የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Open in Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Show more4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
4 374
🌾✞ #እናት_አለኝ ✞🌾
እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምህረት ኪዳነምህረት
ኪዳነምህረት አንባ መጠጊያ ናት
ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤተን አድምቀሻል
#አዝ---
ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
#አዝ---
ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በህይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
#አዝ---
በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቀወሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዮ በልጅሽ ጣፈጠ
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
✞ #ኪዳነ_ምሕረት_የእረፍቴ_እናት ✞
ኪድነ ምሕረት የእረፍቴ እናት
ሠላም ሆነ በአንቺ አማላጅነት
ንጽሕት ድንኳን በዕምነት የአጌጥሁብሽ
ሠላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ/፪/|//፪//
#አዝ---
የብርሐን ዝናር በአይኖረኝም
በንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በምልጃሽ ነው ሥሜ መቀየሩ
በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አዎ ሥሜ ተጠርቷል በልጅሽ
ከታች በምድር እስከ ሠማያት ድረስ
ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ/፪/
#አዝ---
የከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለክብርሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሠማይ ጸሐይ
ሥለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሠሠ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሠ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ጽናቱ/፪/
#አዝ---
ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለ አንቺ እናቴ
ተዋብሁብሽ ነፍሴ በአንቺ አበራ
አንደበቴ ሥምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫዬ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲኽማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ/፪/
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾✞ #ኪዳነ_ምሕረት_እመቤት ✞🌾
ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት/፪/
ነይልን ነይልን ከአለንበት/፪/
#አዝ---
ከሠማያት በላይ ከአለው ከማደሪያሽ/፪/
ዝማሬ ከሞላው ከዘለዓለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ /፪/
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሠረገላሽ /፪/
#አዝ---
ከጸጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ /፪/
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ
ሰአሊ ለነ ቅድስት ውዳሴ ሲሠማ /፪/
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ /፪/
#አዝ---
ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሠማያት/፪/
ዕንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት
በጽዮን ዝማሬ ተሞላ ነፍሳችን /፪/
ንዒ ንዒ ንዒ እንበል እንደ አባቶቻችን/፪/
#አዝ--
ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ /፪/
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይኽን አምኖ ብጽዕት ይልሻል/፪/
እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል /፪/
#አዝ---
የልብን ሲያዋዩሽ ሠምተሽ ዝም አትይም/፪/
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም
ከዓይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሽለታለሽ /፪/
ከሐዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ /፪/
#አዝ---
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
ሀለዉ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ወተቀበልዋ ኲሎሙ ነፍሳተ አበው እለ አዕረፉ እምአዳም እስከኔሁ ወሰገዱ ላቲ እንዘ ይብሉ ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘፈጠረ ለነ ኪያኪ ሥጋ እምሥጋነ ወዐፅመ እምዐፅምነ” ይላል መላእክት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉበትን የጻድቃን የማረፊያቸውን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ ወደ ገነት አሳረጓት፤ በዚያም ከአዳም ዠምሮ እስከዚያው ያረፉ ያባቶች ነፍሳት ተቀብለዋት “ከዐፅማችን አንቺን ዐጥንት ከሥጋችን አንቺን ሥጋ ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባው” እያሉ የአክብሮት ስግደት ሰግደውለታል፡፡
❖ ከዚያም መላእክት የጻድቅ ሰው ነፍስ ከሥጋው ሲለይ ያለውን ፍጹም ክብርና የሚወርሰውን የገነት ርስቱን መላእክት ካሳዩዋት በኋላ፤ ኃጥኣን ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሲለይ ያላቸውን ጭንቅ ነፍሳቸው በሲኦል የምትቀበለውን ከፍተኛ መከራ አሳዩዋት፤ “ወሶበ ተስእኖሙ አምስጦ ይቤሉ እንዘ ይኬልሑ ኦ እግዝእትነ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን ንዒ ኀቤነ ከመ ትፍትሕነ እማእሰሪሁ ለሰይጣን ወኢትኅድግነ” ይላል ለማምለጥ ባልተቻላቸውም ጊዜ “የመድኅን እናቱ የብርሃን መገኛ እመቤታችን ሆይ ከዚኽ ከዲያብሎስ ቊራኝነት ታላቅቂን ዘንድ ድረሺልን ቸል አትበዪ” እያሉ ምልጃዋን ሽተው በታላቅ ጩኸት ያለቅሱ ዠመር፡፡
❖ ያን ጊዜ ርኅርኅት የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ወይ ሎሙ ወአሌ ሎሙ መኑ እምዜነዎሙ ለውሉደ ሰብእ ኢይምጽኡ ዝየ” (ወዮላቸው ወዮታ አለባቸው ወደዚኽ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ኹሉ ማን በነገራቸው) እያለች ስታለቅስ፤ መላእክትም ለርሷ “ኢትፍርሂ ኦ ማርያም እስመ እግዚአብሔር ምስሌኪ ወምስለ እለ የአምኑ ብኪ” (እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ስለኾነና ባንቺ አማላጅነት ከአመኑት ኹሉ ጋር ስለ አለ አይዞሽ) በማለት ነገሯት፡፡
❖ ርሷም “እስእለከ እግዚኦ ወአስተበቊዐከ በእንተ ኲሉ ዘየአምን ብየ ረስዮ እግዚኦ ግዑዘ እምሲኦል ተዘኪረከ ረኃበ ወጽምዐ ወኲሎ መከራ ዘረከበኒ ኀቤከ ወምስሌከ” (አቤቱ በኔ ቃል ኪዳን ስላመነ ኹሉ እማልድኻለኊ እለምንኻለኊ፤ መራቤን መጠማቴንም ካንተ ጋር በምድረ ግብጽ ያገኘኝን ረኃብና ጥም ኹሉ አስበኽ አቤቱ ወደ ሲኦል ከመውረድ ነጻ አድርገው) በማለት ወደ ልጇ ፍጹም ልመናን አቀረበች።
