cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ውሉደ ጥምቀት ዘገዳመ ኢየሱስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በገዳመ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል መነሻ በማድረግ የተቋቋመ ማህበር ነው

Show more
Advertising posts
435
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-930 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
452Loading...
02
https://www.youtube.com/live/qd7ouDG1Jew?si=TajBbTlzK55LWtXC
640Loading...
03
ቅድስት ኪዳነ ምህረት እናቴ 16♥️🎚️ እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡ የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፡የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘው የደህንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ እኮ ነሽ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኃዘን ከገነት በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኃዘን ተረጋግቶብሻልና፡፡ (መልክአ ኪዳነ ምህረት) ኪዳነ ምህረት እኛንም ከሀዘን ከመከራ ታውጣን🙏 ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን አሜን!!🙏
610Loading...
04

10Loading...
05
Media files
1170Loading...
06
#ለእናታችን #ቅድስት #ክርስቶስ #ሠምራ #ጌታችን #አምላካችንና #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #የተሰጣት #ቃል #ኪዳን! (ዛሬ ግንቦት 12 ቀን ቃል-ኪዳን የተቀበለችበት ዕለት ነው!) 👉"እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ" - ዘዳ. 7፥9 👉"የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል" - መዝ. 111 (112)፥6 “እውነት በእውነት እልሻለሁ ወይም እነግርሻለሁ በፍጹም ደስታ መታሰቢያሽን ያደረገ በመንግስተ ሰማያት አስደስተዋለሁ። በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን ስምሽን ቢጠራ እኔ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ። የገድልሽን ዜና የሚናገረውን መጽሐፍ የጻፈ ወይም ያጻፈ እኔ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፍላቸዋለሁ። ቤተ ክርስቲያንሽን የሠራ ወይም ያሠራ ያሳነጸ ወይም ያነጸ እኔ በመንግስተ ሰማያት ንጹሕ አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ። በስምሽ ለተራበ ያበላ እኔ በዕለተ ዓርብ ከተቆረሰው ሥጋዬ አበላዋለሁ። በስምሽ ለተጠማው እፍኝ ውኀ ያጠጣ እኔ በዕለተ ዓርብ ከጎኔ በፈሰሰው ደሜ አረካዋለሁ። በዓልሽ በሚከበርበት ዕለት ጧፍ ዕጣን ወይም ዘይት ንጹሕ ሥንዴ የመሰለውንም ሁሉ መባ ያገባ መሥዋዕቱን እንደ አብርሃምና እንደ መልከጼዴቅ መሥዋዕት አድርጌ እቀበልለታለሁ። አላት። ...አቤቱ እንዲህ ከሆነ መታሰቢያዬን እያደረገ ስሜን እየጠራ በስሜ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚቀበረውን እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ አለችው። እስከ ዓሥር ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ አላት። ይህንም ቃል ኪዳን በተሰጣት ጊዜ ፈጽማ ተደሰተች። ...እውነት እውነት እልሻለሁ ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሣለመ ይቆጠርላታል። እውነት እውነት እልሻለሁ አንቺን ያከበረ ሁሉ እኔ በሰማያዊ መንግሥቴ አከብረዋለሁ። ...ስለዚህ አንቺን የሚያከብሩ ሁሉ አንቺ ካለሽበት ቦታ ገብተው ካንቺ ጋር ይደሰታሉ። ከዚህም አምላካዊ ቃል ጋር በነሐሴ ሃያ አራት ቀን የአባታችን የተክለ ሃይማኖት በዓል በሚከበርበት ዕለት ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለየች።” ምንጭ፦ ገድለ ክርስቶስ ሠምራ፤ ዘነሐሴ፤ ገጽ 152 -157 ቁጥር 11-17፣ 23-25፣ 31-32፣ 44-45፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤1992 ዓ.ም፤ አዲስ አባባ
1000Loading...
07
ቅዱስ ጴጥሮስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚለውን የትንሣኤውን ጌታ ድምጽ ከሰማ ፣ የተጠራጠረው ቶማስ እጁን በጎኖቹ አግብቶ “ጌታዬ አምላኬ” ብሎ ሲያምን ከተመለከተ በኋላ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” ብሎ ሲናገር እናገኘዋለን።(ዮሐ 21፥3) ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት በሐሙስ ምሽት ከእሳት ዳር ተቀምጦ ያደረገውን ሊረሳውና ራሱን ይቅር ሊል ስላልቻለ፣ ጌታው ቀድሞ የሰጠውን የወንጌል መረብ ተወና የዓሣውን መረብ ጨብጦ ወደ ገሊላ ባሕር ሮጠ።(ማቴ 4፥19) በኃጢአት ምክንያት የተሰማው ኃፍረትና መሸማቀቅ ሐዋርያነቱን ትቶ በድሮ ማንነቱ ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ አደረገው። የካደን ማን ለምስክርነት ይፈልገዋል በሚል ዓይነት ስሜት ለወንድሞቹ  “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። ደስ የሚለው ነገር ግን ይህን አስቀድሞ የሚያውቅ ይቅር ባይ አምላኩ ጴጥሮስን “በገሊላ ቀድሞት ነበር”። በበደሉ ተሸማቆ የተወውን ሐዋርያነት ሥልጣን በፍቅሩ መማለጃነት መልሶ ሊሰጠው፣ አይገባኝም ብሎ ያስቀመጠውን የወንጌል መረብ ዳግመኛ ሊያሲዘው በገሊላ ባሕር ዳር ቀደመው። እኛም አንድ ኃጢአት ይኖረናል። መርሳት ያልቻልነው፣ ንስሐ እንኳን ብንገባበት ራሳችንን ይቅር ለማለት የተቸገርንበት፣ “ከዚህ በኋላማ...” እያሰኘ የድሮ መረብ አስይዞ ወደ ገሊላ የሚመልስ አንድ በደል ይኖረናል። ነገር ግን ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው ለእኛም እንዲሁ ያደርጋል። ከባሕሩ ዳር ይጠብቀናል፣ “ትወደኛለህ” ብሎ ይጠይቀናል፣ ከዚያ በማይለወጥ ፍቅሩ ወልውሎ ሰንግሎ አፍረን ወደ ሸሸነው መንፈሳዊነት ይመልሰናል። +++ ጌታችን በገሊላ ይቀድመናል! +++
1330Loading...
