cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የግጥም ማህደር

👉👉እንኳን ደህና መጡ 👈👈 🌟ለየት ያሉ እና የተለያዩ የግጥም አይነቶች 🌟 ⭐ የሚያገኙበት ቻናል ⭐

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
210
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የግእዝ ልሳንን በድሮ ጊዜ አንድ ባለስልጣን ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ይህ ባለሥልጣን አንድ ጎበዝና ጠንካራ ወደሆነ ገበሬ ቤት ወታደር ይልካል። " ካፈራኸው ወተት፣ እርጎ፣ ቅቤና አይብ ላክልኝ" ብላችሁ ንገሩት ብሎ ይልካል። ወታደሮቹም የተባሉትን ሊያደርሱ ሄዱ ከጠንካራው ገበሬ ቤት። ደርሰውም "ጌታችን ካፈራኸው ወተት፣ እርጎ፣ ቅቤና ወተት ላክልኝ ብሎኻል" ይሉታል። ገበሬውም የተባለውን ትቶ ወተት ብቻ ላከለት ለባለስልጣኑ። ባለሥልጣኑም በጣም ይናደድና "ያንን ትእቢተኛ ገበሬ አምጡልኝ" ብሎ ወታደሮቹን ላከ። ወታደሮቹም ሄደው የተባሉትን ሰው እያዳፉ እያቃኑ አመጡት። ባለሥልጣኑም "እንዴት ብትንቀኝ ነው ወተት፣ እርጎ፣ ቅቤና አይብ ላክልኝ ብልህ ወተት ብቻ የላክልኝ?" ይለዋል በንዴት እየተንተከተከ። ገበሬውም "አዎ ጌታየ ያልኸኝን ሁሉ ልኬያለሁ" ይለዋል በኩራት። ባለሥልጣኑም በጣም ተናዶ ሀሀሀሀ... ብሎ የንዴት ሳቅ ሳቀና........ "እንዴት ብትንቀኝ ነው ወተት ብቻ ልከህ ሁሉንም ልኬልሃለሁ የምትለኝ" እያለ ወደ ገበሬው ፊት ቀረበ ለመምታት እየቋመጠ። ገበሬውም የባለሥልጣኑን ዓይን እያየ.... "ጌታየ በወተቱ ውስጥ ሁሉም ነገር አለ። ወተቱ ሲረጋ እርጎ፣ ወተቱ ሲናጥ ቅቤ፣ ከቅቤው በኋላ ደግሞ አይብ ይገኛል። እንዲያውም ሳትለኝ አሬራ ጨምሬልሃለሁ።" አለው። ባለሥልጣኑም በገበሬው ጥበብ ተደነቀና ሸልሞ አሰናበተው ይባላል።፨ ፨ አዎ ወገኖቼ ግእዝ ወተት ነው። የኢትዮጵያ ማንነት የተመሰረተበት፣ ምሥጢራት የተከተቡበት፣ ሥነፈለኩና ሥነ ጠፈሩ የተደጎሰበት፣ ሥነ ብዕልና ሕክምና ጥበቡ የተቀመረበት፣ የሃይማኖት ነገራት የተመሰከሩበት፣ የአዳም ብሎም የመላእክት ቋንቋ የሆነ፣ሜ ነገረ መለኮት እስከ ነገረ ፍጥረታት የተከተበበት፣ እጅግ እልፍ አእላፍ ምስጢራትና ኩነታት የተጻፉበት እጅግ ወተት የሆነ በውስጡ ብዙኃን ነገራትን የያዘ ቋንቋ ነው። አያችሁ ጓደኞቼ ፈረንጆቹ ግእዝን በዩኒቨርስቲያቸው እስከ ማስተርስና ዶክትሬት ድረስ ማስተማር ከጀመሩ 200 (፪፻) ዓመታትን አሳልፈዋል። በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን መቅደላ ላይ እንግሊዝ ብቻ በ200 (፪፻) በቅሎና ከ20 (፳) በላይ ዝሆን ብራና መጻሕፍትን ጭና ነው የተመለሰች። በውጪ ሀገር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብራናዎች ተዘርፈው እየተመራመሩ ሁሉን ነገር እየሰሩ ለእኛ ይሸጡልናል። የሚቀመሙ መድኃኒቶች፣ ናሳ የሚነግረን ፕላኔቶች፣ የኮምፒውተር ቀመር ሁሉንም ከግእዝ እየተረጎሙ በእንግሊዝኛ ለኛ ይልኩልናል። ለዚህ ነው ጀርመናዊው ግእዝ ችሎ ኢትዮጵያዊው የሐገሩን ቋንቋ ግእዝን ሳይችል የፈረንጁን ቋንቋ ሲናገር የሚውለው። እኛ እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ቻይንኛ መናገርን እንደ ሥልጣኔና እንደ እድገት ቆጥረን ስንኩራራ እንውላለን። ትልቅ ምስጢር የነበረው ግን ንቀን ከተውነው የግእዝ ቋንቋ ነው። ሀገራችን የመውደቋ፣ ያለማደጓ ምስጢር ከዚህ ላይ ነው። የራሷን ማንነት ጥላ የሰውን አንጠልጥላ እየሮጠች ስለሆነ። የአሥር ዓመት ልጅ ልብስ ለሃምሳ ዓመት አዛውንት ሊሆን አይችልም። ቢለብሰው ጠቦት ይቀደዳል። የ50 ዓመቱን ሰው ልብስ 10 ዓመት ልጅ ቢለብሰው አይሆነውም ይደብቀዋሎ፣ ጠልፎ ይጥለዋል... ኢትዮጵያም የራሷን ነገር ወዲያ ወርውራ የምዕራቡን ጥበብና ቋንቋ በመያዟ ይሄው እስካሁን ባለችበት አለች። ትልቁ ነገር ራስን መሆን ነውና ወደ ጥንቱ ቋንቋችን እንመለስ ምስጢራትን እንመርምር ለማለት ነው። "ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር.. ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ #ሼር @eth_top
Show all...
