en
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Show more
4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ማርያም አይደለችምን፤ ስለዚኽ እግዚአብሔር ስለ እመቤታችን ጥንታዊ የልደቷን አመጣጥ በየጊዜው ምልክት እንደሚሰጥ ልብ አድርገን ማስተዋል ይገባናል) በማለት አብራርተው ተርጒመዋል፡፡ 👉 ሊቁ አባ ሕርያስቆስም በቅዳሴው በቊ ፴፪ ላይ "ተናግዶቱ ለአብርሃም" (የአብርሃም እንግድነቱ አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን ጠቅልሎ የገለጠውን ይኽነን ድንቅ ምስጢር፤ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ በስፋትና በጥልቀት፡- "ወዓዲ ኀይመት ዘአብርሃም ዘውስቴታ ተአንገደ እግዚአብሔር አኮ ከማሁ ዘኮነቶ ምጽላለ በእንተ ምዕር አላ ኮነቶ እመ ወተከድነ ሥጋሃ ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ" (ዳግመኛም እግዚአብሔር (በሦስትነት) በዕንግድነት ያረፈባት የአብርሃም ድንኳን አንቺ ነሽ፤ ለጥቂት ጊዜ ብቻ መጠለያን፣ መጠጊያን የኾነቺው አይደለም፤ እናትን ኾናው ሥጋዋን ተዋሕዶ ከመለኮቱ አንድ አደረገው እንጂ) በማለት በአብርሃም ድንኳን ብትመሰልም እንኳ ክብሯ ከፍ ያለ፤ ለዘላለም የአምላክ ማረፊያውና እናቱ መኾኗን አብራርቶ ገልጧል፡፡ 👉 ሊቅነትን ከንግሥና ጋር ያስተባበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በመጽሐፈ ሥላሴ መጽሐፉ ላይ፦ "ኦ ብእሲ ዘትትከሓድ አይኑ ዕለት ለአግዚአብሔር ሰገዱ ሎቱ ምስለ መላእክቲሁ በዕሪና እምነ ኩሉ ፍጡራኒሁ..." (ሥላሴን የምትክድ አንተ ሰው ሆይ ከፍጡሮች ወገን በመላ እግዚአብሔርን ከመላእክቱ ጋር በአንዲት ዕሪና የሰገዱለት በማናቸው ዕለት ነው? በማናቸው ዕለት እግዚአብሔር ከፈጠራቸው መላእክቱ ጋር ተካክሎ እግሩን ታጠበ? በማናቸው ዕለት በሰው መጠለያ በታች ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ ተጠለለ? በማናቸው ዕለት ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ እግዚአብሔር በላ? በማናቸው ዕለት ከአዳም ልጆች ወገን ሰው ወደ ፈጣሪው በለመነ ጊዜ መላእክቱ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር ተካክለው እንዲኽ አድርግ መቼ አሉ? አንተ ሥላሴን የካድኽ ከሓዲ ፍጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር በመተካከል እንዲሰገድላቸው ለምን ታመጣቸዋለኽ? ፈጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር ተካክለው በአብርሃም ቤት እንደተጠለሉ፤ እግራቸውን እንደታጠቡ፤ ዐብረው እንደበሉ አድርገኽ ለምን ታስተካክላለኽ? አንተ ከእኛ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የኾንኽ ክርስቲያን አንዱ እግዚአብሔር ነው፤ ኹለቱ መላእክት ናቸው አትበል) በማለት አስፍቶ ይጽፋል፡፡ 🌿🌿🌿🌾🌼🌻🌼🌾🌿🌿🌿 🙏በቤተ አብርሃም የገቡ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዘወትር በቤተ ልቡናችን ውስጥ ግቡልን አሜን🙏"ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ" ተዋህዶ ሐይማኖቴ: ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በየቀኑ ወደናንተ ያቀርባል፡፡ለጓደኞቻችሁ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ 👇👇👇👇👇👇👇 👉 @EOTC2921 👈 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌿🌿🌾 @EOTC2921 🌾🌿🌿 ✝#የሥላሴ_በዓል_ድንቅ_ሚስጥር✝ 🌿በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ🌿 👉 አብርሃም ከደግነቱ ብዛት እንግዳን ከመውደዱ የተነሣ ድንኳኑን በተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን ሲቀበል የሚኖርበሥራው ኹሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጻድቅ ነበር (ዘፍ 18:1-10)፡፡ጽድቁም ሊታወቅ ስድስት ሰዓት ላይ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ፤በመምሬ ዛፍ ሥር እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ተገለጸለት ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፤ ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው አይቶ፤ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ። 