cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

The Home of all የሁሉም ቤት

Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day * Motivate for free * learn for free * earn more for free Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0 ══════❁✿❁═════════

Show more
Advertising posts
16 057
Subscribers
-7524 hours
-1187 days
-38030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉ 🌺🌷ክፍል 1⃣1⃣🌷🌺 ❣ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ በርግጥ ካሌብዬን አሁንም ቢሆን አልጠላሁትም ያም ማለት ግን በሱ ተስፋ አልቆረጥኩም ማለት አይደለም እናም ካጠገቤ መጥቶ ሲቆም ብደነግጥም በንግግሩ ግን በጣም ተናደድኩ የከዳኝ ሳያንሰው ከዮናስ ጋር ጠረጠረኝ መጠርጠሩም ሳያንሰው ይሄን ያክል ቀን የት እንደሆንኩ እንኳ የማያውቅና ያላሳሰበው ሰው ዛሬ ደርሶ እሱው ተበዳይ ሆነ ሁኔታዬ ሲቀያየርበት ዮናስ ያስሚን ችግር አለ እነሱ ማናቸው አለኝ ይሄኔ ሰላም ቀበል አድርጋ እሱ ፍቅረኛዋ ነው እኔ ደግሞ ጓደኛዋ ስትል ንዴቴን መቆጣጠር ይሳነኝ ጀመር ግን ከመናገር ይልቅ ጥያቸው መሄድን መረጥኩ ዮናስ አላስቻለውም ጠብቂኝ ቢያንስ ልሸኝሽ አለኝ ፀጥ ብዬው እርምጃዬን ቀጠልኩ ፡፡ ዮናስም ከጎን ከጎኔ እየሄደ ባለትዳር ነበርሽ እንዴ አለኝ ዝም አልኩት እሺ ተይው አትንገሪኝ ቅድም ስታቅፊኝኮ ሀንግ ልትሰሪኝ ነው የሚመስለው የማቀፍ ልምድ እንደሌለሽ ያስታውቃል ሆ አንቀሽ ልገዪኝ ... አለና ከት ብሎ ሳቀ እውነትም ዮናስ ይለያል ከካሌብ ጋር ያሳለፍኩትን እያሰብኩ ስረበሽ እሱ ግን አስረሳኝ ጭራሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን እረስቼ መሳቅ ጀመርኩ ከዛ ወደስራዬ ገባሁ ማታ ልምጣ ሲለኝ እና ላትመጣ ነው አልኩት እውነትም ቢቀር ይደብረኛል እሱም አንድ ቀን እንደካሌብ ቢከዳኝም እስከዛው ግን አብሬው በንፁ ጓደኝነት እቀጥላለው፡፡ እየሰራው የማስበው ጠዋት ካሌብዬ እንዴት ሰላምን አግኝቷት ነው አሷ ደሞ ማን ካፌ እንዳለው አውቃ ነው ይዛው የመጣችው እንዴት ወደኛ መጡ የሚለውን ነው ሲቀጥል ሰላም እንደዛ እንደተጎዳሁ እያወቀች ከካሌብ ጎን እንዴት ትቆማለች ጭራሽ ዮናስ እንዲርቀኝ ብቻ ሰላም ሁሉም ጠባሳዎቼ ላይ አሻራዋ ይታየኝ ጀመር እቺ ልጅ ከኛ ስር ለምን አልጠፋ አለች?? ብቻ ጭንቅላቴ እነዚን ጥያቄዎች እየፈጠረ ያስጨንቀኛል ግን ምንም መልስ ስላልነበረኝ በቃ አጋጣሚዎች ናቸው ብዬ አልፈዋለው. እንደምንም መሸ ይሄኔ ተጣጥቤ ልብሴን ቀይሬ ልወጣ ስል በር ላይ ካሌብን አገኘሁት አናግሪኝ አለኝ ግን ላናግረው አልቻልኩም ምክንያቱም በሱ ምክንያት እየሆንኩ ያለሁት በጣም ይጎዳል ዝምብዬው ስሄድ ለዚ ነበር ብዙ ፈተና አልፈሽ እኔን መርጠሽ የመጣሽው ለዚ ነበር አባትሽን አልሰማ ብለሽ እኔን የመረጥሽው? አለኝ ይሄኔ እርምጃዬን ገታ አድርጌ ማሰብ ጀመርኩ ከዛም ዞር ብዬ ምን ቀረህ ወይስ ሪታ ጥላክ ሄደች አልኩት እንደምታስቢው አይደለም ሲል ሊያሳምነኝ ሞከረ እኔም ከስካሁኑ ልፋቴ አይበልጥም ይቅርታ ላርግለት ብዬ ይቅርታ አረኩለት፡፡ ከካሌብ ጋር እንደገና አብረን መኖር ጀመርን በርግጥ በሙሉ ልቤ አላመንኩትም ግን ግዜ ሁሉን ያሳየኛል በሚል ፍቅር መስጠቴን ቀጠልኩ ሪታ ከቤታችን ወታለች ግን የት እንዳለች መጠየቅ አልፈለኩም ዮናስንም ሳገኘው ስለካሌብ  ሁሉንም አጫወትኩት ግን ዮኒ ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም አላለኝም ወንድም ሊሆነኝ ቃል ገባልኝ ካሌብዬ ደግሞ ዮናስ ከሚባል ልጅ ራቂ ሲል አስጠንቅቆኛል እኔም ካሌብዬን ቅር ከሚለው እያልኩ ዮናስን ማግኘት ተውኩ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ ቁርስ እየሰራው ቤት አፀዳለው ይሄኔ የፍቅሬ እንቅፋት ሪታ በር አንኳኳች ስከፍት እሷ ናት በሩን ብጠረቅምባት ደስ ባለኝ ግን እንደምንም እራሴን ተቆጣጥሬ ምን ፈለግሽ አልኳት ካሌብን አለችኝ ካሌብዬ ተኝቷል አልኳት ፊቷ ልክ አይደለም እናም ችግር አለ አልኳት ይሄን ስል እንባዋ ዱብ ዱብ እያለ እርጉዝ ነኝ አለች ይህን ስትል ከካሌብ ነው እንደምትለኝ እርግጠኛ ሆንኩ ብዥ አለብኝ ... እኔና ካሌብ ታርቀን በፍቅር 3 ወር እንኳ ሳንቆይ ሪታ እንደገና ህይወቴ ውስጥ ጣልቃ ገባች መቋቋም አቅቶኝ እራሴን ሳትኩ......ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
👍 14 2
እንኳን ለ እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል ።
Show all...
16👍 7🥰 2👏 2
🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉ 🌺🌷ክፍል 1⃣0⃣🌷🌺 ❣ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ እንዴት በቶሎ ሰከርኩ ወይስ እራሴን እንዳላውቅ መጠጤ ውስጥ መዳኒት አረጉብኝ? ምንም አላውቅም ብቻ ከንቅልፌ ባልነቃ ይሻለኝ ነበር እንደዛ እያለቀስኩና ደፍሮኛል ብዬ ያሰብኩትን ሰውዬ ምን እንደማደርገው እየዛትኩ እያለ ስልኬ ጠራ  በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ማውራት አይደለም ደዋዩን ማየት አልፈለኩም ዘጋ ከዛ ድጋሚ ተደወለ አሁንም ዘጋ በመጨረሻ አነሳሁት ይሄኔ የኔሰካራም አስቸኳይ ጉዳይ ስለነበረኝ ነው ሳትነቂ ትቼሽ የሄድኩት አለኝ ይሄ በትክክልም የዮናስ ድምፅ ነው ግን ጆሮዬን ማመን  አቃተኝና ማን ልበል አልኩ ወይ ጣጣ ሰካራም ጓደኛ መያዝኮ ችግሩ ይሄ ነው ዮናስ ነኝ ስመጣ የተፈጠረውን እነግርሻለሁ አለኝ የማወራው ስለጠፋብኝ ምንም ሳልለው ተሰናብቶኝ ስልኩን ዘጋው፡፡ በህይወቴ እንደዚ ጓጉቼ የማውቅበት ቀን ትዝ አይለኝም ዮናስን አግኝቼው ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጓው አንድ ልቤ ደግሞ ከኔ ጋር ነው ያደርሽው ቢለኝ ሀፍረቱን መቋቋም የምችል አልመስልሽ አለኝ ብቻ ግን ሰአቱ መገስገሱን ቀጥሎ ፀሃይዋ ለመጥለቅ ትሰናዳ ጀመር እኔም ስራ የማታ ተረኛ ስለነበርኩ የመስተንግዶ ዩኒፎርሜን ለበስኩ  ምሽት 12፡00 ሰአት ላይ ዮናስ ደወለ ስራ መሆኔን ስነግረው መጣ ግን ለማውራት እድል አጣሁ እሱም ይህን ተረድቶ ጠዋት እንደሚመጣ ቃል ገብቶልኝ ወደ ቤቱ ሄደ:: ልክ ሲነጋ ከእንቅልፌ ስነቃ ቶሎ ብዬ ስልኬን አየሁ መልክት ገብቶልኝ ነበር ዮኒ ነው እዛው አካባቢ የሚገኝ ካፌ ቀጠረኝ ተጣጥቤ ወደዛው አመራሁ ልክ ስደርስ ተነስቶ ሰላም አለኝና እንድቀመጥ ወምበር ስቦ ጋበዘኝ ለሴት ልጅ ክብር እንዳለው ያሳያል እኔ ግን ጉዳዬ የትላንት አዳሬን ማወቅ ነበር እናም ትኩስ ነገር አዘን ማውራት ቀጠልን፡፡ እእእእእእ አልኩ ጥያቄዬን ከምን መጀመር እንዳለብኝ ለማሰብ እየሞከርኩ የኔ ቆንጆ የምሬን ልንገርሽ በጣም ታምሪያለሽ አለኝ ይሄኔ እንዲ ሊከዳኝ እንደንግስት ሲክበኝ የኖረው ካሌብ ትዝ አለኝና አይደል አልኩት እውነቴን ነው ትላንት ያ ሰውዬ ቀጥሮሽም ቢሆን ፈልገሽም ብትሄጂም የእንቅልፍ ኪኒን ብርጭቆሽ ውስጥ መጨመሩ አናዶኛል ሲቀጥል ገና ልጅ ነሽ እድሜሽን ከሚመጥን ሰው ጋር አትዝናኚም?አለኝ፡፡ ንግግሩ ይበልጥ ሳበኝ ኪኒን? ብዬ ቃሉን ደገምኩትና አስከትዬ ከዛስ ቆይ አንተ እንዴት... ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ እኔ ገና በግዜ ስደውልልሽ ያለሽበትን ነግረሽኝ ነበር በርግጥ ና አላልሽኝም ግን መጣሁ ስመጣ ከሰውጋ ሳይሽ ልክ ባልሆንም ከፋኝ ከዛ ሰውዬውን እህቴ ናት ስለው አንቺም ምንም ብሰክሪም እንኳን አላሳፈርሽኝም ወንድሜ ነው ብለሽ ሙጭጭ አልሽብኝ እናም ይዤሽ ያደርሽበት ሆቴል ወሰድኩሽ አለና ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ደሞ ያሳቅሽኝ አብረከኝ ሁን እፈራለው እያልሽ ስታለቅሺ አንጀቴን ነበር የበላሽኝ አለ ይሄኔ እኔም ምን እንዳረኩ እንኳ ባለማስታወሴ በሀፍረት አቀርቅሬ ፈገግ አልኩ  ሳላስበው ደግሞ ምንም ሳያረገኝ ከዛ ሰውዬ ስላስጣለኝ በጣም ተደስቼና ወንድም ያገኘው ያህል ተሰምቶኝ ተነስቼ ጥምጥም አልኩበት ይሄኔ ከየት መጣ ሳልለው ካሌብዬ ከሰላም ጋር ካጠገቤ መቶ ቆመ ድንግጥ ብዬ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ይሄኔ ካሌብ  አሀ ለካ አንቺም  ወንድ አጊንተሽ ነው ትተሺኝ የሄድሽው አለኝ..........ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
10👍 6👏 3🥰 1💯 1
🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉ 🌺🌷ክፍል 9⃣🌷🌺                ❣ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ሰውየው ካጠገቤ መቶ ለመቀመጥ ወንበር እያመቻቸ ሁላቹም ጠጡ ሂሳብ እንዳትጨናነቁ አላቸው አብረውኝ ወደተቀመጡት ፊቱን አዙሮ እነሱም በደስታ ሰውየውን በየተራ አቀፉት እኔ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አይኔን ብርጭቆዬ ላይ ተክዬ ብቻዬን ማውራቴን ቀጠልኩ በንግግሩ መልስ ያጣው በቀላል አማርኛ ሹገር ዳዲ የሚባለው ሰውዬ ቆንጆ የተከፋሽ ትመስያለሽ አለኝ አሁንም የአይኖቼን አቅጣጫ ሳልቀይር ዝም አልኩት ይሄኔ ማነህ ና ሌላ መጠጥ ታዘዛት አለና ለአንዱ አስተናጋጅ ትዛዝ ሰጠ እኔም ገልመጥ እያረኩት አመሰግናለው መቸገር አይጠበቅብህም አልኩት፡፡ እሱም በመልሴ የምፀት ቃል ፈገግ እያለ ምን መሰለሽ ቆንጆ ብሎ እጁን ወደ ትከሻዬ ላከው ይሄኔ መጠጥ ባደፋፈረው ልቤ ተማምኜ ከወንበሬ ተፈናጥሬ እየተነሳሁ እንዳትነካኝ ሰውዬ ወንዶች ስትባሉ ከሴት ጭን ውጪ የሚያስብ አእምሮ አልታደላቹም አልኩትና ጥያቸው መታጠብያ ክፍል ገባሁ፡፡ መታጠብያ ቤት ገብቼ ትንሽ እራሴን ካረጋጋው ቡሃላ ልወጣ ስል ሰላም ተከትላኝ ኖሮ መጣች እኔም አልፌአት ልሄድ ስል ያስሚን አለች እርምጃዬን ገታ አድርጌ ቆም አልኩ ተረጋጊ ውዴ ሰውዬው ላይ እንደዛ መሆን አልነበረብሽም አለችኝ ምንም ሳልመልስላት ትቻት ወደ ቦታዬ ሄድኩ ልክ ስቀመጥ ሰውየው ጠጪ አለኝ ባትለኝም እጠጣለው ብዬ ብርጭቆዬን አንስቼ ጨለጥኩትና ተነስቼ ወጣሁ ከዛም ወደ ሆቴል መንገድ ጀመርኩ፡፡ ሞቅ ስላለኝ ምንም አላውቅም ነበር  ብቻዬን ስሄድ አንዴ ስስቅ አንዴ ሳለቅስ እብድ እመስል ነበር በዚ መሀል አንድ መልኩን በደምብ ያላየሁት ወጣት ሰላም አለኝ ቀናም ብዬ ሳላየው ዝም ብዬው መንገዴን ቀጠልኩ ኧረ አናግሪኝ ብቻሽን ከምትሄጂ ስለሀገር ጉዳይም ቢሆን እናውራ ሲል ንግግሩ ፈገግ አስብሎኝ ቀና ብዬ አየሁት  ከዛም አመሰግናለው አብረሽኝ ለመሄድ ስለተስማማሽ አለ ፈገግ እንዳልኩ እብድ አልኩት   ልጁ ዮናስ ይባላል አቋሙ በጣም ያምራል በዛ ላይ ለዛ ያለው ቀልዱ ሀዘን ያስረሳል ያን ቀን ሆቴል ድረስ እያሳቀኝ ሸኝቶኝ ስልኬን ተቀብሎኝ ተለያየን፡፡ በርግጥ ከዚ ቡሃላ ምንም አይነት ወንድ መቅረብ አልፈልግም በነጋታው እራሴን አሞኝ ስለነበር ተኝቼ ዋልኩ ከዛ ወደማታ ስልኬ ጠራ አንስቼ ሀሎ ስል ሪታ ነኝ ያስሚን የካሌብ ብላ... ንግግሯን ሳትጨርስ ስልኩን ዘጋሁባት ንዴት መላ አካሌን አንቀጠቀጠኝ ከዛ ተነስቼ ትላንት ስጠጣ ያመሸሁበት ክለብ ሄድኩ ልክ ስደርስ የማላውቀው ስልክ ተደወለ ላለማንሳት ፈልጌ ዝም አልኩት ደግሞ ሲጠራ ግን አንስቼ ማን ልበል አልኩ ቁጣ በሚመስል ድምፅ ይሄኔ ኧረ ቀስ ሆ ስልኬን በቁጣ አታሳቂያት አለኝ ዮናስ ነበር ባያየኝም ፈገግ አልኩ የት ነሽ አለኝ ከዛ ያለሁበትን ነግሬው አየጠጣሁ ነው እንዳትመጣ ብዬ ዘጋሁበት፡፡ ከደቂቃዎች ቡሃላ የትላንትናው ሰውዬ መጣ ከዛም ከጎኔ ተቀመጠ ዝም ብዬ መጠጣቴን ቀጠልኩ ከዛ ግን እንዴትና በምን እንደሰከርኩ ባላቅም ስነቃ የሚያምር አልጋ ላይ እርቃኔን ተኝቻለሁ ደንግጬ ተፈናጥሬ ስወርድ ማንም የለም የማታው ሰውዬ አስክሮ እንደደፈረኝ ገባኝ መጨረሻዬ ይህ መሆኑ ይበልጥኑ አስለቀሰኝ......ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
👍 18 3👏 2🔥 1🥰 1
They predicted yesterday the DUMP of Bitcoin Already in the channel published the dates of the next BTC PUMP! Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈 Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈 Click 👉 CHECK NEXT PUMP DATES 👈 JOIN FAST! Only the first 1000 people will be accepted! 🔥
Show all...
