cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Bboytomy 33

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
143Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የትግራይ ሚሳኤሎች ጉዳይ ! ትላንትና ባወጣነው የሳተልስይት መረጃ መሰረት በ Aerial location 13.557794° , 39.548316° ላይ የታዮ S-125 ( SA-3 Goa ) የተሰኙ ምርታቸው የሩስያ የሆኑ ሚሳኤሎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሎል ። •በጉዳዮ ላይ ተጨማሪ የሳተላይት ምስል ለማያያዝ ሞክረናል። ከሳተላይት ምስል ለማየት እንደሞከርነው ሚሳኤሎቹ ከተጠመዱበት ቦታ ወይም ከላይ በaerial location ከተገለፀው ቦታ ተነስተን የሚሳኤል ጥቃት ተሰነዘረባቸው በተባሉት ቦታዎች ልኬት ለመውሰድ ሞክረናል ። በዚሁም መሰረት Map length 📐 ከAerial location 13.557794° , 39.548316° - ጎንደር ያለው እርቀት = 219 Km ከ Aerial location 13.557794° , 39.548316° - አስመራ ያለው እርቀት = 209 Km በ Aerial location 13.557794° , 39.548316° - ባህር ዳር ያለው እርቅት = 320 Km ነው ። የሚሳኤሉ ዝርዝር ሁኔታዎች ሚሳኤሉ ከ 200 - 250 Km ተጉዞ የመምታት አቅም አለው ። ወደላይ ደግሞ ከ28 - 32 Km ከፋታ ( Attitude) መወንጨፍ የሚችል ነው ። በውስጡም 3 የተለያዮ የራዳር system ያሉት መሳሪያ ነው ። በቀላሉ በተለያዮ ከባድ መኪናዎችን በመጠቀም መንቀሳቀስ የሚችሉ ናቸው ። #ምልከታ ! • እነዚህን ሚሳኤሎቹን በመጠቀም ጎንደር እና አስመራ ላይ ጥቃት መሰንዘር ይቻላል ። ( እርቀቱ ሚሳኤሉ መወንጨፍ ከሚችልበት አቅም ጋት ይመጣጠናል ወይም Comparable ነው ) • ሆኖም ከተጠቀሰው ቦታ ባህር ዳር 320 km ስለሆነ ሚሳኤሉን ከ Aerial location 13.557794° , 39.548316° ሆኖ መመታት አይቻልም ። ለዚህም እንደማብራሮያ ሊቀርቡ የሚችሉ ሀሳቦቻ ፦ 1. ሚሳኤሎቹ ተንቀሳቃሽ ( Mobile feature ) ስለሆኑ ጥቃት ለመሰንዘር ቦታቸው ተቀይረው ሊሆን ይችላል ። 2. በ Aerial location 13.557794° , 39.548316° ከተጠቀሱት ሚሳኤሎች ውጭ በሌሎች ቦታዎችም ተጨማሪ ሚሳኤሎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሆኖም Observer IL የተሰኝው የእስራኤል የTweeter ገፅ ከተጠቀሰው ቦታ 4 ሚሳኤሎች መወንጨፋቸውን ገልፃል ። ሚሳኤሎቹ ስለተወነጨፉባቸው ቦታዎች ግን የጠቀሰው መረጃ የለም ። • ከታች የሳተላይት Video የምናጋራቹ ይሆናል@Addis_Merejas
Show all...
вroĸen нearт 💔 ❤life is not about finding Your self........... 💙life is all about creating Your self. ғor тнoѕe вroĸen нearтed and leav wιтн paιn❗ Let's creat our selves👏 Creator 👉 @Lastzking @letsfoundBot https://telegram.me/letsfound
Show all...
вroĸen нearт 💔

❤life is not about finding Your self........... 💙life is all about creating Your self. ғor тнoѕe вroĸen нearтed and leav wιтн paιn❗ Let's creat our selves👏 Creator 👉 @Lastzking @letsfoundBot

በወጋገን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ከሚያስፈልገው በላይ የጦር መሳሪያ መገኘቱ ተሰማ! የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በዛ ያለ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ መገኘቱ ተሰማ።በአዲስ አበባ በርካታ የጦር መሳሪያ የተገኘባቸው ሌሎች ድርጅቶችም አሉ ተብሏል።በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል። በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር ናቸው ብለዋል፡፡ሱር ኮንስትራክሽንም የተለያየ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሌላው የሕወሓት አካል ነው ተብሏል።በእነዚህ መሥሪያ ቤቶች በሕዝብ ጥቆማ እና ኮሚሽኑ ካለው መረጃ በመነሳት ብርበራ እና ፍተሻ መደረጉን ሸገር ሰምቻለው ብሏል። የጦር መሣርያ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን መከላከያ በራሱ ካምፕ ነው የሚያስቀምጠው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ በእነዚህ ተቋማት በብርበራ የተገኙትም ከፍተኛ የጦር መሣርያዎች ናቸው ብለዋል።በከተማው ውስጥ ካሉ ባለሀብቶች መካከል ለሕወሓት ድጋፍ የሚያደርጉ እንደነበሩም ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል፡፡ ባለሀብቶች በተለያየ መንገድ ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ተጨባጭ መረጃ እና ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጥፋት በመፈፀም ተቀናጅተው የሚሠሩ አካላት ላይ ያተኮረ ሥራ ነው የሚያከናውነው ብለዋል፡፡ Via Sheger FM @Addis_Merejas
Show all...
