en
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Show more
4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#አምስቱ_አዕማደ_ምስጢራት https://t.me/EOTC2921 አምስቱ አዕማደ ምስጢር፣ እነማናቸው እንማራቸው፣ እነማናቸው እንወቃቸው፡፡ #ምስጢረ_ሥላሴ___እንማራቸው #ምስጢረ_ስጋዌ___እንወቃቸው #ምስጢረ_ጥምቀት___እንማራቸው #ምስጢረ_ቁርባን___እንወቃቸው #ትንሳኤ_ሙታን___እንማራቸው አምስቱ አዕማደ ምስጢር፣ እነማናቸው እንማራቸው፣ እነዚህ ናቸው እንወቃቸው፡፡ #ምስጢረ_ሥላሴ የእግዚአብሔር አንድነትን ደግሞም ሦስትነትን፣ ምስጢረ ሥላሴ ነው የምንማርበት፣ ለአብርሃም አባታችን የተገለፀለት፣ በዘፍጥረት ምዕራፍ አራባ ስምንት። https://t.me/EOTC2921 #አዝ•••✞•••✞•••✞••• #ምስጢረ_ስጋዌ አምላክ ወደ እኛ መጣ ከሰማያት ወርዶ፣ አዳነን ሰው ሆኖ ከማርያም ተወልዶ፣ ይህ ምስጢር አምላክ ሰው የሆነበት፣ ምስጢረ ስጋዌ ነው የምንማርበት፡፡ https://t.me/EOTC2921 #አዝ•••✞•••✞•••✞••• #ምስጢረ_ጥምቀት በኤፌሶን መልዕክት ምዕራፍ አራት፣ እንደተጻፈው ጥምቀት አንዲት ናት፣ የእግዚአብሔር ልጅነት የምናገኝባት፣ ምስጢረ ጥምቀት ሁለተኛ ልደት። https://t.me/EOTC2921 #አዝ•••✞•••✞•••✞••• #ምስጢረ_ቁርባን ደሜን ጠጡ ስጋዬንም ብሉ፣ ብሎ ተናግሯል ጌታ በወንጌሉ፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ሁላችን፣ ምስጢረ ቁርባንን መቀበል አለብን፡፡ https://t.me/EOTC2921 #አዝ•••✞•••✞•••✞••• #ትንሳኤ_ሙታን ጌታችን ሲመጣ በመጨረሻው ቀን፣ ፍጥረታት ሁሉ ይነሳል ከሙታን፣ እንደማንቀር እኛ ፈርሰን በስብሰን፣ በፍጹም እናምናለን ትንሳኤ ሙታንን፡፡ https://t.me/EOTC2921 አምስቱ አዕማደ ምስጢር፣ እነዚህ ናቸው እንማራቸው፣ እነዚህ ናቸው እንወቃቸው፡፡ ☞ለሕፃናት እንዲሁም ማወቅ ለሚሻው ምዕመን ሁሉ እንዲህ እናስተምር፡፡ ☞ከወደዱት #Share

✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

አለ ና ሚካኤል.m4a3.19 MB

ኦ ሚካኤል.m4a1.12 MB

ሚካኤል.m4a1.11 MB

ንዓ ንዓ ሚካኤል.m4a1.05 MB

ሚካኤል ነው የደረሰልኝ.m4a1.03 MB

ሚካኤል ወረደ.m4a10.20 KB

ቅዱስ ሚካኤል አጽናኝ.m4a8.66 KB

ሚካኤል ይላል አንደበቴ.m4a8.04 KB

ት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን✞✞✞ ✍✍ @EOTC2921 ✍✍

✞የቅዱስ ሚካኤል ክብር✞ ❖ መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ ስለኾነ የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡ ❖ ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን (ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ❖ ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤ የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡ ❖ ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የክሕደት ንግግርን በተናገረ ጊዜ አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡- “በሰማይም ሰልፍ ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል” ተብሏል፡፡ ❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡- ስለ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃነቱ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይለዋል፡- ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ” (የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡- የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ፡- ╬ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ” (የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ╬ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት ለሚካኤል ሊቀ መላእክት ዘይስእል በእንተ ምሕረት መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት” (የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡ ❖ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡ ❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ ╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ” (የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ መልአኮሙ ሥዩሞሙ የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ” (ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል ❖ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር። ❖ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ” (መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው) ❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡- ╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ” (የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ ❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡- ╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ” (ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡ ❖ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፣ ዳዊትን ከጎልያድ እጅ በተራዳኢነቱ የጠበቀ ሲኾን፤ ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት ነቢዩ ዳንኤል፡- “ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ…ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርኻለኊ በዚኽም ነገር ከአለቃችኊ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም… በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብኽ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” በማለት አማላጅነቱን መስክሮለታል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡ ❖ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡- ╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ በመንክር ትሕትናከ አስተምህር ለነ ሰአልናከ” (በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ) ╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ” (ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡ ╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል፤ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ዳዊትን ከጎልያድ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፤ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት፣ ሶስናን ከረበናት፤ ቅድስት አፎምያን ከዲያብሎስ እጅ በምልጃው የታደገው፤ አስቀድሞም ዘንዶው ዲያብሎስን ተፋልሞ የጣለው ይኽ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል፤ ራሶቹ ሰባት ቀንዶቹ ዐሥር ከተባለው ዓለምን እየተበተባት ካለው ከዘንዶው ከ666 የሐሳዌ መሲሕ ክፉ አሠራር በቀንም በሌሊትም ተራድቶ ይጠብቀን እላለኊ (ራእ 12፡7፤ ራእ 13፡1-3)፡፡ ❖ ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎ

ሰው ለሰው.mp31.54 MB

አድነኝ አምላኬ.m4a8.84 KB

#የጥበብ_መጀመሪያ_እግዚአብሔርን_መፍራት_ነው መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ፡ 1፥7-23 7፤የጥበብ፡መዠመሪያ፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ነው፤ሰነፎች፡ግን፡ጥበብንና፡ተግሣጽን፡ይንቃሉ። 8፤ልጄ፡ሆይ፥የአባትኽን፡ምክር፡ስማ፥ የእናትኽንም፡ሕግ፡አትተው፤ 9፤ለራስኽ፡የሞገስ፡ዘውድ፡ለዐንገትኽም፡ድሪ፡ይኾንልኻልና። 10፤ልጄ፡ሆይ፥ኀጢአተኛዎች፡ቢያባብሉኽ ፡ዕሺ፡አትበል። 11፤ደምን፡ለማፍሰስ፡ከእኛ፡ጋራ፡ና፡እናድባ ፥ለንጹሕም፡ያለምክንያት፡ወጥመድን፡እንሸምቅበት፡ቢሉ፤ 12፤በሕይወታቸው፡ሳሉ፡እንደ፡ሲኦል፡ኾነን ፡እንዋጣቸው፥በሙሉም፡ወደ፡ጕድጓድ፡እንደሚወድቁ፡ይኹኑ፤ 13፤መልካሙን፡ሀብት፡ዅሉ፡እናገኛለን፥ ከምርኮውም፡ቤታችንን፡እንሞላለን፤ 14፤ዕጣኽን፡ከእኛ፡ጋራ፡ጣል፤ለዅላችንም ፡አንድ፡ከረጢት፡ይኹን፡ቢሉ፤ 15፤ልጄ፡ሆይ፥ከነርሱ፡ጋራ፡በመንገድ፡አትኺድ፥ከጐዳናቸውም፡እግርኽን፡ፈቀቅ፡አድርግ፤ 16፤እግሮቻቸው፡ወደ፡ክፋት፡ይሮጣሉና፥ ደም፡ለማፍሰስም፡ይፈጥናሉና። 17፤መርበብ፡በወፎች፡ዐይን፡ፊት፡በከንቱ፡ትተከላለችና። 18፤እነርሱም፡በደማቸው፡ላይ፡ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም፡ላይ፡ይሸምቃሉ። 19፤እንዲሁ፡ይህ፡መንገድ፡ትርፍን፡ለማግኘት፡የሚሣሣ፡ዅሉ፡ነው። የባለቤቱን፡ነፍስ፡ይነጥቃል። 20፤ጥበብ፡በጐዳና፡ትጮኻለች፤ በአደባባይ፡ድምፇን፡ከፍ፡ታደርጋለች፤ 21፤በአደባባይ፡ትጣራለች፤በከተማዪቱ፡መግቢያ፡በር፡ቃልን፡ትናገራለች። 22፤እናንተ፡አላዋቂዎች፥እስከ፡መቼ፡አላዋቂነት፡ትወዳ፟ላችኹ፧ፌዘኛዎችም፡ፌዝን፡ይፈቅዳሉ፧ሰነፎችም፡ዕውቀትን፡ይጠላሉ፧ 23፤ወደ፡ዘለፋዬ፡ተመለሱ፤እንሆ፥ መንፈሴን፡አፈስ፟ላችዃለኹ፤ቃሌን፡አስተምራችዃለኹ።

✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✞ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ምስጢረ_ስላሴ_በጥቂቱ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የእግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ በሆነው በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡ #አንድ_ሲሆን_ሦስት_ሦስት_ሲሆን_አንድ_በአካል_ሦስት_ሲሆን_በመለኮት_በአንድ_አምላክ_በሆነው_በልዑል_እግዚአብሔር ብቻ ነው የምናምን፡፡ ይህ ምስጢር ስጋን በለበሰ ህሊናችን ተመራምሮ ማወቅ አይቻልም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ካልሆነ በስተቀር፡፡ ለዛም ነው ቤተ ክርስቲያናችን አምስቱ አዕማደ ምስጢራትን ስታስተምር በመጀመሪያ ምስጢረ ስላሴን መማር እንዳለብን ያስቀመጠችልን፡፡ ምስጢር ማለት፦ እጅግ ጥልቅ፣ የተሰወረ፣ የረቀቀ፤ ከመሆኑ የተነሳ #ምስጢር ይባላል፡፡ #ስላሴ ማለት ደግሞ "ሰለሠ" ወይም ሦስት አደረገ ማለት ሲሆን ትርጉሙም፦ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ✞✞✞ #የስላሴ_አንድነትና_ሦስትነት፦ ✞✞✞ ☞✞ #የስላሴ_አንድነት ፦ በአገዛዝ፣ በስልጣን፣ ይህን አለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በልብ፣ በቃል፣ በእስትንፋስ፤ በእነዚህ ሁሉ የመለኮት ባህርይ #አንድ ነው፡፡ #የእግዚአብሔር_ሦስትነት_ስንል፦እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነትም፦ በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው። ☞✞ እግዚአብሔር #በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍ፡1፥2 ፣ ምሳ፡30፥4" ። ☞✞ እግዚአብሔር #በግብር ሦስት ነው ስንል፤ ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦ መውለድና ማስረጽ =የአብ፤ መወለድ=የወልድ፤ መስረጽ =የመንፈስ ቅዱስ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝ፡2፥7" ☞✞ እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ #ለአብ፦ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው። #ለወልድ ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ። #ለመንፈስ_ቅዱስ ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። ☞✞ የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም፦ #አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው። #ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝ፡2፥7" #መንፈስ_ቅዱስ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "እዮ፡26፥13" ✞በመጽሐፍ_ቅዱስም ከበቂ በላይ ሁኖ ተገልፆልናል፡፡ ዘፍ፡1፥26 ፣ ዘፍ፡11፥7 ፣ ኢሳ፡6፥1-3 ፣ ኢሳ፡48፥16 ፣ ማቴ፡3፥16 ፣ ማቴ፡28፥19 ሉቃ፡1፥35 ፣ ዮሐ፡14፥25 ፣ ማቴ፡21፥18 ፣ 1ኛ ቆሮ፡12፥3 ፣ 2ኛ ቆሮ፡13፥14 ፣ ዘፍ፡3፥22 ፣ ማር፡10፥6 ፣ ማር፡10፥18 ፣ ዘፍ፡1፥3 ፣ ዘፅ፡5፥1 ፣ ዘፅ፡7፥17 ፣ ኢያ፡3፥17 ፣ ሐዋ፡1፥23 ወዘተ.... ከዚህም በላይ ስለአንድነትና ሦስትነታቸው እናገኛለን፡፡ የእግዚአብሔር አብ በረከት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞

🌿🌾✞ #ሰማዕቷ_ቅድስት_አርሴማ ታኅሣሥ 6 ✔በዚች ቀን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያኗ የከበረበትና የስጋዋ ፍልሰት የሆነበት እለት ነው። ✔እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ ✔ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በጸሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል፡፡ በዚህ ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ' ፀሐይንም የሚያመልክ' ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር፡፡ ✔እናታችን ቅድስት አርሴማም ተጋድሎዋን የጀመረችው የዚህ ጨካኝ ንጉሥ አገልጋይ ወይም ሹም ፳፯ ክርስቲያኖችን እንደልማዱ እየደበደበ' እየገረፈና ልዩ ልዩ ስቃይ እያደረሰባቸው ሲወስዳቸው በማየቷ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ስለኔ ወደገዢዎችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ፡፡’’ (ማቴ. ፲፡፲፮፡፲፱)፡፡ ያለውን በማሰብ ቅድስት አርሴማም ገና በሃያ ዓመቷ የዚህን ዓለም ንጉሥ እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ወገኖቿ ጋር ግንባር ቀደም በመሆን ትመሰክር ጀመር፡፡ የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ልትሠዋ በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ለእርሱም ሙሽራ እንድትሆን ብዙ ወተወታት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን ናቀችው ‘‘እኔ የሰማያዊው ንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለትም መለሰችለት፡፡ ✔ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ በመናቁም ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሰሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡ አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡ ንጉሡ ይበልጥ ነደደው ክርስቲያኖቹ በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሰሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን የጠበቀ አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡ በሌላም በብዙ መንገድ ሊያጠፋቸው እንደሞከረ ገድሏ ይተርካል፡፡ ✔በመጨረሻም ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ በሰይፍ እንዲያልቁ ይወስናሉ፡፡ እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር፡፡ በመደሰቷም እየጸለየች አይዟችሁ ጽኑ ትላቸው ነበር፡፡ በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽናቷን ተመልክቶ ቃል ኪዳን ይገባላታል፡፡ ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም ስቃይሽን አጸናብሻለሁ ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት አይኗን አስወጥቶ በእጇ ያሲዛታል፤ ጡቷን ያስቆርጣል፤ በኋላም አንገቷን ያሰይፋታል በዚሁ ሁኔታ እናታችን ሰማዕትነትን ተቀበለች፡፡ ይህንን ሁሉ መከራ ስለአምላኳ ስትል እራሷን አሳልፋ የሰጠች ድንቅ ሰማዕት ናት፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’ (መዝ.) እንዳለ ለእናታችንም የገባላት ቃል ኪዳን ‘‘በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤ የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን የዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ ፲፪ ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ እገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው፡፡ 🙏የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ጸሎትና ምልጃ ከእኛ ከምዕመናት ጋር ለዘላለሙ ይኑር፡፡ አሜን🙏

ሰው ለሰው.mp31.54 MB