3👏 1
🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉ 🌺🌷ክፍል 8⃣🌷🌺 ❣ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ሰላም ካሌብ ከሪታ ጋር ያረገውን ስትነግረኝ እራሴን ስቼ ወደኩ ይሄኔ ሁሉም ደንግጠው ከበቡኝ እናም ውሃ አደረጉልኝ ... ልክ ስነቃ የሆቴሉ አንደኛው መኝታ ክፍል ተዘርሬ ነበር እራሴን ያገኘሁት ልክ ክፍሉን ሳየው በጣም ደንግጬ እንዴ እዚ ምን አረጋለሁ ስል ወድያው ሰላምና የሆቴሉ ማናጀር ተከታትለው ገቡ ልክ ሰላምን ሳያት ተፈጥሮ የነበረውን ለማስታወስ ቻልኩ እንባዬ ጉንጮቼን እያቋረጠ ቁልቁል ይወርድ ጀመር  ካሌብዬ በኔ ላይ ሴት ደርቦ እኔን በሳመበት ከንፈሩ ሌላን ሴት መሳሙን ማመን አቃተኝ፡፡ ከማንም ጋር ምንም ሳላወራ ወጥቼ ወደቤቴ መንገድ ጀመርኩ በየመንገዱ እኔና ካሌብዬ ያሳለፍነውን ሳስብና ያለፍናቸውን ብዙ ችግሮች ሳስታውስ ተስፋዬ ይለመልማል ከዛ ደግሞ እናትና አባቴን ከመተው ጀምሮ እምነት አልባ እስከመሆን መድረሴ እውነቴን ነው ወይ እስልምናዬን አጥብቄ አልያዝኩ ወይ አንደኛዬን ክርስትያን ሆኜ አልተጠመኩ ብቻ መሀል መቅረቴ እንዲሁም ትምህርት ማቆሜ እሱ ግን ብዙ ነገሮች እንደሚፈልገው እየሄዱለት እኔም እንደፈለገው እየሆንኩለት ሌላ ሴት ወደ ህይወቱ ማስገባት መቻሉ እራስ ወዳድ ነው እንድል ያረገኛል ... እቤት ልክ ስደርስ ሁለቱም በየ ፍራሻቸው ተኝተዋል እራትም ሳልበላ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ እስከዛሬ ቡና ይፈላ ይደምቅ የነበረው ቤት በረዶ ሰራ ሰላም ያለችኝን ለማረጋገጥ ያለሰአቴ እቤት ድንገት መድረስ ጀመርኩ ታድያ አንድ የተረገመ ቀን ልክ እቤት ስገባ እሷ ፍራሽ ላይ የእጅና ጓንት ያህል ተጣብቀው ተኝተው ደረስኩ ያኔ ተስፋ ቆረጥኩ ከእምነት ፍቅር ማስቀደሜ ጥፋት መሆኑ ግልፅ ብሎ ታየኝ በድንጋጤ ፈዝዤ እያየኋቸው ሳለ ካሌብ ነቃ ልክ ሲያየኝ በድንጋጤ ተፈናጥሮ ተነሳ እኔም የሀዘኔን መርሻ እንባዬን እያዘራሁ የለበስኳትን እንደለበስኩ ወጥቼ ወደሆቴል አመራሁ ፡፡ ...ከዛ ቀን ቡሃላ እዛው ሆቴል ውስጥ እያደርኩ መስራት ጀመርኩ ግን ሁሌም ሃሳቤ አንድና አንድ ነው እሱም ካሌብ ምንም ባደርግ እሱን ማሰቤን ማቆም አቃተኝ በቃ አፈቅረዋለሁ ልረሳው ከበደኝ በጣም ስጨነቅ ደግሞ እራሴን እስታለሁ ያለኝ አማራጭ መጠጣት እራሴን መርሳት ነው ሰላምን ስነግራት ከጓደኞቿ ጋር አስተዋወቀችኝ እነሱ በጣም ዱርዬና ሱሰኛ ናቸው እኔም ከስራ ቡሃላ ከነሱ ጋር ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡ አንድ ቀን ታድያ ሰላምና ጓደኞቿ የሚያመሹበት ክለብ ተቀምጠን ስንጠጣ እኔ እንደለመድኩት ስለካሌብ እያሰብኩ ብቻዬን አወራለሁ ይሄኔ ገንዘብ የሚሰጠኝ ሰውዬ ከሰላም ጋር መቶ ካጠገቤ ተቀመጠ.........ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
👍 12👏 1
