cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Gedooooo Shooting ,,,,,,,,photo store

* ፎቶችን ማስራት የምትፈልጉ # 0987172734/ @yane_yabechaye በውስጥ መስመር ማነጋገር ትችላላቹ Be adobe light Rome # ሀሳብ እና አስታየት ካሎት / @yane_yabechaye መናገር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
184Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​🌺የከንቲባው ልጅ🌺 🔥ክፍል 27 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ሀዘናቸው ሲጨንቀኝ ጊዜ 'እና አሁን እኔ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጉት ...?' ስላቸው "አሁንማ ያለኝ አንድ አማራጭ ብቻ ነው ። እሱ ደግሞ ካላንተ ፍቃድና ውሳኔ ውጪ መቼም የሚሆን አይነት አይደለም" ሲሉኝ 'ግድ የለም ይንገሩኝ ፤ ምንድነው እሱ...?' አልኳቸው ። "ምን መሰለህ ፡ ቅድም እንዳልኩህ የኔ ልጅ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና የኔ እሷን ከዚህ ሀገር ይዞ መሄድ ከሞት ለማዳን ቢሆንም ግን ለሷ ስሜት ጥሩ ላይሆን ይችላል ። እናም ፍቃድህ ቢሆንና አብረኸን ወደ አሜሪካ ብትሄድ ምን ይመስልሃል...? ፡ አውቃለሁ እዚህ ደስ የሚል ህይወት ሊኖርህ ይችላል ። ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ፣ ትምህርት ፣ ብዙ ነገሮችን ማጣትና መራቅ አትፈልግ ይሆናል ። ግን ምን ላድርግ...? ፡ በኔ ምክንያት ለአራት ዓመታት በአንድ ቤት ውስጥ ብቸዋን የሰቆቃ ህይወት ማሳለፏ ሳያንስ ፤ አሁን ደግሞ ነፃ ላወጣት ነው ባልኩበት በመጨረሻዋ ሰዓት ካንተ ጋር በፍቅር ወደቀችብኝ ። እሺ እኔ ብቻዬን ምን ላድርግላት ...? ፡ ሱቅ ሄደህ አትገዛው ነገር ፍቅር ነው ። በጣም ስለጨነቀኝ እና የልጄ ጉዳት ከአቅሜ በላይ ስለሆነብኝ ነው አንተንም የማስጨንቅህ" አሉኝ አይኖቻቸው በዕምባ ተሞልተው ። ጥያቄውን ለመመለስ ስጨነቅ አይተውኝ ነው መሠለኝ "ግድየለም ፡ በደንብ የምታስብበት በቂ ጊዜ እሰጥሃለሁ ። እንዳልኩህ እናንተን ለመከታተል ብዬ የአሜሪካ ጉዞዬን ሰርዤ ነበር ። እና እሱን process ለማስጨረስ ግዴታ ነገ ወደዛው በረራ ማድረግ ይኖርብኛል ። እናም በዚሁ ምክንያት ለአንድ ሳምንት እዛው ስለምቆይ አሁን የጠየኩህን ከዛ እስክመለስ ድረስ በደንብ አስበህበት መልስ እንደ ምትሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ ። ይቺን አንድ ሳምንት ህይወቴን ላንተ ነው አደራ ሰጥቼ የምሄደው ። ቢቻልህ ከትምህርት ሰዓትህ ውጪ ያለህን ጊዜ ከሷ ጋር ብታሳልፍ ደስ ይለኛል ። ደግሞ ዛሬ ስለሆነው ነገር ሁሉ እሷ ማወቅ የለባትም ። በቃ በጣም ስለመሸ ወደ ጊቢ ልመልስህና ከነገ ጀምሮ እስከ ምመለስበት ቀን ድረስ ህይወት ጋር እየመጣህ ከጎኗ መሆን ትችላለህ ። ምናልባት በወቅታዊው ጉዳይ ትምህርት የማይኖርህ ከሆነ ለደህንነታችሁ ሲባል እስክመጣ ድረስ ሀረር ብትሄዱ ለሷም ጥሩ ይመስለኛል ። ግን የሚመችህ ከሆነ ብቻ ነው ። እና ደግሞ ስልክህን ቅድም ለጥንቃቄ ብዬ ከኪስህ ወስጄ ነበር ። ልጄ በመቅረትህ እንዳታስብ በራሴ ስልክ ተመልሼ እየመጣሁ ነው ብዬ txt አድርጌላት ነበር ። እሷም "የኔ ጌታ እንዳትመጣ በቃ ፤ አባቢ እየተመለሰ ነው" የሚል txt ልካልሀለች" ብለውኝ ስልኬን መለሱልኝና መልዕክቱ እንደገባ አረጋግጬ ወደ ጊቢ ለመመለስ ተነሳሁኝ ። ከነበርንበት ክፍል ወጥተን ወደ ታች በደረጃ ወርደን በጣም የሚያምር ሳሎን ውስጥ አልፈን ደጃፍ ላይ ወደ ቆመው መኪና ገብተን የጊቢውን በር በሪሞት ከፍተው ወጣንና መልሰው በሪሞቱ ዘግተውት ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጉዞ ጀመርን ። ሌላ ነገር እንዳይመስል ዩኒቨርስቲው በር ጋር ሳንደርስ በቅርብ ርቀት ላይ መኪናውን አቁመው "አደራህን ፡ ያልኩህን በደንብ አስብበት ። ደግሞ እራስ ወዳድ ነህ እንዳትለኝ ፤ የልጄ ጉዳይ ሆኖብኝ ነው ። ስለሁሉም ግን በጣም ይቅርታ" አሉኝ ። ከልባቸው እንደሆነ ያስታውቃል ። እኔም 'ፈጣሪ ይቅር እንዲለንና ፣ በሰላም ሄደው በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞቴን ገልጬላቸው ፣ በቶኒ በር ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዘለኩኝ ።ብቻዬን እራት በልቼ ወደ ዶርም ገባሁ ። የኛ ጊቢ ሰሞኑን ከሶሪያ በላይ ስለሚያስፈራ የዶርሜን ልጆች ጨምሮ አብዛኛው ተማሪ ጊቢ ውስጥ አያድሩም ። ውጪ ሶስት ሶስት ተማሪ ሆነው ቤት ተከራይተው ነው የሚኖሩት ። በዛ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ብቻዬን ዶርም ጋደም ብያለሁ ። #03 ሰዓት ላይ የኛ block አካባቢ ቅልጥ ያለ ጩኸት ሰምቼ በፍጥነት ከአልጋዬ ላይ ተነሳሁና በሁለተኛው በር በኩል የሚሆነውን ማየት ጀመርኩኝ ። አንድ የፋሲል መለያ የለበሰ ልጅ ከአምስት በላይ በሚሆኑ ልጆች እየተደበደበ ፣ እየጮኸ ፣ በስተመጨረሻ እንደምንም አምልጧቸው ወደ ዶርም ኡኡኡ እያለ ሮጦ ገባ ። ደብዳቢዎቹ የ turk ልጆችም ወደ ዶርማቸው ተመልሰው ገቡ ። እኔም ወደ አልጋዬ ተመልሼ በልቤ 'ወይ ዘንድሮ' እያልኩኝ ተኛሁ ። ከደቂቃዎች በዋላ ግን የቅድሙ ጩኸት በእጥፍ ጨምሮ ቅልጥልጥ ያለ ኡኡታ ይሰማኝ ጀመር ። የአንድ ሰው ድምፅ ሳይሆን የብዙ ሰዎች እሪታ ነው ። እንደ ቅድሙ ማየቱን ተያያዝኩኝ ። ለካ የቅድሙን ልጅ መመታት ሰምተው Wolfsburg'ኦቹ ከዋና በር ተጠራርተው በጀማ ሆነው ጊቢ ገብተው turk'ኦቹን በየዶርሙ እየገቡ መሸክሸክ ጀምረዋል ። ጥቁር ልብስ ለብሰው ፣ በእጃቸው ላይ ደግሞ ለምልክት ቀይ ጨርቅ አስረው ነበር የመጡት ። ጩኸቱና ኡኡታው ለደቂቃዎች ቀጥሎ በስተመጨረሻ turk'ኦቹ የድረሱልን ድምፅ እያሰሙ ከየዶርሙ መሰባሰብ ጀመሩና ጊቢውን ሞሉት ። ወዲያውኑ ግን federal ከዚህ በፊት ሰምቼው የማላውቀውን የጥይት ድምፅ አከታትሎ ወደላይ ተኩሶ ካለሁበት አነጠረኝ ። ሁሉም ተበታትነው ወደየ ዶርማቸው በሩጫ ገሰገሱ ። ይሄን ሁሉ ብቻዬን ዶርም ውስጥ ሆኜ በሁለተኛው የዶርሙ በር መስታወት ስከታተል ነበር ። ጠዋት ነግቶ አብዛኛው ተማሪ class የሚጀመር መስሎዋቸው ወደ ጊቢ ተመልሰው ነበር ። ግን አሁንም በማታው ረብሻ ምክንያት ትምህርት ሊጀመር አልቻለም ። ምሳ ሰዓት ደርሶ ልንበላ ከጊቢ ልንወጣ ስንል ሶስቱም የጊቢው በሮች ተዘግተው ጠበቁን ። መግባት እንጂ መውጣት አይቻልም ። ተማሪ አንዴ ከጊቢ ከወጣ እንደ ማይመለስላቸው ስላወቁ ነው በሮቹን የዘጉት ። አብዛኛው ተማሪ ፍቅር cafe ተሰብስበው የበሮቹን መከፈት በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል ። እያስፈራሩን ነው መሠለኝ ፌደራሎቹ patrol መኪና ላይ ሆነው ጊቢውን እያሰሱት ነው ። ምሳ ሰዓት አልፎ ተማሪ በጠኔ ተመቶ ፌንት ሊሰራ ሲል ልክ #09 ሰዓት ላይ የጊቢው የተማሪዎች president መጥቶ ሰበሰበንና በዛው ሄደንባቸው እንዳንቀር ID card አስይዘን እንድንወጣ አሰፈቅዶልን ፣ በዛው ወጥቶ የሚቀር ተማሪ ላይ ግን እርምጃ እንደሚወሰድ ነገረን ። በጣም እርቦን ስለነበር መታወቂያችንን ፊታቸው ላይ ወርውረን ከጊቢ ወጣን ። (ፊታቸው ላይ ወርውረን የምትለዋ ሳክስ ናት ...🙆) ። ምሳ በልተን ወንጀለኛ ላለመባል ወደ ጊቢ ተመልሰን ID card ወስደን የህንድ ፊልም ለመስራት ከ #20 ተማሪዎች ጋር strategy መንደፍ ጀመርን ። ጊቢ ውስጥ መቆየቱ ለኛ በጣም መጥፎ ሊሆን ስለሚችል በአጥር ለመውጣት set up አዘጋጅተን እቅዱን አሳክተን ተደብቀን በአጥር ዘለን ወጣን ። የስራ ባልደረቦቼን አመስግኜ ጉዞዬን ወደ ከንቲባው ልጅ ቤት አደረኩኝ ✎ ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ይ................ ቀ.................. ጥ................... ላ.................... ል.................... ┈┈••◉❖◉●••┈🌹✿🌹 https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0 ┈┈••◉❖◉●••┈ ❣ :¨·.·¨: ❣SHARE ❣ :¨·.·¨: ❣ 💞 ጌዶኦኦኦኦኦኦኦ 💞
Show all...