#ሰበር_ዜና ! የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ❗️ የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያለቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡ ▪️እነዚህ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፡- 1.ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 2.ጌታቸው ረዳ 3. ፈትለወርቅ ገ/እግዝያብሄር 4. አስመላሽ ወ/ስላሴ 5.ዶ/ር አብርሃም ተከስተ 6.ኪሪያ ኢብራሂም 7.ረዳይ አለፎም 8.አማኑኤል አሰፋ 9.ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ 10.ኪሮስ ሀጎስ 11.ያለም ፀጋ 12.ሰብለ ካህሳያ 13.ጌታቸው አሰፋ 14.ዳንኤል አሰፋ 15.ኢሳያስ ታደሰ 16.ዶ/ር አክሊሉ ሀ/ሚካኤል 17.አለም ገ/ዋህድ 18.ተክላይ ገ/መድህን 19.ዶ/ር እያሱ በርሄ 20.ዶ/ር ረዳይ በርሄ 21.ዶ/ር ኪዳን ማርያም በርሄ 22.ነጋ አሰፋ 23.ሺሻይ መረሳ 24. ዶ/ር ገ/ህይወት ገ/እግዝያብሄር 25. አፅብሃ አረጋዊ 26.ዶ/ር ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ 27.ሀዱሽ ዘነበ 28.በርሄ ገ/እየሱስ 29.ይትባረክ አምሃ 30.ዶ/ር ገ/መስቀል ካህሳይ 31.ዶ/ር ፍስሃ ሀ/ፂዮን 32.ርስቀ አለማየው 33.ዶ/ር አዲስ አለም ቤሌማ 34.ዘነበች ፍስሃ 35.ፍሬወይኒ ገ/እግዝያብሄር 36.አቶ ስዩም መስፍን 37.አቶ አባይ ፀሐዬ 38.እያሱ ተስፋይ 39.ለምለም ሀድጎ 40.ፕሮፌሰር ክንድያ ገ/ህይወት 41.ሀብቱ ኪሮስ 42.በየነ ምክሩ 43.ካሳዬ ገ/ህይወት 44.ሩፈኤል ሽፈራ 45.ሊያ ካሳ 46.ተወለደ ገ/ፃዲቅ 47.ሙሉ ገ/እግዝያብሄር 48.ኪሮ ስጉዑሽ 49.ዶ/ር አማኑኤል ሀይሌ 50.ደሳለኝ ተፈራ 51.ኢንጅነር አርአያ ብርሀኔ 52.አልማዝ ገ/ፃድቅ 53.ሰለሞን መአሾ 54.ተኪኡ ማዕሾ 55.ገነት አረፈ 56.ብርክቲ ገ/መድህን 57.ዶ/ር ሀጎስ ገዳፋይ 58.ዘራይ አስጎዶም 59.አሰፋ በላይ 60.አቶ ሸዋንግዘው ገዛኸኝ 61.አፅብሃ ግደይ 62.አቶ ስብሀት ነጋ 63.አቶ ሴኮትሬ ጌታቸው 64.በሪሁን ተ/ብርሃን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ የነበረ ናቸው፡፡ ▪️ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው የወንበዴው የጁንታው ሕወሓት የጥፋት ቡድን አባላት የአገር ክህደት ወንጀል ከመፈጸማቸውም በተጨማሪ በከፍተኛ የአገር ሃብት ምዝበራና ዘረፋ እንዲሁም በሰበአዊ መብት ጥሰት ወንጀልም ጭምር የሚፈለጉ መሆናቸውን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አሳውቋል፡፡ ▪️በተመሳሳይም ከጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ የሀገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና አገር በማፍረስ ሴራ በተሳተፉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ አመራሮች ላይም የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ▪️ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ሕዝብ የጣለባቸውን አገራዊ ኃላፊነትና ህገመንግስታዊ ግዴት ወደጎን በመተው መቀመጫዉን ትግራይ ክልል ካደረገዉ ከወንበዴው የህወሃት የጁንታው ቡድን አባላት ተልዕኮ በመቀበል በሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ውስጥ ሴሎችን በማደራጀት ከማዕከል የነበረው ግንኙነት እንዲቋረጥና ጥቅምት24 