08
+ የሚሮጥ ዲያቆን + የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ:: በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው:: እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር:: በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ:: ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣ ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው:: አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ? ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው:: ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ? ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ዲበ ሠረገላ ሰማይ ለኢጃት ዲያቆናት ሲመት ግንቦት 6 2016 ዓ.ም.
1041Loading...
09
#እንኳን_ለዳግማይ_ትንሣኤ_አደረሳችሁ! #አግብኦተ_ግብር ፤ #ዳግማይ_ትንሣኤ የቴሌግራም ቻናሌ 👇 https://t.me/MoaeTewahedoB "ጊዜው ደረሰ" ዮሐ 17÷1 ✝ዳግማይ ትንሣኤ እና አግብኦተ ግብር፡- ለሐዋርያት በጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ቶማስ ባለበት የተገለጠበት ቀን ስለሆነ ዳግማይ ይባላል እንጂ ትንሣኤው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ✝ ዳግማይ ትንሣኤ ከመባሉ በተጨማሪ በሊቃውንት ምሥጢራዊ አጠራር "አግብኦተ ግብር" ይባላል፤ ቀጥታ ትርጉሙ "ሥራን መመለስ" ማለት ነው፤ ምሥጢሩ ግን "ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" ብሎ እንዲያመጣው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥጋ የለበሰበትን ዓላማ በመስቀል የሚያጠናቅቅበት ጊዜው መድረሱን የሚያሳይ ነው፤መስቀሉ ላይ "ተፈጸመ ኩሉ" ብሎ መጮኹም የዚሁ የመጨረሻ ክፍል ነው፡፡ ✝በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ የዮሐንሰ ወንጌል 17÷1-ፍጻሜ ድረስ ሙሉው ይነበባል፡፡ በዓሉ የጸሎተ ሐሙስ ሲሆን በዕለቱ ብዙ የተደራረቡ በዓላት በመኖራቸው ምክንያት "አግብኦተ ግብሩ" ከዳግማይ ትንሣኤ ተደርቦ ይታሰባል፡፡ ✝የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 17 ሙሉው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነው፡፡ ✝ይህም ጸሎቱ እንደ ብሉዩ ሊቀ ካህናት የኃጢአት መሥዋዕትን ተክቶ የቀረበ ጸሎት ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ የካህናት አለቃ ለሕዝቡ የኃጢአት ሥርዬት የሚሆነውን መሥዋዕት ከማቅረቡ አስቀድሞ እሱ ራሱ ኃጢአተኛ ነውና ፤ ስለኃጢአቱ ስለ ጥንተ አብሶው ለራሱ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ስለ ሕዝቡ ሥርዬተ ኃጢአት የሚሆነውን መሥዋዕት አርዶ አወራርዶ ፤ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ስለ ሕዝቡ ኃጢአትም ይለምናል፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርበትም ነገር ግን ሕግን ለመፈጸም ነውና የመጣው እንደ ብሉዩ ሥርዓት ኃጢአት ሳይኖርበት ወይም ኃጢአተኛ ሳይሆን የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል ፤ ይህም ያለ ኃጢአት የሚቀርበው ጸሎቱና መሥዋዕቱ የሁሉ ነገር መዝጊያና ማብቂያ ነው፤ የአዳምና የልጆቹ የነቢያት እንባቸው ፤ኀዘናቸውና ትካዜያቸው ማብቂያ የሚያገኘው በጌታ እንባ፤ኀዘንና ትካዜ ነው፤ጸሎታቸው የሚታተመው በጌታ እንባ ጸሎት ነው፤የካህናቱ መሥዋዕታቸውና አገልግሎታቸው የሚታተመው በጌታ አገልግሎትና መሥዋዕት ነው፤ በአጠቃላይም የብሉይ ኪዳኑ አስተምሕሮ የሚጠናቀቀው በጌታ አስተምሕሮ ነው፡፡ የነቢያት አስተምሕሮ "በዘመንየኑ ትፌኑ ወልደከ…."፤ "አንሥእ ኃይለከ ፤ፈኑ እዴከ፤ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት፤ወነዓ አድኅነነ፣ ፍጡነ ይርከበ ሣህልከ እግዚኦ፤እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤አድኅነነ ወባልሐነ……" (መዝ 78÷8) እያሉ ነበር፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጊዜው ደርሷል" ብሎ ነው የሚጀምረው ይኸውም የመዳን ዘመን ምሕረት የተደረገበት ዓመት መሆኑን ለማጠየቅ ነው “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤”   — ገላትያ 4፥4 አምላካችን ለሁላችንም ምሕረቱን ቸርነቱን አያጉድልብን መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል ከ ኖርዌይ ኦስሎ
1140Loading...
10
Media files
1020Loading...