❖ ጌታችን ተገልጾላት “ይኩን በከመ ትቤሊ እፌጽም ለኪ ኲሎ መፍቅደኪ አኮኑ ተሰባእኩ በእንተ ዝንቱ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ከመ ኢይሔሱ ኪዳንየ” (የለመሺዉን ኹሉ ይደረግልሽ፤ የምትፈቅጂውን ኹሉ እፈጽምልሻለኊ የለመንሺዉን ኹሉ ላደርግልሽ ሰው ኹኜአለኹና፤ መሐላዬን እንዳላፈርስ አማንየ በርእስየ ብዬ በራሴ ማልኹልሽ) ሲል ለእናቱ የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳንን ገብቶ ገብቶላታልና በዓሉ “ኪዳነ ምሕረት” በመባል ይታሰባል::
❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ ጌታ ለእናቱ ስለገባላት ቃል ኪዳን፡-
✍ “ይቤላ ለእ ማርያም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ዘመሐልኩ አነ ለኖኅ ገብርየ ወለአብርሃም ፍቁርየ፤ ዘመሐልኩ አነ ለዳዊት ኅሩይየ ብእሲ ምእመን ዘከመ ልብየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ በቅዱስ ሥጋየ ወበክቡር ደምየ መሐልኩ ለኪ በርዕስየ ከመ ኢይሔሱ ማእኰትየ”
✍(ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን እንዲኽ አላት በምልጃሽ ያመነብሽን አድን ዘንድ ካንቺ ጋራ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተጋባኊ፤ ለአገልጋዬ ለኖኅና ለወዳጄ ለአብርሃም ቃል የገባኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ እንደ ልቤ ለምለው ለታመነው ለዳዊት የማልኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የማልኊ እኔ ምዬ እንደማልከዳ ማልኹልሽ) በማለት ጽፎታል፡፡
[በቀራንዮ ከፈጣሪያችን የተቀበልንሽ ስጦታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
4 374
ኪዳነ ምሕረት
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ቃል ኪዳን” የሚለው ቃል 257 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፤ ኪዳን ማለት ቃል “ተካየደ” ከሚለው ከግእዝ ቃል የወጣ ሲኾን “ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ” ማለትን ሲያሳይ እግዚአብሔር ሰውን ከማፍቀሩ የተነሣ ለሰው ልጅ እንደ ባልንጀራ አድርጎ መሐላን ይምላል፣ ቃል ኪዳንም ይገባል፡፡
❖ ክቡር ዳዊት በመዝ 88፡2-3 ላይ “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” እንዳለ ከኹሉም ቅዱሳን በላይ ኾና ሰማይ ምድር የማይወስኑትን አምላክ በማሕፀኗ ለመሸከም፣ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚሸከሙትን ሰማያዊ መለኮትን በዠርባዋ ለማዘል፣ በክንዷ ለመታቀፍ፣ ሰማይ ምድር ከፊቱ የሚሸሹትን የባሕርይ አምላክን በከናፍሮቿ ለመሳም፣ ፍጥረታትን ኹሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሓይ አብስሎ የሚመግበውን፤ ለቅዱሳን መላእክት ርሱ የገለጸላቸው ምስጋና ምግብ ኹኗቸው እንዲኖሩ ያደረገውን ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለውን እግዚአብሔር ወልድን የድንግልና ጡቶቿን ለማጥባት ከተመረጠች ከእናቱ ጋር የገባው ጽኑዕ የምሕረት ቃል ኪዳን እጅግ ልዩ እና ለኃጥኣን ኹሉ ተስፋ የሚኾን ነው፡፡
❖ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም በአምላክ እናት ፊት ቆሞ “ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻልና አትፍሪ” በማለት ከፍጡራን ወገን ማንም ሊያገኘው የማይችለውን ይኸውም በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ መወደድን በማግኘት ከባለሟልነት ኹሉ የላቀ ባለሟልነት ይኸውም የአምላክ እናት የመኾንን የማማለድ ልዩ ጸጋና ክብር እንደተሰጣት ነግሯታል፡፡
❖ መልአኩ በዚኽ ምስጋናው ላይ “ሞገስን አግኝተሻልና” አለ እንጂ “ወደ ፊት ታገኛለሽ” አለማለቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንቱኑ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተጠበቀችና በልዑል የተመረጠች መኾኗን የሚያረጋግጥም ነበር፡፡ ከዚኽ ከተሰጣት ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ልጇን በማሳሳብ ውሃው ወደ ወይን እንዲለወጥ አስደርጋለች (ዮሐ 2፡1-10)፡፡
❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እንደምናነብበው በአምላካቸው ፊት ባለሟልነትን ያገኙ ብዙዎች ቅዱሳን ቢኖሩም ቅሉ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ግን ለነዚኽ ኹሉ ቅዱሳን ሰማያዊ ክብርን ቃል ኪዳንን የሰጠውን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና በመውለዷ “ወላዲተ አምላክ” የመባል ታላቅና ልዩ ባለሟልነት ተሰጥቷታልና የርሷ ክብር ከማንም ቅዱሳን ክብር ጋር ፈጽሞ የማይነጻጸር ነው፡፡
❖ ከ 432-447 ዓ.ም ሴሌኡሲያ ላይ ጳጳስ የነበረው ሊቁ ባስልዮስም እግዚአብሔር ለእናቱ የሰጣት ልዩ ባለሟልነትን ከቅዱሳን ጋር በማነጻጸር ሲጽፍ “What encomiums can we offer her as she deserves, when everything of this world is beneath her merits?...” (የሚመጥናትን ምን ዐይነት ልዩ ምስጋና እናቅርብላት? የዚኽ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር “ዓለም አልተገባቸውም” (ዕብ ፲፩፥፴፰) ካላቸው፤ ለአምላክ እናትማ ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሓይ ለኾነችው ለርሷ ምን ልንል እንችል ይኾን? (ራእ ፲፪፥፩)... ምን ምስጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናንና አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነ አስተውል፤ ታዲያ የአምላክን እናት ታላቅነት ኹሉም ሰው እንደምን አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ላገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ (የሐዋ ፭፥፲፭)፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ ፲፱፥፲፩)፤ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን?
✔ ለቅዱሳኑ ይኽነን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሰደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይኾን? በምን ዐይነትስ ስጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ” ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቊልፍ ከተሰጠው (ማቴ ፲፮፥፲፮-፲፱)፤ ርሷ ከኹሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትኾን? (ሉቃ ፩፥፵፭)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ “ምርጥ ዕቃ” ከተባለ (የሐዋ ፱፥፲፭)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች ርሷ ምን ዐይነት ልዩ ዕቃው ትኾን?
