cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቁምነገር

አሁን ትሞት በሗላ ዛሬ ትሞት ነገ ለማታውቅበት ለዚች አጭር ህይወት በቆምክበት ደቂቃ ቁምነገር ሰርተህ የነብስ ስንቅህን አዘጋጅ ! እነሆ ቁምነገር!!! #እንቆጳውያን_ነን ከጎደለን ይልቅ ያለን እጅግ ይገዝፋል #ለመቀበልም መስጠት ያስፈልጋል @Fekrawi 0948000004

Show more
EthiopiaAmharicThe category is not specified
Advertising posts
885
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከጎንህ ያለችው ሚስትህ የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት ደስተኛ ያልሆንክበት ልጅህ መውለድ ለማይችሉት ሁሉ ምኞት ነው ትንሿ ቤትህ ቤት ላጡ ሁሉ ምኞት ናት አድካሚ ስራህ ስራ ላጡት ሁሉ ምኞት ነው ትንሿ ገንዘብህ ምንም ገንዘብ ለሌላቸው ሁሉ ምኞት ናት በገንዘብ የማይተመነው ጤናህ ጤንነት አጥተው ለሚሰቃዩ ሁሉ ምኞት ነው በነፃነት በእግርህ መጏዝህ እስር ቤት ሆነው ለሚሰቃዩ ሁሉ ምኞት ነው ፈጣሪህ የደበቀልህ ነገር ሁሉ ተዋርደው ላፈሩ ሁሉ ምኞት ነው ፈጣሪን ተመስገንእንበለው ምንጭ Facebook @Fekrawi
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ከድሀ ጋር ከዚህ በላይ መቆየት አልችልም ብላ ፍቅረኛዋን ባለበት ጥላው ሄደች ልቡ ክፉኛ ተሰበረ አበባውን ታቅፎ ብቻውን ፈዞ ቀረ...:: ህይወት ቀጠለ እርሷ ከአመታት በኃላ የአንድ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አግብታ ጥሩ ኑሮን መኖር ጀመረች .... አንድ ቀን የባሏ መስሪያ ቤት በሄድችበት ወቅት የድሮ ፍቅረኛዋን አገኘችው እንዴት ያለ ሀብታም ባል እንዳገባች ልታሳየው አስባ ለማስተዋወቅ ስትዘጋጅ ባሏ ቀድሟት እንዲህ አለ .... ውዴ ተዋወቁ እርሱ ማለት የድርጅታችን ባለቤት የኔም አለቃ ነው ይህን ጨምሮ 4 ድርጅቶች አሉት እንዴት ያለ መልካም ሰው መሰለሽ አላት ... ድይህን ጊዜ ሚስት የመትናገረው ጠፋት አፏ ተሳሰረ ደርቃ ቀረች.... ብሩክ ዚቲ ወዳጆቼ ቂቤ ተገፍቼ ነው አናት ላይ የወጣሁት እንዳለችው ሁሉ እናንተም መገፋታችሁን መጠላታችሁን በሙከራዎቻችሁ የሚመጡባችሁን ዘለፋ እና ንቀት አጋዥ እረዳት ማጣታችሁን እንደ መልካም አጋጣሚ ቁጠሩት መጋፋት መናቅ መተው እና ችላ መባላችን ላለምስራት ሳይሆን እንዲያውም በትኩረት በትጋት ለመስራት ምክንያት ይሁነን:: ሰናይ እለት ቸር ይግጠመን:: @Fekrawi
Show all...
