cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✍የ አቤኔዘር ደብዳቤዎች✉

🔰በዚህ ቻናል ላይ🔰 ✏ግጥሞች📝 ✏ደብዳቤዎች✉ ✏ወጎችን ያገኛሉ። አንዳንድ ጊዜ መተው ጥሩ ነው ያልሽኝ እራስሽ አይደለሽ?! ይኸው እኔም… ግጥም ልፅፍልሽ ሞከርኩ ቤት አልመታ አለኝ ተውኩት፤ ደብዳቤ ልፅፍልሽ ሞከርኩ ስርዝ ድልዝ በዛበት ተውኩት፤ ልስልሽ ሞከርኩ ልብሽ አልታይ አለኝ ተውኩት፤…… ✍#እኔ ☀☀☀☀ @ITSmeABENI_23

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
293
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በመጨረሻ ጭር ወደማለት መጣ የሚያስጠላው ሰአት እየደረሰ ነው ልቤን ፍርሀት ፍርሀት እያለው ነው … እኔ ራሱ አብሬው ለመኖር የመጣው እንጂ ትንሽ ቆይቼ የምሰናበተው አልመሰለኝም ወደ 2 ሰአት ገደማ ላይ ቤላ በተራው ተስፍሽን እዛው ሳሎን ቁጭ እንዳልን ፍቅሩን ይገልፅለት ጀመር … አባቴ …ድምፁን በሀዘን ስብር አርጎ ማውራት ቀጠለ … በጣም ነው ያዘንኩት ህይወቴን ሙሉ ከኔ እንድትነጠል አልፈልግም ለደቂቃዎች ላጣህና ከአይኔ እንድትርቅ አልፈልግም ፍቅርህና አባትነትህን በጣም እፈልገዋለው ያስፈልገኛልም ራቅ ራቅ ብለው ሶፋ ላይ ተቀምጠው ባሉበት ቤላ ወደ ተስፍሽ ተጠግቶ እጆቹን ያዛቸው … የኔ እጅግ ልዩ ምርጥ አባት … አባቴ በመሆንህ በጣም ደስተኛ ነኝ … እውነት እልሀለው እንዳንተ አይነት ጀግና አባት ያለውን ሰው እስካሁን አይቼ አላውቅም … ያንተ አባትነት ይለያል … እኔን ለማሳደግ ስትል ህይወትህን ሰውተሀል … ህይወትህን በኔ ምክንያት አልኖርክም … መጥፎ እድል የሆንኩብህን እኔን ከልብህ በፍቅር ተቀብለህ ስለኔ ስትል ኖረህ አሳድገሀኛል … ለዚህ አብቅተሀኛል … ስላንተ …ስላንተ ስላለኝ ስሜት ለመግለፅ ቃላቶች ዋጋ ቢስ ናቸው … አንተን ጥዬህ በመሄዴ ከምልህ በላይ ከፍቶኛል አብረን ብንሄድ አልያም እዚሁ ብንቀር ደስ ይለኝ ነበር ግን እኔም አለመሄድ አንተም አለመቅረት አንችልም … ልጆች ወልጄ አንተ እኔን ባፈቀርክበት ፍቅር ልጆቼን እስካፈቅርና አባትነትን እስከማየው እጎጎለው በጣም ነው ምወድህ እጅግ በጣም ነው ምወድህ … እባክህ ራስህን ተንከባከብ ለኔ ደስታ እና ለኔ ሰላም ስትል ራስህን መንከባከብ እንዳትዘነጋ … ቤላ የአባቱ ፍቅር ውስጡን እያሳዘነውና እያሳሳው ተስፍሽን አቀፈው … አንተም አደራ ልጄ ራስህን ከመጥፎ ነገሮች ጠብቅ ስለሁሉም ነገር ፈጣሪ ያውቃል ማድረግ ያለብህን ብቻ አድርግ ስለኔ አታስብ … እንዴት ደስ ይላሉ የተባረከች መልካም ሚስት የተባረከ ትዳር እና የተባረከ ቤተሰብ ይስጥህ ልጄ … እኔ እድል ተበላሽቶብኝ ላሳይህ ላልቻልኩት የእናትት እና የቤተሰብ ፍቅር እጅግ ይቅርታ እጠይቅሀለው … ከፈጣሪ ጋር ሆነህ አንተ ልታገኘው ያልቻልከውን የቤተሰባዊ ሙሉነትን ለልጆችህ እንደምትሰጥ እምነቴ ነው … ተስፍሽ ወደኔ ዞር ብሎ ማሂ ነይ ልጄ … የተቀመጡበት ሶፋ ላይ ጠጋ ጠጋ እያሉ ወደነሱ ጋበዙኝ … ሄጄ ተቀላቀልኳቸው ምርቃቱ ቀጠለ እግዚያብሄር ፍቅራቹን ይባርከው … ፍሬያችሁን ይባርከው … ተባረኩ ፈጣሪ የልባችሁን መሻት ሁሉ ይስጣችሁ … እጃችንን ዘርግተን የጎን እየተያየን ከስር ከስር አሜን አሜን አሜን አሜን በድጋሚ ተስፍሽ እና ቤላ ተቃቀፉ … የመጨረሻዋን የጋራችንን እራት በላን በረራው 12 ሰአት ላይ ስለሆነ ከናዝሬት ወደ ሸገር የሚወስደን ሚኒባስ እንዲመጣ የተነጋገሩት 9 ሰአት ነው ተስፍሽ እራት በልተን እንደጨረስን … በረራው ረጅም ስለሆነና ስለሚደክም በግዜ እንድንተኛ ነግሮን ወደ መኝታው ገባ … ይሄኔ ከቤላ ጋር ወደ አይኑ ክፍል ሄድንና ቤላ ስለተስፍሽ ጤንነት እና ህይወት ለአይኑ አደራን በአደራ ላይ ይደራረብባት ጀመር … ብቸኝነት እንዳይሰማው በሚል ብዙ አደራዎችን አሳደረባትና ደና እንድታድር መልካም ምኞት ተመኝተን ከክፍሏ ወጣን … ወደራሳችን ክፍል እንደገባን የቤላ አጎት ከእንግሊዝ ደውሎ እያንዳንዱን ዝግጅት መዘጋጀቱን እርስ በእርስ ተረጋገጡና ለበረራው መልካም ምኞትን ተመኝቶለት ንግግራቸው ተጠናቀቀ …ወዲያው ደሞ ቤቲ ደወለች … ቀን እዚህ እዚያ ሲል አልደወለላትም ነበር ሌሊት 11 ሰአት አካባቢ አየር መንገድ እንድትመጣ ተነጋግረው ስልኩ ተዘጋ …በድጋሚ ሁሉንም አንድ በአንድ አስበን እና ፈትሸን ሁሉንም መያዙን ካረጋገጥን በዃላ ለ8 ሰአት አላርም ሞልተን አልጋችን ውስጥ ገባን … …ተቃቅፈን ተኝተናል ቤላ በደንብ እቀፈኝ በደንብ የራስህ አርገኝ … በመሀከላችን መርፌ አታልፍም … ከራሱ አጣብቆ እቅፍ አርጎኝ ሁሉ ነገሬን የራሱ አድርጎታል … በሰውነቱ አደላድሎኝ ሰላሜን አጎናፅፎኛል … ትንፋሼን በእጄ እየተቆጣጠርኩና ለቅሶዬን እዛው ውስጤ እያፈንኩት ሌሊቱን ሙሉ አንዳች እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ስንሰቀሰቅ አደርኩ … ቤላ ሚያቀው ተለያይተን እንደማንቆይ ነው ስለዚ ጭንቀቴ ብዙም አላስጨነቀውም … በመሀል በመሀል ግን በእንቅልፉ ውስጥ እንዳለ … ወደሞት የምሄድ አስመሰልሽው እኮ እያለ በአንድ እጁ ፀጉሬን በአንድ እጁ ሰውነቴን ይደባብሰኛል … ትንሽ ተኝቶ ደሞ … አንቺ አልቃሻ አፈቅርሻለው እኮ ወይ በቃ ሻንጣ ውስጥ እከትሽና ይዤሽ እሄዳለው … ትንሽ ፈገግ አስባለኝና ብዙ አስለቀሰኝ … አሁንም በድጋሚ እንቅልፍ ወሰደው ቀና ብዬ ፊቱን ያለማቋረጥ እያየውና ፀጉሩን እየደባበስኩ የሆዴን ብሶት እያባባስኩ በዛው ቆየው … 8 ሰአት የስምንት ወርን ያክል ተለጥጦብኝ 8 ሰአት ላይ ደረስን … አላርሙ ጮሀ ፀሀፊ ~ ረድኤት ✉️ @Red_ii ✉️ 💜 ●●● ስሜቶቼ ●●●💜
Show all...