👉 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሰለዚኽ ነገር በድጓው ላይ፦"ዮም አብርሃም ሰገደ ለፈጣሪሁ ሶበ ነጸረ ዋሕደ በሥላሴሁ" (ዋሕደ ባሕርይ የኾነ እግዚአብሔርን በአካላዊ ሦስትነቱ ባየው ጊዜ አብርሃም ዛሬ ለፈጣሪው ሰገደ) ይላል፨ 👉 የተገለጡለት ሰዓቱ ቀትር (ስድስት) ሰዓት በዕንጨት ሥር በሰው አምሳል መኾኑ ቀደምት ሊቃውንት ሲያራቅቁት በአብ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በራሱም ፈቃድ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ዘመኑ ሲፈጸም የአብርሃምን ባሕርይ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ በስድስት ሰዓት በዕንጨት መስቀል ላይ ለቤዛ ዓለም የሚሰቀል መኾኑን ያጠይቃል ይላሉ፨ 👉 ይኽነን ይዞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሕማማት ሰላምታው፦ "ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ ቀትረ ታሕተ ዕፀ ድርስ ተሰቀልከ ከመ እቡስ ስብሐት ለከ" (ምስጋና የተገባኽ ጌታ ድርስ በሚባል የዛፍ ዐይነት ሥር በስድስት ሰዓት ለአባታችን አብርሃም ቀድሞ የተገለጥኽለት ክርስቶስ ሆይ እንደ በደለኛ ተሰቀልኽ) ይላል፨ 👉 ከዚኽ በኋላ "አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…" በማለት ተናግሯል፡፡ "በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ" ብሎ አንድነታቸውን፤ "ውሃ ይምጣላችኍ፣ ዕረፉ፣ ትኼዳላችሁ" ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ 👉 ይኸው ሊቅ ያሬድ ይኽነን ይዞ በድጓ ላይ፦"ይቤሎሙ ዮም አብርሃም ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አመጽእ ማየ ወአሐጽብ እገሪክሙ ወእርከብ ሞገሰ በቅድሜክሙ" (አብርሃም ዛሬ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን ባለሟልነትን በፊታችሁ አገኝ ዘንድ ውሃን አምጥቼ እግራችኹን አጥባለሁ አላቸው) ይላል 👉 ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ "አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ"(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፤ 👉 ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡- "እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣ ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት" (ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡ 👉 ከዚኽም ምስጢር የተነሣ አብርሃምም ሳራን “ሦስት መስፈሪያ የተሠለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ” በማለት የተገለጸለትን የሦስትነት የአንድነት ምስጢርን አጒልቶ ተናግሯል፡፡ 👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይኽነን ይዞ በሕማማት ሰላምታው ላይ፦ "ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ነገሥተ ሰብዐቱ አብያት እለ በላዕክሙ ውሣጤ ኀይመት አሐደ ኅብስተ ትሥልስት" (ከሦስት መስፈሪያ ዶቄት የተጋገረ አንድነት ያለው ኅብስትን በድንኳን ውስጥ የተመገባችሁ የሰባት ቤቶች (ሰማያት) ነገሥት ሆይ ለእናንተ መገዛት (ምስጋና) ይገባል) ይላል፨ 👉 አብርሃምም በደስታ ኾኖ መዐር፣ ወተት፣ ያዘጋጀውን ጥጃ አመጣላቸው፤ እነርሱም ደስ ይበለው ብለው በግብር አምላካዊ ተመግበዋል፤ መላእክት ሎጥ ቤት፤ ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት ቤት ተመገበ የተባለው አንድ ነው፤ እሳት ቅቤ በላ እንደማለት ብቻ ነው፨ 👉 ይኸውም ወተትና መዐር መመገባቸው ኦሪትን ወንጌልን መሥራታቸውን ሲያጠይቁ ነው፤ መዐር የኦሪት፤ ቅቤ የወንጌል ምሳሌ ነው፨ ማር ለጊዜው ሲይዝ የሚለቅ አይመስልም፤ ግን ይለቃል ኦሪትም ስትሠራ የምታልፍ አትመስልም ነበር ግን በኽዋላ ዐልፋለች፨ ወተት የወንጌል ምሳሌ ነው፤ ይኽ ወተት ለጊዜው የሚለቅቅ ይመስላል በኽዋላ ሲያጥቡት አይለቅም ወንጌልም ለጊዜው ስትሠራ የምታልፍ ትመስል ነበር፤ በኽዋላ ግን ጸንታ የምትኖር ኾናለችና በማለት መተርጉማን ያራቅቁታል፡ ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ወልድ አብርሃምን "የዛሬ ዓመት እንደዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለኍ፤ ሚስትኽ ሳራም ልጅን ታገኛለች" በማለት ዘመኑ ሲፈጸም እግዚአብሔር ወልድ ከቤተ አብርሃም ከተገኘች ከእመቤታችን የመወለዱንና፤ በሳራ የተመሰለች ወንጌል ምእመናንን እንደምታስገኝ በምስጢር ገልጾለታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም አካላዊ ቃል በሰጠው ተስፋ መሠረት ከነገደ አብርሃም የመወለዱን ነገር ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ "በሕይወታቸው ኹሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ኹሉ ነጻ እንዲያወጣ፤ በሥጋና በደም እንዲኹም ተካፈለ፣ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" በማለት ገልጾታል (ዕብ ፪፥፲፭-፲፮)፡፡ 👉 ይኽቺ ሥላሴ የገቡባት ኀይመተ አብርሃም (የአብርሃም ድንኳን) የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ይኸውም ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ኹሉ፤ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም፤ አብ ለአጽንኦ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመዋሐድ ዐድረዋል (ሉቃ ፩፥፴፭)፤ በመኾኑም አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ 👉 ሊቁም በነገረ ማርያም ይኽነን ምስጢር ሲገልጽ "ወይእቲ ኀይመት ትትሜሰል በድንግል ወዕደው አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሙንቱ፤ አብ አጽንኣ፣ ወወልድ ተሰብአ እምኔሃ፣ ወመንፈስ ቅዱስ ቀደሳ ከመ ትጹር አምላከ በከርሣ" (ያቺ ድንኳንም በድንግል ትመሰላለች፤ ሰዎቹም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ አብ አጸናት፣ ወልድም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ቃል አምላክን ትሸከም ዘንድ ለያት) በማለት ተርጉሞታል፨ 👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በሰላምታ መጽሐፉ ላይ መጽሐፉ፦ "ኀይመተ አብርሃም አብ ሰላም ለኪ፤ ዘኮንኪ ከመ ተድባብ ሰላም ለኪ" (እንደ ጥላ የኾንሽ የአባት አብርሃም ድንኳን ሰላምታ ይገባሻል) በማለት አመስግኗታል፡፡ ❖ ይኽ አብርሃም የተቀበለውን የተስፋ ቃል ሊቃውንት ሲተረጒሙት "ኦ አኃውየ በይነ መኑ እንከ ዘይቤ እግዚአብሔር ለአብርሃም አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ አኮኑ እግዝእትነ ማርያም ይእቲ ዘወፅአት እምነ ሥርው ለአዳም ..." (ወንድሞቼ ሆይ እግዚአብሔር አብርሃምን እንደዛሬው ኹሉ ወደአንተ ተመልሼ እመጣለኍ ያለው ስለማን ይመስላችኋል? ከአዳም ሥር ወጥታ፤ ከኖኅ አብራክ ተገኝታ፤ ወደ አብርሃም አብራክ ልትከፈል፤ ሥላሴ በአብርሃም ቤት በእንግድነት ተገኝተው፤ ከአብርሃም ዘር ከእመቤታችን የእግዚአብሔርን ልጅ ሰው መኾን ስለርሷ የተናገሩላት እመቤታችን ድንግል

‹‹ሃይማኖት_አንዲት_ናት››@EOTC2921.3gp3.14 MB

