cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፍቅር ሰው❤️

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔር አያውቅምና እግዚአብሔር ፍቅር ነው 1ዮሀ 4:8

Show more
Advertising posts
195Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

**ዘወር በል!** አንድ ዝሆን ገላውን በወንዝ ይታጠብና መንገድ ይጀምራል። ከመሻገሪያው ድልድይ እንደደረሰም፣ አንድ መላ አካሉ በጭቃ የተጨማለቀ አሳማ ከፊት ለፊቱ ሲመጣ ይመለከታል። ይህን ጊዜ ዝሆኑ ዘወር በማለት፣ አንዱን ጥግ ይዞ፣ በጭቃ የጨቀየውን አሳማ ያሳልፍና መንገዱን ይቀጥላል። ከቆይታ በኋላም፣ አሳማው በእብሪት ተወጥሮ ለጓደኞቹ፦ "አያችሁ አይደል ምን ያህል ትልቅ እንደሆንኩ?፡ ዝሆን እንኳን ሳይቀር እኔን ስለሚፈራኝ ጥጉን ይዞ ያሳልፈኛል!" ይላል። ታዲያ የአሳማውን ንግግር የሰሙ ጥቂት ዝሆኖችም ጓደኛቸውን "እውን ያደረከው ነገር ከፍርሃት የመነጨ ነውን?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ዝሆኑ ግን ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦ "አሳማውን በቀላሉ በእግሬ ልጨፈልቀው እችል ነበር፤ ይሁንና እኔ ንጹህ ስሆን አሳማው ግን ሲበዛ የቆሸሸ ነበር፤ እሱን ልጨፍልቅ ብል እግሬ ይቆሽሽብኛል። እናም ይህን ሽሽት ነበር ከፊቱ ዘወር ያልኩት"። ልብ በል፤ • የምታመዛዝን ነፍስም እንደ ዝሆኑ ናት፤ ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ሳይሆን ከቆሻሻ/ግርድ አሳብ/ ራሷን ለመጠበቅ ስትል ከአሉታነት (negativity) ጋር ከሚኖር ግንኙነት ራሷን ታሸሻለች። - በመሆኑም ቆሻሻን (የወረደ አሳብ፣ ተራ ወሬ፣ ስድብና ጥላቻ) በቀላሉ ለማስወገድ ይቻላታል። • የግጥሚያ ስፍራህን በብልሃት ምረጥ። - የገጠመህን ነገር ወደጎን እየተወክ ወደፊት ብቻ ተራመድ! • ለእያንዳንዱ አመለካከት፣ አስተያየትና ሁኔታ ምላሽ መስጠት አይጠበቅብህም። - ሁሉም ሰው ሆነ ሁሉም ነገር፡ ጊዜህንና ትኩረትህን ሊወስድ የተገባው አይደለምና - ከፊቱ ዘወር በል!! ሰናይ ምሽት
Show all...
