cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች

Advertising posts
10 942
Subscribers
-724 hours
-227 days
+13530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቃሳም ሙጃሂዶችን አርማ ጭንቅላታቸው ላይ አስረው ፍሪ ፍሪ ፓለስታይን የሚል ድምፅ ማሰማታቸውን እነሆ ዛሬም ቀጥለዋል። #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
🔥 45👍 31 5😍 2
የወራሪዋ አይሁድ ዜጎች እህል ውሀ ለራቃቸው ለፍልስጤማውያን የሰብአዊ እርዳታ መኪኖች እንዳይገቡ መንገድ ዘግተው እህሉን እያወረዱ ሲከፋፈሉ ስታይ አንጀትህ ይነዳል። ውስጥህ በብሶት ይቀጣጠላል። ብቻ ታሪክ ይህንንም በብዕሩ መዝግቧል። #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
😢 36👍 5🤔 1
መኖርያው በሚሳኤል ተደብድቦ ዶግ አመድ ሲሆን ፍርስራሹ ሰውነቱ ላይ ተከምሮ መውጫ ቀዳዳ አሳጣው። ለሶስት ቀናት ከእህል ውሀ አራርቆ ሆዱን በርሀብ አቆራመደው። ለሊቱ አብቅቶ ማለዳው ሊበሰር ጎህ ሲቀድ ከፍርስራሹ ስር በአይን ጥቅሻና በአንደበቱ የሱብሂን ሰላት በመስገድ ላይ ሳለ የነፍስ አድን ሰራተኞች በቦታው ደረሱ። አላህን በችግርም በድሎትም ወቅት የሚያስታውሱ ትውልዶች ድላቸውም ድል ሽንፈታቸውም ድል አይደለም ትላላችሁን?! ጌታዬ ሆይ ለእነርሱ ፅናትና ድልን ለእኛም ተቅዋና ኢኽላሱን ወፍቀን #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
😢 84👍 19 9😍 1
ከጥቂት ቀናት በፊት በግብፅ ብሄራዊ ደህንነት ኢንተለጀንሶች በኩል አንድ መልዕክት ተላከ። ከዋሽንግተን ነበር። ለቀሳሙ መሪ ለየህያ ሲንዋር። ለግሉ 15 ቢሊዮን ዶላር ስጦታ፣ ምቹና ቅንጡ መኖርያ፣ ጋዛ ከተማን መልሶ ለመገንባት ቃል የሰፈረበት ደብዳቤ! በምትኩ የህያ ሲንዋር ቀሳሞችን ከውስጥ በኩል ሰርስሮ በመናድና በመሰነጣጠቅ ህብረታቸውን እንዲንድላቸው ይጠይቃል። አደራ ይላል መልዕክቱ መጨረሻ ላይ "አደራ ከግብፅ አስታራቂዎች በኩል የቀረበውን ልዩ ጥያቄ ተጠቀምበት ይህ እድል እንዳያመልጥህ" በማለት ይቋጫል። የህያ ሲንዋር ከአራት ቀናት በኋላ ለዚህ ጥያቄ በአንድ አንቀጽ ምላሽ ሰጠ እንዲህ ይላል፡- فَلَمَّا جَاءَ سُلَيْمَانَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٍ فَمَا آتَانِيَ اللَّهُ خَيْرٌ مِّمَّا آتَاكُم بَلْ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمْ تَفْرَحُونَ "ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ" [አን-ነምል 36] #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
👍 69 23🔥 13🥰 4
አስገራሚውን ፅናት የተላበሱት የቀሳም ሙጃሂዶች የወራሪዋን ጦር እያነደዱት ይገኛሉ። አዎ ወጀቡ ሳይንጣቸው በንፋሱ ሳይወዛወዙ እየደሙ እየወደቁ የተዛነፈውን ፍትህ አስፍነው የአላህ ጠላቶች አደብ ሊያስይዙ ከእህል ውሀ ተራርቀው ጠመንጃቸው ከሰበቁ ሁለትመቶ ቀናት አለፉ። ከዋሻው ጥግ ተደግፈው ቁርአኑን እያነበቡ በዚክር ታጅበት በበስመላ ይተኩሱታል። የጋዛ ምድር ስለነርሱ ያወጋል ብሶት ስሜቱን በሊሳነል ሀሉ ያወራል "ለበራሪው ጎጆ፣ ለሰው ለአራዊቱ ጥላና ከለላ ነበርን የምድር ድምቀት የተፈጥሮ ውብ ስጦታ" አዎ ለዘመናት የተከፈለውን መስዋዕትነት ያስታውሰናል ላዩ ላይ የተፈፀመውን ያየውንና የታዘበውን ጀግንነት በደልና ግፍ ሊያወጋን ከቦታው ተሰይሟል ሲቃ እየተናነቀው እንዲህ ንግግሩን ይቀጥላል "የበይተል መቅዲስን ክብር ለማስመለስ በኛ ላይ ለተጠለሉ ጀግኖች ዱዓ እያደረግን ስለ ውለታቸው ስለኛም እጣ ፈንታ እናነባለን። የተሰሩት ፎቆች ረግፈው ተራቁተን ተመናምነን የፍርስራሽ ክምር ሆነናል። ለተጠጉን ሙጃሂዶች ጎጆና መጠልያ ሆነን እነሆ ዛሬም ድረስ አለን" ዛሬ የወራሪዋ እስራኤል ሎጀስቲክና ተጨማሪ አጋዥ ኃይሎች በሰላሀዲን ጎዳና በኩል ሲያልፉ በቀሳሞች ዶግ አመድ ሆነዋል። የወራሪዋ ጀቶችና ሚሳኤል የሚተፉ ድሮኖች ከሰማይ እሳቶቻቸውን እየለቀቁ መኖርያ ቤቶችን በማደባየት ህፃናት አረጋውያን ሴቶችና ሰላማዊ ሰዎችን እየቀጠፉ ይገኛል። ድርድሩ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል አዲሱ የስምምነት ምዕራፍ ወራሪዋ እስራኤል ጦሯን ከከተማው ለማስወጣትና የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለመስማማት ዳር ዳር እያለች ይገኛል። የሐማሱ ኢስማኤል ሀኒያ ዛሬ ከሉብናን ከተውጣጡ ዲፕሎማቶች ጋር ስለ ጉዳዩ ለመወያየት ቱርክ ገብተዋል። ድልና ብስራትን የምንሰማበትን ቀን አላህ ቅርብ ያድርግልን። #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
👍 44🥰 3😢 2 1😁 1
የመኖች ዛሬም ስራ ላይ ናቸው። የእንግሊዝን መርከብ በባልስቲክ ሚሳኤል ሲያጋዩት መርከቦችን ለመጠበቅ ተሰማርቶ የነበረውን የአሜሪካውን MQ-9 Reaper ድሮን አየር ላይ አንድደውታል። ጥቃቶቹን የፈፀሙት በሶስት ባልስቲክ ሚሳኤሎችን መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል። #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
👍 83 17🔥 17
በጅምላ የተገደሉ በጅምላም የተቀበሩ ጀናዛዎች! ከተማው ጋዛ ቦታውም ናስር ሆስፒታል ነው። እጃቸው የፍጢኝ ታስሮ ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመትተው ወድቀዋል እርሱም እድለኛ ስለሆኑ ከነ ነፍሳቸው አፈር በላያቸው ላይ የለበሱ በርካቶች ናቸው። አዎ የኋሊት ታስረው ሁለት እጆቻቸው ከእግሮቻቸው ጋር ተገምዶ በርካታ ህፃናትና አረጋዊያን የታካሚ ቱታ እንደለበሱ አፈር በላያቸው ላይ የተጫነባቸው በርካቶች ናቸው። አላህም አይቷል እኛም መስክረናል። #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
ስማቸው አላህ ዘንድ የሰፈረ ማንነታቸው ሰዎች ዘንድ ያልታወቀ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጀናዛዎች በጀመዓ ሊቀበሩ ተሰናድተዋል። ስማቸው አላህ ዘንድ ተመዝግቧል። ድርጊታቸው ተከትቦ ሩሐቸው ከጀሰዳቸው ተላቃ በጨርቅ ተጠቅልለዋል። ከፊል ጀናዛዎች በስብሰው አካላቸውን እንኳ መለየት ከብዷል። አላሁምመግፊር ለሁም ወርሀምሁም #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
😢 56👍 8 1
በሀርቫርድና ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲዎች የተጀመረው ተቃውሞ እነሆ በመላው አሜሪካ እንደ ሰደድ ተቀጣጥሏል። ሚቺጋን፣ ኦሀዩ፣ ፕሪንስተን፣ ካሊፎርኒያ ስቴት፣ ዋሽንግተን፣ ሚኒሶታ፣ ቴክሳስና ዳላስን አጥለቅልቋል። የጋዛን ዘር ማጥፋት እየተቃወሙ ስለ ፍልስጤም ይዘምራሉ። ትምህርት ቆሟል። ፍልስጤም የሚል ዝማሬ ከወዲህ ወዲያ ይደመጣል። ተማሪዎቹን ለመበተን ከተማሪዎቹ ቁጥር የሚበል በሺህ የሚቆጠር የፀጥታ ሀይል ቢሰማራም ተቃውሞው እየተዛመተ ወደ አውሮፓ ሀገራት ጭምር እየተዛመተ ይገኛል። #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
44👍 12🔥 1
ዕድሜያቸው ሰማንያ ገደማን ያለፉ አዛውንት ናቸው። ልጃቸው ይህንን ምስል አያይዞ እንዲህ ይላል:- "አቡ ኡበይዳ በቴሌቪዥናችን መስኮት ብቅ ሲል አባቴ ከተቀመጠበት ይቆማል። ምርኩዙን ደገፍ ብሎ የተወዳጁን አቡዑበይዳን ንግግር ያደምጣል። አይደክምም አይታክትም ንግግሩን ሳይጨርስ አይቀመጥም ተቀምጦም ንግግሩን ሰምቶ አያውቅም። ለክብሩ ከመቀመጫው ይነሳል" #Mahi mahisho ቴሌግራም 👇👇👇 t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch
Show all...
😍 68 58👍 10🔥 3