💪💯 #አብርሃም ሊከን በ21 አመቱ ንግድ ለመስራት ሞክሮ ከሰረ ። ተስፋ አልቆረጠም ። በ22 አመቱ ከህግ ትምህርት ቤት ተባረረ ። ተስፋ አልቆረጠም ። በ24 አመቱ በድጋሚ ንግድ ሊሰራ ሞክሮ ከሰረ ። አሁንም ተስፋ አልቆረጠም ።  በ26 አመቱ ጣም የሚያፈቅራት የልጅነት ፍቅረኛውን በሞት አጣ ። ፈጣሪውን አላማረረም ። በ34 አመቱ ለምክር ቤት ተወዳድሮ ሳይሳካለት ቀረ ። ድጋሜ መሞከርን አላቋረጠም ። በ45 አመቱ ለሴናተርነት ተወዳድሮ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ ። 💪💯 #አብርሃም ሊከን አሁንም ተስፋ እንደሰነቀ ነው ። ተስፋ ሳይቆርጥ በ47 አመቱ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳደረ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ ። ነገርግን ከመወዳደር ወደኋላ አላለም ። በ49 አመቱ በድጋሚ ለሴናተርነት ተወዳድሮ በድጋሚ ሳይሳካለት ቀረ ።  በመጨረሻ ግን በ52 አመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆን ቻለ ። የሰው ልጅ ተስፋ ካልቆረጠ መሆን የሚችለውን ይሆናል ። 💪💯 ተስፋ የሰው ልጅ ተረጋግቶና በሠላም ይኖር ዘንዶ ከፈጣሪው የተሰጠ ዋነኛው ስጦታ ነው ። ከ22ቱ ፍጥረታት መካከል በተስፋ የሚኖር የሰው ልጅ ብቻ  ነው ። ሰው በተስፋ የማይኖር ከሆነ ባዶ ፣ ተቅበዝባዥና በጭንቀት የሚኖር ብሎም ራሱን ወደ መጥላትና ማጥፋት የሚጓዝ ግደለሽ ይሆናል ። 💪💯 ተስፋ ማለት በየዕለቱ ሊገጥሙን ለሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች መፍትሔ ፣ ለሃዘናችን መጽናኛ ፣ ለደስታችን ፍሬ በጉጉት የምንጠብቅበት ብቻም ሳይሆን  አስቸጋሪ መስለው ለሚታዩን ነገሮች በጎ ነገርን የምናይበት ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው ። 💪💯 ለዚህም ነው ሰዎች በምክራቸው "ተስፋችሁ ሕያው ፣ ጠንካራ ፣ ጽኑና የማይናወጥ መሆን አለበት" የሚሉት ። ተስፋ ካለን ብዙ ነገሮች አሉን ፤ የምንሄድበት አቅጣጫ ፣ የምንንቀሳቀስበት ኃይል ፣ ብዙ አማራጮች ፣ ሺህ መንገዶችና ሊገመቱ የማይችሉ ህልሞች አሉን ። ተስፋ ካለን መሄድ ወደ ምንፈልግበት ቦታ ግማሽ መንገድ ላይ ደርሰናል ማለት ሲሆን ፣ ተስፋ ከሌለን ወይም ተስፋ ከቆረጥን ግን ለዘለዓለሙ ጠፍተናል ማለት ነው ። መልካም ቀን ይሁንላችሁ 💚💛❤️ @enkopawiyan @enkopawiyan       @betina21 https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
❤️በመንገድህ ሁሉ ለለመነህ የምትሰጠው ነገር አታጣም ፤ 💛ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ ። አንዳንዶች ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው ፤ አንዳንዶች ሰላምታህን ፤ አንዳንዶች ጊዜህን ፤ አንዳንዶች ሃሳብህን ፤ አንዳንዶች ድጋፍህን ፤ አንዳንዶች ጓደኝነትህን ። 💚 ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን (ከምንም በላይ ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች) ፤ ያልተጠቀምንባቸው ሰስተን ሳይሆን አለን ብለን ስላላመንን ይሆናል ። 💙ሌላው ይቅር ፈገግታና ደስታችን ፤ እንኳን የምናውቀውን ሰው ይቅርና የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ሃይል አላቸው ። 💜የሚለኩሳቸው ያጡ ብዙ ሻማዎች አሉ ፤"ለኳሾቹም ሻማዎችም ግን እኛ ነን ፤ ክብሪቱ ደግሞ ፍቅር‼️          መልካም ቀን🙏 💚💛❤️💚💛❤️💚 @enkopawiyan @enkopawiyan     @betina21 https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
የሕይወት ትልቁ ስህተት ማርፈድ ነው። ሁሉም የሚያምረውና የሚበጀው በጊዜው ሲሆን ነው። እናም ማድረግ ያለብህን ነገር ሳታመነታ አድርገው፤ መተው ያለብህም ነገር ሳታቅማማ  በጊዜ ተወው፤ መወሰን ያለብህ ጉዳይ ካለም ዛሬውኑ ወስን። ህይወት ማለት እንደ አልፎ ሄያጅ ወንዝ ናት፤ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አትራመድም። ጊዜና ዕድሜህን በአግባቡ መጠቀም ደግሞ የብስለትህ መለኪያ ይሁን። ፀፀት_መጀመሪያ_መጥቶ_አያውቅም_መጨረሻ_እንጂ ስለዚህ ነገን እንዳይቆጭህ ዛሬን አታርፍድ። ዉብ ቀን ይሁንላችሁ!!! @enkopawiyan @enkopawiyan @enkopawiyan       @betina21
Show all...