✔ ነገር ግን ስለርሷ ብዙ እናገራለኊ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኊ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጬአለኊ) በማለት በእግዚአብሔር ፊት የተሰጣት ባለሟልነት ፍጹም እንደኾነና ከቃላት በላይ እንደኾነ አስተምሯል፡፡
❖ ዳግመኛም ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ካገኙት ሞገስ የተነሣ ወደ ፈጣሪያቸው እንዲያማልዱን ስንማጸናቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ግን የአምላክ እናት ናትና ካገኘችው ከዚኽ ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ወደተወደደው ልጇ እንድታማልደን እንማጸናታለን፤ ከዚኽም የተነሣ ነው ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬምም በእሑድ ውዳሴ ማርያም ላይ፦
✍ “ለኪ ይደሉ ዘእምኲሎሙ ቅዱሳን ትሰአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ…” (ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኚልን ዘንድ ላንቺ ይገባል፤ አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጪያለሽ፤ ከነቢያትም ከመምህራንም ትከብሪያለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ፤ በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ) በማለት ያመሰገናት፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ካገኘችው ታላቅ ባለሟልነት የተነሣ ፭ሺሕከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ያለ ዘርዐ ብእሲ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና የፀነሰች፤ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በኅቱም ድንግልና የወለደች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በጀርባዋ ያዘለች ርሷ ብቻ ናትና፤ በርሷ አማላጅነት የምናቀርበው ጸሎት ምን ያኽል ታላቅ እንደኾነ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ፡-
✍“ወፈድፋደሰ በእንተ ማርያም እምከ እንተ ይእቲ ትምክህተ ዘመድነ …” (ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ ስለምትኾን ስለ እናትኽ ስለ ማርያም አንተን በመፅነስና አንተን በመውለድ ዕድፍ ጒድፍ ስላላገኘው ስለ አልተለወጠ ድንግልናዋና ስለ ተሸከመኽ ማሕፀኗ፤ ስለ ታቀፉኽ ስለ ክንዶቿና፣ ስለ ዳሰሱኽ ስለ እጆቿ፤ ስለ ሳሙኽ ስለ ከንፈሮቿ ስለ አሳደጉኽ ስለ ጡቶቿ፤ ከአንተ ጋር ስለ ተመላለሱ ስለ እግሮቿና፤ ስለ ዐዘለኽ ስለ ጀርባዋ፤ ብሩሃት ስለሚኾኑ ስለ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ስላላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች ስለሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ስለ ተበሠሩ (ብሥራትን ስለ ሰሙ) ስለ ጆሮቿ፤ ከርሷ ስለነሣኸው ሥሮችና ጸጒር፣ ደምና፣ ዐፅም ስለ ነፍስና ሥጋ፤ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮትነትኽ ጋራ አንድ ያደረግኸው) በማለት እንዳስተማረ፤ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ባለሟልነት እንዳገኘች በብርሃናዊዉ መልአክ የተመሰከረላት የአምላካችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ታማልደን ዘንድ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያልን እንማጸናታለን፡፡
❖ ይኸውም ታላቁ የነገረ ማርያም መጽሐፍ እንደሚያስረዳን ጌታችን ካረገ በኋላ እመቤታችን ጌታችን ወደ ተቀበረበት ጎልጎታ እየኼደች ትጸልይ ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸው በየካቲት ፲፮ ዕለት ስትጸልይ “አዕረግዋ ውስተ ሰማይ ከመ ያርእይዋ መካነ ዕረፍቶሙ ለጻድቃን ኀበ
4 374
🌿🌾✞ #ንጹም_ጾመ ✞🌾🌿
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ/፪/
ወንትቅፋቀር/፬/ ንትፋቀር በበይናቲነ//፪//
|
|
|...፫
#ትርጉም፦
ጾምን እንጹም ወንድሞቻችንን እንውደድ
እርስ በእርሳችን እንዋደድ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌿🌾✞ #ድንግል_ማርያም_በሉ ✞🌾🌿
ድንግል ማርያም በሉ ምዕመናን ሁላችሁ
በአማላጅነቷ ጥላ ስር ያላችሁ
እንደኔ ከፍቅሯ ፍቅርን ያገኛችሁ/፪/ //፪//
#አዝ
የሐና የኢያቄም የበረከት ፍሬ
ድንግል ስጦታዬ ክብሬ ከለላዬ
ጥላሽን ጣይብኝ ያኔ እጽናናለሁ
አረጋጊኝ ድንግል ባንቺ ታምኛለሁ
#አዝ
ድንግል እመቤቴ ድካሜን እዪና
ፍርኃት ጭኝቀቴን አርቂልኝና
የሕይወትን ፍሬ ሁሌ እንዳፈራ
ነይልኝ እናቴ ከዮሐንስ ጋራ //፪//
#አዝ
4 374
#በእመቤታችን_ስም_የተሠራች_የመጀመሪያዋ_ሕንፃ_ቤተክርስቲያንና_ቅዳሴ_ቤት_የእመቤታችን_ሁለቱ_ክብረ_በዓላት_ታሪክ ⛪️🍇🌾🌿🙏
ሰኔ 20 እና 21
✅በሰኔ 20 ለመጀመሪያ ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በፊልጵስዩስ
የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ትታሰባለች፤ ይኸውም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ገብተው ባስተማሩ ጊዜ ሕዝቡ “መካነ ጸሎት ለዩልን” ብለዋቸዋል፤ ይኽነንም ለጴጥሮስ በነገሩት ጊዜ ጌታችን የሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን አሠራር እንዲገልጽላቸው ሱባዔ ገቡ፤ ሱባዔውም ሲፈጸም ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፨
✅“በናቴ ስም አብያተ ክርስቲያናት ሊታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ላሳያችኊ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናትን ላስተምራችኊ ሰብስቤያችኋለኊ” ብሏቸው፤ ወደ ምሥራቅ አገር ይዟቸው ወጣ፤ በዚያ በምሥራቅ ሀገር ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ ተራርቀው የነበሩትን አቀራረባቸው፤ ጥቃቅን የነበሩትን ታላላቅ
አደረጋቸው፤ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፤ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ ነው፡፡