Gedooooo Shooting ,,,,,,,,photo store

* ፎቶችን ማስራት የምትፈልጉ # 0987172734/ @yane_yabechaye በውስጥ መስመር ማነጋገር ትችላላቹ Be adobe light Rome # ሀሳብ እና አስታየት ካሎት / @yane_yabechaye መናገር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0

​💐የከንቲባው ልጅ💐 🔥ክፍል 26 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ሽጉጡን አስቀመጡና ወደኔ ቀርበው እጄንና እግሬን ፈተው ወንበር አመጡና ፊትለፊቴ ተቀመጡ ። ​​እኔ በሁኔታው ስለ ተገረምኩኝ ምን ማለት እንዳለብኝ እራሱ ጠፍቶኝ ዝም ብዬ ተቀምጫለሁ ። እሳቸውም ትንሽ እንደ ማሰብ አረጉና "እየውልህ" ብለው ማውራት ጀመሩ።"እየውልህ በመጀመሪያ ምናልባት ካላወከኝ እኔ የህይወት አባት ነኝ።በዚህች ምድር ላይ ያለችኝ ብቸኛዋ ልጄና ሁሉ ነገሬ ናት።የሷ ነገር ከማንም እና ከምንም ነገር በላይ ስለሚያስጨንቀኝ ነው አንተ ላይ እንደዚህ ያደረኩት" ሲሉኝ 'ቆይ ፡ የእርሶ ለሷ መጨነቅ እና እኔን እንደዚህ ማድረግ ምን ያገናኘዋል ...?' አልኳቸው ። ቀጥለው "ሲመስለኝ ህይወት ስለራሷ ብዙ ነገር ነግራሃለች ። ከአራት ዓመት በፊት በተፈጠረ አደጋ ምክንያት ከቤት ወጥታ አታውቅም ። እኔ ደግሞ በስራዬ ምክንያት በየቀኑና በየሰዓቱ ከሷ ጋር መሆን ስለማልችል ደህንነቷን ለማረጋገጥ ብዬ በቤቱና በጊቢው ውስጥ security camera እና ድምፅ መቅጃ መሳሪያ ገጥሜ ነበር ። በዚህም መሳሪያ ለተከታታይ አራት ዓመታት ሁሌም የማየው እና የምሰማው ነገር ተመሳሳይ ነበር ። ታነባለች ፣ ትተኛለች ፣ ትንሽ ትበላለች ፣ ፊልም ታያለች ፣ በጊታር ትዘፍናለች ፣ ታለቅሳለች ፣ ትፅፋለች ። ነገር ግን በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ከኔ በስተቀር አንድም ሰው እቤት እሷጋ የሚመጣ ሰው አልነበረም ። ሁሌም የምታደርጋቸው ነገሮች ተመሳሳይ ከመሆናቸው የተነሳ ፣ በዛላይም በየ ሰዓቱ ስለምንደዋወል check ማድረግ እራሱ አቁሜ ነበር ። ነገር ግን ከሳምንታት በፊት አሜሪካ ሄጄ ስመለስ ጠረጴዛ ላይ የወንድ ልጅ የእጅ ሰዓት እና የአንገት ሀብል ተቀምጦ አየሁኝ ። (ስልክ ተደውሎላት ፡ አባቢ በር ላይ ነኝ ብሎኛል ብላኝ በጓሮ በኩል የደበቀችኝ ቀን እንደሆነ ትዝ አለኝ ። ከዛ ቀን በፊት ሶፋ ላይ ስተኛ አውልቄያቸው እዛው እንደረሳዋቸው ትዝ አለኝ) ። አባቷ ማውራታቸውን ቀጥለዋል ። "በሁኔታው ብደናገጥም እሷ እንዳታውቅብኝ ብዬ ሳምንት እመለሳለሁ አልኳትና ተሰናብቻት ወጣሁ ። በዛ ጊዜ እቅዴ የነበረው ወደ ውጪ ይዣት ለመሄድ የመጨረሻውን process ለማስፈጸም ነበር ። ግን ጠረጴዛው ላይ ያገኘሁት ነገሮች ስለረበሹኝ ወደ ውጪ መሄዱን ትቼ ወደ ቢሮዬ በረርኩኝ ። እቤት ውስጥ የሚፈጠረውን ነገር እየቀዳ የሚያሳየኝን screen ከፍቼ ከሳምንት በፊት እስከ ዛሬ የተቀዳውን ማየት ጀመርኩኝ ። ትኩረቴን የሳበው ግን ከሚያዝያ #30 ፡ ጀምሮ ያለው ነበር ። ህይወቴ በመኪና ከጊቢ ስትወጣ ያሳያል ። ከሰዓታት በዋላ ደግሞ ይበልጡኑ ትኩረቴን መሳብ ቀጠለ ። መኪናውን ይዛ ከወንድ ጋር ተመለሰች ። እኔ ሳላውቅ የኔ ልጅ ከአራት ዓመት በዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤት ወጥታ ከማላውቀው ሰው ጋር ተመለሰች ። ልጁም አንተ ነበርክ ። ስታወሩ የነበረውን ሁሉ አዳመጥኩኝ ። በንጋታው ምሽት እኔ መጣሁ ። በቀጣዩ ቀን ወደ ጊቢ ልመለስ ብለሃት ሄድክና ከሰዓታት በዋላ ተመልሰህ መጣህ ። ከዛን ወደ ደብረ ዘይት ለመሄድ አቅዳችሁ በንጋታው ከቤቱ ለቃችሁ ወጣችሁ ። እኔም ልክ እንደወጣችሁ ወደ ቤት ገባሁና እንዳልታወቅ ሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሼ ፣ መብራት ሳላጠፋ ከቤት ወጣሁኝ ። አዲስ አበባ ፣ ደብረዘይት ፣ በሄዳችሁበት ሁሉ ተከትያችሁ በስተመጨረሻም ኩሪፍቱን በጠዋት ለቃችሁ እንደወጣችሁ አወኩና እኔም ተመለስኩኝ" ብለው በረጅሙ ተነፈሱ ። የህይወት አባት ሳያቋርጡ ሁሉን ነገር ለኔ መተረካቸውን ቀጥለዋል ። "ከደብረ ዘይት ስትመለሱ የቤቱ መብራቶች በርተው ስለጠበቋችሁ መረበሻችሁን በ security camera'ው አይቻለሁ ። ግን እኔ ነበርኩ ሳላጠፋ ረስቼ የወጣሁት ። በዛም ምክንያት የኔን ልጅ በችግሮቿ ቀን እንዳልተለየሀት አየሁኝ ። ልጄ ሁሉን ነገር እንደማውቅ እንዳታውቅብኝ ብዬ ባልኳት ቀን መሠረት ሀሙስ ከአሜሪካ የመጣሁ አስመስዬ ቤት ገባሁ ። ወደ ቤት ስመለስ እንኳን አንተ እቤት ውስጥ እንደነበርክ አውቅ ነበር ። ግን ሁሉን ነገር ከልጄ መስማት ስለፈለኩኝ ምንም አይነት ጥያቄ አላነሳሁባትም ። እሷ ግን እንኳን ልትነግረኝ ቀርቶ ጭራሽ ደበቀችህ ። ምስጥረኛዬ ፣ ሁሉ ነገሬ ፣ ህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኔ ከአባቷ ምስጢር ደበቀች ። ቢሆንም ግን አልተቀየምኳትም ። ሁሉም ነገር የኔ ጥፋት ነው ። እንዳንተ ሙሉ ጊዜዬን ፣ ሁሉ ነገሬን አልሰጠዋትም ። የኔ ልጅ ከኔ ለመደበቅ የፈለገችው ለክፋት አይደለም ። ምናልባት እኔ ካወኩኝ ካንተ ጋር የምትለያይ መስሏት ወይንም ደግሞ ፈርታኝም ሊሆን ይችላል ። ሴቶች ካፈቀሩ ምስጥረኛዬ ከሚሉት ሰው ጭምር ምስጢር መደበቅ ይጀምራሉ ። ይህ ደግሞ ምናልባት የወደዱት ሰው ላይ የሆነ ነገር እንዳይደርስ ከማሰብ የመነጨ ተፈጥሯዊ ቅድመ ጥንቃቄያቸው ይሆናል ። ባለፈው አርብ ጠዋት እንኳን ሙዚቃ እንደዛ አስጩሀ ከፍታ አንተን በዘዴ ከቤት እንዳስወጣችህ አውቃለሁ ። ይሄን ሁሉ እያየሁ ግን ዝም ያልኩት በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው ። አንደኛው ልጄን ከማንም በላይ ስለምወዳትና ከኔ የሚጠበቅብኝን ነገር ስላላደረኩላት ስሜቷን መጉዳት ስላልፈለኩ ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ያንተ ጥሩና መልካም ፀባይ ነው ። እኔ ይሄን ያክል ቀርቤያት ፍቅር ስሰጣት ፣ ስጨነቅላት እና ስንከባከባት ትዝ አይለኝም" ብለው በትካዜ ተውጠው ዝም አሉ ። ከዛን እኔም 'እሺ ፡ የሆነው ሁሉ ይሁን ፤ ግን የዛሬው ድርጊታችሁ ምንም አልገባኝም' አልኳቸውና መልስ ሊሰጡኝ ተዘጋጁ ። "ምን መሰለህ ፡ የህይወቴ ፀባይ ሀሙስ ወደ ቤት ከተመለስኩ በዋላ ሙሉ በሙሉ ተቀየረብኝ ። በተለይ በቅርቡ ወደ አሜሪካ እንሄዳለን ካልኳት በዋላ ከኔጋር ማውራት እራሱ አቁማለች ። ትካዜ ታበዛለች ፣ እየዘፈነች ታለቅሳለች ፣ ለብዙ ሰዓታት በሯን ዘግታ ብቻዋን ትሆናለች ። ቃል አውጥታ ባትነግረኝም ሁኔታዋ ሁሉ ከዚህ ሀገር ለቃ መሄድ እንደማትፈልግ ነው ። ምክንያቷ ደግሞ አንድና አንድ ብቻ ነው ። እሱም አንተ ነህ ። ወይ ካንተ ጋር ሀገር ለቆ መሰደድ ወይም ደግሞ እዚሁ ካንተ ጋር ሆና ሞቷን እንደምትመርጥ አውቃለሁ ። እኔ ደግሞ ልጄን እዚሁ ትቻት እንድትሞት መቼም አልፈቅድም ። ለዚህ ነበር አንተን ይዤ እሷን እንድትከዳትና ለሞት አሳልፈህ እንድትሰጣት መንገድ ያመቻቸውልክ ። ሞትን ወይንም እስር ቤትን ፈርተህ የምትሸጣት መስሎኝ ነበር ። እዚህ እያወራን ያለነው በሙሉ በድምፅ እየተቀዳ ነው አና ሞትን ፈርተህ እሷን እኔ ወዳልኩህበት ቦታ አመጣታለሁ ብትል ኖሮ ይሄንን ድምፅ መቅጃ ይዤ ሄጄ እሷም ባንተ ተስፋ ቆርጣ ትሄድልኝ ነበር ። አሁን ግን ነገሩ ጭራሹኑ አየከረረ መጣብኝ ። እንሂድ ብላት እምቢ እንደማትለኝ አውቃለሁ ። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና ብትሄድ በጣም ትጎዳብኛለች ። ከዚህ በፊት ብቻዋን ለአራት ተከታታይ ዓመታት ያሳለፈችው አስቀያሚ ህይወት እራሱ ይበቃታል" አሉኝ በጣሙን እያዘኑ ✎ ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ይ................ ቀ.................. ጥ................... ላ.................... ል.................... ┈┈••◉❖◉●••┈🌹✿🌹 https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0 ┈┈••◉❖◉●••┈ ❣ :¨·.·¨: ❣SHARE ❣ :¨·.·¨: ❣ 💞 ጌዶኦኦኦኦኦኦኦ💞
Show all...