💡'እኔ ማን እንደሆንኩኝ አታውቅም, ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ' 'She doesn't know who I am, but I know who she is 💎 የ85 አመት አዛውንት ናቸው  ከ 60 ዓመት በላይ ከባለቤታቸው ጋር በትዳር ኖረዋል, ባለቤታቸውን በሄዱበት ሁሉ እጃቸውን አጥብቃ እንድትይዛቸው ባለመሰልቸት ይጠይቋታል, ስትቆም ቆመው ስትቀመጥ ተቀምጠው  ስታስቸግር አብረው ተቸግረው . . . ሳይሰለቹ የድሮ ፍቅራቸውን ሳይቀንሱ በ 85 ዓመት የአዛውንት ጉልበታቸው አሁንም በትዕግስት አብረዋት አሉ :: ሰዎች ሚስታቸው ምን ሆና እንዲህ እንደሆነች  ይጠይቃሉ “አልዛይመርስ' የመርሳት በሽታ አለባት” ሲሉ ይመልሱላቸዋል 💡እና  ምንም አታስታውስም ?  ምንም  !ያን ሁሉ ዓመት የሕይወት ውጣውረዳችንን,ደስታችንን ሀዘናችንን   ወልደን ኩለን መዳራችንን ዘመድ አዝማድን  ኧረ እኔንም ዘንግታኛለች እናም "ሚስትህ እጅህን ብትለቅህ ትጨነቃለህ  ማለት ነው ?" ለምን አልጨነቅም ምንም ነገር  ማንንም አታስታውስም እኮ  በዚህ ዓለም ያላትን ነገሮች ሁሉ ረስታለች እኔንም ጭምር , ለብዙ አመታት አላወቀችኝም  እና ያለኔ ማን አላትና ነው የማልጨነቀው ?! 💎  "እናም አንተን ባታውቅህም በየቀኑ መንገድ ላይ እየመራሃት ትቀጥላለህ" ማለት ነው , ፈገግ አሉና አይኖቼን እምባ ባቀረሩ አይናቸው እየተመለከቱ  . "እኔ ማን እንደ ሆንኩኝ አታውቅም ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ "   ውዷ  ከ 60 ዓመት በላይ ብዙ ነገር የሰጠችኝ ሕይወቴ ናት " እናም  ሕይወቴን ሙሉ በሄደችበት ሁሉ አብሪያት አለሁ , ሰው ካለ ህይወቱ  ምን ሕይወት አለው ...  እከተላታለሁ።      መልካሞችን ሁሌም ያብዛልን።          ውብ አዳር❤️
Show all...
#ከእለታት አንድ ቀን አንድ የፐርሺያ ንጉሥ ሁለት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡ በመጨረሻም፤ “የሞት ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት የፈለጋችሁትን ተናገሩ” ሲል እድል ይሰጣቸዋል፡፡ አንደኛው፤ “ምንም የምናገረው የለኝም” አለ ሁለተኛው፤ ንጉሡ ምን ያህል ፈረሳቸውን እንደሚወዱት ስለሚያውቅ፤“ንጉሥ ሆይ፤ የአንድ ዓመት ጊዜ ከሰጡኝ ፈረስዎ ወደ ሰማይ እየከነፈ እንዲሄድ ላስተምረው እችላለሁ” አላቸው፡፡ንጉሡ በሰማይ ላይ የሚከንፍ ፈረስ እየጋለቡ ሲሄዱ ታያቸው፡፡ ካሁኑ ነሸጣቸውና ይቁነጠነጡ ጀመር፡፡“ይሁን አንድ ዓመት ሰጥተንሃል፡፡ ፈረሱን አምጥተው እንዲያስረክቡህ አደርጋለሁ” አሉ፡፡ የመጀመሪያው እሥረኛ በምንም አይነት ፈረስ እንደማይበር ስለሚያውቅ ፈረስ አስተማሪውን እሥረኛ ጓደኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤“ወዳጄ፤ ፈረስ በሰማይ እንደማይበር አሳምረህ ታውቃለህ፡፡ እንዲህ ያለ የዕብድ ሀሳብ ከየት አምጥተህ ነው ቃል የገባኸው፡፡ የመሞቻችንን ጊዜ ከማራዘም በስተቀር ምን ይፈይድልሃል?” ፈረስ አስተማሪውም፤“አይምሰልህ ወዳጄ፤ ነፃነቴን የማገኝባቸውን አራት ዕድሎች ራሴ መስጠቴ ነው”አለ አንደኛው እሥረኛም፤ “አራቱ ዕድሎች ምን ምን ናቸው?” ሲል በመጓጓት ጠየቀው፡፡ ፈረስ አስተማሪው፤ እንዲህ ሲል ዘረዘረለት፡- 1ኛ ወይ በዚህ ዓመት ውስጥ ንጉሡ ሊሞቱ ይችላሉ 2ኛ እኔም ልሞት እችላለሁ 3ኛ ወይ ደሞ ፈረሱም ሊሞት ይችላል 4ኛ ደሞስ ማን ያውቃል እኔ ፈረሱ በሰማይ እንዲበር ላስተምረው እችል ይሆናል አለው ይባላል። እና ምን ልልህ ፈልጌ መሰለህ በችግሮች ተሸንፈህ ቀድመህ እጅ አትስጥ ጣር ሞክር ልፋ ታገል በነገሮች ተስፋ አድርግ እንጂ ተስፋ አትጣ።ህይወት አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ የምታደርግባት የግብግብ መድረክ ናት።   "ተስፋ በሌለበት እንኳ ተስፍ አድርግ  ያለው ጸሐፊው በምክንያት ነው።አይህ ወዳጄ ከመሰንበት መላ አይጠፋምና።
Show all...
