ማቆምን ስትረሳ አሸናፊ ተሆናለህ፤
ተስፋ መቁረጥን ስትዘነጋ ለድል ትበቃለህ፤
ውድቀትን ስትዳፈር ከፍ ትላለህ፤
ፍረሃትን ስትጋፈጥ ለዩነትን ትፈጥራለህ፤
አዎ! ጀግናዬ..! ላለመውደቅህ፣ ላለመጎዳትህ፣ ላለመሰበርህ ዋስትና የለህም። ዋስትና የሚሆንህ ፍራቻ ሳይሆን ድፍረትህ ነው፤
ብርታትህ የዛሬ ድካምህ ሳይሆን የነገ እረፍትህ ነው፤ ተስፋህ ዛሬ የምትከፍለው ሳይሆን ነገ በእጥፍ የሚከፈልህ ነው።
አቁም የሚል ቃል አትሰማም፤ አትችልም የሚል ቃል አታዳምጥም። አዕምሮህ የሚያስገባው ጉልበት የሚሆንህን፣ የሚያበረታህን፣ የሚደግፍህን፣ የሚያነቃቃህን ብቻ ነው። ትርጉም አልባ ቃላት ለህይወቱ ትርጉም ያገኘ ሰው ጋር ምንም አይሰሩም።
መርጠህ የምታነባቸው መፅሃፍት፣ ፈልገህ የምትሰማቸው ንግርቶች፣ ወደህ አድንቀህ የምትከተላቸው ሰዎች፣ ተመችቶህ ለምታጣጥመው የህይወት አላማና ወደህ ለምትኖረው ህልምህ ዋናዎቹ መንገድ ጠቋሚዎችህ ናቸው።
እንቅፉቶችን አስወግድ፤ በምትኩ ብርታቶችህን ተካ። ስብራትን ለጥንካሬ፣ ውድቀትን ለተስፋ፣ ፍራቻን ለድፍረት፣ ብክነትን ለጥንቃቄ ቦታቸውን አስለቅቅ፤ በብርቱዎች መንገድ ተጓዝ፤ በእራስህ መሪነትም የፈለክበት ቦታ ድረስ።
Show more ...