#ማሂ ክፍል 40 🌹🌹 ጨዋታ ፈልጌያለው ከሱ ጋር ማበድን እፈልጋለው … ቤላ አብረን ሻወር እንውሰድ … ያን ውብ ፈገግታውን ፈገግ እያለ በዚህ ሰአት አለኝ … ፈለኩኛ እሺ አትለኝም … ቀና ብሎ የግድግዳውን ሰአት አየው 3 :09 ይላል … የሰጠኝን ቱታ ቆሜ በያዝኩበት አጠገቤ መጥቶ ከንፈሬን በከንፈሩ ነካክቶና አጎጉቶ ተወኝና ከዚህ አለም በሚያስጠፋ አይኖቹ ተመለከተኝ … እኔም እፈልጋለው ማሂ ፨፨፨፨፨ ፎጣችንን እና ስልካችንን ይዘን ወደ መታጠቢያ ክፍል ሄድን … ሁሉም ገና በዚህ ሰአት ተኝተዋል … በቤቱ ውስጥ ያሉት የክፍሎቹ መብራቶች ጨላልመዋል ውዱ ክፍላችን ውስጥ እንደገባን ሁለታችንም በተረጋጋ መንፈስ ልብሳችንን አወላለቅንና የውሀውን የሙቀት መጠን ጨምረን ቁልቁል ከሚወርደው ውሀ ስር ገባን … ምንም ሳንነጋገር እንደተቃቀፍን የውሀውን ሙቀት እና የፍቅራችንን ነፃነት እያጣጣምን ቆየን … ከዚያም የመዘፍዘፊያ ገንዳውን ሞቅ ባለ ውሀ ሞላንና ገንዳ ውስጥ ተዘፈዘፍን … ለዛሬ ለውሀው አረፋ አላስፈለገንም አካሌን ሊያየው አና አካሉን ላየው ፈልጌያለው … በውሀው ሙቀት እና በፍቅራችን ውበት ልዩ ስሜት እየተሰማን ማውራት ጀመርን … አንድ ሰው ብቻ በሚዘፈዝፈው ገንዳ ውስጥ ጥብቅብቅ ብለን እየተያየን እንዳለን ቀጠልን … እብዶ ልገላገልሽ ነው በቃ … እየተሽኮረመምኩ ግን ናፍቀሽኛል እንዳትል … የኔን ተይውና አንቺ እንዳታለቃቅሺ … ነው ነው ቤላ አሳይሀለው አንተ ቀድመህ ካላለቃቀስክ … አንገቴ አካባቢ ቀርቦኝ ምትሀቱን በትንፋሹ እየሰራ …አሁንም እያለቀስኩ ነው ጥዬሽ መሄድ እኮ አልፈልግም ማሂ … እኔም እኮ ጥለሀኝ እንድትሄድ አልፈልግም ግን ጥለሀኝ ልትሄድ ነው … ከአንገቴ ስር ወጥቶ ደረቱ ላይ ልጥፍ አርጎ አቀፈኝና መላ ሰውነቴን በአካሉ ሸፈነው … መልስ ሳይኖረው ሲቀር እንደዚህ ነው ምንም አያወራም … ቤላ …ወዬ … ቅድም ባደረከው ነገር ምን ተሰማህ … ሰላም ውስጣዊ ሰላም … ስላደረከው በጣም ተደስቻለው የኔ ቸኮሌት …እኔም በጣም ተደስቻለው … አመሰግንሻለው ማሂ … ለምኑ … የኔ ፍቅር ስለሆንሽ ፍቅርን ስላሳየሽኝ … ምስጋና ኪስ አይገባም ቤላ ፍቅርህ መቼም አይበቃኝም ከዚህም በላይ አፍቅረኝ በአይኖቻችን ሳንተያይ ማውራታችንን ቀጠልን … እኔም አንቺን ከማፍቀር ሱሱ ይዞኛል … ፍቅርቅር እያረኩሽ እኖራለው ቤላ እኔም አመሰግናለው …ምን አድርጌልሽ ህይወትን ስላሳየሀኝ ህይወቴን ስለሰጠሀኝ … ይሄኔ ደረቱ ላይ ለጥፎኝ ሲያወራኝ ከነበረበት በቀኝ እጁ ጣቶች ከአገጬ ከፍ አርጎና ወደ ከንፈሩ አቅርቦ ከንፈሮቼን ይስመኝ ጀመር … እኔ ተሳምኩለት እንጂ አልሳምኩትም ለዛሬ አሳሳሙን ነው ማጣጣም ምፈልገው ቤላ ምን ላድርግልህ ምን ልሁንልህ … አንገቴ እና ደረቴ አካባቢ በጣቶቹ እንደሰመመን እያደነዘዘኝ ራስሽን ስጪኝ አለኝ … ፈገግ እያልኩ ትፈልገኛለህ አልኩት በዛው ቀጥዬ እኔም እፈልግሀለው ራስህን ስጠኝ እሺ በቃ በቃ እንዳታለቃቅሺ … አየሽ አንቺ ነሽ ቀድመሽ ምትሸነፊው አንቺ ነሽ ቀድመሽ ምትናፍቂኝ እያለ የስረኛውን ከንፈሬን ለምቦጫም እያደረገ የውሸት ሊያናድደኝ ሲሞክር የእውነት ተደሰትኩለት … እንደውም ከሄድክ በዃላ አላወራህም ብትደውልም አላነሳልህም ይሄን እወቅ እሺ በራስህ ፈርደሀል … በእጆቼ ጣቶች ፀጉሩን እያበጠርኩ ያቺ የኔ ብቻ የሆነችዋን አሳሳም እስመው ጀመር … በቀስታ ወደጆሮዬ ተጠግቶ … ራሴን እሰጥሻለው የኔ ፍቅር … ደስ እያለኝ እኔም ሁሉነገሬን እሰጥሀለው አልኩት ገንዳ ውስጥ ፍላጎታችን እስከፈለገው ድረስ ቆየን ከዛም ፎጣችንን አርገንና ስልካችንን ይዘን ከዚች ውብ ደሴታችን ወጣን የቤላ ክፍል ጋር ስንደርስ ቤላ ሞባይሉን አስይዞኝና ሰውነቴን ተሸክሞኝ ወደ አልጋችን ይወስደኝ ጀመር … መታቀፍ በጣም ደስ ይላል …እውነቱን ለመናገር ግን እንዳይጥለኝ ፈርቻለው … ይሄኔ ነው ቤቲ የቤላ ስልክ ላይ የደወለችው … ተሸክሞኝ ባለበት የሱን ይሁኝታ እንኳን ሳልጠብቅ ይዤ የነበረውን የሱን ስልክ አነሳሁት … ሄሎ ቤቲዬ … ማን ልበል የቤል ስልክ ነው አይደል … አዎ ቤቲዬ ማሂ ነኝ እንዴነሽልኝ ቤላ በቃላት ምርጫዎቼና ፊቴ ላይ በማሳየው አሽሙር እየተገረመ አልጋው ላይ በቀስታ አስቀመጠኝ ቤቲ ቀጠለች … ማሂዬ አለውልሽ እንዴነሽ አንቺ … አለው ቤቲሻ ቤል ሻወር ውስጥ ነው ያለው ነገ ይደውልልሽ … ነው እንዴ እሺ ማሂታ ደውዬ እንደነበር ንገሪው … ስልኩ ተዘጋ አይኖቼን አንቺ ቅናተኛ አፈቅርሻለው እያሉኝ ባሉት አይኖቹ እያየኝ ልትገቢኝ አልቻልሽም አለኝ … ልትረዳኝ ከሞከርክ በቂ ነው ውዱ ቤል ብዬ ጥሜን ለማርካት ከንፈሮቹን ከንፈሮቼ አደረኳቸው …ከነፎጣችን አልጋ ላይ ባለንበት የመጨረሻውን የፍቅራችንን ፍቅር ተፋቀርን … የመጨረሻውን የፍቅራችንን ውብ ልፊያ ተላፋን… የመጨረሻውን የፍቅራችንን እርካታ ተጎነጨን …ወሲብ አድርጎ መለያየትና ወሲብ አድርጎ አንድ ላይ ማደር እጅግ የተለያዩ መሆናቸውን ዛሬ ከልቤ ንጉስ ጋር ጥቅልል ብዬ ሳድር አወኩኝ … ኡፋ ጥልቅ ሰላም እየተሰማኝ ነው … ሲንተከተክ የነበረውን የውስጤን እሳትነት በፍቅሩ አብርዶ እና አስክኖ የህይወቴን ውቡን