cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dawah Tube

Dawah Tube በዋናነት በተለያዩ ጊዜ እና ቦታዎች አንዳንድ ሚሽነሪዎች ላነሷቸው ሹበሃዎች መልስ የሚሠጥበት እና ተጨማሪ ንፅፅራዊ ትምህርቶች የሚቀርብበት channel ነው። وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًۭا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحًۭا وَقَالَ إِنَّنِى مِنَ ٱلْمُسْلِمِين ሀሳብ፣አስተያዬት ካለ በዚህ 👉 @DawahT_bot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
162
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በሃይማኖት ንጽጽር ተማሪዎች የሚቀርብ ወሳኝ እና አስተባሪ ውይይት እንደቀጠ ነው ።ከዚህ በፊት የአምላክ ልጅ.? የሚለውን እና የአምላክ ማን በሚል አርእስት በተከታታይ አይተናል ። ቀጣይ ' ' ' የኢየሱስ ማንነት ከቁርኣን እና ከባይብ እይታ ! በአስሓቡል የሚን ሥር በቅርብ ቀን ....... YOU tube subscribe https://www.youtube.com/watch?v=x1gQ-qOiwEs Telegram Join http://t.me/AshaBuleyamine
Show all...
#ሰለምቴዋ_ሄለን_ከኡስታዝ_ወሒድ_ጋር ያደረገችው ቆይታ #part_1

አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ! "ቁርኣን አይጋጭም" የሚለው የወንድም ወሒድ ዑመር መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል። በአት-ተውባህ የመጽሐፍት መደብር፣ በአን-ነጃሺይ የመጽሐፍት መደብር፤ በአቅሷ የመጽሐፍት መደብር ያገኙታል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ዐብዱ አር-ራሕማን 0920781016 ብለው ይደውሉ!
Show all...
🌍ጠቃሚ የንፅፅር ቻናሎች። 🔰Ustaz Abu Hyder. ➢ @abuhyder 🔰Ustaz Mohammed Essa. ➢@MuhammedChannel 🔰Ustaz wahid Omar. ➢በአማርኛ:- @Wahidcom ➢በኦሮምኛ:-@Wahid_oro1 ➢በትግርኛ:- @wahidtigiriga 🔰Ustaz Yahya ibnu nuh. ➢ @Yahya5 🔰Ustaz Eliyah Mahmoud. ➢ @religionandphylosophy 🔰Ustaz Abu Yusra. ➢ @Abuyusra3 🔰Brother Mahdi. ➢ @shoaibinfo 🔰Sister Sarah ➢ @ethiofu 🔰Brother Abdulkerim. ➢ @Abdulkerimcomparative 🔰Brother Bilal dari. ➢ @Bilalcomparative_Com 🔰Brother Uthmanovic. ➢ @uthmanovich 🔰Brother Mame. ➢ @askomame 🔰Brother Khalid Yohannes. ➢ @comparativereligious 🔰Brother Sαlαh. ➢ @Mahircomp123 🔰Brother Triple A. ➢ @Abu_Mussaab 🔰Brother Unknown. ➢ @orthox 🔰Brother khadir. ➢ @ewnet_lehulum 🔰Brother Ibnu nezif. ➢ @Ibnu_Nezif_channal 🔰Brother Jemal. ➢ @jemalcomparative
Show all...
Show all...
🔴ፈጣሪን ማን ፈጠረው ? Ethio Muslim Apologetics

በዚህ ጉዳይ ላይ በሌላ ጊዜ ሰፋ ባለ መልኩ የምንመጣበት ይሆናል። በዚህ ርዕስ የተዳሰሱት ነጥቦቹ አብዛኛው ከሚፖስ መፅሐፍ የተወሰዱ ናቸው። በተረፈ የቴሌግራም አአድራሻችንን ከፈለጉ

https://t.me/comparativereligious

🌐የሴት ልጅ መብት ☪በኢስላምና Vs በክርስትና✝ 𝓘𝓷 𝓘𝓼𝓵𝓪𝓶 𝓪𝓷𝓭 𝓥𝓼 𝓒𝓱𝓻𝓲𝓼𝓽𝓲𝓪𝓷𝓲𝓽𝔂 🎙 卂乃Ɗㄩㄥ 尺卂ㄩ千 ለሌሎች ትምህርቶችና መልሶች ⤵️ @ewnet_lehulum
Show all...
3.08 MB
ጥያቄዎቻችን "Our Question" ❓ ክፍል 9 እነ መግደላዊት ማርያም ያዩትን ተናግረዋል ወይስ አልተነገሩም¿¿ አልተናገሩም!🤐 “መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹ፤ ይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች #አልነገሩም። እነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።” — ማርቆስ 16፥8 ተናግረዋል!🗣 “ቃሎቹንም አሰቡ፥ ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለአሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ #ነገሩአቸው።” — ሉቃስ 24፥8-9 አራቱ ወንጌላቶች መቼም ላይስማሙ ቃል የተጋቡ እስኪመስል ድረስ የግጭት ጦርነት ላይ ናቸው።እናም ይህ ጥቅስ ግጭቱ ግልፅ ነው።በተጨማሪም ማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ሌሎችም ችግሮች አሉበት ጥንታዊ እደክታቦች የሚያትቱት ምዕራፍ 16:8 ድረስ እንደሆነ ማብቂያው ይናዘዛሉ።ግን ከ4ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ አክለው አካክለው እስከ አንቀፅ 20 አድርሰውታል። ሌላኛው የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16:8 ችግር እንዲህ የሚለው፦ እነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።” በግሪኩም ሆነ በእንግሊዘኛ ቅጂዎች ላይ የሌለ ግን በአማርኛው ትርጉም ላይ የተጨመረ ቀኖና ነው። ጉድ በል! እንግዲህ እንደዚህም ከሽነው አቁላልተው እየመራረቁ አሁንም የአምላክ ቃል ነው ይሉሃል። ለሌሎች ትምህርቶችና መልሶች ⤵️ @ewnet_lehulum
Show all...
አንድም ነቢይ በአላህ ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር ከራሱ ተዓምርን ሊያሳይ አይገባውምም አይችልምም።የአላህ ትዕዛዝ በመጣም ጊዜ በእውነት ይፈርዳል። وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ ۗ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِيَ بِآيَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ فَإِذَا جَاءَ أَمْرُ اللَّهِ قُضِيَ بِالْحَقِّ وَخَسِرَ هُنَالِكَ الْمُبْطِلُونَ [ ሱረቱ አል-ሙእሚን - 78 ] ካንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አልለ፡፡ ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነው አልለ፡፡ *ለማንኛውም መልክተኛ *በአላህ ፈቃድ ካልኾነ ተዓምርን* ሊያመጣ አይገባውም*፡፡ *የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ በእውነት ይፈረዳል*፡፡ እዚያ ዘንድም አጥፊዎቹ ይከስራሉ፡፡ ኢየሱስ አለይሂ ሰላም ምንድን ነው ያለው? “*እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም*፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ *የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና*።” — ዮሐንስ 5፥30 لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا [ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 172 ] አልመሲሕ (ኢየሱስ) *ለአላህ ባሪያ* ከመኾን *ፈጽሞ አይጠየፍም*፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም (አይጠየፉም)፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍና የሚኮራም ሰው (አላህ) ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፡፡ ክርስቲያን ወገኖች ሆይ! ኧረ ፍጡር ማምለክ ይብቃችሁ ኑ በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነች ቃል ኑ! እርሷም የፈጠረንን አላህን ብቻ እንጂ ሌላን ላንገዛ ነው። قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ [ ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 64 ] የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ አላህ ሒድያ ይስጣቸው ለእኛም ፅናቱን አሜን! ✍ ኸድር ኢብኑ ሙሀመድ(አብዱል ራኡፍ) ለሌሎች ትምህርቶችና መልሶች ⤵️ @ewnet_lehulum
Show all...
የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ተአምራት! Part 1 بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ በትዕግስት እና በማስተንተን ያንብቡት!!! ከነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" በፊት የመጡት ነቢያት እና መልእክተኞች የሰው ልጆችን ወደ እውነተኛው እና ቀጥተኛ መንገድ ወደሆነው የአላህ ሃይማኖት ህዝቦቻቸውን እንዲመሩ ተልከዋል፡፡ ሁሉም ነቢያቶች አንድ ዓይነት ሥራ ነበራቸው ይህም ሰዎችን አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩና ቀና ሕይወት እንዲመሩ ማስተማር ነው።በጠላቶቻቸው እንኳን እንደ ሐቀኛ እና እምነት የሚጣልባቸው ሰዎች እንደሆኑ አድርገው እንዲቆጥሯቸው በሚያደርጉዋቸው ብዙ ድርጊቶች ሁሉ እውነተኛ ቅንነትን እና ሐቀኝነትን በምሳሌነት አስተምረዋል፡፡ እነዚህ አላህ በውስጣቸው የለገሳቸው ባሕሪዎች ስለ ሚስጥራዊነት ለሚነሱት የይገባኛል ጥያቄ እንደ የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉ በመሆናቸው በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ አላህም እነዚህ ሰዎች በአላህ አልተላኩም የሚለውን ጥርጣሬ ለማስወገድ ተአምራትን ለእነሱ በአላህ ፍቃድ ያሰራቸዋል፡፡ስለ ውዱና አዛኙ ነቢዩ ሙሐመድ"ﷺ" ከእነዚህ ተአምራት መካከል ብዙዎቹ በግልፅ በቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ ናቸው። ይህም ማለት እኛ ሙስሊሞች እነዚህ ክስተቶች በእውነቱ የተከናወኑ መሆናቸውን ማመን አለብን ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" ከሌሎቹ ነቢያቶች የተለዩ አልነበሩም ግን በአላህ እገዛ ሌላ የሰው ልጅ ማድረግ የማይችላቸውን ተአምራት አድርገዋል፡፡ በሕይወታቸው በሙሉ ብዙ ተአምራት ተሰጥቷቸዋል፡፡ብዙ ክርስቲያን ሚሽነሪወች ነቢያችሁ ተዓምር መች ሰራ እያሉ ሲዘፍኑ ይስተዋላል።እናም እነሱ የማያውቁት ሊሆኑ የሚችሉትን በክፍል በክፍል በማድረግ የተለያዩ የውዱን ነቢይ የሙሐመድን "ﷺ" ተአምራት እንዳሳለን፦ አነስ ረድየላሁ አንሁ እንደተረከው፦ የነቢዩ ሙሐመድ የጨረቃን መክፈል የማያምኑ ሰዎች ነቢዩን ተዓምር እንዲያደርጉ ሲጠይቁ፡፡ እሳቸውም ወደ ጨረቃ ጠቆሙ በአላህም ፈቃድ ጨረቃዋ ለሁለት ተከፈለች፡፡ የመካ ሰዎች የአላህ መልእክተኛ ተአምር እንዲያሳዩላቸው ስለጠየቁ የጨረቃን መከፈሉን አሳያቸው ፡፡ ﺣَﺪَّﺛَﻨَﺎ ﻋَﺒْﺪُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺑْﻦُ ﻣُﺤَﻤَّﺪٍ، ﺣَﺪَّﺛَﻨَﺎ ﻳُﻮﻧُﺲُ ﺑْﻦُ ﻣُﺤَﻤَّﺪٍ، ﺣَﺪَّﺛَﻨَﺎ ﺷَﻴْﺒَﺎﻥُ، ﻋَﻦْ ﻗَﺘَﺎﺩَﺓَ، ﻋَﻦْ ﺃَﻧَﺲٍ ـ ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪـ ﻗَﺎﻝَ ﺳَﺄَﻝَ ﺃَﻫْﻞُ ﻣَﻜَّﺔَ ﺃَﻥْ ﻳُﺮِﻳَﻬُﻢْ ﺁﻳَﺔً ﻓَﺄَﺭَﺍﻫُﻢُ ﺍﻧْﺸِﻘَﺎﻕَ ﺍﻟْﻘَﻤَﺮِ ’[ሳሂህ አል ቡኻሪ 6/4867] በዚያ ሁኔታ ጨረቃን ከገመሱ በኋላ መልሳ ተገጠመች፡፡የመጀመሪያውን ሁኔታ ምንም እንኳን ከሃዲዎቹ ይህ ክስተት በፊታቸው ልክ እንደ ጠራራ ፀሐይ በግልፅ ሲከናወን ቢያዩም አሁንም ነቢዩን አስማተኛ ወይም ድግምተኛ ብለው ጠርተው ካዱት፡፡ አምላካችን አላህም ጨረቃ እንደተገመሰች በተከበረው ቃሉ ይነግረናል። اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ (ሱረት አል-ቀመር - 1) ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ *ጨረቃም ተገመሰ*፡፡ وَإِن يَرَوْا آيَةً يُعْرِضُوا وَيَقُولُوا سِحْرٌ مُّسْتَمِرٌّ [ ሱረት አል-ቀመር - 2 ] *ተዓምርንም* ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ *ድግምት ነውም*» ይላሉ፡፡ እግረ መንገዳችንን እስኪ ኢየሱስ አለይሂ ሰላም እንደ ነቢይነቱ ተዓምር ሰርቶ ሰዎቹ አምነውት ነበርን?