11
ቅዳሜ - ቅዱሳት አንስት፤ “የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው፤” እንዲል:- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ:-ከተከተሉት አምስት ገበያ ሕዝብ መካከል የመረጠው አንድ መቶ ሃያውን ቤተሰብ ብቻ ነው። እነርሱም:-፩ኛ/፲፪ቱ ሐዋርያት፤ ፪ኛ/፸፪ ቱ አርድዕት፤ ፫ኛ/፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት (የተቀደሱ ሴቶች) ናቸው። በመሆኑም የዛሬዋ ከትንሣኤ በኋላ ያለች ቅዳሜ የቅዱሳት አንስት መታሰቢያ ናት።በረከታቸው ይደር ብን። የ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ስም ዝርዝርና የመታሰቢያ ቀናቸው:- ፩ኛ:-ቅ.ኤልሳቤጥ - የካቲት ፲፮፤ ፪ኛ:-ቅ.ሐና - መስከረም ፯፤ ፫ኛ:-ቅ.ቤርዜዳን ወይም ቤርስት - ታኅሣሥ ፲፤ ፬ኛ:-ቅ.መልቲዳን ወይም ማርና - ጥር 4፤ ፭ኛ:-ቅ.ሰሎሜ። - ግንቦት 25፤ ፮ኛ:-ቅ.ማርያም መግደላዊት - ነሐሴ 6፤ ፯ኛ:-ቅ.ማርያም እንተ እፍረት እኅተ አልዓዛር የካቲት ፮፤ ፰ኛ:-ቅ.ሐና ነቢይት - የካቲት ፳ እና ጥቅምት ፮፤ ፱ኛ:-ቅ.ማርያም እሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ ጥር ፲፰፤ ፲ኛ:-ቅ.ሶፍያ (በርበራ) - ጥር ፴፤ ፲፩:-ቅ.ዮልያና (ዮና) - ኅዳር ፲፰፤ ፲፪:-ቅ.ሶፍያ (መርኬዛ) - ጥር ፴፤ ፲፫:-ቅ.አውጋንያን (ጲላግያ) - ጥቅምት ፲፩፤ ፲፬:-ቅ.አርሴማ - ግንቦት ፲፩፤ ፲፭:-ቅ.ዮስቲና - ጥር ፴፤ ፲፮:-ቅ.ጤግላ - ነሐሴ ፮፤ ፲፯:-ቅ.አርኒ (ሶፍያ) - ኅዳር ፲፤ ፲፰:-እሌኒ - ጥር ፳፱፤ ፲፱:-ቅ.ኢዮጰራቅሊያ -መጋቢት ፳፮ እና ነሐሴ ፪፤ ፳:-ቅ.ቴዎክላ (ቴኦድራ) - ጥር ፬፤ ፳፩:-ቅ.ክርስቲያና (አጥሩኒስ) - ኅዳር ፲፰፤ ፳፪:-ቅ.ጥቅሞላ (አሞና) - ጥር ፴፤ ፳፫:-ቅ.ጲስ። - ጥር ፴፤ ፳፬:-ቅ.አላጲስ - ጥር ፴፤ ፳፭:-ቅ.አጋጲስ - ጥር ፴፤ ፳፮:-ቅ.እርሶንያ (አርኒ) - ጥር ፴፤ ፳፯:-ቅ.ጲላግያ - ጥር ፴ እና ጥቅምት ፲፩፤ ፳፰:-ቅ.አንጦልያ (ሉክያ) - የካቲት ፳፭፤ ፳፱:-ቅ.አሞን (ሶፍያ) - ጥር ፲፭ አና ነሐሴ ፫፤ ፴:-ቅ.ኢየሉጣ - ነሐሴ ፮፤ ፴፩:-ቅ.መሪና - ሐምሌ ፳፯፤ ፴፪:-ቅ.ማርታ እኅተ አልዓዛር-ጥር ፲፰ እና ግንቦት፳፯፤ ፴፫:-ቅ.ማርያም የማርቆስ እናት - ጥር ፴፤ ፴፬:-ቅ.ሣራ (ሶፍያ) የይሁዳ እናት - ጥር ፴፤ ፴፭:-ቅ.ዮሐና (ዮላና) የኩዛ ሚስት - ታኅሣሥ ፳፮፤ ፴፮:-ቅ.ሶስና - ግንቦት ፲፪፤
1160Loading...
12
Media files
990Loading...
13
☞ከትንሳኤ በኃላ ያለቸው 6ኛ ቀን ቀዳሚ ሰንበት "ቅዱሳን አንስት"ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ☞በዚህ ዕለት የክርስቶስን አካል ሽቶ በመቀባት ፍርሃተቸውን በክርስቶስ ፍቅር ለውጠው በጋለ ፍቅር አካሉን መፈለጋቸውን ወደ መቃብሩ መገስገሳቸውን፡፡ ☞ቅዱሳን ሐዋርያት በአገልግሎት ማገዛቸውን፤ መራዳታቸውን፤ ማገልገላቸውን፡፡ ☞የክርስቶስን ትንሣኤ ቀድመው ስለማየታቸው በማሰብ ቤተክርስቲያን ይህችን ቀን"ቅዱሳን አንስት"በማለት ሰይማለች፡፡ ☞ከሳምንቱ በመጀመሪያ በእሑድ ሰንበት መቅደላዊት ማርያም ወደ መቃብሩ መጣች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች፡፡ ☞እየሮጠችም ወደ ስምዖን ጴጥሮስ ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር መጥታ ጌታን ከመቃብር ወሰደውታል ወዴትም እንዳኖሩትት አናውቅም አለቻቸው፡፡ ሰለዚህ፡ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወጥተው ወደ መቃብሩ ሄዱ፡፡ ሁለቱም አብረው ሮጡ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ፡፡ ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ ነገር ግን አልገባም፡፡ ☞ስምዖን ጴጥሮስም ተከተሎት መጣ ወደ መቃብሩም ገባ የተልባ እግሩ ልብስ ረየ ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በእንድ ስፍራ ተጠምጥጥሞ እንደነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳ ነበር አየ፡፡ ☞በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደ መቃብሮ የመጣውም ሌላው ደቀ መዝሙር ገቤ አየም፤ አመነም፤ ከሙታን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፍን ቃል ገና አላወቁም ነበር፡፡ ☞.ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቤታቸው ደግሞ ሄዱ፡፡ ☞ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር፡፡ ስታለቅስም ወደ መቃብርም ዝቅ ብላ ተመለከተች ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላው በእግርጌ ተቀምጠው አየች፡፡ ☞እነሱም አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ? አሉአት፡፡ እርስዎም ጌታዬን ወስውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው፡፡ ☞ይህንም ብላ ወደ ኃላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ኢየሱስም እንደ ሆነ አላወቅችም፡፡ ☞ኢየሱስም አንቺ ሴት ስለምን ታላቅሻለሽ?ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት ጌታ ሆይ አንተ ወሰደኸው እንደሆነ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም ወሰጄ ሽቱ እንድቀባው አለችው፡፡ ☞ኢየሱስም ማርያም አላት እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ "ረቡኒ አለችው ትርጓሜውም መምህር ሆይ ማለት ነው፡፡ ☞ኢየሱስም ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው አላት፡፡ ☞መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታ እንዳየች ይህንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች፡፡(ዮሐ20-1-18) ☞መልካም ቀዳሚ ሰንበት ይሁንላችሁ፡፡
1160Loading...