ምሽት እጅግ ውብ አደረገልኝ ጠዋት 1 ሰአት ተነስተን ቁርስ በላንና ጉድ ጉዱን ተያያዝነው … የበረራ ትኬን , ፓስፖርት ,ኢትዮፕያ ሲጠቀማቸው የነበሩትን የተለያዩ መታወቂያዎች , አጠቃላይ የት/ ት ዶክመንቶች , አስፈላጊ የሆኑ ወረቀቶችንና ዕቃዎችን አነስ ባለች ቦርሳ ቼክ እያረግን ከታተትን … በአንደኛው ሻንጣ ጫማዎቹን, ቀበቶ, ክፍሉ ውስጥ ያለውን የሱን እና የተስፍሽን በፍሬም የተቀመጠ ፎቶ እና አንዳንድ መውሰድ የሚፈልጋቸው ፎቶዎች እየመረጥን ወደ ሻንጣው ኪስ ከታተትን … ትላንት ልብሱን በከታተተበት ሻንጣ ደሞ ስከርቮች , ሚጠቀመውን አንድ ሽቶ , አንድ ሎሽን , ካልሲዎች ጃኬቶች እና ሹራቦች , ጥቃቅን ልብሶችን ከታተትን … ከቤት ይዤ የመጣውትን ቦዲ ቲሸርቴን ይዤ በመጣውት ዶዶራንት እስኪጨመቅ ድረስ እጥን ካረኩት በዃላ በጎን በኩል ሻንጣ ውስጥ ከተትኩት .. መክተት ምንፈልገውን ከታተን እንደጨረስን ሻንጣዎቹ ከ23 ከ23 ኪሎ አለመብለጣቸውን አረጋግጠንና ሻንጣዎቹ ላይ ለልዩ ምልክት የኢትዮጵያን ባንዲራ በጎን በጎን አስረንባቸው … የሻንጣውን ፕሮሰስ ጨረስን ከዚያም ቤላ ከተስፍሽ ጋር ሆኖ ጎረቤቶቹን ለመሰናበት ከቤት ወጣ … የሰፈሩን ሰዎች ዞር ዞር ብለው ተሰናብተው እንደመጡ ባለፈው አክስቴ ቤት የነበረው ሽምግልና ላይ የመጡት የተስፍሽ የልብ ጎደኞች ቤት መጡ … ተሰብስበን ምሳ በላንና ቡና ተፈልቶ ትንሽ ተጫዋወትን … ለቤላ የመሰናበቻ ስጦታ ብለው የምታምር ወርቅ ሰጥተውትና ባርከው መርቀውት ተለቃቅሰውና አዝነው ተሰነባበቱና ትንሽ ቆይተው ሄዱ 10 ሰአት አካባቢ ላምሪና ዮኒም ቤላን ለመሰናበት ቤት መጡ … ብዙም ሳይቆይ የሙዚቃ ቤት ጎደኞቹም መጡና በጋራ ስንስቅ ስንጫወት በመሀልም እነ ቤላ ቅድም ቤት ለቤት እየዞሩ ሲሰናበቱ ቤት ያልነበሩ ሰዎች ዜናውን ሰምተው ሊሰናበቱት ሲመጡ ሁሉንም ሰዎች እያስተናገድን አመሸንና ሁሉንም አንድ በአንድ እየተሰናበቱት ተሸናኙ በመጨረሻም ከጠዋት ጀምሮ በተለያዩ ሰዎች ፋታ አጥቶ ያመሸው ቤት አሁን
Show all...
… ደግሜ ይሄን ጉዳይ አላነሳብሽም ህይወታችንን እንደድሮው እንቀጥላለን … ሰላማችንም ይመለሳል ግን እናቴ የመጨረሻ የምጠይቅሽ ጥያቄ ይሄ ብቻ ነው ቢያንስ ይሄን እምቢ አትበይኝ … አተኩራ አየችኝና ግን እየውልሽ ማህሌት ውሳኔዬ እንዲፀፅተኝ የሚያደርግ ነገር እንዳታደርጊ … እሺ እሺ የኔ እናት … በደስታ ሰከርኩ እድሜ ዘላለምሽን ከቤላ ጋር ለመኖር ሂጂ ፈቅጄልሻለው ያለችኝ ይመስል ፈነጠዝኩ … ወደ ጎዳ ገብቼ ቤላ ሲሄድ ይዞት የሚሄደውን አንድ የኔን ቲሸርትና ቤላ እኔን ካገኘኝ ጀምሮ ምቀባውን ዶዶራንት በትንሽዬ ቦርሳ ውስጥ ከትቼ ለብሼ የነበረውን ልብስ እንደለበስኩ ሞባይልና ብር ይዤ ከቤት ወጣው … ለእናቴ የነገርኳትን ነገሮች እያሰብኩ ደረስኩ … በአብዛኛው ያልኳት ነገሮች ውሸቶች ናቸው … ህይወቴ በቤላ ላይ ከተመሰረተ ቆይቷል… ብቻ ያስቃል የውሸቴን ማሳመን ከቻልኩኝ ጥሩ ተዋናይ ነኝ ማለት ነው … እሷ ራሱ ውጪ የማደርን ያክል ነገር እንድትፈቅድልኝ ያደረጋት … ትታኝ ትሄዳለች የሚለው ስጋቷ ይመስለኛል … የአባቴ ቤት ደርሻለው ምሽቱን አይኑ ቡና አፍልታ ሁላችንም ተሰብስበን ስንስቅ እና ስንጫወት አመሸንና እኔና ቤላ የቤላን ሻንጣ ወደማስተካከል ገባን … አይኑ ሁሉንም ልብሶቹን ተኩሳ አጥፋለታለች የሱ ስራ መውሰድ ሚፈልገውን ወደ ሻንጣ ማስገባት ብቻ ነው … ክፍሉ ጭንቀት ጭንቀት ይላል … 2 ሰአት አካባቢ ተስፍሽ የክፍሉን በር አንኳክቶ ገባና ቤላን ይዞት አልጋ ላይ ተቀመጡ … ተስፍሽ ማውራት ቀጠለ … ብቸኝነት እና ባዶነት ተሰማኝ በዚ ምድር ላይ አንድ አንተ ብቻ ነው ያለሀኝ … ልጄ ጭንቀት እና ሀዘን ውስጥ ልጨምርህ አልፈልግም … ግን አንተ ማለት እጅግ በጣም የምወድህ ልጄ ነህ … ልጄ ብቻም አይደለህም ሁሉነገሬ ነህ … ጎደኛዬ ወንድሜ ጎረቤቴ ዘመዴ … በቃ ሁሉ ነገሬ … ስላንተ ነው እስካሁን የኖርኩት ብርታቴ አንተ ነበርክ ስብራቴን ምረሳው ባንተ ነው ማመስገኛዬ አንተ ነበርክ … እጅግ የምወድህ ልጄ ነህ ግን ፈራሁ … መቼስ እየሳቅኩ አልሸኝህ ነገር ማልቀሴ ሚጠበቅ ነው አይደል … ህህህ እራሱ ባወራው እራሱ እየሳቀ አለቀሰ … ግን ሁሌም አንድ ነገር እንዳትረሳ በምድር ላይ ካሉት ነገሮች ሁሉ አብልጬ እወድኸለው የኔን አባትነት እና ያንተን ልጅነት መቼም እንዳትረሳ … የፍቅር ጥግ ድረስ እወድሀለው የኔ ልጅ … ተስፍሽ እና ቤላ ተቃቀፉ… ቤላ ምንም ቃል ሳይተነፍስ ስሜቱን ጥብቅ አርጎ በማቀፍ ገለፀለት ኡፍ ያስቀናሉ … ማን ታቅፎ ማን ይቀራል እኔም ሄጄ አቀፍኳቸው … ለ3 ተቃቅፈን ከቆየን በዃላ ተስፍሽ ከአልጋው ተነስቶ … በሉ ደና ደሩ መልካም አዳር ብሎ አሽኮርምሞን ከክፍሉ ወጣ … ቤላ ሚፈልጋቸውን ልብሶች ወደ ሻንጣ ከቶ ከጨረሰ በዃላ ከራሱ ልብሶች ውስጥ ምቀይረውን ለመተኛ ሚሆን ቱታ ሰጠኝ … ግን እኔ ከቅድም ጀምሮ ሀሳቤ ውስጥ የነበረው አንድ ነገር ብቻ ነው … አብረን ሻወር እንድንወስድ አልያም ገንዳ ውስጥ እንድንዘፈዘፍ ፈልጌያለው ፀሀፊ ~ ረድኤት 🌴 @Red_ii 🌴
Show all...
