cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አብሮነት/Abronet

አብረን ስንሆን ያምርብናል!!

Show more
Advertising posts
1 305Subscribers
+324 hours
+57 days
+1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✨ወዳጄ ሆይ አንዳንድ ጊዜ አጠገብህ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን በቀላሉ ሲያገኙና በትምህርት ፣ በሥራ በትዳር ... ቶሎ ስኬትን ሲጨብጡ ታያለህ። አንተ ግን አንድ ቦታ ቆመሃል። ወቅቱ የእነርሱ ነውና ከመቅናት ይልቅ ባገኙት ስኬት የደስታቸው ተካፋይ ሁን። ለእነርሱ ያደረገ አምላክ ላንተም እንደሚያደርግልህ እመን። ይኸውልህ ፤ 🌗የማንጎ ዛፍ የቡርቱካን ዛፍን ከርሱ ወቅት ቀድሞ ምርትን ስለሚሰጥ አይጨነቅም። ስኬት፣ በወቅት የሚታጨድ መኸር ነው፣ወቅትህ ሲሆን ምንም ነገር ከመንገድህ ሊቆም አይችልም። የአንበሳ በዝግታ መራመድ ስንፍናን ወይንም ድካምን አያመለክትም፤ ያለመውን አደን በእጁ ለማስገባት እርምጃውን እያሰላ እንጂ። የሰዎች ፈጥነው መራመድ አያውክህ። የራስህን ኑሮ ኑር! ✨ፈጣሪህን ታመን። ልብ በል፤ ቤትህን በፍጥነት ሠርተህ መጨረስህ ሳይሆን ንፋስና ጎርፍን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አድርገህ መሥራትህ ነው ቁምነገሩ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። የእውቀት ሰውና ጠንካራ ሠራተኛም ሁን! ደግሞ ሁሉንም አታገኝም!አንተ የተሳፈርክበት አውሮፕላን መሬት ሲያርፍ፣ ከዛ መሬት የሚነሣ አውሮፕላን አለ፤ ሌሎች ደግሞ ለመነሳት በሂደት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም መዳረሻቸው የተለያየ ነው፤ ምናልባትም ወዳንተ መነሻ ሊሆን ይችላል። አየህ ህይወት እንዲ ናት፤ "ደረስኩ" ብለህ ስታስብ ሌሎች ያንን ሥፍራ "ጥለው" ሲነሱ ታገኛቸዋለህ። አንዳንዶቹ አንተ ወደ ተነሳህበት፣ ሌሎቹም ወደ ሌላ። 🌗በልጅ ማጣት ምክንያት ቀን ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዳሉ በልጆቻቸው ምክንያት ቀንና ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች አሉ፣ባል ባለማግባታቸው የሚጨነቁ ሰዎች እንደገጠሙኝ ሁሉ በማግባታቸው የሚጨነቁም ሰዎች ገጥመውኛል። በሥራ እጥረት ምክንያት የታመሙ እንዳሉ በሥራ ብዛት ምክንያት የሚታመሙ አሉ። ልጆቻቸው ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡላቸው የሚጨነቁ እንዳሉ፣ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲገቡላቸው የሚጨነቁ አሉ። እናም ወዳጄ ህይወት እንዲህ ነው፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም!፣ ንፋስን አባሮ እንደመያዝ ነውና። ሁሉንም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ እንደሚያሸጋግርህም ፈጣሪህን ታመን። ሁልጊዜም በአምላክህ ደስ ይበልህ! በእምነትም ኑር!      መልካምነት ለራስ ነውና       
Show all...
3
ተማጽኖ (በእውቀቱ ስዩም) አቤቱ የጠፈር ባለቤቱ በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ? በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ አቤቱ የፍጥረት አባት ከሰማኸኝ ምናልባት ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው አልልህም! ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች ! ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ ወሰን የሌለህ ዝምታ እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ ባይመችህም ስማኝ ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ ከአውሎ ነፋስም በላይ ከመሬት መራድም ይልቅ ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ ሰው ነው የሰው አደጋ ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ !
Show all...
👍 4
ለመላዉ የክርስትናና እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም ፆም ይሁንላችሁ🙏 ሰላም ለሀገራችን : ፍቅር : ለህዝባችን 💚💛❤
Show all...
ዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ እንደፃፈው!… የአንጋፋው ድምጻዊ የጌታቸው ካሳ፣ ‹ሀገሬን አትንኳት› የሚለው ዘፈን አብልጬ ከምወዳቸው ሀገርኛ ዘፈኖች አንዱ ነው። እናም ከጥቂት ዓመታት በፊት አንድ ‹ምሳሌ በተሰኘው መጽሐፌ ውስጥ ያለ አብዲሳ የተሰኘ መሪ ገጸ-ባህርይ: ዘፈኑንም ዘፋኙንም በሚከተለው መንገድ እንዲገልጸው አድርጌ ነበርና ከዘመኑ መንፈስ ጋር ስለሚናበብ ዳግም ላቋድሳችሁ ወደድኩ። …. “…ከሰለሞን ጋር – ባዶ ሜዳ መግቢያ በር ላይ የጀበና ቡና አፍልታ እምትሸጥ ሴት አለች – እዚያ ነበር እንድንገናኝ ቀጠሮ የተጣጣልነው፡፡ ቀድሜው ደረስኩ፡፡ “የአጋጣሚ ነገር ሆኖ፣ የጀበና ቡና ቤቱ፣ የጌታቸው ካሣን፣ ‹የብዙኃን እናት፣ መመኪያዬ የምንላት› የተሰኘውን ዘፈን ከፍቶ ጠበቀኝ፡፡ “ይሄ ዘፈን ብቻቸውን አገር ከሚመስሉኝ ዘፈኖች አንዱ ነው፡፡ ዘፈኑን ስሰማ ወደ ዐድዋ ተራራ ሄጄና ተዋግቼ ድል የመታሁ፣ ማይጨው ዘምቼም የቆሰልኩና አርበኞቹን የሆንኩ ይመስለኛል፡፡ ሙዚቃው ዕድሜዬን ያስረሳኛል፡፡ እቴጌ ጣይቱ የጣልያኑን የጦር አዛዥ ሲያመናጭቁትና የውጫሌ የስምምነት ፊርማ ውዝግብ ሲፈጥር፣ እዚያው እቤተ-መንግሥት ተገኝቼ፣ በነጮቹ ድንፋታ ቁጣዬ ነድዶ፣ ‹ዘራፍ የአባ ዳኘው አሽከር!› ብዬ የሸለልኩና የፎከርኩ ይመስለኛል፡፡ “ድምጻዊው ይህን ዘፈን የዘፈነው ለእኔና ለቢጤዎቼ ይመስለኝ ከጀመረ ሰነበተ፡፡ ወይስ እኔ ነኝ፣ ድሮ፣ በሌላ ሰው ነፍስ ውስጥ አድሬ፣ ግጥሙንና ዜማውን ደርሼ ለድምጻዊው የሰጠሁት? ታዲያ እንዲህ ካልሆነ፣ ለምንድነው የድምጹ ቅላጼ ነፍሴን ውርር የሚያደርጋት? ለምንድነው፣ ሙዚቃውን የሠሩት የዋልያስ ባንድ አባላት፣ እንደ ጅረት በሚፈስ /መስዋዕት በተከፈለበት/ የሰው ልጅ ደም መሃል፣ እንደ ማገዶ በተበታተነ አጥንት መሃል፣ ሕይወት በተከፈለበት ደም መሃል መንፈሳቸው እየተመላለሰ ሙዚቃውን የተጫወቱት የሚመስለኝ? “ይገርመኛል፡፡ “ከዐድዋ የድል ዘመን ሌላ እነ ራስ አበበ አረጋይ፣ እነ ገረሱ ዱኪ፣ እነ ዘርዓይ ደረስ፣ እነ በላይ ዘለቀ አብረውኝ በአርበኝነት የነበሩ፣ እነ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ እነ ተመስገን ገብሬና ሌሎችም…በማይጨው ዘመቻ ጊዜ አብረውኝ ሱዳን፣ ሱማሌና ሮም የተሰደዱ፣ ግዞት የተላኩ… ይመስለኝና፣ አሁን ግን ብቻዬን በሕይወት ቀርቼ፣ በአርበኞች ስም ስለ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ተጋድሎ ምስክርነት እንድሰጥ የተጋበዝኩ አረጋዊ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ “በዚህ በአንድ ዘፈን አማካይነት፣ በድምጻዊው ሾፋሪነት አገር እዞራለሁ፤ በየተራራው አደባለሁ፤ በየሜዳው እፎልላለሁ፤ በየሸለቆው እወሸቃለሁ፡፡ ትላንትን ዐያለሁ፡፡ እናም ሆዴ ይባባል፤ ዕንባዬ ይመጣል፤ በዚህ ስሜት መሃል ስሆን ደግሞ ማንም እንዲያውከኝ አልፈልግም፡፡ የብዙኃን እናት፡፡ “…ዘርዐይ ደረስ: ወንዱ በሮም የቆመላት፣ ጀግኖች በጦር ሜዳ ወድቀው የቀሩላት እኔም በተጠንቀቅ አለሁሽ የምላት ጥቁሯ አፍሪካዬን አገሬን