አንድ ነቢይ ተዓምር የሚያደርገው በአምላኩ ፍቃድ ነው።ይህም የሚሆነው ነቢያቶቹ ከአለማቱ ጌታ ከአምላካችን አላህ እንደተላኩ ለማሳመን ብቻ ነው።ኢየሱስ አለይሂ ሰላምም በአምላኩ ስም በሚሰራቸው ተዓምራቶች የእርሱን ነቢይነት ይገልፃሉ። “ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ *አታምኑምም* እኔ በአባቴ ስም *የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል*፤” — ዮሐንስ 10፥25 በአባቴ ስም የማደርገው ስራ የሚለው ይሰመርበት። ማርቆስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ ኢየሱስም፦ *ነቢይ* ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። ⁵ በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ *ተአምር ሊያደርግ* ምንም አልቻለም። ⁶ ስለ *አለማመናቸውም ተደነቀ*። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር። ነቢያቶች ተዓምርን ቢያሳዩ በቀላሉ ሰዎች አያምኗቸውም።የነቢያቶች መስካሪ አንዱ አላህ ነው።እንዴት ነው የሚመሰክረው?ለነቢያቶች ተዓምራትን በመስጠት መልእክተኞቹ እንደሆኑ ይመሰክራል ማለት ነው።ልብ በሉ እርሱ አላህ ለነቢያቶች ሲመሰክር ተዓምራትን በማሰራት እንጂ ድምፁም ሆነ መልኩ አልታየም። ዮሐንስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁶ እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ *የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና*። ³⁷ *የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል*። *ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም*፤ ኢየሱስ አለይሂ ሰላም የሚያደርገው ስራ አላህ እንደላከው እንዲመሰክርለት ብቻ ነው።
Show all...
ከክርስትያን ወገኖች የመጡ ጥያቄዎች? ሙስሊሞች ነቢዩ ሙሐመድﷺ የመጨረሻ ነቢይ ናቸው ብለው ለምን ያምናሉ? ሙስሊሞች የሚከተለውን የቁርአን ጥቅስ ጨምሮ በእስልምና መጽሐፍ ውስጥ በተገለጹት መግለጫዎች መሠረት ነቢዩ ሙሐመድﷺ የመጨረሻው ነቢይ እንደሆኑ ያምናሉ። Al-Ahzab 33:40 (40) مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّۦنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًا (40) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና *የነቢዮች መደምደሚያ* ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ሙስሊሞች ነቢዩ ሙሐመድﷺ ከርሱ በፊት ብዙ ነቢያት እንዳለፉ ያምናሉ ለምሳሌ፦ አዳም፣ኖህ፣አብርሃም ፣ዳዊትን እና ኢየሱስን አለይሂሙ ሰላም ወዘተ ብዙ ነቢያት እንደነበሩ ያምናሉ ፡፡ ሙስሊሞች ሁሉም ነቢያት ከአላህ የተላኩ እንደሆኑ እና ብዙዎቹ የነቢዩ ሙሐመድንﷺ መምጣት አስቀድመው በትንቢት እንደተናገሩ ያምናሉ ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድﷺ ለምን ብዙ ሚስቶችን አገቡ? ከአንድ በላይ ማግባት በአረቦች አለም የተለመደ ነገር ነበር። በሌሎች በርካታ ባህሎች ውስጥ እንደነበረው፤በተለይም ለፖለቲካ መሪ ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ አባቶችና ነቢያቶች ብዙ ሚስቶች እንዳሏቸው የተገለጸ ሲሆን የእስራኤል ነገሥታት በአንዳንድ ሁኔታዎች እስከ ሰባት መቶ የሚደርሱ ሚስቶች እና ብዙ ሴት ባሪያዎች እንዳሏቸው ተገልጿል፡፡በጥቂቱ ምዕራፍና አንቀፆቻቸውን ላስቀምጥላችሁና ገብታችሁ አረጋግጡ።