#ማሂ ክፍል 39 ❣ ደነገጥኩ … በዝግታ እየተከተሉት የነበሩት እግሮቼ መራመዳቸውን አቆሙ … ይዞኝ ሲራመድ የነበረውን እጁን እጥብቄ ወደ ራሴ ጎተት አድርጌ እሱንም እንዲቆም አደረኩት … አሁን አይምሮዬ ውስጥ እያሰብኩ ያለውትን ነው እያደረክ ያለሀው ቤላ … ግራ በመጋባት ጠየኩት … ማድረግ አለብኝ ማሂ ድምፄን ለስለስ አድርጌ … እሺ ግን በደንብ አስበህበታል … ፈጠን ብሎ መሆን ያለበት እንደዚህ ነው ብሎኝ ካቆምንበት ለመራመድ እግሩን ሲያነሳ መልሼ አሁንም በእጆቼ አጥብቄ ይዤ አስቆምኩት … በአይኑ ለምን እንዳስቆምኩት ጠየቀኝ … በቀስታ ቁናውን ተነፈስኩና እይኖቼን እያቁለጨለጭኩ ቤላዬ ትንሽ ፈርቻለው … እኔምኮ ትንሽ ተረብሻለው ማሂ ለኔ ቀላል ነገር አይደለም … አንቺን ይዤሽ የመጣሁት በንዴት መጥፎ ወደሆነ ነገር እንዳልገባ ብዬ ነው … ሳይሽ መስመሬን አልስትም ማድረግ ያለብኝን አድርጌ እወጣለው … ለዛሬ አጠነክሪልኝም ማሂ … የኔ ፍቅር እጠነክርልሀለው … ጉንጩን ሳም አድርጌ አሁን መግባት እንችላለን አልኩት … እጅ ለእጅ ተያይዘን ዘጋ ተደርጎ የነበረውን በር ከፍተን ገባን … መጀመሪያ ቤት የገባውት እኔ ነኝ … ደና ዋሉ ማዘር … ትንሽ የእናትነት ስሜት ቢሰማት ብዬ ትልቅነቷን አሳብቄ ደና ዋልሽ አልኳት … በሩ ጋር ቆሜያለው ቤላ እጄን እንደያዘ ከበስተጀርባዬ በበሩ ተከልሎ ቆሟል … እቺን ተንከሲስ ሴትዮ የተሸከማትን አልጋ እና እጅግ ሰፋ ያለ ቁምሳጥን ጨምሮ 6 ኩርሲዎች ብቻ በቤቱ ውስጥ ይታዩኛል … ማዘሯ አልሰማችኝም መሰለኝ ድምፄን ጠራርጌ እና በደንብ ጮክ ብዬ በድጋሚ ደና ዋሉ ማዘር አልኩ … ይሄኔ እንደሰመመን ከወሰዳት እንቅልፏ በድንጋጤ ነቃች… እነደው ቀላ ያለች አርጎ ፈጥሯት እንጂ ቁንጅና በደረሰበት አልደረሰችም … ከቤላ ስትተያይ እሷ በጣም አርጅታለች … ከአንገቷ በትንሹ ቀና እንደማለት ብላ ብቸኝነት ባገረጣው ድምፅ ደህና ዋልሽ ልጄ አለችኝ … ያኔ ከቤላ ጋር ፍቅር የጀመርን ግዜ ከወገቧ በታች ፓራላይዝድ ናት ያለኝ ትዝ አለኝ … ማንቀሳቀስ የምትችለው በትንሽ በትንሹ እጇን እና አንገቷንብቻ ነው … ውስጤ ተረባበሸብኝ የተያያዙት የቤላ እና የእኔ እጅ በላብ እየተጠመቁ ሙቀታችንን ጨምረውታል … በቀስታ ወደውስጥ ገባው ቤላም ተከተለኝ … ውስጥ ገብተን በሩን ልክ እንደመጀመሪያው ገርበብ አደረግነው … የኔን ፊት አይታ ግራ ተጋብታ ሳትጨርስ የቤላን ፊት አየች … የቤላን እጅ በቀስታ ለቀኩት … ትንፋሿ ራሷን እያፈናት እና እያስጨነቃት ልትናገር አፏ ላይ ያመጣችውን ቃል መልሳ እየዋጠች በድንጋጤ በዚህ ስሜት ለደቂቃዎች ባሌን ተመለከተችው … በተረጋጋ መንፈስ በሩ አፋፍ ጋር ያለው ኩርሲ ላይ አካሌን አሳረፍኩ … ቤላም ከአልጋው ጎን ለጎን ካለው ቁም ሳጥን አጠገብ ከተቀመጠው ኩርሲ ላይ ተቀመጠ … ከእኔ ይልቅ እሱ ለሷ ቀርቧታል … ቀና ብሎ እንኳን ሳያያት ፊቱን ጎንበስ አርጎ በጣቶቹ ቅንድቡን ያለማቋረጥ እያሻሸ ነው … ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶታል ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ትንፋሹ እየተናነቀው እና ባጎነበሰበት ቅንድቡን እያሻሸ እንዳለ ማውራት ጀመረ … እኔ እኔ ያንን አልፈልግም ነበር … እኔ … ትንፋሹን ያዝ አደረገ … እኔ ህይወቴ እንዲበላሽ አልፈልግም ነበር … ሊቆጣጠራቸው ያልቻላቸው እምባዎቹ ከአይኑ እየፈሰሱ እኔ መጥፎ ትዝታዎችን አልፈልግም ነበር … ውይ አወራሩ እና ሁኔታው አንጀት ይበላል … የኔ ጌታ ለራሱ እንጂ ለሰው ሚያወራ አይመስልም እኮ … እኔም ጥጌን ይዤ በእንባ ተዋጥኩ ቀጠለ … እኔ ከራሴ ጋር መጣላት አልፈልግም ነበር ደስተኛ እና አባቴን ማስደስት ልጅ መሆን ብቻ ነበር ምፈልገው … ከትንሽ ዝምታ በዃላ ድምፁን አፀዳና አሁን ለወቀሳ አይደለም የመጣውት ለአመታት የተሸከምኩትን ከባድ ሸክም ለማቅለል ነው የመጣውት … እኔ ከዚህ በዃላ ያንን አስቀያሚ ሸክም መሸከም አልፈልግም አሁንም ሳያስበው በድጋሚ ለቅሶ ውስጥ ገባ … ህይወቴን በድጋሚ እንዲበጠብጠውና እንዲረብሸኝ አልፈልግም … ሁሉም ለሰራው ዋጋ ይከፈለዋል … አንዳች አይቀርም … እኔም እጅግ ብዙ ዋጋዎችን ከፍያለው ከዚህ በዃላ ግን ሳስታውሰው እንደፍም እየለበለበ የሚያቃጥለኝን ያን ታሪክ ማሰብ አልፈልግም ጥላቻዬን በውስጤ ቦታ ልሰጠው አልፈልግም ፨፨፨፨ ሴትየዋ ልታናግረው ስትጠብቅ የከረመች ይመስል ንግግሯን አክተለተለችው … ሀጥያተኛ ነኝ ሀጥያተኛ ነኝ ብዙ በድያለው ብዙ አጥፍቻለው … ኡኡ አቀለጠችው ሰው ሰማ አልሰማ እንኳን ግድ አልሰጣትም … ረክሻለው የረከስኩ ሰው ነኝ … ለቅሶዋ ቃሏን እያጀበው ማበዷን ቀጠለች … ራሴን መቼም ይቅር አልልም ይቅር መባል አይገባኝም …ቃሎቹን ልክ እንደ ሙዚቃ የተለያየ ዜማ እየሰጠቻቸው ለፈለፈች … ፀፀተኛ ነኝ … ፀፀተኛ ነኝ ፀፀት አለብኝ ፀፀት… ውስጥን እንደ ብል የሚበላ ፀፀት … የማልናገራቸውን ብዙ ህመሞችና ስቃዮችን ተሸክሜያለው … ሰላም አጥቼ ነው የኖርኩት ሰላም አጥቼ ነው የከረምኩት … ልክ ነህ ልክ ነህ ዋጋዬን እያገኘው ነው ገና ከዚህም በላይ አገኘዋለው በደሌን አገኘዋለው የበደሌን ይሰጠኛል … አንተ የተባረክ ሰው ነህ ትንሽ እረፍት አግኚ ሲለኝ ነው አንተን የላከልኝ … … በቤቱ ዝምታ ሰፈነ ቤላ አንገቱን እንዳቀረቀረ ቀጠለ እንደ እናቴ ነበርሽ አሳድገሽኛል አንቺን ይቅር ለማለት ሌላ ምንም ምክንያት አያስፈልገኝም ይቅር ለማለት መፈለጌ ብቻ በቂ ነው … ያን ያደረግሽበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን … ንግግሩን ገታ አድርጎ ትንፋሽ ስቦ የውስጡን ትንፋሽ አወጣ … ምክንያትሽ ምንም ይሁን ምን ከልቤ ይቅር ብዬሻለው ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ተመለከታት … ስላደረግሽልኝ መልካም ነገሮች ሁሉ ከልቤ አመሰግንሻለው … በፍፁም ትህትና ተሞልቶ መናገር ቀጠለ … መልካም ግዜ ይሁንልሽ መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለው ወዲያው ከመቀመጫው ተነስቶ በፍጥነት ከቤቱ ወጣ እኔም ተከተልኩት … ሴትየዋን ልወጣ ስለ በጨረፍታ ተመለከትኳት ደና ሁኚ … በሩን ዘጋውት … ከግቢ ስንወጣ ጥቁር ሻርፕ የለበሱ መንደርተኛ ሴቶች ወደግቢው ሲገቡ ተገጣጠምን … ቅድም ሴትየዋ ስትጮህ ማንም ያልመጣበት ምክንያት አሁን ገባኝ ሁሉም ጎረቤቶቿ ለቅሶ ሄደው ነበር ፨፨፨፨፨፨፨ የኔ ጀግና አፈቅርሀለው እሺ … ማሂ ለመሄድ የቀረኝ እኮ 2 ቀን ብቻ ነው ይሄን ሁለት ቀን ለምን እኛጋር አታድሪም … ስለዚህ እቤት ሄጄ እናቴን ላስፈቅዳታ … የኔ ፍቅር ብታደርጊውማ ምደሰተውን ደስታ አትጠይቂኝ … እኔ ራሱ ቤላዬ ስለዚህ ልሞክር … 11 ሰአት ሊሆን ሲል ወደ ቤት ሄድኩ … እናቴን ቡና እየቆላች አገኘዋት … በትህትና አጠገቧ ቁጭ አልኩ … ውድዬ ስላልሽው ነገር ሳስብበት ነበር እናም ልክ ነበርሽ እናንተ እኮ ህይወቴ ናችሁ ምርጫ ውስጥ ልትገቡ ምትችሉ ነገሮችም አይደላችሁም …ውድዬ ቤላ ከሁለት ቀን በዃላ ነው በረራው … ለኔም ለሱም ያለችን ይቺ ሁለት የተቀናነሰች ቀን ብቻ ናት … ቢያንስ ትዝታ እንዲኖረኝ ፍቀጂልኝ በትንሹ ሀዘኔን ለመቀነስ ተባበሪኝ … ውድዬ ይሄን ሁለት ቀን ዛሬን እና ነገን እነ ቤላ ቤት ልደር … እባክሽን …
Show all...
