cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ራስን የመሆን ጥበብ

Advertising posts
11 242
Subscribers
-924 hours
-697 days
-28030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_6521426530 ኖት ኮይን (NOTCOIN) Tap ስታደርጉ የነበራችሁ እንዲሁም ሳታደርጉ አልፏችሁ የቆጫችሁ ከኖት ኮይን በላይ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀዉ በ SOLANA የተዘጋጀ Tapswap አሁኑኑ start በማድረግ አሁኑኑ ይጀምሩ ማሳሰቢያ :- 16 ቀን ብቻ ነዉ የቀረዉ ይፍጠኑ
Show all...
ጥያቄዎ:- 1.ስራ የለኝም እና ምን ሠርቼ የተሻለ ገቢ ላግኝ? ከሆነ 2. ስራ አለኝ ግን በማገኘው ደሞዝ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልኩም እና እንዴት ተጨማሪ ገቢ ላግኝ? ከሆነ 3.ተማሪ ነኝ ግን ከትምህርቴ ጎን ለጎን ቢዝነስ በመስራት ለነገዬ የሚሆን ገቢ እንዴት ማግኘት ችላለው? ከሆነ ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ። ቢሮአችን መታቹህ ሙሉ መረጃውን ለመውሰድ  ፍቃደኛ ከሆናቹህ! 👉ሰም 👉ሰልክ 👉አድራሻ( ከተማ) ይላኩልን! ክፍላገር ለሆናቹም በ online ይህን ድንቅ እድል ማግኘት ይችላሉ 👇👇👇 ለበለጠ መረጃ 0906067696 በዚህ ያገኙናል
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እውነተኛ ሕይወት ሲመዘን! አንድ አሜሪካዊ ነጋዴ በአንዲት የሜክሲኮ የወደብ ከተማ ዳር ቆሞ ሳለ አንዲት ትንሽ ጀልባ አንድ አሳ አጥማጅ ይዛ ወደ ወደቡ ተጠጋች፡፡ በጀልባ ውስጥ አንድ የሜክሲኮ ተወላጅ አሳ አጥማጅ ያጠመዳቸው ቁጥራቸው ከመጠን ያለፈ ትናንሽ አሳዎች አሉ፡፡ አሜሪካዊው ሜክሲኮአዊውን ስለአሳ ማጥመድ ችሎታው ካደነቀው በኋላ አንድን ጥያቄ አቀረበለት፣ “እነዚህን አሳዎች ለማጥመድ ስንት ጊዜ ፈጀብህ?” “በጣም አጭር ጊዜ” ብሎ መለሰ፣ ሜክሲኮአዊው፡፡ አሜሪካዊው፣ “ይህንን ያህል አሳ በአጭር ጊዜ ማጥመድ ከቻልክ ለምን ቀኑን ሙሉ ውለህ ብዙ አሳ ለማጥመድ አትሞክርም” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሜክሲኮአዊው፣ “አሁን በምሰራበት ሁኔታ ለቤተሰቤ በቂ አቅርቦትን ይዤ እገባለሁ” ብሎ መለሰ፡፡ አሜሪካዊው ጥያቄውን በመቀጠል፣ “በቀረህ ጊዜ ምን ታደርጋለህ?” አለው፡፡ ሜክሲኮአዊው ገበሬ፣ “ጠዋት በቂ እረፍት እወስዳለሁ፣ በቂ አሳ ካጠመድኩ በኋላ ልጆቼ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከእነሱ ጋር እጫወታለሁ፣ ከዚያም ከባለቤቴ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ እንወስዳለን፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ እልና ከጓደኞቼ ጋር ሻይ እየጠጣን ጊታሬን መታ መታ አደርጋለሁ፤ ቀኔ በእነዚህ ሁኔታዎች ሙሉ ነው”፡፡ አሜሪካዊው በመገረምና በማሾፍ፣ “እኔ የታዋቂው የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ተመራቂ ነኝ፡፡ ልምከርህ! ከጠዋት እስከማታ አሳ ማጥመድ አለብህ፡፡ ከዚያም ተለቅ ያለ ጀልባ መግዛት ትችላለህ፡፡ ከዚያ በአሳ ጠመዳ የምታሳልፈውን ጊዜህን ትንሽ ጨመር በማድረግ በርካታ ጀልባዎችን ትገዛለህ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙ ጀልባዎች ይኖሩሃል፡፡ ከዚያም ዋና አከፋፋይ መሆን ትጀምርና ለአሳ ጠመዳ በምትወስደው ጊዜህ ላይ ጥቂት ጨመር በማድረግ የራስህን ፋብሪካ ትከፍታለህ፡፡ ከዚያም ከዚህች መንደር ትወጣና ወደ ሜክሲኮ ዋና ከተማ ትገባለህ፣ ከዚያ ወደ ሎስ አንጀለስ፣ ቀስ በቀስም የአለም የገበያ ማእከል ወደሆነችው ወደ ኒውዮርክ በመግባት ታላቅ ሰውና ሚሊየነር ትሆናለህ፡፡” ሜክሲኮአዊው በመገረም፣ “ይህ የምትለው ጉዳይ ስንት ጊዜ ይፈጃል?” አለው፡፡ አሜሪካዊውም፣ “ከ20 እስከ 25 ዓመታት ይፈጃል” አለው፡፡ ሜክሲኮአዊውም መልሶ፣ “ከ25 ዓመታት በኋላ እዚያ ደረጃ ከደረስኩ በኋላስ?” አለው በፍጥነት፡፡ አሜሪካዊው በመሳቅ፣ “ያን ጊዜማ የሚያጓጓ ነገር ውስጥ ትገባለህ፡፡ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቀህ ይህንን የገነባኸውን ንግድ ለሕዝብ በማቅረብ አክሲዮን ትሸጥና ብዙ ቢልየን ብር በማግኘት እጅግ ባለጠጋ ትሆናለህ፡፡” አሁንም ሜክሲኮአዊው መልሶ፣ “በቢልየን የሚቆጠር ብር ካገኘሁ በኋላስ” አለው፡፡ “ከዚያማ ጡረታ ትወጣና ወደነበርክበት የባህር ወደብ ከተማ ትመለሳለህ፡፡ አሁን እንደምታደርገው ጠዋት በቂ እረፍት ትወስዳለህ፣ በቂ አሳ ካጠመድ በኋላ ከልጅ ልጆችህ ጋር ትጫወታለህ፣ ከዚያም ከባለቤትህ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ ትወስዳለህ፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ ትልና ከጓደኞች ጋር ሻይ እየጠጣህ ጊታርህን መታ መታ ታደርጋለህ”፡፡ ሜክሲኮአዊው ተገረመ፡፡ በሃሳቡ፣ “አሁን የምኖረውን የተረጋጋ የሕይወት ሁኔታ ከ25 ዓመታት ልፋት በኋላ ለማግኘት ምን አስሮጠኝ” ብሎ በማሰብና በአሜሪካዊው ሃሳብ ስቆ መንገዱን ቀጠለ፡፡ 1. ራሳችንን መመዘን ያለብን በሕይወት ዘመናችን ውስጥ ባሉት ዓመታት ሳይሆን በዓመታቶቻችን ውስጥ ባለው ጣፋጭ ሕይወት ነው፡፡ 2. ስኬታችን መመዘን ያለብን በገነባነው ቤት ግዝፈት ሳይሆን በቤቱ ውስጥ በሚኖረው በፍቅር የተገነባ ቤተሰብ ነው፡፡ 3. አቅጣጫችንን መመዘን ያለብን እኛ በነዳነው መኪና አይነት ሳይሆን እኛን በነዳን ራእይ ምንነት ነው፡፡ ስራ፣ ገንዘብ፣ ታዋቂነት፣ ውበት፣ ስልጣን፣ እውቀትና የመሳሰሉት ቁሳቁስ-ነክ ነገሮች ሰላምና ፍቅር የሞላበትን ቤተሰባዊ ሕይወት እንድንኖር ካላደረጉን ከንቱ ናቸው፡፡