(መፅሃፈ ሳሙኤል ካልዕ 5:13)፣(ኦሪት ዘፍጠረት 16:3)፣(መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 11:3)፣(መፅሃፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 13:21)፣(መፅሃፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 11:22)፣(መፅሃፈ ዜና መዋእል ቀዳማዊ 14:3) ከብዙ በጥቂቱ እነዚህን ይመልከቱ። የሙስሊም ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ጋብቻ የተቸገሩ ሴቶችን እንዲሁ መሐኖችን እና አግብተው የፈቱ ሴቶችን ለመርዳት እንዲሁም በመዲና እና በአከባቢዋ ባሉ ጎሳዎች መካከል ትስስር በመፍጠር ውዱ ነቢይ በጋብቻዎቹ የዘር፣የባህል የጎሳ እና የብሔር ልዩነቶችን እና ጭፍን ጥላቻን ለማስወገድ ችለዋል፡፡ ከውዱ ነቢዩ ሙሐመድﷺ ጋብቻዎች መካከል ተከታዮቹን ከተለያዩ ጎሳዎች ጋር በጋራ በውዴታ እና በፍቅር አንድ አድርገዋል፡፡ በዚህ ጊዜ የተፋቱ ሴቶች እንደየ ደረጃቸው ዝቅተኛ እንደሆኑ ተደርገው የሚታዩ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ እንደገና ማግባት አይፈቀድላቸውም ነበር። ውዱ ነቢዩ ሙሐመድﷺ የተፋታችውን ሴት በማግባቱ እንዲህ ዓይነቱ ጋብቻ ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን የተፋታችውን ሴት በሕብረተሰቡ ዘንድ የክብር ቦታ በማሰጠት እና የሰውን ልጅ ትልቅ ትምህርት አስተምረዋል፡፡ አንዳንድ የውዱ ነቢይ ጋብቻዎች ተስፋፍተው የነበሩትን መጥፎ ልማዶችን ለማጥፋት እና ለማስቀረት ነበር፡፡በነቢዩ ዘመን የጦር እስረኞች እንደ ባሪያ ተወስደው ነበር፡፡ ውዱ ነቢይ ግን በገንዘብ እና በብዙ አጋጣሚዎች ምንም ክፍያ ሳይከፍሉ ነፃ በማውጣት ምሳሌ ትተውላቸዋል፡፡ ለምእመናን የግል አርአያነት ለማሳየትም በባርነት ከተያዙት ሁለት ሴቶችን ከባርነት በማውጣት አግብተዋል፡፡ ከጊዜው እና ከቦታ አንፃር ነቢዩ ሙሐመድﷺ በርካታ ሴቶችን ማግባታቸው ምንም ልዩና ያልተለመደ ነገር አልነበረም፡፡ በተጨማሪም በወጣትነት ዕድሜያቸው ከአሥራ አምስት ዓመት ከዕድሜያቸው በላይ የሆነች ሴት አግብቶ እስከ ሃምሳ ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ እስከሞትዋ ጊዜ ድረስ ለሃያ-አምስት ዓመታት ከእሷ ጋር በአንድነት ተወስኖ መቆየቱ ሀዲሳቶች የሚናገሩት እውነታ ነው፡፡እና ከዚያ ቡኋላ ያገቡዋቸው ሚስቶች መሐን፣ አግብተው የፈቱ፣በእድሜ የሚበልጧቸውን እና የተቸገሩትን ለመርዳት ብቻ ነው።ከሚስቶቻቸው አንዷና በእድሜ ትንሿ አዒሻ ረድየላሁ አንሁማ ናት እሷንም ያገቧት ለትምህርት ስርጭት ነበር።ምክንያተም አይደለም በዚያን ጊዜ የነበሩት ሴቶችጋ አሁን ያሉ ሴቶችምጋ ማለትም በሴቶች ጉዳይ ለምሳሌ በወር አበባ እንዲሁም በተለያዩ የሴቶች ጉዳይ ላይ ወንድ እና ሴት አውርተው መግባባት አይቻልም ነበር።በዚያን ጊዜ ሴቶችን ማስተማር የሚቻለው አማራጩ በሴትና በሴት ብቻ ነበር። Source(ምንጭ): The Holy Prophet Muhammad (peace by upon him) by Maulana M.A. Cheema, Chapter: “Polygamy and the Prophet of Islam”, pages 13-15. ለሌሎች ትምህርቶችና መልሶች ⤵️ @ewnet_lehulum
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.