cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዲን ምክክር ነው

//طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ// ‘ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው።’ (("الدين النصيحة"، قلنا: لمن يا رسول الله؟ قال:" لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم")). joinand share via link t.me//nesihaa ለአስተያየት @nesihaabot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
925
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የውሸት ውዴታ! 🔅በየአመቱ ረቢዕ አል-አወል ወር በመጣ ቁጥር ነቢዩን ﷺ  እንወዳለን የሚሉ ሰዎች ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ሲፈጥሩ እያየን ነው!። 🔅ነቢዩን ﷺ መውደድ ወደ አላህ የሚያቃርብ ዒባዳህ እንደሆነ ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። 🔅ታድያ ወደ አላህ የሚያቃርብ ዒባዳህ ሰዎች ተስማምተው እንዳወጡት ምድራዊ ህግ በየጊዜው ሊሻሻልና ሊቀያይር ይችላልን? ☄አላህ በተከበረው ቃሉ {ٱلۡیَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمْ...} المائدة ٣ "ዛሬ ዲኑን ሞላሁላችሁ" የማለቱ ትርጉምና ጥቅምስ ምንድነው ታድያ?! 🔅በነቢዩ ﷺ ውዴታ ስም እሳቸውም ይሁን ሰሓባዎቻቸው ያልሰሩትን የሚሰሩ ሰዎች ከመውሊድ ጋር አያይዘው የሚፈጽሟቸው እጅግ በጣም ከሱናህ የራቁ ተግባሮቻቸውን የዲኑ አካል ናቸው ካሉ ከላይ ከተጠቀሰው የሱረቱል-ማኢዳህ አንቀጽ 3 ጋር ይጋጫል!። 🔅የዲን አካል አይደለም ካሉ ደግሞ ከነቢዩ ﷺ ውዴታ ጋር ማያያዝና ጭፈራ እና መሰል አሳፋሪ ድርጊቶቻቸውን ከመስጂዶች እንዲያርቁ እንጠይቃቸዋለን!። 🔅ካልሆነ ግን ትውልድን በማበላሸት፣ የዲኑን ገጽታ በማጠልሸትና የተከበረውን ለርሱ ብቻ የሚሰገድበትን የአላህን ቤት/ መስጂድን ጫት መቃሚያና የጭፈራ ስፍራ በማድረጋቸው አላህ ዘንድ ተጠያቂዎች መሆናቸውን ልብ እንዲሉ እናሳስባቸዋለን!። ☄ገጣሚው እንዲህ ይላል:- " لَوْ كانَ حُبُّكَ صَادِقاً لأَطَعْتَهُ إنَّ الْمُحِبَّ لِمَنْ يُحِبُّ مُطِيعُ." "ጌታዬን ወዳለሁ እያልክ ታምጸዋለህ?! ይህ ፍጹም የማይሆንና የማይመስል ነገር ነው... ውዴታህ እውነትኛ ቢሆን ኖሮ ትታዘዘው ነበር፤ ወዳጅ እኮ ለወዳጁ ታዛዥ ነው።" 🔅እውነተኛ የነቢዩ ﷺ ወዳጅ የሆነ ሰው በሁሉም ነገር (በማድረግም በመተውም) እሳቸውንና ሰሓባዎቻቸውን ለመምሰል ይጥራል እንጂ ሰበብ አስባብ እየፈጠር በነቢ ﷺ ውዴታ ስም የመዝለልና የመጨፈር አምሮቱን አይወጣም!። 🔅ይህ የስሜት ውዴታና ግልቢያ እንጂ የነቢ ﷺ ውዴታ አይደለም። 🔅ከማንም በላይ ነቢን ﷺ በቃልም በተግባርም ይወዱ ከነበሩ ሰሓባዎቻቸው ውስጥ አንድ ሰሓባ እንኳ ከበሮ የሚመታና በእጆቹ የሚያጨበጭብ አልነበረም❗️። 🔅ታድያ አሁን የሚታየው ጀለቢያና ኮፊያ ያደረጉ ሰዎች መስጂዶች ላይ የሚያደርጉትስ ከየት መጣ?! ከተባለ:- ነቢዩ ﷺ፣ ሰሓባዎችና ተከታዮቻቸው (ደጋግ ቀደምቶች) ከጌታቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ሱፊያህ የሚባሉ ሰዎች የፈጠሩትና ዲኑ ላይ የጨመሩት ተግባር ነው። " وَكُلُ خَيْرٍ فِي اتِّبَاعِ مَنْ سَلَفْ وَكُلُّ شَرٍّ فِي ابْتِدَاعِ مَنْ خَلفْ." "መልካም ነገር ሁሉ ያለው ደጋግ ቀደምቶችን በመከተል ውስጥ ነው... አደጋና ክፋት ሁሉ ያለው ደግሞ ከኋላ የመጡ መጥፎ ተተኪዎችን በመከተል ውስጥ ነው።" 💥አላህ ለሁላችንም እውነተኛውን የኒቢዩን ﷺ ውዴታ ያድለን! ዲን ላይ አዲን ነገር ከመፍጠርም ይጠብቀን!። ኣሚን። ✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረቢዕ አል-አወል 1/1445 ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 ~ https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
Show all...
Log in to Facebook

Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.

ዓሹራን የመጾም ትሩፋት 🔅ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል (ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለ እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው <በጉጉት ጠብቀው> ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! ) ብለዋል ነቢዩም፥ ( የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል(ያስሰርዛል) ብዬ አሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ ) ብለዋል። 🔅አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም! 🔅የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያሰርዛል በቀላል ስራ ይህን የሚያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን፤አዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር፤ አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞች የሰው ልጆች አያውቁም} አርሩም 6 ☄የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነው?... የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል ምክንያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል፤ ( አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን ) ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል። 🔅ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክንያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል፤ ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ክልክል ከመሆኑ አንጻር እነሱን ለመቃረን ተብሎ ሸሪዓችን አንድን ነገር ማድረግ ሲከለክል ወይም ደግሞ ሲያዝ ሁሉ እናያለን ይህም ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሙስሊሞች አይሁድና ነሳራ ያደረጉትን ለማድረግ ሲሽቀዳደሙ እንመለከታለንል! 🔅ይህ በእንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ ያደርጋል፤በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል።እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል። 🔅ጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ቀንን ለብቻው (ከፊት ወይም ከኋላ አንድ ቀን ሳይጾሙ) ነጥሎ መጾም እንደማይቻል በሐዲሶች የተገለጸ ሲሆን አጋጣሚ ዓሹራ ጾም በጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ዕለት ቢሆን መጾም አይከለከልም። 🔅ዓሹራ ጾም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንደ ቀዷ ወይም የነዝር (ስለት) እና መሰል ምክንያት ያላቸው ጾሞችንም መጾም አይከለከልም። ☄ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው? ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ጠቅሰናል ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከባባዶችንም ጭምር? ይህን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል፤ " የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን" ☄ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን? እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም። 🔅ከዓሹራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ቢድዓዎች  ታላቁ የዲን መሪ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ይህን በተመለከተ የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ "በዓሹራ ቀን ሰዎች ገላቸውን ሲታጠቡ፤ ሲኳኳሉ፤ሂና ሲቀቡ፤ልዩ ሰላምታ ሲለዋወጡና ሲጨባበጡ፤ልዩ ምግብም ሲሰሩ እና ልዩ ደስታ ሲደሰቱ ይታያል ይህ ነገር በሸሪዓችን መሰረት አለውን?" እሳቸውም ሲመልሱ {{ ይህን አስመልክቶ ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተገኘ አንድም ሷሒሕ ሐዲስ የለም ሷሓቦቻቸውም ይህን አስመልክተው ያሉት ነገር የለም ቀደምት የዲን መሪዎችም አራቱም መሪዎች (ኢማም፥አቡ ሐኒፋ፣ማሊክ፣ሻፊዒ እና አሕመድ) ይሁን ሌሎችም ከነሱም ውጪ ያሉት ታዋቂ የሸሪዓ እውቀት ምንጭ የሚባሉ መጻህፍት ባለቤቶችም በዚህ ጉዳይ ከነቢዩም ይሁን ከሷሓቦች ወይም ከተከታዮቻቸው ምንም የዘገቡት ነገር የለም) ብለው መልሰዋል። 💥ከቢድዓ በመጠንቀቅ በዲኑ የተፈቀዱ ነገሮችን ብቻ በመስራት ወደ አላህ እንቃረብ! 💥የዘንድሮ (የ1445ዓ.ሂ) ዓሹራ የሚሆነው የፊታችን ጁሙዓህ (ከነገ ወዲያ) ሙሐረም 10 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 21 /2015) ሲሆን ከፊቱ ሐሙስን ወይም ከኋላው ቅዳሜን መጾም ተገቢ ነው። ከ11ኛው ቀን ይልቅ ከፊት ያለውን 9ኛውን ቀን መጾሙ ተመራጭ ነው። በተለይ ዘንድሮ 9ኛው ቀን ዕለቱም ሐሙስ ስለሆነ ሐሙስ ቀን የመጾምን ትሩፋትም ያስገኛል። ሁለት ቀን መጾም የሚከብደው ሰው 10ኛውን ቀን ብቻ መጾምም ይችላል። አላህ ይወፍቀን! ✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ 🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸 🌐https://telegram.me/ahmedadem
Show all...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