✅24ቱ የ24ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ 12ቱ የ12ቱ ሐዋርያት ምሳሌ
ነው፤ ከዚኽ በኋላ ሥራ ጀመሩ፤ ሲሠሩትም ሰም እሳት ሲያሳዩት እንዲለመልም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ሠርተው ፈጽመውታል፤ ይኽ የኾነ እመቤታችን ባረገች በአራተኛው ዓመት በሰኔ 20 ቀን ነው፨
✅በሰኔ 21ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ መጣ፤ እመቤታችንን
ታቦት፤ ሐዋያትን ልኡካን አድርጎ፤ ጌታ ዐቢይ ካህን ኾኖ ቀድሶ አቊርቧቸዋል፤
ከዚያም “እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ” (ከእንግዲኽ ወዲኽ እናንተ
እንዲኽ ሥሩ) ብሎ አዝዟቸው ዐርጓል፤ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ በቅድስት
ድንግል ስም ነው፡፡
✅ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው 3 ከላይ
ሕንፃቸው 1 ነው ይኽም የአንድነታቸው የሦስትነተኛው አምሳል ነው፤
✅አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፡-
“በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ”
(ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራት ከፈጸመ በኋላ፤ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ) በማለት ገልጸዋል፡፡
✅ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯ በሰማያት አምሳል እንደኾነ ሊቃውንት
ይተነትናሉ፤ ይኸውም የመጀመሪያዋ ሰማይ “ጽርሐ አርያም” ስትባል ከእሳት
ብርሃኗን ነሥቶ ከብርሃን ብርሃንን ጠምቆ አጥርቶ፤ ኹለንተናዋን በብርሃን ቀለም
ሸልሟታል “አልቦ ሰማይ ዘይጼልል ላዕሌሃ እስመ መልዕልታዊት ወጽንፋዊት
ይእቲ ወኲለንታሃ ብርሃን ፍጹም ዘኢይትነገር በልሳነ ኲሉ ፍጡር ወኲሎሙ ብርሃናት አምሳለ ቀለምጺጸ እሳት በኀቤሃ” ይላል ፤ ብርሃኗን ማንም ከቶ ሊገልጸው አይችልም፤ ከርሷ ብርሃን አንጻር ሲታዩ ሌሎቹ ብርሃናት የእሳት ፍንጣሪ ያኽላሉ፤ ከሰማይ ኹሉ በላይ ስትኾን ከርሷ በላይ ምንም ሰማይ የለም፤ ከዚኽ የተነሣ “ሰማየ ሰማያት” ትባላለች (ዘዳ ፲፥፲፬፤ ፩ነገ ፰፥፳፯)፡፡
✅ምሳሌነቷን ሊቃውንት በመጽሐፈ ቅዳሴ መቅድም ላይ የሰማይ ሥርዓት
በምድር ላይ ስለመሠራቱ ሲተነትኑ በጽርሐ አርያም ውስጥ መንበረ ብርሃን፣
ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን፣ አራቱ ጸወርተ መንበር፣ ኻያ አራቱ ዐጠንተ
መንበር ይኖራሉ፤ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን የመንበር፤ ታቦተ ብርሃን የታቦት፤ መንጦላዕተ ብርሃን የመንጦላዕት፤ አራቱ ጸወርተ መንበር የአራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፤ 24ቱ ዐጠንተ መንበር የጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል ናቸው፡፡
✅ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይም “ወኊልቈሙ
ለእሙንቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት... ወቡርክት ዛቲ ቤተ ክርስቲያን እንተ
አሕዛብ ትመስል ኀይለ ሰማያት” (የእነዚኽ መላእክት የመላእክት አለቆች
ቊጥርም መናብርትና ሥልጣናት፣ አጋዕዝትና ኀይላት፣ ሊቃናት፣ ኪሩቤልና
ሱራፌል ነው፤ እየጮኹም እንዲኽ ይላሉ የእስራኤል አምላክ ይመስገን የሕዝቡ
የአሕዛቡ የምትኾን የተባረከች ቤተ ክርስቲያን የሰማያት ኀይልን ትመስላለች)
ይላል፡፡
✅ሊቁ ሰራዊተ መላእክትን በሚያመሰግንበት በዚኽ ክፍል ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯና እና አከፋፈሏ በመላእክት ከተማ እና በአሰፋፈራቸው ልክ የተመሰለች መኾኗን አስረግጦ አስተምሯል፡- ይኸውም ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች (መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት) የሦስቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ ሲኾን ይኸውም መቅደስ የኢዮር፤ ቅድስት የራማ፤ ቅኔ ማሕሌት የኤረር ምሳሌ ናቸው፡፡
✅ኢዮር በተባለችው ሰማይ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኀይላት ይኖራሉ፡፡ ራማ
በተባለችው ሰማይ አርባብ፣ መናብርት፣ ሥልጣናት ይኖራሉ፡፡ ኤረር በተባለችው
ሰማይ ሊቃናት፣ መኳንንት፣ መላእክት ይኖራሉ፡፡ እነዚኽ 9ኙ ነገድ የ9ኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን አምሳል ናቸው፡፡
✅ይኸውም በኢዮር የሚኖሩት ኪሩቤል የሊቃነ ጳጳሳት፤ ሱራፌል የጳጳሳት፤ ኀይላት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል፡፡
✅በራማ ሰማይ የሚኖሩት አርባብ የቆሞሳት፤ መናብርት የቀሳውስት፤ ሥልጣናት የዲያቆናት አምሳል፡፡
✅በኤረር ሰማይ የሚኖሩት ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፤ መኳንንት
የአናጒንስጢሳውያን፤ መላእክት የመዘምራን አምሳል ናቸው፡፡
✅ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፦ “እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ ወተቀደሰት
በደሙ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር
ላዕሌሃ” (በስሙ ታነጸች፤ በደሙም ከበረች፤ በዕፀ መስቀሉም ተባረከች፤ ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና) ይላል፡፡
✅ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ተአምኆ ቅዱሳን በሚባለው ታላቅ
መጽሐፉ ላይ፡- “ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ”
(የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፡፡
✅ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ መልኩ እናትነቷን በሰባቱ ጊዜያት የሕማማት ሰላምታው ላይ፡-
“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ዘትጼንዊ መጽርየ
ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ
ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ”
(እንደ ቀጋ የምትሸትቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ
ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኊ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል)
“በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ
ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ
እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ
ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ”
(ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሰላም ሰላም እንልሻለን፤
በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ፤ ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ፤ ልመናሽም ከእኛ
ጋራ ይኹን) በማለት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አወድሷል፡፡
🙏የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረከት ይደርብን፡፡🙏
✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌿🌾 #ይቺን_ዓመት_ተወኝ!🌾🌿
✔ከዓመት እስከ ዓመት፦ ፍሬን ሳላፈራ፥ ደረቅ እንደሆንኩኝ፤
✔በራድ ወይም ትኩስ፦ ሁለቱንም ሳልሆን፥ እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ፤
✔አለሁኝ በቤትህ፦ ለሙ መሬትህን፥ እያጎሳቆልኩኝ፤
✔አውቃለሁ አምላኬ፦ ፍሬዬን ለመልቀም፥ እንዳመላለስኩህ፤
✔ዛሬም ሳላፈራ፦ እሾህን አብቅዬ፥ ደርቄ ጠበቅሁህ፤
✔ያልተደረገልኝ፦ ያላፈሰሰክብኝ፥ ያልሰጠኸኝ የለም፤
✔ነገር ግን ይህ ሁሉ፦ አላርምህ አለኝ፥ አልለየኝም ከዓለም፤
✔የማትሰለቸኝ ሆይ፦ ተነሥቼ እስክቆም፥ እባክህ ታገሠኝ፤
✔የእኔን ክፋት ተወው፦ መልአክህን ሰምተህ፥ ይህችን ዓመት ተወኝ፤
✔አውቃለሁ ታውቃለህ፦ ቀጠሮን ሰጥቼ፥ እንደማላከብር፤
✔ብዙ ጊዜ አቅጄ፦ ብዙ ጊዜ ዝቼ፥ በወሬ እንደምቀር፤
✔ዘንድሮስ…! እንዳልኩኝ፦ አምና ይሄን ጊዜ፥ ሰምተኸኝ ነበረ፤
✔ምንም ሳልለወጥ፦ ዘንድሮዬ› አልፎ፥ በአዲስ ተቀየረ፤
✔ፍሬ የማይወጣኝ፦ እኔን በመኮትኮት፥ እጆችህ ደከሙ፤
✔እኔ ግን አለሁኝ፦ ዛሬም አልበቃኝም፥ በኃጢአት መታመሙ፤
✔የቃልህን ውኃ በድንጋይ ልጅህ ላይ፦ ሳታክት ስታፈስ፥ ዘመን ተቆጠረ፤
✔ወደ ልቤ ሳይሰርግ፦ ሕይወቴን ሳይለውጥ፦ እንዲያው ፈስሶ ቀረ፤
✔ቃልህን ጠግቤ፦ እያገሳሁት ነው፥ ሌሎች እስኪሰሙ፤
✔በቃልህ መኖር ግን፦ አልያዝህ አለኝ፥ ከበደኝ ቀለሙ፤
✔ብዙ ጥቅስ አገኘሁ፦ ከቅዱስ መጽሐፍህ፥ ገልጬ አይቼ፤
✔ከራሴ ላይ ብቻ፦ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ፥ በበደል ተኝቼ፤
✔ውጤቴ ደካማ፦ ትምህርት የማይሠርጸኝ፥ ተማሪ ብሆንም፤
✔ይህችን ዓመት ተወኝ፦ ደግሞ ትንሽ ልማር፥ ታገሠኝ አሁንም፤
✔እባክህ አልቆረጥ፦ በቅዱስ መሬትህ፥ ልቆይ ፍቀድልኝ፤
✔ያፈሩት ቅዱሳን፦ የፍሬያቸው ሽታ፥ መዓዛ እንዲደርሰኝ፤
✔የተሸከምከኝ ሆይ፦ ዛሬም ተሸከመኝ፥ አትሰልቸኝ አደራ፤
✔ማን ይታገሠኛል፦ ጠላት እየሆንኩት፥ አይሠሩ ስሠራ፤
✔አታውጣኝ ከቤትህ፦ ብዙ ቦታ አልይዝም፥ ፍሬ ስለሌለኝ፤
✔ስፍራ የማያሻኝ፦ ቤት የማላጣብብ፥ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ፤
✔ቦታስ የሚይዙት፦ ባለ ምግባሮቹ፥ ቅዱሳንህ ናቸው፤
✔ልክ እንደ ዘንባባ፦ የተንዠረገገ፥ ተጋድሎ ጽድቃቸው፤
✔ከሊባኖስ ዝግባ፦ እጅጉን የበዛ፥ ገድል ትሩፋታቸው፤
✔እኔ አይደለሁም፦ ቦታስ የምትይዘው፥ የአንተው እናት ናት፤
✔ሥሮቿ በምድር፦ ጫፎቿ በሰማይ፥ ሲደርሱ ያየናት፤
✔ይቺን ዓመት ተወኝ፦ ከሥርዋ እሆናለሁ፥ ባፈራ ምናልባት፤...
✔ይቺን ዓመት ተወኝ፦ እባክህ አምላኬ፥ አንድ ዓመት ምንህ ናት፤
✔ሺህ ዓመት አንድ ቀን፦ አይደለም ወይ ለአንተ፥ ዓመት ኢምንት ናት!፤
✔ይሄ ዓመት አልፎ፦ ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ›፥ እስከምልህ ድረስ፤
✔እባክህን ጌታ፦ ይቺን ዓመት ተወኝ፥ የወጉን እንዳደርስ!።
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#እንደ_አናንያ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#ገብርኤል_ማን_ነው?
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
#ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን
ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን
አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ
ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ”
እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
#ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው
ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ
👉*ገብርኤል ነው፡፡*
የአሸናፊና የኃይል መልአክ
*ገብርኤል ነው፡፡*
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
*ገብርኤል ነው፡፡
🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
•••
✔ለምሳሌ አንድ አሣ አስጋሪ ሰው መርምህናም ( ማር ምህናም፤ ቅዱስ ምህናም ማለት ነው) እርዳኝ እያለ ሲጠራ ‹‹ወበጊዜሃ መጽአ ኅቡረ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቅዱስ መርምሕናም ተፅኢኖሙ ዲበ አፍራሲሆሙ...›› ተብሎ እንደተገለጸው ቅዱስ ጊዮርጊስም አብሮ ተገልጾ እንደረዱት የሚነግር ተአምር በገድለ ጊዮርጊስ ተአምሩ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ግን በዋናነት ሊገለጽ የሚችለው በገድለ መርምሕናም እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ በቅዱሳን ዘንድ አንዱ ብቻ ነው እንጂ ሌሎቹ የሉም የሚያስብል ታሪክም ድርጊትም የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ ልዩነት ያለ የሚመስለን መገለጦችን የምንረዳበት ሒደት አነስተኛ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
✔ይህ ከሆነ ታዲያ በሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ገብርኤል ጎልቶ ለምን ይወጣል? በዓል ሆኖ የሚከበረው ለቅዱስ ገብርኤል፤ በሥዕልም ላይ አራተኛው ተብሎ በናቡከደነጾር የተገለጸው ሰው የቅዱስ ገብርኤል ሥዕል ሆኖ የሚሣለው ለምንድን ነው?