💪💯 ሴት ነሽ! 💪💯 አዎ! ሴት ነሽ ፤ በሴትነትሽ ሃሳብ አለሽ ፤ ህልም አለሽ ፤ ራዕይ አለሽ ፤ ውጥን አለሽ፤ ግብ አለሽ ። በቀድሞ ማንነትሽ መቀጠል አትፈልጊምና ለመቀየር ወስነሻል ፤ የሚያስጠቃሽን ባህሪ ለይተሻልና ለማሻሻል ተነስተሻል ። ማንም እንደፈለገው የሚገምትሽ ፣ የሚጎዳሽ ፣ የሚጫወትብሽ አይደለሽም ። ሴትነትሽ የምትጠቂበት ሳይሆን እራስሽን የምታስከብሪበት ፣ ለሌሎች ከለላ ፣ ድጋፍ የምትሆኚበት ፣ ብቻሽን ብቁ እንደሆንሽ የምታረጋግጪበት ፣ ጠንካራ እንደሆንሽ የምታስመሰክሪበት ፣ ማንም ሳይኖር ጎልተሽ የምትወጪበት ፣ ደምቀሽ የምትወጪበት ብርቱ ሃይልሽ ነው ። 💪💯 አዎ! ጀግኒት..! ሴት ነሽ! ብርቱ ሴት ፣ ጠንካራ ሴት ፣ እራሷን የሆነች ፣ እራሷን ያገኘች ፣ ማንነቷን የተቀበለች ፣ በእራሷ ደስተኛ የሆነች ፣ ጥገኝነትን የጠላች ፣ እራሷን ያገኘች ጀግና ሴት ነሽ ። በሰዎች ተገደሽ ፣ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ወድቀሽ ፣ በወዳጅ በዘመድ ጫና ውስጥ ገብተሽ ፣ የእራስ ምክንያት ሳይኖርሽ ፣ ምርጫ አጥተሽ የምትቀየሪ ፣ ሌላ ሰው የምትሆኚ አይደለሽም ። ሰዎችን ከማጣት በላይ እራስን ላለማጣት ቅድሚያ ትሰጪያለሽ ፣ ከውጪው ጫጫታ ይልቅ የልብ መሻትሽ ሚዛን ይደፋብሻል ፤ ፍላጎትሽ ያይላል ፤ መሆን የምትመኛት ሴት ትበልጥብሻለች ። አዎ! ምርጫሽ የሰነፍ አይደለምና በምርጫሽ ልክ ብርቱ ሁኚ ፣ ውሳኔሽ ቀላል አይደለምና በውሳኔሽ ልክ ጠንክሪ ፣ የሚጠብቅሽ የለውጥ መንገድ ፈተኝ ፋታ የማይሰጥ የሚገዳደርሽ ነውና ይበልጥ እራስሽን አዘጋጂ ፣ ፍላጎትሽ ልዩ ነውና ልዩ መሆንን እወቂበት ። የተለወጠችውን መልካም ብርቱ ሴት ትፈልጊያታለሽና ጉዞሽን አታቋርጪ ፤ ያለምሺያትን ሴት ሳትፈጥሪ አታቁሚ ፤ የዘወትር ምኞትሽን ሳትጨብጪ አትመለሺ ። ቸር ዋሉልኝ!!! @enkopawiyan @enkopawiyan      @betina21 https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
💪💯 ሴት ነሽ! 💪💯 አዎ! ሴት ነሽ ፤ በሴትነትሽ ሃሳብ አለሽ ፤ ህልም አለሽ ፤ ራዕይ አለሽ ፤ ውጥን አለሽ፤ ግብ አለሽ ። በቀድሞ ማንነትሽ መቀጠል አትፈልጊምና ለመቀየር ወስነሻል ፤ የሚያስጠቃሽን ባህሪ ለይተሻልና ለማሻሻል ተነስተሻል ። ማንም እንደፈለገው የሚገምትሽ ፣ የሚጎዳሽ ፣ የሚጫወትብሽ አይደለሽም ። ሴትነትሽ የምትጠቂበት ሳይሆን እራስሽን የምታስከብሪበት ፣ ለሌሎች ከለላ ፣ ድጋፍ የምትሆኚበት ፣ ብቻሽን ብቁ እንደሆንሽ የምታረጋግጪበት ፣ ጠንካራ እንደሆንሽ የምታስመሰክሪበት ፣ ማንም ሳይኖር ጎልተሽ የምትወጪበት ፣ ደምቀሽ የምትወጪበት ብርቱ ሃይልሽ ነው ። 