cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Peace for Ethiopia®™

Join for truth!! @selamethiobot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
197
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

" ብልጡ ፍቅርሽ ሲያጃጅለኝ የጫርኩት" (መልአኩ ስብሐት ባይህ) ************************** የውበት ዳርቻ የአድማሷን መባቻ። አንቺን የእኔን ጠሀይ የተድላዬን ሰማይ። ልስልሽ ፈለጌ ምስልሽን አጣሁት ከምስሌ አድርጌ። ከስብዕናሽ ጠለል ከሀሳብሽ ከፍታ አየሁኝ በሳቅሽ ጨረቃ ተከፍታ። ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ ጨረቃ ያቺ ድንቡል ቦቃ አንቺ ስትፈዢ ይሆን ምትነቃ? አንቺ እንደሁ አትፈዢ ከቶ አደበዝዢ በመውደድሽ ሸጠሽ ታደርጊያለሽ ገዢ። ያውም በሠላሳ ያውም በሠላሳ ክደሸ ስታበቂኝ ምንም እማልመስልሽ በገደልሽኝ ቁጥር ሳትሞች ምሞትልሽ በገፋሽኝ ቁጥር ሳትወድቂ ማነሳሽ በሸጥሽኝ መጠን ልክ ለመክሰር ምገዛሽ ይሁዳ ነሽ አንቺ እኔ ደግሞ ጌታሽ።
Show all...
ሰላም ውድ የጅጋ ልጆች ለተማርንባቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በቤታችን ተጠቅመን ያስቀመጥናቸውን መፅሀፍት የበዓል ስጦታ አድርገን እንድናበረክት የቀረበው ሀሳብ በብዙዎቻችን ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ሀሳቡ ሲንሸራሸር መቆየቱ ይታወቃል በዚህ ሂደትም ብዙዎቻችሁ አይዟችሁ የቻልነውን ለማድረግ ዝግጁ ነን ብላችሁናል የተወሰናችሁ እህት ወንድሞቻችንም የቻላችሁትን አበርክታችኋል ለዚህም ላቅ ያለ ምስጋና በትምህርት ቤቶቻችን ስም እናቀርባለን። አሁን የፋሲካ በዓል መቃረቡን ተከትሎም የተግባር እንቅስቃሴ ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለብን የመፅሐፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ያምናል ስለሆነም በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት የአሳያችሁ የከተማችን ተወላጆች እንዲሁም እስካሁን ፍላጎታችሁን በይፋ ያልጉፃችሁ ግን ደሞ የማበርከት ፅኑ ፍላጎት ያላችሁ እህት ወንድሞቻችን ሀሳባችንን ወደተግባር መለወጡ ላይ በንቃት እንድትሳተፉ በእየ ከተማው የሚገኙ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ጋር ተነጋግራችሁ መፅሀፍቱ በአንድ የሚሰበሰቡበትን ሁኔታ እንድታመቻቹ በታላቅ ወንድማዊ ፍቅር እንጠይቃለን። ጅጋ ያላችሁ እና ለበዓል ወደ ጅጋ የምትመጡ መፅሀፎችን በአካል ጅጋ ለሚገኘው አሰባሳቢ ኮሚቴ ማበርከት የምትችሉ ሲሆን ጅጋ መገኘት እና መምጣት የማትችሉ ደግሞ ለጓደኛ በመላክ በቅርብ ለሚገኙ ኮሚቴዎች በማቀበል እንዲሁም ሌሎችን አማራጮች በመከተል መፅሃፍቶችን ለትምህርት ቤቶቻችሁ ማበርከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። አንድ ሆነን ከተባበርን ማሳካት የማንችለው ነገር የለም እና በወንድማማችነት ፍቅር ተመስርተን በጋራ ለአላማችን መሳካት ጠንክረን እንስራ በእየከተማው የተመደቡ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ዝርዝር ጅጋ 1. ጌታቸው ምህረት 0922271942 2. መስፍን ሞሴ 0918558014 3. መምህር አለሙ 0910051731 4. ኪዳነማርያም አባተ 0922403219 አዲስ አበባ 1ኛ. አይሸሽም ጥበቡ 0913169731 2ኛ. ማማሩ መኳንንት 0918496350 3ኛ. ደመቀ ገብያው 0900004569 ባህር ዳር 1ኛ. ባንታየሁ ደምሴ 0922403970 2ኛ. መልካም አስናቀ 0912676469 3ኛ. ተዋቸው ሞላ 0939716353 ጎንደር 1ኛ. ዮሴፍ ወርቀልዑል 0918505178 ደሴ 1ኛ. ህግነህ ፈንታሁን 0934114622 #ይህን መልዕክት በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች በማጋራት ለእህት ወንድሞቻችን እንዲደርስ ያድርጉ
Show all...