ሶፋ ላይ ተቀምጣ በነበረችበት ተንበርክኬ ጉልበቷ ላይ ተደግፌ አቀለጥኩት … በስቃይ እና በጭንቀት እምባዬ ፊቴን እየታጠብኩ ልመናዬን ቀጠልኩ … በማርያም ፍቀጅልኝ በምቶጂው አምላክ ይዤሻለው … በማርያም እናቴ በማርያም… ከዚህ በላይ አልችልም… አልቻልኩም … ቤላ ጥሎኝ ሊሄድ ነው … በፍቅር አምላክ እንድሄድ ፍቀጂልኝ … ቆይ እኔ ልጅሽ አይደለውም እንደዚ ስሰቃይ አላሳዝንሽም … እሞታለው መኖር አልችልም … በጣም አፈቅረዋለው በእመቤቴ ማርያም በቃ ፍቀጂልኝ … የማርያም ስም አፌ ላይ የተፃፈ ይመስል ደጋግሜ ስሟን ጠራሁት … አንዳች ነገር ከሰው መጠየቅ ስፈልግ ከሁሉም ቀድሞ የሚመጣልኝ የእሷ የእመቤቴ ስም ነው … እናቴ መልስ ሳትሰጠኝና ሳትከላከለኝ በመገረም ሆና የፈጠርኩትን ድራማ እያየች ነው … በሚያስተዛዝን የድምፅ ቅላፄ እያባበልኳት … ውድዬ መልሽልኛ በናትሽን አትጨክኚብኝ … በዃላ ሚቆጭሽን ነገር አታድርጊ … ውድዬ መልሽልኛ … ትክ ብላ አየችኝና እ ጨረሽ ብላ ማውራት ጀመረች … ያኔ በደንብ ግልፅ አላደረኩልሽም መሰለኝ እኔ የምለውጠው ሀሳብ የለኝም … አንቺ ነሽ ለህይወትሽ ሚያስፈልግሽን ምታውቂው … ከኛ ጋር እዚህ ስትቀሪ የምትሞቺ ከመሰለሽ ያው በሩ … ሳይሄድብሽ ህይወቴ ምትይውን ሰው ተከተይው … ድጋሚ ይሄን ጉዳይ ምታነሺው ከሆነ መጥፎ መጥፎ ቃሎችን ተጠቅሜ ላስከፋሽ እችላለው … ወይ ቤትሽን አክብረሽ ትኖሪያለሽ ወይ ከነ ውልቅ ትያለሽ … እንዳንቺ አይነት ራስ ወዳድ ልጅ ማሳደጌን ግን አላወኩም ነበር ብላ ልክ እንደባለፈው ዛሬም ጥላኝ ወጣች … በጆሮዬ የሰማውትን ቃላቶች እያብሰለሰልኩና ቃላቶቹን ድጋሚ በአይምሮዬ እየሰማው ይህን የተረገመ ቀን አሳለፍኩ … የእናቴ ጭካኔ በጣም ገርሞኛል … ቢያንስ እንኳን ልታፅናናኝ አልሞከረችም … ጳጉሜ 2 ነው … ቤላ ወደ 9 ሰአት ላይ ምውስድሽ ቦታ አለ ብሎኝ ተገናኝተናል … ራቅ ወዳለ ሰፈር ወስዶኝ ውስጥ ለውስጥ ካጎጎዘኝ በዃላ አንዲት ደቀቅ ወዳለች ግቢ ይዞኝ ገባ … ሰርፕራይዝ ስለሚወድ እኔም ማን ጋር ነው ብዬ አልጠየኩትም … ልክ ስንገባ በሩ ጋር የቆመውን ልጅ … ወ/ሮ ጥሩነሽ አለች ብሎ ጠየቀው … ልጁም አዎ አለች በማለት ፊት ለፊት ወዳለው ቤት ጣቱን ጠቆም አደረገ … ይሄኔ አፌን መቆጣጠር አልቻልኩም … ቤላ ማናት ወ/ሮ ጥሩነሽ ? … በቀስታ ወደፊቴ ዞር ብሎ በህይወቴ ውስጥ ያለችው መጥፎ ሴት … ብሎ መለሰልኝ ፀሀፊ ~ ረድኤት @Red_ii📝 💞●●● ስሜቶቼ ●●●💞
Show all...
#ማሂ ◈◈ ክፍል 38❣◈◈ ከፍቶኛል … ለቤላ እውነቱን ንገሪውና እውነቱን አትንገሪው እያሉ የሀሳብ ጭንቀት መአበል ውስጥ የከተቱኝ ሁለት ተቃራኒ ሀሳቦቼ እርስ በእርስ ተጋጭተው እኔንም ከራሴ ጋር አምታተው አጋጩኝ … እናቴንና ቤተሰቦቼን አጨልሜ የቤላን ብርሀን ልከተል ብዬ ሳስብ … ፀፀቱን እፈራዋለው አለምን ያለነሱ መቋቋም የማልችል መስሎ ይሰማኛል … እናቴን ተቀብዬ ቤላን ለመከተል ያሰቡትን እግሮቼን ካስቆምኩኝ ደግሞ ያለሱ ምኖረው ዳፍንታም የጨለመ እርባና ቢስ ህይወት ከፊቴ ይጋረጣል… በህይወት ውስጥ ብዙ ከባባድ ነገሮችን አይቼ አውቃለው … ከሁለት ለኛ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች የመምረጥን ያክል ከባድ ነገር ግን የለም … አዎ በድፍረት መናገር እችላለው ምርጫ እጅግ ከባዱ የህይወት ውሳኔ ነው … ምርጫን ከባድ የሚያደርገው ትልቁ ነገር ደሞ ባልመረጥነው አንደኛው ነገር ውስጥ የምናጣውን ነገር መፍራታችን ይመስለኛል … ራስ ወዳዶች አይደለን ሁልግዜም ለራሳችን እንፈራለን … በማግኘታችን ማጣጣም ባለብን ግዜ ላይ ስለማጣት እና ስለመለየት እንሰጋለን ለነገሩ ካለልምዴ ይሄ ከባድ የህይወት ውሳኔ አስጨንቆኝ እንጂ ማጣትና መለየትን በመፍራት ዛሬን ከማይደሰቱን ሴቶች መሀል ሆኜ አይደለም … ነሀሴ 25 ነው … ቤላ ለማታ ቀጥሮኛል… ረጅም ጥቁር ቀሚስ እንዳደርግ ታዝዣለው … ረጅም ጥቁር ቀሚስ ስለሌለኝ ከጎደኞቼ ፈለግለግ አድርጌ ለምሽቱ የሚሆን የዕለቱን ዝግጅቴን ጨርሻለው … ጥቁር ልብስ ስለብስ አጉል ከምቀላው ነገር ተደምሮ ውብ ሆኛለው … የት እንደሚወስደኝ አላውቅም 12: 30 ላይ ሰፈር አካባቢ ከአስፋልቱ ባሻገር መጥቶ በባጃጅ ወሰደኝ … ባጃጁ አሽሎክሎኮን አሽሎክልኮን የሆነ የምሽት መዝናኛ ጋር ጣለን እንደለመደው እጄን ይዞ እየመራ ወደ ውስጥ አስገባኝ … ውው ውው ጭብጨባ እና ጩሀት የማየውን ማመን አልቻልኩም … የኔና የቤላ የጋራ የክፍል ጎደኞች ባሚ መሲና ሜሪ … ወዲህ ደሞ ላሞሪና ዮኒ … ዞር ስል የቤላ የሙዚቃ ቤት ጎደኞች … ለምን እንደጮሁ ባይገባኝም ናፍቄ የቆየዋቸውን ጎደኞቼን ተራ በተራ በማቀፍ ላይ ነኝ … እነ ሜሪ ከክፍል ደብቀን የቆየነውን ፍቅራችንን ዛሬ ይፋ ስላዩብን