en
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Show more
4 374
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

⚛️🔘 #አልቦ_አበቅቴ 🔘⚛️ ➣ የቀመር መጀመሪያ አልቦ አበቅቴ ነው፡፡ ➣ በአልቦ አበቅቴ፣ በ11 አበቅቴ፣ 22 አበቅቴ የተነሳ ወንጌላዊ በአንድ ንዑስ ቀመር 5፣ 5 ጊዜ ይመላለሳል፡፡ ምሳሌ፡- 1987፣ 1988፣1989፣ 2006፣ 2007፣ 2008 ዓ.ም ➣ በ3 አበቅቴ የተነሳ ወንጌላዊ ግን 4 ጊዜ ተመላልሶ በ5ኛው አልቦን ይቀበላል፡፡ ምሳሌ፡- 1990 ዓም ወንጌላዊ ማርቆስ አበቅቴ 3 ነበር፤ በተመሳሳይ 1994፣ 1998፣ 2002፣ በነዚህ ዓመታ ወንጌላዊው ይውልና በ2006 ዓ.ም አልቦን ይቀበላል፡፡2009፣ 2013፣ 2017፣ 2021፣ ማቴዎስ ይሆንና በ2025 አልቦን ይቀበላል፡፡ ➣ በአልቦ አበቅቴ የተነሳ ወንጌላዊ በ2ኛው 14፣ በ3ኛው 28 ፣ በ4ኛው -12፣ በ5ኛው 26 አበቅቴ ይቀበላል፡፡ ማርቆስ 2006-አልቦ፣ በ4ኛ ዓመቱ 2010 ማቆስ ወንጌላዊ 14 አበቅቴን ይቀበላል፡፡ ምሳሌ፡- 2006፣ 2010፣ 2014፣ 2018፣ 2022፣ 2026 ዓ.ም ➣ በ11 አበቅቴ የተነሳ ወንጌላዊ በ2ኛው 25፣ በ3ኛው 9፣ በ4ኛው 23፣ በ5ኛው 7 አበቅቴ ይቀበላል፡፡ ምሳሌ፡- 2007፣ 2011፣ 2015፣ 2019፣ 2023፣ 2027፣ 2031 ዓ.ም ➣ በ23 አበቅቴ የተነሳ ወንጌላዊ በ2ኛው 6፣ በ3ኛው 20፣ በ4ኛው 4፣ በ5ኛው 18 አበቅቴ ይቀበላል፡፡ ➣ በ3 አበቅቴ የተነሳ ወንጌላዊ በ2ኛው 17፣ በ3ኛው 1፣ በ4ኛው 10፣ በ5ኛው 29 አበቅቴ ደርሶ አልቦን ይቀበላል፡፡ ምሳሌ፡-2009 ዓ.ም፣ 2013 ዓ.ም፣ 2017 ዓ.ም፣ 2021 ዓ.ም፣ 2025 ዓ.ም ➣ አልቦ አበቅቴ በሆነ በዓመቱ መጥቅዕ መስከረም 19 ቀን ይውላል፡፡ ምሳሌ፡- 2007 ዓ.ም በ2ኛው ዓመት ጥቅምት 8 ቀን ይውላል (2008 ዓ.ም) በ3ኛው ዓመት መስከረም 27 ቀን ይሆናል፡፡ በ4ኛው ዓመት መስከረም 17 ቀን፣ በ5ኛው ዓመት ጥቅምት 5፣ በ6ኛው ዓመት መስከረም 24፣ በ7ኛው ዓመት ጥቅምት 13 ቀን፤ በ8ኛው ዓመት ጥቅምት 2 ቀን፤ በ9ኛው ዓመት መስከርም 21 ቀን፤ በ10ኛው ዓመት ጥቅምት 10፤ በ11ኛው ዓመት - መስከረም 29 ቀን፤ በ12ኛው ዓመት - መስከረም 18 ቀን፤ በ13ኛው ዓመት - ጥቅምት 7 ቀን፤ በ14ኛው ዓመት - መስከረም 26 ቀን፤ በ15ኛው ዓመት - መስከረም 15 ቀን፤ በ16ኛው ዓመት - ጥቅምት 4 ቀን፤ በ17ኛው ዓመት - መስከረም 23 ቀን፤ በ18ኛው ዓመት - ጥቅምት 12 ቀን ይውልና ደርሶ አልቦ ይቀበላል፡፡ ◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶ ይ🀄️ጥላል ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

#አበቅቴ_ተረፈ_ዘመን_ነው #ስንል_ምን_ማለት_ነው? https://t.me/EOTC2921 🔵 እንደሚታወቀው አበቅቴ በጨረቃና በፀሐይ መካከል ባለ የጉዞ ልዩነት ጋር የተያያዘ ነው። አበቅቴን ተረፈ ዘመን ነው ስንልም ጨረቃ ጉዞዋን ፈጽማ ካቆመችበት ቀን አንስቶ ፀሐይ ጉዞዋን እስከምትፈጽምበት (ጳጉሜን አምስት) ቀን ድረስ ያሉት ቀናት ተረፈ ዘመን ወይም አበቅቴ ይባላሉ። እነዚህ ቀናት ለሚቀጥለው ዓመት (ዘመን) አበቅቴ ይሆናሉ። ⚛️ ለምሳሌ፦ ጨረቃ የ2003 ዓ.ም ጉዞዋን የፈጸመችው 28፣ 2003 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ከነሐሴ ሃያ ዘጠኝ ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን ያሉ ቀናት ሰባት ናቸው። ይህ ሰባት ተረፈ ዘመን ሲሆን ለሚቀጥለው ዓመት ማለትም ለ2004 ዓ.