💪💯 አዎ! ጀግኒት..! ሴት ነሽ! ብርቱ ሴት ፣ ጠንካራ ሴት ፣ እራሷን የሆነች ፣ እራሷን ያገኘች ፣ ማንነቷን የተቀበለች ፣ በእራሷ ደስተኛ የሆነች ፣ ጥገኝነትን የጠላች ፣ እራሷን ያገኘች ጀግና ሴት ነሽ ። በሰዎች ተገደሽ ፣ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ወድቀሽ ፣ በወዳጅ በዘመድ ጫና ውስጥ ገብተሽ ፣ የእራስ ምክንያት ሳይኖርሽ ፣ ምርጫ አጥተሽ የምትቀየሪ ፣ ሌላ ሰው የምትሆኚ አይደለሽም ። ሰዎችን ከማጣት በላይ እራስን ላለማጣት ቅድሚያ ትሰጪያለሽ ፣ ከውጪው ጫጫታ ይልቅ የልብ መሻትሽ ሚዛን ይደፋብሻል ፤ ፍላጎትሽ ያይላል ፤ መሆን የምትመኛት ሴት ትበልጥብሻለች ። አዎ! ምርጫሽ የሰነፍ አይደለምና በምርጫሽ ልክ ብርቱ ሁኚ ፣ ውሳኔሽ ቀላል አይደለምና በውሳኔሽ ልክ ጠንክሪ ፣ የሚጠብቅሽ የለውጥ መንገድ ፈተኝ ፋታ የማይሰጥ የሚገዳደርሽ ነውና ይበልጥ እራስሽን አዘጋጂ ፣ ፍላጎትሽ ልዩ ነውና ልዩ መሆንን እወቂበት ። የተለወጠችውን መልካም ብርቱ ሴት ትፈልጊያታለሽና ጉዞሽን አታቋርጪ ፤ ያለምሺያትን ሴት ሳትፈጥሪ አታቁሚ ፤ የዘወትር ምኞትሽን ሳትጨብጪ አትመለሺ ። ቸር ዋሉልኝ!!! @enkopawiyan @enkopawiyan      @betina21 https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ለናንተ የሀገሬ ልጆች ... በትናንት እና በዛሬ በዛሬ እና በነገ መካከል ለምንኖር ለእኛ ... ካለንበት ከምንኖርበት ያለመጉደል ቀጠና ወጥተን ከመኖር ወደ አለመኖር ከመብላት ወዳለመብላት ከመልበስ ወደመታረዝ የምንመጣበት ቀን አይታወቅምና እንደ ሰው ነግ በኔን በመፍራት አንድም ፈጣሪያችንን ለማስደሰት እንዲያም ሲል ልባችንን በማድረግ ደስታ ለመሙላት በጎ ምግባርን እንከውን ... አሀዱ ቁምነገር የበጎ አድራጎት ድርጅት የፊታችንን የዘመን መለወጫ በዓል የ 2015 ዓ.ም አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ቁጥራቸው 1000 ለሚያህሉ የጎዳና አዳሪ ወንድም እህቶችችን አስታዋሽ ጠያቂ የሌላቸውን ምስኪን አረጋውያንን የመመገብ የማልበስ እና የመዝናኛ ፕሮግራምን በማሰናዳት ላይ እንገኛለን :: በመሆኑም "ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለፈጣሪው ያበድራል" ነውና ነገሩ እርሶም እራሶን እና በዙሪያዎ ያሉትን በማስተባበር #የገንዘብ #የዐይነት #የአልባሳት እና የመሳሰሉትን ድጋፎች በማድረግ ከምስኪኖች ጎን ይቆሙ ዘንድ በፍፁም ትህትና እንጠይቃለን:: ልበለጠ መረጃ 0948000004 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይሂሳብ ቁጥር 1000312029999 @Ahadukumneger https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