14
Media files
940Loading...
15
Media files
1270Loading...
16
ዐርብ፡- ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም ተዋጅታ ለተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዐርብ ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትጠራለች፡፡ ማቴ.26-26-29, የሐ. ሥራ. 20-28 ይህች ዕለት ሦስት ስያሜዎች አሏት፡፡ ይኸውም፡- 1.ተጽዒኖ፡- አንደኛው ከሆሳዕና ቅዳሜ በፊት ያለችው ዐርብ የጌታችን ጾም የሚፈጸምባት፤ የጾመ ድጓው ቁመትም የሚያበቃባት፣ በመሆኗ በቤተ ክርስተያን ተጽዒኖ ስትባል፤ በሕዝቡም ዘንድ በሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤው ከባዱን ሥራ ስለሚያቆምባት የወፍጮ መድፊያ፣ የቀንበር መስቀያ ትባላለች፡፡ 2.አማናዊቷ ዐርብ፡- ሁለተኛውም በመጀመሪያ የሰው አባትና እናት አዳምና ሔዋን ስለተፈጠሩባት፣ ኋላም በሐዲስ ኪዳን ጌታችን ለቤዛ ዓለም መከራ ተቀብሎ ስለተሰቀለባትና የማዳን ሥራውን ስለፈጸመባት ዕለተ ስቅለት አማናዊቷ ዐርብ ትባላለች፡፡ 3.ቤተ ክርስቲያን፡- ሦስተኛው በሰሙነ ትንሣኤው ያለችው ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች ማለት ነው፡፡
1100Loading...
17
☞እንኳን አደረሰን ከትንሳኤ በኃላ ያለው ዓርብ"ቅድስት ቤተክርስቲያን" ተብላ ተሰይማለች፡፡⛪ ⛪ከደጀ ሰላሙ አያርቀን🙏❤
1150Loading...
18
እንኳን አደረሳችሁ ለአባታችን አዳም በሀገራችን የአባታችን አዳም በአመት አንድ ጊዜ የሚነግሰው በደብረ ሰዋሰው አደሬ ኪዳነ ምህረት ገዳም ብቻ ነው ቦታው ከአዲስ አበባ 57 ኪሎ ሜትር ገዳሟ ዛሬ አባታችን አዳምን እናታችን ልደታ ማርያም ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጠው ተባርከናል የአመት ሰው ይበለን አሜን
1100Loading...
19
Media files
870Loading...
20
አዳም - ሐሙስ፤ ከትንሣኤ በኋላ የምትገኘው ዕለተ ሐሙስ የአዳም የመታሰቢያ ዕለት ናት።አዳም በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣቱን፥ከዘለዓለማዊ ሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት መሸጋገሩን፥ከተፈረደበት ስፍራ ከሲኦል ወደ ጥንተ ርስቱ ወደ ገነት መመለሱን የምናስብባት ዕለት ናት። አዳም ከአምስት ሺ አምስት መቶ ዓመት ዓመተ ፍዳ እና ዓመተ ኩነኔ በኋላ ይህቺን ዕለት ዓመተ ምሕረትን ያገኘው በብዙ ዕንባ ነው።መቅድመ ወንጌል:-“አልቦቱ ካልዕ ኅሊና ለአዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ።አዳም በኃጢአቱ ምክንያት በመጣበት ብድ ራት (በተፈረደበት ፍርድ) ከማልቀስ በስተቀር ሌላ ኅሊና አልነበረውም።”ይላል።ከዚህ በኋላ ነው ያ በገ ነት ሲመላለስ የሰማው የእግዚአብሔር ድምፅ (አካላዊ ቃል) “አምስት ቀን ተኩል (አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ) ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ (ከድንግል ማር ያም) ተወልጄ አድንሃለሁ።”ያለው።የተናገረውንም ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በመቀበል በዕለተ ዓርብ ፈጽሞታል። ከአባታችንከቀዳማዊ አዳም ስለ ኃጢአት ማልቀስን፥ማንባትን፤ከዳግማዊ አዳም ከኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰለ ሌላው ተላልፎ መሞትን ልንማር ይገባል። አዳም በመልዕልተ መስቀል ዋጋ ከተከፈለለት በኋላ ጻድቅ ነው፥በመሆኑም በረከቱ ይደርብን።
860Loading...
21
Media files
790Loading...