ቀን 2013 ዓ/ም ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ የሞት፣የአካል ጉዳት እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም ማድረጋቸውን የኮሚሽኑ መግለጫ ያመለክታል፡፡ ▪️ባለፉት 21 አመታት በምሽግ አብረው ሲኖሩ የነበሩ ጓዶቻቸውን የጁንታው ቡድን እኩይ አላማ ማስፈጸሚያ በማድረግ አገር በማፍረስ ተልዕኮው በመምራትና በመሳተፍ የሚፈለጉት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፖሊስ አባላት፡- 1.ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ ተስፋዬ (ውድወርደ) 2.ሜ/ጄኔራል ዮሐንስ ወ/ጎርጊስ ተስፋይ (መዲድ)፣ 3.ሜ/ጄኔራል ብርሃነ ነጋሽ በየነ (ውድመድህን)፣ 4.ብ/ጄኔራል ሀ/ስላሴ ግርማይ ገ/ሚካኤል 5.ብ/ጄኔራል ምግበ ሃይለ ወ/አረጋይ (አባበርሃ፣) 6.ሜ/ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል መሀመድዙን 7.ብ/ጄኔራል ገ/ኪዳን ገ/ማርያም የእብዮ 8.ሜ/ጄኔራል ገብረ ገ/አድሃና ወ/ዘጉ (ገብረዲላ) 9.ሜ/ጄኔራል ገ/መስቀል ገ/ዮሀንስ /አስቴር/ 10.ብ/ጄኔራል አብርሃ ተስፋይ በርሄ /ድንኩል/ 11.ብ/ጄኔራል ፍስሃ በየነ (ወርቅአይኑ) 12.ሜ/ጄኔራል ህንፃ ወ/ጎርጊስ ዮሐንስ 13.ብ/ጄኔራል አለፎም አለሙ ወ/ማርያም /ቸንቶ/ 14.ብ/ጄኔራል ገ/መስቀል ገ/እግዝያብሄር (ጠቀም) 15.ብ/ጄኔራል ተ/ብርሃን ወ/አረጋዊ 16.ሜ/ጄኔራል አታክልቲ በርሄ ገ/ማርያም 17.ኮሚሽነር መኮንን ካህሳይ ገ/መስቀል (ፅንቡላ) የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር 18.ም/ኮሚሽነር መንግስቴ አረጋዊ የትግራይ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር 19.ኮ/ር ጌታቸው ኪሮስ የትግራይ ፖሊስ አመራር የነበረ 20.ም/ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ማንጁስ/ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የነበረ 21.ም/ኮሚሽነር ተክላይ ፀሃዬ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ሃላፊ የነበረ 22.ኮ/ር ንጉስ ወ/ገብርኤል የትግራይ ልዩ ሃይል ፖሊስ ሃላፊ፣ 23.ኮ/ር ገ/ስላሴ ታፈረ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ 24.ኮ/ር ፍስሃ ተ/ማርያም (ወዲአርባ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ 25.ኮ/ር ተስፋዬ ገ/ኪዳን (ተስፋዬ ባንዳ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ 26.ሜ/ጀነራል ገ/መድህን ፍቃዱ ሃይሉ (ውድነጮ) በቁጥጥር ስር የዋሉ 27.ሜ/ጀነራል ይርዳው ገ/መድህን ገ/ፃድቅ(አስቴር)በቁጥጥር ስር የዋሉ 28.ብ/ጀነራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ 29.ብ/ጀነራል ኢንሶ እጃጆ እራሾ በቁጥጥር ስር የዋሉ 30.ብ/ጀነራል ፍስሃ ገ/ስላሴ እንሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ 31.ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ በቁጥጥር ስር የዋሉ 32.ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ በቁጥጥር ስር የዋሉ ▪️በመጨረሻም የጁንታው ሕወሓት ወንበዴ ቡድን ተፈላጊዎችን በዝርዝር እየገለፅን የምንሄድ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እናሳውቃለን፡፡ @Addis_Merejas
Show all...