አትንኳት፡፡…” “ብዙውን ጊዜ ስለ እዚህ ዘፈን አስባለሁ፡፡ ሁልጊዜ ይህን ዘፈን ስሰማ፣ አንድ ቀን፣ ዘፈኑን እንዴት እንደ ምወደው ለመናገር መድረክ አግኝቼ በደሰኮርኩ፣ ታሪካዊ ፋይዳውንም በመረመርኩ እላለሁ፡፡ ሞክሬው ግን ዐላውቅም፡፡ እንኳንም አልሞከርኩት፡፡ ቃላት ከየት አመጣለሁ? ሃሣብ ከየት አመነጫለሁ? እኔ የወደድኩትን ያህል ሌላው ተደራሲ የተሰማኝን እንዲሰማው የማድረግ ብቃቴስ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ “በልጅነቴ፣ በሙዚቃ ክፍለ-ጊዜ ይህንን ዘፈን ዘፍኜው፣ ከመቶ 90 አግኝቼበታለሁ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ቆይታዬ በሕይወቴ ከተማሪዎች በልጬ የታየሁበት ነጥብም ይህ ነው፡፡ ውጤቱ በሌሎች የትምሕርት ዓይነቶች አልተደገመም፡፡ “የተቀዳልኝ ቡና አንድም አልተጎነጨሁለት፡፡ አቀርቅሬ ነበር፡፡ ዘፈኑ ባይከፈት ኖሮ፣ ተከፍቶም የዐድዋን ድልና በፋሽስት ጣልያን ዘመን የተፈጸመውን ገድል ባያስታውሰኝ ኖሮ፣ አገባድጄው በነበረና አስተናጋጇን ሌላ ቡና በጥቅሻ ባዘዝኳት፡፡ ግና ስሞት፣ በወዳጆቼና በዘመዶቼ ልቅሶ ከምታጀብ ይልቅ፣ አስከሬኔ አፈር እስኪገባ ምናለ በዚህ ዘፈን በተሸኘሁ ብዬ ስመኝ፣ ፈዝዤ ቀረሁ፡፡—-“ *** የአንጋፋው ድምጻዊ ጌታቸው ካሳ ነፍስን ይማርልን።
Show all...
👍 3
በሳቅሽ ብርሃን ከደመቀዉ ፊትሽ..ከፈገግታሽ ጀርባ ውስጥሽ እንደ ገፅሽ ሁሌ ይስቃል ወይ..ወይስ ኣዝሏል እንባ ቦግ ካሉ አይኖችሽ የሚወጣ ጨረር በውስጡ ምን አዝሏል? ቅጭም ክስም ብሎ አንጄቴን ይወጋል ከሰው ተዘንቀሽ ስታወሪ ኣይቼ ካንቺ ጋር ሳወራ የጭዋታሽ ልኩ የወግሽ መቆንጠጥ ያሳያል አሻራ እስኪ አውሪኝ ውስጥሽን..ያንጀት የሆድሽን ልስማው አበሳሽን..የሴትነትሽን በመዉደድ ታውረሽ አምነሽ ሠ'ጠሻቸው ውብ ንፅህናሽን በእድፋቸው አጉድፈው እደጃፍሽ ታዛ ጣሉብሽ ክብርሽን? ስንት ቃል ተገብቶ አፍ ስንቱን ለፍልፎ የልቡን እስኪያደርስ ልብሽን አጣድፎ ጥሎሽ በረረ ወይ በዚያ ቡቡ ሆድሽ አበሳ ቆልፎ! ወይስ ያስወራል ወይ ክፉ ነች እያለ ክፋት ከሱ ተርፎ እስኪ አውሪኝ ውስጥሽን.. ያንጀት የሆድሽን ልስማው አበሳሽን.. የሴትነትሽን በጏዳሽ ተቀብሮ ከሆድሽ ያደረ የቤትሽ ገመና ያንች ብቻ ፀሎት ያንች ብቻ ለቅሶ ሞትሽን ልመና ሀ,ለ,መ,ሠ ብለሽ ምርጫ አትደርድሪ እንስት ነሽና የሴትን አበሳ ተሸክመሽ ኑሪ ተብሎ ተፈርዶብሽ በወል ባደባባይ በሆድሽ አምቀሽ, አምቀሽ, አምቀሽ ስትፈነጂ እንዳላይ እስኪ ተንፍሻቸው ንገሪኝ ልስማቸው አይንሽ ስንቴ አበጠ ልብሽ ስንቴ ደማ ጨርቅሽ ስንቴ ራሰ ስምሽ ስንቴ ታማ ስንቱ አይኑን ገለጠ ጩኸትሽን ሰማ? በልብሽ ሰሌዳ የፃፍሻቸው ሁሉ የውስጥ ህመምሽን አይተውት ያውቃሉ? ከፊቴ ከማየው ከውብ ሴትነትሽ ከፈገግታሽ ጀርባ የተሸከምሽውን የጣፈንታ ቁስል አይቼ ብባባ እስኪ አውሪኝ ውስጥሽን.. ያንጀት የሆድሽን ልስማው አበሳሽን.. የሴትነትሽን አበረ ሳህለ (ታላቅዬው)
Show all...
1
👍 1
የአብሮነት ቤተሰቦች እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳቹ
Show all...