cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Qomoo foo'amoo/ የተመረጠ ዘር

1phex 2:9 “Isin garuu qomoo fo'amaa dha, .." " እናንተ ግን... ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:9) yaada qabdan (@gatiidhiigaa) nin nuuf hiraa

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የደም ሚስጥር .... ✍ ሰዎች ሳያስቡት የሚያደርጉት ነገር ካለ ደም ሲያዩ መደንገጥና ምንድን ነው ማለት ነው። በሬ ታርዶ ደም ከፈሰሰ በኋላ ሸፈን ሸፈን ይደረጋል ። በየትኛውም አጋጣሚ ምንም ነገር ፈሶ ስናይ ምንም አይመስለንም። ደም ፈሶ ስናይ ግን ጥያቄ ይፈጥርብናል ፤ ምክንያቱም ደም ያወራል። በዘመናት መሃከል ብዙ ደሞች ፈሰው ቀርተዋል ፤ ፈሰው ጠፍተዋል። ፈሶ ያልቀረ ፤ ፈሶ ምድር ያልዋጠችው ሕያው ሆኖ ለዘላለም የሚያወራ አንድ ደም አለ እሱም የኢየሱስ ደም ነው። “የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል።” — ዕብራውያን 12፥24 (አዲሱ መ.ት) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናገኛቸው ትልቅ ሚስጥር ኪዳን ሲሆን እግዚአብሔር ኪዳናትን ራሱን ከፍጥረታት ጋር ያስተሳሰረበት ስርዓት ነው። ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራእይ ድረስ ባሉ ሀሳቦች ብዙ የኪዳናት ግንኙነት አሉ። ከእነዚህ ኪዳኖች መሃከል አስደናቂ የሆነ ኪዳን የደም ኪዳን ነው። ደም የሌለበት ኪዳን ፤ ኪዳን ሳይሆን ውል ሲሆን ውል ደግሞ ይፈርሳል። እግዚአብሔርም ለሰው ልጆች በአዲስ ኪዳን ፤ የኪዳናችን መሰረት ያደረገው የኢየሱስን ደም ነው። #የኢየሱስ_ደም_የአዲስ_ኪዳን_መሰረት_ነው!! “እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው።” — ሉቃስ 22፥20 (አዲሱ መ.ት) የኢየሱስ ደም የእግዚአብሔር የመጨረሻው ሐይል ነው። የእግዚአብሔርን ሐይል ማወቅ የምንፈልግ ከሆነ የደሙን ሐይል ማወቅ አለብን። ሰው የደሙን ሐይል ካላወቀ የእግዚአብሔርን ሐይል ማወቅ አይችልም። WE MUST KNOW THE POWER OF THE BLOOD, IF WE ARE TO KNOW THE POWER OF GOD. የእግዚአብሔር ሐይል በእኛ ሕይወት የሚሰራው ከእኛ ጥረት ሳይሆን በኢየሱስ ደም ሐይል ላይ በመመስረት ነው። መልካም ቀን በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ @Qomoofooamo
Show all...
መለኮታዊ ጉብኝት መለኮታዊ ጉብኝት ቆይቶ እግዚአብሔርን ደጅ በመጥናት እንጂ በምትሃት አይመጣም! ብዙ መታዘዞች ሲጠራቀሙ አንድ ቀን የሰማይን ደጆች ይነድላሉ!! የሰማይ ፊት ሲዘነብል የምድር ፊት ይታደሳል! ከላይ በሚመጣው ጠል ታች ያለው ጠጥቶ ይረካል!! መንፈሳዊ እመርታና መለኮታዊ ክንውን በምሪት እንጂ በጀግንነት አይሆንም! በመንፈሱ እንጂ በሃይልና በብርታት አይደረግም!! የሰው ድርሻ (ከብዙው ጥቂቶቹ) 1. በትዕግሥት መቆየት -- እግዚአብሄርን መታገስ/ጌታን ማስጨረስ/መልካም እጆቹ በጎ ፈቃዱን አበጃጅተው እስኪጨርሱ መታገስ 2. ደጅ መጥናት --ፊቱን መፈለግ/ከጌታ ጋር የቅርበት ግንኙነት/የልብ ወዳጅነት መፍጠር /ግንኙነቱን በቀጣይነት መንከባከብና ማሳደግ 3. መታዘዝ ---እሺ ማለት/ መመሪያውን ማክበር/እሺታን በተግባርና በኑሮ መግለጥ/ሲያጠፉና ከፀጋ ሲጎድሉ ንስሃ መግባት/እምቢተኝነትንና እልከኝነትን ማስወገድ 4. ምሪትና አቅጣጫ መቀበል- ፈቃዱን መለየት/መቼ እንዴት በምን ዓይነት አካሄድ በየትኛው ስልትና strategy የሚሉትን ዝርዝር ጥቆማዎች ከራሱ ከመንፈስ ቅዱስ መቀበል በራስ ማስተዋል አለመደገፍ የትላንቱ መንገድ የዛሬው ላይሆን ይችላልና! የሰማይ ፊት ያብራላችሁ! ቀኙና ክንዱ ትደግፋችሁ! ©ዘማሪ ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን (ላሊ) Join us @Qomoofooamo
Show all...