✔ይህም የሆነበት ምክንያት ዝም ብሎ ወይም በአጋጣሚ አይደለም፡፡
እግዚአብሔር ሥጋዌውን አስቀድሞ የገለጸው መላእክትንም በሰው አምሳል እንዲገለጹ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሙሴ መጀመሪያ የተገለጠለት በዚሁ መንገድ ነበረ፡፡ ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ›› / ዘጸ 3፤2/ ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ይህም ግን ነገረ ተዋሕዶን የሚስረዳ
የምስጢረ ሥጋዌ መገለጥ ነው፡፡
እግዚአብሔር ራሱን በመላእክት አምሳል ሲገልጥ ደግሞ ቅድሚያውን ስፍራ የሚይዘው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ምክንያቱም ገብርኤል ማለት
ቃለ እግዚአብሔር እንዲሁም ሰውና አምላክ ማለት ስለሆነ ነው፡፡ እመቤታችንን ሊያበስር የተላከውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
✔ስለዚህ እግዚአብሔር ለናቡከደነጾር ሥጋዌውን ‹‹ አራተኛ ሰው አያለሁ››
እስኪል ድረስ ሰውነቱን በመገለጥ ያሳየው ከሦስቱ ሊቃነ መላእክት
ይህን ምስጢር በስሙም በተልእኮም ቅዱስ ገብርኤል የተሸከመው በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ሦስቱም ሊቃነ መላእክት በጠባቂ መላእክትነታቸውና ረቂቃን ኃይላት በመሆናቸው ቢኖሩም እግዚአብሔር ሊገልጠው ለፈለገው ታላቅ ምስጢር ተስማሚ የሆነውን (ራሱ ገብርኤል መሆኑ ትርጉምና መልእክት ያለው ነውና) መልአክ በአምሳ ወሬዛ ኀየል ወይም የነገሥታትን ልጅ በሚመስል መንገድ የንጉሠ ሰማይ ወምድር የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ምሳሌ ሆኖ እንዲገለጽለት አደረገ፡፡
በዓሉ ለእርሱ የተሠጠውና ሥዕሉ የእርሱ የሆነበት ምክንያትም ይኸው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ቅድሰት ተዋሕዶ ይህን ሁሉ ምስጢር እንዲህ ባለ ታላቅ ሥርዓተ በዓል እንዲከበር በሥዕልም እንዲታይ በማደረግ ነገረ ሠጋዌውንም የሕጻናቱን ተጋድሎም የመላእክቱንም ጠባቂነት ስትገልጽበትና ስታስረዳበት ትኖራለች፡፡
✔መጽሐፍ ቅዱስን በምልዓት መረዳት ያለው በእውነተኛው የሐዋርያትና የሊቃውንት ትምህርት ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ ጸንታ በምትኖረው ቅድስት ተዋሕዶ ነው፡፡
የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል፡የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ልመና ረድኤትና በረከት አይለየን።
••• ተፈፀመ •••
4 374
••• በእያንዳንዱ ነገራችንና ፈተናችን ላይ ወደ እግዚአብሔር እያመለከቱ የሚጠብቁን የሚያድኑን የሚያስፈርዱልን ወይም የሚያስፈርዱብንም እነርሱ ናቸውና፡፡
✔እንደናቡከደነጾር ያለውን አስፈርደውበት አውሬ አድርገው ሣር
ያስግጡታል፤ እርሱም ራሱ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ብሎ አሁንም አረጋግጧል /ዳን 4 ፤13/፡፡ እንደ ሔሮድስ ያለውን ደግሞ ‹‹ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ›› /ሐዋ 12 ፤23/ ተብሎ እንደተጻፈው አስፈርደው ይቀስፉታል፡፡ እንደ ዳንኤል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ዮሴፍ፣
ሠለስቱ ደቂቅ ያሉትን ደግሞ ያድኗቸዋል፡፡ ‹‹... እርሱ ከአዳኝ
ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥
በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ
ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ
እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። ... ›› /መዝ 90 / ተብሎ ተጽፏልና፡፡
✔ጠባቂ መላእክቶቻቸው የሚያድኗቸው ቢሆንም በራእዩ የታየው አንድ ሆኖ ሳለ ሦስቱ ተደርገው በሦስት ድርሳናት ለምን ተገለጸ የሚል ጥያቄም ልናነሣ እንችላለን፡፡ እንዲህ ያሉትን ምስጢራት መረዳት የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ተመሳሳይ ታሪኮችና ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ስናውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የጌታችንን ትንሣኤ አስመልክቶ አራቱም ወንጌላውያን
መዝግበውልናል፡፡ አራቱም የመዘገቡበት መንገድ ግን ተቃርኖ ባይኖረውም ልዩነት አለው፡፡ አበይት ልዩነቶቹ ሦስት ነገሮች ላይ ናቸው፡፡ የተገለጹት መላእክት ቁጥር ላይ፤ የመጡት ሴቶች ማንነትና ሴቶቹ የመጡበትን ሰዓት በተመለከተ የአዘጋገብ ልዩነት አለ፡፡ ለዛሬው
ለጉዳያችን ቅርበት ያለው የመላእክቱ ብዛት ላይ እናተኩር፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ‹‹እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ
አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ፈጥናችሁም ሂዱና። ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው /ማቴ 28 ፤2-7/ ሲል ይገልጻል፡፡