ጠራው፣ የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብ ሔር መኾኑን በትክክል ካስረዳ በኋላ በመቀጠልም ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ባባቱ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጡን “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በትክክል አስተማረ፤ ሞትን ድል አድርጎ ስለመነሣቱም ፊተኛው እና ኋለኛው ርሱ ስለመኾኑ ራሱ ጌታ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ” በማለት ይኽነን እውነት እንዲጽፍ ለዮሐንስ እንዳዘዘው ቅዱስ ጳውሎስም እውነቱን መሰከረ፡፡ ወንጌላዊ ማርቆስም ስለዚኽ ነገር “ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” (ማር 16፡19) በማለት ባባቱ ዕሪና መቀመጡን እንደነገረን ቅዱስ ጳውሎስም በድጋሚ ይኽነን አስተማረ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ፡- “እግዚአብሔር ጌታዬን፡- ጠላቶችኽን በእግርኽ መረገጫ እስካደርግልኽ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ብሎ እንደተነበየ /መዝ.፻፱ (፻፲)፡፩/ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይኽ ትንቢት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ አስተምሯል /ዕብ.፲፡፲፪/፡፡ ዓምደ ሃይማኖት የተባለው ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ የሉቃስ ወንጌልን በተረጐመበት ፳፬ኛው ምዕራፍ ላይ ይኽን በተመለከተ ሲናገር እንዲኽ ይላል፡- “ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝ (ዕሪናም) ተቀመጠ፡፡ የተቀመጠውም በባሕርየ መለኮቱ ብቻ አይደለም፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ጭምር እንጂ፡፡ አካላዊ ቃል ባሕርያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና፡፡ … እግዚአብሔር ሲኾን ስለ እኛ ሰው ኾነ፡፡ በፍቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ፡፡ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል” /Commentary on Luke, Chap.24/፡፡ አኹን ለመለኮት የተገደበ የተወሰነ ቀኝ ግራ ፊት ኋላ አለው ማለትም አይደለም ቀኝ ማለት ኀይል ምልአትን በዕሪና መተካከልን የሚያመለክት ብቻ ነው ሊቁ “እስመ ብሂለ የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ ወዕሪናሆሙ በክብር” (ቀኝ ማለት በክብር መተካከላቸውን ተዋሕዶቸውን ያመለክታል) እንዳለ፤ እንግዳን “ንበር” (ተቀመጥ)፤ ይሉታል እንጂ እንደ ባለቤት “ነበረ” (ተቀመጠ) እንዳይሉት ለዐይን ጥቅሻ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብሩ አልተለየምና “ነበረ” ይለዋል፤ ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ 1፡3 ላይ “በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” በማለት የጻፈው፡፡ እስኪ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ቀኝ የሚለውን ኅሊናን በመሰብሰብ እንየው፡፡ “እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ” (መዝ 109፡1) “እኔ ነኝ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ (መዝ 48፡12-13) እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ማቴ 22፡43-44 “አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ” (ዘፀ 15፡6) “አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው” (ዘፀ 15፡11-12) “የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” መዝ 117፡15-16) “ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ” ማር 14፡62 ይላል፡፡ በመኾኑም ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን ሐዋርያቱን የጠራው የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለመኾኑና ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ በአብ ቀኝ (ዕሪና) እንዳለ ከገለጸ በኋላ በዕለተ ዐርብ ባደረገው የድኅነት ምስጢር ዓለምን አድኖ ዋጋችንን