💎መዘግየትህን አትጥላው! ⏰ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህርት፣ በስራ፣ በሀብት፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ። 💡ልብ እንበል!! ጉንደን ካስበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች። ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች:: ወዳጄ ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል.. 🕰ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት እንደሚተኮስ አስብ፤ ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም! 💎ፋንዲሻ እንዴት አማርሽ ቢሏት እሳቱን ስለቻልኩት አለች ይባላል ፣ በህይወት መስመር ስኬትን ለማግኘት የግድ መከራውን ማለፍ አለብን!!              ውብ ምሽት!❤️
Show all...
💎በዚህ ምድር ላይ ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል። ይህ ህገ ተፈጥሮ ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚሰራ ህግ ነው። እንደ ህገ-መንግስት በአንድ ሉአላዊ ሀገር ብቻ የተገደበ አይሆንም። በምድር ላይ ለሰራው ደግነት ይሁን ክፋት ብድራት መከፈሉ የማይቀር ይሆናል።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቻልከውን ያህል መልካም ውለታ ብትውል ብድራት ተከፋይ ትሆናለህ። ካለህ ላይ መስጠት ማለት ነው። … የምትሰጠው ነገር ባይኖርህ ጥሩ ፈገግታ ስጥ። ምናልባት ይህች ፈገግታ አንተ ባታውቅ እንጂ አንዲት የጨነቃት ነፍስ ትታደጋለች ። 💛ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል። 💫መልካም ገበሬ ለነፍሱም ለቤተሰቦቹም ብሎም ለሃገር ለህዝብ የሚተርፍ ዘር ዘርቶ ፍሬውን ይመግባል።  በየትኛውም የህይወት ሜዳ ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ ግለሰብ መልካም ገበሬ ለመሆን የሚያግደው የለም። 🔆ሁሌም በጎ በጎውን ማሰብ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ።  ከራስህ አልፎ ተርፎ ለሌላው የሚጠቅም መልካም ሐሳብ ወደ ዓለም ብትልክ መልካምነት ዞሮ ይከፍልሃል። ብድራቱን ታገኛለህ። የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። …መልካም መሆን ኪሳራ ከሌለው ክፉ መሆን ምንም ትርፍ የለውም። … ወዲህም ባንተ ላይ እንዲሆንየማትፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ። …ፍቅር ትሻ እንደሆን ፥ ቀድመህ አንተ ፍቅር ስጥ።  ያልሰጡትን ለማግኘት ማሰብ ፥ ስንዴ ዘርቶ የጤፍ ምርት እንደመጠበቅ እንዳይሆን። … ከመስተዋት የተሰራ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከቤቱ ሆኖ  ወደ ውጭ ድንጋይ መወርወር የለበትም።  💡ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ፤ እያንዳንዱ ሰው በሌላው ህይወት በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ  ተፅእኖ ማሳደሩ ህገ-ተፈጥሮ ነው።አይመለከተኝም፥ አይደርስብኝም የምትለው ነገር ላይሆን ይችላል። … ጉንፋን የያዘው ሰው አጠገብህ ተቀምጦ ቫዮረሱ አንተ ዘንድ እንዳይደርስ ለማድረግ አትችልም። በአንድም በሌላ መልክ ኢንተርአክሽን ይኖራል።            
Show all...