​​​​​​​​​  ​🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ┉┉✽‌»‌ክፍል 7           ❣ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ካሌብዬ ከኔ ሌላ ሴት በእጆቹ መንካቱ የሚያንገበግበኝ ልጅ ዛሬ ተቃቅፎ በጠራራ ፀሀይ መሄዱ እውን አልመስልሽ አለኝ ከማገናዘብ ይልቅ በስሜት መመራት ጀመርኩ እንደ እብድ እያረገኝ እርምጃዬን ጨመርኩ ልክ ካጠገባቸው ልደርስ ስል ድንጋይ አንስቶ ልጅቷን መፈንከት አማረኝ ግን እንደገና ተውኩትና ቀዝቀዝ ለማለት ሞከርኩ እርምጃዬንም ገታሁት ከዛ ካሌብዬን እቤት ሲገባ ተረጋግቼ ልጠይቀው ወይንስ ድንገት ያየሁት መስዬ ላስደንግጠው እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ድንገት  እንዴ የኔ ፍቅር በዚ ሰአት ብቻሽን ለምን አልደወልሽልኝም እ አመመሽ አለኝ ካሌብዬ ደረቱ ላይ ልጥፍ እያረገኝ ይሄኔ ያሰብኩት ልክ ባለመሆኑ የደስታ ሲቃ እየተናነቀኝ ደና ነኝ ውዴ እሷ ማናት ግን አልኩት ካሌብዬም ፈገግ ብሎ እየተመለከታት የክፍሌ ልጅ ናት ሪታ ትባላለች አለኝ ፡፡ካሌብዬ ድሮም ሴት ጓደኞች ይኖሩታል ግን በኔ ቀልድ አያውቅም ባጉል ጥርጣሬዬ እራሴን እየወቀስኩ ልጅቷን ተዋወኳት . ሪታ ደስ የምትል ተጫዋች ልጅ ናት ከዛን ቀን ቡሃላም ከካሌብ ጋር ለማጥናት መምጣቷን ቀጠለች ይህ በንዲህ እንዳለም ሪታ የቤት ኪራይ ጨምረውባት አቅም ስላነሳት እስከግዜው ከኛ ጋር ደባልነት ገባች፡፡ ይህ ሆኖም ካሌብና ሪታ እረጅም ግዜአቸውን አብረው እያሳለፉ እንኳን እኔ ምንም አላስብም በካሌብዬም እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ካሌብዬና ሪታ ከትምህርት ሲወጡ እቤት ቡና አፍልተውና ምግብ ሰርተው ይጠብቁኛል ሪታ በጣም ስለምትጫወት ሁሌም ቤታችን ድምቅ ብሎ ነው የሚያመሸው እናም ዛሬም እንደወትሮዬ ሁሉ ሰዓት ደርሶ እቤት እስከምደርስ እየተጣደፍኩ ሳለ አለቃዬ መጥቶ ከሰኞ ቡሃላ አንድ ቀን ቀን አንድ ቀን ምሽት በፈረቃ እንደምንሰራ ተናገረ ይሄኔ ከምንም በላይ ካሌብዬን ያናደዋል ብዬ እየፈራሁ ማታ ላይ ነገርኳቸው ይሄኔ ካሌብ እንዳሰብኩትም እንዴ ፍቅር አይሆም ጭራሽ ማታ ሲል ሪታ ካፉ ነጥቃ ምን አለበት ስራ አይደል? አለች ይሄኔ ባንዴ እሺ በቃ አለ በሰአቱ ደስ ብሎኝአቀፍኩት ከዛ ግን እሷ ስትናገር ባንዴ መስማማቱ ጥርጣሬ ውስጥ ከተተኝ፡፡ ሁሌም ምሽት ተረኛ ስሆን ካሌብ እየወጣ ይቀበለኛል አንድ ቀን ታድያ ልክ ስወጣ ሆቴሉ በር ላይ አንድ ወጣት ስልክሽን ካልሰጠሽኝ ብሎ ይነዘንዘኛል ይሄኔ ካሌብ አይቶት ከሚጣሉ ብዬ ስልክ ቁጥሬን መናገር ስጀምር ከየት መጣ ሳልለቅ ካሌብ ከጎኔ ቆማል በህይወቴ እንደዛ ቀን ተሸማቅቄ አላውቅም ... አኩርፎኝእቤት ደረስን ከዛም ፊቱን አዙሮ ተኛ፡፡ ከዛ ቀን ጀምሮ ካኮረፈኝ ሳምንት ሞላው የስራ ቦታ ጓደኛዬ ሰላምም ካላናገርኩት ብላ እኔን ቀድማኝ ከስራ ወታ እኛ ቤት ሄደች ከትንሽ ደቂቃ ቡሃላ ስትመለስ ግን ጥሩ ዜና ይዛ አልተመለሰችም ነበር ካሌብዬና ሪታ ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ እንዳየች ነገረችኝ በድንጋጤ ሰማይና ምድር ተገለባበጡብኝ........ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
👍 12👏 2
🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺 ❣️ :¨·....................:¨·.❣️ ┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉ 🌺🌷ክፍል 6️⃣? ❣️ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ካሌብዬ ከሰውየው ጋር ሲያየኝ በጣም ተናዶ ጥሎኝ መሄዱ ይበልጥ አስደነገጠኝ እኔ እንኳን ከሱ ሌላ ወንድ የማማግጥበት እና ስለክብሬ እንኳ የማስብ ሴት አይደለሁም እናም ለምን ጠረጠረኝ? ብቻ ተከትዬው ቤት ገባን ከዛ ላረጋጋው ፈልጌ ካሌብዬ አልኩት እሱም ብስጭቱ ሳይለቀው አትጥሪኝ አይነት አስተያየት አየኝ ይሄኔ መታገስ አቃተኝ ምን ሆነሃል እኔኮ ቤተሰቤንና ያደኩበትን ቀዬ ትቼ የመጣሁት አንተን ብዬ ነው ሂጃቤን ፈትቼ ፀጉሬን እያሳየው ማንነቴን አርክሼ በማላውቀው ማህበረሰብ ውስጥ የምሰራው ላንተ ስል ነው ይግባህ እንጂ እኔኮ ያለምንም እቅድ ድንግልናዬን ያስረከብኩህ ካንተ ውጪ ባዶ መሆኔን እንድታውቅ ነው ለምን አትረዳኝም ለምን ትጠራጠረኛለክ... እያልኩ እንባ እየተናነቀኝ በጩኸት ተናገርኩ ካሌብዬ ስሜቱ እንደተረበሸ ለማወቅ አይኖቹን መመልከት በቂ ነበር ትንሽ በዝምታ ከቆየን በኀላ ካሌብዬም ይቅርታ ጠይቆ አባበለኝ ከዛም የጀመረውን አመት ተምሮ ቀጣይ እኔን እንደሚያስተምረኝ ቃል ገባልኝ በርግጥ ግን እኔ እሱ ቢማርልኝ እመርጣለሁ ከካሌብዬ ጋር ያለምንም ጥንቃቄ ወሲብ መፈፀማችንን ቀጠልን በሰአቱ ማገናዘብ አልቻልንም ነበርና ትንሽ አሞኝ ክሊኒክ ስሄድ እርጉዝ እንደሆንኩ ነገሩኝ ያባቴ እርግማን ወይስ የኔ እንዝላልነት ሁለቱም መልስ ሊሆኑ ይችላሉ ብቻ ግን ለኔ ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ተሰማኝ በሰአቱ ለካሌብ መንገር አልፈለኩም ምክንያቱም እንዳያጣኝ ስለሚፈራ ይወለድ ይል ነበር እኔ ደግሞ በኔ ስህተት ካሌብ ትምህርቱን አቋርጦ እንዲሰቃይ አልፈልግም ለዛም ሀጥያትን መርጬ ለማሶረድ ሀኪሞቹን ለምኜ ሰውየው ይሰጠኝ በነበረው ብር በመሀፀን የሚከተት እንክብል ሰጡኝ በመጀመርያ ቀላል መስሎኝ ነበር ግን ያን ሳደርግ ከሞት አፋፍ ነበር የተመለስኩት ብዙ ደም ፈሶኝ እራሴን ሳትኩ ከዛ ሀኪም ቤት ገባሁ ይሄኔ ነበር ካሌብዬም አርግዤ እያሶረድኩ መሆኑን ያወቀው ለአንድ ሳምንት ያህል ስራ ቀረሁ ይሄኔ ያ ብር የሚሰጠኝ ሰውዬ በሠላም ገንዘብ ይልክልኝ ነበር በጣም የገረመኝ ደግሞ ፍቅረኛ እንዳለኝ እያወቀ ገንዘቡን መስጠቱ ነው ምክንያቱን ስጠይቀው ስለምታሳዝኚኝ ነው ይለኛል ይህ በንዲህ እንዳለ ልክ በሳምንቴ ስራ ጀመርኩ የዛኑ የጀመርኩ ቀን እራሴን አሞኝ ሰአቴ ሳይደርስ ወጥቼ ወደቤት ሄድኩ ይሄኔ ህይወቴን መሉ አስቤው ቀርቶ ላስበው የማልፈልገው ነገር ነበር ያጋጠመኝ ካሌብዬ ከሌላ ሴት ጋር ተቃቅፎ ይሄዳል ማመን አቃተኝ.......ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
👍 21 5🥰 1
አረ ወገን ሞያዬ ተናቀ 🙆 አንዱ ዛሬ ደዉሎ እንኳን ለላብ አደር ቀን አደረሰህ አላለኝም🙄 አረ አትሳሳት ብሮ እኔ ፅፎ አደር ነኝ እስኪ ላይክ 👍 አድርጉ እጃቹህ ቁርጥማት አይንካው😍
Show all...