ም አበቅቴ ይሆናል ማለት ነው። ⚛️ ይህንን ያገኘነው ከላይ ከዚህ ቀደም ሲል ዓውደ አበቅቴ ወይም ንዑስ ቀመር ስንመለከት በአስራ ዘጠኝ ዓመት አንድ ጊዜ ፀሐይና ጨረቃ በተፈጠሩበት ኆኅት (መስኮት) ውስጥ በተራክቦ ያድራሉ ብለናል። ይህ ማለት በዚህን ዓመት ፀሐይና ጨረቃ ዑደታቸውን በአንድ ላይ ስለሚጀምሩ በመካከላቸው የሚኖር ልዩነት የለም ማለት ነው። ⚛️ ስለዚህ አበቅቴው አልቦ ወይም ዜሮ ይሆናል ማለት ነው። በዚህ ዓመት ፀሐይና ጨረቃ ዑደታቸውን መስከረም አንድ ቀን ይጀምራሉ። ⚛️ ለምሳሌ በ1987 ዓ.ም ወንበሩ ዜሮ ስለነበር አበቅቴው አልቦ ወይም ዜሮ ነበር። ከዚህ ዓመት ጀምሮ በአንድ አውደ ጨረቃ ወይም 354 ቀን እያዞርን ብንመጣ በ2003 ዓ.ም ጨረቃ ጉዞዋን ነሐሴ 27፣ 2003 ዓ.ም ትፈጽማለች። ስለዚህ ከነሐሴ 29 ቀን ጀምረን እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን ያሉት ሰባት ቀናት የ2004 ዓ.ም አበቅቴ ነበር ማለት ነው። አበቅቴ ዜሮ ከሆነበት ቀን አንስቶ አስራ አንድ ቀን እየደመርን ብንመጣም የየዘመኑን አበቅቴ ማግኘት እንችላለን። ይህ አበቅቴ ሁልጊዜ በየአስራ ዘጠኝ ዓመት ተመሳሳይ ነው። አስራ አንድ ጥንተ አበቅቴ መሆኑን ወይም በፀሐይና በጨረቃ መካከል ያለ የአንድ ዓመት ልዩነት መሆኑ መረሳት የለበትም። 👉 ከዚህ ቀጥለን የአንድ አውደ አበቅቴ ወይም የአስራ ዘጠኝ ዓመት አበቅቴን እንመለከታለን፡፡ ፩. በ1987 ዓ.ም አበቅቴ ዜሮ ነበር።     ፪. በ1988 ዓ.ም 0 + 11 = አበቅቴው 11 ይሆናል፡፡ ፫. በ1989 ዓ.ም 11 + 11 = አበቅቴው 22 ፬. በ1990 ዓ.ም 22 + 11 = 33፤ በ30 ስንገድፈው አበቅቴው 3 ይሆናል። ፭. በ1991 ዓ.ም 3 + 11 = 14 ፮. በ1992 ዓ.ም 14 + 11 = 25 ፯. በ1993 ዓ.ም 25 + 11 = 36፤ በ30 ስንገድፈው አበቅቴው 6 ይሆናል። ፰. በ1994 ዓ.ም 6 + 11 = 17 ፱. በ1995 ዓ.ም 17 + 11 = 28 ፲. በ1996 ዓ.ም 28 + 11 = 39፤ በ30 ስንገድፈው 9 ይሆናል። ፲፩. በ1997 ዓ.ም 9 + 11 = 20 ፲፪. በ1998 ዓ.ም 20 + 11 = 31፤ በ30 ስንገድፈው 1 ይሆናል። ፲፫. በ1999 ዓ.ም 1 + 11 = 12 ፲፬. በ2000 ዓ.ም 12 + 11 = 23 ፲፭. በ2002 ዓ.ም 23 + 11 = 34፤ በ30 ስንገድፈው 4 ይሆናል። ፲፮. በ2002 ዓ.ም 4 + 11 = 15 ፲፯. በ2003 ዓ.ም 15 + 11 = 26 ፲፰. በ2004 ዓ.ም 26 + 11 = 37፤ በ30 ስንገድፈው አበቅቴው 7 ይሆናል። ፲፱. በ2005 ዓ.ም 7 + 11 = 18 በ2006 ዓ.ም 18 + 11 = 29 ይሆናል፡፡ አበቅቴው 29 ከሆነ መጥቅዕ አንድ ይሆናል። እዚህ ጋር አንድ አዋጅ ወይም የሐዋርያት ትዕዛዝ አለን። ይኸውም “ወኢይኩን አሐደ መጥቅዕ ለዘመን - ለዘመን አንድ መጥቅዕ አይሁን” ስለሚል አንድ መጥቅዕ አይሆንም። መጥቅዕ ደግሞ አንድ ከሆነ በዚህ ዘመን አበቅቴው አልቦ ወይም ዜሮ ይሆናል ማለት ነው። ከላይ እንዳየነው በ19 ዓመት አንድ ጊዜ ፀሐይና ጨረቃ በተራክቦ ስለሚያድሩ ከ1987 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ያለው ዓመት 19 ሲሆን አንድ አውደ አበቅቴ ያበቃል። በ2006 ዓ.ም እንደገና ተመልሶ አበቅቴው ዜሮ ይሆንና ሌላኛው አውደ አበቅቴ ዑደት ይጀምራል። በሌላም መንገድ ማለትም ወንበር በምናወጣበት መንገድ የ2006 ዓ.