የፈጣሪ ግዜ ! የመሸ የመሰለ ቀን ሁሉ ይነጋል የማይነጋ ሌሊት የለም ግን ሲነጋ ሰዐቱን ጠብቆ ነው ፤ ሲመሽ ሁሉም ቀን በስራ የደከመ ሰውነቱን ሊያሳርፍ ወደ መኝታው ይሄዳል ፤ በህይወታችንም የመሸ ሲመስለን የደከመ ሰውነታችን ወደ ፈጣሪው ይበልጥ መቅረብና እርፍ ማለት አስፈልጎታል ማለት ነዉና ሁሌም ጨለመብኝ ብለህ አትዘን አምላኬ እረፍት አዘጋጀልኝ በል ከሱ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እድል ሰጥቶካልና በሚገባ ተጠቀምበት የፈጣሪ ግዜ መቼም ቢሆን አይሳሳትም! እጅግ የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️
Show all...
ተመስገን! ከፍ ዝቅ የሚሉ ስሜቶችን ታግሶ ለዛሬ መድረስ ቀላል አይደለም፤ ራስን ለመለወጥ ወስኖ መንገድ መጀመር ቀላል አይደለም፤ ከባዱን እያደረክ ነው። ለውጥ የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ የሚጨርሱ ግን ጥቂት፤ ከጥቂቶች አንዱ ለመሆን ምስጋናን የሚያክል ሀያል ነገር የለም። ስለዚህ በዚህ የለውጥ ጉዞ እስከ ፍፃሜ መጓዝ የሚፈልግ 'ተመስገን' ይበል! @Inspire_Ethiopia @Qomoofoamoo
Show all...
Callisuun waaqayyoo dubbachuu seexanaa caalaatti dhagaa'ama🙏
Show all...
ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ከመቀላቀላችሁ በፊት ማወቅ ያለባችሁ... [ ሰላም ወንድማችሁ ነኝ። እጅግ ተጠፋፍተናል አውቃለው። ጌታ ቢፈቅድ በቅርቡ በአዲስ ነገር በሰፊው እንገናኛለን፡ እስከዛ ግን አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ እና የግል ኮሌጆች ከምትገቡት ጋር እንዳንተላለፍ ከዚህ በፊት ከተዘጋጀ መልዕክት አጠር እያደረኩ አካፍላችኋለው።] እነዚህን የትምህርት ተቋማት እንደ ክርስቲያን ስንቀላቀል ማድረግ ያለብን... በተጠራንበት መጠራት መመላለስ “እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ (ኤፌ.4፡1) ••• በተጠራንበት መጠራት መመላለስ የሚለው ሃሳብ በርካታ ነገሮችን ይይዛል: ከታች ለመግለጽ የተሞከረው በጣም በጥቂቱ ነው እነዚህም :— በብርሃን መመላለስ ፣ መልካሙን ሥራ በመስራት መመላለስ ፣ ከአህዛብ ጋር ባለመተባበር መመላለስ ...ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ በብርሃን መመላለስ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።” ማቴ 5:14 ••• ብርሃን የተደበቀውን ይገልጣል ___ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ (ዮሐ 3፡20)፡፡ ብርሃን ከጨለማ ጋር ትብብር የለውም ፡፡ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ለጨለማ እጅ አይሰጥም ፡፡ ብርሃን ከጨለማ ጋር በአንድ ቦታ በፍጹም ሊቀመጡ አይችሉም ፡፡ ሁሌም ብርሃን አሸናፊ ነው፡፡ በብርሃን የሚኖር ሰው ወይም ብርሃን በእጁ ያለው ሰው ወይም እራሱ ብርሃን የሆነ ሰው በሄደበት ሁሉ መብራቱን ያበራል እንጂ ሊደብቀው አይችልም፡፡ መብራቱን ስለፈለገ ሳይሆን የሚያበራው እራሱ ብርሃን ስለሆነ ሊደብቀው ስለማይችልም ጭምር ነው ፡፡ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።