ትንሽ እንደማፈር ብያለው … የምሽት መዝናኛ ቤቱ የመናፈሻ ይዘት ያለው ግቢ ነው … ውስብ በሚያረጉ ሞቃት ብርሀኖች ዙሪያውን ተከቧል … ለስላሳ ሙዚቃ ተከፍቶበት የነበረው ቤት ወዲያው በዳዊት ፅጌ '' እወድሻለው '' ሙዚቃ ተናወጠ … ቤሌ ከጎደኞቼ አላቆ ለሁሉም እኩል ምንታይበት ዋናው ቦታ ላይ ይዞኝ ቆመ … እንዴት አድርጌ የሆዴን ላሳይሽ ምን ቃል ተናግሬስ ውስጤት ልግለፅልሽ ጨነቀኝ ጠበበኝ ጠፋኝ የምልሽ እወቂልኝ ባክሽ እንደምወድሽ … የሙዚቃው ዜማና ግጥም ከቤቱ ሞቃት ብርሀን ጋር ተዳምረው ልብን ፍዝዝ ያደርጋሉ … ቤላ ከኪሱ የልብ ቅርፅ ያላት ቀይ የቀለበት ሳጥን አውጥቶ እፊቴ ተንበረከከ … ሳቂ ሳቂ አለኝ … አልቅሺ አልቅሺም አለኝ … ዞር ብዬ እንግዶቻችንን አየዋቸው ሁሉም ቆመዋል … ሁሉም ከልብ በመነጨ ፈገግታቸው ቀጥተኛ ያልሆነ የእሺ በይው ማበረታቻ እየሰጡኝ ነው … ሳላስበው ከት ብዬ ሳቅኩኝ … መለስ ብዬ ደሞ በፍቅር የሚያዩኝን የቤላን ፍቅር የሆኑ አይኖች በፍቅር አየዋቸው … በኖርኩበት እድሜ በስካሁን ዘመኔ እንዳንቺ ምወደው ሰው የለኝም እኔ ትላንትናም ዛሬም ነገም ለከርሞው ልቤ አይለወጥም ሁሌም ያንቺው ነው ዘፈኑ እንከን የለሽ ነው …እየሳቅኩ አለቀስኩ … ከሀዘን ይሁን ከደስታ የመነጨ ግን እንጃ … ቆሜ ከነበረበት ከቤላ ፊት ዝቅ ብዬ ተንበረከኩ … በዙሪያችን ሰዎች መኖራቸውን ረሳውት … በአይኖቹ ውስጥ ጠፋው … ቤላ የቀለበት ሳጥኑን ከፍቶ እጄን እየጠበቀ እንዳለ … ማሂ አፈቅርሻለው አለኝ … ቀልጠፍ ብዬ ግራ እጄን ሰጠሁት … እኔም አፈቅርሀለው … ቀለበቷን በደስታ መፍነክነክ ተሞልቶ የቀለበት ጣቴ ላይ አጠለቀልኝ … ቤቱ በጩሀት ተሞላ … ለጥ ባለው ሰፊ ሰማይ ላይ እንደፈለጋት እንደምትንሸራሸረው ቢሪቢሮ የሆንኩ መሰለኝ … ክንፍ አላወጣውም እንጂ በልቤ በርሬያለው … ተንበርክከን ከነበርንበት ተነሳንና ዘፈኑ እስከሚያልቅ ተቃቅፈን ደነስን … እንደ አዲስ ህፃን ጡት እንደሚጠባ ፍቅርሽ ተናፋቂ ልጅ ነው ሆድ ሲያባባ ልጅማ እያደሮ ሲያድግ አፍ ፈቶ ያወራል ትልቁ መውደድሽ ገና ይኮላተፋል …ወገቤን በእጆቹ እቅፍ አርጎ ከሰውነቱ አጣብቆኝ እኔም እጆቼን አንገቱ ላይ አቆላልፌ ተደግፌው አይን ለአይን እየተያየን እግራችን እነዳዘዘን እየደነስን ነው … በቀኝ በኩል ወደ አንገቴ ጠጋ ብሎ በጆሮዬ አንሾካሾከልኝ … ይሄ ዘፈን ያንቺ ዘፈን ነው… ምንም እንደማታቅ ልጃገረድ መሽኮርመም ጀመርኩ እንዴት ሰው ከራሱ በላይ ሰውን ይወዳል እንዳላልኩኝ ያኔ ዛሬ በኔ ደርሷል ከኔ በላይ አንቺን አንቺንም ከራስሽ ልማል እኔ ልሙት በጣም ነው ምወድሽ ልቤን የደስታ ሙቀት ሞቃት ዘፈኑ አለቀና የቡዙአየው ደምሴ የህልሜ ንግስት ዘፈን ቦታውን ተካ … ማመን አቃተኝ የህልሜን ንግስት የኔ አረኩና ብሩህ ቀን መጣ ሂወት ሊታደስ ባንቺ እንደገና ማን አለ እንደኔ እድል የቀናው ቀን የወጣለት ምኞት ውጥኑ የሰመረለት በፍቅርሽ ዜማ ኑሮው ተቃኝቶ ብርሀን ተሞላ የኔ አለምማ … የሆነች ቆንጅዬ አስተናጋጅ መሀል ለመሀል ያለው ጠረጴዛ ላይ ኬክ, የኬክ ሳህኖች , የወይን ጠርሙሶች እና ርችት ምናምን እያሰናዳች ነው … ሁላችንም ወደ ጠረፔዛዋ ቀረብን … እንደው እግሬ ለስሙ አቆመኝ እንጂ ልቤ ክንፍ ብላ በደስታ እያበደች ነው … ነፍሴ በደስታ ሰክራለች … እኛን ጨምሮ ጠረጴዛዋን 10 ሰዎች ከበናታል … ላምሪ አጠገቤ ናት … ምንም የማላቀው ፊት ስለሌለ ምሽቱን ሙሉ ራሴን ነበርኩ … አልፈራም ነገን እንዳላይ አንቺ አለሽና በፍቅርሽ ከፍ ያደረግሽኝ እንደደመና ንግስቴ የቤቴ ግርማ የንጋት ጮራ አምሮብኝ ታየው በይፋ ጎኔ አለሽና እውነተኛ ደስታ ለሰው ይጋባ የለ … ሁሉም ከልባቸው ተደስተዋል … እኔና ባሌ ኬካችንን ቆርሰን ወይናችንንም ተጎንጭተን እጮኝነታችንን በይፋ አወጅን … ሁሉም ሰው ሞቅታ ውስጥ ገብቶ ምሽቱን እጅግ የማይረሳ ምሽት አደርገን አሳለፍነው … የኔ ብረት መዝጊያ ባል በኮንትራት ባጃጅ ሰፈር አድርሶኝ ተመለሰ ያለአቅሙ ጠጥቶ ከልክ በላይ እንደሰከረ ሰካራም … ልቤም ከአቅሙ በላይ ተደስቶ እግሬ እዚያና እዚህ እየረገጠ ቤቴ ደረስኩ … ሌሊቱን በሙሉ ስላሳለፍኩት ምሽት እያሰብኩ ቀለበቴን አየት አረጋለው … ከቀለበቱ ፕሮግራም በፊት ስጨነቅበት የነበረውን ጉዳይ እርስት አርጌ በደስታዬ እየተደሰትኩ ነው … የዛሬን ምሽት ጭንቀት እንዲበክልብኝ ስላልፈለኩ ደስታዬን እያሽሞነሞንኩ እንቅልፍ ወሰደኝ … ቤላ ጳጉሜ ላይ ስለሚሄድ የዛን ሰሞን ቢዚ ላለመሆን ለአመትበአል የማደርገውን የቤት ፅዳት ካሁኑ ጀምሬያለው … … እንዴት እንደሆነ አላወኩም ደሞ ምንም አላሰብኩበትም … ብቻ ራሴን እናቴን እያለቀስኩ ስለምናት አገኘውት … በማርያም በማርያም በጌታ በእናትሽ ቤላን በጣም ነው ማፈቅረው እባክሽን ተረጂኝ …
Show all...
