 ዓመት ልጆች የሚሆኑ የትላልቅ ዳይፐር ሽያጭ መጨመሩ ሌላኛው አሳሳቢ ምልክት ሆኗል።የዳይፐር ምርቶቹ ይበልጥ ምቹ እየሆነ መምጣት እንደ መደበኛ የውስጥ ሱሪዎች ሊለበሱ መቻላቸው ሌላኛው ፈተና ነው። በዚህ የተነሳ ልጆች ዳይፐርን  ሙሉ በሙሉ ልክ ነው ብለው እየተቀበሉ ይገኛል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
የሞባይል ስልኩ ግድብ ውስጥ የገባበት ባለስልጣን 2 ሚሊየን ሊትር ግድብ ውሃ እንዲለቀቀ አደረገ ለባለስልጣኑ ስልክ ሲባል ከግድብ የፈሰሰው ውሃ ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መስኖ የማልማት አቅም ነበረው ተብሏል። ህንድ አንድ ባለስልጣን ሰልፊ ፎቶ ራሱን ለማንሳት ሲሞክር ስልኩ ወደ ግድቡ ውስጥ ይገባበታል። ይህ የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን 1 ሺህ 200 ዶላር ዋጋ ያለቀው ሳምሰንግ የእጅ ስልኩ ወደ ግድቡ ገብቶብኛል፣ ስልኩ በርካታ እጅግ አንገብጋቢ የመንግስት መረጃዎችን ይዟል በሚል ግድቡ እንዲመጠጥ አስደርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ባለስልጣኑ መጀመሪያ ላይ ስልኩን ለማስወጣት በአካባቢው ያሉ ዋናተኞችን ቢያሰማራም አለመገኘቱን ተከትሎ በውሃ መሳቢያ ፓምፕ የግድቡ ውሃ እንዲመጠጥ አስደርጓል ተብሏል። ራጂሽ ቪሽዋስ የተባለው ይህ ባለስልጣን ስልኩን ለማግኘት ሲባል ባለሙያዎች የግድቡን ውሃ ለመምጠጥ እና ለማፍሰስ ሶስት ቀናት እንደፈጀባቸው ተገልጿል። በመጨረሻም የባለስልጣኑ ስልክ ቢገኝም በውሃ ተሞልቶ የመስራቱ ነገር አጠራጣሪ ነው የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በህንድ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህን ተከትሎም የሐገሪቱ መንግስት ባለስልጣኑ በፈጸመው ድርጊት ስልጣኑን ያለ አግባበብ በመጠቀም ከስራ የታገደ ሲሆን ጉዳዩ አሁንም መነጋገሪያነቱን ቀጥሏል ተብሏል። ለዚህ ባለስልጣን ሲባል እንዲመጠጥ እና እንዲባክን የተደረገው ውሃ ከስድስት ሺህ በላይ ሄክታር መሬት መስኖ የማልማት አቅም እንደነበረው ተገልጿል ሲል አል ዓይን ዘግቧል። ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ! ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot የሚለውን ይጠቀሙ! ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!!
Show all...
ለልጃቸው ሰርግ የገዟት ላም ሲሳይ ይዛ መጣች! በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ ደዋሮ ቀበሌ ልዩ ስሟ «አካሌ ባድማ» በተባለች መንደር ልጃቸውን ለመዳር በ18 ሺህ ብር  የገዟት ላም 40ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያለው ማዕድን ለባለ ሰርጎቹ አበርክታለች። በበህር ዳር ከተማ የጋፋት ወርቅ ቤት ባለቤት አለልኝ ማተቤ ማዕድኑ በተለምዶ ወርቅ ይባል እንጂ ወርቅ አይደለም፣ ዋጋው ግን ከወርቅ ማዕድን በእጅጉ ከፍ ያለ እንደሆነና በዋናነትም ጃፓነችና ቻይናዎች እንደሚገዙት ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ማሞ በበኩላቸው በአንዳንድ የቆላማ አካባቢዎች በሚገኙ እንስሳት አልፎ አልፎ የሐሞት ጠጠር ይፈጠራል፤ ሆኖም ይህ ነገር በተለምዶ ወርቅ ይባል እንጂ ወርቅ አለመሆኑን ያስረዳሉ። ፕሮፌሰሩ፥ እንደዚህ ዓይነቱ የሀሞት ጠጠር  ወደ ቻይናና ጃፓን አገር እንደሚሸጥ እንደሚያውቁ ጠቁመው ለምን አገልግሎት እንደሚውል ግን በትክክል እንደማያውቁ ነው የተናገሩት። የወርቅ ባለሙያው አቶ አለልኝ ማተቤ ራሳቸው ከዚህ በፊት ከእንስሳት የተገኘውን ይህን የአሞት ጠጠር እስከ 80ሺህ ብር ገዝተው እስከ 100ሺህ ብር ሸጠው እንደሚያውቁ አመልክተዋል ሲል ዘገባው ያመለክታል፡፡ @tikvahethmagazine
Show all...
በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ 👉ወርቁ 21 ሺህ 500 መቶ ብር ተሽጧል በምስራቅ አርሲ ለትንሳኤ በዓል የገዙት በሬ ለእርድ በሚቀርበበት ሰዓት በሀሞቱ ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ መገኘቱን የጢዮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ግረማ ጣፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ ግለሰቦቹ  ኩማ ተሰማ እና ንጉሴ ዲንቃ የተባሉ ሲሆን ለበዓል ቅርጫ በ38 ሺህ ብር በሬ ገዝተው  በሚያርዱበት ወቅት  በበሬው ሃሙት ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ አግኝተዋል። ወርቁ ሃያ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር መሸጡ ተሰምቷል። ከቀናት በፊትም በዚሁ አካባቢ 18.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ በበሬ ሀሞት ላይ ስለመገኘቱ እና ወርቁን 53 ሺህ ብር ስለመሸጡ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው እንዳሁኑ ይፋ የወጣ ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ  በበሬዎች ሃሞት ላይ ወርቅ ስለመገኘቱም ኮማንደር ግርማ ጣፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
በኢትዮጲያ ባለፉት ሶስት ዓመታት በኮቪድ -19 ከ7500 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል በኢትዮጲያ በሶስት ዓመት ውስጥ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ሲያዝ ከ7500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ። ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በኮቪድ -19 በሽታ 500 ሺ 774 ሰዎች ሲያዙ ከነዚህም ውስጥ 7574 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል ። ክትባት በሶስት ዙር የተሰጠ መሆኑንና የተፈናቀሉ እና እስረኞች የክትባት ተከታታይ ተጠቃሚነት ላይ ቁጥሩ ዝቅተኛ እንደሆነ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ኤክስፐርት የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ አየለ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል ። በዓለም ላይ በኮቪድ -19 በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እንደሚጠቁ የተገለፀ ሲሆን ምክንያቱ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ እና ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል ። በተጨማሪ በዓለም ከ685 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲያዙ ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ መረጃዎች ያሳያሉ ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
ለቅርጫ ከታረደ በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ተገኘ! በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል።በሬውን በ40 ሺሕ ብር የገዙት ተቃራጮቹ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺሕ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺሕ ብር ማትረፍ መቻላቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡ ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል፡፡ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል። @YeneTube @FikerAssefa
Show all...
ከፀሐይ ክብደት 30 ቢሊየን እጥፍ የገዘፈ በርባኖስ ተገኘ‼️ በአፅናፈ-ሰማይ ላይ ከተዘረጉ በርካታ “ጋላክሲዎች” ይልቅ የገዘፈ በርባኖስ ወይም ጥልቁ ጥቁር ጉድጓድ “ብላክ ሆል” መገኘቱን የእንግሊዝ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዶክተር ጀምስ ናይቲንጌል የተመራው የእንግሊዙ ዱርሃም ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን ያገኘው በርባኖስ የፀሐይን ክብደት በ30 ቢሊየን ጊዜ እጥፍ የሚልቅ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ተመራማሪወቹ ይህን ያክል መጠን ያለው በርባኖስ መገኘቱን እንግዳ እንደሆነባቸውም ነው የጥናት ቡድኑ መሪ የሚናገሩት። በህዋ ላይ ከሚገኙ አካላት በመጠኑ ትልቁ ነው የተባለው ይህ በርባኖስ እንደ ሚልክዌይ (ፀሐይን ጨምሮ የፕላኔቶችን ስብስብ በያዘው) ጋላክሲ ባሉ ትላልቅ ጋላክሲዎች መሃል ላይ እንደሚገኝም ይታመናል። የበርባኖሱ ግኝት ከዳር እንዲደርስ ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ የጀርመኑ ማክስ ፕላንክ ኢንስቲትዩት ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም የናሳው “ሃብል ቴሌስኮፕ” ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምሥሎች በማንሳት እና ትርጉም እንዲያገኙ ለዱርሃም ዩኒቨርሲቲ በመላክ በሱፐር ኮምፒዩተር በርባኖሱ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ጥናቱ ትናንትና ይፋ የሆነው በሮያል የሥነ-ፈለክ ማኅበር መሆኑንም አር ቲ ዘግቧል፡፡ በርባኖስ ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር “ብላክ ሆል” በኅዋ ላይ ያለ ጥልቅ ጉድጓድ ሲሆን ከፍተኛ የስበት ኃይል ያለውና ብርሃን እንዳይታይ አድርጎ የማስቀረት ዐቅም ያለው መሆኑን የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ።
Show all...