✔ማርቆስ ደግሞ ‹‹ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ፤ ...›› /ማር 16 ፤5/ ይላል፡፡
✔ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ‹‹እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ ›› /ሉቃ 24 ፤4/ ይለናል፡፡
✔ቅዱስ ዮሐንስም ብዙ ነገር ስለ ትንሣኤው ካተተ በኋላ ‹‹ ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም
በእግርጌ ተቀምጠው አየች /ዮሐ 20 ፤ 11-12/ ሲል መዝግቦልናል፡፡
✔እነዚህን አገላለጾች ስናያቸው የአዘጋገብ ልዩነት ቢታይባቸውም ቅራኔና የእውነታ ልዩነት ግን የላቸውም፡፡ ማቴዎስና ማርቆስ ስለ አንድ መልአክ
ማነጋገር ቢገልጹም ሌላ መልአክ እንዳልነበረ ግን አላመለከቱም፡፡ እንዲያውም ማቴዎስና ማርቆስ የመዘገቡልን ስለ አንድ መልአክ ይሁን
እንጂ ሁለቱም የመዘገቡት ግን ስለተለያዩ መላእክት ነው፡፡ ማቴዎስ ከመቃብሩ ወጭ ድንጋዩን አንከባሎ ስለተቀመጠው ዘግቦ ከመቃብሩ ውስጥ በቀኝ በኩል (በራስጌ ወይም በግርጌ) ስላለው አልመዘገበም፡፡ ማርቆስ ደግሞ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስላለው መዝግቦ በውጭ በኩል ስላለው ወይም የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ስላለው አልመዘገበም፡፡ ሁለቱም ግን ሌላውን መልአክ አልነበረም አላሉም፤ ‹‹የለም›› በሚያሰኝ መንገድም አልገለጹም፡፡ ሉቃስና ዮሐንስ ደግሞ ሁለቱንም መኖራቸውንና በግርጌና በራስጌ መሆናቸውን ገለጹልን፡፡ ስለዚህ
ሁሉም ትክክል ናቸው፡፡ የተለያዩና የማይቃረኑ የተባለው ለዚህ ነው፡፡
ይህም ቢሆን በተዘገበው መንገድ ስለተገለጹት መላእክት ይናገራል
እንጂ በትንሣኤው ዕለት ስለነበሩት መላእክት አጠቃልሎና ዘግቶ
አይናገርም፡፡ የነበሩትን መላእክትም ሁለት ብቻ ነበሩ ማለት ፍጹም
ስሕተት ላይ ይጥላል፡፡
✔ወንጌላውያኑ በዚህ በመላእክቱም ቁጥር ሆነ በሌሎቹ ጉዳዮች
የተለያዩትስ ለምንድን ነው ስንል ደግሞ አንድ መሠረታዊ መልእክት እናገኛለን፡፡ ይኸውም ስለመላእክቱ የተለያየ ዓይነት መገለጥ የገለጹት ለተለያዩ ሰዎች በትንንሽ የጊዜ ልዩነት የታየውን መገለጥና ለአንዳንዶችም በተቀራራቢ ግን በተለያየ ጊዜ የተገለጠውን
ስለመዘገቡ ነው፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ መቅደላዊት ማርያም መመላለሷ ከማሳየቱም በላይ ለእርሷ የተደረገውን የአንድ ጊዜ መገለጥ ብቻ ነው የነገረን፡፡
ሉቃስ ደግሞ ለሌሎች ሴቶች የተደረገውን (ምክንያቱም ተመላልሰው
ያዩም አንድ ጊዜም ያዩ አሉ፤ ብዙ ታሪኮች በውስጡ አሉና) እያሉ ከነጊዜው ስለመዘገቡ እንጂ አንዱን ነጠላ ድርጊት ለያይተውና አሳሰተው መዝግበው አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት ቀስ ብሎና በዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ ክፍል ላይ እንዳየነው ከመንፈስ ቅዱስ መገለጥ
ተሰጥቷቸውና በጊዜው የነበረውን እውነተኛውን ትውፊት ከሐዋርያትና
ከነበሩት ሰምተው ከተረጎሙት ሳይረዳ ልክ እንደዚያ ርኩሳን እንደተባሉት እንስሳት ሳያመሰኳ ወይም እውነታውን ሳይቆነጥጥ ወይም እንደ አሳዎቹ ሐዋርያት የእምነት መከላከያ ጋሸ (ቅርፊት) እና ምስጢራትን የሚረዳበት ክንፈ ጸጋ ሳይኖረው በአመክንዮ (ሎጂክ) ብቻ እረዳለሁም አስረዳለሁም ቢል ይሳሳታል፡፡
✔ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ገብርኤል ላይ
ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ያለ ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡በዚሁ መሠረት ሦስቱን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልንም ያዳኗቸው ጠባቂ
መላአክቶቻቸው ናቸው፡፡ እነዚህም ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ናቸው፡፡ ልክ ሥላሴ ለአብርሃም በተገለጹለት መንገድ ሦስት ሆነው ከሦስቱ ጀርባ ቆመው መታየት ነበረባቸው ካላልን በቀር ከጥንት ጀምሮ በተላለፈው ትውፊት ሦስቱ መላእክት የሦስቱ ሕጻናት ጠባቂ መላእክት ነበሩ፡፡ እንኳን ሰዎቹ ሦስት ሆነው ይቅርና አንድም ሰው ቢሆን ሦስትና ከዚያ በላይ መላእክት ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ዮናታን ወልደ ሳዖል ‹‹በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና›› /1ኛ ሳሙ 14 ፤ 6/ እንዳለው በአንድም በብዙ ማዳንም የእግዚአብሔር ፈቃድና ምስጢር እንጂ የማነስና የመብዛት
ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው ነገር እንኳን በመላእክት ቃል ኪዳን ተቀብለው በሚያማልዱና በሚያድኑ ሰማዕታትና ቅዱሳንም ታሪክ ላይ በተደጋጋሚ የተገለጸ መሆኑን ከተለያዩ ገድላት መረዳት ይቻላል፡፡
••• #ይቀጥላል •••
4 374
#ሠለቱ_ደቂቅን_ያዳናቸው_ማን_ነው?
❖በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ምሥጢሩ ምን ይሆን?