#ማሂ ክፍል 37 🖤 መንገዳችን አንድ ቢሆንም ሁሌም በአዲስ መልኩ እያጎጎ ጣፋጭ እርካታ ያረካኛል … የፍቅር ጥማቱን ተወጥቶ በእርካታ ከጨረስን በዃላ … ማሂ ያልሽው ነገር ግን ምንም ምቾት አልሰጠኝም … ወይ ካልሆነ እናትሽን አብረን እናናግራት … ከአፉ እንኳን ሳላስጨርሰው አይ አይ ቤላ የምር ይቅር እሷ ሀሳቧን የምትቀይር ሰው አይደለችም … የኔ ፍቅር ይሄንንስ መፍቀዷ አትልም በቃ እሺ በለኝ እባክህ በቃ እኔንም ከዚህ በላይ አታስጨንቀኝ … አልጋው ላይ ተጋድመን ባለንበት ምንም መልስ ሳይሰጠኝ አንገቴ ስር ገብቶ ተሸጎጠ … እያቃጠለ እንደሚያስደስት እሳት የሚሞቀውን የሚቆራረጥ ትንፋሹን በአንገቴ በኩል አርጎ ለመላ ሰውነቴ እየለገሰ በዛው ብዙ ቆየን … ማሂ ይሄን እቅፍ በደንብ አጣጥሚው ትንፋሹንም እስከ ህይወት ዘመንሽ እንዲቆይ አድርገሽ በደንብ ሙቂው ምክንያቱም በነዚህ እጆች መታቀፍ በከንፈሮቹ መሳም በአይኖቹ መታየት ብቻ ከሱ ጋር ያለሽ ሁሉም ነገር ወደ ማብቂያው እየደረሰ ነው … ውስጤ ውስጥ ያለችው ሴት እንዲህ እንዲህ እያለች ዝም ብላ ትለፈልፋለች … አንዱ አይኔ ለምን እንደደረቀ ባላውቅም አንደኛው አይኔ ግን ያለማቋረጥ እያነባ ፊቴን አርሶታል … ሁሉንም ነገር ልነግረው እልና ያለችንንም ቀሪ ግዜ ጥሩ ባልሆኑ ትዝታዎች ማጨቅ ነው ብዬ አስባለው … ሁሉንም ነገር ልነግረው እልና ከነገርኩት በዃላ የሚመጣውን ሀላፊነት መውሰድ የማልችል ነኝ ብዬ ራሴን አሳንሳለው … ብቻ አሁን የውሸቴን ድራማ ጥሩ አርጌ እየተወንኩ እሱ ዘንድ አለው … የሚፈሰውን እንባዬን ከስር ከስር በጄ ጠረኩና ቤላን በድጋሚ እሺ እንዲለኝ ወደማሳመን ገባው … በቀስታ ከአንገቴ ስር አወጣሁትና ወሬያችንን ቀጠልን … ማሂ ቃል ግቢልኝ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ላልተውሽ ላትተይኝ … በስስት የሚያዩኝ አይኖቹን ሳያቸው አሁንም እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ … የኔ ፍቅር … በድጋሚ አቀፍኩት … ቤ/ክ የተገባባነው ቃል እኮ ከምንም በላይ ነው … ደሞ ስለቃላችን ሳይሆን ስለፍቅራችን ነው ምንታመነው … ህይወቴን በጭራሽ ካንተ ውጪ አላስበውም ትላንቴም ዛሬዬም ነገዬም አንተ ነህ … ከፊቴ ላይ እንባዬን እየጠረገ … እሺ የኔ ፍቅር ታዲያ ለምንድነው ምታለቅሺው … ቀለል አርጌ ፈገግ እያልኩ ፍቅርህ ነዋ ሚያስለቅሰኝ … የኔ ቆንጆ ከዚህ በዃላ ምንም አይነት እንባ በኔ ምክንያት ከአይንሽ አይፈስም እሺ … አስበሽዋል ማሂ ከመተኛቴ በፊት ለመጨረሻ ግዜ የማይሽና ከእንቅልፌ ስነሳ ለመጀመሪያ ግዜ የማይሽ ሴት ልቶኚ ነው … እጆቼን በእጆቹ ሙቀት እያሞቃቸው እነዚህን ውብ አይኖችሽን እያየው የምተኛበት ቀን ሩቅ አይደለም … በፍቅር ተሞልተን ራሳችንን የምንሆንባቸው ቀናቶች እየቀረቡልን ነው … ቤተሰቤ ልትሆኚ ነው አካሌ ላረግሽ ነው የመጨረሻዬ ልትሆኚ ነው … ቅንድቤን እና ፊቴን በስሱ እየዳበሰኝ … ማሂ ለምን ዝም አልሽ አንቺስ ምንም አላለምሽም አለኝ … ሁልግዜም የኔ ፍቅር ይሄን ሳስብ ልቤ ይሞቃል … ከልቤ ፈገግ እላለው … እሺ ግን ደና ነሽ አይደል ለሞንድነው ተቀዛቅዘሽ የምታወሪኝ … ንገሪኝ ያስጨነቀሽ ነገረ አለ … ማሂ መስማት እፈልጋለው … ትክዝ ድንዝዝ ካልኩበት ነቃውና የውሸት ፈገግታ ፈግጌ … no no የምር ምንም የለም … ቆይ አታምነኝም … እኔ ቃሎችሽን ብቻ ሳይሆን ሁለነገርሽን ነው ማምነው ለዛ ነው እየጠየኩሽ ያለውት … አፈቅርሀለው ምንም ሌላ ነገር የለም አሁን ቤት አድርሰኝ … እንደለመድነው ኮንትራት ባጃጅ ይዘን ሄድን አንገቱ ስር ጋደም ብዬ በትንፋሼ በደስታ ስቅጥጥ እያደረኩት ሰፈር አደረሰኝና ተለያየን … … ቤላ ያልኩትን አምኖ እና ተስማምቶ ነሀሴ 10 ቀን አዲስ አበባ እንግሊዝ ኤምባሲ ሄዶ ሂደቱን ጀመረ … ከአጎቱ የተላከለትን ደብዳቤ አቅርቦ ለተወሰነ ግዜ የቪዚት ቪዛ እንዲሰጠው ጠየቀ እዛ ያሉት ሰራተኞችም ለኢንተርቪው በቀጣይ ሳምንት ቀጥረውት ተመለሰ … ከሳምንት በዃላ በተባለው ቀን ሸገር ሄዶ ኢንተርቪውን በተሳካ ሁኔታ አደረገ … አጎቱ ደብዳቤውን ሲሞላ በሞላው ፎርም መሰረት የተጠየቀውን ጥያቄዎች ሁሉ ጥሩ አርጎ መለሰ … አጎቱ ያለበትን ስኬታማ የህይወት ደረጃ ባማከለ መልኩ ቤላን ብዙም ሳያንገላቱት ቪዛ መቱለት እድሜ ልኩን ሲፈልገው የነበረው ህልም ተሳካለት … ይሄን ሰሞን አዲስ አበባ ያለውን ጉዳይ ፅድት አድርጌ ሂደቱን እስክጨርስ ብሎ አዲስ አበባ ያለው አጎቱ ጋር አርፏል … እኔንም ከነሱ ጋር ሊያስተዋውቀኝ እንደሚፈልግና ባጠቃላይ ከተስፍሽ ጋርም ጥሩ የቤተሰብ ግዜ ሊያሳልፉ እንዳሰበ ነግሮኝ ነገ አዲስ አበባ ደርሶ መልስ እንድመጣ ቀጠሮ አስይዞኛል … እኔ እንዳለው አለው … ከእናቴ ጋር ከዛን ቀን ጀምሮ አውርተን እንኳን አናውቅም … አይኗን ባለማየት… እሷን ባለማውራት እና ቤት ውስጥ ሀዘን ብቻ እየፈጠሩ ደስታን በማጥፋት ጥሩ አርጌ እየቀጣዋት ነው … ከቤላ ጋር ተራርቀን ሳለ በስልክ በምናወራባቸው ግዜያቶች ላይ የሱ በህልም በተስፋ እና በደስታ የተሞላው ድምፅ ከኔ በሀዘን በጭንቀት እና በእልህ ከተሞላ ድምፅ ጋር አልጣጣም አለ … እንደዚህም ሆኖ ግን ትወናዬን ያለማቋረጥ ስለምተውን እሱ አይደለም ሊያውቅ ቀርቶ ሊገምት እንኳን አልቻለም … ይሄን ሰሞን አይደለም ከቤት መውጣት ቀርቶ ከእንቅልፌ ባልነሳና በዛው እያሰብኩ ቢመሽ እራሱ ደስተኛ ነኝ … ሰው የሚባል አስጠልቶኛል … በተቻለኝ መጠን በዚም በዚያም ብዬ በቤቴ ውስጥ ራሴን ቆላልፌ አስቀምጫለው … ሌሊት ይሁን ቀን በሚያጠራጥር መልኩ አይኖቼ በሰበብ በአስባቡ በእንባ እየታጠቡ ነው … ባሁኑ ትንሽ ለየት የሚለው ሀዘኔን እና ለቅሶዬን ለእናቴ አለመደበቄ ነው … ለማልቀስ እንደድሮው መደበቅና መሸጎጥ አልተጠበቀብኝም … ከዚህም የበለጠ ስብራቴንና ስቃዬን እንድታውቅልኝ ሆነ ብዬ አኩርፌያትም ሳለው እንኳን የልቤን ሀዘን አጠገቧ አዝናለው … ብቻ እሷም እንዳለች አለች … እንዴት ይሄን ሁሉ ቀን እንዳስቻላት ባላውቅም እስካሁን እኔም እንዳኮረፍኩ እሷም ዝም እንዳለችኝ አለው … ነገ ከሰዎች ስለምቀላቀል ብዬ ዛሬ አይኖቼን ከማልቀስ ታድጌ ለነገው ቀን ውበቱ ጥሩ እንዲሆን በሚል በመተኛት ተንከባከብኩት … ራሴን ከተንከባከብኩ ስለቆየው ነው መሰለኝ ነቃ ነቃ ብዬ ስሜቴን ለወጥወጥ ሳረገው ለወትሮው ከቦኝ የነበረው ተስፋ የቆረጠ ሰው ገፅታ ተለወጠ … ለጉዞሞ ለጥሪም የሚመች አሪፍ ልብስ ለብሼ ፀጉሬንም በሚያምርብኝ ስታይል አሳምሬና ፊቴን በአንዳንድ ነገሮች አስውቤ ዝግጅቴን ጨረስኩ … በእርግጥ ዛሬ ናዝሬት በትንሹ ከብርዱ ወከክ ብትልም አዲስአበባ አትታመንምና ጃኬትም አድርጌያለው … ነፈስፈስ በሚለው አየር 8 ሰአት አካባቢ ከቤት ወጣው … ቤላ አዲስ አበባ መናሀሪያ ተቀብሎኝ ጉዞ ወደ ቦሌ … ለቦሌ ሰፈር ድምቀት ከሆኑት ቤቶች ውስጥ አንደኛው ስዕል የመሰለ ቤት ውስጥ ገባን … ያሁኑ ፍርሀት ለየት ያለ ነው … በቤቱ ውስጥ የቤላ አጎት የአጎቱ ሚስት እንዲሁም የነሱ ሁለት ወንድ ልጆች እና ተስፍሽ አሉ … ብቻ ምን ልበላችሁ የሚያስፈራ ፍርሀት ነው በቤቱ ያለው … የቤላ የአጎቱ ልጆች የቤላ እኩዮች ናቸው በእርግጥ ቆንጆ ናቸው ከቤላ ሚለያቸው እንደ ቤላ ቸኮላት ከለር አለመሆናቸው ብቻ ነው …
Show all...