22
የእግዚአብሔር ሰው ሰሎሞን ለአምላኩ ሕንፃ መቅደስን ሊያንጽ በተነሣ ጊዜ ፤ "በጥበብና በማስተዋል በብልሃትም የተሞላ" የናሱን ሠራተኛ ኪራምን ከጢሮስ አስመጥቶ ነበር። ከዚህም ጥበበኛ ጋር ሆኖ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መቅደስ በታላቅ ጥንቃቄ አንጿል። በእውነት ይህን ሰሎሞን ያሳነጸውን ውብ መቅደስ ማየት ምንኛ ያጓጓ ይሆን? በእርግጥም መቅደሱንና የመሥዋዕቱን ሥርዓት የተመለከተች ንግሥተ አዜብ ማክዳ "ነፍስ አልቀረላትም" ነበር (1ኛ ነገ 10:5)። ሆኖም ግን እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ አድሮ "ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?" ብሎ መጠየቁ አልቀረም (ኢሳ 66:48)። ለጊዜው በረድኤት የሚያድርበትን መቅደስ ንጉሥ ሰሎሞን ውብ አድርጎ ቢያንጽለትም ፤ በኋላ ግን የሰውን ልጆች ለመቤዠት በአካል የሚያድርበትን ሕያው መቅደስ ማንም ማዘጋጀት አልቻለም ነበር። ስለዚህም "ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም" ተብሎ ተጻፈ (ሐዋ 7:50)። በመሆኑም መቅደሱን ላነጹ ለሰሎሞን እና ለኪራም ጥበብን የሰጠው ጥበበኛ "ለራሱን ቤት ሊሠራ ፣ሰባት ምሰሶዎችንም ሊያቆም" ፈቃዱ ሆነ። የመቅደሱንም መሠረት እንቁ አደረገ። ቤቱንም እጅግ በከበሩ ድንጊያዎች አነጸ። ይህች በአምላክ እጅ የታነጸች ፣እግዚአብሔር በረድኤት ሳይሆን በአካል የሚያድርባት ሕያው መቅደሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የተመሠረተችባቸውም አዕናቁ (እንቁዎች) ቅዱሳን ቤተሰቦቿ ናቸው። የታነጸችበትም የከበሩ ድንጊያዎች ንጽሕና ፣ቅድስና ናቸው። "ይህች ዓለም አይቶ የማያውቃት በተስፋ ትጠበቅ የነበረችው ድንቅ አማናዊት መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ የታየችው በዛሬው ቀን ነበር" ኪራም ያነጸው የሰሎሞንን መቅደስ መጎብኘት "ነፍስ የማያስቀር" ፣ልብን በሐሴት የሚሞላ ከሆነ ፤ በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ፣የአምላክ ጥበብ የፈሰሰባት እውነተኛ መቅደሱን የእመቤታችንን መወለድ የማየትና የመስማት የደስታ ጥጉ ምን ያህል ይሆን? እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን
790Loading...
23
ልደታ ለማርያም እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሰን!!! ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡ የተመረጠች ክብርት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በከበረች ቀን ግንቦት አንድ ቀን ተወለደች፡፡ የመወለዷም ነገር እንዲህ ነው፡፡ በጥሪቃና ቴክታ የተባሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ነበሩ፤ ባለጸጎች ቢሆንም ልጅ ግን አልነበራቸውም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ቴክታ ሕልም አለመች፡፡ ለባሏም እንዲህ ስትል ነገረችው «በራእይ ነጭ ዕንቦሳ ከማሕፀኔ ስትወጣ፤ ያችም ዕንቦሳን እየወለደች እስከ ፮ ትውልድ ስትደርስ ፮ኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ደግሞ ፀሐይን ስትወልድ አየሁ» አለችው፡፡ (ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ)          ባሏ በጥሪቃም «ራእዩስ ደግ ነው፤ የሚፈታልን የለም እንጂ» አላት፡፡ በማግሥቱ ለሕልም ፈቺ ሔዶ ነገረው፡፡ ሕልም ፈቺውም «እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል፤ በሣህሉ መግቧችኋል» ብሎ ፮ቱ እንስት ጥጆች መውለዳቸው ፯ ሴቶች ልጆች እንደሚወልዱ፤ ፯ኛይቱ በጨረቃ መመሰሏ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት እንደሚወለዱ፤ የፀሐይ ነገር ግን እንደንጉሥ ያለ ይሆናል አልተገለጸልኝም ብሎ ነገረው፡፡ (ነገረ ማርያም)   🌷ሰላም እደሩ🤲☦
911Loading...
24
Media files
1070Loading...
25
ረቡዕ - አልዓዛር፤ ከትንሣኤ እሑድ በኋላ ያለችው ረቡዕ የአልዓዛር መታ ሰቢያ ናት።አልዓዛር በሞተ በአራተኛው ቀን ጌታ ከሞት ያስነሣው የእርሱ ወዳጅ ነው።እኅቶቹም የጌታ አገልጋዮች ማርታ እና ማርያም ናቸው። ፩ ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢታንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር። ፪ ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። ፫ ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ። ፬ ኢየሱስም ሰምቶ፥ይህ ሕመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ። ፭ ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን አልዓዛርንም ይወድ ነበር። ፮ እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ፤ ፯ ከዚህም በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ:-ወደ ይሁዳ ደግሞ እንሂድ አላቸው። ፰ ደቀ መዛሙርቱ:-መምህር ሆይ፥ አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፥ ደግሞም ወደዚያ ትሄዳለህን? አሉት። ፱ ኢየሱስም መልሶ:-ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ ፲ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል አላቸው። ፲፩ ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ:-ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው። ፲፪ እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ:-ጌታ ሆይ፥ ተኝቶስ እንደ ሆነ ይድናል አሉት። ፲፫ ኢየሱስስ ስለ ሞቱ ተናግሮ ነበር፤ እነርሱ ግን ስለ እንቅልፍ መተኛት እንደ ተናገረ መሰላቸው። ፲፬ እንግዲህ ያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጥ አልዓዛር ሞተ፤ ፲፭ እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ አላቸው። ፲፮ ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት:-ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ። ፲፯ ኢየሱስም በመጣ ጊዜ በመቃብር እስከ አሁን አራት ቀን ሆኖት አገኘው። ፲፰ ቢታንያም አሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ለኢየሩ ሳሌም ቅርብ ነበረች። ፲፱ ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑ አቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር። ፳ ማርታም ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ ልትቀ በለው ወጣች፤ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር። ፳፩ ማርታም ኢየሱስን:-ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤ ፳፪ አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው። ፳፫ ኢየሱስም:-ወንድምሽ ይነሣል አላት። ፳፬ ማርታም። በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲ ነሣ አውቃለሁ አለችው። ፳፭ ኢየሱስም:-ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያም ንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ፳፮ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት። ፳፯ እርስዋም:-አዎን ጌታ ሆይ፥አንተ ወደ ዓለም የሚ መጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው። ፳፰ ይህንም ብላ ሄደች፤እኅትዋንም ማርያምን በስ ውር ጠርታ:-መምህሩ መጥቶአል፥ይጠራሽማል አለ ቻት። ፳፱ እርስዋም በሰማች ጊዜ ፈጥና ተነሣች፥ወደ እርሱም መጣች፤ ፴ ኢየሱስም ማርታ በተቀበለችበት ስፍራ ነበረ እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር። ፴፩ ሲያጽናኑአት ከእርስዋ ጋር በቤት የነበሩ አይሁ ድም ማርያም ፈጥና እንደ ተነሣችና እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ:-ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሎአ ቸው ተከተሉአት። ፴፪ ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ:-ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር አለችው። ፴፫ ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመ ጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ፥በራ ሱም ታወከ፤ ፴፬ ወዴት አኖራችሁት? አለም፤እነርሱም:-ጌታ ሆይ፥ መጥተህ እይ አሉት። ፴፭ ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ። ፴፮ ስለዚህ አይሁድ:-እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ አሉ። ፴፯ ከእነርሱ ግን አንዳንዶቹ:-ይህ የዕውሩን ዓይኖች የከፈተ ይህን ደግሞ እንዳይሞት ያደርግ ዘንድ ባልቻ ለም ነበርን? አሉ። ፴፰ ኢየሱስም በራሱ አዝኖ ወደ መቃብሩ መጣ፤ እር ሱም ዋሻ ነበረ፤ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር። ፴፱ ኢየሱስ:-ድንጋዩን አንሡ አለ፤የሞተውም እኅት ማርታ:-ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው። ፵ ኢየሱስ:-ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እን ድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት። ፵፩ ድንጋዩንም አነሡት፤ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ:-አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ፵፪ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። ፵፫ ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ:-አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ። ፵፬ የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር።ኢየሱስም:-ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው። በዚህ ተአምር ውስጥ የእያንዳንዱ ድርሻ ምን ነበር? ፩ኛ/የአልዓዛር ድርሻ ከመሞቱ በፊት የጌታ ወዳጅ መሆኑ ነበር።ይህ ወዳጅነቱ ነው የጌታን ዕንባ እንዲ ፈስ ያደረገው።በታመመ ጊዜም “ብሞትም እርሱ ሊያ ድነኝ ይችላል፤”የሚል እምነት በውስጡ ነበረ።ሌላው አስደናቂ ነገር ደግሞ ለጌታ በሕይወቱ ሳለ ይታዘዘው እንደ ነበር በሞቱም በመቃብር ሆኖ መታዘዙ ነው። ምክንያቱም “ከመቃብር ውጣ፤”ባለው ጊዜ “እሺ በጀ ፤”ብሎ ከመቃብር ወጥቶአልና ነው።ልክ እንደዚህ የእርሱ ወዳጆች በአጸደ ሥጋም በአጸደ ነፍስም የእ ርሱ ናቸው።ከዚህ አንፃር ከእኛ የሚጠበቀው በንስሐ ከኃጢአት መቃብር መውጣት ነው። ፪ኛ/እኅቶቹ ማርታና ማርያም የነበራቸው ድርሻ በሰማ ይም በምድርም ብድራትን የሚከፍል የጌታ ወዳጆችና አገልጋዮች መሆናቸው ነው።ለጊዜው ለትንሣኤ ሙታን በመቃብር ያሉትን ሁሉ ማስነሣት የሚችል አምላክ ዛሬም ማስነሣት እንደሚችል ባያስተውሉም በትንሣኤ ሙታን ማመናቸው ትልቅ ነገር ነበር።ለወን ድማቸው የነበራቸውም ፍጹም ፍቅር በራሱ በጌታ ዘንድ ዋጋ ነበረው።ከዚህ አንፃር እኛም በእርሱ ዘንድ ዋጋ ያለው ፍጹም ፍቅር ለወገኖቻችን ይኑረን።ከዚ ህም ከፍ ብለን የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታ ችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጆች እንሁን።በአለን፥በተ ሰጠን ነገር እናገልግለው።ያን ጊዜ ሞተው የተቀበሩት ሰላምና ፍቅር ከመቃብር ይወጣሉ።ነገ ሳይሆን ዛሬ ይነሣሉ። ፫ኛ/የለቀስተኞቹ ድርሻ ክርስቶስ እንዳዘዘ በአልዓዛር መቃብር አፍ የተገጠመውን ደንጊያ ታግሎ ማንሣት ነበር፥አደረጉት።ከእኛም የሚጠበቀው በውስጣችን ሞተው የተቀበሩት እምነት፥ፍቅርና ሰላም ሕያዋን እንዲሆኑ እንደ ደንጊያ የከበደውን ኃጢአታችንን በንስሐ ልናነሣው ይገባል። ፬ኛ/የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ድርሻ ወደ ልቅሶ ቤት መጥቶ ሐዘንተኞችን ማጽና ናት፥ዕንባውን በማፍሰስ ፍቅሩን መግለጥ፥ እስከ መቃብሩ መጓዝ፥ቢሸትም መቃብሩን ማስከፈት ፥በመጨረሻም አልዓዛርን ማስነሣት ነበር፥አደረገው ።እንግዲህ ክርስትና ማለት ክርስቶስን መምሰል ስለ ሆነ ለበጎ ምግባራት ሁሉ እርሱን አብነት ልናደርግ ይገባል።
1010Loading...
26
፭ኛ/የደቀ መዛሙርቱ ድርሻ በመግነዝ እንደ ታሰረ ከመቃብር የወጣውን አልዓዛርን መፍታት ነበር። ይህም የካህናትን ድርሻ ያመለክታል።በመሆኑም ከቅ ዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ “በምድር ያሰራችሁት በሰ ማይ የታሰረ፥በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”በተባለው መሠረት:-ምእመናንን በትምህ ርታችን፥በምክራችን እና በተግሣፃችን ለንስሐ አብቅ ተን ከኃጢአት እስራት ልንፈታቸው ይገባል።ያን ጊዜ አልዓዛር ከእስራት ተፈቶ እንደ ተመላለሰ፥እነርሱም በብርሃነ ጽድቅ የሚመላለሱ የብርሃን ልጆች ይሆናሉ ።
1020Loading...