የሰጠን ዳግመኛም በታላቅ ጌትነት ለፍርድ ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና “ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” በማለት በትክክል ተናገረ እንጂ፤ ምክንያቱም ከላይ ዠምሮ የጥቅሱን ሐሳብ እንዳየነው ሙሉ ነገሩ የክርስቶስን እግዚአብሔርነት፣ መራጭነት፣ አጽዳቂነት፣ ኰናኝነት፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት፣ በአብ ዕሪና መቀመጥ ብቻ ነው፤ ታዲያ ራሱ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር ከኾነና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ አንሶ ወደ ማን ሊማልድ ነው ይባላል? ወደ አብ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንዳንል በአምላክነት፣ በፈጣሪነት፣ በቅድምና፣ በእግዚአብሔርነት፣ በዕበይ፣ በመንግሥት፣ በሥልጣን፣ በመመለክ፣ በመመስገን፣ በገናንነት፣ በክብር፣ በኀይል፣ በክሂል፣ በፈቃድ፣ በትእዛዝ አንድ ናቸው፡፡ ስለዚኽ ከጊዜ በኋላ እነዚኽ ቀሳጮች ምስጢረ ሥላሴን አፋልሰው የማይለየውን አንድነት ለመበታተን እንዲመቻቸው በማድረግ አስገብተውበታል እንጂ ክብር ይግባውና ጌታስ በዘመነ ሥጋዌዉ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ዓለምን ከራሱ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ ዳግመኛም ታረቀ ከዚያም የማስታረቅን ቃል ለሐዋርያት ሰጥቶ በክብሩ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በጌትነት ይመጣል እንጂ አኹንም እንደገና ያደነውን ዓለም እንደገና እንዳልዳነ አኹንም መልሶ ይማልዳል ማለት ሎቱ ስብሐት ጠላት ዲያብሎስ የዘራው መርዝ ኑፋቄ ክሕደት ነው፡፡ ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ቆሮ 5፡18-20 “ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” በማለት የማስታረቅ አገልግሎት ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን አበው የተሰጠ መኾኑን ትክክለኛውን ትምህርት ያስተማረው፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሌሎችም በተጠራጣሪዎች የሚነሱ ጥቅሶችንም ወደፊት ተንትነን እናያለን፡፡ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ነገረ ክርስቶስ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የቀናውን እውነት የኾነውን የሐዋርያትን ትምህርት ሳትበርዝ ሳትከልስ ሳትቈራርጥ ያስተማረችውን በደምህ የመሠረትካትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቅልን አሜን✞✞✞ 🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻 🌻💐🌹 #Share it...🌹💐🌻 ❀✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞❀ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 @EOTC2921 👈 👉 @EOTC2921 👈 👉 @EOTC2921 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 #አንብበው #share⇩ ያድርጉ 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 【የመናፍቃን የሮሜ 8፡34 የማታለያ ጥቅስ ሲጋለጥ】 ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር) 👉የኢየሱስን የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ መኾኑን ለማመን የተቸገሩና ፈራጅነቱን የካዱ ተጠራጣሪዎች ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አንደኛው በሮሜ 8፡34 ላይ ያለው ኀይለ ቃል ነው፡፡ ይኽ “እስመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ሞተ ወተንሥአ እሙታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀስ በእንቲኣነ” (ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል) የሚለው የጠራው የግእዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ኀይለ ቃል በተለየ መልኩ በዘመናት ኹሉ ለዚኽች ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢኾን መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁኑ ፈራርሳ ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ የክርስቶስን ፈራጅነት በካዱ በባሕር ማዶ ቀሳጮች ብዙ ጊዜ ተሰርዞ (ይማልዳል) በሚል ተቀይሮ እናነብባለን፡፡ ለምስክርነት እስቲ እንይ፡- 👉በ1938 ዓ.