(ማቴ 5: 14 ) መልካሙን ሥራ በመስራት መመላለስ “እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”(ኤፌ 2 :10 ••• ሰው ስለ እኛ ያለው አመለካከት መልካም ብቻ እንዲሆን ማድረግ አለብን፡፡ “___በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና።” (2 ቆሮ 8 ፡ 21)ይላልና፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘ ሰው ሁሌም በሰው ፊት ሞገስን ያገኛል ማለት አይደለም ምክኒያቱም አንዳነድ ሰው ክፉ ነውና፡፡ ••• በሌላ በኩል ደግሞ በሰው ፊት ሞገስን ያገኘም ሁሉ በጌታም ፊት ሞገስን ያገኛል ማለት አይደለም፡ ኃጥአትን በማድረግ በሰው ፊት መክበር አለና፡፡ ከዚህ ሃሳብ ጋር ተያይዞ መናገር ምፈልገው ነገር ቢኖር ለእኛ ለክርስቲያኖች የሚሻለን ግን ሁሌም በጌታ ፊት ሞገስን ያገኘ በመልካም ስራ የተሞላ ኑሮ መኖር ነው፡፡ በሰው ፊት ከመክበር በጌታ ፊት ሆኖ እግሩ ስር መሆን እንኳ የተመረጠ ነውና፡፡ መልካሙ ሥራ ምንድነው ? √ በዋናነት ወንጌል ነው √ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት ፡ √ መጨረሻው በፍጹም ወደ ሃጢአት የማያመራ ነገር ሁሉ መልካም ሥራ ነው፡ √ ሌላውን የሚያንጽ እንጂ የማይጎዳ ነው (የጌታ ፈቃድ አለበት) ለምን በመልካም ሥራ መመላለስ አስፈለገ ? √ የተፈጠርነው ለመልካም ሥራ ብቻ ስለሆነ ___”እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”(ኤፌ 2 :10) √ በእኛ መልካም ሥራ እግዚአብሔር ሰለሚከብር ___ “ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።”( ጴጥ 2 : 12 ) “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” (ማቴ 5: 16) ከአህዛብ ጋር ባለመተባበር መመላለስ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው፡”(2 ቆሮ 6 ፡ 14 ) ••• ይህን ሃሳብ ከመወያየታችን በፊት ስለ ህብረት ጥቂት ግንዛቤ ብንጨብጥ ሃሳቡን በይበልጥ ለመረዳት ያስችለናል፡፡ ህብረት ፡— •• ሁለትና ከዚያ በላይ አካላት የታቀፈ ቡድን ነው ••• በመተባበር ለአንድ ዓላማ የሚሯሯጥ ቡድን ነው ••• በርካታ የተለያዩ አመለካከቶች ተዋህደው ተቻችለው የሚቆዩበት ቦታ ነው ••• የሃሳብ መደጋገፍ አለበት ••• በህብረት ውስጥ የሌላውን አመለካከትና ህይወት መካፈል የግድ ነው ••• በህብረት ውስጥ ሌላው አዘውትሮ የሚጠቀመውን ነገር መልሶ መጠቀም የግድ ነው (ለምሳሌ ፡ — ንግግር፣ አለባበስ፣ የመሳሰሉት ) ••• መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ክርስቲያን ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች ከአህዛብ ጋር በአንዳቸውም ተካፋዮች እንዳንሆን ያስተምረናል፡፡ በአጭሩ እኛ ወጣቶች ከማያምኑ ጋር የጠበቀ ህብረት/ ጓደኝነት እንዳይኖረን እና ከህብረታቸው እንድንወጣ ይፈልጋል፡፡ “ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ።”(2 ቆሮ 6 ፡ 17) ከአህዛብ መለየት አስፈለገ ? ••• የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ስለሆነ “...ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥__ ”( ኤፌ 5 ፡ 11) √ ብርሃን ከጨለማ ጋር ህብረት ስለሌለው “ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው” ( 2 ቆሮ 6 ፡ 14 ) √ የአህዛብን ህይወት ወደመጋራት እና ወደመለማመድ ሊወስደን ስለሚችል የአህዛብ ህይወት ምን ዓይነት ነው? “እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤ ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።” ( ኤፌ 4 ፡ 18 ) አህዛብ ፡ — √ ያለ ክርስቶስ ናቸው √ ያለ መንፈስ ቅዱስ ናቸው √ የስጋቸውንና የልቦናቸውን ፈቃድ የማድረግ ህይወት አላቸው “የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።”