…ተስፍሽም በመኖሩ ቀስ በቀስ ከያዘኝ ፍርሀት ለቀቅ አልኩ … ከሚገባው በላይ እንደ ትልቅ እንግዳ አስተናግደውኝና አክብረውኝ ጥሩ ግዜን ከዚህ ቤተሰብ ጋር በጋራ አሳለፍኩ … 1 ሰአት አካባቢ ለመሄድ ተነሳው … ቤላም መናሀሪያ ድረስ ሊያደርሰኝ ከቤት ይዞኝ ወጣ … ትንሽ ወክ እናርግ ብሎኝ ወክ እያረግን ሳለ ስንፈልገው የነበረውን ጥሩ ጨለማ አገኘንና ሁለታችንም እራሳችንን ሆንን… በአንዴ ሌላኛው በፍላጎት የተሞላው አቤል መጣ … ፍላጎታችንና እብደታችን በሰፈረልን ቁና ለመሰፈር እየተጣደፍን እና እየተጣጣምን ሳለ አንድ ተንከሲስ መኪና ሀሳባችንን አኮላሸብን … አምሮታችን ላይ ውሀ ከልሶ ከጋልንበት አቀዘቀዘን … ወዲያው እንደ ጨዋ ሰው እየሳቅን ጉዞ ወዳቋረጥነው መንገዳችን … መናሀሪያ ስንደርስ ከንፈሬን በጣፋጭ ከንፈሩ አንገቴን ደሞ በጣፋጭ ትንፋሹ ካሞቀኝ በዃላ … ታክሲ አሳፍሮና እንደለመደው ለረዳቱ ሂሳብ ከፍሎ ተለያየን … ሰው እንዴት ነው አካሉ ከሆነ ሰው ጋር ሚለያየው ቤላኮ የማፈቅረው ሰው ብቻ አይደለም … ቤላ አካሌ ሆኗል እኔና እሱ እኮ አንድ ሆነናል … እንዳጋጣሚ የደረሰኝ መቀመጫ ጥግ ላይ ስለነበር ለማልቀስ የሆነ ስሜት ይሰጣል … የዝምታ ለቅሶዬን እዬዬዬን ተያያዝኩት … እንጃ ብቻ ብዙም ሳላመሽ ቤት ደርሻለው … ከቤላ ጋር የተላፋውት ይሁን መንገዱ ባላውቅም ድክም ብሎኛል … ከቀናቶች በዃላ …ቤላና አጎቱ ተነጋግረው የቤላ የመብረሪያ ቀን ጳጉሜ 4 እንዲሆን ተስማምተዋል … የመብረሪያ ትኬቱንም ቤላ እዚህ ቆርጦ ገንዘብ ከሚያወጣ ብሎ የሚበርበትን ትኬት ኢሜይል አድርጎለታል … ቤላም ኢሜይሉን ፕሪንት አውት አድርጎ ወረቀቱን ይዞል … ከኢትዮፕያ ውስጥ ጠቅልሎ ለመውጣት የቀረው ጊዜ ከ 10 ቀን ያላለፈ ግዜ ነው … አሁን ወደ ናዝሬት ተመልሷል … ይሄን ሰሞን አንድ የማቀው ነገር እኔ እኔን አለመሆኔን ብቻ ነው … በቃ በድኔ ነው ያለው … ምንም አይነት ነገር እያደረኩ አይደለም … ከማን ጋር ታግዬ ከማን ጋር ማሸነፍ እንዳለብኝ እንኳን አላወኩም … ቆይ እናት ናት ወይስ የህይወት አጋር ነው ሚበልጠው … እውን ደሞ እነዚህ ነገሮች ይወዳደራሉ … እንጃ አላውቅም ፀሀፊ ~ ረድኤት ( @spy_girll ) @Red_ii 💚💜
Show all...
…… ስጨነቅ ጠቆርቆር እላለው ቆዳዬ ወዘናው ይጠፋል … ጨጎራዬንም ስለሚያመኝ በብዙ ነገር dis order እሆናለው … ዛሬ ከቤላ ጋር የቤላ ክፍል ውስጥ ነን … እየመሻሸ ነው የክፍሉን መብራት አጥፍተን ተቃቅፈን ተኝተናል ከረጅም የዝምታ መተቃቀፍ በዃላ ድምፄን ከፍ ባረግ ህፃን ልጅ እቀሰቅስ ይመስል በቀስታ ማውራት ጀመርኩ … የኔ ፍቅር …ከንፈሬን እየሳመ ወዬ ብሎ ምናገረውን እየጠበቀኝ ነው … በቃ አንተ ቀድመህ ሂደቱን ጀምር … በፍጥነት የክፍሉን መብራት ለማብራት ቀኝ እጁን ወደ ግድግዳው ከፍ እያደረገ በተደናገጠ ድምፅ ለምን ብሎ መለሰልኝ … የድምፄን ስሎው ሞሽን ጠብቄ … ቤላ ተው አታብራው ምን መሰለህ እኔ የኢንትራንስ ውጤት ከመጣ በዃላ ሂደቱን እንድጀምር እናቴ ፈቅዳልኛለች … እንዴ ማሂ ቆይ አሁን ጀመርሽ ያኔ ጀመርሽ ለሷ ልዩነቱ ምኑ ላይ ነው …እኔንጃ ቤላ ይሄንን ብቻ ነው አስረግጣ የነገረችኝ … አታስብ የኔ ፍቅር እንዲም እኮ አሪፍ ነው … አንተ ቀድመህ ሂደቱን ከጀመርክ በዃላ ቀድመሀኝ ትሄዳለህ … ለንደን ያለውን ሁኔታም ይበልጥ አስተካክለህ ትጠብቀኛለህ … የኔ ፍቅር እንደውም ጥሩ ነው አይደል … አይ እኔ አልመለለኝም እጅሽን ይዤሽ ከሀገር እንድወጣና እጅሽን ይዤሽ ለንደን እንድንገባ ነው ምፈልገው … ቤላዬ ምንም ለውጥ የለውም እኮ እኔ እንደሆን እከተልሀለው ስለዚህ እሺ በለኝ የኔ ፍቅር አንተ እዛ ያለውን ሁኔታ አስተካክል እኔም እዚህ ያለውን ሁኔታ አስተካክዬ ለንደን እንገናኛለን … ቤላዬ እሺ በለኝ … እያወራው ባለውበት በድጋሚ ከንፈሬን ጎረሰው … በጣፋጭ አለማችን በድጋሚ የፍቅር ሲቃ ውስጥ ገባን… ፀሀፊ ~ ረድኤት @ABEN_E 📄📃
Show all...