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከ6ኛ ፎቅ የወደቀችው ሰራተኛ በህይወት ተረፈች። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዕድሜዋ 40 የተገመት አንዲት የሆስፒታሉ ሰራተኛ ትላንት ሌሊት 10:30 ላይ ከ6ኛ ፎቅ ላይ "ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል" ሲል የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥሪ የተደረገውም፥ ከ6ኛ ፎቅ ወደ ታችኛዉ ወለል ወደ ቤዝመንት ዉስጥ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ መሆኑ ተገልጿል። የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በህይወት ማውጣት ችለዋል። ተጎጂዋ ከአደጋዉ በህይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል ተብሏል። ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ስራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን እንደነበር ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በተያያዘ ዜና በትላንትናው ዕለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታ አትላስ አካባቢ ግንባታዉ በተጠናቀቀ ህንጻ ላይ ቀለም በመቀባት ላይ ያሉ ሰራተኞች የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦዉ ተበጥሶ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጉዳት የደረሰባቸዉ አራት ሰዎች በኮሚሽኑ አምቡላንስ  ዘዉዲቱ ሆስፒታል ተወስደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ሲሆን ጉዳት ከደረሰባቸዉ ዉስጥ አንዱ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ነዉ። አደጋዉ በአጋጠመበት ጊዜ አራቱም ተጎጂዎች በሊፍቱ ላይ እንደነበሩ ኮሚሽኑ አስታውቋል
Show all...
የሶርያ ጦርነት 12 ዓመታትን አስቆጠረ (ረጅም ፅሁፍ) እንዴት ተጀመረ? መጋቢት 15 ቀን 2011 በሶርያ ዴራ፣ ደማስቆ እና አሌፖ ጎዳናዎች ላይ ከፍተኛ ብጥብጥ ተቀሰቀሰ፤ ተቃዋሚዎች ዲሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲደረግ እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቁ። ለተቃውሞ መቀስቀስ ምክንያት የሆነው ከጥቂት ቀናት በፊት በዴራ ከተማ ፕሬዝዳንት አል አሳድን ለማውገዝ አደባባይ የወጡ በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን በማሰር እና በማሰቃየት ነበር። ተቃውሞውን ተከትሎ በሶርያ መንግስት ከፍተኛ ርምጃ እና ጭቆና ተከተለ። እ.ኤ.አ. በሀምሌ 2011 ከሶርያ ጦር ኃይል የከዱ ሀይሎች መንግሥትን ለመገልበጥ ዓላማ ያለው የነፃ የሶሪያ ጦር መቋቋሙን አስታውቀው አመፁን ወደ እርስበርስ ጦርነት ለወጡት። እ.ኤ.