"Ahun bezi seat kechen guwadegnawan besekar deferea deweye lanagerat ? keldun degemilegn bakesh enem lesak beye lelemenat? "... Join Now 🔻@Sleenee🦋 #comment 👉🏾@Yohannn #size_only_2mb
Show all...
Kamst 4 kilo YoHannes.ogg2.14 MB
ልጠይቅሽ እቴ . . እስቲ ልጠይቅሽ መልሽልኝ እቴ ከድፍረት ሳትቆጥሪው ንገሪኝ በሞቴ ላንቺ ማለት ውበት ማማር መቆናጀት ያልተሰጠን ጠጉር በጎረምሳው አይን ዞማ አርጎ ለመሳል በፈረሶች ጭራ ሲገመዱ መዋል ያልተሰጠን ቅላት የዘመኑን ቅባት ሁሌ በመቀባት ፊትሽን በማንጣት ካንገት በታች ጠቁሮ መምሰሉ ዳማነት ይህ ነው ላንቺ ውበት?? ወይስ ቅንድብ እየላጩ በርሳስ ማደማመቅ ከላብ ጋር እንዳይወርድ ቀን ሙሉ መሳቀቅ ባልታወቀ ቀለም ከንፈርን መለቅለቅ ደቃቅ ዱቄት መሳይ እፊት ላይ ማጣበቅ ጡትሽን በእስፓንጅ አክብቦ ማድቦልቦል ካርቶን አቀራርፆ ዳሌን ማሞናደል ይህ ነው ላንቺ ውበት? ጠዋት እና ማታ ቀን እና መኝታ ፍፁም መለያየት መሆን ሁለት አይነት እግዜር በፈጠራት በንጥል ሰውነት ይህ ነው ላንቺ ውበት ማማር መቆናጀት?? @fetslaw24 ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @yexbbalm @yexbbalm @yexbbalm #Join & @shre
Show all...
. . ከመዳፍ ለማትበልጥ እርም ታክል ጫንቃ ከሰማይ ስባሪ የገዘፈ ኑሮ ጭኖብን ሲያበቃ ሀበሻ እንቅልፋም ነው ከተኛ ማይነቃ ብሎ ማማት ይብቃ ልላቸው ብፈቅድም ተው አታነካኩኝ ፖለቲካ አልወድም ፤ ህዝቡ ንጉስ ወዳጅ በጎጥ በመንደሩ ጧት ማታ ያነግሳል ያልበሰለ ንጉስ በንግግር ብቻ ሀገርን ያፈርሳል ሴራ እንደ መረብ እያደናቀፈ በሾህማ መዳፍ ስትወድቅ እያቀፈ እንዳሸን እንዳሻን ባያረማምድም ዝምታ ነው መልሴ ፖለቲካ አልወድም ፤ እውነት እንደ ሹመት በንጉስ ይወድቃል በንጉስ ይፀድቃል ያንድ ዘመን እውነት ባንዱ ዘመን ያልቃል አንድ ሰው አስመራጭ አንድ ሰው ተመራጭ አንድ ሰው አማራጭ ሆኖ ሊሾም ሲታጭ እያየሁ ዝም እንድል ብዕሬ ባይፈቅድም ዝምታ ወርቅ ነው ያየ እንዲናገር ህግ አያስገድድም ቢያስገድድም እንኳን መኖር ስለፈለኩ ፖለቲካ አልወድም። ✍ፋሲል ━━━━━ ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯ @Ketbeb_Mender @Ketbeb_Mender ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
Show all...
• ይታሰባል በሆድ! #ገጣሚ Samuel የገኒ ልጅ (ብሩኬ) ሆድ በነገሰበት ስም በሌለው አለም ጭንቅላት ተይዞ ባዶ ሲሆን ቀለም አዕምሮ ተርቦ ምነው አጉራሽ የለም? ሆድ እየተሞላ ይኖራል ዘላለም! ✍@Lanchisel ° ° JOIN US👇👇 @getem_besamuel @getem_besamuel
Show all...