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

#በራስህ_ላይ_አተኩር‼️ ስለሰዎች ጤና-ቢስ ወሬን ማራባት የዝቅተኝነት ስሜት መገለጫ ነው። የዚህ በሽታ መነሻ እኛ የምንከበረው እና የምንተልቀው ሌላውን ስንጥል እና ስናጣጥል ስለሚመስለን ነው። የእኛ ሁኔታ የሚደምቀው የሌላውን ሰው ስም ስናጠፋ ብቻ የሚመስለን ብዙዎች ነን፡፡ ይህ ስህተት የሚመጣው ደግሞ በራሳችን መቆምና ማደግ እንደማንችልና የተበለጥን እንደሆንን ስናስብ ነው፡፡ ስለዚህ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ሌላውን ለማደናቀፍ፣ ለማደግ ከመስራት ይልቅ ሌላውን ለማድቀቅ የሚታትር እጅግ ብዙ ሰው ነው፡፡ በራሱ የሚተማመን ሰው የሰውን ነገር በማውራትና ሰውን በማሳነስ እርሱ የሚተልቅ ስለማይመስለው የራሱ ስራ ላይ የሚያተኩር ሰው ነው፡፡ በራስህ ላይ አተኩር!! 🙏
Show all...
የመጀመር ህግ! 1) ሁሉንም ነገር ሳይሆን በአንድ ነገር መጀመር፦ አንድ ፈገግታ ዘላቂ ጓደኝነት ሊጀምር ይችላል፣ አንድ ሻማ ጨለማን ያጠፋል፣ አንድ ቃል፣ አንድ እድል፣ አንድ መምህር፣ አንድ ብእር ... አንድ መጽሐፍ ዓለምን ሊለውጡ ይችላሉ። ሁሉንም ሳይሆን አንዱን ነገር እንጀምር! 2) ከሌሎቹ የበለጠ ብልህ መሆን አይጠበቅብንም፦ ለመጀመር ከሌሎቹ የበለጠ ዲሲፕሊን እንጂ አውቀት አያስፈልገንም! 3) እራስን ማሸነፍ፦ በቀን ተቀን ሰርክ ህይወታችን ውስጥ ያገኘነው ስኬት ወይም ውድቀት በሌሎች ሰዎች ምክንያት ሳይሆን በራሳችን ተነሳሽነት ወይም ቸልተኝነት ነው። በህይወት ትልቁ ስኬት ደግሞ እራስን ማሸነፍ ነው። አሸናፊዎች በማሸነፍ ላይ ያተኩራሉ፣ ተሸናፊዎች ደግሞ በአሸናፊዎች ላይ ያተኩራሉ። 4) እይታችን አለምን የምንረዳበትን መንገድ ይቀይራል፦ ነገሮችን የምናይበት መንገድ ሲቀየር...ለነገሮች የሚኖረን አረዳድ፣ ተነሳሽነት እና የመፈፀም አቅማችን ይለወጣል። በልባችን ውስጥ የምንሸከመው አለም በነባራዊ ሁኔታችን እሱ እራሱ አለማችን ይሆናል። 5) ሀሉም የሆነው በሂደት ነው፦ እያንዳንዱ አስተማሪ በአንድ ወቅት ተማሪ ነበር። እያንዳንዱ አሸናፊ በአንድ ወቅት ተሸናፊ ነበር። እያንዳንዱ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር። በየቀኑ የምንወስዳቸው ትናንሽ እርምጃዎች ወደ ስኬታማነት በሂደት ይመሩናል። 