አ. በ2012 ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በዓመቱ በመላው አገሪቱ የተለያዩ አማፂ ቡድኖች ብቅ አሉ። በዚያው በ2013 አመት መጨረሻ ላይ የአይኤስ መነሳት በሰሜን እና በምስራቅ ሶሪያ እንዲሁም በርካታ የኢራቅን ግዛቶች በመውረር ፈተናው የሰፋ ሆነ። ከአስራ ሁለት አመታት በፊት የሶርያ መንግስት ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ጎዳናዎች ላይ ደፍረው በመውጣት መንግስት እና ፕሬዚዳንቱን ባሽር አል አሳድን በመቃወም ነበር የእርስ በእርስ ጦርነቱ የተጀመረው። ተቃውሞዎቹ በፍጥነት አብዮታዊ ተፈጥሮን ይዘው “የአገዛዙን ውድቀት” ጠየቁ፣ ነገር ግን ከመንግስት ሃይለኛ ምላሽ በኋላ ህዝባዊ አመፁ ወደ ጦርነት ተቀየረ፣ ብዙ የውጭ ሃይሎችን እየጎተተ ሚሊዮኖችን አፈናቅሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገደለ። በጦርነቱ የተነሳ የሶሪያ ኢኮኖሚ እያሽቆለቆለ መጥቷል፣ አሁን ላይ 90 በመቶ የሚሆነው የሶርያ ህዝብ ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖር የዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያሳያል። የሶርያ ቀውስ ከተጀመረበት ከመጋቢት 2011 ጀምሮ በሀገሪቱ ከ306,000 በላይ ንፁሀን ዜጎች ወይም ከሶርያ ህዝብ 1.5 ከመቶ ያህሉ ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው አመት ያወጣው አሃዛዊ መረጃ ያሳያል። መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን በበኩሉ በጦርነቱ በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 610,000 እንደሚደርስ ገምቷል። በየካቲት ወር ሰሜን ምዕራባዊ ሶሪያን ካወደመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 14.6 ሚሊዮን ሶሪያውያን ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል፣ 6.9 ሚሊዮን ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቅለው የሚገኙ ሲሆን ከ5.4 ሚሊዮን በላይ የሶሪያ ስደተኞች በጎረቤት ሀገራት ተገን ጠይቀው ይኖራሉ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በጀርመን እና በሌሎች የአውሮጳ ህብረት ክፍሎች እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ጥገኝነት ጠይቀዋል። በሶርያ የሚገኙ ተፋላሚዎች እነሆ እነማን ናቸው? 👉 የሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሽር አል አሳድ እ.ኤ.አ. ከ1971 ጀምሮ በስልጣን ላይ ከነበሩት አባታቸው ሃፌዝ አል-አሳድ ስልጣኑን ተረክበው ሀገር መምራት የጀመሩት በ2000 ዓመት ነበር። ሀገሪቱን በብረት መዳፍ በመምራት ተቃዋሚዎችን በማፈን የኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም በሺዎች በማሰር እና በማሰቃየት ምዕራባውያኑ ክስ ቢያቀርቡባቸውም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶርያውያን ግን በደማስቆ ቤተመንግስት መቆየታቸው እንደሚያስደስታቸው ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። 👉 ነፃ የሶሪያ ጦር (FSA) ወይም የሶሪያ ብሔራዊ ጦር የሚባለው እ.ኤ.አ በ2011 ከሶሪያ ጦር በከዱ እና በቱርክ እንዲሁን በበርካታ የአረብ ሀገራት በሚደገፉ ሲቪሎች የተቋቋመ የታጠቁ ብርጌዶች ስብስብ ነው። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2016 ከአሌፖ ጦርነት ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ውስጥ የኢድሊብ ውስን ቦታዎችን ቡድኑ እንደተቆጣጠረ እስካሁን ቆይቷል። 