ም ወንበርን ብናወጣ ወንበሩ ዜሮ ነው የሚሆነው። ወንበሩ ዜሮ ከሆነ ደግም አበቅቴውም ዜሮ ይሆናል። #ተከታታዩን_አበቅቴ_ለማወቅ_የሚስችሉ_ስሌቶች 💎 የጨረቃ ወር አንድ ጊዜ 29 አንድ ጊዜ 30 ነው፡፡ ከአበቅቴ ቢነሱ 18፤ ከአልቦ አበቅቴ ቢነሱ 19 ይሆናል፡፡ አልቦ አበቅቴ በሆነ በዓመቱ 11 አበቅቴ ይሆናል፡፡ የ2ኛው ዓመት አበቅቴ 22፣ የ3ኛው ዓመት 3፣ የ4ኛው ዓመት 14፣ የ5ኛው ዓመት 25፣ የ6ኛው ዓመት 6፣ የ7ኛው ዓመት 17፣ 8ኛው ዓመት 28፣ 9ኛው ዓመት 9፣ 10ኛው ዓመት 20፣ የ11ኛው ዓመት 1፣ የ12ኛው ዓመት 12፣ የ13ኛው ዓመት 23፣ የ14ኛው ዓመት 4፣ የ15ኛው ዓመት 15፣ የ16ኛው ዓመት 26፣ የ17ኛው ዓመት 7፣ የ18ኛው ዓመት 18፣ የ19ኛው ዓመት 29 ነው፡፡ይህ አልቦ ነው፡፡ ከመመላለሻው ተላልፎ በሕፀፅ ወርኅ ልክ ስለሆነ ባላው ይያዛል፡፡ ትገድፎ ወኢታመጽኦ ኀበ ፳ ዓመት እስመ ኮነ መጠነ ኅልቆ ወርኅ ሕጹጽ እንዲል መራሒ ዕውር አልቦን ተቀበል ይሏል፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ባለው አበቅቴ ላይ 11 ቢጨምሩ የሚመጣው ዘመን አበቅቴ ይታወቃል፡፡ 22 ቢጨምሩ የ2ኛው ዓመት አበቅቴ ይታወቃል ማለታችን ይታወሳል፡፡ እንዲሁም ባለው አበቅቴ ላይ 3 ቢጨምሩ የ3ኛው ዓመት አበቅቴ ይታወቃል፤ 14 ቢጨምሩ የ4ኛው ዓመት፤ 25 ቢጨምሩ የ5ኛው፣ 6 ቢጨምሩ የ6ኛው፤ 17 ቢጨምሩ የ7ኛው፤ 28 ቢጨምሩ የ8ኛው፤ 9 ቢጨምሩ የ9ኛው፤20 ቢጨምሩ የ10ኛው፤ 1 ቢጨምሩ የ11ኛው፤ 12 ቢጨምሩ የ12ኛው፤ 23 ቢጨምሩ የ13ኛው፤ 4 ቢጨምሩ የ14 ኛው፤ 15 ቢጨምሩ የ15ኛው፤ 26 ቢጨምሩ የ16ኛው፤ 7 ቢጨምሩ የ17ኛው 18 ቢጨምሩ የ18ኛው ዓመት አበቅቴ ይታወቃል፡፡ ዳግመኛም በመጨረሻው በ18 አበቅቴ ላይ 19 ቢጨምሩ ያለፈው ዓመት አበቅቴ ይታወቃል፡፡ 8 ቢጨምሩ ያለፈው የ2ኛው ዓመት አበቅቴ ይታወቃል፤ 27 ቢጨምሩ ያለፈው የ3ኛው ዓመት አበቅቴ ይታወቃል፡፡ እንደዚህ እያልን እስከ 19 ድረስ ማስላት ይቻላል፡፡ #በጨረቃ_አበቅቴን_የማውጣት_ሌላኛው_ስሌት ♣ ጨረቃ ከመወለጃዋ ነሐሴ 8 ወደ ነሐሴ 7 አትወርድም ከጳጉሜ 5 ወደ ጳጉሜ 6 አትወጣም፡፡ ከነሐሴ 23 ከጳጉሜን 5 ስንደምራቸው 28 ይሆናል፡፡ መመላለሻዋ 28 ዕለት ነው፡፡ ስድስተኛው ጳጉሜን ስለምን ከአበቅቴ ሳይገባ ቀረ? ቢሉ 👉 አራቱ ወንጌላውያን በሰዓት፣ በኬክስ፣ ከአራት አድርገው ይካፈሉታል እንጂ እንደ አምስተኛው ጳጉሜ ለአንዱ ወንጌላዊ አይደርስምና ስለዚህ ከአበቅቴ ገብቶ ሳይቆጠር ቀረ፡፡ ከ17 አበቅቴ በላይ 18 ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ጊዜ ሐምሌ 30 ብሎ ከሐምሌ 30 ላይ አበቅቴውን ጨምሮ ቆጥሮ ከቆጠሩ በኋላ 84 እንዲሆን ከነሐሴ ወር ጨምሮ የጨመረውን ያህል ከነሐሴ ወር አንስቶ ትርፉ አበቅቴ ይሆናል፡፡ 💙 ምሳሌ፡- 1995 ዓ.ም አበቅቴው 28 ነው፡፡ ከነሐሴ ለመቀነስ የጨረቃ ኢይወርዱ ነሐሴ 8 ስለሆነ ሐምሌ 30ን እና 28ቱን አበቅቴ ቢያገናኙ 58 ይሆናል፡፡ 84 ለማድረግ 26 ቀን ያስፈልገዋል፤ ይህ 26 ቀን የመጣ ከነሐሴ ወር ነው፡፡ ከነሐሴ 26 ቀን ይዞ እስከ እስከ ጳጉሜ 5 ቢቆጥሩ የ96 ዓመተ ምህረትን አበቅቴ ያስገኛል፡፡ ይ🀄️ጥላል

📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖 💚💛❤️ ክፍል ፲፬ 💚💛❤️ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞ https://t.me/EOTC2921 🛅✝⛪️💠⛪️💠⛪️💠✝🛅 የ፳፻፲፫ ዓ.ም አጽዋማትና በዓላት ስሌት 🛅✝⛪️💠⛪️💠⛪️💠✝🛅 #መደብን_እና_ወንበርን #አበቅቴን_በቀመረ_ዳንኤል_ማውጣት ፲፬. #ሱባኤ_ዳንኤል (133 ዓመት)፡- ዳንኤል 133ዓመትን 1ሰንበት ይላል፡፡ 133ን 60 ጊዜ እያመላለሱ ቢቆጥሩ ምጽዓተ ክርስቶስን ያስረዳል፡፡ ይህም ‘‘ሱባኤ ሰንበታት ፷ በምጽአትከ ተሐትመ አበሳ’’ ፷ ሱባኤ በተፈጸመ ጊዜ በመምጣትህ አበሳ ተዘጋ፡፡ 1ዐቢይ ቀመር 4 ቀመረ ዳንኤል ይሆናል፡፡14 ዐቢይ ቀመር 56 ቀመረ ዳንኤል ይሆናል፡፡15 ዐቢይ ቀመር ሲሆን ቀመረ ዳንኤል ፷ ይሆናል፡፡ 60 x 133 = 7980 