Gedooooo Shooting ,,,,,,,,photo store

* ፎቶችን ማስራት የምትፈልጉ # 0987172734/ @yane_yabechaye በውስጥ መስመር ማነጋገር ትችላላቹ Be adobe light Rome # ሀሳብ እና አስታየት ካሎት / @yane_yabechaye መናገር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0

​🌺የከንቲባው ልጅ🌺 🔥ክፍል 25 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . Notice : በትላንትናው ክፍል ላይ ማለትም ክፍል 25 ላይ የመጨረሻዎቹ አከባቢዎች ተስፋዬ እንደታገተ ህይወት ከዲያሪዋ የነገረችው ትዝ እንዳለው ገልጾልን ነበር ያለቀው! ስለሆነም ተስፋዬ ትዝ ያለውን ዲያሪ ከራሷ በህይወት አንደበት በሪከርድ ድምጽ ቀርቦላችሁዋል..ከስር ከዚህ ክፍል ጋር ዲያሪውን በድምፃ አታች ስላረግንላችሁ አዳምጡት የታሪኩ አንድ አካል ነውና!🔥 . . በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሽጉጥ ተደቅኖብኝ እየተዛተብኝ ነው።ከዚህ ለማምለጥ ደግሞ ሰውዬው የሚለኝን ነገር ማድረግ የግድ ነው ። 'እሺ ምንድነው እንዳደርግልህ የምትፈልገው ...?' አልኩት በብስጭት ። "አንድ ነገር ብቻ ነው የማዝህ ፣ እሱም የከንቲባውን ልጅ እኔ ወደ ምልህ ቦታ ይዘሀት ትመጣለህ ። ከዛን ልጅቷን በሰላም ተረካክበን ፣ አንተ ደግሞ በምላሹ ወደ ጫካ ስትገባ የተቀረፅከውን ፣ እንዲሁም የእጅ ሰዓትህና የአንገት ሀብልህን ከነ ህይወትህ ይዘሀቸው ትመለሳለህ ። አለቀ ፤ በቃ ይኸው ነው" አለኝ ቀለል አድርጎ ። የመጀመሪያ ቀን ከህይወት ጋር ስንገናኝ "የከንቲባ ልጅ ነኝ" ብላኝ ስትተዋወቀኝ ያን ቀን በልቤ ለራሴ 'በቃ ተስፍሼ ቁርጥህን አወቅ ፡ ነገ ወይ ከርቸሌ ፡ ወይም ደግሞ ሲኦል ትገባታለህ' ያልኩት ትዝ አለኝ ። 'ቆይ ግን ከሷ ምንድነው የምትፈልገው ...?' ስለው "እሱ ያንተ ጉዳይ አይደለም" አለኝ በሽጉጡ ግንባሬን እየተጫነኝ ። ባይታየኝም ወደላይ ቀና ብዬ እያየሁት 'ቆይ አንተ ማነህ ፡ ለምንስ ነው እንደዚህ የምታደርገው...?' አልኩት በልመና አይነት ድምፅ ። "እኔ ማለት የናንተ ጥቁር ጠባቂ መላክ ነኝ ። በሄዳችሁበት ሁሉ አለው ። ደብረዘይት ብትል ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ብትል ፣ ሌላው ይቅር ፣ የከንቲባውን ልጅ ቤት መብራት ማጥፋትና ማብራት እንኳን የኔ ስራ ነው" ሲለኝ ሙሉ ነገር ጭልምልም አለብኝ ። ከዚህ በፊት ሲከታተለን የነበረውና በፍርሃት ስንጠብቀው የነበረው ሰውዬ እንደሆነ ተረዳሁ ። ግን ጥያቄ የሆነብኝ ነገር ነበር ። ህይወትን ከሆነ የሚፈለገው ፡ ለምን ከዚህ በፊት ያገኛቸውን አጋጣሚዎች እንዳልተጠቀመ ጠየኩት ። እሱም "ደብረዘይት ፡ ኩሪፍቱ ሪዞርት ውስጥ ሁሉ ነገር አልመች አለኝ ። ከዛ ስትወጡ ልይዛት አቅጄ ነበር ። ግን እኔ ባላሰብኩበት ቀን ከዛ ለቃችሁ ወጣችሁ ። እዚህ ደግሞ እንዳልይዛት ልጅቷ ከቤት አትወጣም" ። ሲለኝ 'ታድያ ምን ይሳንሀል ፣ መብራቶቹን ያበራኻቸው በፀሎት ነው እንዴ ፣ ልክ ገብተህ እንዳበራኻቸው ልጅቷንም ገብተህ መውሰድ እኮ ትችላለህ' አልኩት ። እሱ ግን ይበልጡኑ በሽጉጡ እየተጫነኝ "ስማ አንተ ወጠጤ ፡ እዚህ ያመጣውክ እንድትመክረኝ አይደለም ። ለመጨረሻ ጊዜ ደግሜ እጠይቅሃለሁ ። ልጅቷን እኔ ወደ ምልህ ቦታ ይዘሀት ትመጣለህ ወይስ እዚሁ ግንባርህን ለሁለት ልክፈልልህ...?" አለኝ እየደነፋብኝ ። በጣም ጨንቆኛል ፤ እሱ ባይተኩስብኝም ጭንቅላቴ አሁን እራሱ ለሁለት ክፍል ብሏል ። አንደኛው 'ተው ተስፋዬ ለማታውቃት ልጅማ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋዕትነት መክፈል የለብህም ። ባይሆን ላንተ ሲሉ ቀን ከሌሊት የሚለፉ ቤተሰቦችህን አስባቸው ። ደግሞስ እሷ የከንቲባ ልጅ እንጂ ማራኪክ አይደለች' ይለኛል ። ሁለተኛው ደግሞ 'አይዞህ ፡ በርታ በል ፡ ይሄ የህይወት ፣ የህሊናና የሰውነት ጉዳይ ነው ። ልጅቷ ፡ እህትህ ፣ ፍቅረኛህ ፣ እናትህ ወይንም ደግሞ ወደፊት የምትኖርህ ሴት ልጅህ እንደሆነች አስብና የሰውዬውን ጥያቄ ውድቅ አድርግ' ይለኛል ። ሰውዬው በሀይል "አንተን እኮ ነው የማወራው" ብሎኝ ከሀሳቤ አነቃኝ ። ትዕግሥት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም ። ቀጠለና #10 second እሰጥሃለሁ ። ካንተ መስማት የምፈልገው 'እሺ' የሚለውን ቃል ብቻ ነው አለኝና መቁጠር ጀመረ ። #10 ፣ #09 ፣ #08 ፣ #07 ፣ #06 ፣ #5 አለና #4 ላይ ሲደርስ ሽጉጡን አቀባብሎ መቁጠሩን ቀጠለ ፣ #03 ፣ #2 ፣ #1 ... 'እሺእእእ ...' አልኩት ቅልጥ ባለ ድምፅ ። የሱ አንድ እና የኔ እሺ ማለት እኩል ከአፋችን ሲወጣ የሽጉጥ ድምፅ ሳይሆን "አንድ ሺ" የሚል ቃል ነበር የተሰማኝ ። በእጆቹ እያጨበጨበ "ጎበዝ ልጅ ፤ ጥሩ ምርጫ ነው" አለኝ የፌዝ ይሁን የደስታ የማላውቀው የሳቅ አይነት እየሳቀ ። ቀጠልኩና 'እሺ ለምን እንዳልኩህ ግን ገብቶሃል ...? ሳታስጨርሰኝ ነው እኮ ማጨብጨብ የጀመርከው' ስለው "ያልኩህን ለመፈፀም ነዋ ፣ ሌላ ለምን ሊሆን ይችላል...?" አለኝ ። እኔም 'አይደለም ፡ አላስጨርስ አልከኝ እንጂ ልልህ የፈለኩት እኮ ፡ እሺ ከምትገለኝ ምናለበት እስር ቤት እንድገባ እንኳን ብትፈቅድልኝ ለማለት ነበር' አልኩት የማላገጥ ሳቅ እየሳኩበት ወኔዬ ከየት እንደመጣ ሳላውቅ ። ወዲያው መልስ ምት ነው መሰለኝ አይቼውም ቀምሼውም የማላውቀውን ጥፊ ድርግም ሲያደርግብኝ ለአስር ሴኮንድ ምድር ጨለመችብኝ ። ቀጥሎም አንገቴን አንቆኝ "ቆይ ማነኝ ነው የምትለው ...? ለልጅቷስ ይሄን ያክል እራስህን ለሞት አሳልፈህ የምትሰጠውስ ለምንድነው ? ልጅቷ ምንህ ነች .?" አለኝ ሀይል በተቀላቀለበት ድምፅ 'ስሟን አታውቅም እንዴ ? ህይወቴ ናት እኮ' አልኩት እንደ ማይገለኝ ስለታወቀኝ ደፋር ሆኜበት የሚለኝን እሺ ካላልኩት የሚገድለኝ ቢሆን ኖሮ መጀመሪያውኑ ወደ ጫካው ስገባ Video መቅረፅ አይጠበቅበትም ነበር video ሊቀርፀኝ የፈለገበት ምክንያትም እሺ ካላልኩት ለማስፈራሪያነት ሊጠቀምበት አስቦ እንደሆነ ግልፅ ነው ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሚገድለኝም ከሆነ ግን የጀግና ሞት ልሙት ብዬ እንጂ ለመሞት ዝግጁ ሆኜ እንኳን አይደለም በዚች ምድር ላይ የምንሞትለት ሰው ከሌለ የምንኖርለትም ሰው አይኖርም አለውልሽ የሚለው ቃል ትርጉም የሚያገኘው ስትሞትላትም ጭምር ብቻ ነው በአፍ ብቻ አለውልሽ ከጎንሽ ነኝ ፣ ምንጥሴ ቅብጥርሴ ማለት እራስን ማታለል ነው ለሰው ልጆች ሁሉ መኖር ብቻ ሳይሆን መሞትንም ጭምር ከክርስቶስ ተምሬያለሁ እየሰቀሉት እንኳን "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" እያለ ለገዳዮቹ ይፀልይ ነበር እኔ ደግሞ እንደ እርሱ ለጠላቶቼ ጭምር የምሞትበት አቅም ባይኖረኝ እንኳ ፤ ብያንስ ለወዳጆቼ መሞት አይከብደኝም ህይወት ደግሞ ለኔ ከወዳጅም በላይ ናት አይኖቿ እንዴት በስስት እንደሚያዩኝ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ወደ ጊቢ ለመመለስ ከቤታቸው ስወጣ እንኳን ፀሀይ የሚመስለው ፊቷ በአንዴ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ይሆናል እርግጠኛ ነኝ በኔ ቦታ ብትሆን ሳታንገራግር ህይወቷን ትሰጠኛለች በዚህም በዚያም ግን እኔ ለሰዎች መሞትን እንጂ ሰዎች እንዲሞቱልኝ አልፈልግም ከጥቂት ደቂቃ በዋላ የቤቱ መብራት ሲበራ አይኖቼ ሰውዬው ላይ ፈጠው ቀሩ ፊቱ አዲስ አልሆነብኝም አይኖቼን ጨፍኜ ለማስታወስ ሞከርኩ አይምሮዬ ይህ የህይወት አባት አይደሉም እንዴ ? ይለኛል አይኖቼን ገልጬ ድጋሜ ትኩር ብዬ ተመለከትኩት አዎ ልክ ነኝ ፤ እራሳቸው ከንቲባው ናቸው ሀሙስ ምሽት እነ ህይወት ቤት ግንባሯን ስሟት ወይናቸውን ይዘው ወደ መኝታ ክፍላቸው ሲሄዱ በትንሹም ቢሆን ፊታቸውን አይቼ ነበር ታድያ ምን እየተካሄደ ነው ? ምንስ ለማድረግ እየሞከሩ ነው ? ✎ ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ይቀጥላል..... ┈┈••◉❖◉●••┈🌹✿🌹 https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0 ┈┈••◉❖◉●••┈ ❣ :¨·.·¨: ❣SHARE ❣ :¨·.·¨: ❣
Show all...