ም ታትሞ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፤ ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል 👉በ1975 ዓ.ም ታትሞ ከግእዙ ወደ ዐማርኛው የተመለሰው “ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል፡፡ 👉በ1980 ዓ.ም ግእዙን የሚያውቁ ዐይናማ ሊቃውንት ሳያዩት በጥቂቶች አስተባባሪነት የክርስቶስን ፈራጅነት በማያምኑ በምዕራባውያን የዶላር ድጋፍ የታተመው ደግሞ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል፡፡ ይኽ ዕትም ችግሩ ይኼ ብቻ ሳይኾን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈበትን የግሪክን ቋንቋ እና ቀደምት የተተረጎመትን የግእዝ፣ የሶርያ፣ የአርመን፣ የቅብጥ ቅጅ በተለይ በግሪክ የተጻፈውን የ1900 ዓመት እድሜ ያለውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ከማየት ይልቅ እንግሊዞች እንዲመቻቸው አድርገው ቃላቱን በድፍረት እየጨመሩና እየቀነሱ በ1611 ዓ.ም ያሳተሙትን የ400 ዓመት ዕድሜ ያለውን የኪንግ ጀምስ ቅጂን ወደ ዐማርኛ ተርጒመው ለማቅረብ ሞክረዋል፤ በዚኹ በሮሜ 8፡27 ላይ “ወባሕቱ መንፈስ ለሊሁ ይትዋቀስ ለነ በእንተ ሕማምነ ወምንዳቤነ ወውእቱ የሐትቶ ለልብነ ወየአምር ዘይኄሊ መንፈስ ወይትዋቀስ በኀበ እግዚአብሔር በእንተ ቅዱሳን” (ርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ይመልስልናል፤ ርሱ ልቡናችንን ይመረምረዋል፤ ልብ ያሰበውን ርሱ መንፈስ ቅዱስ ያውቃል፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ለቅዱሳን ጸሎት መልስ ይሰጣል) የሚለውን ገጸ ንባብ ለውጦ በድፍረት “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” በሚል በድፍረት ቃሉን በመለወጥ መንፈስ ቀዱስንም አማላጅ አድርገው መንፈስ ቅዱስን በመናቅ አሳትመውት እናነብባለን፡፡ ይኽ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ የተጻፈውን ቅዱስ ቃል ሰዎች እንደገዛ ፈቃዳቸው አጣምመው ለማቅረብ የሚሞክሩ ቢኾንም እስቲ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8፡33-34 ላይ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ …… ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” የሚለውን ኀይለ ቃል በዝርዝር ዐይተን ሰዎች በተለያየ ጊዜ የጨመሩበት በባዶ ቦታው ላይ ያለው በእውነት ስለምን እንደሚያስገነዝብ መረዳት እንችላለን እስቲ ከዚኽ በታች እንየው፡- “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” ቅዱስ ጳውሎስ በዚኽ ምዕራፉ ላይ በትክክል እንዳስቀመጠው እግዚአብሔር መራጭ እንደኾነ ነው፤ ከላይ በትክክል እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ በእውነት እግዚአብሔር እንደኾነ የታወቀ የታመነ የተረጋገጠ ነውና ስለዚኽ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት አረጋግጦ ጻፈ፤ የመረጣቸውስ ማንን ነው ቢሉ “ንዑ ትልዉኒ” (ኑ ተከተሉኝ) ብሎ የጠራቸው ብሎ ሐዋርያትን፤ ዳግመኛም 72ቱ አርድዕትን፣ 36ቱ ቅዱሳት አንስትን ነው፤ ይኽነንም ወንጌላዊዉ ማቴዎስ “ዐሥራ ኹለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ርሱ ጠርቶ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ኹሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው” በማለት ፲፪ቱ ሐዋያትን እንደጠራና ሥልጣንን እንደሰጣቸው በትክክል አስቀመጠ፡፡ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስም በዚኹ ምዕራፍ ቊ፴ ላይ “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” በማለት ሐዋርያት ሰብአ አርድዕት እያለ የሾማቸው ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስ ልብድዮስ የተባለው ታዴዎስ፤ ዲዲሞስ የተባለውን ቶማስ እየለ የጠራ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን መሰከረ፡፡ “የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው” በማለት የጠራቸውን የሐዋርያት ነገራቸው ወንጌልን በተአምራት እያስረዳ እያጸደቀ እውነት መኾኑን ሰዎች እንዲያውቁት ያደረገው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን አስረዳ፡፡ ከዚያም “ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” የጠራቸው ሐዋርያቱን በዚኽም ዓለም በተአምራት በወዲያኛውም ዓለም “እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ” (ማቴ 19፡28) በማለት ያከበረው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በትክክል እንዳስተማረ በቊ 32 ላይ ላይም “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት ማንም ሊወቅሳቸው የማይችለውን ቅዱሳን ሐዋርያትን የመረጠው ፍጹም እግዚአብሔር የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ገለጸ፡፡ የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ በትክክል በዚኽ ላይም ማጽደቅ እና መኰነን የሚችል ርሱ ልዑል እግዚአብሔር እንደኾነ በትክክል አስቀምጧል፤ እውነት ነው ዓለምን በታላቅ ግርማ አሳልፎ መላእክቱን አስከትሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ለኹሉም እንደ የሥራው የሚከፍለው፤ ጻድቃንን በቀኙ አቁሞ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ብሎ የሚያጸድቅ፤ በግራው የቆሙትን ኃጥኣንን ደግሞ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” በማለት የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር መኾኑን በትክክል ገለጸ፡፡ ራሱ ጌታ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል” በማለት እንዳስተማረን (ማቴ 25፡31-46)፡፡ ታዲያ ማጽደቅና እና መኰነን የፍርድ ሥራ እንጂ የማማለድ ሥራ ነውን በፍጹም አይደለም፡፡ “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያትን የ

ሥርዓተ_ቁርባን@EOTC2921ዲ_ን_ዮርዳኖስ_አበበ.3gp10.50 MB

የሚጠብቀኝ አይተኛም.m4a8.93 KB

አድነኝ አምላኬ.m4a8.84 KB

ክርስቲያን ነኝ @EOTC2921.3gp1.16 MB

ተስፋዬ ድንግል ናት @EOTC2921 ግጥም.3gp4.68 KB

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ✍🏻 @EOTC2921 ውድ የተዋህዶ ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ? አንዴትስ ቆያችሁ? አሜን እግዚአብሔር ይመስገን✞✞✞ አዎ የአባቶቻችን አምላክ የኛ አባት የድንግል ማርያም ልጅ ክብርና ምስጋና አምልኮና ውዳሴ ከአጽናፋ አለም እስከ አጽናፋ አለም በፈጠረው ፍጥረት ሁሉ የተከበረና የተመሰገነ ይሁን አሜን✞✞✞ እነሆ አለም እየታመሰበት ፥ እየተቀዘፈበትና አውቆም ይሁን ሳያውቅ ወደተጠለፈበት የሰይጣን ዲያብሎስ(666)፡ምልክት መፅሐፍ ቅዱሳችን በትንቢቱ እንደሚፈፀም ነግሮን ነበር፡፡ እናም ከመፅሐፍ አንዳችም ነገር ተፅፎ ስለማይቀረው ትንቢት እነሆ አልናችሁ፦፦፦፦ @EOTC2921 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ____የዮሐንስ፡ራእይ፥ምዕራፍ፡13።____ 😭😭😭😰😪🙏😰😪😭😭😭 👉1፤አንድም፡አውሬ፡ከባሕር፡ሲወጣ፡አየኹ፤ዐሥር፡ቀንዶችና፡ሰባት፡ራሶች፡ነበሩት፥በቀንዶቹም፡ላይ፡ ዐሥር፡ዘውዶች፡በራሶቹም፡ላይ፡የስድብ፡ስም፡ነበረ። 