ይህም ምጽአተ ክርስቶስ ነው፡፡ 💙 አንድም ሰንበተ ዳንኤል፡- ዳንኤል ፯ቱን ዓመት ፩ ሱባኤ እያለ ይቆጥር ነበር ይህን በዓውደ ንዑስ ቀመር (19) ቢያባዙት 7 x 19 =1 33 ይሆናል፡፡ 133 x 60 = 7980 ይህም ምጽአተ ክርስቶስን ያመለክታል፡፡ ♥ ቀመረ ዳንኤል 133 ዓመት እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል፡፡ 💙 የ2013 ዓመተ ምህረት ወንበርን ለማውጣት = ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) + ዓመተ ምህረት =5500 + 2013 = 7513 ዓመተ ዓለም ይሆናል፡፡ 7513 ዓመተ ዓለምን ለቀመረ ዳንኤል (133) ማካፈል ነው፡፡ 7513 ÷ 133 = 56 ቀመረ ዳንኤል፣3 ንዑስ ቀመር ሆኖ 8 ዓመት ይተርፋል፡፡ = 8 የ2013 ዓ.ም መደብ ናት፡፡ ወንበር = መደብ-1 = 8-1 = 7 ይህ የ2013 ዓ.ም ወንበር ነው፡፡ #አዋጅ (ሕግ)፡- ‘‘አንዱን ለዘመን ስጠው’’ ይህ አዋጅ (ሕግ) ይባላል፡፡ 💙 አንድ ያተትንበት (የቀነስንበት) ምክንያት ዓመቱ ስለተጀመረ አብረን 2013 ዓ.ም ብለን ቆጠርን ዓመቱ ስላላለቀ አተትን (ቀነስን) ስለተጀመረ ተቆጠረ ስላልተጨረሰ ታተተ እንዲል፡፡ 💙 አበቅቴ = ወንበር X በጥንተ አበቅቴ÷ 30 ፲፭. #አበቅቴ፡- አበቅቴ አፖክቴ ከሚል የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ተረፈ ዓመት (ከዓመት የተረፈ)፣ ሥፍረ ሌሊት፣ ቁጥረ ሌሊት ማለት ነው። 💙 ተረፈ ዘመን የተባለበት ምክንያት እንደሚታወቀው ፀሐይና ጨረቃ በአንድ መስኮት ውስጥ የተፈጠሩ ሲሆን ዑደት በሚያደርጉ ጊዜ ግን በተለያየ ቀን ዑደታቸውን ይፈጽማሉ። በዚህም የተነሳ በመካከላቸው የቀናት ልዩነት የሚኖር ሲሆን ይህ ልዩነት አበቅቴ ወይም ተረፈ ዘመን ይባላል። የፀሐይ አንድ ዑደት 365 ቀን ከአስራ አምስት ኬክሮስ (ከስድስት ሰዓት) ሲሆን የጨረቃ አንድ ዑደት ደግሞ 354 ቀን ከሃያ ሁለት ኬክሮስ ነው። ስለዚህ የጨረቃ ዑደት ፀሐይ ላይ ለመድረስ አስራ አንድ ቀን ይቀራታል። ይህ ቀሪ (አስራ አንድ) አበቅቴ ይባላል። ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፋቸው ሲተረጉሙት፡- አበቅቴ በጽርዕ ሄፓክቴ ሲሆን ጭማሪ፣ ተውሳክ፣ የቁጥር ሟሟያ ማስተካከያ፣ ተረፈ ዓመት፣ የቀመር ትራፊ ትርፍ፣ ፍድፋጅ፤ አበቅቴ ፀሐይ አበቅቴ ወርኅ አበቅትያት፣ ሠርዐ ሐሳበ አበቅቴ (አቡሻኽር ስንክሳር ጥቅምት 12) ኪ.ወ.ክ ገጽ 199 ♥አበቅቴ 16፣ 29፣ 30 አይሆንም፡፡ ♥አበቅቴ ማለት በፀሐይና በጨረቃ መካከል ያለ ልዩነት ማለት ነው፡፡ #️የአበቅቴ_አፈላለግ_መንገዶች፦ ➣አበቅቴን በብዙ ዓይነት መንገድ ማግኘት (መስራት) ይቻላል። በዚህ ክፍለ ትምህርት 13 የሚሆኑ የተለያዩ የአበቅቴ መፈለጊያ መንገዶችን እናያለን። ፩. አበቅቴን በወንበር ማግኘት፡- = ወንበር X በጥንተ አበቅቴ ÷ 30 = 7 X 11 = 77 / 30 = 2 ይደርስና ቀሪ 17 ይሆናል፡፡ ስለዚህ የ2013 ዓ.ም አበቅቴ 17 ወጣ ማለት ነው፡፡ ፪. ያለፈውን ዓመት አበቅቴና ጥንተ አበቅቴን በመደመር የዘንድሮውን (ያለንበትን) ዓመት አበቅቴ ማወቅ ይቻላል። ✔ምሳሌ የ2012 ዓ.ም አበቅቴ 6 ነበር ጥንተ አበቅቴ (11) ስንደምርበት 6 + 11 = 17፣ የ2013 ዓ.ም አበቅቴ ወጣ፡፡ ፫. ያሉበትን ዘመን አበቅቴና ጥንተ አበቅቴውን ቢያገናኙ ወደ ፊት ያለውን ዓመት አበቅቴ ማወቅ ይቻላል፡፡ ✔ምሳሌ፡- የ2012 ዓ.ም አበቅቴ 6 ነው፤ ጥንተ አበቅቴ ደግሞ 11 ነው፤ ሁለቱን ስናገናኝ = 6 + 11 = 17፣ የ2013 ዓ.ም አበቅቴ አገኘን፡፡ ፬. አበቅቴን በዓመተ ዓለም ማግኘት (ማወቅ) ይቻላል። ይህም ከምንፈልገው ዓመተ ዓለም ላይ አንድን ቀንሰን በ19 ማካፈል የተረፈውን በ11 ማባዛት ከ30 በላይ ከሆነ ለሰላሳ በማካፈል ማግኘት ይቻላል። ✔ምሳሌ፡- የ2013 ዓ.