💪💯 ፅኑ ፍቅሩ ነው! 💪💯 የመጥፎ ልማድን ክብደት ፣ ለማቆም ወይም ለመቀየር በምንታገልበት ጊዜ እናውቀዋለን ። ምንያህል እንደተቆጣጠረን ፣ ምንያህል እንደተዋሃደን ፣ ምንያህል ነብሳችንን እንደሚያስጨንቃት እንገነዘባለን ። አንወደውም ግን እንደጋግመዋለን ፤ ጠዓሙ መራራ ፣ ስሜቱም ጎምዛዛ ነው ነገር ግን እንደጣፈጠንና እንደተመቸን ለማስመሰል እንሞክራለን ። እየገደለን እንደሆነ እያወቅን እርሱን ተቀብለን በሌላ መንገድ መኖርን እንመርጣለን ። የዚህ ሁሉ ምክንያት መቀየሩን ወይም ማቆሙን ሳንፈልግና ሳንችል ቀርተን ሳይሆን ለማቆም ጠንካራ ምክንያት ስላጣን ነው ። 💪💯 አዎ! እራስን መውደድ ፣ ለእራስ ማዘን ፣ እራስን መቀበል ፣ በእራስ መኩራት ምክንያት ካልሆነን ፣ ብርታት ካልሰጠን ፣ ፍላጎታችንን ካላጠነከረ መጥፎና አስከፊ የተባለውን የለውጥና የእድገት ጠር የሆነን አጉል ልማድ ማቆም እጅግ አስቸጋሪና አዳጋች መሆኑ አይቀርም ። ነገር ግን ከእኛ የሚበልጥ ፣ ሊቆጣጠረን የሚገባ ሌላ ትልቅ ሃይል ፣ ትልቅ ምክንያት አለ ። በእራሳችን እስክንጨክን ያደረገን ክፋት ፣ እራሳችንን እንድንጠላ ያደረገንን መጥፎ ስሜት የምንገታው ፣ እኔ ብቻ ልኑር የምንልበትን የከፋ እራስወዳድነትን የምናስቀርበት ፣ ደግነት የምናደርገው ፣ ሰላምን የምንመርጠው ፣ ለእራሳችን የምናዝነው ፣ ሰዎችን የምንረዳው ፣ የምናስብላቸው ፣ ቅንነት የሚዋሃደን ከፈጣሪ ፍቅር የተነሳ ነው ። 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ፅኑ ፍቅሩ ነው! አምላክህን ትወደዋለህ ፣ ታፈቅረዋለህ ፣ ዘወትር ትለምነዋለህ ፣ ትማፀነዋለህ ። ለአምላክህ ያለህ ፍቅር ገደብ የለውም ፤ በህይወትህ ሙሉ እንደርሱ የምታምነው ማንም የለም ። እምነትህ ፍቅርህን አጠነከረው ፣ ከወትሮው በተለየ ቁርኝትህን አጎለበተው ። እርሱ ቸር አባትህ የሚጠላውን እንድትጠላ ፣ የሚወደውን እንድትወድ ፣ የሚጠየፈውን እንድትጠየፍ ፣ የሚያቀርበውን እንድታቀርብ የሚያደርግህ አምላክህን መውደድህ ነው ። 💪💯 አዎ! በእራስህም ሆነ በሰዎች ላይ የምታደርገውን ክፋት ፣ ጭካኔ ፣ በደል ፣ ስቃይ ለማንም ብለህ ሳይሆን የምትወደው አምላክህ ስለማይወደው ፣ የመረጠህ የመረጥከው አባትህ ስለማይመርጠው ፣ የዘላለም ገዢህ የዘላለም ንጉስህ እጁን ስለማያስገባበት ፣ ስለሚጠየፈው በእርግጥም አንተም ፣ ትጠየፈዋለህ ፣ ትተወዋለህ ። ፍቅሩን ማሰብህ ፣ መውደዱን በልብህ መያዝህ ከክፋት ፣ ከበደል ፣ ከሀጢያት እንድትርቅ ያደርግሃል ። ትወደዋለህና የሚወደውን አድርግ ፤ መርጠሀዋልና የመረጠውን ፈፅም ፤ በእራስህ ተስፋ ብትቆርጥ ፣ ብታዝን እንኳን ተስፋ ባደረከው ፣ በተማመንከው አምላክህ ፍቅር የተነሳ መልካም ፣ አዛኝና ልባም ሰው ሁን ። ቸር ዋሉልኝ!!! @enkopawiyan @enkopawiyan @enkopawiyan             @betina21 https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