27
"ክንፎቻቸው የእሳት ነበልባል የሆኑ ቅዱሳን መላእክት ሱራፌል እና ኪሩቤል ኃይልን ታምራትን የምታደርግ ቅዱስ ማርቆስ ሆይ እያሉ ሊቀበሉህ ወረዱ" 🌷ሚያዝያ 30 የቅዱስ ማርቆስ በዓለ ዕረፍቱ ነው በረከቱ ይደርብን🤲 🌷እንደምን አደረሳችሁ🌹
950Loading...
Show all...
የወልታ ጽድቅ ዘተዋሕዶ ዓለም አቀፍ የመነኮሳት ጉባኤ የአቋም መግለጫ::

የወልታ ጽድቅ ዘተዋሕዶ ዓለም አቀፍ የመነኮሳት ጉባኤ የአቋም መግለጫ:: Wolta Tsdik zeTewahedo Global Monks Assembly - Official Statement

Photo unavailableShow in Telegram
ቅድስት ኪዳነ ምህረት እናቴ 16♥️🎚️ እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡ የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፡የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘው የደህንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ እኮ ነሽ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኃዘን ከገነት በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኃዘን ተረጋግቶብሻልና፡፡ (መልክአ ኪዳነ ምህረት) ኪዳነ ምህረት እኛንም ከሀዘን ከመከራ ታውጣን🙏 ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን አሜን!!🙏
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቅድስት ኪዳነ ምህረት እናቴ 16♥️🎚️ እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ፤ በብርሃናዊው ኮከብ ለተመሰለው ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፤ በጨለማ ለሚኖሩ ሕዝቦች ብርሃኑን አብርቶላቸዋልና፡፡ የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፡የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘው የደህንነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ እኮ ነሽ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቅና በኃዘን ከገነት በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኃዘን ተረጋግቶብሻልና፡፡ (መልክአ ኪዳነ ምህረት) ኪዳነ ምህረት እኛንም ከሀዘን ከመከራ ታውጣን🙏 ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን አሜን!!🙏
Show all...
#ለእናታችን #ቅድስት #ክርስቶስ #ሠምራ #ጌታችን #አምላካችንና #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #የተሰጣት #ቃል #ኪዳን! (ዛሬ ግንቦት 12 ቀን ቃል-ኪዳን የተቀበለችበት ዕለት ነው!) 👉"እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ" - ዘዳ. 7፥9 👉"የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል" - መዝ. 111 (112)፥6 “እውነት በእውነት እልሻለሁ ወይም እነግርሻለሁ በፍጹም ደስታ መታሰቢያሽን ያደረገ በመንግስተ ሰማያት አስደስተዋለሁ። በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን ስምሽን ቢጠራ እኔ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ። የገድልሽን ዜና የሚናገረውን መጽሐፍ የጻፈ ወይም ያጻፈ እኔ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፍላቸዋለሁ። ቤተ ክርስቲያንሽን የሠራ ወይም ያሠራ ያሳነጸ ወይም ያነጸ እኔ በመንግስተ ሰማያት ንጹሕ አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ። በስምሽ ለተራበ ያበላ እኔ በዕለተ ዓርብ ከተቆረሰው ሥጋዬ አበላዋለሁ። በስምሽ ለተጠማው እፍኝ ውኀ ያጠጣ እኔ በዕለተ ዓርብ ከጎኔ በፈሰሰው ደሜ አረካዋለሁ። በዓልሽ በሚከበርበት ዕለት ጧፍ ዕጣን ወይም ዘይት ንጹሕ ሥንዴ የመሰለውንም ሁሉ መባ ያገባ መሥዋዕቱን እንደ አብርሃምና እንደ መልከጼዴቅ መሥዋዕት አድርጌ እቀበልለታለሁ። አላት። ...አቤቱ እንዲህ ከሆነ መታሰቢያዬን እያደረገ ስሜን እየጠራ በስሜ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚቀበረውን እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ አለችው። እስከ ዓሥር ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ አላት። ይህንም ቃል ኪዳን በተሰጣት ጊዜ ፈጽማ ተደሰተች። ...እውነት እውነት እልሻለሁ ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሣለመ ይቆጠርላታል። እውነት እውነት እልሻለሁ አንቺን ያከበረ ሁሉ እኔ በሰማያዊ መንግሥቴ አከብረዋለሁ። ...ስለዚህ አንቺን የሚያከብሩ ሁሉ አንቺ ካለሽበት ቦታ ገብተው ካንቺ ጋር ይደሰታሉ። ከዚህም አምላካዊ ቃል ጋር በነሐሴ ሃያ አራት ቀን የአባታችን የተክለ ሃይማኖት በዓል በሚከበርበት ዕለት ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለየች።” ምንጭ፦ ገድለ ክርስቶስ ሠምራ፤ ዘነሐሴ፤ ገጽ 152 -157 ቁጥር 11-17፣ 23-25፣ 31-32፣ 44-45፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤1992 ዓ.ም፤ አዲስ አባባ
Show all...