ም አበቅቴን ማወቅ ብንፈልግ መጀመሪያ 5500 + 2013 = 7513 ከዚህ ላይ 1 እንቀንስና ለንዑስ ቀመር (19) እናካፍለዋለን፡፡ = 7513 - 1 = 7512 ÷ 19 = 395 ዐውደ ንዑስ ቀመር ይደርስና 7 ይተርፋል፡፡ 7ን በጥንተ አበቅቴ (11) አባዝተን ከ30 በላይ ከሆነ ለ30 እናካፈለውና ቀሪው የዘመኑ አበቅቴ ይሆናል፡፡ = 7 x 11 = 77 = 77 / 30 = 1 ጊዜ ደርሶ 17 ይተርፋል፡፡ ይህም የ2013 ዓ.ም አበቅቴን አወጣን ማለት ነው፡፡ ፭. አበቅቴን ለማግኘት ከ30 ላይ የዓመቱን መጥቅዕ በመቀነስ ማግኘት ይቻላል። ✔ይህ ማለት አበቅቴ = 30 - የዓመቱ መጥቅዕ ምክንያቱም አበቅቴና መጥቅዕ ሲደመሩ ሰላሳ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን መጀመሪያ አበቅቴን ማወቅ አለብን፡፡ ፮. አበቅቴን በጨረቃ ዑደት (ጉዞ) ማግኘት ይቻላል። ◉ ከአለንበት ዓመት ያለውን አበቅቴ ከነሐሴ 24 ወደ ኋላ የዘመኑን አበቅቴ ከቀኑ ቀንሰህ ከትርፉ ቀን ይዘን እስከ ጳጉሜ 5 ቢቆጥሩ ወደፊት ያለውን ዓመት አበቅቴ ያስገኛል፡፡ ✔ምሳሌ፡- የ2012 ዓ.ም አበቅቴው 6 ነው፤ ከነሐሴ 24 ላይ 6 ሲቀነስ 18 ቀን ይተርፋል፡፡ የጨረቃ ዓመት ነሐሴ 18 ቀን ሞላ ማለት ነው፡፡ ከነሐሴ 19 ይዞ እስከ ጳጉሜ 5 ቢቆጥሩ 17 ይሆናል (ይተርፋል)፡፡ ይህም የ2013 ዓመተ ምህረት አበቅቴ 17 መሆኑ በዚህ ያስረዳል። ፯. ከአለንበት ዘመን አበቅቴ ላይ ጥንተ አበቅቴውን ብንቀንሰው ያለፈውን ዓመት አበቅቴ ያስገኝልናል፡፡ ✔ምሳሌ፡- የ2011 ዓ.ም አበቅቴ 25 ነበር፤ ጥንተ አበቅቴውን (11) ብንቀንስለት የ2010 ዓ.ም አበቅቴን ይሰጠናል፡፡ = 25 - 11 = 14 የ2010 ዓ.ም አበቅቴ ነው። ፰. ያለንበትን ዘመን አበቅቴ ላይ 19 ቢደምሩ (ቢጨምሩ) ያለፈውን ዓመት አበቅቴን ያስገኛል፡፡ ✔ምሳሌ፡- የ2012 ዓ.ም አበቅቴ 6 ነው፤ ከ6 ላይ 19 ቢጨምሩ (ቢደምሩ) 6 + 19 = 24 የ2011 ዓ.ም አበውቴን ያስገኛል፡፡ ፱. ያለንበትን ዘመን አበቅቴና ጥንተ መጥቅዕን ቢያገናኙ ያለፈውን ዓመት አበቅቴን ያስገኛል፡፡ ✔ምሳሌ፡- የ2012 ዓ.ም አበቅቴ 6 ነው፤ ጥንተ መጥቅዕ (19) = 6 + 19 = 25 የ2011 ዓ.ም አበቅቴ ነው። ፲. ከአለው አበቅቴ ላይ 8 ቢጨምሩ ያለፈውን የ2ኛ ዓመት አበቅቴ ያስገኛል፡፡ ✔ምሳሌ፡- የ2012 ዓ.ም አበቅቴ 6 ነው፤ 6+8=14 የ2010 ዓ.ም አበቅቴ 14 ነበር፡፡ ፲፩.በአለው አበቅቴ ላይ 14 ቢጨምሩ በ4፣ በ4 ዓመት የሚመጣውን ወንጌላዊና አበቅቴ ማወቅ ይቻላል፡፡ በማቴዎስ ቢጨምሩ የማቴዎስ፤ በማርቆስ ቢጨምሩ የማርቆስ፤ በሉቃስ ቢጨምሩ የሉቃስ፤ በዮሐንስ ቢጨምሩ የዮሐንስ ይታወቃል፡፡ ✔አልቦ በሆነ ጊዜ ግን ያው አልቦ ነው፡፡ በዓመቱም 11 አበቅቴ ይሆናል፡፡ ፲፪. ባለው አበቅቴ ላይ 17 ቢጨምሩ በየ4 ዓመት የሆነው ያለፈው ወንጌላዊና አበቅቴ ይታወቃል፡፡ ይ🀄️ጥላል

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

🌾✞ #ያከብርዋ_ለሰንበት ✞🌾 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት ||፪ ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያዕረፋ ባቲ እስመባቲ አዕረፈ እምኩሉ ገብሩ |||፪ 🌾✞¤¤¤~~~✞~~~¤¤¤✞🌾 ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃንም በገነት ||፪ ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ |||፪ ➤➤➤➤➤➤✞➤➤➤➤➤➤ ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌿🌾✞ #ኦ_ርኅርኅተ_ኅሊና ✞🌾🌿 ኦ ርኅርኅተ ኅሊና አፍቅሮተ ሰብአ ልማዳ/፪/ ለእለጌሰሙ/፬/ ትመስል/፫/ እንግዳ//፪// | | |...