ማለፊያ - Malefia
እኛ ከዮቶር፦ ☞ የጥበብ ምሳሌን ☞ የአስተሳሰብ ውጤትን ☞ የፍልስፍና ዳራን ☞የአመራር ብቃትን ☞የአኗኗር ዘይቤን ተምረናል!!! ስለዚህ ሁላችንም የዮቶር ልጆች ነን ማለት ነው። ለአስተያየት ና ሀሳብ via creater @Adwa1888 [አምባዬ ጌታነህ] YouTube https://youtube.com/channel/UCTQKMrpvRybbd9C552bMVQQ
Show more5 753
Subscribers
-2324 hours
-1257 days
-19030 days
- Subscribers
- Post coverage
- ER - engagement ratio
Data loading in progress...
Subscriber growth rate
Data loading in progress...
ስቅለትና ማርያም
∞ [ አምባዬ ጌታነህ ] ∞
የፍቅር መግለጫ ሆኖ ሳለ ስስት
ማስያዝ እንዴት ሆነ የመሳም ምልክት
አልፋና ኦሜጋ
ትሁት ሆኖ ታዛዥ ወደየትም የሚሄድ
በበርባን ተተካ
የዓለም ሁሉ ገዥ የዓለም ሁሉ መንገድ
አርብ የስቃይ እለት
ሌሎቹን ከሚያድን
እስኪ ራሱን ያድን በሚል የሰው ስላቅ
ሲገርፉት ሲመቱት
ሚካኤል ገብርኤል ትዕግስታቸው እስኪያልቅ።
ከዋክብት ሲረግፉ
ጨረቃም ስትጠፋ ተፈትቶ ሰማይ
ብርሃኗን አጥፍታ
በጠራራ ሰአት ቀን ስትጨልም ፀሐይ
ሁሉን ፈጥሮ ሳለ
ለአዳም ድህነት ብሎ
በፈጠረው ፍጡር ሲገረፍ ሲመታ
ሌላው ይቅርና
ድንግልም እናትም ያደረጋት ጌታ
በወላድ አንጀቷ
እንዴት ሆና ዋለች ማርያም አርብ ለታ!
እንደ ልጅሽ ታዞ
እንደ አምላክ አክብረሽ በፍቅር ያሳደግሺው
ልጅሽን አምላክሽን መስቀል ላይ ስታይው
ምን እያልሽ አለቀስሽ
ምን አይነት ቃል ይሆን ከአፍሽ ያወጣሺው
አንቺ መከረኛ
የተሰደድሺለት
ሲመቱት ሲወግሩት
ራሱን በበትር ፊቱንም በጥፊ
ስንት አመት ይፈጃል
መራብ ማዘንሽን በለቅሶሽ ብትፅፊ?