👏 1
ቅዱስ ጴጥሮስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚለውን የትንሣኤውን ጌታ ድምጽ ከሰማ ፣ የተጠራጠረው ቶማስ እጁን በጎኖቹ አግብቶ “ጌታዬ አምላኬ” ብሎ ሲያምን ከተመለከተ በኋላ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” ብሎ ሲናገር እናገኘዋለን።(ዮሐ 21፥3) ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት በሐሙስ ምሽት ከእሳት ዳር ተቀምጦ ያደረገውን ሊረሳውና ራሱን ይቅር ሊል ስላልቻለ፣ ጌታው ቀድሞ የሰጠውን የወንጌል መረብ ተወና የዓሣውን መረብ ጨብጦ ወደ ገሊላ ባሕር ሮጠ።(ማቴ 4፥19) በኃጢአት ምክንያት የተሰማው ኃፍረትና መሸማቀቅ ሐዋርያነቱን ትቶ በድሮ ማንነቱ ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ አደረገው። የካደን ማን ለምስክርነት ይፈልገዋል በሚል ዓይነት ስሜት ለወንድሞቹ  “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። ደስ የሚለው ነገር ግን ይህን አስቀድሞ የሚያውቅ ይቅር ባይ አምላኩ ጴጥሮስን “በገሊላ ቀድሞት ነበር”። በበደሉ ተሸማቆ የተወውን ሐዋርያነት ሥልጣን በፍቅሩ መማለጃነት መልሶ ሊሰጠው፣ አይገባኝም ብሎ ያስቀመጠውን የወንጌል መረብ ዳግመኛ ሊያሲዘው በገሊላ ባሕር ዳር ቀደመው። እኛም አንድ ኃጢአት ይኖረናል። መርሳት ያልቻልነው፣ ንስሐ እንኳን ብንገባበት ራሳችንን ይቅር ለማለት የተቸገርንበት፣ “ከዚህ በኋላማ...” እያሰኘ የድሮ መረብ አስይዞ ወደ ገሊላ የሚመልስ አንድ በደል ይኖረናል። ነገር ግን ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው ለእኛም እንዲሁ ያደርጋል። ከባሕሩ ዳር ይጠብቀናል፣ “ትወደኛለህ” ብሎ ይጠይቀናል፣ ከዚያ በማይለወጥ ፍቅሩ ወልውሎ ሰንግሎ አፍረን ወደ ሸሸነው መንፈሳዊነት ይመልሰናል። +++ ጌታችን በገሊላ ይቀድመናል! +++
Show all...
👍 1
+ የሚሮጥ ዲያቆን + የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ:: በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው:: እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር:: በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ:: ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣ ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው:: አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ? ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው:: ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ? ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ዲበ ሠረገላ ሰማይ ለኢጃት ዲያቆናት ሲመት ግንቦት 6 2016 ዓ.ም.
Show all...
#እንኳን_ለዳግማይ_ትንሣኤ_አደረሳችሁ! #አግብኦተ_ግብር ፤ #ዳግማይ_ትንሣኤ የቴሌግራም ቻናሌ 👇 https://t.me/MoaeTewahedoB "ጊዜው ደረሰ" ዮሐ 17÷1 ✝ዳግማይ ትንሣኤ እና አግብኦተ ግብር፡- ለሐዋርያት በጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ቶማስ ባለበት የተገለጠበት ቀን ስለሆነ ዳግማይ ይባላል እንጂ ትንሣኤው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ✝ ዳግማይ ትንሣኤ ከመባሉ በተጨማሪ በሊቃውንት ምሥጢራዊ አጠራር "አግብኦተ ግብር" ይባላል፤ ቀጥታ ትርጉሙ "ሥራን መመለስ" ማለት ነው፤ ምሥጢሩ ግን "ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" ብሎ እንዲያመጣው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥጋ የለበሰበትን ዓላማ በመስቀል የሚያጠናቅቅበት ጊዜው መድረሱን የሚያሳይ ነው፤መስቀሉ ላይ "ተፈጸመ ኩሉ" ብሎ መጮኹም የዚሁ የመጨረሻ ክፍል ነው፡፡ ✝በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ የዮሐንሰ ወንጌል 17÷1-ፍጻሜ ድረስ ሙሉው ይነበባል፡፡ በዓሉ የጸሎተ ሐሙስ ሲሆን በዕለቱ ብዙ የተደራረቡ በዓላት በመኖራቸው ምክንያት "አግብኦተ ግብሩ" ከዳግማይ ትንሣኤ ተደርቦ ይታሰባል፡፡ ✝የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 17 ሙሉው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነው፡፡ ✝ይህም ጸሎቱ እንደ ብሉዩ ሊቀ ካህናት የኃጢአት መሥዋዕትን ተክቶ የቀረበ ጸሎት ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ የካህናት አለቃ ለሕዝቡ የኃጢአት ሥርዬት የሚሆነውን መሥዋዕት ከማቅረቡ አስቀድሞ እሱ ራሱ ኃጢአተኛ ነውና ፤ ስለኃጢአቱ ስለ ጥንተ አብሶው ለራሱ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ስለ ሕዝቡ ሥርዬተ ኃጢአት የሚሆነውን መሥዋዕት አርዶ አወራርዶ ፤ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ስለ ሕዝቡ ኃጢአትም ይለምናል፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርበትም ነገር ግን ሕግን ለመፈጸም ነውና የመጣው እንደ ብሉዩ ሥርዓት ኃጢአት ሳይኖርበት ወይም ኃጢአተኛ ሳይሆን የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል ፤ ይህም ያለ ኃጢአት የሚቀርበው ጸሎቱና መሥዋዕቱ የሁሉ ነገር መዝጊያና ማብቂያ ነው፤ የአዳምና የልጆቹ የነቢያት እንባቸው ፤ኀዘናቸውና ትካዜያቸው ማብቂያ የሚያገኘው በጌታ እንባ፤ኀዘንና ትካዜ ነው፤ጸሎታቸው የሚታተመው በጌታ እንባ ጸሎት ነው፤የካህናቱ መሥዋዕታቸውና አገልግሎታቸው የሚታተመው በጌታ አገልግሎትና መሥዋዕት ነው፤ በአጠቃላይም የብሉይ ኪዳኑ አስተምሕሮ የሚጠናቀቀው በጌታ አስተምሕሮ ነው፡፡ የነቢያት አስተምሕሮ "በዘመንየኑ ትፌኑ ወልደከ…."፤ "አንሥእ ኃይለከ ፤ፈኑ እዴከ፤ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት፤ወነዓ አድኅነነ፣ ፍጡነ ይርከበ ሣህልከ እግዚኦ፤እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤አድኅነነ ወባልሐነ……" (መዝ 78÷8) እያሉ ነበር፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጊዜው ደርሷል" ብሎ ነው የሚጀምረው ይኸውም የመዳን ዘመን ምሕረት የተደረገበት ዓመት መሆኑን ለማጠየቅ ነው “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤”   — ገላትያ 4፥4 አምላካችን ለሁላችንም ምሕረቱን ቸርነቱን አያጉድልብን መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል ከ ኖርዌይ ኦስሎ
Show all...
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። "

https://t.me/MoaeTewahedoB

አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014