፫ #ትርጉም፦ ሰውን ማፍቀር ልማዷ የሆነ እመቤታችን በየጊዜው/ዘወትር/ አዲስ ትመስል ነበር ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 @Orthodox2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✝ ️💒 ከ ታቦተ ፅዮን ቤተክርስቲያን የተላከ በሀገራች ኢትዮጲያ ውስጥ በምትገኘው የኢ/ት ጥንታዊ ገዳሞች  ታሪክ የታቦተ ፅዮን ቤተክርስቲያን ታሪኮች ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን አማኞች በትግረኛ , በአማርኛ በ Youtube ቻናል ትምህርቶችን ለማስተማር  ዝግጅቶችንን አጠናቀን መተናል ። በዚህ መንፈሳዊ የዩትዩብ ቻናል የተለያዩ ስብከቶችና ትምህርቶች በታላላቅ መምህራን በትግረኛ , በአማርኛ ማግኘት ትችላላቹ ! 🌻🎯ወንጌሎችን 🌻🎯 መዝሙሮች 🌻🎯 ስነ ፅሑፎች 🌻🎯 ምክረ አበው  እና ለመናፍቃን መልስ የምንሰጥበት የታቦተ ፅዮን ትክክለኛው የ Youtube ቻናል ነው ። ከታች ያለውን Link ተጭነው የ Youtube ቻናላችንን Subscribe ያርጉ  ! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCJQ33VxRatkDMgl3CKcCDOQ?subconfirmation=yes 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 ብስም መንበረ ታቦተ ፅዮን ዝተሰየመ መንፈሳዊ ናይ ዩትዩብ ቻናልና ብሊቃውንቲ ትግራይን ብዘማርያንን ዝ/ዩ ስብከታትን መዝሙራትን  ምድላዋቱ ዛዚሙ ስርሑ ጀሚሩ ኣሎ ።  "ተመለሱ ፣ ኣበሳኹም መዓንቀፊ ኸይኰነኩምሲ፣ ካብ ኵሉ ግህሰትኩም ተመለሱ። ... ሓድሽ ልብን ሓድሽ መንፈስን ድማ ግበሩ" (ሕዝ 18፡30-31)

እንኳን አደረሳቹ ለታላቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እያልን የሳቸው ገድል እንዲያደምጡ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጋብዘኖታል ገድሉን ለመከታተል ገድል የሚለውን መንካ ይቻላል። ገድለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገድለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገድለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩት እንዳታልፋ በቻናሉ ቀን በቀን አዳዲስ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይለቀቃል በማግስቱም የቻናሉ አባላት ድምፅ ከሰጡ በኋላ መልሱ ይለቀቃል። በጣም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ ቻናል ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ያለውን JOIN የሚለውን ይጠቀሙ። JOIN JOIN JOIN JOIN JOIN JOIN ከመከፈቱ የብዙዎች ቀልብ የሳበው ማህሌት ቲዩብ እሆ አስተማሪ በሆኑ ቪዲዮዎች መቶልናል። በቻናሉም ◽️መንፈሳዊ ጥያቄዎች ◽️መዝሙሮች ◽️ገድላት ◽️ታሪኮች 🔖ሁሉንም በአንድ ላይ በ ማህሌት ቲዩብ ያገኛሉ ይቀላቀሉን። ቻናላችንን subscribe በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ። ✝ማህሌት-ቲዩብን ለመከታተል✝ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን መጫን በቂ ነው። ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት

✞✞✞ #የአምላክ_አቃቤ_ሕግ ✞✞✞ https://telegram.me/EOTC2921 ገባሬ መንክራት በግብሩ ያወቅነው፣ የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው፣ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ አቃቤ ህግ፣ የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ፡፡ #አዝ•••••••✞✞✞••••••• ፀሐይ /2/ የምድራችን ፀሐይ፣ በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ፣ የመላዕክት ወዳጅ /2/ ገብረ ህይወት ሰማይ፡፡ #አዝ•••••••✞✞✞••••••• መብረቅ/2/ ሰረገላው መብረቅ፣ የቃል ኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ፣ የፍጥረቱ ደስታ/2/ ገብረ ህይወት ጻድቅ። #አዝ•••••••✞✞✞••••••• ኮከብ/2/ ክብረ ገዳም ኮከብ፣ አለምን የሚያስንቅ መዓዛው የሚስብ፣ አልክ ስሉስ ቅዱስ/2/ ገብረ ህይወት ኪሩ። #አዝ•••••••✞✞✞••••••• ስሒን/2/ ፄና ልብሱ ስሒን፣ የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን፣ የሚነበብ መጽሐፍ/2/ ገብረ ህይወት ድርሳን። #አዝ•••••••✞✞✞••••••• መቅረዝ/2/ የማህቶት መቅረዝ፣ ምድረ ከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ፣ የዝግቲው ፈዋሽ/2/ ገብረ ህይወት ምርኩዝ፡፡{➋} #አዝ•••••••✞✞✞••••••• https://telegram.me/EOTC2921

🌾✞ አባታችንም ‹‹አዎ እኔ ሰው ነኝ ያውም የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ›› አሉት፡፡ ንጉሡም መልሶ ‹‹በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን?›› አላቸው። አባታችንም ‹‹አዎን እኔ በእርሱ አምናለሁ አላፍርም ስለእኔ የተሰቀለውን በሰው ፊት አምነዋለሁ፡፡ ስለእኔ ብቻ አይደለም ንጉሥ ሆይ ስለ አንተና ካንተ ጋር ስላሉትም ነው እንጂ፡፡ በእርሱ እመኑ የዘላለምን ሕይወት ታገኙ ዘንድ አላችሁ። ንጉሡም ይህንን በሰማ ጊዜ በጣም ተቆጥቶ ሠራዊቱን ሁሉ ጠርቶ በቶሎ እሳት እንዲያነዱ አዘዛቸው፡፡ የእቶን እሳቱንም ካነደዱ በኋላ ‹‹በሉ ይህንን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ነኝ የሚለውን ፀጉረ ለባሹን አንስታችሁ ከእሳቱ ውስጥ ጨምሩት›› አላቸው፡፡ አባታችንም ንጉሡና መኳንንቱ ሠራዊቱ ሁሉ እያየአቸው ከእቶኑ እሳት ውስጥ ገቡ። ነገር ግን እሳቱ እንደ ወንዝ ውኃ ሆነ። የንጉሡም ሠራዊት ይህንን ከመለከቱ በኋላ ግማሾቹ ‹‹በዚህ ሰው አምላክ አምነናል›› አሉ፡፡ ንጉሡም 77 አዛዦቹን በማዘዝ ‹‹አምነናል›› ያሉትን ሰዎች አንገታቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸው፡፡ ቁጥራቸውም አርባ እልፍ ነበር፡፡ 🌾✞ ንጉሡም ሰይፉን መዝዞ የአባታችንን ራስ ሊቆርጥ ተወርውሮ ወደ አባታችን ሲሄድ ወዲያው ጽኑ የመብረቅ ነጎድጓድና ንውጽውጽታ ሆነ፡፡ ጌታችንም ወደ አባታችን ዘንድ መጣ፡፡ መብረቁም በአንድ ጊዜ ንጉሡንና ሠራዊቶቹን ሁሉ አጠፋቸው፡፡ የሞቱም ሰዎች ቁጥራቸው አራት መቶ ሺህ ሆነ፡፡ አንድስ እንኳን ሳይቀር ሁሉም አለቁ፡፡ አባታችንም በመብረቅ የሞቱን ሰዎች ባዩ ጊዜ ውስጣቸው በሀዘን አለቀሰ ነፍሶቻቸውን የጽልመት መላእክት ወደ ገሀነመ እሳት ሲያወርዷቸው ተመልክተዋልና፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ጌታችንን ‹‹እነዚህን ሰዎች ማርልኝ›› አሉት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሰው ስሕተተኛ ነው፣ አንተ ግን መሐሪ ይቅር ባይ ነህና በእኔ ምክንያት በእነዚህ ሰዎቸ አትፍረድባቸው…›› እያሉ በለመኑት ጊዜ ጌታችን ተሰወረባቸውና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አባታችንም ወዲያው አጠገባቸው ካለው ገደል እግራቸውን በገመድ አሥረው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ተሰቀሉ። ሰይጣንም መጥቶ ያችን ገመድ በቆረጣት ጊዜ አባታችን በገደሉ ሲወድቁ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ መጥቶ አባታችንን አቅፎ ያዛቸውና ‹‹በእግርህ ላቁምህ/ ወይስ በራስህ ላቆምህ ትወዳለህ/›› አላቸው፡፡ አባታችንም ገብረ መንፈስ ቅዱስም መልአኩን ‹‹ተወኝ በራሴ ልቁም›› አሉትና መልአኩም በዚያው ትቷቸው ዐረገ፡፡ 🌾✞ አባታችንም በጥርሳቸው ድንጋይ ነክሰው እስከ 30 ዓመት ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖሩ፡፡ ናላቸው ሁሉ ፈሶ አለቀ፣ አንጀታቸውም ፈሰሰ፣ እንደ ዕንጨትም ቅርፊት ሆኑ፡፡ ከ30 ዓመትም በኋላ ጌታችን ሰባቱን ሊቃነ መላአክትና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያን አስከትሎ ወደ አባታችን መጣና ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠርቶ ‹‹እነዚያን ከሐዲዎች ምሬልሃለሁ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ነክሰውት የነበረውን ድንጋይ በጣሉት ጊዜ ጥርሶቻቸው አብረው ተነቅለው ወደቁ፡፡ ጌታችንም በክቡራን እጆቹ ቢዳስሳቸው ሰውነታቸው ታደሰችላቸው፡፡ አባታችንም ጌታችንን ‹‹ምሬልሃለሁ ካልከኝና ከማርክልኝስ ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ጋር አዋሕድልኝ›› አሉት፡፡ ጌታችንም አባታችንን ‹‹እንዳልክ እንደወደድክ ይሁንልህ እኔ ሙታንን ልታስነሣ ሥልጣን የሰጠሁህ አይደለምን አሁንም ወደሞቱት ሰዎች ሂድና አማትብባቸው›› አላቸውና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ያንጊዜም አባታችን ወደሞቱት ሰዎች ሄደው በላያቸው ከጸለዩ በኋላ ‹‹እናንት ሁላችሁ በጌታዬ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሡ›› ቢሏቸው ሙታኑም ወዲያው አፈፍ ብለው ተነሥተው በአባታችን ፊት ቆሙ፡፡ አባታችንም ሃይማኖትን አስተምረው አጥምቀው ክርስቲያን አደረጓቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ከእነርሱ ተለይተው በመብረቅ ተጭነው ወደ ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡ 🌾✞ ዳግመኛም አባታችን እነዚያን ሰዎች ይጎበኟቸው ዘንድ ወደ ዐረብ አገር ሄዱ፡፡ እነዚያ ከሞት አስነሥተው ክርስቲያን ያደረጓቸው ሰዎችም ሃይማኖታቸውን ጥምቀታቸውን አጽንነተው ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በጽድቅ ሕይወት እየኖሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆነው ‹‹አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ›› እያሉ ሲያመሰግኑ ተመለከቷቸው፡፡ አባታችንም ይህንን አይተው ስለሰዎቹ መዳን ደስ ተሰኝተው ተመልሰው ወደ ምድረ ከብድ መጡ፡፡ ነገር ግን አባታችን ሄደው ሄደው እንደጎበኟቸው ሰዎቹ አላወቁም ነበር፡፡ እነዚያም ክርስቲያኖች እስከዛሬ ድረስ አሉ፡፡ 🙏የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!🙏 #ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤ ተስፋ ገብረ ሥላሴ 1992ዓ.ም፤ ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