💪💯 እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል! 💪💯 ሰው በሁኔታዎች ሲለካ አምላክ ግን ከሁኔታዎች በላይ ነው ፤ ሰው ደስታን ሲመኝ ደስታ በእራሱ ፈጣሪ ነው ፤ ሰው አምላኩን ፍለጋ ሲደክም እርሱ ግን በውስጡ አለ ። የነገሮች መደራረብ ፣ የሃዘን ብዛት ፣ የጭንቀቱ ማየለ የአንድ ሰሞን ሁኔታ ነው ። የችግሮች ክብደት ጊዜያዊ ሁኔታ ነው ። ከነዚህ በላይ የሆነ አምላክ ግን ምንጊዜም አብሮን አለ ፤ ውስጣችን ይገኛል ። "አምላክ የት ይገኛል ቢባል ሁሉም ቦታ ይገኛል ?" በተለይ የእጅ ስራው በሆነውና አምሳሉ በሆነው የሰው ልጅ ውስጥ በሙላት ይገኛል ፤ ዘወትር ይመላለሳል ። ስራውን ለመስራት፣ ተአምራትን ለማድረግ ግን የእኛን ፍቃድ ይፈልጋል ። 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ጫጫታ ውስጥ ሆነህ የአምላክህን ድምፅ አትሰማም ፤ ውስጥህን አታዳምጥም ፤ ከመንፈስህ ጋር አትገኛኝም ፤ ተዓምራዊውን አንተ አታገኘውም ። የእራስህ ጊዜ ያስፈልግሃል ፤ አምላክህን በግልፅ የምታወራበት ፣ መንፈስህን የምታናግርበት ፣ ውስጥህን የምትቃኝበት ፣ ሰላምን የምትሰብክበት የተነጠለ ፣ ከምንም ያልተገናኘ ያንተና የፈጣሪህ ብቻ የሆነ ጥርት ያለ ጊዜ ያስፈልግሃል ። ብቸኝነት አያስፈራም ፤ ከእራስህ ጋር ስታወራ ከአምላክ ጋር እንደምትወያይ አስብ ፤ ቀጣይ እርምጃዎችህን ሲመራህ ትመለከታለህ ፤ ልዩነትህን ያሳይሃል ፤ የሁኔታዎችን አላፊት ያንተን ጥንካሬ ያስገነዝብሃል ። 💪💯 አዎ! እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል ፤ የተሰጠህ አቅም በትናንሽ ክስተቶች የሚደክም አይደለም ፤ ሰውነትህ በጊዜያዊ ክስተቶች የሚከስም አይደለም ። ስራውን የሚሰራው ፣ ያልቻልከውን የሚያስችልህ ፣ የከበደህን የሚያቀልልህ ፣ ዛሬህንም ሆነ ትናንትህን ወደ ታሪክ የሚቀይር ፣ የሰጠህን የሚያስችልህ ፣ የመጣብህን የሚያሳልፍህ የዘወትር ጠባቂህ ፈጣሪህ ነው ። በእርግጥ ከገንዘብህ ፣ ከንብረትህ ፣ ከዝናህ ፣ ከወዳጅህ በላይ በአምላክህ ሃይል የተማመንክበት ጊዜ ካለ አስታውስ ። በቸገረህ ሰዓት መጠለያህ ማነው ? በፈተና ወቅት መደበቂያህ የት ነው ? በጨለብህ ጊዜ ብረሃንህን የት ትፈልጋለህ ? ሁሉን አንድ ላይ የያዘ ፣ የጥያቄዎችህን ምላሽ ከምታገኝበት ከአባትህ እቅፎፍ አትራቅ ፤ በቻልከው ልክ ተጠጋው ፤ ከሁሉም በፊት እርሱን አስቀድም ። @enkopawiyan @enkopawiyan @enkopawiyan          @betina21 https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.