Gedooooo Shooting ,,,,,,,,photo store

* ፎቶችን ማስራት የምትፈልጉ # 0987172734/ @yane_yabechaye በውስጥ መስመር ማነጋገር ትችላላቹ Be adobe light Rome # ሀሳብ እና አስታየት ካሎት / @yane_yabechaye መናገር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0

​💐የከንቲባው ልጅ💐 🔥ክፍል 24 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ድሬዳዋ ግን UNESCO ላይ አልተመዘገበችም ...? ማለቴ ባላት በቂና አስተማማኝ የአዋራ ክምችት መመዝገብ ያለባት ይመስለኛል ። (#10 09 2011) ከእንቅልፋችን ስንነቃ ያየነውን ግን እንኳን ዩኔስኮ ፡ ቅዱስ ገብርኤል እራሱ በህይወት መፃፍ ላይ ይከትበዋል ። (የከተሜ ልጆች ፡ ይከትበዋል የምትለዋ ቃል ደግሞ ክትባት እንዳት መስላችሁ ...) ። ተቀርፆ አለም ሁሉ በቲቪ ቢያየው ደስ ይለኝ ነበር ። anyways እኛ በስልክም ቢሆን ቀርፀናል ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፈጥሮ ሲቀየር አየሁ ። አዋራ እንደ ጉም ሙሉ ድሬዳዋን ሲሸፍናት ሳሉት ። እንኳን ሰውን ከሰው ለመለየት ይቅርና ፤ አንተ እራሱ የት እንዳለህ አታውቅም ። ብቻ ወደ ውስጥ እራሱ የምናስገባው oxygen ሳይሆን ክሽን ያለች ንፁህ አዋራ'gen ነው ። (ቅቤ አለው እንዴ ይሄ ነገር ...?) ። ወደ ውጪ ደግሞ በ carbondioxide ፋንታ የምናወጣው አፈር'dioxide ነው ። (እዚጋ chemistry ሲፎርፍ የነበረ ተማሪ ምን እያወራሁ እንደሆነ አይገባውም ...) ። በጠራራ ፀሀይ ድሬዳዋ ከተማ ሙሉ በሙሉ ጨለመች ። የመንገድ ዳር መብራቶች እራሱ ሶላር ናቸውና ሲመሽ በራሳቸው system ነው የሚበሩት ። ዛሬ ግን በቀን የጨለመ መስሏቸው ሲበሩ ውለዋል ። ምሳ ከጓደኞቼ ጋር በልቼ ወደ bank ቤት አመራሁ ። እቅዴ ባንክ ውስጥ ያለኝን ሙሉ capital ማውጣት ነው ። (ይቅርታ small ለማለት ነው...) ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ ሁሌም የማሰለፉበት ባንክ ደረስኩኝና ሰልፉን ተቀላቀልኩ ። የባንክ ቤቱ ጊቢ ባዶ ኪሳቸውን ባሉና ሙሉ ፌስታል ብር በያዙ ሰዎች ተሞልቷል ። ባዶውን የመጣ ኪሱን ሞልቶ ይሄዳል ። ፌስታል ሙሉ ብር ይዞ የመጣ ደግሞ ባዶ ኪሱ ውስጥ ፌስታሉን አስቀምጦ ይመለሳል ። ይሄ ነው እንግዲህ ቁጠባና ቁንጠራ ማለት ። ያለው ሲቆጥብ የሌለው ይቆነጥራል ። ተራዬ ደርሶ ባለፈው የገባልኝን cost #450 ብር አውጥቼ ቀሪውን ብር ሳይ ልቤ በሀሴት ተሞላች ። የማታሳፍር ንፁህ የኢትዮጵያ #27.50 ዶላር አለችኝ ። ቀጣይ ወር ስመጣ ወልዳልኝ #28 ብር እንደ ምትሆንልኝ ተስፋ አለኝ ። ይቺም ብር ሆና ይዣት ወደ አሸዋ አቀናሁ ። (ማነሽ ድሬዳዋን የማታውቂዋ ፡ አሸዋ ደግሞ የሰፈር ስም እንጂ ድንጋይ አይደለም ...) ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ባዶ ሆኖ ካገኛችሁት ብዙም አትደንግጡ ። ምክንያቱም አዳሜና ሄዋኔ የወር አስቤዛዋን ለመሸመት እዚህ አሸዋ ውስጥ ናቸውና ። ተማሪ ፣ አስተማሪ ፣ ነዋሪ ፣ ዘዋሪ እንዳለ ከዚህ ነው የሚሸምቱት ። ኧረ ባለፈው ዘፋኙ Sancho (ታናሞ ካሻሞ ...) እዚህ መጥቶ ለ clip የሚሆኑትን ጫማዎች ገዝቶ ሄዷል አሉ ። ደግሞ ለራሱ ብቻ አይደለም ። ለኔ ጊልዶ እና ያሬዶ ጭምር ይዞ ሄዷል ይባላል ። (አሉባልታ አይደለም ደግሞ ፤ አሉ ብሎ የነገረኝን ልጅ አምነዋለሁ ...) ። brand ጫማ ፣ ልብስ ፣ electronics ፣ ወዘተ እዚህ በርካሽ ዋጋ ይገኛል ። (ኧረ ጀለሴ ፡ ማስታወቂያ ውስጥ ገባሽ እኮ ...። አይኔን ጨፍኜ cost ላይ #250 dollar ጨምሬ vans ጫማ ገዛሁ ። ምሽት ላይ እራት ከጓደኞቼ ጋር በልተን ወደ ዶርም ተመልሰን telegram ገብቼ ከህይወት ጋር ማውራት ጀመርን ከኔ ጋር የምታወራቸው እያንዳንዷ ቃላት ሀይል አላቸው የዋህነቷ ፍቅሯ ፣ ድምጿ ፣ ሁሉ ነገሯ ከአቅሜ በላይ ናቸው ። ደግሞ ነገ አባቷ የሆነ ቦታ እሄዳለው ስላሏት እቤታቸው መምጣት እንደ ምችል ነግራኛለች "ና ናፍቆኛል ትያለሽ አሉ ፡ የኔንም ላንቺ ባወሩ ፣ ካንቺ ብቻ ሰምተው መጡ ፡ ሳይነግሩሽ የኔን በቅጡ ።ሊመሻሽ ሲል #11 ሰዓት አካባቢ ከህይወት "አባዬ ወቷል መምጣት ትችላለህ" የሚል txt ገባልኝ ደቂቃ ሳላባክን ከዶርም ተነስቼ ፣ በቶኒ በር ወጥቼ ሰፈራቸው አካባቢ ደረስኩኝ ። ወደ ቤታቸው በር ቀርቤ ላንኳኳ ስል መሬት ላይ ፖስታ አገኘሁ ማንኳኳቱን ትቼ እሱን አነሳሁትና ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩኝ "የፃፍኩልህን አቅጣጫ ተከትለህ ና አታስጠብቀኝ እሺ የኔ ጌታ" ይላል ህይወት እንደሆነች ተረዳሁና ሰፈሩን አንድ ጊዜ ዞር ዞር ብዬ ከቃኘሁ በዋላ በፃፈችልኝ GPS መሠረት መጓዝ ጀመርኩኝ ቤታቸው የተሰራው ወደ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ፡ ከቤታቸው በታችኛው በኩል ትንሽዬ ጫካ መሳይ በዛፎች የተሸፈነ ቦታ አለ አቅጣጫውን ስከተል በስተመጨረሻ ጫካው ውስጥ እራሴን አገኘሁ ፀጥታው ድምፅ አውጥቶ ጆሮዬ ላይ መጮህ ጀመረ ልቤ ከልክ በላይ ይመታል እየመሸም ስለሆነ በጣም ያስፈራል ወዲያው የኮሽታ ድምፅ ከጫካው ውስጥ ይሰማኝ ጀመር የረገፉ የዛፎች ቅጠል በእግር ሲረገጡ የሚፈጠረው ድምፅ ከደቂቃ ወደ ደቂቃ በደንብ ይሰማኝ ጀመር ስለመሸ ብዙ ነገሩ በደንብ አይታይም ኮሽታው በጀርባዬ በኩል እንደሆነ ተረዳሁና ድምፁን ወደ ሰማሁበት አቅጣጫ ስዞር ጭንቅላቴን ምን እንደሆነ የማላውቅ ነገር በሀይል መታኝና ተዘረርኩኝ ለስንት ደቂቃ ወይንም ሰዓት እራሴን እንደሳትኩ አላውቅም ግን እራሴን ጨለማ ክፍል ውስጥ ወንበር ላይ ተቀምጬ ፣ እግሮቼና እጆቼ ወደዋላ ታስረው ነው ያገኘሁት ሳላስበው ፊቴ ላይ የእጅ battery ብልጭ አለብኝና አይኔን አቃጥሎኝ ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ ብልጭ የሚሉ የተለያዩ የመብራት ቀለሞች ይመላለሱ ጀመር ከላይ እስከ ታች በያዘው ባትሪ scan አደረገኝ ወይ ቤቱ ስለጨለመ ይሁን ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሷል መሠለኝ በደንብ አይታይም ባትሪውን እንዳበራብኝ በቀኝ እጁ ግንባሬ ላይ ሽጉጥ ደቀነብኝ አይኔ ላይ ስላበራው ማን እንደሆነ እንኳን አይታወቅም ። ወፈር ባለና በሚያስፈራ ድምፅ "በዚህ ዕድሜ ፡ መሞት ትፈልጋለህ ?" አለኝ አልፈልግም' ስለው "መኖር የምትፈልግ ከሆነ የምልህን ነገር ማድረግ ይኖርብሃል" አለኝ ። ፈራ ተባ እያልኩ 'ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልገው ?' አልኩት እሱም "ህይወትህን የምትፈልግ ከሆነ የማዝህ ነገር በጣም ቀላል ነው" ሲለኝ 'የምትለኝን ባላደርግስ...?' አልኩት በንዴት ። እሱም "ወይ እዚሁ ግንባርህን ብዬክ ፤ ወይም ደግሞ እስር ቤት ለዘላለም እንድትማቅቅ አደርግሃለሁ" አለኝ የእስር ቤቱ ገርሞኝ 'እንዴት አርገህ ነው ደግሞ እስር ቤት የምታስገባኝ ?' አልኩት የስላቅ ሳቅ እየሳኩኝ ። እሱም እየተሳለቀብኝ "እረሳህ እንዴ ደፍረህ የገደልካትን ልጅ" ሲለኝ ደንግጬ 'የምን ልጅ አልኩት ?' እሱም "አቅጣጫውን ተከትለህ ወደ ጫካው ስትገባ ከዋላህ ሆኜ በካሜራ ሳነሳህና ስቀርፅህ ነበር ። ጫካው ውስጥ ደግሞ የሆነች ልጅን እራሴው ደፍሬ ገድያታለሁ ለማስረጃ ደግሞ የእጅ ሰዓትህንና የአንገት ሀብልህን ቦታው ላይ አስቀምጫለሁ ። ስለዚህ አሁን የምልህን ነገር ካላደረክ በአንድ የስልክ ጥሪ ለፖሊስ አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ" ሲለኝ በድንጋጤ ፈዝዤ ቀረሁ ። በዚህ መሀል ግን ህይወት የሆነ ቀን ከዲያሪዋ ላይ ያነበበችልኝ ትዝ አለኝ ✎ ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ይ................ ቀ.................. ጥ................... ላ.................... ል.................... ┈┈••◉❖◉●••┈🌹✿🌹 https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0 ┈┈••◉❖◉●••┈ ❣ :¨·.·¨: ❣SHARE ❣ :¨·.·¨: ❣
Show all...