👉2፤ያየኹትም፡አውሬ፡ነብር፡ይመስል፡ነበር፥እግሮቹም፡እንደ፡ድብ፡እግሮች፥አፉም፡እንደ፡አንበሳ፡አፍ፡ ነበሩ።ዘንዶውም፡ኀይሉንና፡ዙፋኑን፡ትልቅም፡ሥልጣን፡ሰጠው። 👉3፤ከራሶቹም፡ለሞት፡እንደ፡ታረደ፡ኾኖ፡አንዱን፡አየኹ፥ለሞቱ፡የኾነውም፡ቍስል፡ተፈወሰ።ምድርም፡ ዅሉ፡አውሬውን፡እየተከተለ፡ተደነቀ፥ 👉4፤ለዘንዶውም፡ሰገዱለት፥ለአውሬው፡ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ለአውሬውም፦አውሬውን፡ማን፡ ይመስለዋል፥ርሱንስ፡ሊዋጋ፡ማን፡ይችላል፧እያሉ፡ሰገዱለት። 👉5፤ታላቅንም፡ነገርና፡ስድብን፡የሚናገርበት፡አፍ፡ተሰጠው፥ባርባ፡ኹለት፡ወርም፡እንዲሠራ፡ሥልጣን፡ ተሰጠው። 👉6፤እግዚአብሔርንም፡ለመሳደብ፡ስሙንና፡ማደሪያውንም፡በሰማይም፡የሚያድሩትን፡ሊሳደብ፡አፉን፡ከፈተ። 👉7፤ቅዱሳንንም፡ይዋጋ፡ዘንድ፡ድልም፡ያደርጋቸው፡ዘንድ፡ተሰጠው፥በነገድና፡በወገንም፡በቋንቋም፡ በሕዝብም፡ዅሉ፡ላይ፡ሥልጣን፡ተሰጠው። 👉8፤ከዓለምም፡ፍጥረት፡ዠምሮ፡በታረደው፡በግ፡ሕይወት፡መጽሐፍ፡ስሞቻቸው፡ያልተጻፉ፡በምድር፡የሚኖሩ፡ ዅሉ፡ይሰግዱለታል። 👉9፤ዦሮ፡ያለው፡ቢኖር፡ይስማ። 👉10፤ይማረክ፡ዘንድ፡ያለው፡ማንም፡ቢኖር፡ወደ፡ምርኮነት፡ይኼዳል፤በሰይፍ፡የሚገድል፡ማንም፡ቢኖር፡ራሱ፡ በሰይፍ፡እንዲገደል፡ይገ፟ባ፟ዋል።የቅዱሳን፡ትዕግሥትና፡እምነት፡በዚህ፡ነው። 👉11፤ሌላም፡አውሬ፡ከምድር፡ሲወጣ፡አየኹ፥የበግ፡ቀንዶችን፡የሚመስሉ፡ኹለት፡ቀንዶችም፡ነበሩት፡እንደ፡ ዘንዶም፡ይናገር፡ነበር። 👉12፤በፊተኛውም፡አውሬ፡ሥልጣን፡በርሱ፡ፊት፡ዅሉን፡ያደርጋል።ለሞቱ፡የኾነውም፡ቍስል፡ተፈወሰለት፡ ለፊተኛው፡አውሬ፡ምድርና፡በርሱ፡የሚኖሩት፡እንዲሰግዱለት፡ያደርጋል። 👉13፤እሳትንም፡እንኳ፡ከሰማይ፡ወደ፡ምድር፡በሰው፡ፊት፡እስኪያወርድ፡ድረስ፡ታላላቆችን፡ምልክቶች፡ ያደርጋል። 👉14፤በአውሬውም፡ፊት፡ያደርግ፡ዘንድ፡ከተሰጡት፡ምልክቶች፡የተነሣ፡በምድር፡የሚኖሩትን፡ ያስታል፤የሰይፍም፡ቍስል፡ለነበረውና፡በሕይወት፡ለኖረው፡ለአውሬው፡ምስልን፡እንዲያደርጉ፡በምድር፡ የሚኖሩትን፡ይናገራል። 👉15፤የአውሬው፡ምስል፡ሊናገር፡እንኳ፡ለአውሬውም፡ምስል፡የማይሰግዱለትን፡ዅሉ፡ ሊያስገድላቸው፥ለአውሬው፡ምስል፡ትንፋሽ፡እንዲሰጠው፡ተሰጠው። 👉16፤ታናናሾችና፡ታላላቆችም፡ባለጠጋዎችና፡ድኻዎችም፡ጌታዎችና፡ባሪያዎችም፡ዅሉ፡በቀኝ፡እጃቸው፡ወይም፡ በግንባራቸው፡ምልክትን፡እንዲቀበሉ፥ 👉17፤የአውሬውም፡ስም፡ወይም፡የስሙ፡ቍጥር፡ያለው፡ምልክት፡የሌለበት፡ማንም፡ሊገዛ፡ወይም፡ሊሸጥ፡ እንዳይችል፡ያደርጋል።ጥበብ፡በዚህ፡አለ። 👉18፤አእምሮ፡ያለው፡የአውሬውን፡ቍጥር፡ይቍጠረው፤ቍጥሩ፡የሰው፡ቍጥር፡ነውና፥ቍጥሩም፡ስድስት፡ መቶ፡ስድሳ፡ስድስት፡ነው። ✞አምላክ ሆይ እባክህን የትንቢት መፈፀሚያ አታድርገን✞ 🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻 #Share #Share #Share #Share ❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክEOTC2921: 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 💐🌍ስርዓተ በዓል ወጾም ዘኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን🌍💐 🌹 @EOTC2921 @EOTC2921🌹 ❀☞ ዓመተ ምህረት🌾🌾🌾🌾፪ሺ፲፩ ❀☞ ወንጌላዊ🌾🌾🌾🌾🌾ሉቃስ ❀☞ የዘመን መለወጫ ቀን🌾ማክሰኞ ❀☞ አበቅቴ🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾፳፭ ❀☞ መጥቅዕ🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾፭ ❀☞ ጾመ ነነዌ🌾🌾🌾🌾የካቲት ፲፩ ❀☞ ዐብይ ጾም🌾🌾🌾የካቲት ፳፭ ❀☞ ደብረዘይት🌾🌾🌾መጋቢት ፳፪ ❀☞ ሆሳዕና🌾🌾🌾🌾ሚያዝያ ፲፫ ❀☞ ስቅለት🌾🌾🌾🌾ሚያዝያ ፲፰ ❀☞ ትንሣኤ🌾🌾🌾🌾🌾ሚያዝያ ፳ ❀☞ ርክበ ካህናት🌾🌾🌾ግንቦት ፲፬ ❀☞ ዕርገት🌾🌾🌾🌾🌾ግንቦት ፳፱ ❀☞ ጰራቅሊጦስ🌾🌾🌾🌾ሰኔ ፱ ❀☞ ጾመ ሐዋርያት🌾🌾🌾🌾ሰኔ ፲ ❀☞ ጾመ ድኅነት🌾🌾🌾🌾ሰኔ ፲፪ 👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇#Join #Join #Join👇 👇👇👇👇👇👇👇👇 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌼 @EOTC2921 🌼🌻🌻 🌻🌻🌼 @EOTC2921 🌼🌻🌻 🌻🌻🌼 @EOTC2921 🌼🌻🌻

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻እንቁጣጣሽ🌻🌻🌻 🌻መልካም አዲስ አመት🌻 🌻🌻🌻@EOTC2921🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