(ኤፌ 2 ፡ 3) ••• ከአህዛብ ጋር ህብረት ባለማድረግ መመላለስ ማለት ወደ አህዛብ አለመቅረብ ማለት አይደለም ፡፡ ነገር ግን የአህዛብን የኑሮ ዘይቤ ወዲያ በመተው በክርስቲያኒያዊ የኑሮ ዘይቤ መመላለስ ማለት ነው ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ከአህዛብ የሚለየን ሃጢአት ባደረግን ጊዜ የሚወቅሰን ሃይል አለ እሱም መንፈስ ቅዱስ ይባላል፡፡ ይህ መንፈስ ድንገት ተሳስተን እራሳችንን በሃጢአት ልምምድ ውስጥ ብናገኝ ተጸጽተን በይቅርታ እንድንመለስ ያደርገናል፡፡ ይህ መንፈስ ከሌለው ሰው ጋር ገደቡን ያለፈ ግንኙነት ወይም ህብረት ማድረግ ደግሞ ለምን ያህል የከፋ ተጽኖ እንደሚዳርግ መገመት አያዳግትም፡፡ 👤ወንድማችሁ ነኝ👤 YOUTUBE | TIKTOK ◈sʜᴀʀᴇ◈ ✅ ይቀላቀሉን ✅ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ [ https://t.me/sozo_purity ]
Show all...
ዮሐንስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ² ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። #በመጀመሪያው> ማለት ቅድመ - ዓለም ማለት ሲሆን ቅድም - ዓለም ማለት ደግሞ ከዘመን ውጭ የሆነ ዘላለም ማለት ነው። በዘላለም ውስጥ ደግሞ የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ የለም። የጊዜ ጽንሰ-ሐሳብ ከሌለ ደግሞ #መቼ የለም። "መቼ" ከሌለ ደግሞ #ንጽጽር የለም። "ንጽጽር" ከሌለ #መቅደምም #መቀዳደምም የለም። ስለዚህ እርሱ ከዘላለም ከአብ ጋር የነበረ እንጂ ከአብ ቡሀላ የተገኘ አይደለም።
Show all...
Mul. 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ Isaan faarfannaa haaraa yommuu faarfatan, "Ati macaaficha fudhachuudhaaf, mallattoo isaas banuudhaaf kan maltee dha; ati ofii keetii qalamtee, gosa hundumaa keessaa, afaan hundumaa keessaa, nama hundumaa keessaa, saba hundumaa keessaas, namoota dhiiga keetiin Waaqayyoof bitte. ¹⁰ Waaqayyo keenyaaf mootummaadhaaf luboota isaas akka ta'an isaan godhatte, isaanis lafa irratti mo'uuf jiru" jedhan.❤❤❤❤❤❤❤😍😍😍😍😍😍
Show all...
😍ፋሲካዬ😍 ፋ-ታ አልሰጥ ብሎኝ፤ የበደሌ ብዛት ሲ-ኦል አፉን ከፍቶ፤ ነፍሴን ሲጠብቃት ካ-ጠገቤ እሚሆን፤ አንድ እንኳ ሲጠፋ ች-ጋር ላይ ወድቄ፤ አንገቴን ስደፋ ን-ቆ ሁሉም ሲያልፈኝ፤ ሆኜ ያለ ተስፋ ክ-ርስቶስ ግን አየኝ፤ ቀረበ ወደኔ ር-ህራሄው ፍቅሩን፤ ሊያሳየኝ በአይኔ ስ-ጋ ለብሶ መጣ፤ ከሰማይ ወረደ ቶ-ሎ ብሎ እኔን ፤ለራሱ ወሰደ ስ-ለ እኔ ሃጥያት፤ ሊቀጣ ወደደ ታ-ሪኬን ሊቀይር፤ ሊፅፍ እንደገና ር-ቄ የነበርኩትን፤ ሊያቀርብ ወደደና ዶ-ሴው ተከደነ፤ የተከሰስኩበት ል-ያዩ ከሳሾቼ ፤ስትሻገር ነፍሴ፤ ከሞት ወደ ህይወት ና ልጄ እያለ ፤በአባት ፍቅሩ ጠራኝ ል-ቤን በፍቅሩ ፤ነፍሴንም በደሙ፤ በውድ ዋጋ ገዛኝ
Show all...