cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጉዳያችን...(የሙስሊም ወጣቶች ሀላፊነት)

ታዳጊ ቻናል ነው። እዚ ድረስ ከመጡ አይቀር ጆይን ይበሉ እንዲሁም ለሚወዱት ያጋሩ ባረከላሁ ፊኩም። በቅርቡ አሪፍ አሪፍ በምንላቸው ጠቃሚ ነገሮች በአዲስ መልክ እንክሰሰታለን ኢንሻአላህ! ረሱል (ﷺ)“ወደ መልካም ያመለከተ የሰራው ሰው አይነት አጅር (ምንዳን) ያገኛል።” 👉ለማንኛውም አስተያየት ➢ t.me/gudayachin_bot@salihul ላይ ያናግሩን

Show more
Advertising posts
214
Subscribers
-124 hours
-27 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የቁርአን ትምህርት ከትምህርቶች መካከል በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ አይደለም። በትርፍ ጊዜ ከዐስር በኋላ፣ በዕረፍት ቀናትና በክረምት ብቻ የሚማሩት መሆን የለበትም። ቁርአን የዕድሜ ልክ ትምህርታችን ነው። በሆነ ነገር ውስጥ አይገባውም ያንን ነገር ያሳደገውነ ያፋፋው ቢሆን እንጂ። ከሆነ ትምህርት ጋር ቢማሩት በረከትን ይጨምርለታል። ቁርአናችን ለኑሮአችን፣ ለቀልባችን፣ ለመንፈሳችን። ከናንተ መካከል ምርጡ ቁርአንን የተማረና ያስተማረው ነው። ምርጥ ሁኑ። ሶባሐል ኸይር !
Show all...
👍 1
لَقَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا مِن قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡ (አል- ኢምራን 164) ይህችን አያ በደንብ አስተንትኑልኝማ 💚💚💚 አላህ ውለታ ውሎልናል የአለማት ሁሉ አይነታን ለእኛ በመስጠት አስውቦናል 💚💚💚 ❣صلُّوا على خير العباد وسلِّـموا     فصلاتنا ذُخـــــرٌ لنا ووسَـــامُ     يا ربُّ صَـلِّ على النَّبيِّ محـمَّدٍ     مَــا لاحَ برقٌ وأسـتهلَّ غَمـــامُ     اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمدﷺ❤ 🩵አላህ ሆይ ሰላም እና እዝነትህን የልባችን   ብርሀን የሆኑት መልክተኛህ ላይ አውርድ🤲 የሀቢባችንን ፍቅር በሰለዋት ምናጎላበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
አስጨናቂው የክረምት ወቅት መጥቷል ‼️ ፖስቱ ቫይራል መሆኑ ለእናቶች ይጠቅማቸዋል። ላይክ አርግ። ኮፒ አርጋችሁም በየፔጃችሁ ፖስቱት 🙏 ክረምቱ በዝናብ ታጅቦ መጥቷል ይህም ደግሞ ያለ መከለያ ጎዳና ላይ ጉሊት ለሚሸጡ እናቶች መከራ ሆኗል። የሚሸጧቸውን አትክልትና ፍራፍሬ ከማከፋፈያ ቦታ ከማምጣት ጀምሮ ቸርችሮ እስከመሸጥ ድረስ ያለውን ሂደት ክረምቱ ይበጠብጠዋል። አብዛኞቹ እናቶች በጋ ላይ ያገኙት የነበረውን ገቢ ግማሹንም አሁን ላይ አያገኙትም። በእንቅርት ላይ ... እንዲሉ ገቢያቸው ሲቀንስ ወጪያቸውን ደግሞ ክረምቱ ያንረዋል። አብዛኞቹ እናቶች ልጆቻቸውን መንግስት ትምህርት ቤት ያስተምራሉ። በጋውን ልጆቻቸውን መንግስት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ይመግብላቸው ነበረ። ክረምቱ ግን የልጆቻቸውን ፊት ከባዶ ሌማታቸው ጋር ያፋጥጠዋል። አስቤዛ ስትገዙ እስቲ ጉሊት ግዙ። ዋጋ አትከራከሩ ። ቲፕም ስጡ 🙏 አቅሙ ያላችሁ ሰዎች ደግሞ ጉሊት ጋ መኪና አቁሙና አንዱን መደብ በሺዎች ግዙ። አስደስቷቸው። ተመረቁ🙏 #ጉሊት #ጉሊት_challenge
Show all...