👉 በጦርነቱ ሌላኛው ተፋላሚ ሀያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) ሲሆን ቀደም ሲል ጀብሃ ፈታህ አል ሻም ወይም ጀብሃ አል-ኑስራ ተብሎ ይጠራ ነበር። ጀብሃ አል-ኑስራ የአል-አሳድ መንግስት ተቃዋሚ ሲሆን የአልቃይዳ አጋር ሆኖ በ 2011 ተመስርቷል።በአሁኑ ጊዜ ይህ ኤች ቲ ኤስ የተሰኘው ቡድን "ማንኛውንም ድርጅት ወይም ፓርቲ የማይከተል ገለልተኛ አካል" መሆኑን ይገልፃል። 👉 ሌላኛው የጦርነቱ ተዋናይ ሲሆን ሂዝቦላህ ሲሆን የሺአ የታጠቀ ቡድን ነው። ሂዝቤ በሊባኖስ እና በኢራን የሚደገፍ የፖለቲካ ሃይል ሲሆን የፕሬዝዳንት አል-አሳድን መንግስትን ለመደገፍ ወደ ሶሪያ የገባ ሀይል ነው። በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ውስጥ ምንም አይነት ግዛት አይቆጣጠርም። 👉 የሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች (ኤስዲኤፍ) ይህ ቡድን የኩርድ እና የአረብ ሚሊሻዎች ጥምረት ሲሆን የተመሰረተው በ2015 ዓመት ነበር።በአብዛኛው የYPG ተዋጊዎችን እና የአረብ፣ የቱርክ እና የአርመን ተዋጊዎችን ቡድኑ ያካትታል። ቱርክ ግዛት ገንጥሎ የኩርዶች ሀገር ለመመስረት የሚንቀሳቀሰው ይህው ቡድን ከ1984 ጀምሮ ከ40,000 በላይ ሰዎችን የገደለ የትጥቅ ዘመቻ ከአንካራ መንግስት ጋር አድርጓል።በኤስዲኤፍ ቁጥጥር ስር የሶርያ ዋና ዋና ከተሞች የሆኑት ራቃ፣ ኳሚሽሊ እና ሃሳኬህ የተሰኙ ከተሞች በቡድኑ እጅ ስር ይገኛሉ። 👉 አይኤስ አይኤስ በውጭ ተዋጊዎች የተደራጀው ይህው ቡድን የመንግስት ስርዓት የፈጠረ እና በጠንካራ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴው ይታወቅ ነበር። ይህው ቡድን እ.ኤ.አ በ2014 በግምት አንድ ሶስተኛውን የኢራቅ እና ሶሪያን ግዛቶች ተቆጣጥሮ የነበረ ቢሆን ከ2019 ወዲህ ድባቅ ተመቷል። 👉 በሀገራት ደረጃ የሩሲያ መንግስት ዋንኛው የደማስቆ አስተዳደር ደጋፊ ሲሆን ሞስኮ በአሁኑ ወቅት በሶርያ የጦር ሰፈር ገንብታ ከባሽር አላሳድ ጎን ትገኛለች።ኢራን በተመሳሳይ ከሶርያ ጎን ተሳፋለች። 👉 ቱርክ የባሽር አላሳድ ወዳጅ የነበረች ቢሆንም በአመፁ መነሻ ወቅት ከአቋማ ተንሸራታ የዋይፒጂን ታጣቂዎች ለመውጋት በሚል የሶርያ ታጣቂዎችን በምድሯ እስከማስታጠቅ ደርሳ ነበር።አሜሪካ የደማስቆ መንግስት ከስልጣን እንዲነሳ ታጣቂዎችን በመርዳት በጦርነቱ ሚናዋ ከፍ ያለ ነበር። ጦርነቱ በሶርያ በዩኔስኮ ከተመዘገበችው የቤልና የባአል ሻሚ ቤተመቅደሶች መገኛ ፓልምይራ ከተማ እስከ ቱርክ ድንበር የምትጋራውን ኢድሊብን አፈራርሷል።በነዳጅ ሀብቷ ዝነኛ ከነበረችው ዴር አዝ ዞር ከተማ አንስቶ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ የተመሰረተችውን ራቃን 80 በመቶ መሰረተ ልማት አውድሟል።የሶርያ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ከተማ አሊፖ የወንበዴዎች መሸሸጊያ አድርጓታል። ከ12 ዓመታት በኃላ ታዲያ ምን አዲስ? ዛሬም የሶርያ ፕሬዝዳንት የዓይን ሀኪሙ ባሽር አላሳድ ናቸው።ለፕሬዝዳንቱ ጀርባ ሰጥተው ግንኙነት አቋርጠው የነበሩ የአረቡ ዓለም ሀገራት ዳግም ወዳጅነቱን ፈልገዋል። ኤምሬትስ በድማስቆ የዘጋችውም ኤምባሲ በድጋሚ ስትከፍት አል አሳድም አቡዳቢ ደርሰው ተመልሰዋል።ግብፅ፣ ኦማን፣ ኢራቅና ሊቢያ ወዳጅነታቸውን አጠናክረዋል።ሶርያ ወደ አረብ ሊህ እንድትመለስም ሂደቱ ተጀምሯል።ዳግም ከ12 ዓመት በፊት ሶርያ ወደነበረችበት ትመለሳለች።መቶሺዎች ሲገደሉ ሚሊዮኖች ስደተኛና የአካል ጉዳተኛ ሆኑ፣ንብረት ሲወድም፣ኢኮኖሚው ሲናጋ፣ፍርሃት ሲነግስ ከዚህ ሁሉ የእልቂት አዙሪት በኃላ ግን እየነጋ ይመስላል። እውነታው ደግሞ የተለወጠ የተገኘ አዲስ ድል ግን የለም።
Show all...