የዘንድሮ ዓሹራ 🔅የዓሹራ ፆም ከነገ ወዲያ ጁምዓ እለት ሲሆን ነገ ሐሙስ እለትንም ጨምሮ መፆም ተመራጭ ነው። 🔅ነገ መፆም የማይችል ሰው ጁምዓና ቅዳሜንን መፆም ይችላል። 🔅የዓሹራ ፆም በጥቅሉ ሱና እንጂ ግዴታ አይደለም። 🔅የማይችልና የሚከብደው ሰው ባይፆም ምንም ችግር የለውም። 🔅አስረኛውን ቀን ( ዘንድሮ -ጁምዓን-) ብቻ መፆም ቢፈልጉም ይቻላል። በዚህ ብቻም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ምህረት ማግኘት ይቻላል! በላጩ ግን  ከአስረኛው ቀን ከፊት ወይም ከኋላ አንድ ቀን መፆም ነው፡፡ 🔅ቀዷ ያለበት ሰውም ቢሆን ዓሹራን መፆም ይችላል፡፡ 🔅በአሹራ ቀን ከፆም ውጪ ሌላ ተጨማሪ ምንም አይነት ዒባዳ የሚደረግና ልዩ አጅር ያስገኛል የሚባል ነገር የለም። ከመፆሙ ውጪ በዓሹራ ትሩፋት ዙሪያ አንዳንድ ሰዎች የሚጠቅሷቸው ሐዲስ የሚባሉ ነገሮች በሙሉ ደዒፍና መውዱዕ ናቸው። 🔅የዓሹራ ፆም ኒያው፦ በልብ ( ነገ እፆማለሁ ብሎ መወሰን ) ብቻ ነው በምላስ የሚባል ምንም ነገር የለም! 🔅በተለያዩ ምክንያቶች መፆም የማይችሉ ሰዎች ሌሎችን በማስታወስና የፆሙ ሰዎችን በማስፈጠር ኢን'ሻ አላህ አጅሩን ማግኘት ይችላሉ! @ዛዱል መዓድ 🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
Show all...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

#የዙልሒጃህ #ጨረቃ #ዛሬ ምሽት #በመታየቷ የዙልሒጃህ ወር #ነገ ሰኞ አንድ ብሎ ይጀምራል። በዚህም መሰረት የዒድ አል-አድሓ በዓል እሮብ ሰኔ 21 የሚከበር ሲሆን #የውሙ ዐረፋ #ፆም ማክሰኞ (ሰኔ20/2015 ይሆናል። ዛዱል-መዓድ https://telegram.me/nesihaa
Show all...
ዲን ምክክር ነው

//طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ// ‘ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው።’ (("الدين النصيحة"، قلنا: لمن يا رسول الله؟ قال:" لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم")). joinand share via link t.me//nesihaa ለአስተያየት @nesihaabot

ኢድ ሙባረክ!  ጨረቃ በመታየቷ ነገ ጁምዓ ዒድ ይሆናል። እንኳን አደረሳችሁ! አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ። @nesihaa
Show all...
📮ተራዊሕ በመስገድ ከሚገኙ  ጥቅሞች... 🔹ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦቻቸው  የተገበሩት ተወዳጅና ሱናህ ዒባዳህ ነው። የተራዊሕ ሰላት በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት፤ ከነዚህም በጥቂቱ:- ① ቀኑን በጾም፣ ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች መሆን ያስችላል። ② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኝበታለን። ③ ተራዊሕ በዛ ያለ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን። ④ ከወንጀልና ከማይጠቅሙ ነገሮች ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን። ⑤ ዒባዳህ ላይ መታገስን እንማርበታለን። ⑥ አመቱን ሙሉ ሰላተል-ለይል ለመስገድ ልምምድ እናደርግበታለን። ⑦ በተደጋጋሚ ከኢማምና ከማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል። ⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል። ⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል። ①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን። ①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል። ①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅና ዲን ላይ ቀጥ ማለት ለሚፈልገው ወጣት መልካም አርዓያና ማበረታቻ እንሆናለን። ①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እንረዳበታለን። ①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማታችን እንገሰጻለን፤ እንዲሁም የተለያዩ አንቀጾችን በተደጋጋሚ በመስማታችን ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራር ለማወቅም ይረዳናል። ①⑤  በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን። ①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እናገኛለን። ①⑦ ለሰላት ረጅም ጊዜ መቆማችን የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፤ ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውምና። ①⑧ ሰግደን ስንመለስ አላህ የሚወደውን ስራ በመስራት የሚገኘውን የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን። 💠ሌሎችንም የዱኒያም የኣኺራህ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን መቼም አንተው! አላህ ያግራልን። اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمين ✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ ረመዷን 1444 ዓ.ሂ 🔸   🔹  🔸  🔹  🔸  🔹 @nesihaa
Show all...
እንኳን ለ1444 ዓ.ሒ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ። ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ መልካም የረመዳን ወር አላህ እዲያደርግልን እንለምነዋለን፡፡ ረመዳን ሙባረክ!! @Nesihaa
Show all...
🔴 ሰበር ዜና! በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች የረመዷን ጨረቃ አልታየችም። ስለሆነም ነገ እሮብ የሸዕባን ማሟያ 30ኛ ቀን ረመዷን 01/ 1444 ሀሙስ እንደሆነ ተገልጿል። https://t.me/nesihaa
Show all...
ዲን ምክክር ነው

//طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ// ‘ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው።’ (("الدين النصيحة"، قلنا: لمن يا رسول الله؟ قال:" لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم")). joinand share via link t.me//nesihaa ለአስተያየት @nesihaabot

205የጁሙዓ_ኹጥባ_በአማርኛ_የጾም_ህግጋትና_ስነ_ስርዓት_በኡስታዝ_አሕመድ_ሸይኽ_ኣደም_.mp38.04 MB
አልሐምዱሊላህ ስርጭታችን ተመልሷል። ስላደረጋችሁት ድጋፍ ሁሉ በአላህ ስም እናመሰግናለን። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን 11555 ነሲሓ ቲቪ 📡 Satellite: Nilesat Fequency: 11555 or 11554  Polarization: Vertical Fec. 5/6 Symbol rate: 27500 @nesihatv
Show all...