👍 1
00:44
Video unavailableShow in Telegram
ኃጥያቴ ቢበዛም  ለበይከ ጌታዬ… አንተን የተጠጋ ልብ እድለቢስ ሆኖ አያውቅምና። በቅዱሱ ስፍራ ከሁጃጆች መሀል  ሆኜ ባልጠራህም … ካለሁበት ቦታ አቤቱ እልሃለሁ። ልቤ ደርቆ ስምህን ደጋግሜ ባላነሳም… መመለሻዬ አንተ ብቻ ነህና ለበይከ ረቢ።  ቤትህን ከሚወዱን ከምንወዳቸው ጋር የምንዘይርም አድርገን ያ አላህ። https://t.me/gudayachin_new
Show all...
3.28 MB
ኃጥያቴ ቢበዛም  ለበይከ ጌታዬ… አንተን የተጠጋ ልብ እድለቢስ ሆኖ አያውቅምና። በቅዱሱ ስፍራ ከሁጃጆች መሀል  ሆኜ ባልጠራህም … ካለሁበት ቦታ አቤቱ እልሃለሁ። ልቤ ደርቆ ስምህን ደጋግሜ ባላነሳም… መመለሻዬ አንተ ብቻ ነህና ለበይከ ረቢ።  ቤትህን ከሚወዱን ከምንወዳቸው ጋር የምንዘይርም አድርገን ያ አላህ። https://t.me/gudayachin_new
Show all...
- آخر ساعة من يوم عرفة: جمعكم الله بأمانيكم وحقق مبتغاكم وجبر قلوبكم بإجابة دعواتكم
Show all...
በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው? ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ  የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐ ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- 1️⃣ የዓረፋን ቀን መፆም:- አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል) 2️⃣ መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል:: 3️⃣ የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን  “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።" 4️⃣ አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ  መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል) በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል። 5⃣ በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ  ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል:: አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን! ✍️ ጣሀ አህመድ https://t.me/gudayachin_new
Show all...
🛑ቅዳሜ ቀንን መጾም የተወገዘ ነውን? 🔅የተወሰኑ ሊቃውንት ከግዴታ ጾም ውጪ ቅዳሜ ቀንን በጾም ማሳለፍ አይቻልም የሚል እይታ አላቸው። ነገር ግን ትክክለኛው (ብዙሃኑ የፊቅህ ሊቃውንትም የመረጡት) ምክንያት ያለው ጾም እስከሆነ ድረስ ቅዳሜ ቀንን በጾም ማሳለፍ ይቻላል። በመሆኑም የነገን (የ1445 ዓ.ሂ) የአረፋ ጾም ዕለቱ ቅዳሜ ቢሆንም ያለምንም ማመንታት መጾም ይቻላል። 🔅ቅዳሜ ቀንን መጾም የሚከለክለው ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ነው እንኳ ቢባል ጾሙ ምንም ዓይነት ምክንያት ከሌለው ወይም በልዩ ሁኔታ መጾሙ የተፈቀደና የሚወደድ ጾም ካልሆነ ብቻ ነው። በመሆኑም እንደ ዓአሹራና አረፋ ያሉ ቀናትን በቅዳሜ ቀን መጾም ክልከላው አይመለከተውም። 🔅የነገው ዕለት የሚጾመው ቅዳሜ ቀን እራሱ ታስቦና ተፈልጎ ሳይሆን የዘጠነኛው ቀን (የአረፋ) ጾም ታስቦ ነው የሚጾመው። 🔅የነገውን ቀን መጾም የሁለት ዓመት ወንጀልን እንደሚያስምር ነቢዩ ﷺ ተናግረዋልና የወንጀል ጉዳይ የሚያሳስበው በሙሉ ዕድሉን ሊጠቀም ይገባዋል። 🔅ጉዞ ላይ የሚሆኑ ሰዎችም ቢሆን በጣም እስካልከበዳቸው ድረስ መጾም ይሻላቸዋል! ደጋግ ቀደምቶች ጉዞ ላይ እንኳ ሆነው አረፋን ሲጾም "ግዴታውን የረመዳን ጾም እንኳ በጉዞ ምክንያት ማፍጠር የሚቻል ከመሆኑ ጋር ለምን ትጾማለህ?" ሲባሉ "ረመዳን ቀዳ ይወጣል (አያመልጥም) አረፋ ግን ቀዳ አይወጣም (ያመልጣል) " ብለው ይመልሱ ነበር! 🔅ሐጅ ላይ ያለ ሰው ግን የሐጅ እንቅስቃሴ ሊያደክመው ስለሚችልና ቀኑንም ነቃ ብሎ በዱዓ እንዲያሳልፍ ብዙሃኑ ሊቃውንት ዘንድ አለመጾሙ ይመረጣል፤ ነቢዩም ﷺ ሐጅ ላይ አልጾሙም ነበር። ✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ዛዱል-መዓድ https://telegram.me/ahmedadem
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.