#ሰሙነ_ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ #ሰኞ #መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። #አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። #ማክሰኞ #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። #የትምህርት_ቀን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። #ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። #የእንባ_ቀን_ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። #ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። #ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። #ቅዳሜ #ቀዳም_ስዑር_ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። #ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። #ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። መልካም ህማማት
Show all...
የብልጽግና አባል ሆኜ መቀጠል ይከብደኛል ሲሉ በአማራ ክልል ራያ ቆቦ ውሀና ኢነርጂ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ተናገሩ፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን በዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረጉ በርካታ ጥቃቶች በተለያዩ አካባቢዎች እየፈጸመ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከሰሞኑም በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ እና አካባቢዋ ላይ እስካሁን ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ዜጎችን ህይወት አሳጥቷል ቤት ንብረትም ወድወሟል ከ250 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው አፈናቅለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ነው የራያ ቆቦ ውሀና ኢነርጂ ፅህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ወልደትንሳይ ገብረ ሚካኤል ከኦሮሚያ ብልጽግና ጋር በአንድ ድርጅት ውስጥ በሀላፊነት መቀጠል አልችልም ብለው ዛሬ መልዕክታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰፈሩት፡፡ የኦሮሚያ ብልጽግና ኦነግ ሸኔ ላይ እርምጃ ይወስዳል ብዬ ስለማላምን በአንድ ድርጅት ውስጥ በሀላፊነት መቀጠል ይከብደኛል የሚለውን የማህበራዊ ድረገጽ ጽሁፋቸውን ተመልክተን ጉዳዩን ለማጣራት ደውለንላቸው ከብልጽግና ፓርቲ ጋር አልቀጥልም ማለታቸው እውነት መሆኑንም ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጠዋል፡፡
Show all...
በስቅላት ወንጀለኞችን ከሚቀጡ የአለማችን አምስት ሃገራት መካከል አራቱ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ መሆናቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ በመላው ዓለም ከተፈፀሙ 483 የሞት ቅጣቶች መካከል 88 በመቶ ያህሉ በኢራን ፣ ግብፅ ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ኢራቅ የተፈጸሙ ናቸው፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በዛሬው እለት ባወጣው ሪፖርት መሰረት በ 2020 ዓመት በመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ የተፈጸሙ የሞት ቅጣቶች 437 ያህል ሲሆኑ በ 2019 ከተፈጸሙ 579 ያህሉ ያነሰ ሁኗል፡፡ ባለፈው 10 ዓመታት የሞት ቅጣት በመላው ዓለም ቢቀንስም የቻይናን ሪፖርት ማካተት ግን አልተቻለም፡፡ በግብጽ በአንድ ዓመት 107 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ከነዚህ መካከል 23ቱ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ግጭት አስነስተዋል በሚል ክስ ቢሆንም የአልሲሲ አስተዳደር በራሱ ከፍተኛ ጥያቄ የሚነሳበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በስምኦን ደረጄ
Show all...
ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለመራጭነት የሚመዘገቡበትን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ይፋ አደረገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለመራጭነት የሚመዘገቡበትን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ይፋ አድርጓል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁን እና ሂደቱ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ማቅረቡ እና ምክክር እንደተደረገበት ምርጫ ቦርድ ገልጿል። በዚህም መሠረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ይፋ አድርጓል። ተማሪዎቹ ለመራጭነት የሚመዘገቡበት ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) http://www.nebe.org.et/ovrs እንደሆነ ነው የተገለጸው ከምርጫ ቦርድ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ
Show all...
የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ድንበር ለቆ እየወጣ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ! የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መግለጫ በሰጠው ምላሽ፣ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ግዛት በመውጣት ላይ መሆናቸውን አስታውቋል። የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ከቀናት በፊት በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ከገለፁ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች በፍጥነት እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው። ሚኒስቴሩ በመግለጫው “ባለፈው ሳምንት እንደተገለጸው በሕወሓት ቀስቃሽነት ድንበር አቋርጠው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች አሁን ለቀው መውጣት የጀመሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይልም ድንበሩን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል” ብሏል። (አዲስዘይቤ)
Show all...