👍 50🤣 6👏 3💯 3 2🫡 2
​​​​​​​​​  ​🌹#ፍቅር_ያሸንፋል🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉ ክፍል 5⃣ ❣ልብ አንጠልጣይ እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ✍✍✍✍ሆቴል ውስጥ በፅዳትነት ተቀጥሬ ስሰራ ሰላም የምትባል የዚው ሆቴል አስተናጋጅን ተዋወኩ ይሄኔ እንደጓደኛ ተቀራረብን ያለሁበትን ሁኔታ ስነግራት በጣም ነበር ያዘነችልኝ  ከዛ በዚ እድሜሽ ለምን ፅዳት ትሰርያለሽ ለምን አስተናጋጅነት አትገቢም ከዛ በቀን የምታገኚው ቲፕ ብዙ ነገር ያግዝሻል ስትል መከረችኝ ይሄኔ በሷ ሀሳብ ተስማምቼ ካሌብዬን ሳላማክረው ቀጥታ ስራ ጀመርኩ እንዳለችው ለግዜው በጣም ጠቀመን ካሌብም ከቀን ወደቀን ለውጣችንን ሲያይ ጠየቀኝ እኔም እውነቱን ነገርኩት ቀን እስኪያልፍ ካሌብዬ እየተማረ እኔም መስተንግዶዬ እየሰራው ኑሮአችንን ቀጠልን በዛች ጠባብ ቤት ውስጥ ብዙ ፍቅር አለ እኔና ካሌብዬ ለብዙ ሰው ምሳሌ ሆንን አንድ ቀን ስራ ቦታ አንድ እድሜው ወደአርባዎቹ የሚጠጋ ጎልማሳ አንድ ጥብስ በልቶ 80 ብር መክፈል ሲኖርበት 500 ብር ሰጠኝ ከዛ ተከትዬ መሳሳቱን ስነግረው ያዥው ቆንጂዬ አለኝ ምን ያህል የተባረከ ሰው ነው ብዬ በውስጤ ልክ ሰአቴ ደርሶ ስወጣ ልክ ፊልም ላይ እንዳየሁት ፍቅረኛዬን ሰርፕራይዝ ለማድረግ አበባ ጎዝጉዤ ጥሩ ጥሩ እራት ሰርቼ መብራት አጥፍቼ በሻማ ጠበኩት ካሌብዬ  ሲገባ ግን እንደጠበኩት ደስተኛ አልሆነም ብሩ ከየት መጣ ሲል መጨቃጨቅ ጀመርን እናም ብሩን እንዴት እዳገኘው ስነግረው አላምንም ብሎኝ መጠራጠር ሲጀምር ጊዜ እኔም በጣም ስለማፈቅረው  የኔ ፍቅር ካላመንከኝ በቃ ክብሬን ልስጥህ እኔ ያንተ ብቻ ነኝ አልኩት እሱም ትንሽ ካቅማማ ቡሃላ ትምርት እስክንጨርስ ላለማድረግ ወስነን የነበርን ቢሆንም አንሶላ ተጋፈፍን (ክብረ ንፅህናዬን) ደስ እያለኝ ሰጠሁት፡፡ ሲነጋ ሁለታችንም ተጣጥበንና ጥሩ ቁርስ በልተን እኔ ወደ ስራዬ እሱ ወደ ትምህርት ቤቱ ሄድን ታድያ ልክ እንደተለመደው ዛሬም የትላንቱ ሰውዬ ብዙ ገንዘብ ሰቶኝ ሄደ ይሄኔ የምቀርባው አብራኝ ለምሰራው ለሰላም ነገርኳት ሰላምም ምንም ሳይመስላት ባክሽ የተለመደ ነው እዚ ቤት አዲስ ፊትና ቆንጆ ሲያገኙ እጃቸው ለማስገባት ገንዘብ ይረጩልሻል አለችኝ ከዛ ይሄ ግን ፍቅረኛዬን ያስከፋዋል ስላት እንዳልነግረው መከረችኝ እኔም ካሌብዬ ላለማስከፋት ገንዘብ ስለሚሰጠኝ ሰው ምንም አልነግረውም ነበር፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ሰአቴ ደርሶ ልክ ስወጣ ሰውየው በመኪና እየጠበቀኝ አገኘሁት ከዛ ካልሸኘሁሽ ብሎ አስጨነቀኝ ከሱጋ እየተሟገትኩ ሰላም  መጣች ይሄኔ ባክሽ ነይ እንግባና ያድርሰን ብላ አስገባችኝ እኔም እየቀፈፈኝ መኪና ውስጥ ገባሁ ልክ ደርሰን ስወርድ ሰውየው ወርዶ ደና እደሪ ብሎ ሲያቅፈኝ ካሌብ ተመለከተን፡፡ ልክ እንደሌባ ደንግጬ ካሌብዬ ብዬ ወደሱ ስሄድ ትቶኝ  ሄደ......ይቀጥላል ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: Share➨ @yehulum_bet Share➨ @yehulum_bet ::::::::::::::::::::::::::::::::::::: 🍂🍀🍂🍂🍀🍂🍀🍂
Show all...
👍 16 3🔥 1👏 1💯 1