Gedooooo Shooting ,,,,,,,,photo store

* ፎቶችን ማስራት የምትፈልጉ # 0987172734/ @yane_yabechaye በውስጥ መስመር ማነጋገር ትችላላቹ Be adobe light Rome # ሀሳብ እና አስታየት ካሎት / @yane_yabechaye መናገር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0

​🌺የከንቲባው ልጅ🌺 🔥ክፍል 23 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ሁሉም ተማሪዎች calculator ይዘው ነው የመጡት ። እኔ ግን በህልሜ የመረቀንኩት አለቀቀኝም መሰለኝ ብዕር እንኳን አልያዝኩም ። ብዕሩን እንደምንም ከመምህር አግኝቻለሁ ። calculator ቀድሞውኑ ለድምር አያስፈልገኝም ፤ አየር ላይ አጫውተዋለሁ ። ብዙ ጊዜ ተማሪ ፈተና ሲደርስ ሲጨናነቁ አያለሁ ። እኔጋር ግን እሱ የለም ። የምችለው ከሆነ እሰየው ፤ ካልሆነ ግን ሲፈልግ ገደል ይግባ ። (ፈተናው ሳይሆን አንተ ነህ ገደል የምትገባው...🙆) ። ፈተናው ተሰጠንና አየሁት ። #5 ጥያቄ ነው ። ከነሱ ውስጥ ግን እኔ ከአንደኛው ጥያቄ ውጪ አንድም info የለኝም ። እያንዳንዳቸው #4 ፣ #4 ነጥብ አላቸው ። ስለዚህ ከ #20% ውስጥ #4% ነው የማገኘው ማለት ነው ። የማውቃትን #1 ጥያቄ ሰርቼ የቀሩትን ደግሞ ከልጆች copy paste ላደርግ ብዬ ቀና ስል #2 አስተማሪዎች አንዱ ከፊት ሌላኛው ደግሞ ከዋላ ሆነው ድምበር እየጠበቁ ነው ። ጥሎብኝ ፈተና ሲከብደኝ መጨናነቅ አልፈልግም ። የቀሩትን #4 ጥያቄዎች በመሰለኝና ደሳለኝ ሞልቼ ወጣሁ ። ከሳምንታት በፊት "ምነው አንተ ልጅ እያሽቆለቆልክ እኮ ነው ፣ በጣም ከስተሃል" ባሉኝ አንደበታቸው ዛሬ ግን class ውስጥና መንገድ ላይ ያገኙኝ ልጆች እንዳለ "ምን ተገኘ ደግሞ ፡ በጣም ተስማምቶሃል" እያሉኝ ያልፉኝ ጀመር ። እንደውም የተመልካች አይን ሲበዛብኝ ሰግቼ ትፉልኝ ማለት ጀመርኩኝ ። እነሱ ግን ትፉልኝ እና ትፉብኝ መለየት ስለከበዳቸው በዋላ ላይ ማስታጠብያ ገዛሁና እሱ ውስጥ እንዲተፉልኝ አደረኩ ። ሁሉም የውፍረቴን ምክንያት ቢጠይቁኝም ፡ እኔ ግን ትንፍሽ አላልኩም ። ምክንያቱም ከዚህ በፊት ስከሳ አንድም ሰው የክሳቴን ምስጢር አልጠየቀኝምና ። ዶርም መሄድ ስላስጠላኝ ወደ Library አቀናሁ ። የተባረከው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ንሰሐ ይገባል ፤ እንደኔ አይነቱ ደግሞ ቤተ መፅሐፍት ገብቶ ላይገባው ግራ ይጋባል ። Final ፈተና እየደረሰ በመሆኑ ሶስቱም የጊቢው Library እንደ አባይ ሞልተው ተማሪዎች ወደ ግብፅ እየፈሰሱ ይገኛሉ ። አሁን ያለሁት ከሶስቱ አንዱ በሆነውና ዘንድሮ ተመርቆ ስራ በጀመረው Central Science and technology Library ውስጥ ነው ። ይሄ ቤተ መፅሐፍት ግን በጣም ዕድለኛ ነው ። ስንቱ ተምሮና ተመርቆ ስራ ባጣበት ዘመን ላይ ነው ሳይማር ተመርቆ ስራ የጀመረው ። anyways እኔ እንኳን የገባሁት እንደ ሌሎቹ የትምህርት መፃፍ ላነብ አይደለም ። ላይብረሪው ከትምህርት መፅሐፍ ውጪ ፡ ጋዜጣ ፣ መፅሔት ፣ FB ፣ Telegram ፣ ወዘተ መጠቀምያ ቦታ አለው ። ያውም እንደ ሳሎን በሶፋ የተሽቆጠቆጠ ቦታ ። እና ብዙ ጊዜ እዚህ እየመጣሁ Telegram ስለምጠቀም ላይብረሪስቶቹ ጭምር ሸምድደውኝ እንደ ድንገት እንኳን አርፍጄ ቦታው ላይ ሰው ሊቀመጥ ሲመጣ "ሰው አለው" ማለት ጀምረዋል አሉ ። እዚህ የሚገኙ ጋዜጦች ግን አይመቹኝም ። ከነሱ ይልቅ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሽንት ቤቶች ግድግዳ ላይ በተለያዩ የጊቢው Activist ተማሪዎች የሚፃፉት ሺህ እጥፍ ይማርካሉ ። ብዙ ጊዜ እንደውም የETV ዜና ሲናፍቀኝ ወደ ሽንት ቤት ጎራ እልና አነባለሁ ። ወደ ውስጥ ሳትዘልቅ ገና ከበሩ መግቢያ ላይ ይጀምራል ። "እንኳን ወደ ተመስገን በየነ የምግብ ማስወገጃ አዳራሽ በደህና መጣችሁ ። እናንተ ብቻ ጠንክራችሁ ብሉ እንጂ እኛ የናንተን የከበሩ ማዕድናት ለመቀበል #24 ሰዓት ዝግጁ ነን ። ለደንበኞች ቦታ ይያዛል ፣ በተጨማሪም በራሳችን ጉልበት ውሃ ወደ ሽንት ቤቱ እንደፋለታለን" ። ወደ ውስጥ ገብታችሁ ሱሪ አውልቃችሁ ቁጭ ስትሉ ደግሞ በአምስቱም አቅጣጫ (ከፊት በር ላይ ፣ ከዋላ ፣ በቀኝ ፣በግራ እና ኮርኒስ ላይ) ከሽንት ቤቱ ውጡ የማያስብሉ ምርጥ ምርጥ ቀልዶችን ያገኛሉ ። ከሁሉም ግን እኔን የምትመቸኝ "ለዚሁ ነበር እንደዛ የበላሁት ...?🙆" የምትለዋ ነች ። ምሽት ላይ እራት ከጓደኞቼ ጋር በልተን ቶኒ ላይ ሻይ ጠጥተን #01:30 ወደ ዶርም ስንመለስ ህይወት ደውላልኝ telegram እንድገባ ነገረችኝ ። ቀኑን ሙሉ ያልደወለችልኝ አባቷ እቤት ስለዋሉ እንደሆነና በቅርቡ ደግሞ ከሀገር እንደሚወጡ ነገረችኝ ። አብዛኛው ወሬዋ ግን ናፍቆት ነክ ነበር ። እንደውም በ voice ጭምር እየዘፈነች ልካልኛለች ። Studio ሳትገባ ዝምብላ እንደ ቀልድ የምትልክልኝና እቤቷ እያለሁም የምታዜምልኝ ሙዚቃዎች ህይወት አላቸው ። እሱ ብቻ አይደለም ፤ የምትፅፍልኝ መልዕክቶች ጭምር ልቤን ያቆሙታል ። "ቀኑን ሙሉ ስላንተ ሳስብና ስፅፍልህ ነበር የዋልኩት" ብላኝ ይሄን መልዕክት ላከችልኝ ። "ከዋክብትንና የምድር አሸዋን መቁጠር ከሚሳንህ በላይ ላንተ ያለኝን ስሜት በቁጥር ማወቅ ያዳግትሀል ። በዚች ምድር ላይ ለመኖር #1ሺህ ምክንያቶች ላያስፈልጉኝ ይችላሉ ። ባይሆን ያንተ መኖር ብቻ በራሱ በቂዬ ነው ። አንተ የቀኔ ፀሀይ ነህ ፤ ብሩህ ታደርግልኛለህ ። የምሽቴም ጨረቃ ነህ ፤ ጨለማዬን ትገፍልኛለህ ። ልቤ ፣ ደምስሬ ፣ አይምሮዬ ፣ ንግግሬ ፣ ልብ ምቴ ፣ ህይወቴ ፣ ሁሉ ነገሬ ውስጥ ገብተሃል ። ሌላው ይቅር ፡ አይኔን እንኳን ስጨፍን የምትታየኝ አንተ ነህ ። ብዙ ጊዜ ስትጎጂ እና ስታለቅሺ ማየት አልፈልግም ብለኸኛል ። የኔ ጌታ እየተጎዳሁና እያለቀስኩ ነው የዋልኩት ። አውቃለሁ አጠገቤ መሆን ስላልቻልክ እንጂ እኔን ለመጉዳት እንዳልራከኝ ። ቢሆንም ግን በጣም እየፈራሁ ነው ። ህይወት ላንተ ናት ፡ ሞት ግን ለኔ ፣ ደስታ ላንተ ነው ፡ ሀዘን ግን ለኔ ፣ አብሮ መሆን ላንተ ፡ ብቸኝነት ግን ለኔ ፣ ሁሉ ነገር ላንተ ፡ አንተ ግን ለኔ ነህ ። አንተን መናፈቅ ያስደስታል ፤ ለዛም ነው ቀኑን ሙሉ የማስብህ ። ምሽት ላይ ሆኜ አንተኑ ሳስብህ ከዋክብት አዝነውልኝ ሊያፅናኑኝ ከሰማይ ላይ ይረግፋሉ ። ምናልባት ሰማይ ባዶ ሆና ካገኘሀት ብዙም አትደነቅ ። ምክንያቱም በደምብ እንዳስብህ አድርገህኛልና ። ቀኑን ሙሉ ድምፅህን ሳልሰማ ፣ አይኖችህን ሳላይ ፣ በናፍቆት አሳለፍኩኝ ። ረስተኸኝ ይሁን እያልኩ እጨነቃለሁ ። የኔን ስሜት ሳልነግርህ ከማንም በላይ ታውቀዋለህ ብዬ አስባለሁ ። አብጄ አማኑኤል ብገባ እራሱ አንተን መርሳት የሚቻለኝ አይመስለኝም ። ደግሞ ህይወት መልሳ እንደምታገናኘን እና ወደፊት አንድ ቀን አብረን እንደ ምንህን ተስፋ አደርጋለሁ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ፤ ጉዞው ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። ለኔ ግን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የኔ ጌታ ፡ ያንተ አለመኖር ያማል ። ከአለም ጋር ከተለያየን ቆየን ፤ ምክንያቱም የኔ አለም አንተ ነህ ። ፀሀይ ፊቷን አዙራብኝ ብርሃን ካጣሁ ቆይቻለው ፤ ምክንያቱም የኔ ፀሀይ አንተ ነህ ። ጨለማ ውስጥ ነኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ነኘ ፤ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፤ በውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑንና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። በቶሎ ላገኝህ ብዬ ተኝቼ አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልማል ። እኔ አንተን ሳጣህ እንኳን ቀኑን እራሴንም እረሳለሁ ። ግን የኔ ጌታ እስካሁን ድረስ ያልረሳሁት # 1 ነገር አለ ። እሱም አንተ ነህ ። ምክንያቱም አንተን እረሳሁ ማለት በህይወት የለሁም ማለት ነው" ። ይሄን ሁሉ ብላኝ ፣ በድምጿም እየዘፈነች ልቤን ብታቆመውም የኔ መልስ ግን ዝምታ ነው ። ዝም ....ይቀጥላል
Show all...
​😘የከንቲባው ልጅ😘 🔥ክፍል 22 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ቶኒ በር ላይ ፈታሾቹ ከኔ ምንም ላያገኙ ፈትሸውኝ ፣ በርብረውኝና ዘቅዝቀውኝ ምንም ነገር ሲያጡ ወደ ውስጥ አስገቡኝ ። እና አሁን ያ አመዳም ጊቢ ውስጥ ነኝ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላኝ አጠይቁኝ ። (እንግዲህ በግድ ከጠየቃችሁኝ ምን ይደረጋል...🙆) ። ገና በቶኒ በር ስገባ ጀርባዬን ያሳክከኛል ። ብታዩት Campus ሳይሆን የአዋራ ፋብሪካ ነው የሚመስለው ​​። በዛላይ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ከዶርም ወደ cafe ስንሄድ ከመኝታ ቤት ወደ ሳሎን የሄድን ነው የሚመስለኝ ። ዶርም ሆነን ከሴቶች ጋር ማውራት ከፈለግን እኮ መስኮት መክፈት ብቻ ነው የሚጠበቅብን ። መሀል ላይ በቆርቆሮ አጥር ቢለያዩንም ከወንዶች ዶርም ጋር face to face ስለሆኑ ጎረቤቶቻችን ናቸው ብል ማጋነን አይሆንም ። እንደውም አንዳንድ ጊዜ ቺኮቻችን ሲደብራቸው መስኮት ከፍተው ይደበሩብናል ። professional የሆኑ የ GC ወንድ ተማሪዎች ደግሞ ጭራሽ micraphone ገዝተው ለሁሉም ዶርሞች እንዲዳረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ። አልፎ አልፎ ግን ወደ ሴቶቻችን ዶርም ስንመለከት ከ #18 ዓመት በታች ለሆኑ የተከለከለ ነገር እናያለን ። ከሙቀቱ የተነሳ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዶርም ውስጥ ልብስ መልበስ አቁመዋል ። ለነገሩ የድሬ ሙቀት እንኳን ልብስ ቆዳም ያስገፍፋል ። ሻዎር ውስጥ ስትገባ እንኳን fan ያስፈልግሃል ። አየሩ ፣ ውሃው ፣ መሬቱ ፣ ከሰው በስተቀር ሁሉነገሩ የተመታ ከተማ ። በቶኒ በር ገብቼ ፣ ፍቅር cafe ፣ cenrtal library ፣ የሴቶች ዶርም እና senior cafe'ን አልፌ ፣ ወደ ወንዶች ዶርም ዘለኩኝ ። ጊቢው ያለወትሮው ጭር ብሏል ። ጥሎበት ደግሞ ተማሪ ከሌለበት ሲኦል ነው የሚመስለው ። (አንተ ልጅ ደግሞ አንዳንዴ ታበዛዋለህ ፡ ሲኦልን ደግሞ መች አየሃት ...?) ። የተመደብኩበት block ደርሼ ፣ የዶርሜን በር (white house F #45) ከፍቼ ገባሁ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላ idea'ው የላቹም ። ተሳስቼ ሽንት ቤት የገባሁ ነበር የመሰለኝ ። ዶርም መሆኑን ያወኩት አልጋና ሎከር በመኖራቸው ነው ። ከሁሉም ግን ድንቅ የሚለኝ ፡ ሽንት ቤቶቹ እንዳለ ቀለም ተቀብተዋል ። የምናድርበት ዶርም ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቀለም የተቦረሸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄ ጊቢ ሲመሠረት ነው ። ግድግዳው የወፍጮ ቤት ይመስላል ፣ ፍራሾቹ ደርቀው ከድርቆሽ በላይ ጠንክረዋል ፣ ሎከሮቹ ተሰባብረው የማገዶ እንጨት መሥለዋል ፣ ኮርኒሱ ኩሽና ይመስል ጠቁሮ የጨለመ ሰማይ ሆኗል ፣ ሊሾው አፈር ለብሶ ወደ መሬትነት ተለውጧል ። በቃ ምን ልበላችሁ ...? ፡ ዶርሙ ከዶርምነት ተራ ወጥቶ ዱሪዬ ዶርም ሆኗል ። እዚህ ውስጥ እየኖርኩማ እንኳን ትምህርት ሊገባኝ ቀርቶ እንቅልፍ እራሱ የሚወስደኝ አይመስለኝም ። አማራጭ የለኝም ፤ ጠልቼ በግድ አንዴ ገብቼበታለሁ ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ፣ በዛላይ ጊቢው ስለዘገነነኝ ዶርሜን ዘግቼ አልጋ ላይ ፌንት ሰራሁ ። (ፌንት ግን ይሰራል ወይስ ይወደቃል ...?) ። ይሄን የመሠለ ዶርም ውስጥ ሆኜ በየት በኩል እንቅልፍ ይውሰደኝ...? ። anyways ቤት ሳይሆን ዱር እንዳደርኩ እቆጥራለሁ ። ኧረ ዱር እራሱ በስንት ጣዕሙ ። እውነት አያ ጅቦ እዚህ ቢመጣ "እኔን ፡ እኔን ፡ ምን ሆነክ ነው ጎዳና ላይ የምታድረው...? ፡ በል ተነስና ወደ ቤቴ ልውሰድክ" እንደ ሚለኝ አልጠራጠርም ። የዶርም ልጆች class ሄደዋል መሠለኝ ሁሉም የሉም ። ሙሉ ብሎኩም ባዶ ነው ። አንዳንዴ ግን ከጦርነት በላይ ፀትታም ያስፈራል ። እንደዚህ አይነቱ ቀንማ ዳዊት ካልደገሙበት በስተቀር የሚያልፍም አይመስልም ። (እሺ ሊቀ ጠበብት ተስፋዬ ...) ። anyways የዛሬው እቅዴ እስከ ከሰዓቱ ፈተና ድረስ መተኛት ነው ። በህልሜ የማቴሪያል ትምህርት መፃፍ ካገኘሁ አጠናለሁ ። ካልሆነ ግን በፈተናው ላይ ለሚ ብዛት ሀላፊነቱን አልወስድም ። ብዙም ሳልቆይ ግን ዶርም የነበርኩኝ ልጅ ማን እዚህ ቦታ እንዳመጣኝ ሳላውቅ ሌላ ቦታ ላይ እራሴን አገኘሁ ። ለመጨረሻ ጊዜ ትዝ የሚለኝ ነገር ቢኖር 'የሰላም እንቅልፍ ጣልብኝ ፈጣሪዬ' ብዬ መተኛቴን ነው ። አሁን ግን አልጋ ሳልሆን መሬት ላይ በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ እግሮቼን አጣምሬ ፤ በብዙ ወንዶችና ሴቶች ተከብቤ ነው ያለሁት ። ጆሮ ደግፍ የያዛቸው ይመስል ጉንጫቸው የሌለ አብጦ ፣ አይናቸው ቆንጆ ኮረዳ የሾፈ ይመስል ተጎልጉሎ ወጥቶ ፣ ጥርሳቸው ሳር የጋጡ ይመስል የላይኛው የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለም መስሎ ፣ ባጠቃላይ የሀገሪቱን የመብራት መቆራረጥ ችግር ይፈቱ ይመስል ባንድላይ እየጮኹና እያሽካኩ ያቺን ጠባብ ቤት ሊያፈርሷት ምንም አልቀራቸውም ። የአንዳንዶቹ ፊት ለኔ አዲስ አይደሉም ። እንደውም ወደ ቀኝ ዞር ስል በታሪክ እዚህ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ ብዬ የማላስበውን ልጅ አይቻለሁ ። ያው እኔም እዚሁ ከሱጋ ስለሆንኩኝ አላዘንኩለትም ። እዚህ ቦታ ላይ መተፋፈር የለም ። አሜሪካ በሏት ። ጫት ፣ ሲጋራ ፣ ሺሻ ፣ ሴት ፣ ወንድ ፣ ዊድ ፣ ጋንጃ ፣ ከቦብ ማርሌይ ውጪ ምን የሌለ ነገር አለ...? ። እየቃምኩ መሆኔን እስካሁን አላመንኩም ። እያጨስኩ መሆኔን ደግሞ ላምንም አልፈልግም ። አንዲት የማላውቃት ሴት ተገላልጣ ወደኔ እየተወላገደች ስተመጣ 'አንተ ክፉ ሰይጣን ፡ ከኔ ራቅ' ብዬ #3 ጊዜ ላማትብ ስል እጄን ይዛኝ ከተቀመጥኩበት አስነሳችኝ ። ይዛኝ ወደሆነ ክፍል ወሰደችኝ ። ቀለል ብላ ደስ የምትል መኝታ ቤት ውስጥ ነን ። እኔና እሷ ብቻ ። እንዲህ ውብ ሆኗ እዚህ ቦታ ላይ መገኝቷ ሲገርመኝ ገፍትራኝ አልጋው ላይ ወደኩኝ ። ምን አስባ እንደሆነ እስቲ ልየው ብዬ ዝም አልኩኝ ። ቀስ ብላ ወደ አልጋው ላይ መውጣት ጀመረች ። ለነገሩ እኔ ላይ ነው እየወጣች ያለችው ። ምክንያቱም አልጋው ያለው ከኔ ስር ነውና ። ወደኔ ይበልጥ በ slow motion እየተጠጋች ከንፈሯን ከከንፈሬ ጋር ልታገጣጥም ስትል በሩ ተንኳኳ ። (ምናለበት እስኪ ነገ ቢያንኳኩ ...?) ። ኳ ኳ ኳ ... ። 'ማነው...?' አልኩኝ ጮክ ብዬ በምሬት ። "አንተ አዝግ የፈተና ሰዓት ደርሷል ተነስ" የሚል የዶርሜ ልጅ ድምፅ ተሰማኝ ። ለካ የዶርሜ በር እስኪንኳኳ ድረስ የነበረው ሁሉ በህልሜ ነው ። እኔ ግን 'ማነው' ያልኩት እኮ ከህልሜ ጓደኛ ጋር እያለሁ የተንኳኳ መስሎኝ ነው ። የዶርሜ ልጅም "ጠዋት እኮ ወደ class ስሄድ ከሩቅ አይቼህ ነበር ። ከዛን #2 period ተምረን ምሳ በልቼ መጣሁ ። እንዳጋጣሚ ደግሞ ቁልፌን ምግብ ቤት ስበላ አስቀምጬ ሳላነሳው ረስቼ መጣሁ ። ለዛ ነው ያንኳኳሁት" ብሎኝ ተያይዘን ወደ መፈተኛ ክፍል ጉዞ ጀመርን ። ✎ ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Lik️ ማድረግ አይርሱ። ይ................ ቀ.................. ጥ................... ላ.................... ል.................... ┈┈••◉❖◉●••┈🌹✿🌹 https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0 ┈┈••◉❖◉●••┈ ❣ :¨·.·¨: ❣SHARE ❣ :¨·.·¨: ❣ 💞 ጌዶኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦ💞
Show all...
Gedooooo Shooting ,,,,,,,,photo store

* ፎቶችን ማስራት የምትፈልጉ # 0987172734/ @yane_yabechaye በውስጥ መስመር ማነጋገር ትችላላቹ Be adobe light Rome # ሀሳብ እና አስታየት ካሎት / @yane_yabechaye መናገር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

https://t.me/joinchat/9aw19-VUmNdjZWU0

​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺 🔥ክፍል 21 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ህይወት ልታለቅስ ነው መሠል ደንግጣ ፍዝዝ ብላለች ። ዋነኛው ምኞቷ በነፃነት መኖር እንደሆነ ነግራኝ ነበር ። ታድያ ጊዜው ሲደርስ ምን አሸበራት ...? ነው ወይስ ደስታው ነው ባለችበት ደርቃ እንድትቀር ያደረጋት ...! የሷ ይቆየኝና ግን እኔም ልክ አባቷ "ተያይዘን አሜሪካ ሄደን በነፃነት እንኖራለን" ሲሏት የልብ ምቴ ፈጥኖ ፣ ፊቴም ተለዋውጦ ነበር ። ከውስጤም ልክ የሆነ አካል እንደጎደለ ተሰምቶኛል ። "ምነው የኔ ህይወት ፡ ደስ አላለሽም እንዴ ...? እኔኮ ይሄን ስነግርሽ ከምንጊዜውም በላይ የምትደሰቺ መስሎኝ ነበር" አሏት አባቷ ። ህይወትም ድምጿ እየተቆራረጠ "አያይ አባቢ ፡ ደስ ብሎኛል ፡ ግን በቃ የአቤል ደም ፍትህ ሳያገኝ እንደ ውሃ ፈሶ ቀረ ማለት ነው ...?" አለቻቸው ። አባቷም በረጅሙ ተነፈሱና "አይደለም የኔ ህይወት ፡ አንቺን ለ #4 ዓመት እዚህ በድብቅ አስቀምጬሽ ስራ ላይ ጊዜዬን ያጠፋሁትም ለዚሁ ነበር ። የአቤልን ደም ያፈሰሱትን ሰዎች ህግ ቦታ ይዤ ሄጄ እነዚህ ናቸው ገዳዮቹ ብል የሬሳ ምርመራ ብለው መቃብር ስለሚቆፍሩ ሟቹ አቤል እንጂ አንቺ እንዳልሆንሽ ለጠላቶቼ መንገር ስለ ሚሆንብኝ እሱን መንገድ አልተከተልኩም ። ሁሉም ሰው የሚያውቀው አንቺ እንደሞትሽ እንጂ ስለ አቤል ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ። ፖሊሶቹን ጭምር ለምርመራ ሲመጡ 'ሲገድሏት የት ነበራችሁ ...? አሁን ወሬ ለቀማ ነው የመጣችሁት...?' ብያቸው ስለ ጮኹኩባቸው ፣ በዛላይ የከተማችን ከንቲባም ስለነበርኩ ሬሳውን ለማየት አልደፈሩም ። ስለዚህ የነበረኝ ብቸኛው አማራጭ ሰዎቹን በለመዱት የወንጀል ስራቸው ሲጨማለቁ በጥብቅና በቅርበት ተከታትሎ በቂ ማስረጃ ማሰባሰብ ነበር ። ሰዎቹ በዋዛ የሚያዙ ባይሆኑም በስተመጨረሻ ግን በእጄ ወድቀው ለዘላለም እስር ቤት ውስጥ እንዲማቅቁ አድርጌያቸዋለው" አሏት ። ህይወትም "ታድያ እነሱ ከታሰሩ የኛ መሸሽ ከማነው ...?" አለቻቸው ። እሳቸውም "የኔ ህይወት ፡ እነዚህ ሰዎች እስር ቤት ገቡ ማለት የተንኮል ስራቸውን አቆሙ ማለት አይደለም ። እንደውም እዛ በመግባታቸው ሰይጣንነታቸው ቢብስ እንጂ አይቀንስም ። ፍርድ ቤት ሲፈረድባቸው እንዴት ገላምጠው እንዳዩኝ አታቂም ። በዚህም በዚያም የኔ ህይወት ፤ አሁን ስለነሱ የምናስብበት ጊዜ አይደለም ። ማሰብ ያለብን አሜሪካ ስንሄድ ስለሚጠብቀን አዲሱ ህይወት ነው ። ባለፈው መጥቼ ፋይሎችሽን እንዳለ የወሰድኩትም ለዚሁ process ነበር ። አሁን ሁሉም ነገር አልቋል ። መሄድ ብቻ ነው የቀረን ። አዲስ አህጉር ፣ አዲስ ሀገር ፣ አዲስ ከተማ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ ት/ቤት ፣ አዲስ ጓደኞች ጭምር ይኖሩሻል" አሏትና ፊት ለፊታቸው የተቀመጠውን ወይን አንስተው ተነሱና አንዴ ከተጎነጩ በዋላ ግንቧሯን ሳሟትና "በጣም ደክሞኛል እሺ የኔ ህይወት ፡ ቀሪውን ነገ እናወራለን ፡ አሁን ገብቼ ልተኛ" አሏትና እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ መራመድ ጀመሩ ። በሩ ጀርባ ተሸሸኩኝ ። የክፍላቸውን በር ከፍተው ገብተው ሲዘጉት ተመልሼ በበሩ ወደ ሳሎን ማየት ቀጠልኩኝ ። በህይወት ፊት ላይ ምንም አይነት የደስታ ስሜት አይታይም ። ፊቷን ደመና ያዘለ ሰማይ አስመስላ ከሶፋው ላይ ተነስታ ወደኔ መጥታ ገባችና በሩን በቀስታ ቆለፈችው። ምንም ሳትለኝ አልጋ ውስጥ ገብታ ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች ። ምን ሆነሽ ነው ...? ልላት አልፈለኩም ። አባቷ የተኙት ከአጠገባችን ባለው ክፍል ውስጥ ስለሆነ ለማውራት አይመችም ። በተጨማሪም በራሷ ፍቃድ እንድትነግረኝ ነው የፈለኩት ። እኔም ያወሩትን ነገር እያንዳንዷን እንዳልሰማሁ ምንም እንዳል ተፈጠረ በማስመሰል አልጋው ውስጥ ገባሁና ጀርባዬን ሰጥቻት ተኛሁ ። አይኖቼ ግን አልተከደኑም ። ብዙም ደቂቃ ሳይቆይ ግን ህይወት በጀርባዬ በኩል ተለጥፋብኝ በታፈነ ድምፅ ማልቀስ ጀመረች ። ቀና ብዬ መብራቱን አብርቼ ዞሬ ሳያት በዕምባዋ አንሶላና ትራሱን አረስርሳለች ። እቅፍ አድርጌያት እምባዋን መጠራረግ ጀመርኩኝ ። ግን ማስቆም አልቻልኩም ። ዕምባ ከአይኖቿ ሲፈስ ፡ በእጆቼ ስጠርግ ፣ አሁንም ሲፈስ ፡ ደግሜ ሳብስ ፣ መላው ሲጠፋኝ 'እሽሽሽ በቃ ፡ በቃ ፡ ስወድሽ አታልቅሺ ፡ የዕምባሽ መፍሰስ ትክክለኛውን ምክንያት ባላውቅም ፡ ምናልባት ግን ሊያስቆመው የሚችለውን ጉዳይ ንገሪኝና መፍትሄ እንፈልግለት' አልኳት በለሆሳስ ። እየተንሰፈሰፈች ፣ ከዕምባዋ ጋር በአፍንጫዋ የሚወርደውን ውሃ መሠል ንፍጥ ወደላይ አየመለሰችና እየጠራረገች "ለምን እንደማለቅስ ከነገርኩህ ራስ ወዳድ ነሽ አትለኝም ...?" አለችኝ ። 'አልልሽም ፡ በይ ንገሪኝ' አልኳት ማቆምያ የሌለውን ዕምባዋን እየጠረኩላት ። "እንደውም እርሳው በቃ" ብላኝ እንደ ቅድሙ ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች ። እኔም "ዛሬ እንጂ ነገ የት ይሄዳል ...?" ብዬ መብራቱን አጠፋሁና ለመተኛት ሞከርኩኝ ። ግን አይኔ አልከደን አለኝ ። ስልኬን አወጣሁና data አብርቼ Telegram ገባሁ ። የክፍሌ group ላይ ነገ Material ፈተና አለ ተብሎ ተለቋል ። በልቤ ችግር ላይ ሌላ ችግር አልኩና data አጥፍቼ ፣ አባቷ ቀድመውን እንዳይነሱ Alarm ሞልቼ ተኛሁ ። እንቅልፍ ባይኔ ስላልዞረ ጠዋት አላርሙን እራሴው ቀሰቀስኩትና ተነሳሁ ። ልጅቷንም ቀስ ብዬ በእጄ ትከሻዋን ነካ ነካ እያደረኩ በሹክሹክታ 'ህይወት ፡ ህይወት' እያልኳት ስጣራ ተነሳችና ወደ ጊቢ መመለስ እንዳለብኝ ከነምክንያቱ ነገርኳት ። አባቷ ቤት እንዳሉ ረስታለች መሠለኝ "ሂድ በቃ" አለችኝ በደከመ መንፈስ ። 'መሄዱማ የት ይቀራል ፡ ግን እኮ አባትሽ እቤት ናቸው እንዴት ነው የምወጣው ...?' አልኳት ። ሴት ልጅ መለኛም አይደለች ። እኔ የቤቱንና የአጥሩን በር ከፍቼ ስወጣ አባቷ እንዳይሰሙ እሷ ክፍላቸው ገብታ ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርጋ እንደምትከፍት ነገረችኝ ። ከአባቷ ጋር ጓደኛም ጭምር ስለሆኑ በዛን ሰዓት የሚያስቡት እሳቸውን ለመረበሽ የፈጠረችው ነገር እንደሆነ ነው ። ያለውን ነገር በስልክ እርስ በርስ እንድናሳውቅ ተነጋግረን እሷ ጉንጬን እኔ ደግሞ አይኖቿን ሳምኩኝና ተሰነባብተን እንደ ተባባልነው ልክ እሷ ከሳሎን በጂፓስ የሙዚቃውን ድምፅ መጨረሻ ላይ አድርጋ ስትከፍት በሩን ከፍቼ ሸመጠጥኩት ። ከጊቢው ስወጣ በረጅሙ ተነፈስኩና ቁልፎቹን በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አቀናሁ ። የሙዚቃው ድምፅ ውጪ ድረስ ይሰማ ነበር ። ቤት ውስጥ እያለሁ ሲከፈት ... "ቀኑ መሽቶ ጨላለመ ፡ ብሎ ተስፋ ቆርጦ ከደከመ ፣ ደስታውን ያራቀው ለታ ፡ ያኔ ነው ሰው የሚረታ" ። እያለ ነበር ። አሁን ግን ድምፁ ቀስ በቀስ እንዲህ እያለ እየራቀኝ መቷል ... "እኛ ከሌለን ባዶ ፡ እኛ ከሌለን ባዶ ፣ እኛ ከሌለን ባዶ ፡ አዎ ሁሉም ባዶ" ። ​ ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ይ................ ቀ.................. ጥ................... ላ.................... ል.................... ​┈••◉❖◉●••┈🌹✿🌹 https://t.me/joinchat/5fsxwoZ-vIxlZjdk ┈┈••◉❖◉●••┈ ❣ :¨·.·¨: ❣SHARE ❣ :¨·.·¨: ❣ 💞 መንታ ልቦች💞
Show all...