ከ20 ሚሊዮን በላይ ሴቶች የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ አያገኙም ተባለ! በኢትዮጵያ የወር አበባ ከሚያዩ ከ35 ሚሊዮን ሴቶች ውስጥ 22 ሚሊዮን ወይም 75 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ እንደማያገኙ የአደይ የሴቶች የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ መሥራች አስታወቁ። የአደይ የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ መሥራች ወይዘሮ ሚካል ማሞ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአደይ የሴቶች የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ (ፓድ) ምርት በኢትዮጵያ ያለውን የሴቶች የወር አበባ የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ይረዳል። በዚህም ያለውን ከ20 ሚሊዮን በላይ ቁጥር ለመቀነስ እንዲሁም የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ይረዳል። ለዚህም አደይ ፓድ አንዱ የንጽሕና መጠበቂያ በአንድ የወር አበባ ኡደት ሁለት ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ በአጠቃላይ አንድ መቶ ጊዜ መታጠብ የሚችል መሆኑን መሥራቿ ተናግረዋል። ይህ ድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ያለውን የምርት እጥረት ከመቅረፍ ባለፈ የዋጋ ንረቱንም ሊቀንስ ይችላል ብለዋል። ይህ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ለሰውነት ተስማሚ ከሆነ ግብዓት የሚሠራ ምቹ የሆነ ፣ፈሳሽ የሚችል፣ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑን የጠቀሱት መሥራቿ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለ5ሺ ሴቶች የሚደርስ ንጽሕና መጠበቂያ እንደሚመረት ተናግረዋል። እርሳቸው እንዳሉት፤ አንዲት ሴት በወር አበባ ምክንያት በአማካኝ ከሦስት እስከ አምስት ቀናት ከትምህርት ወይንም ከሥራዋ በንጽሕና በአቅርቦት እጥረት ምክንያት ትስተጓጎላለች። ለዚህም በትኩረት ሴት ተማሪዎች ላይ እየሠሩ ይገኛል። ይህም ምርት ከ18 እስከ 24 ወራት የሚያገለግል በመሆኑ በወር አበባ ምክንያት ከትምህርቷ ሳትስተጓጎል እንድትገኝ የሚያደርጋት ይሆናል። የትኛዋም ሴት የንጽሕና መጠበቂያ በማጣት ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ ይሁን ከአስፈላጊ ሥራዎቿ መቅረት የለባትም የሚሉት ወይዘሮ ሚካል እስካሁንም በሀገሪቱ ለሚገኙ ከ300 ሺ በላይ ሴት ተማሪዎች ንጹሕ የሆነ የንጽሕና መጠበቂያ በመሥራት ተደራሽ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል። ዋናው ችግራችን አብዛኛው ግብዓት ከውጭ የሚመጣ በመሆኑ የቀረጥና የግብር ጉዳይ መፍትሔ አለማግኘቱ ነው ሲሉም ተናግረው እንዲሁም የቦታ ጥበት እንዳለባቸው አስረድተዋል። ሴቶችን ማብቃት ሲባል የመጀመሪያው ነጥብ የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ ማቅረብ ነው። ለዚህም መንግሥት ይህንን የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ ዋጋ ንረት ለመቅረፍ እንዲሁም ተደራሽነቱን ለመጨመር ምርቶቹን እንዲሁም የምርቶቹን ጥሬ እቃ ከቀረጥ ነጻ ማድረግ እንዳለበት ጠይቀዋል። እንደ ወይዘሮ ሚካል ገለጻ፤ ያለውን የወር አበባ ድህነት ለመቅረፍ ፣ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ እና ተደራሽ እንዲሆን የተለያዩ ንቅናቄዎች የተደረጉ ሲሆን ከነዚያም ውስጥ ‹ቀረጥ ይወሰንልን ፣ ዋጋ ይተመንልን›፣ ‹ሰብዓዊ መብቴን አትቅረጹ›፣ ‹አበባ አየሽ ወይ ትምህርት ቤት ትሄጃለሽ ወይ?› የሚጠቀሱ ሲሆን አይ ኬር ኢትዮጵያ እና ጀግኒት ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እንደሚሠሩ ወ/ሮ ሚካል ገልጸዋል። Via EPA
Show all...