❤️አንዳንድ ውብ ልቦች ወደ ሕይወትህ ፍኖት ሲቀላቀሉ የቀድሞ አንተን አትሆንም... ትለያለህ... በጣም ትለያለህ!! 💎የሰው ሰውነቱ መታያው በልቡና ዉስጡ በሰነቀው ቅንነት ፣ ለሌላው በሚሰጠው እኩል ፍቅር ነው፡፡ይህ ልብ ውብ ነው፣ወበትንም በመላው ተፈጥሮ ላይ እነደከርቤ እጣን መአዛውን አግንኖ ያውዳል፡፡ይህ ውብ የደከመን ያበረታል፡፡ይህ ውብ ልብ ያዘነን ያፅናናል፣ይህ ውብ ልብ የወደቀን አንስቶ ያፀናል፡፡ ❤️ይህ ውብ ልብ በኑሮ ዝሎ የመጣበትን ዓላማ የዘነጋን ወደተፈጠረበት ዓላማ ይመልሰዋል፡፡ይህ ውብ ልብ ካጋጠመህ የድሮውን ቀርቶ የቅድሙን አንተ አትሆንም፡፡ይህ ውብ ልብ ይቀይርሀል፡፡ቅየራውም ለመልካም ነውና ራስህንም ውብ ያደርግሀል፡፡                        
Show all...
━━━━━━━━━━━━━━━━━━          ውሳኔ ሕይወት ነው ወዳጄ… በእጅህ ላይ የተያዙ ስንት ውሳኔ ያልሰጠህባቸው ነገሮች አሉ? አእምሮህን እያናወዙ ያሉ ስንት እልባት ያልሰጠሀቸው ሀሳቦች አሉ? አልታወቀህም እንጂ ቀንህን እየበሉት ነው… ኃይልህን እየበሉት ነው… ጊዜህን እየበሉት ነው፣ አእምሮህን እየበሉት ነው… ብዙ ነገርህ እየተበላ ነው! ከምንም በላይ ሕይወትህን እየበሉት ነው፡፡ ውሳኔ ህይወት ነው ሲባል ሰምተህ ታውቅ የለ? ህይወትህን ከመበላት አድን፡፡ ወስን፡፡ ያያዝከው ነገር ላይ ግራ ቀኙን አይተህ… አመዛዝነህ በፍጥነት ወስን፡፡ ናፖሊዮን ሂል ምን ይላል መሰለህ ወዳጄ… “ከህመሞች ሁሉ የከፋው የሰው ልጅ ህመም - ለመወሰን መቸገር!” ነው ይላል፡፡ ከህመምህ መገላገል አለብህ- #እነሆ_መድኃኒት_ወዳጄ- ወስን! የተሳሳተ ውሳኔም ቢሆን እንኳን ወስን፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ የተሳሳተ ውሳኔ ውጤት ነውና! የመወሰን ቀን ይሁንልህ፡፡ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Show all...
❤️ ማንም በያዘው ቃል እየሸራረፈ ልቤን ሲያኮሰኩስ ቤት በኩል መንኜ ቤት በኩል ልመንኩስ መድረክ ላይ ፃድቅ ነው ዓለምን የሚያስንቅ ጥዑም ንግግሩ፤ መሬት ሲወርድ ግን ሰባኪ በv8_ምዕመን በ'ግሩ ከዘፍጥረት ወዲህ በያቅጣጫው ዘርቶን ባራቱም አፍላጋት ያሸጋግረናል እያንከባለለ ከጭንቅ ወደ_ስጋት እዛ ጋር ታረደ እዚህ መንገድ ዘጋ እዛ ተረሸኑ እዚህጋ አበቃልህ በሚል ደዌ ስጋት አመቱን ተጨንቀን ሼኹ ካላፅናናን ቄስ ካለስታረቀን "ይህ ሁሉ ሰባኪ ምን ያደርግለታል የቲፎዞ ብዛት"!? ለሚለው ጥያቄ ቀላል ነው ምላሹ ሞኝ ተማሪና_አሪፍ ጎጆ መግዛት::
Show all...