6) ፅናት፦ ስኬታማነታችን የሚረጋገጠው በተሻለ ተሰጥኦ ብቻ ሳይሆን በፅናት በመበርታታችንም ጭምር ነው። ወንዝ አለቱን የሚሰነጥቀው በኃይሉ ሳይሆን በፅናት ነው። ያሰብናቸውን ደግሞ በውጤት የምናዬው.. ፍርሃቶቻችንን በመቋቋም እርምጃውን በመውሰድ፣ በመቀጠል እና በመጽናት ነው። 7) ትኩረት፦ ጭንቀት የሚመጣው ችላ ልንላቸው የማይገቡ ነገሮችን ችላ በማለታችን ነው። በትንሹ የጀመርነው በትኩረታችን ትልቅ ይሆናል...'የአንድ ሺህ ማይል ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀምራል!' ተነሳሽነት ማሰብ ብቻ ሳይሆን ድርጊትን ይከተላል። 8) መሻሻል፦ ጊዜ ከሰጡት እንቁላል በግሩ ይሄዳል። መውጣታችንን ከቀጠልን በሂደት የተራራው ጫፍ ላይ መድረስ እንችላለን። ያ ደግሞ የሚሆነው ከትላንቱ ተሽሎ በመገኘት ነው። በማሻሻል ወደ ስኬት ከፍታ መውጣት እንችላለን። 9) እራስን መለወጥ፦ በጉዞአችን ምንም ያህል ጊዜ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ብንጓዝም ሁሌም መዞር እንችላለን። ሁኔታዎችን መለወጥ ባንችልም እራሳችንን መቀየር ግን ይገባናል። ብልህነት ከለውጥ ጋር መላመድ መቻል ነው። 10) ከመጸጸት ይልቅ ትምህርት መውሰድ፦ በህይወት ውስጥ ትልቁ አደጋ መሳሳት ወይም መውደቅ ሳይሆን፣ ያለንን አቅም እና የገኘነውን እድል አለመጠቀም ነው። ኖረነው የማናውቀውን ህይወት ከፈለግን ፈፅሞ አድርገነው የማናውቀውን ማድረግ አለብን።
Show all...
🙏አሜን በሉ... ህልሞቻችን ከፍርሀቶቻችን በላይ ግዙፍ ይሁኑ፤ ተግባራችን ከቃላቶቻችን በላይ ይናገሩ፤ ሕይወታችን ካተናገርነው በላይ ስለኛ ይስበክ… ስኬታችን ጫጫታችን ይሁን!
Show all...
👉 በህይወትህ ሊጠቅሙህ የሚችሉ ነገሮችን ብቻ አንብብ፡፡ ንባብን በቻልከዉ ቦታና ጊዜ ልማድ በማድረግ አእምሮህን መግበዉ፡፡ 👉 ካንተ ከተሻሉ ሰዎች ጋር አብረህ አሳልፍ፤ አስታዉስ! የአእምሮህ ብስለት የሚለካዉ አብረህ ብዙ ጊዜ ከምታሳልፋቸዉ አምስት ሰዎች የአስተሳሰብ ዉጤት ተደምሮ ነዉ። 👉 የምትወደዉን ስራ ስራ። ሁሌም ለማሻሻል ጣር፤ ጎበዝ በሆንክበት ሙያ ከማንም የተሻልክ ሆነህ እንድትገኝ በየቀኑ አዳብረዉ። 👉 አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር እራስህን አዘጋጅ፤ ዉስጥህን ደስ ሊያሰኝ የሚችል ጊዜ ማሳለፊያ ወይንም ትርፍ ሙያ ለመማር ፍቃደኛ ሁን። 👉 ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት አዳብር፤ አዳዲስ ሰዎችን ለማወቅ ፈቃደኛ ሆነህ የህይወት ልምድ ተለዋወጥ። 👉 ለራስህ ህይወት ሃላፊነት ውሰድ! የምትነሳው በእራስህ ነው ፤ የምትወድቀው በእራስህ ነው ፤ የምታድገው በእራስህ ነው ፤ የኋሊት የምትጓዘው በእራስህ ነው። ለውድቀትህ የሚጠየቅ ሌላ አካል የለም። የትም ብትሆን ፣ ምንም ብትሰራ ያንተ ህይወት ሃላፊነት የእራስህ ብቻ ነው ። ላለማደግህ ፣ ላለመቀየርህ ፣ ላለማወቅህ ...