በአዲስአበባ ባለፉት 5 ቀናት ብቻ -18 ያህል ቦንብ -ከ174 በላይ ሽጉጥና -ከ 4 ሺ በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስል እንዳዋለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል። ህወሓት በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተለያዩ ጥፋቶችን ለማድረስ እየተንቀሳቀሰ እንደነበር በመረጃና በማስረጃ መረጋገጡንም ኮሚሽነሩ ገለፀዋል። የተለያዩ ለጥፋት ሊውሉ የሚችሉ የጦር መሳሪያዎች የህወሓት ፀረ ሰላም ኃይል ሊጠቀምባቸው የነበሩ ሲሆን የቡድኑን ሴራ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 242 ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። በሐሰተኛ መንገድ እንደሚናፈሰው ማንነትን ትኩረት ያደረገ ሳይሆን መረጃን መሰረት ያደረገ ክትትልና ህግ የማስከበር ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ጌቱ አስረድተዋል። @Addis_Merejas
Show all...
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በማይካድራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶስት ቀን በፊት በጅምላ መገደላቸውን ገልፇል። ግድያውንም የፈፀሙትን አካሎች መንግስት ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋል።ግድያው ወደ ሁመራ መውጫ ባለ ስፍራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ መፈፀሙን በፎቶና ከአይን እማኞች አረጋግጫለው ሲል ሪፖርቱ ፅፏል።ግድያው ምንም ፖለቲካዊ ቁርኝት በሌላቸው በቀን ሰራተኞች ላይ የተፈፀመ ሲሆን የግድያው እውነተኛ አጀንዳ ጊዜ ያወጣዋል ያለ ሲሆን መንግስት እያደረገ ላለው የሚሊታሪ ኦፕሬሽን ግልፀኝነት ሲባልና የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች በቀላሉ ለመስራት እንዲያግዝ በትግራይ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነት አንዲመለስ አምነስቲ የጠየቀ ሲሆን አምነስቲ በስፍራው የሚደርሰውን ማንኛውንም ኢ ሰብአዊ የመብት ጥሰትና ወንጀል እየመዘገብኩ ለአለም ህዝብ አጋልጣለው ብሏል። Via FidelPost @Addis_Merejas
Show all...
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካዔል በተዋጊ አውሮፕላን ጥቃት በክልሉ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሰላማዊ ሰዎች በአየር ጥቃት ተገደሉት በአዲግራት እና መቀሌ ከተሞች መሆኑን የጠቀሱት ደብረ ጺዮን፣ መቼ እና ስንት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ግን ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ደብረ ጺዮን ራሳችን ከጥቃት ተከላከልን እንጅ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት አልፈጸምንም በማለት ማስተባበላቸውን ጠቅሷል ሮይተርስ፡፡ የክልሉ ታጣቂዎች ከክልሉ ውጭ ጥቃት እንደማይፈጽሙ የተናገሩት ደብረ ጺዮን፣ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ጣልቃ ገብቶ ድርድር እንዲያስጀምር ተማጽነዋል፡፡ [Wazema] @Addis_Merejas
Show all...
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 521 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 478 የላቦራቶሪ ምርመራ 521 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 101 ሺህ 248 ደርሷል።በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 63 ሺህ 268 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 554 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 36 ሺህ 424 ሰዎች መካከል 313 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 545 ሺህ 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል። @Addis_Merejas
Show all...
24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደመሰሱ በህወሃት ደጋፊነት በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭቃኔ የተሞላበት ግድያና ጥቃት ያደረሱ 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ሰሞኑን የኦነግ ሸኔ ቡድን በፈጠረው የሽብር ተግባር የዜጎች ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ የሚታወስ ነው። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዘግናኝ የግድያ ጥቃትና የንብረት ማውደም ባደረሱ የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል። በተለይ በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ አካባቢ በነዋሪዎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት በኦነግ ሸኔና በህወሃት ደጋፊነት የተወሰደው እርምጃ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ይታወቃል ብለዋል። የክልሉ ፖሊስ ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ ባደረገው ክትትል በምዕራብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ ላይ በተደረገ ክትትልና በተወሰደው እርምጃ እስካሁን 24 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል። 26 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ አባላት ደግሞ ተማርከዋል፤ 23 የሚሆኑት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለጸጥታ ሀይል መስጠታቸውን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል። @bbc_amharic1 @bbc_amharic1
Show all...
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማን ናቸው? ባይደን የባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ደጋፊዎቻቸው ባይደን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል። በእርጋታቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛ በግል ሕይወታቸው አሳዛኝ ክስተቶችን አሳልፈዋል። ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እአአ 1987 ላይ። ባይደን በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው። @bbc_amharic1 @bbc_amharic1
Show all...