🇯🇲🌷🍁ህይወቴ🍁🌷🇯🇲

💞ለምን ወደድኩህ/ሽ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 💞ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 💞እንዴት ማረከኝ/ክሺኝ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 👉ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💞ማለት፤ ➽ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➽በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ 💁‍♂️💁‍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💞 ✍️ለአስተያየትዎ❤️ 👇 👉 @ZERUBABEL16👈spam @Alzershbot

​😘የከንቲባው ልጅ😘 ክፍል 20 ✍ደራሲ ተስፋዬ በትሩ . . . ወደ ውስጥ አንድ ሰው ገባና በሩን ዘግቶ ከህይወት ጋር ጥምጥም ብለው ተቃቀፉ ። አባቷ ናቸው አልኩኝ በልቤ ። ደንግጬ ወዴት እንደ ምሄድ ግራ ገብቶኝ ወደዚያ ወደዚህ ስል አንዴ ከግድግዳ ጋር ተላተምኩና ግንባሬን እያሻሸው ወደ ከንቲባው ልጅ ክፍል ገባሁ ። ለማየትና ለመስማት እንዲያመቸኝ የክፍሉን በር ሙሉ በሙሉ አልዘጋሁም ። መብራት ግን አጥፍቻለሁ ። አባትና ልጅ ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ ። ደስ የሚለው አባቷ ላለሁበት ክፍል ጀርባቸውን ሰጥተው ነው የተቀመጡት ። ህይወት ደግሞ በኔ ፊትለፊት ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ከፀሀይ በላይ ፈክታ በናፍቆት ወደ አባቷ እያየች ታወራለች ። "አባቢ ደና ነህ አይደል ፡ እኔኮ ተጨንቄ ስልክህ ላይ ከጠዋት ጀምሮ ስሞክር ነበር ፤ ግን አይሰራም" አለቻቸው ። አባቷም "የኔ ህይወት አመሻሹ ላይ ነው እኮ አዲስ አበባ የገባሁት ፤ እረፍት ሳልወስድ ነው በዛው በድሬ plane ወደዚህ የመጣሁት" አሏት ። "ደክሞሀል አይደል በሙቅ ውሃ እግርህን ልጠብልክ ...?" ስትላቸው "አይ ፡ ባይሆን ሻዎር ልውሰድና ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ" ብሏት ተነስቶ ግንባሯን ሳሟትና እኔ ወዳለሁበት ቦታ አመሩ ። ደንግጬ ከበሩ ጀርባ ተደበኩኝ ። ካለሁበት አጠገብ በቀኝ በኩል ያለው ክፍል ሲከፈት ይሰማኛል ። ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ቤት ስመጣ የከንቲባው ልጅ "አባቴ ሲመጣ እዚህ ነው የሚያድረው" ያለችኝ ክፍል ነበር ። ከትንሽ ደቂቃ በዋላ ተመልሶ ተዘጋና ወደኔ እየቀረበ የሚመጣ የእግር ኮቴ እየሰማው አልፎኝ ሄደና በግራዬ በኩል ያለው ክፍል ተከፍቶ ወዲያው ተዘጋ ። በሆዴ 'አባቷ ሻዎር ገቡ ማለት ነው' ብዬ ሳልጨርስ በድጋሜ ወደኔ የሚመጣ የሰው ኮቴ ሰማሁ ። በቅስፈት ያለሁበት ክፍል መብራት ሲበራብኝ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ። ኡፍፍፍ ፡ የከንቲባው ልጅ ነበረች ። "እዚህ ነህ እንዴ ...?" አለችኝ በሹክሹክታ ። (አያይ ፡ ኩሽና ነኝ ...) ። ስናወራ ድምፃችን እንዳይሰማ ሰግተን Telegram ገብተን txt መላላክ ጀመርን ። 'እስከ መች ነው ግን ከአማቼ ጋር ድብብቆሽ የምጫወተው ...?' አልኳት ለጨዋታው ድምቀት ። አንብባ ከት ብላ ሳቀችና መልሳ ደግሞ ደንግጣ በግራ እጇ አፏን ከድና "እኔኮ ወንድ መስለኸኝ ነበር ላስተዋውቅህ እዚህ ድረስ ያመጣሁክ ፤ አንተ ግን እንደ ሴት ጓዳ ለጓዳ ትሽሎኮሎካለህ" ብላ መለሰችልኝ ። 'ተነስቼ ሻዎር ቤት ገብቼ እንዳልተዋወቃቸው' ስላት "ወንድ ነህ አ" አለችኝ ። ወንድነት ተሰማኝ መሰለኝ ከአልጋዋ ላይ ተነስቼ ወደ በሩ አመራሁ ። በሩን ከፍቼ ልወጣ ስሞክር ምንም ሳይመስላት ቁጭ ብላ ታየኛለች ። "ኧረ ተመለሰ ቀልድ አታውቅም እንዴ ...?" የሚል ልመና ነበር የጠበኩት ። (ግን ወፍ የለም ...) ። ወደ አልጋው ተመልሼ ሥርዓቴን ይዤ ተቀመጥኩ ። የከንቲባው ልጅ ለሴኮንዶች ስልኳ ላይ አቀርቅራ ቀና ስትል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ። ማንበብ ጀመርኩኝ "አየህ ፡ የብዙ ሰዎች ችግር ይሄ ነው ገላጋይን ተስፋ አድርገው ይጣላሉ ፣ ይለምኑኛል ብለው ይዳፈራሉ ፣ ይጠሩኛል የሚል አጉል ተስፋ ይዘው ይሄዳሉ አንተም እንደዛው ነው የሆንከው የኔ ጌታ የሚል ነበር (sticker እኔ ጨምሬበት አይደለም) እንዲሁ በ txt እየተበሻሸቅን ከደቂቃዎች በዋላ የሻዎር ቤቱ በር ሲከፈት ተሰማን ወዲያውኑ አባቷ "ህይወት ፣ ህይወት" እያሉ መጣራት ጀመሩ የሲሊፐር ድምፅም "ጣ ጣ" እያለ እኛ ወዳለንበት ክፍል እየቀረበ መጣ በብርሃን ፍጥነት እኔ ከአልጋው ላይ ተነስቼ በሩ ጀርባ ስደበቅ የከንቲባው ልጅ ደግሞ ተስፈንጥራ በሩን ከፍታ ደጃፋችን ላይ የደረሱት አባቷ ወደ ውስጥ እንዳይገቡ በሩ ላይ ቆማ "አባዬ ክፍል ተሳስተሃል ቀጣዩ እኮ ነው ያንተ" አለቻቸው በፍርሃትና በሚንቀጠቀጥ ድምፅ "እሱማ መች ጠፋኝ ከሳሎን ሳጣሽ ጊዜ ነው የጠራውሽ" አሏትና ወደ ክፍላቸው ሄዱ ህይወት በረጅሙ "ኡፍፍፍ" ብላ ተነፈሰች ፤ እኔም እንደዛው "ከዚህ ክፍል ንቅንቅ እንዳትል" የሚል ማስጠንቀቂያ በጆሮዬ እያንሾካሾከች ሰጠችኝና ወደ ሳሎን ተመልሳ ተቀመጠች ያለሁበት ክፍል በር እንደ ቅድሙ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም ሳሎን ውስጥ የሚደረገውን ማየትም መስማትም እችላለሁ አባቷ ከደቂቃዎች በዋላ በለሊት ልብስ ከክፍላቸው ወተው ወደ ሳሎን ተመለሱ ። ትልቅ ሰው ናቸው እድሜያቸው በግምት ወደ #40 ዓመት ይጠጋል አሁንም እንደ ቅድሙ ጀርባቸውን ሰተውኝ ተቀመጡ "እስቲ ሂጂና ወይን አምጪልኝ!" አሏትና ወይን ከነመጠጫው ይዛላቸው ተመለሰችና እየቀዳችላቸው "አባቢ ቅድም እኮ ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ ብለህ ነበር ። ምንድነው እሱ ?" ብላ ጠየቀች ። "እይውልሽ የኔ ህይወት" ብለው ንግግራቸውን ጀመሩ "አንደኛው ነገር ፡ እንደ ምታውቂው የከንቲባነትን ስራ የጀመርኩት የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ ነበር እናም በየ #4 ዓመቱ ሌላ ዓዲስ ከንቲባ ይመረጣል በዚህም መሠረት የኔ የስልጣን ጊዜ ቆይታ ተገባዶ ወደ ሌላ ሰው የሚያልፍበት ሰዓት ላይ ደርሷል ስለዚህ ከቅርብ ቀን በዋላ እኔ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አይደለሁም ማለት ነው" ሲሏት ህይወት በደስታ ዘላ ተጠመጠመችባቸው አባቷ ንግግራቸውን ቀጠሉ ፡ "የኔ ህይወት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለስልጣን መሆን ክብደቱ ከስራው ይልቅ አንዴ ገብተውበት የስልጣን ጊዜውን ሳይጨርሱ ለመልቀቅ መሞከሩ ነው የዛሬ #4 ዓመት ያኔ ልክ አንቺላይ የግድያ ሙከራ እንዳደረጉ ስራውን ለቅቄ ይዤሽ ከሀገር ለመውጣት አስቤ ነበር ግን ስልጣኑን የተረከብኩበት ጊዜ ስለነበር ሁሉም ነገሮች በኔ እጅ ውስጥ ሆነው ስለተጀመሩና ሴኔቱ እንዳለ የኔን መልቀቅያ ወረቀት ውድቅ ስላደረገው ምንም ማድረግ አልቻልኩም ለማንኛውም አሁን እሱን ተይና ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እኔ ያንቺና ያንቺ ብቻ ነኝ ። ሁለተኛው እና ዋነኛው ነገር ደግሞ" ብለው ቀጠሉ "የኔ ህይወት አሁንም ለኔና ላንቺ እዚህ መኖር አደጋ ሊኖረው ይችላል ከሰዎቹ ጋር ችግር ውስጥ መግባት አልፈለኩም ። ክፉ ሰው የተቀጣው ክፉ የሆነ ቀን ነው እነሱን ብበቀል ያንቺ ህይወት ያሳስበኛል ትቻቸው እዚህ ብኖር ደግሞ ምናልባት ያንቺን በህይወት መኖር ካወቁ ሊነጥቁኝ ይችላሉ ያኔ አንቺን ለመግደል ብለው አቤል ላይ የተኮሱት በወቅቱ እኔ ስልጣን ላይ ከወጣሁ በዋላ በከፍተኛ የሀላፊነት ወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ይሄን ፍቅር የሆነ ምስኪን የድሬዳዋ ህዝብ እየበዘበዙ ነበር ። እነሱን ግማሹን ከስልጣን ላይ አንስቼ ሌላ ሰው ስተካና ለቀሩት ደግሞ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ስሰጣቸው ነበር ባንቺ ፋንታ አቤል ላይ ጉዳቱ የደረሰው ከቅጣት ሁሉ የበለጠ ቅጣት ጠላትሽን መግደል አ ​​ይደለም ፤ እሱ አብልጦ የሚወደውን እና የሚኖርለትን ነገር ማሳጣት እንጂ ለዛም ነበር እኔን ትተውኝ አንቺን ለማጥፋት የተነሳሱት" ስለዚህ ከዚህ ሀገር ወተን መሄድ ግድ ነው በቅርቡ ተያይዘን አሜሪካ ሄደን በነፃነት እንኖራለን" አሏት .✎ ክፍል ሀያ አንድ ከ25 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል.... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። ይ................ ቀ.................. ጥ................... ላ.................... ል....................
Show all...