ካንተ ውጪ ሌላ ተጠያቂ አካል የለም። 👉 በእራስህ ታገል ፤ በእራስህ ተጣጣር ፤ ተፋለም ። በእራስህ ተማመን ፤ የሚመጣውን ተቀበል ፤ ያለፈው አልፏልና መጪውን ለማስተካከል ዛሬን በሚገባ ኑር። ቀጣዩን የህይወት ምዕራፍህን አስተካክለህ ፃፈው ፤ እርሱንም እመነው ፤ በነፃነት ፣ በልበሙሉነትም ተግብረው። 👉 በልዩነት አስብ! በተሻለ መንገድ አስብ ፤ የተሻለ ሃሳብ ሲኖርህ ብቻ ተመራጭ ትሆናለህ። በተለየ መንገድ አልም፣ በተለየ ሁኔታ ማለም ስትጀምር ብቻ የተለየ ነገር መፍጠር ትችላለህ ።ያለመከውን በተሻለ መንገድ አድርገው። 👉 በአምላክህ ተማመን! ከፈጣሪህ ጋር የማትችለው ፣ የማታልፈው ፣ የማትቋቋመው ምድራዊ ፈተና ፣ የማታሳካው ፣ የማታገኘው ፣ የማትኖረው ህልም የለም። 👉 ትኩረትህን ሙሉ ለሙሉ መድረስ የምትፈልግበት፣ መገኘት የምትመኘው ቦታ ላይ አድርገው ምንም ሳትሰስት የሚፈለግብህን ሙሉ ለሙሉ አድርግ ወደ ሌላ ቦታ በፍፁም እንዳታይ። የምትፈልገውን እስክታሳካ አትተኛ። 👉 ፉክክርህን ከሌሎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነትህ ጋር አድርግ! 👉 ሂደት በሚጠይቅ የረጅም ጊዜ ለውጥ ማመን አለብህ። እውነተኛ እርካታ እና ደስታ ያለው በመልፋትና በፅናት በሚገኝ ስኬት ውስጥ ነው። አቋራጭና ጥድፊያ የበዛበት ሰላም የሚነሳውን ህይወት ለሰነፎች ተውላቸው፤ የተሻለ ሰው የሚያደርግህ፣ የሚያስከብርህ የማይቆም ጥረትህ ነው! 👉 አስተውል! ዛሬህን ልክ እንደትላንትናህ ካሳለፈከው... የሚለወጡት አንተ ልትለውጣቸው የማትችላቸው ነገሮች ብቻ ናቸው! 👉 አስተውል! ባንተ ቁጥጥር ስር ያሉትን እውቀትህን፣ ልምድህን፣ የማኅበራዊ ህይወት ክህሎትህን፣ የገንዘብ ምንጭህን፣ የቤተሰብህን ሠላምና ደህንነት... የመሳሰሉትን ነገሮች ለመለወጥ አንዲት እንኳን እርምጃ የማትራመድ ከሆነ... መልክህ የዛሬ፣ ማንነትህ ግን የትላንት ሆኖ ነው የምትኖረው! 👉 ክቡርና ድንቅ አድርጎ የፈጠረህ አምላክም የልብህን መሻት አይቶ ከጎንህ እንደሚቆም እመን። የምትፈልገውን ጠይቀው፣ ላደረገልህ ነገር ሁሉ አመስግነው! 👉 ማደግህን አታቁም! አጋጣሚዎችን መፍጠር ፣ የተለያዩ አማራጮችን መሞከር ፣ እራስን ማብቃት ፣ እራስን ማሳደግ ፣ ከፍ ማለት የየለት ተግባሩ የሆነ ሰው ሁሌም እድገቱ ይቀጥላል ፤ ነገዎቹ በሙሉ ከዛሬ የተሻሉ ይሆናሉ። 👉 ተደላድሎ የተቀመጠን ማንም አይረዳውም ፤ ተመቻችቶ የተኛውን ማንም አይቀሰቅሰውም ፤ እንዳልደላህ በመልፋት አሳይ ፤ እንዳልተመቸህም በመንቃት አሳይ የሚያግዝህ የሚረዳህም ፈጣሪ የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ አግዘው!!! ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #share ማድረግን አትርሱ 🙏🙏🙏
Show all...