“ታዲያ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣቸው ማን ነው?” ለሚለው የተሐድሶዎች ጥያቄ በመ/ር ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የተሰጠ መልስ፦
✔መጀመሪውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ገብርኤል ነው አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው፤
‹‹የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም፤ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ›› /ዳን 3 ፤ 24 -25/ ፡፡
✔በዚህ ገለጻ መሠረት አራተኛውን ያየው ንጉሡ ናቡከደነጾር ነው፡፡
እርሱም አየሁ ያለው አራተኛ ሰው ነው፡፡ የጨመረበት ቢኖር አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል የሚለውን ነው፡፡ ለመሆኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየ? ሌሎቹ ለምን አላዩም? አንደኛው የጥያቄው ቁልፍ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው።
✔እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሣት
የጣለው ራሱን ምስል አቁሞ ለምስሉ ሕዝቡን በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አምላክ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ የሚያየውን አራተኛውን ሰው ‹‹የእኛን ልጅ ይመስላል ወይም እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹የአማልክትን ልጅ›› ይመስላል ያለበት ምስጢር ምንድን ነው? ይህን ያለበት ምክንያቱ ያየው ነገር አራተኛው አካል ከህልውና ያለው በዘር በሩካቤ የተወለደ ሰው እነርሱ ሳያዩት እሳቱ ውስጥ ገብቶ ሳይሆን ነገሩ መገለጥ ስለሆነ ነው፡፡
✔በብሉይ ኪዳን ከተገለጹት ታላላቅ ሦስት የእግዚአብሔር መገለጦች
ውስጥ አንዱ ይህ የሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ነው፡፡ ➊አንደኛው በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠው መገለጥ ነው / ዘፍ 18/፡፡ ➋ሁለተኛው ደግሞ አሁንም እግዚአብሔር ለአባታችን ለያዕቆብ
በጎልማሳ አምሳል ተገልጾ ሲታገለው ያደረበት ታሪክና ያዕቆብንም መጀመሪያ ‹‹ካልባረከኝ አልለቅህም›› ከተባረከ በኋላም ‹‹እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው›› /ዘፍ 32 ፤ 25 - 32/ ያሰኘው መገለጥ ነው፡፡ ➌ሦስተኛው ይህ ለባቢሎኑ አላዊ ንጉሥ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት በጣለበት ወቅት ያደረገው መገለጥ ነው፡፡
✔ሦስቱም መገለጦች የሚያመሳስሏቸው ሁለት ጠባያት አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው በሦስቱም ጊዜ እግዚአብሔር በሰው መልክና አምሳል መገለጡ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ ቃለ እግዚአብሔር በሥጋዌ (ሰው በመሆን) ተገልጦ ለሰው ፍጹም ድኅነት የሚሰጥ መሆኑን አስቀድሞ በምሳሌ መግለጽ ነው፡፡ መሠረታዊ መልእክቱ ደግሞ አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ የሚያድነው የተስፋውን ዘር እሥራኤልን ብቻ ሳይሆን አሕዛብንም ጭምር መሆኑን ለማሳየትና አሕዛብም የሥጋዌው ነገር ቀድሞ የተገለጸው ለእሥራኤል ብቻ ስለሆነ እኛ ልናምንበት
አይገባም እንዳይሉ ለዚህ ደንዳናና ጫካኝ ናቡከደነጾርም ጭምር ገለጸለት፡፡ የእነ ነነዌ ታሪክም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሆኖ የተቀመጠውና
እግዚአብሔር ለአሕዛብም ድኅነት ይፈጽም እንደነበር የተዘገበው
እግዚአብሔር የእሥራኤል ብቻ ሳይሆን የሁሉም አምላክ የነበረ መሆኑን ራሱ ብሉይ ኪዳንም ምስክር እንዲሆን ነው፡፡ እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ታሪኮችና ምሳሌዎችም በብዛት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፡፡ ስለዚህ የዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጥ ዋናው ምስጢሩና መልእክቱም የአካላዊ ቃልን ሰው ሆኖ መገለጥና አዳኝ
መሆኑንን በሐዲስ ኪዳንም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጎራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉትን ሰማዕታት ሁሉ የሚያድናቸው እርሱ መሆኑን መግለጽ ነው፡፡
✔ታዲያ ዋናው መልእክቱና ምስጢሩ ይህ ከሆነ ገብርኤልም ሆነ ሌሎቹ
መላእክት ለምን አዳኑ ይባላሉ? በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት
መሠረት ለሰዎች ከጊዜያዊና ምድራዊ አደጋና ሰዎች ከሚያመጡባቸው መከራ ድኅነት ሲደረግላቸው ድኅነታቸውን
የሚፈጽሙላቸው ቅዱሳን መላእክት ማለትም ጠባቂ መላእክቶቻቸው
ናቸው፡፡ ምንም አንኳ ይህ መሆኑን አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ
ጊዜ ደግሞ በምስጢር ቢገለጽም የእግዚአብሔር መላእክት
ከሚጠብቋቸው ሰዎች ተለይተው አያውቁም፡፡ ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለው ሔሮድስ ቅዱስ ጴጥሮስንም ለመግደል ባሰረው ጊዜ በዚያ ወቅት ሊሞት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ መልአኩ እንዲያድነው አድርጓል፡፡ ‹‹እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው።
ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።
የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ። ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ /ሐዋ 12፤ 7 -11/ ተብሎ እንደተጻፈ ሙት ላነሣውና ስንት ተአምራት ላደረገው ቅዱስ ጴጥሮስ አሁን ግን ይህን ሁሉ የሚያደርግለት መልአኩ ነው፡፡ ይህ መልአክ የቅዱስ ጴጥሮስ ጠባቂ መልአክ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት በትርጓሜያቸው አስተምረዋል፡፡
✔በዚሁ ታሪክ ላይ ‹‹ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። እነርሱም፦ አብደሻል አሉኣት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ›› / 13-15 / ተብሎ እንደተጻፈው ውስጥ የነበሩት ጴጥሮስ አይሆንም ‹‹መልአኩ›› ነው ያሏት እርሱን ሊመስልሽ የሚችለው ጠባቂ መልአኩ ነው ለማለት ነበር፡፡ ይህም የሆነው በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ የጠባቂ መላእክት ጥበቃና መገለጥ በሰፊው ይታወቅ ስለነበረ ነው፡፡
✔በመጽሐፈ ጦቢትም ላይ ቅዱስ ሩፋኤል ሰው መስሎ ለጦብያና
ለቤተሰበው እንዲሁም ለራጉኤልና ለቤተሰቡ ቀድሞ ጸሎታቸውን
በማሳረግ በኋላም ከፈተናቸው በማዳንና ሕይወታቸውን በመባረክ ተገልጾ አይተነዋል፡፡
✔እነዚህ ሁለት ታሪኮች የሚያሰረዱን ጠባቂ መላእክት በድሕነታችን ውስጥ ትልቅ ስፋራ የሚሰጣቸውና በርግጥም እነርሱ የሌሉበት ድኅነት የሌለ መሆኑን ነው፤ ልዩነቱ በአንዳንዶቹ ታሪኮች ላይ መገለጣቸው በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ተገልጠው ለሰው አለመታየታቸው ብቻ ነው፡፡
✔ጌታችንም በወንጌል ‹‹ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና›› /ማቴ 18 ፤10/ ያለው ስለ ጠባቂ መላዕክቶቻችን ነው፡፡
••• #ይቀጥላል•••
